ETHIO-MEREJAÂŽ
110K subscribers
25.9K photos
486 videos
22 files
12.9K links
News & Media CompanyÂŽ

USA : Washington

Addisababa, Ethiopia🇪🇹
.
Buy ads: https://telega.io/c/ethio_mereja
.
ለጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት
ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ!!
👉 @ethio_merejabot ✔
Download Telegram
ከ60 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ወርቅ ይዘው በሕገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ!!

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከ60 ሚሊየን ብር በላይ የዋጋ ግምት ያለው ወርቅ እና ከ4 ሚሊየን ብር በላይ ይዘው በሕገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ተጠርጣሪዎችን ከእነኤግዚቢቱ በአሶሳ ከተማ አምባ አንድ በሚባል ቦታ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል፡፡

በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረው ወርቅና ጥሬ ገንዘብ ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ሊውል የቻለው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ የኮንትሮባንድ ቁጥጥር ፖሊስ መምሪያ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ባደረገው ክትትል መሆኑን በመምሪያው ሬጅመንት አንድ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ዳኘ አለማየሁ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ምርመራ እያጣራባቸው መሆኑን ዋና ኢንስፔክተሩ ገልጸው፤ የተያዘው ወርቅና ጥሬ ገንዘብም ለአሶሳ ከተማ ጉሙሩክ ቅርንጫፍ ገቢ መደረጉን ተናግረዋል።

ፖሊስ ኮንትሮባንድና ሕገ-ወጥ ንግድ በሀገር ኢኮኖሚ እና በሕጋዊ ነጋዴዎች ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት በመገንዘብ ከሕዝብና ከመንግሰት የተጣለበትን አደራ ለመወጣት ሕዝብን ባሳተፈ መልኩ ስኬታማ የመከላከል ሥራ እያከናወነ መሆኑን ዋና ኢንስፔክተር ዳኜ አለማየሁ ጠቁመዋል።

  T.me/ethio_mereja
      ኢትዮ-መረጃ
❤45👍12🥰2👎1
ከመቅደላ የተዘረፈ የወርቅ የፀጉር ማስያዣ ሊመለስ ነው

በ19ኛው ክፍለ ዘመን ከመቅደላ የተዘረፈየወርቅ የፀጉር ማስያዣ በጥር ወር መጀመሪያ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለስ ተገለፀ።

ይህ ቅርስ የዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ ሁለተኛ ባለቤት የነበሩት የእቴጌጥሩወርቅ ውቤ ሲሆን፥ አሁንም በቀድሞው ጌጣጌጥ ማቅረቢያ ሣጥኑ ውስጥ ተጠብቆ ይገኛል።

ጥንታዊ ቅርሱ ከ150 ዓመታት በላይ በግል ንብረት ስብስቦች ውስጥተይዞ ቆይቷል።

የፀጉር ማስያዣው በቅርቡ ከተመለሰው የ1868ቱ የመቅደላ ጦርነት ጋሻ ጋር በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም ለዕይታ እንደሚቀርብ ስፑትኒክ ዘግቧል።

  T.me/ethio_mereja
      ኢትዮ-መረጃ
❤60👍12👎1
ታዋቂው የቪዲዮ ማጋሪያ መተግበሪያ ቲክቶክ፣ በአሜሪካ ከተደቀነበት የእገዳ አደጋ ለመዳን ሲባል የአሜሪካውን የቢዝነስ ዘርፉን ለሶስት ግዙፍ የአሜሪካ ኢንቨስተሮች ለመሸጥ ከስምምነት ላይ ደረሰ።

ገዢዎቹ ኦራክል፣ ሲልቨር ሌክ እና ኤምጂኤክስ የተባሉ ኩባንያዎች ናቸው። ይህ ስምምነት ተወዳጁ መተግበሪያ በአሜሪካ ምድር ያለ ምንም ገደብ አገልግሎቱን እንዲቀጥል የሚያስችለው እንደሆነ ተገልጿል።

አሶሼትድ ፕሬስ እንደዘገበው፣ ሽያጩ በመጪው ጃንዋሪ 22 ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል። በስምምነቱ መሠረት የሚቋቋመው አዲሱ የ"ቲክቶክ ዩ.ኤስ." የሽርክና ኩባንያ የባለቤትነት ድርሻ እንደሚከተለው ተዋቅሯል። አዲሱ የባለሀብቶች ስብስብ በአጠቃላይ 50 በመቶውን ድርሻ ይይዛሉ። ከዚህ ውስጥ ኦራክል፣ ሲልቨር ሌክ እና ኤምጂኤክስ እያንዳንዳቸው 15 በመቶ ድርሻ ይኖራቸዋል። የቲክቶክ እናት ኩባንያ የሆነው የባይትዳንስ ነባር ባለሀብቶች ተባባሪዎች 30.1 በመቶ ይይዛሉ። የቻይናው ኩባንያ ባይትዳንስ በበኩሉ 19.9 በመቶ ድርሻ ብቻ ይዞ ይቆያል።

ይህ ስምምነት የተደረገው የአሜሪካ መንግስት "ቲክቶክ ከቻይናው ኩባንያ ቁጥጥር ካልወጣ በብሔራዊ ደህንነት ስጋት ምክንያት ይታገዳለ" የሚል ህግ ካወጣ በኋላ ነው። የቀድሞው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የፈረሙት ይህ ህግ [PAFACA Act]፣ መተግበሪያው የአሜሪካውያንን መረጃ ለቻይና መንግስት አሳልፎ ሊሰጥ ይችላል በሚል ስጋት ላይ የተመሰረተ ነበር።

በመጀመሪያው የሥልጣን ዘመናቸው ቲክቶክን ለማገድ ሞክረው የነበሩት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ በ2024 ምርጫ አሸናፊ ሆነው ከተመለሱ በኋላ አቋማቸውን በማለዘብ ለእገዳው የተቀመጠውን የጊዜ ገደብ አራዝመውት ነበር።

  T.me/ethio_mereja
      ኢትዮ-መረጃ
❤37🥰2
ETHIO SPARK COMPUTER & ACCESSORIES

ETHIO SPARK   ፈጣን እና ዘመናዊ  የሆኑ á‹¨á‹“áˆˆáˆá‰˝áŠ•áŠ• ምርጥ
🖥  አዳዲስ  ላፕቶፖች
🖥  ጌሚንግ  ላፕቶፖች
🖥  ቢዝነስ  ላፕቶፖች
🖥  ዱባይ ዩዝድ ላፕቶፖች እና
🖥  የተለየዩ የላፕቶፕ  አክሰሰሪዎችን ከ አንድ አመት ዋስትና ጋር እንዲሁም  ከልዩ  መስተንግዶ ጋር    እንጠብቆታለን።

 á‹­á‹°á‹áˆ‰ 👇

☎️+251974967884

የፁሁፍ መልዕክት 👇👇

💌    @Dm4ethio

📍 Location: 📌 Addis Ababa, Megenagn

Telegram link: https://t.me/EthioSpark16

You tube link:https://www.youtube.com/@EthioSpark0

Instagram link: https://www.instagram.com/ethiopark16/

Facebook :https://www.facebook.com/share/177eogKin1/

Tiktok link: tiktok.com/@ethiospark

🌐 Website:www.ethiospark16.com
❤9
"የአእላፋት ዝማሬ" በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ለሦስተኛ ጊዜ ይካሄዳል

የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ (ኢጃት) ከታኅሣሥ 16 እስከ ታኅሣሥ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በግዮን ሆቴል ግራውንድስ ላይ የሚቆይ "የአእላፋት ሳምንት" የተሰኘ ዘርፈ ብዙ ዐውደ ርዕይና የጃን ፎረም መድረክ ማዘጋጀቱን አስታወቀ።

ማኅበሩ በዛሬው እለት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተገለጸው የመርሐግብሩ ዋና ዓላማ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሊቃውንት፣ ደራሲያንና ታሪካዊ ሰዎችን መዘከር፣ የምሁራን ጥናታዊ ጽሑፎችን ማቅረብ፣ የአብነት ትምህርት ቤቶችንና ገዳማትን ማስተዋወቅ እንዲሁም የኦርቶዶክሳውያን የንግድ ትስስር መድረክ መፍጠር መሆኑ ተገልጿል።

በዐውደ ርዕዩ ላይ የኢትዮጵያዊው ነባቤ መለኮት የቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ 600ኛ ዓመት መታሰቢያ ከደብረ ባሕርይ ገዳም ጋር በመተባበር የሚከበር ሲሆን የዘንድሮው የገና መባዕም ለዚሁ ገዳም እንዲውል ተወስኗል።

በመድረኩ ላይ መምህር ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ፣ ረዳት ፕሮፌሰር ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል፣ ዲያቆን ምሕረት መላኩ፣ ጆናታን ፒያዦ እና ሌሎች ታዋቂ ምሁራን በነገረ መለኮት፣ በዕቅበተ እምነትና በሥነ-ልቦና ዙሪያ ጥናታዊ ጽሑፎችን ይቀርባሉ።

የአእላፋት ዝማሬ አስመልክቶ ማህበሩ በሰጠው መግለጫ መሠረት በበዓለ ልደት ዋዜማ ታኅሣሥ 28 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ለሦስተኛ ጊዜ እንዲሁም በድሬደዋ ከተማ ለገሀር አደባባይ ለሁለተኛ ጊዜ በድምቀት እንደሚካሄድ ገልጿል።

ዘንድሮ ከአዲስ አበባ እና ከድሬዳዋ ከተማ ባሻገር ለመጀመሪያ ጊዜ በአሰላ፣ በአሶሳ፣ በሆለታ፣ በአምቦ፣ በደሴ፣ እንዲሁም በሲያትልና በኡጋንዳ የአእላፋት ዝማሬ እንዲካሄድ የልምድ ልውውጥና ዝግጅት መደረጉ ተገልጿል።


  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
❤147👍23👎15🙏8😁3🤯2🥰1
ጥንቃቄ!! ከአጭበርባሪዎች ተጠበቁ!!!

📌ማንኛውንም በስልክ የሚመጣ ጥያቄ ባለመቀበል እራሳችሁን ከአጭበርባሪዎች ጠብቁ!!!

''ባንካችን ብሔራዊ ባንክ ያወጣውን መመሪያ መሰረት በማድረግ ደንበኞቻችን በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ በመሄድ የባንክ ሒሳብ ቁጥራቸውን ከፋይዳ መታወቂያቸው ጋር እንዲያጣምሩ ያስተላለፈውን መልእክት እንደ አጋጣሚ በመጠቀም አጭበርባሪዎች ደንበኞቻችን ጋር እየደወሉ አገልግሎቱ በስልክ እንደሚሰጥ እንዲሁም የባንክ ሂሳብ በዚህ ምክንያት እንደሚዘጋ በማስመሰል ለማጭበርበር እየተጠቀሙበት እንደሚገኙ ደርሰንበታል።

በመሆኑም ክቡራን ደንበኞቻችን ሒሳብን ከፋይዳ መታወቂያ ጋር የማጣመሩ ሥራም ሆነ ሌሎች ከሞባይል ባንኪንግ ጋር የተያያዙ እና ማናቸውም አገልግሎቶች እርስዎ በአካል ወደ ቅርንጫፍ ካልሄዱ/ካልቀረቡ በስተቀር በስልክ ተደውሎ የማይሰጥ መሆኑን አውቃችሁ በስልክ ለሚመጡ ጥያቄዎች ምላሽ ባለመስጠት እራሳችሁን ከአጭበርባሪዎች እንድትጠብቁ በአክብሮት እናሳውቃለን!''

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
❤74👍30👏4😁2🤔1
አሌክሳንደር ኢሳክ ለወራት ከሜዳ እንደሚርቅ ተረጋገጠ

የሊቨርፑል የፊት መስመር ተጫዋች አሌክሳንደር ኢሳክ ለወራት ከሜዳ እንደሚርቅ ተረጋግጧል፡፡

አልክሳንደር ኢሳክ በ17ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ሊቨርፑል ቶተንሃም ሆትስፐርን ባሸነፈበት ጨዋታ ጉዳት አጋጥሞት ተቀይሮ ከሜዳ መውጣቱ ይታወቃል፡፡

ተጫዋቹ ያጋጠመውን ጉዳት ተከትሎ በትናንትናው ዕለት ቀዶ ህክምና አድርጓል፡፡

በዚህም ስዊድናዊው የፊት መስመር ተጫዋች አሌክሳንደር ኢሳክ ቢያንስ ለሁለት ወራት ከሜዳ እንደሚርቅ አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ማረጋገጣቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የ26 ዓመቱ የፊት መስመር ተጫዋች ለሊቨርፑል በሁሉም ውድድር ባደረጋቸው 16 ጨዋታዎች ሦስት ግቦች አስቆጥሮ አንድ ለግብ የሚሆን ኳስ አመቻችቶ አቀብሏል፡፡ አሌክሳንደር ኢሳክ በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ከኒውካስል ዩናይትድ በ125 ሚሊየን ፓውንድ ሊቨርፑልን መቀላቀሉ ይታወሳል፡፡

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
❤52😢6😁4🤯3👍1
የአዲስ አበባ ፖሊስ "በትውልዱ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሲያሳድር ነበረ "ያለውን ቲክቶከር ናትናኤል ባደግን አስሮ ምርመራ እያከናወነ መሆኑን ገለፀ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ከህብረተሰቡ ባህል፣ ሞራልና እሴት ተቃራኒ የሆኑ መልዕክቶችን በማህበራዊ ሚዲያ ሲያሰራጭ ነበረ በማለት ናትናኤል ባደግ (ሞን) የተባለ ቲክቶከር ዛሬ ማሰሩን ገልፇል።

ተጠርጣሪው በተለምዶአዊው ንግግር ሊገለፁ የማይችሉ አስፀያፊ ቃላትን በመጠቀም በትውልዱ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሲያሳድር እንደነበር እና መሰል ይዘቶችን በተደጋጋሚ ጊዜ በመስራት በማህበራዊ ሚዲያ (YouTube እና tiktok platform) በመጠቀም ሲያሰራጭ እንደነበር ፖሊስ አብራርቷል፡፡

ፖሊስ በቁጥጥር ስር በዋለው ናትናኤል ባደግ ወይም "የማህበራዊ ሚዲያ አንቂ ወይም ይዘት ፈጣሪ ነኝ" በሚለው ግለሰብ ላይ ምርመራ መጀመሩንም ገልፇል።


  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
❤67😁37👍22👏12
ቲክቶከሮች ግብር ሊከፍሉ ነው

📌በኦንላይን ይዘት ገቢ ላይ ግብር ሊጣል ነው

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ቲክቶክና ዩቲዩብን ጨምሮ ከሌሎች የዲጂታል ገጾች ገቢ የሚያገኙ አካላት ግብር እንዲከፍሉ የሚያስገድድ አሰራር እየዘረጋ መሆኑን አስታውቋል።

ባለፈው ዓመት በተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ መሰረት፥ በኦንላይን ይዘቶች ገቢ የሚያገኙ አካላት በሙሉ በገቢዎች ቢሮ ተመዝግበው የግብር መለያ ቁጥር የማውጣት ግዴታ ተጥሎባቸዋል።

ቢሮው ይህን ሥራ ከኢትዮ ቴሌኮም፣ ከንግድ ቢሮ እና ከፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ነው የገለጸው።

የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች ገቢያቸውን በፈቃደኝነት እንዲያሳውቁ ጥሪ ቀርቦላቸዋል መባሉን ሸገር ኤፍ ኤም ዘግቧል።

ቁጥጥሩ ከይዘት ፈጣሪዎች ባለፈም ምርትና አገልግሎት የሚያስተዋውቁ ነጋዴዎችንም ይመለከታል ነው የተባለው።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
😁56❤25👎1
#ሰበር: እስራኤል ለሶማሊላንድ የአገርነት እውቅና በይፋ መስጠቷን አስታወቀች

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ አገራቸው የሶማሊላንድ ሪፐብሊክን እንደ ነጻ እና ሉዓላዊት ሀገር በይፋ መቀበሉን አስታወቁ። ይህም በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ ትልቅ ዲፕሎማሲያዊ ለውጥ መሆኑ ተገልጿል።

ኔታንያሁ ባወጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ ዕውቅናው የተረጋገጠው ከእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ሳር እና ከሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት አብዲራህማን መሐመድ አብዱላሂ ጋር በጋራ በተፈረመ "የሁለትዮሽ ስምምነት" አማካኝነት ነው።

ጠ/ሚሩ በመግለጫቸው ቀደም ሲል በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አነሳሽነት የተፈረመውን "የአብርሃም ስምምነት" መንፈስን የተከተለ መሆኑን ገልፀዋል።

ነታንያሁ ፕሬዝዳንት አብዲራህማንን "ታሪካዊ መግለጫ" ባሉት በዚህ ስምምነት ላይ እንኳን ደስ ያለዎት ያሏቸው ሲሆን፤ ለሰላም እና ለመረጋጋት ላሳዩት ቁርጠኝነትና አመራር ምስጋና አቅርበውላቸዋል። በተጨማሪም የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት በእስራኤል ይፋዊ ጉብኝት እንዲያደርጉ ግብዣ አቅርበውላቸዋል።

እንደ ኔታንያሁ ገለጻ፣ ፕሬዝዳንት አብዲራህማን በወሰዱት እርምጃ ደስታቸውን ገልጸው፤ እስራኤል ሽብርተኝነትን በመዋጋትና ቀጣናዊ ሰላምን በማስፈን ረገድ ለምትጫወተው ሚና ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዚህ ሂደት መሳካት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ሳር፣ የሞሳድ ዳይሬክተር ዴቪድ ባርኒያ እና የእስራኤል የደህንነት ተቋማት ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና ሰጥተዋል።

ነታንያሁ እንደገለጹት፤ እስራኤል በግብርና፣ በጤና፣ በቴክኖሎጂ እና በኢኮኖሚ ዘርፎች በሚደረጉ ሰፊ ትብብሮች አማካኝነት ከሶማሊላንድ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማስፋፋት አቅዳለች።
❤88👍26😁7😢5
ኢትዮ ቴሌኮም ላለፉት ስድስት ዓመታት ሲያከናውን የቆየውን ተከታታይ የታሪፍ ቅናሽ እና የመሠረተ ልማት ማስፋፊያ ተከትሎ፣ አሁን ላይ ያለውን የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታ ከግምት ውስጥ ያስገባ መጠነኛ የታሪፍ ማስተካከያ ማድረጉን አስታወቀ።

ኩባንያው ማስተካከያውን ያደረገው የሥራ ማስኬጃ ወጪዎች መጨመርን ተከትሎ የአገልግሎቱን ቀጣይነት ለማረጋገጥ መሆኑን ገልጿል።

ኩባንያው ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው፣ ባለፉት ስድስት ዓመታት የደንበኞችን የመግዛት አቅም ያገናዘቡ ቅናሾችን በማድረጉ የደንበኞቹን ቁጥር ከ86 ሚሊዮን በላይ ማድረስ ችሏል። በተመሳሳይ የቴሌብር ተጠቃሚዎች ቁጥር ከ56 ሚሊዮን ማለፉን የገለጸው ኩባንያው፤ ይህም ለሀገሪቱ 'ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025' ስትራቴጂ ስኬት ትልቅ ሚና መጫወቱን አብራርቷል።

የታሪፍ ማስተካከያው የተደረገባቸውን ምክንያቶች የገለጸው ኢትዮ ቴሌኮም፤ እየታዩ ያሉ የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታዎች እንዲሁም የካፒታልና የሥራ ማስኬጃ ወጪዎች መጨመር ዋነኞቹ መሆናቸውን ጠቁሟል።

ይሁን እንጂ ማስተካከያው ሲደረግ የማህበረሰቡን የተለያዩ ክፍሎች ተጠቃሚነት ከግምት ውስጥ ያስገቡ ልዩ ድጋፎች መካተታቸውን ኩባንያው አስታውቋል። ከነዚህም መካከል:- ደንበኞች በቴሌብር ጥቅል ሲገዙ ያገኙት የነበረው የ10% ቅናሽ ወደ 20% ከፍ እንዲል ተደርጓል።

ይሁን እንጂ በርካታ ደንበኞች የሚጠቀሙባቸው 38 የተለያዩ ጥቅሎች ላይ ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ አልተደረገም ብሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በኢትዮጵያ የቴሌኮም ዘርፍ ውስጥ ሁለተኛው ግዙፍ ኦፕሬተር በመሆን በከፍተኛ ፍጥነት እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ፣ በዳታ (ኢንተርኔት) ጥቅል አገልግሎቶቹ ላይ ከቀናት በፊት እስከ 82 በመቶ የሚደርስ የዋጋ ማሻሻያ ማድረጉ ይታወቃል።

  T.me/ethio_mereja
     ኢትዮ-መረጃ
❤59😁14😱4👍1😢1
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለዘመናት ተግባራዊ ሲያደርግ የቆየውንና በሕግ ተወስኖ የነበረውን የ7 በመቶ ዝቅተኛ የቁጠባ ወለድ (Minimum Deposit Saving Rate) በማንሳት፣ ከዚህ በኋላ የወለድ መጠን በገበያ ፍላጎትና አቅርቦት እንዲወሰን መወሰኑን አስታወቀ።

​ባንኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ያስላለፈው ይህ ታሪካዊ ውሳኔ፣ ከሐምሌ 2016 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እየተደረገ ያለውን በወለድ ላይ የተመሰረተ የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍ ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ ያለመ ነው።

እንደ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፓሊሲ ኮሚቴ መረጃ ከሆነ፤ ቀደም ሲል መንግስት ዝቅተኛውን የወለድ መጠን ወስኖ አስቀማጮች በከፍተኛው መጠን ላይ ብቻ እንዲደራደሩ የሚያደርገው አሰራር ተቀይሮ፣ አሁን ግን የወለድ ተመኑ በአስቀማጮች እና በባንኮች መካከል በሚደረግ ነፃ ድርድርና ስምምነት እንዲወሰን በባንኩ ቦርድ ጸድቋል።

​የዚህ ፖሊሲ ዋና ዓላማ በኢኮኖሚው ውስጥ የሚዘዋወረውን የገንዘብ መጠን በወለድ በኩል በመቆጣጠር የዋጋ ንረትን ለማረጋጋትና የባንኮችን የውድድር መንፈስ በማሳደግ ቁጠባን ለማበረታታት መሆኑ ተጠቁሟል።

ብሔራዊ ባንክ አክሎም፣ ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲው በዋጋ መረጋጋት ላይ ችግር እንደሚገጥመው በተረዳ ጊዜ ያሉትን የፖሊሲ መሣሪያዎች ሁሉ እንደሚጠቀም አስታውቋል።

የገንዘብ ፖሊሲው አሁን ላይ ከማላላት ይልቅ ይበልጥ ጥብቅ ያደረገዉ ኮሚቴዉ ባንኮች በብሔራዊ ባንክ ዘንድ እንዲያስቀምጡ የሚገደዱት ወርሃዊ አማካይ የመጠባበቂያ ክምችት ምጣኔ ከነበረበት በሁለት በመቶ በማደግ ወደ 10 በመቶ እንዲያድግ ተወስኗል። ዕለታዊ ዝቅተኛው የመጠባበቂያ ክምችት ግን በነበረበት 5 በመቶ እንዲቀጥል ተደርጓል። (ዘገባው የካፒታል ነው።)

  T.me/ethio_mereja
     ኢትዮ-መረጃ
❤50😱3👍1🤯1
በማይናማር አስቸጋሪ ሁኔታ ዉስጥ የነበሩ 1 ሺህ 300 የሚሆኑ ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት መመለሱን ዉጪጉዳይ ሚኒስቴር ተናገረ

በተለያዩ ሀገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ዉስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ዜጎችን ወደ ሀገር ለመመለስ እየተሰራ ቢገኝም አስቸጋሪ ሁኔታ እንዳለ እያወቁ የስራ እድል አለ በሚል የሚሄዱ ዜጎች እያጋጠሙት መሆኑን ዉጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።

ሆኖም በህጋዊ መንገድም ሄደዉ ችግር የሚያጋጥማቸው ኢትዮጵያውያንን መብት ለማስጠበቅ ቆንስላ እና ኤምባሲ ትኩረት ሰጥተዉ እንዲከታተሉ ቋሚ የስራ መመሪያ ተሰጥቷል ተብሏል።

የኢትዮጵያዉያኑ ክብር እና መብት ተጠብቆ እንዲቆዩ ከሚሲዮን መሪዎች በተጨማሪ ይህንን ጉዳይ ብቻ እንዲከታተሉ ዲኘሎማቶች መመደባቸዉን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ ተናግረዋል።

ከማይናማር በተጨማሪ በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታዉ ነበሩ የተባሉ 26 ሺህ ዜጎችን በአምስት ወራት ዉስጥ ማስመለሱን ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

ለስራ የተጓዙ ኢትዮጵያዉያን ከአንድ የስራ ቦታ ወደ ሌላ የስራ ቦታ ለመለወጥ ወይም ወደ ሀገር ለመመለስ እንዲሁም የካሳ ክፍያ እንዲያገኙ እንዲሁም ከደሞዝ ጋር የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት ጥረት እየተደረገ ነዉ ተብሏል።

በጅዳ፣ ሪያድ ፣አቡዳቢ፣ዱባይ እንዲሁም በኩዌት ቆንስላ ፅ/ቤት ይህንን ለማድረግ እየተሰራ ነዉ ብለዋል።

ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ያልሄዱ እና ኢትዮጵያ የሁለትዮሽ የስራ ስምምነት ያላደረገችበት የስራ ጉዞ ያደረጉ ዜጎች ለዘርፈ ብዙ ጥቃት የተዳረጉ መሆናቸዉ ተገልጿል።

የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ ዛሬ በእንደራሴዎች ምክር ቤት ተገኝተው ከአባላት ለቀረበላቸው ጥያቄ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
❤55👍6👏5👎1🥰1😱1😢1
"የተከለከለው ለአንድ ጊዜ ጥቅም ላይ የሚውሉ ፕላስቲኮችን መጠቀምና ማምረት ነው"

- የአዲስ አበባከተማ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን

ለአንድ ጊዜ ጥቅም ላይ የሚውሉ ፕላስቲኮችን መጠቀምና ማምረት የሚከለክለው አዋጅን ከጥር 23 ጀምሮ በተሟላ ሁኔታ ተግባራዊ ለማድረግ በቂ ዝግጅት ማድረጉን የአዲስ አበባከተማ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አስታውቋል::

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ አዋጅ ቁጥር 1383/2017 ለአንድ ጊዜ ጥቅም ላይ የሚውሉ ፕላስቲኮች በሰዎችና በእንስሳት ህይወት ላይ እያስከተሉ ያሉትን አስከፊ ጉዳት የማስቆም አላማ አለው።

የባለስልጣኑ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ሙሉቀን ዮናስ በተለይ ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ኤፍ ኤም 96.3 ራዲዮ እንደተናገሩት፣ አዋጁ በ2017 ከመውጣቱ 1 ዓመት ቀደም ብሎ በፌደራል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጭምር ከአምራቾችና ከማህበረሰቡ ጋር ሰፊ ውይይት ሲደረግ መቆየቱን አስታውሰዋል ።

ውይይቶችና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን ተከትሎ በወጣው አዋጅ መሰረትም ለእምራቾች ከ6 ወር በላይ በቂ የምርት ሽግግር ማድረጊያ ጊዜ መሰጠቱን አመልክተዋል ።

የተሰጠውን የሽግግር ጊዜ ተጠቅመውም ብዙዎቹ አምራች ድርጅቶች የምርት ሽግግር ማድረጋቸውን ለማረጋገጥ መቻሉንም ነው ኃላፊው ያስረዱት።

ክልከላ የተጣለው በጣም ስስ የሆኑና ለአንድ ጊዜ ጥቅም ላይ የሚውሉ የእቃ መያዣ ፕላስቲኮች ላይ ብቻ መሆኑን ያስረዱት አቶ ሙሉቀን፣ ክልከላው በአካባቢና በዜጎች ህይወት ላይ እያስከተለ ካለው ጉዳት አንጻር ሊታይ እንደሚገባም እስገንዝበዋል።

የፕላስቲክ መያዣውን የሚተኩና ዳግም አገልግሎት ላይ የሚውሉ የወረቀት፣ የጨርቅና መሰል የእቃ መያዣዎች በበቂ ሁኔታ ወደ ገበያ መቅረባቸውንም ኃላፊው አመላክተዋል ፡፡

  T.me/ethio_mereja
     ኢትዮ-መረጃ
❤75👍7👏1
ማንቸስተር ዩናይትድ ዋና አሰልጣኙን ሩበን አሞሪምን ማሰናበቱ ተረጋገጠ።

ፖርቹጋላዊው በህዳር 2024 የቀያይ ሰይጣናቱ ዋና አሰልጣኝ ሆነው የተሾሙ ሲሆን፥በግንቦት ወር በስፔን ቢልባኦ በተካሄደው የዩሮፓ ሊግ ፍጻሜ ቡድኑን መምራታቸው ይታወሳል ።

ማንቸስተር ዩናይትድ በአሁኑ ወቅት በፕሪምየር ሊጉ 6ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን፥የክለቡ አመራሮች ለውጥ ለማድረግ ትክክለኛው ጊዜ አሁን ነው የሚል ውሳኔ ላይ ደርሰዋል።

ይህ ውሳኔ ደግሞ ቡድኑ በሊጉ የተሻለ ውጤት እንዲያመጣ ዕድል እንደሚሰጠውም ታምኖበታል። ስለዚህ እሳቸውን ማሰናበት ተመራጭ ሆኗል።

ክለቡ ሩበን አሞሪ ለቡድኑ ላበረከቱት አስተዋጽዖ ምስጋናውን እያቀረበ፣ ለወደፊት ህይወታቸውም መልካሙን ሁሉ እንደሚመኝላቸው በመግለጫው አስታውቋል። ቀያይ ሰይጣናቱ የፊታችን ረቡዕ ወደ ተርፍሙር አምርተው ከበርንሌይ ጋር ምሽት 5:15 የሚያደርጉትን ጨዋታ የቀድሞ ኮከባቸው ዳረን ፍሌቸር ቡድኑን በጊዜያዊነት የሚመራ ይሆናል።

  T.me/ethio_mereja
     ኢትዮ-መረጃ
❤62