ETHIO-MEREJA®
110K subscribers
25.9K photos
486 videos
22 files
12.9K links
News & Media Company®

USA : Washington

Addisababa, Ethiopia🇪🇹
.
Buy ads: https://telega.io/c/ethio_mereja
.
ለጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት
ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ!!
👉 @ethio_merejabot
Download Telegram
የመስቀል ደመራ በዓል አከባበር ሥነ ሥርዓት በጅማ ከተማ በምስል
36👍1
ባልሰሩት ወንጀል 38 ዓመታት የታሰሩት ግለሰብ የ25 ሚሊዮን ዶላር የካሳ ክፍያ አገኙ!!!

በካሊፎርኒያ የሚኖሩት የ72 ዓመቱ አዛውንት ሞሪስ ሄይስቲንግዝ ባልሰሩት ወንጀል የዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸው 38 ዓመታትን በእስር አሳልፈዋል።

ድፍን ሶስት 10 ዓመታትን ከተሻገረው የእስር ቆይታቸው በኋላ ነፃ ወጥተዋል የተባሉት ግለሰቡ የ25 ሚሊዮን ዶላር ካሳ ክፍያ አግኝተዋል።

እ.አ.አ በ1983 ሮቤርታ ዋይደርሚየር በተሰኘች ግለሰብ ላይ በተፈፀመ ጥቃት እና የግድያ ወንጀል ለእስር የተዳረጉት ሄይስቲንግዝ ፤ ለዓመታት የዲኤንኤ ምርመራ እንዲደረግላቸው ቢጠይቁም ጥያቄው ውድቅ ተደርጎባቸው ቆይቷል። በመጨረሻ በተደረጉ የዲኤንኤ ምርመራዎች ወንጀሉን እርሳቸው ሳይሆኑ ሌላ ግለሰብ እንደፈፀመው ታውቋል።

ሄይስቲንግዝ በሰጡት መግለጫ "ከእኔ የተሰረቁትን 38 የሕይወቴን ዓመታት ምንም አይነት ገንዘብ ሊመልስልኝ ባይችልም ፤ ይህ ውሳኔ በመጨረሻ የረዥም ጊዜ ትግል ማብቂያ ሆኗልና ወደፊት ለመራመድ ዝግጁ ነኝ" ብለዋል።

    T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
113👍24👏13🥰1🤯1
#ቴምርፕሮፐርቲስ

⩩ 100% ለሚከፍሉ ከ30% እስከ 35% የሚደርስ ታላቅ እውነተኛ ቅናሽ አዘጋጅተናል።
⩩ እንዲሁም 40% ለሚከፍሉ፣ ከከፈሉት ላይ የ20% ቅናሽ አዘጋጅተናል።

📍 ሊሴ ገ/ማርያም
👉 66 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 7,590,000
                 ቅድመ ክፍያ = 10% (759,000)
👉 71 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 8,165,000
                 ቅድመ ክፍያ = 10% (816,500)
👉 132 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 14,520,000
                   ቅድመ ክፍያ 10% (1,452,000)
👉 146 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 16,060,000
                   ቅድመ ክፍያ = 10% (1,606,000)

📍ሐይሌ ጋርመንት
ባለ 3 መኝታ
👉 139ካሬ ሙሉ ክፍያ = 14,590,000
                  ቅድመ ክፍያ = 10% (1,459,000)

📍 አያት (ፈረስ ቤት)
👉 88 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 8,360,000
                 ቅድመ ክፍያ = 10% (836,000)
👉 108 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 10,260,000
                   ቅድመ ክፍያ = 10% (1,026,000)
👉 137 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 15,070,000
                   ቅድመ ክፍያ = 10% (1,50,000)

⩩ ቀሪውን 90%፤ በግንባታ ሂደት፤ ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት።

ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን!
+251964439488
+251907232222

Telegram: https://t.me/OusmanTemer
WhatsApp: https://wa.me/251964439488
13👍1😱1
በነዳጅ ምርቶች ላይ አጠቃላይ የ30 በመቶ ግብር በተያዘው በጀት ዓመት ተግባራዊ መደረግ ይጀምራሉ ተባለ

የገንዘብ ሚኒስቴር ከ2018 የበጀት ዓመት ጀምሮ በነዳጅ ምርቶች ላይ አጠቃላይ 30 በመቶ ግብር ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንደሚያደርግ ማረጋገጡ ተሰማ። ይህ አዲስ ግብር 15 በመቶ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) እና 15 በመቶ የኤክሳይዝ ቀረጥን የሚያካትት መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ይህ እርምጃ በአገሪቱ የፋይናንስ ፖሊሲ ላይ ከፍተኛ ለውጥ የሚያመጣ መሆኑና የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ አንዱ አካል እንደሆነ ተመላክቷል።

​ሚኒስትሩ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ባቀረቡት አጠቃላይ የዜጎች በጀት ዉስጥ፣ በተያዘው በጀት ዓመት ተግባራዊ የሚደረጉ የግብር አይነቶችን በዝርዝር አስቀምጠዋል።

​በዚህ መሰረት፣ ከነዳጅ ላይ ከሚጣለው አጠቃላይ 30% የኤክሳይዝ ታክስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ በተጨማሪ፣ የንብረት ታክስ ይገኙበታል። እንዲሁም አማራጭ አነስተኛ ታክስ እና የቅድመ ግብር ክፍያ በተመሳሳይ መልኩ በ2018 በጀት ዓመት ተግባራዊ ለማድረግ መታቀዱን ካፒታል ጋዜጣ ለመረዳት ችሏል።

​ነዳጅ በማዕከላዊነት የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ፣ የግብር ጭማሪው የዋጋ ግሽበቱ እንዲባባስ ያደርጋል የሚል ስጋት ሲከሰት እንደነበር ይታወሳል።(ካፒታል ጋዜጣ)
33😱21👎8👏3🥰2🤯2👍1
የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አባል ነኝ በማለት ሰዎችን በማስፈራራት እያገተ ገንዘብ ሲቀበል የነበረን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ።

ዳዊት ጥላሁን ወይም ምንተስኖት ጥላሁን የተባለው ግለሰብ ሀሰተኛ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት መታወቂያ በመጠቀም የተቋሙ ሰራተኛ ነኝ በማለት ሰዎችን በማገትና በማስፈራራት ገንዘብ እንደሚቀበል ከህብረተሰቡ የመጣን ጥቆማ መነሻ በማድረግ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ በጥምረት ባደረጉት ክትትል ግለሰቡን መስከረም 16 ቀን 2018 ዓ/ም በቁጥጥር እንዲውል አድርገዋል።

ተጠርጣሪው ከሜክሲኮ ወደ ጋርመንት በታክሲ ተሳፍራ የምትሄድን የግል ተበዳይን ሳሮን ተስፋዬን ደህንነት ነኝ በማለት በማስፈራራት እና በመደብደብ ጉዳት ያደረሰባት መሆኑን የግል ተበዳይ በማህበራዊ ሚዲያ ማሰራጨቷ ይታወቃል። ግለሰቡ በግል ተበዳይ ላይ ባደረሰው ጉዳት በህግ የሚጠየቅ መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል።

ግለሰቡ በቁጥጥር ስር በዋለበት ወቅት ሀሰተኛ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት መታወቂያ እንደተገኘበት ፖሊስ አስታውቋል።

በግለሰቡ በተመሳሳይ የወንጀል ድርጊት የተፈጸመበት ግለሰብ እና ስለ ግለሰቡ ማንኛውም መረጃ ያለው ሰው ለአዲስ ለአበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ መረጃ በመስጠት ትብብር እንዲያደረግ እና የጸጥታ አካላትና አባል ነን በማለት የሚያስፈራሩና ተጽዕኖ የሚያሳደሩ ግለሰቦች ሲያጋጥሙት በወቅቱ ለፖሊስ እንዲያሳውቅ መልዕክት ተላልፏል።

    T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
55👍12😁6👏2🤯1
የግሸን ደብረ ከርቤ ዓመታዊ በዓል በድምቀት ይከበራል

የግሸን ደብረ ከርቤ ዓመታዊ በዓል በነገው ዕለት በድምቀት ይከበራል።

ዓመታዊ ክብረ በዓሉ መስከረም 21 በዞኑ አምባሰል ወረዳ ግሸን ተራራ ላይ በደመቀ መልኩ የሚከበር ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች እና ጎብኚዎች ወደ ቦታው እየገቡ ነው።

በዓሉ እንደወትሮው ሁሉ ዘንድሮም በደመቀ ሁኔታ እንዲከበር አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር አስታውቋል።

የአካባቢው ማህበረሰብ የኖረ የእንግዳ ተቀባይነቱን ለማሳየት የዞኑ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የሚመራቸው የተለያዩ ኮሚቴዎች ተዋቅረው ወደ ስራ ገብተዋል። በዋናነት በዓሉ በሰላም እንዲከበር የጸጥታ ኮሚቴ ተዋቅሮ ሲሰራ የቆየ ሲሆን የመከላከያ ሰራዊትና የክልሉ የጸጥታ ተቋማት በጋራ በመሆን ስራዎችን እየሰሩ ይገኛሉ።

    T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
63👍14🙏10😢2🥰1
#ቴምርፕሮፐርቲስ

⩩ 100% ለሚከፍሉ ከ30% እስከ 35% የሚደርስ ታላቅ እውነተኛ ቅናሽ አዘጋጅተናል።
⩩ እንዲሁም 40% ለሚከፍሉ፣ ከከፈሉት ላይ የ20% ቅናሽ አዘጋጅተናል።

📍 ሊሴ ገ/ማርያም
👉 66 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 7,590,000
                 ቅድመ ክፍያ = 10% (759,000)
👉 71 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 8,165,000
                 ቅድመ ክፍያ = 10% (816,500)
👉 132 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 14,520,000
                   ቅድመ ክፍያ 10% (1,452,000)
👉 146 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 16,060,000
                   ቅድመ ክፍያ = 10% (1,606,000)

📍ሐይሌ ጋርመንት
ባለ 3 መኝታ
👉 139ካሬ ሙሉ ክፍያ = 14,590,000
                  ቅድመ ክፍያ = 10% (1,459,000)

📍 አያት (ፈረስ ቤት)
👉 88 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 8,360,000
                 ቅድመ ክፍያ = 10% (836,000)
👉 108 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 10,260,000
                   ቅድመ ክፍያ = 10% (1,026,000)
👉 137 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 15,070,000
                   ቅድመ ክፍያ = 10% (1,50,000)

⩩ ቀሪውን 90%፤ በግንባታ ሂደት፤ ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት።

ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን!
+251964439488
+251907232222

Telegram: https://t.me/OusmanTemer
WhatsApp: https://wa.me/251964439488
15
የገንዘብ ሚኒስቴር ለሩብ ዓመቱ የ243 ቢሊዮን ብር የግምጃ ቤት ሰነዶች ጨረታ መርሃ ግብር ይፋ አደረገ

የገንዘብ ሚኒስቴር እ.ኤ.አ በ2025 የመጨረሻ ሩብ ዓመት የሚካሄደውን ጠንካራ የግምጃ ቤት ሰነዶች (T-Bills) የጨረታ መርሃ ግብር ይፋ ማድረጉን አስታውቋል።

ከመስከረም 21 እስከ ታኅሣሥ 15 ቀን 2018 ዓ.ም. የሚካሄደው ይህ የሶስት ወራት መርሃ ግብር በአጠቃላይ 243.05 ቢሊዮን ብር የሚገመት የዕዳ ሰነድ ለሀገር ውስጥ ባለሀብቶች የሚያቀርብ ሲሆን። መንግሥት የሀገር ውስጥ የዕዳ ገበያን ለማጥለቅና ግልጽነትን ለማሳደግ በያዘው ቀጣይነት ባለው የፋይናንስ ማሻሻያ አጀንዳ ውስጥ ቁልፍ እርምጃ መሆኑ ተመላክቷል።

በተለይም ይህ የዕዳ ሰነድ አቅርቦት በየሁለት ሳምንቱ የሚካሄድ ሲሆን፣ ለባንኮች፣ ለኢንሹራንስ ኩባንያዎች፣ ለጡረታ ፈንድ እና ለሌሎች ተቋማት የተረጋጋ የኢንቨስትመንት ዕድልን ይፈጥራል።

ባለሀብቶች በአራት የተለያዩ የጊዜ ገደቦች ማለትም 28 ቀናት፣ 91 ቀናት፣ 182 ቀናትና 364 ቀናት ላይ መጫረት የሚችሉ ሲሆን፣ ይህም የኢንቨስትመንት ፖርትፎሊዮአቸውን በተለያየ መልኩ እንዲያስተዳድሩ ያስችላቸዋል ሲል ካፒታል ዘግቧል ።

    T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
37
የተሻሻለው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት…

ትምህርት ሚኒስቴር የ2017 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤትን ከ300 ወደ 297 ዝቅ አድርጓል፡፡

ሚኒስቴሩ እንደገለጸው ÷ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ ተማሪዎች ወደቀጣይ የትምህርት ደረጃ ለመዛወር 50 በመቶና ከዚያ በላይ ማምጣት እንዳለባቸው ይደነግጋል።

በዚህ መሰረትም በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና አማካይ ውጤታቸው 49 ነጥብ 50 እስከ 49 ነጥብ 99 በመቶ ያመጡ ተማሪዎች ወደ 50 በመቶ እንዲጠጋጋ መወሰኑን አመልክቷል፡፡

ውሳኔውን ተከትሎም 49 ነጥብ 5 እና በላይ አማካይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ዝቅተኛውን 50 በመቶ የማለፊያ ነጥብ እንዳሟሉ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

ስለሆነም 49 ነጥብ 5 እና በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመግባት መማር እንደሚችሉ ሚኒስቴሩ አረጋግጧል፡፡

    T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
34😁3
አሳዛኝ ዜና🕯🕯

በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ መሸጋገሪያ እንጨት ተደርምሶ የበርካታ ሰዎች ህይወት አለፈ

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አረርቲ ማርያም ለግንባታ መሸጋገሪያ የተሰራ እንጨት ተደርምሶ የበርካታ ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር አህመድ ገበየሁ እንደገለጹት፥ የመደርመስ አደጋው የደረሰው ምዕመናን በወረዳው እየተሰራ ያለውን ቤተክርስቲያን ግንባታ በመጎብኘት ላይ በነበሩበት ወቅት ነው፡፡

በአደጋው እስካሁን ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች ህይወት ማለፉንም ፖሊስ ገልጿል፡፡ኢንስፔክተር አህመድ ከ200 በላይ ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ገልጸው፥ በአረርቲ ሆስፒታል ህክምና እያገኙ ነው ብለዋል።

    T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
😢5549👎2👍1😁1
የኢትዮጵያ መንግስት በግንባታ መወጣጫ መደርመስ ምክንያት ባጋጠመዉ አደጋ በደረሰዉ ጉዳት ኀዘኑን ገልጿል፡፡

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አረርቲ ከተማ አስተዳደር በግንባታ ላይ የሚገኝ የማሪያም ቤተክርስቲያን ሕንፃን በመጎብኘት ላይ የነበሩ ሰዎች በደረሰባቸው አደጋ ተጎድተዋል፡፡

ሕይወታቸዉን ያጡ፣ ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት የደረሰባቸዉ በርካታ ሰዎች መኖራቸዉ በመሰማቱ መንግሥት የተሰማዉን ኀዘን ገልጻል፤ ለተጎጂ ቤተሰቦች መጽናናትን፤ በሕክምና ላይ ለሚገኙት በፍጥነት ማገገምን እንመኛለን ብሏል፡፡


በአረርቲ ከተማ ለሕንፃ ግንባታ የተረበረበ እንጨት በመደርመሱ እስካሁን ከ30 ሰዎች በላይ ሕይወታቸው ማለፉ ተገልጿል።

በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ በአረርቲ ከተማ አስተዳደር አረርቲ ማርያም ቤተክርስቲያን ዓመታዊ ክብረ በዓል እየተከበረ ነበር። በዓሉን አስመልክቶም ከጠዋቱ 1:45 ላይ እየተሰራ ያለው ቤተክርስቲያን እየተጎበኘ ባለበት ‎ሰዓት ለፊኒሺንግ ሥራ የተረበረበው እንጨት ተደርምሶ በርካታ ምዕመናን ላይ የሞት እና የአካል ጉዳት ደርሷል።

የዛሬ ከማለዳው 2:00 ላይ በቤተክርስቲያኑ ግንባታ የሕንፃ መወጣጫ የእንጨት ርብራብ መናድ አደጋ በርካቶች መጎዳታቸውን ተነስቷል።

እስከአሁን #30 ሠዎች ሕይወታቸው ማለፉ በሆስፒታል ተረጋግጧል።

በተጨማሪ 55 ሰዎች ላይ ከመካከለኛ እስከ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱንም ገልጸዋል። ለተጎጂዎች የመጀመሪያ ሕክምና በአንድ ሆስፒታል እና በ4 ጤና ጣቢያዎች እየተሠጠ ነው ብለዋል።

#ተጎጂዎችን ለማትረፍ ኅብረተሠቡ ጥረት ማድረጉን ያነሱት ኃላፊው፤ ከርብራቡ ሥር ያልወጡትን ዜጎችም ሕይወት ለማትረፍ እና ሕክምና እንዲያገኙ ለማድረግ እየሠራን ነው ብለዋል።

    T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
64😭34
#ቴምርፕሮፐርቲስ

⩩ 100% ለሚከፍሉ ከ30% እስከ 35% የሚደርስ ታላቅ እውነተኛ ቅናሽ አዘጋጅተናል።
⩩ እንዲሁም 40% ለሚከፍሉ፣ ከከፈሉት ላይ የ20% ቅናሽ አዘጋጅተናል።

📍 ሊሴ ገ/ማርያም
👉 66 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 7,590,000
                 ቅድመ ክፍያ = 10% (759,000)
👉 71 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 8,165,000
                 ቅድመ ክፍያ = 10% (816,500)
👉 132 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 14,520,000
                   ቅድመ ክፍያ 10% (1,452,000)
👉 146 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 16,060,000
                   ቅድመ ክፍያ = 10% (1,606,000)

📍ሐይሌ ጋርመንት
ባለ 3 መኝታ
👉 139ካሬ ሙሉ ክፍያ = 14,590,000
                  ቅድመ ክፍያ = 10% (1,459,000)

📍 አያት (ፈረስ ቤት)
👉 88 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 8,360,000
                 ቅድመ ክፍያ = 10% (836,000)
👉 108 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 10,260,000
                   ቅድመ ክፍያ = 10% (1,026,000)
👉 137 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 15,070,000
                   ቅድመ ክፍያ = 10% (1,50,000)

⩩ ቀሪውን 90%፤ በግንባታ ሂደት፤ ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት።

ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን!
+251964439488
+251907232222

Telegram: https://t.me/OusmanTemer
WhatsApp: https://wa.me/251964439488
16
" ባንዲራ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ ፤ ተቋማት ዝግ ሆነው እንዲውሉ ተወስኗል ! "

መስከረም 21 በአረርቲ ከተማ አስተዳደር በአርርቲ ደብር ገነት ቅድስት ደንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን በደረሰው አደጋ ምክንያት በአረርቲ ከተማ አስተዳደርና በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ የሐዘን ቀን ታውጇል።

በአረርቲ ከተማ አስተዳደር ም/ቤት እና የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አስተዳደር ም/ቤት ለአንድ ቀን ባንዲራ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ እና ተቋማት ዝግ ሆነው እንዲውሉ ተወስኗል።

ህክምና ላይ የሚገኙ ረጅ የሌላቸዉ ታካሚዎችን ሁሉም ሰው በማገዝ  ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።

    T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
43😢16👍3😁3