"በሚቀጥሉት ዓመታት የተማሪዎች ምደባ ይቆማል " - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
የመንግሥት የዩኒቨርሲቲ ምደባ ሊቆም ነው፤ ሚኒስትሩ 'ጥራት የሌላቸውን በቢሊዮን አንደጉም' አሉ!!
የትምህርት ሚኒስትር ፤ በተማሪዎች መመረጥ ያልቻሉ ዩኒቨርሲቲዎችን መንግሥት ለሌሎች አገልግሎቶች ሊያውል ይችላል ሲል ማስጠንቀቂያ ሰጠ።
ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ (ፕ/ር) በቅርብ ዓመታት ውስጥ ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምደባ እንደሚያቆም ገልጸዋል። በምትኩም ተማሪዎች በራሳቸው በመረጡት ዩኒቨርሲቲ መማር እንደሚጀምሩ አስታውቀዋል።
ሚኒስትሩ ይህ ውሳኔ ምክንያታዊ መሆኑን ሲያስረዱ፣ በተማሪዎች ለማይመረጡ ዩኒቨርሲቲዎች መንግሥት በቢሊየን የሚቆጠር በጀት መመደቡ ተገቢ አይሆንም ብለዋል።
በተጨማሪም፣ "እንደከዚህ ቀደሙ አንዴ ዩኒቨርሲቲ ተከፍቷልና በዚሁ ይቀጥላል የሚባል አሰራርም እንደማይኖር" አስረድተዋል።
ይህ የተገለጸው የትምህርት ሚኒስቴር ከመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የቁልፍ ተግባራት የፊርማ ስነሥርዓት በዛሬው ዕለት ባካሄደበት ወቅት መሆኑን ኢፕድ ዘግቧል።
"በተማሪዎች መመረጥ ያልቻሉ ዩኒቨርሲቲዎችን መንግሥት ለሌሎች አገልግሎቶች ሊያውል እንደሚችል ጥርጥር አይግባችሁ" ያሉት ሚኒስትሩ ዩኒቨርሲቲዎች ተመራጭ ሆነው ለመቀጠል፣ የመማር ማስተማር ሥርዓታቸው ጥራት ያለው እንዲሆን መስራት እንደሚጠበቅባቸው ማሳሰቢያ ተሰጥቷቸዋል።#CapitalNews
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ

❤61👍45😁15🤔4👎1🤯1
በሰሜን ወሎ ተካሔዶ በነበረው ውጊያ፤ በፋኖ ኀይሎች ተይዘው የነበሩትን የመንግሥት የፀጥታ አባላት መረከቡን ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ አስታወቀ!
በሰሜን ወሎ ዞን ዋና ከተማ ወልዲያ ዙሪያ ተካሔዶ በነበረው ውጊያ በፋኖ ኀይሎች ተይዘው የነበሩትን የመንግሥት የፀጥታ አባላት መረከቡን ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ አስታውቋል።
በመስከረም ወር አጋማሽ በዞኑ የተካሔደው “ድንገተኛ ውጊያ ከፍተኛ ጉዳትን ያስከተለ” እንደነበር ዓለም አቀፉ ድጋፍ ሰጪ ተቋም ገልጿል። ባለፉት 6 ቀናት ሁለት ቡድኖችን በወልዲያና በላሊበላ ከተማዎች በማስፈር የሰብአዊ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን ጉዳዩ ን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ላይ አስፍሯል።
በአንድ ሳምንት ውስጥ ለወልዲያ ሆስፒታል እንዲሁም በሙጃ እና ኩልመስክ አካባቢ ለሚገኙ የጤና ተቋማት የሕክምና መሳሪያዎችን ማበርከቱን አስታውቋል።ከመሳሪያዎቹ ውስጥ የቀዶ ጥገና ሕክምና ለመስጠት የሚያገለግሉ እንደሚገኝበት ተመላክቷል። በዚህም በውጊያው ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰባቸው ውስጥ 250 ለሚሆኑት የቀዶ ጥገና ሕክምና መስጠት እንደቻለ ተገልጿል።
ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ካደረገው የሕክምና ድጋፍ በተጨማሪ በፋኖ ኃይሎች ተይዘው የሚገኙ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎችን መጎብኘቱን ትላንት ባወጣው መግለጫ ላይ አመልክቷል። ኮሚቴው አክሎም ወታደሮቹን ከፋኖ ኃይሎች ተረክቦ ወልዲያ ከሚገኙ አባላቶቻቸው ጋር እንዲቀላቀሉ መደረጋቸውን አመልክቷል።
በላሊበላ ከተማ የሚገኘውን የድጋፍ ሰጪ ቡድን የሚመሩት ማርቲን ታልማን “በቅርብ ቀናት ውስጥ በሰሜን ወሎ በርካታ ሰዎች በውጊያው ተገድለዋል እንዲሁም ቆስለዋል” ሲሉ ተናግረዋል። ሆኖም የጤና ተቋማት “በተገደበ አቅም” የቆሰሉ ወታደሮችንና ሲቪሎችን እያከሙ መሆናቸውንም ቡድን መሪው አስታውቀዋል።

❤91👏15🤔5🥰3
በትግራይ ክልል ዛሬ ቅዳሜ ጥቅምት 1፤ 2018 ምሽት፤ ለሁለት ጊዜያት የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የአሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ መስሪያ ቤት ገለጸ።
ከምሽቱ 1፡01 ላይ የደረሰው ርዕደ መሬት በሬክተር ስኬል 5.3 መለካቱን የገለጸው መስሪያ ቤቱ፤ ከ17 ደቂቃ በኋላ የተከሰተው በሬክተር ስኬል 5.3 መድረሱን አስታውቋል።
ከእነዚህ ክስተቶች አራት ሰዓት አስቀድሞ፤ በሬክተር ስኬል 4.2 የተላከ ሌላ የመሬት መንቀጥቀጥ ከመቐለ ከተማ በሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ 47 ኪሎ ሜትር ርቀት ባለ ቦታ ላይ መድረሱን መስሪያ ቤቱ መዝግቧል። ዛሬ ምሽት ከደረሱት ርዕደ መሬቶች የመጀመሪያው የተመዘገበው ከመቐለ ከተማ 58 ኪሎ ሜትር ርቀት ባለ ቦታ ላይ መሆኑንም ከተቋሙ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ሁለተኛው የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተው ከውቅሮ ከተማ 32 ኪሎ ሜትር በሚርቅ ቦታ ላይ እንደሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከሰቱ ርዕደ መሬቶችን የሚመዘግበው “ቮልካኖ ዲስከቨሪ” በድረ ገጹ ላይ አስፍሯል። ርዕደ መሬቱ ያስከተለው ንዝረት በሻጉባይ፣ በውቅሮ፣ ዶሎ፣ በዕዳጋ ሐሙስ እና በአዲግራት ከተሞች እንደተሰማ ድረ ገጹ ጠቁሟል።
የዛሬው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት፤ ክስተቱ ከተፈጠረበት 92 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው የአረርቲ ከተማ ጭምር እንደደረሰ “ቮልካኖ ዲስከቨሪ” ገልጿል። በትግራይ ክልል ርዕደ መሬት ሲያጋጥም ካለፈው የካቲት ወር በኋላ የአሁኑ የመጀመሪያው ነው።
ባለፈው ዓመት የካቲት ወር መጨረሻ ገደማ ከአዲግራት ከተማ 46 ኪሎ ሜትር በስተምስራቅ ርቀት ላይ በሚገኝ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ እንደነበር ይታወሳል። እኩለ ለሊት አቅራቢያ የተከሰተው ይኸው ርዕደ መሬት በሬክተር ስኬል 5.2 የተለካ ነበር።
Via ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

❤61👍7😢3👏2🤔2🤯1
አሳዛኝ ዜና!
በጨፋ_ሮቢት ከተማ በደረሰ አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ የ11ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ 23 ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት ደረሰ
በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ጨፋ ሮቢት ከተማ ጃራ ድልድይ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በደረሰ አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ 23 ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።
አደጋው የደረሰው ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ በመጓዝ ላይ የነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ኢት 73290 የሆነ አውቶብስ እና ከደሴ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ኢት 41157 ተሳቢ መኪና ጃራ ድልድይ አካባቢ በመጋጨታቸው ነው ተብሏል።
የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ፖሊስ መምሪያ ኀላፊ ዑመር መሐመድ በአደጋው እስካሁን የ11 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ገልፀው 23 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል።
በተጨማሪም በርካታ ሰዎች ቀላል ጉዳት እንዳጋጠማቸው ጠቅሰው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በአሁኑ ሰዓት በጨፋ ሮቢት ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገላቸው መኾኑን ገልጸዋል።
የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችልም የገለፁት ኀላፊው አያይዘውም አሽከርካሪዎች በሚጓዙበት ወቅት በጥንቃቄ ሊያሽከረክሩ እንደሚገባ ማሳሰባቸውን አሚኮ ዘግቧል።
በኢትዮጵያ የተለያዩ አከባቢዎች የሚደርሱ የትራፊክ አደጋዎች መባባሳቸውን ዘገባዎች ያመለክታሉ፡፡ አደጋዎቹ የበርካታ ሰዎችን ህይወት የቀጠፉ ሲሆን አያሌ የአካል ጉዳት እና የንብረት ውድመት አስከትለዋል፡፡

😭79❤59👍5🤯2
#ቴምርፕሮፐርቲስ
⩩ 100% ለሚከፍሉ ከ30% እስከ 35% የሚደርስ ታላቅ እውነተኛ ቅናሽ አዘጋጅተናል።
⩩ እንዲሁም 40% ለሚከፍሉ፣ ከከፈሉት ላይ የ20% ቅናሽ አዘጋጅተናል።
📍 ሊሴ ገ/ማርያም
👉 66 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 7,590,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (759,000)
👉 71 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 8,165,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (816,500)
👉 132 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 14,520,000
ቅድመ ክፍያ 10% (1,452,000)
👉 146 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 16,060,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (1,606,000)
📍ሐይሌ ጋርመንት
ባለ 3 መኝታ
👉 139ካሬ ሙሉ ክፍያ = 14,590,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (1,459,000)
📍 አያት (ፈረስ ቤት)
👉 88 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 8,360,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (836,000)
👉 108 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 10,260,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (1,026,000)
👉 137 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 15,070,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (1,50,000)
⩩ ቀሪውን 90%፤ በግንባታ ሂደት፤ ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት።
ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን!
+251964439488
+251907232222
Telegram: https://t.me/OusmanTemer
WhatsApp: https://wa.me/251964439488

❤21👎2🤔1
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በOBN HORN OF AFRICA TV ሊመጣ ነው
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን ለማስተላለፍ የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ (OBN) የሚያስችለውን የምስል መብት በጨረታ ማሸነፉ በነገው ዕለት ይፋ ይሆናል ።
ታዲያ በነገው ዕለትም ይፋዊ የስምምነት ፊርማ ከሊጉ አወዳዳሪ ጋር የሚፈራረሙ ሲሆን ከ ቅዳሜ ጥቅምት 8 ጀምሮ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን በቀጥታ እንደሚያደርስ ተገልጿል።
የቀጥታ ሰርጭቱ በOBN HORN OF AFRICA በአማርኛ ቋንቋ የሚተላለፍ ሲሆን እንደ አማራጭ በኦሮምኛ ቋንቋም ሊሰራጭ ስለመቻሉ ጣቢያችን ያገኘው መረጃ ያመላክታል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ያለፉትን አምስት አመታት DSTV ሲያሰትላልፍ እንድነበር ይታውሳል። የ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ጥቅምት 08/2018 እንደሚጀምር ይታወቃል።

❤57😁34🤔4
የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ድህነት መጠን በ2025 ዓ.ም. ወደ 43 በመቶ ከፍ ሊል እንደሚችል ገለጸ
የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ያለውን ድህነት በተመለከተ አዲስ ባወጣው ግምገማ፣ በአውሮፓውያን አቆጣጠር 2016 ዓ.ም 33 በመቶ የነበረው የድህነት መጠን፣ በተያዘው 2025 ዓ.ም ወደ 43 በመቶ ከፍ ሊል እንደሚችል አስታወቀ። ይህም የዓመታት ለውጥን ወደ ኋላ የሚቀለብስ ነው ብሏል።
የዓለም ባንክ እንደገለጸው፣ ኢትዮጵያ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ድህነትን በመቀነስ ረገድ ጉልህ እድገት ካሳየች በኋላ፣ ባለፉት ጥቂት አመታት የተከሰቱ ውስጣዊና ውጫዊ ተግዳሮቶች የኑሮ ደረጃ ላይ ተጽዕኖ አድርገዋል። እነዚህ ተግዳሮቶች የኮቪድ-19 ወረርሽኝ፣ የትግራይ ግጭት፣ ከፍተኛ ድርቅ፣ የጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) ዕድገት መቀዛቀዝ እና የዋጋ ግሽበት ናቸው ብሏል።
በዚህም ምክንያት፣ የድህነት መጠኑ እ.ኤ.አ. በ2016 ከነበረው 33 በመቶ በ2021 ወደ 39 በመቶ ከፍ ማለቱ ገልጿል። በቀጣይ ዓመታትም የበለጠ ይጨምራል ተብሎ እንደሚጠበቅ የዓለም ባንክ አስታውቋል።
የዋጋ ግሽበት በከተማ ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያደረሰ ሲሆን፣ አብዛኛው የገጠር ቤተሰቦችም ቢሆኑ ውስን በሆነ የገበያ ተሳትፎ ምክንያት ከምግብ ዋጋ ጭማሪ ተጠቃሚ አለመሆናቸውም ተገልጿል።

❤55😁53😭24👎5👍4🥰2😱1
"አሁን መልሶ ግንባታ እንጀምራለን"- ዶናልድ ትራምፕ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በእስራኤል ምክር ቤት ንግግር ካደረጉ በኋላ ወደ ግብፅ አቅንተዋል።
በግብፅ፣ ሻርም ኤል-ሻይክ ከ20 በላይ የሚሆኑ የአገራት መሪዎች ተሰባስበው በቀጣዩ የጋዛ የሰላም ዕቅድ ላይ ተወያይተዋል።
ግብፅ፣ ኳታር፣ ቱርክ እና አሜሪካ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ጠባቂዎች ሆነው ፊርማቸውን አኑረዋል።
"አዲስ ውብ ቀን መጥቶልናል። አሁን ጊዜው መልሶ የመገንባት ነው" ብለዋል ትራምፕ።"ለመካከለኛው ምሥራቅ ታሪካዊ ቀን ነው" ሲሉም አክለዋል።

"አዲስ ውብ ቀን መጥቶልናል። አሁን ጊዜው መልሶ የመገንባት ነው" ብለዋል ትራምፕ።
"ለመካከለኛው ምሥራቅ ታሪካዊ ቀን ነው" ሲሉም አክለዋል።
ትራምፕ የሰላም ዕቅዱ ሁለተኛ ክፍል ተጀምሯል ብለዋል።
ትራምፕ በግብፁ ውይይት ላይ "ሁሉም ሰው ደስተኛ ነው። እዚህ ለመድረስ 3,000 ዓመታት መውሰዱን ታምናላችሁ? ብለዋል።
የግብፅ ፕሬዝዳንት አብደልፋታሕ አል-ሲሲ በአገራቸው ትልቁ የሆነውን 'ኦርደር ኦፍ ዘ ናይል' ሽልማት ለትራምፕ ሰጥተዋል።
አል-ሲሲ "አስከፊው ጊዜ ያከተመበት ታሪካዊ እርምጃ ነው" ሲሉ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ገልጸዋል።

❤75👎1
#ቴምርፕሮፐርቲስ
⩩ 100% ለሚከፍሉ ከ30% እስከ 35% የሚደርስ ታላቅ እውነተኛ ቅናሽ አዘጋጅተናል።
⩩ እንዲሁም 40% ለሚከፍሉ፣ ከከፈሉት ላይ የ20% ቅናሽ አዘጋጅተናል።
📍 ሊሴ ገ/ማርያም
👉 66 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 7,590,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (759,000)
👉 71 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 8,165,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (816,500)
👉 132 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 14,520,000
ቅድመ ክፍያ 10% (1,452,000)
👉 146 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 16,060,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (1,606,000)
📍ሐይሌ ጋርመንት
ባለ 3 መኝታ
👉 139ካሬ ሙሉ ክፍያ = 14,590,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (1,459,000)
📍 አያት (ፈረስ ቤት)
👉 88 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 8,360,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (836,000)
👉 108 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 10,260,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (1,026,000)
👉 137 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 15,070,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (1,50,000)
⩩ ቀሪውን 90%፤ በግንባታ ሂደት፤ ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት።
ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን!
+251964439488
+251907232222
Telegram: https://t.me/OusmanTemer
WhatsApp: https://wa.me/251964439488
⩩ 100% ለሚከፍሉ ከ30% እስከ 35% የሚደርስ ታላቅ እውነተኛ ቅናሽ አዘጋጅተናል።
⩩ እንዲሁም 40% ለሚከፍሉ፣ ከከፈሉት ላይ የ20% ቅናሽ አዘጋጅተናል።
📍 ሊሴ ገ/ማርያም
👉 66 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 7,590,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (759,000)
👉 71 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 8,165,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (816,500)
👉 132 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 14,520,000
ቅድመ ክፍያ 10% (1,452,000)
👉 146 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 16,060,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (1,606,000)
📍ሐይሌ ጋርመንት
ባለ 3 መኝታ
👉 139ካሬ ሙሉ ክፍያ = 14,590,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (1,459,000)
📍 አያት (ፈረስ ቤት)
👉 88 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 8,360,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (836,000)
👉 108 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 10,260,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (1,026,000)
👉 137 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 15,070,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (1,50,000)
⩩ ቀሪውን 90%፤ በግንባታ ሂደት፤ ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት።
ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን!
+251964439488
+251907232222
Telegram: https://t.me/OusmanTemer
WhatsApp: https://wa.me/251964439488
❤18
ከኢትዮጵያ ጋር ያለስምምነት የተለያዩት የ1 ቢሊዮን ዶላር አበዳሪዎች "ሕጋዊ አማራጭ" ሊከተሉ እንደሚችሉ ተናገሩ
ኢትዮጵያ በጊዜው ያልከፈለችውን የአንድ ቢሊዮን ዶላር ዩሮ ቦንድ በተመለከተ በገንዘብ ሚኒስቴር እና በግል አበዳሪዎች ኮሚቴ መካከል ሲደርግ የነበረው ድርድር ያለ ስምምነት ተጠናቀቀ።
ገንዘብ ሚኒስቴር ለቀናት በቆየው ንግግር "ጉልህ መሻሻል" መታየቱን ቢገልጽም የአበዳሪዎች ኮሚቴ ግን ድርድሩ "ፍሬ አልባ" ደረጃ ላይ በመድረሱ "ሕጋዊ አማራጭ" ሊከተል እንደሚችል አስታውቋል።
ገንዘብ ሚኒስቴር፤ የብድሩን አከፋፈል ሁኔታ ለማስተካከል ሲካሄድ የቆየው ድርድር ያለ ስምምነት መጠናቀቁን ያስታወቀው ትናንት ማክሰኞ ጥቅምት 4/2018 ዓ. ም. ባወጣው መግለጫ ነው።
በፈረንሳይ ፓሪስ ከተማ የተካሄደው ድርድር ላይ የኢትዮጵያ ልዑክ 'ዋይት ኤንድ ኬዝ' የተሰኘውን የሕግ አማካሪ እና 'ላዛርድ' የተባለውን የፋይናንስ አማካሪ ይዞ ቀርቧል።
የቦንዱ ገዢዎችን የወከለው የአበዳሪዎች ኮሚቴም በተመሳሳይ ድርድሩ ላይ የተገኘው ከሕግ እና የፋይናንስ አማካሪዎቹ ጋር ነው።
ኢትዮጵያ በድርድሩ ወቅት፤ ሁሉንም አበዳሪዎችን በእኩልነት ለማስተናገድ በያዘችውን መርሕ ጸንታ እንደቀጠለች በገንዘብ ሚኒስቴር መግለጫ ላይ ሰፍሯል። ኮሚቴው በአሁኑ ሰዓት ድርድሩ "ፍሬ አልባ" ደረጃ ላይ ነው የሚል ድምዳሜ ላይ መድረሱንም ተናግሯል። "የሕግ እርምጃን ጨምሮ ሁሉንም አማራጮች እያጤነ" መሆኑን እንዳስታወቀም ሮይተርስ ዘግቧል።

❤65😁30🤔3🤯2👎1
የደሴ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በወጣት ሊዛ ደሳለኝ ግድያ ምርመራ መጀመሩን አስታወቀ
መስከረም 28 ቀን 2018 ዓ ም በደሴ ከተማ ቦርከና ቀበሌ ሀቢታት ተብሎ በሚጠራ ቦታ ላይ በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወቷ ያለፈው ወጣት ሊዛ ደሳለኝ ግድያ ላይ ምርመራ መጀመሩን የከተማው ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።
ወጣቷ ባሳለፍነው ሳምንት መስከረም 28 ቀን 2018 ዓ.ም. ሞባይል ስልክ ለማሠራት ከምሽቱ አንድ ሰዓት አካባቢ ከቤቷ በወጣች በአንድ ሰዓት ውስጥ ጥቃት ተፈፅሞባት መንገድ ዳር ወድቃ የተገኘች ሲሆን ለሕክምና እርዳታ ወደ ደሴ ሪፈራል ሆስፒታል ብትወሰድም ሕይወቷን ማትረፍ አልተቻለም።
በከተማው ውስጥ በሚገኘው ድሪም ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ የአራተኛ ዓመት የፋርማሲ ተማሪ የነበረችው ሊዛ፣ በዚህ ዓመት ትምህርቷን አጠናቃ ለመመረቅ እየተዘጋጀች ነበር።
ድርጊቱ በማህበራዊ ሚዲያ እና በከተማዋ ነዋሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ቁጣን መቀስቀሱም ተነግሯል። በከተማዋ ከዚህ ቀደም እንዲህ ዓይነት ድርጊት ተፈፅሞ አያውቅም ያሉ አንድ ነዋሪ ድርጊቱ ነዋሪዎችን እንዳሳዘነ እና እንዳስቆጣ ተናግረው ወጣቷ አስቸኳይ ፍትሕ እንድታገኝም ጠይቀዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
የደሴ ከተማ ፖሊስም የፍትህ አካላትን ያካተተ ቡድን በማዋቀር ምርመራውን አጠናክሮ መጀመሩን እና በቀጣይም የምርመራ ቡድኑ የደረሰበትን ውጤት ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ገልጿል።
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በሀገራችን በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች እየጨመሩ መተዋል።
በቅርብ ዓመታት ውስጥ ብቻ በተፈፀመባቸው ጥቃት ሕይወታቸውን ያጡ፣ ለሥነ ልቦናዊ እና ለማኅበራዊ ቀውስ የተዳረጉት ሴቶች ጥቂት የሚባሉ አይደሉም።

❤43😢29😱2👍1👏1🤯1
ከ70 በላይ ደሴቶች ላሉት የንጋት ሐይቅ ማስተር ፕላን ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገለፀ
ከ74 ቢሊየን ሜትሪክ ኪዩብ በላይ ውሃ የያዘው እና ከ70 በላይ ደሴቶች ያሉት ንጋት ሐይቅ ረዥም ጊዜ ሳይበላሽና በደለል ሳይሞላ እንዲቆይ የተቀናጀ ማስተር ፕላን እንደሚያስፈልግ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ገልጿል።
ይህ የተገለፀው የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር የንጋት ሐይቅ ረቂቅ ማስተር ፕላን ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቢሾፍቱ ከተማ የውይይት መድረክ ባካሄደበት ወቅት ነው።
በሕዳሴ ግድብ ላይ የተፈጠረው ንጋት ሰው ሰራሽ ሐይቅ ለኢትዮጵያ ሰፊ በረከት ይዞ መጥቷል ሲሉ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋ ተናግረዋል።
በተጨማሪም የሱዳንን ሪዞሬ ሐይቅና የኢትዮጵያን ንጋት ሐይቅ በልማት እናገናኛለን ያሉ ሲሆን፤ የጥቅም ግጭት ሳይፈጠር ሱዳንን ተጠቃሚ ለማድረግ ይሰራል ብለዋል።
በግድቡ ላይ የተፈጠረው በአፍሪካ 4ኛው ግዙፉ የንጋት ሐይቅ፥ለሀገራዊ ኢኮኖሚ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አንስተዋል።
በሐይቁ ላይ የሚሰሩ የልማት ስራዎች የተደራጁ መሆን እንደሚገባቸው የገለፁት ኢንጅነር ሀብታሙ፤ ለዓሳ ሀብት ልማት፣ ትራንስፖርት እና ቱሪዝምን ጨምሮ ለዜጎች ሰፊ የስራ ዕድል የመፍጠር አቅም ያለው መሆኑን ጠቅሰዋል።

❤38👎3🤔2
የእነማይ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ በተተኮሰባቸው ጥይት ተገደሉ
በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን የእነማይ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኋላፊ የነበሩት አቶ አዲሱ ተሻለ በተተኮሰባቸው ጥይት መገደላቸውን የወረዳው አስተዳደር አስታወቀ፡፡
የአስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ዛሬ ጥቅምት 6 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ላይ ባወጣው የሀዘን መግለጫ ምክትል አስተዳዳሪው በዛሬው ዕለት ከመኖሪያ ቤታቸው ተነስተው ወደ ስራ ቦታ በመሄድ ላይ እያሉ ከጠዋቱ 12:30 አካባቢ በተተኮሰባቸው ጥይት መገደላቸውን ገልጿል፡፡
ለግድያው "ጽንፈኛ" ብሎ የጠራውን አካል ተጠያቂ ያደረገው መግለጫው፤ "መንግስት ችግሮችን በሰለጠነ መንገድና በውይይት ለመፍታት በጫካ ለሚንቀሳቀሱ አካላት ተደጋጋሚ እድልና ጥያቄ ሲሰጥ መቆየቱንና እየሰጠ ያለ መሆኑን" በመግለጫው አመልክቷል፡፡

❤66👎15😁12👍4🥰4😢2🤔1
#ቴምርፕሮፐርቲስ
⩩ 100% ለሚከፍሉ ከ30% እስከ 35% የሚደርስ ታላቅ እውነተኛ ቅናሽ አዘጋጅተናል።
⩩ እንዲሁም 40% ለሚከፍሉ፣ ከከፈሉት ላይ የ20% ቅናሽ አዘጋጅተናል።
📍 ሊሴ ገ/ማርያም
👉 66 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 7,590,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (759,000)
👉 71 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 8,165,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (816,500)
👉 132 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 14,520,000
ቅድመ ክፍያ 10% (1,452,000)
👉 146 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 16,060,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (1,606,000)
📍ሐይሌ ጋርመንት
ባለ 3 መኝታ
👉 139ካሬ ሙሉ ክፍያ = 14,590,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (1,459,000)
📍 አያት (ፈረስ ቤት)
👉 88 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 8,360,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (836,000)
👉 108 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 10,260,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (1,026,000)
👉 137 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 15,070,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (1,50,000)
⩩ ቀሪውን 90%፤ በግንባታ ሂደት፤ ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት።
ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን!
+251964439488
+251907232222
Telegram: https://t.me/OusmanTemer
WhatsApp: https://wa.me/251964439488
⩩ 100% ለሚከፍሉ ከ30% እስከ 35% የሚደርስ ታላቅ እውነተኛ ቅናሽ አዘጋጅተናል።
⩩ እንዲሁም 40% ለሚከፍሉ፣ ከከፈሉት ላይ የ20% ቅናሽ አዘጋጅተናል።
📍 ሊሴ ገ/ማርያም
👉 66 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 7,590,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (759,000)
👉 71 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 8,165,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (816,500)
👉 132 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 14,520,000
ቅድመ ክፍያ 10% (1,452,000)
👉 146 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 16,060,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (1,606,000)
📍ሐይሌ ጋርመንት
ባለ 3 መኝታ
👉 139ካሬ ሙሉ ክፍያ = 14,590,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (1,459,000)
📍 አያት (ፈረስ ቤት)
👉 88 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 8,360,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (836,000)
👉 108 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 10,260,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (1,026,000)
👉 137 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 15,070,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (1,50,000)
⩩ ቀሪውን 90%፤ በግንባታ ሂደት፤ ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት።
ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን!
+251964439488
+251907232222
Telegram: https://t.me/OusmanTemer
WhatsApp: https://wa.me/251964439488
❤20
#MoE
በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች የሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምርጫቸውን በየትምህርት ቤታቸው በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ ጥቅምት 12/2018 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡
የሪሚዲያል ፕሮግራም #የማያስተናግዱ ዩኒቨርሲቲዎች ፦
1. አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
2. አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
3. አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
4. ሲቪል ሰርቪርስ ዩኒቨርሲቲ
5. ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
6. ጅማ ዩኒቨርሲቲ
7. ኮተቤ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ናቸው።
ተማሪዎች የሞሉትን ምርጫ በ student.ethernet.edu.et በኩል ማረጋገጥ የሚችሉ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

❤45👍5🤔1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቪዲዮ🌺Special Base for Refrigerators & washing machine
ለፍሪጅ ማስቀመጫ እና ማንቀሳቀሻ ምርጥ ነው!
👉 እስከ 300 ኪሎ ድረስ ዕቃ የሚሸከም
👉 ወፍራም ብረት የሆነ
👉 ገጠማ ዝባዝንኬ የማይፈልግ
👉 45cm to 70 cm ድረስ የሚለጠጥ…
✅ 2000 Birr
☎️ 0901882392
☎️ 0931448106
አድራሻ፣ መገናኛ ሲሳይ ፕላዛ 1ኛ ፎቅ 1-010ቁ!(ከዘፍነሽ ወረድ ሲሉ ግሬስሞል አጠገብ፣ መሶብ ሀበሻ ሆቴል ፊትለፊት)
💬 በTelegram ለማዘዝ ⤵️ ይጠቀሙ
👉 @AddisEkachat
👉 @Antenehg1
ለተጨማሪ ማብራሪያ የቴሌግራም ገፃችን⤵️
🌞 https://t.me/AddisEka1
🌞 https://t.me/AddisEka1
የዴሊቨሪ ጨምረው ያሉበት እናደርሳለን።

❤12
የትግራይ ኃይል አባላት ለአምስተኛ ቀን ያካሄዱት የመኪና መንገድ መዝጋት ያካተተ ሰልፍ ተከትሎ የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር የሰራዊት አባላት ተጠቃሚ የሚያረጋግጥ ደንብ ማጸደቁ አስታውቋል።
እሁድ ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም የጀመረው የትግራይ ኃይል ሰልፍና ተቃውሞ ዛሬ ቀጥሎ ከእንዳስላሰ-ሽረ ፣ አክሱም ፣ ዓድዋና ተምቤንና ሌሎች አከባቢዎች ወደ መቐለ የሚያስገባ መንገድ ተዘግቶ ውሏል።
ይህንን ተከትሎ ዛሬ ጥቅምት 7/2018 ዓ.ም ከሰዓት በኃላ የፅሁፍ መግለጫ ያወጣው የጊዚያዊ እስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት ካቢኔ ጥቅምት 5/2018 ዓ.ም ያወጣው የትግራይ የፀጥታ ሃይሎች ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ረቂቅ ደንብ ዛሬ ማፅደቁን አመልክተዋል።
ካቢኔው በዛሬው አስቸኳይ ስብሰባው የትግራይ የፀጥታ ሃይሎች ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ደንብ በዝርዝር ተወያይቶ ተግባራዊ እንዲሆን በሙሉ ድምፅ አፅድቆታል።
የፀደቀው ደንብ ፦
- መሰረታዊ ፍላጎቶች
- የህክምና አገልግሎት
- የቤት መስሪያ መሬት
- በመንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት የሚሰጥ የክብር አገልግሎት
- ትምህርት ስልጠናና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች ያካተተ ነው ብሏል ከፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት የተሰጠው የፅሁፍ መግለጫ።

❤70👍15
ታላቁ የሃይማኖት አባት ሐጂ ኡመር ኢድሪስ አረፉ።
የቀድሞ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የክቡር ዶ/ር ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ወደ አኼራ ሄደዋል።
ታላቁ የሃይማኖት አባት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ባጋጠማቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ወደ አኼራ ሄደዋል።
ኢትዮ መረጃ ለታላቁ አባት ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ቤተሰቦች እንዲሁም ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ መፅናናትን ይመኛል።🕯

😭196❤40😢20👍5🤔3😁1