Ministry of Education Ethiopia
119K subscribers
2.95K photos
32 videos
6 files
378 links
This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe
Download Telegram
የከፍተኛ ትምህርት፣ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና፣ የምርምር ተቋማትና የኢንዱስትሪ ትስስር አዋጅን ለማስጀመርና የማስፈጸሚያ የህግ ማዕቀፎችን ለማጽደቅ የሚያግዝ መርሃ-ግብር ተካሄዷል። ዝርዝር መረጃውን ይህንን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይቻላል። https://www.facebook.com/share/7rkmK3ZiaLhY5Lxz/?mibextid=oFDknk
በአገር አቀፍ ደረጃ ለ2ኛ ደረጃ ተማሪዎች ሲሰጥ የነበረው የዘንድሮው የክረምት የኮምፒውተር ፕሮግራሚንግና አልጎሪዚም ሥልጠና መርሃ-ግብር ተጠናቀቀ
====================
በስልጠናው ማጠናቀቂያ መርሃ ግብር ላይ ቁልፍ መልዕከት ያስተላለፉት የትምህርት ሚኒስቴር የማህበረሰብ ጉድኝትና ሀገር በቀል ዕወቀት ዴስክ ኃላፊ ወ/ሮ ሰላማዊት አለሙ ዲጅታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በርካታ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂና ኮምፒውተር ችሎታ ያላቸው ዜጎችን ማፍራት አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰው መርሃ-ግብሩ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በቅርቡ ካስተዋወቁት የ5 ሚሊዮን ኮደርስ ኢንሼቲቭ ፕሮግራም ጋር የሚጣጣም መሆኑን አንስተዋል፡፡

ወ/ሮ ሰላማዊት አክለውም በቀጣይ ጊዜያት የሥልጠናውን ቀጣይነት ከማረጋገጥ በተጨማሪ ተደራሸነቱና ጥራቱም እንዲጨምር ትምህርት ሚኒስቴር ከአዲስ ኮደር ጋር በትብብር የሚሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የአዲስ ኮደር መሥራችና ሥራ አስኪያጅ ፕሮፌሠር ጂላኒ ኒልሰን በበኩላቸው ሥልጠናው በመስኩ ተሰጥኦ እና ፍላጎት ያላቸውን ከ9-11ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎቸን በመመልመል እውቀታቸውንና ከህሎታቸውን በማሳደግ በቀጣይ ሀገራቸውን የሚጠቅሙ ብቁ ዜጎችን ማፍራት አላማ ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በመስኩ ልምድ ያላቸው 26 የአገር ውስጥና የውጪ ሀገራት በጎ ፍቃደኛ አሰልጣኞች እና 99 ተማሪዎች የስልጠናው ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
ለ7ኛ ጊዜ የተሰጠውን ስልጠና የትምህርት ሚኒስቴር አዲሰ ኮደር ከተሰኘ የበጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው መሆኑ ታውቋል፡፡
ማ ስ ታ ወ ቂ ያ

የምዝገባ ጊዜን መራዘሙን ስለማሳወቅ

ትምህርት ሚኒስቴር በ2017 የትምህርት ዘመን የድህረምረቃ ፕሮግራሞች ለመማር ፍላጎት ላላቸው አመልካቾች የሚሰጠው የመግቢያ ፈተና (NGAT) ምዝገባ እስከ ነሐሴ 10/2016 ዓ.ም መራዘሙን እያሳወቅን እስከ ተጠቀሰው ጊዜ ድረስ በ https://NGAT.ethernet.edu.et በኩል መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

የኢፌድሪ ትምህርት ሚኒስቴ
የመምህራንን ክብርና አቅም ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ እንደሆነ ተገለጸ
--------------------------------------
የትምህርት ሚኒስትሩ ክቡር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በሀሮምያ ዩኒቨርስቲ በክረምት መርሃ-ግብር የሚሰለጥኑ መምህራንን ጎብኝተዋል።
ክቡር ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው ወቅት ከሰልጣኞች ጋር ባደረጉት ውይይት መምህርነት ሙያ የተከበረ እና የአንድ ሀገር የእድገት መሰረት በመሆኑ ይህን ታለቅ ሙያ ወደነበረበት ክብር ለመመለስና የመምህራንን አቅም መገንባት ፤ኑሮውን ማሻሻል የግድ በመሆኑ መንግስት ከፍተኛ ትከረት ሰጥቶ አየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ የአጭርና የረጅም ጊዜ እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው ከደመወዝ ጭማሪ ጀምሮ የመምህራን ባንክ እስከመክፈት የሚደርሱ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልጸዋል። በመምህራኑ የሚከፈተው ባንክ ሙያውንና ኑሮአቸውን ለመቀየር ትልቅ ሚና እንደሚኖረውም ጨምረው ተናግረዋል።
ሰልጣኝ መምህራንም በበኩላቸው በክቡር ሚኒስትሩ መጎብኘታቸው ደስ እንዳሰኛቸው ገልጸው ስልጠናውም ለሙያቸው ትልቅ አቅም እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል። መምህራኑ ጨምረውም በስልጠናው አዳዲስ እውቀቶችን እንደቀሰሙና ቴክኖሎጂን በመጠቀም እንዴት ማስተማር እንሚቻል ጭምር አውቀት ያጉኙበትና ከዘመኑ ጋር የሚሄድ መምህር ለመሆን እንዳነሳሳቸው ገልጸዋል፡
የትምህርት ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሠራተኞች አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ
----------------------------------------
በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የትምህርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሠራተኞች አረንጓዴ አሻራቸውን አስቀምጠዋል።

በኦሮሚያ ክልል በሱሉልታ ወረዳ ዋሬርሶ ማሌማ ቀበሌ በተካሄደው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አሻራቸውን ያኖሩት የትምህርት ሚኒስትሩ ክቡር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አረንጓዴ አሻራችንን በማኖር አርአያነታችንንና ቁርጠኝነታችንን ለትውልድ በተግባር ማሳየት ይገባናል ብለዋል፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒሰትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በበኩላቸው በጉጉት ስንጠብቀው ለነበረው ለዚህ ቀን ደርሰው አረንጓዴ አሻራቸውን በማስቀመጣቸው ደስ ያላቸው መሆኑን ገልጸው ሀገራችን ለዓለም አስተዋጽኦ ያደረገችበት መርሃ-ግብር መሆኑን ተናግረዋል።

የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና የተጠሪ ተቋማት ሰራተኞች ችግኞቹን የተከሉት በተራቆተ ቦታ በመሆኑ ከአቻ መስሪያ ቤቶች ጋር በመተባበርም የመንከባከብ ስራ እንደሚሰራ እና ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ የግድ መሆኑን ተናግረዋል።

የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሹኔ በበኩላቸው በሁለንተናዊ መልኩ የበለጸገች አገር ለትውልድ ለማውረስ ችግኝ በመትከልና በመንከባከብ ኃላፊነታችንን ልንወጣ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በኦሮሚያ ክልል በሱሉልታ አካባቢ በተካሄደው አረንጓዴ አሻራ የማኖር መርሀ ግብር የትምህርት ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሠራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
ማስታወቂያ
የድህረምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ተጨማሪ የምዝገባ ጊዜ እና የፈተና ቀንን ስለማሳወቅ

በ2017 የትምህርት ዘመን የድህረምረቃ ፕሮግራሞች ለመማር ፍላጎት ያላቸሁ እና በተለያዩ ምክንያቶች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ምዝገባ ያመለጣችሁ አመልካቾች እስከ ነሐሴ 26/2016 ዓ.ም ድረሰ በ https://ngat.ethernet.edu.et በኩል መመዝገብ የምትችሉ መሆኑንን እየገለጽን በየተመደባችሁበት የፈተና ማዕከላት እና የመፈተኛ ፕሮግራም መሰረት ከ ነሐሴ 30 እስከ ጳጉሜን 1/2016 ዓ.ም ድረስ ፈተናው የሚሰጥ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ
በፈተና ወቅት የተሰጣችሁን User Name and Password፣ እና ማንነታችሁን የሚገልጽ መታዋቂያ ይዛችሁ መቅረብ ይጠበቃባችኋል።


የኢፌድሪ ትምህርት ሚኒስቴር
የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር እና የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በትምህርት ተቋማት ስፖርት ልማት ዙሪያ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡
======================
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የመግባቢያ ስምምነቱን በተፈራረሙበት ወቅት ስፖርት አእምሮአዊና አካላዊ ብቃት የተላበሱ ዜጎችን ለማፍራት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም የትምህርት ሚኒስቴር ብቃት ያላቸው ዜጎችን የማፍራት ተግባር የትምህርት ዘርፉ ሪፎርም አካል አድርጎ እየሰራ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ በዚህም መሠረት በቀጣዩ የትምህርት ዘመን የትምህርት ቤቶች ስፖርት ውድድርን ለማካሄድ እና መርሃ ግብሩን አጠናክሮ ለማስቀጠል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የባህልና ስፖርት ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ በበኩላቸው በሁሉም ዘርፍ አሸናፊ አገር ለመፍጠር ብቁና ንቁ ዜጎች ማፍራት ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው በማህበረሰብ አቀፍ እና በባህላዊ ስፖርቶች ላይ የትምህርት ማህበረሰቡን በማሳተፍ በጋራ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ሁለቱ ተቋማት በዕለቱ የተፈረረሙት የመግባቢያ ሰነድ መሰረት በቀጣይ በየደረጃው ባሉ ቴክኒካል ባለሙያዎች በየጊዜው እየታቀደ እና እየዳበረ ለተሻለ ስኬት እንደሚውል ጠቁመዋል፡፡

የትብብር ስምምንቱ ዓላማ በሁለቱ ተቋማት መካከል ወጥ እና ተከታታይነት ያለው ቅንጅታዊ አሰራርን በመፍጠር የትምህርት ቤት ስፖርት ልማትን በማስፋፋት የስፖርት ትምህርት ጥራትን ለማሻሻል መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

ሰፖርታዊ ልማትን ባህል ያደረገ በመማር ውጤቱ የተሻለ የሆነ ንቁና ሁለንተናዊ ሰብዕናው የተሟላ ተተኪ ትውልድ ለማፍራት ምቹ ሁኔታን መፍጠር የስምምነት ሰነዱ ሌለው ዓላማ መሆኑን ተመላክቷል፡፡
===////====
ቀን፡ 29/12/2016 ዓ.ም

ማስታወቂያ
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን እንደ ፈተና ማዕከል ለመረጣችሁ የ ‘NGAT’ ተፈታኞች በሙሉ
ከነሐሴ 30 እስከ ጳጉሜ 01/ 2016 ዓ.ም ድረስ በመላው ሀገሪቱ ይሰጣል ተብሎ በእቅድ የተያዘው የ “NGAT’ ፈተና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን በፈተና ጣቢያነት ለመረጣችሁ ተፈታኞች ብቻ የፈተናው ጊዜ የተለወጠ መሆኑን እያሳወቅን ፈተናው የሚሰጥበትን ቀን ወደፊት የምናሳውቅ ሆኖ በሌሎች የፈተና ጣቢያዎች (ዩኒቨርሲቲዎች) ፈተናውን ለመውሰድ ያመለከታችሁ በሙሉ ፈተናው በተያዘው ዕቅድ መሰረት ነሐሴ 30/2016 ዓ.ም ከ8:00 (ከስምንት ሰዓት) ጀምሮ የሚሰጥ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ትምህርት ሚኒስቴር
የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ የአሜሪካ የረትገር ዩኒቨርሲቲ-ካምደን ቻንስለር በዶክተር አንቶኒዮ ዲ. ቲሊስ የተመራ የልዑካን ቡድን ተቀብለው በጽ/ ቤታቸው አነጋገሩ፡፡

ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ቻንስለሩንና የልዑካን ቡድናቸውን ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ስለ አገራችን ዘመናዊ ትምህርትና የከፍተኛ ትምህርት ታሪክና መስፋፋት ዙሪያ ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡
የረትገር ዩኒቨርሲቲ ከትምህርት ሚኒስቴርና ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በቴክኖሎጂና በሌሎችም የትብብር መስኮች በጋራ መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይም ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው መክረዋል፡፡

ዶክተር አንቶኒዮ ዲ. ቲሊስ በበኩላቸው የረትገር ዩኒቨርሲቲ-ካምደን ከማላዊ፣ ኬኒያ ፣ ናይጄሪያና ከሌሎችም የአፍሪካ ዩኒቨርስቲዎች ጋር በትብብር እንደሚሰራ ጠቅሰው ከትምህርት ሚኒስቴርና ከኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎች ጋር በተለያዩ መስኮቸ በትብብርና በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡