ETHIO-MEREJA®
110K subscribers
25.9K photos
486 videos
22 files
12.9K links
News & Media Company®

USA : Washington

Addisababa, Ethiopia🇪🇹
.
Buy ads: https://telega.io/c/ethio_mereja
.
ለጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት
ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ!!
👉 @ethio_merejabot
Download Telegram
ታላቁ_የኢትዮጵያ_ህዳሴ_ግድብ ፕሮጀክት በይፋ ተመረቀ

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዛሬ ጳጉሜን 4 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ ተመርቋል።

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)፣ የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ፣ የጂቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦመር ጊሌህ እና የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት ተገኝተዋል።

በተጨማሪም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ሀላፊዎች በምረቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተገኝተዋል፡፡

መጋቢት 24/2003 ዓ.ም የተጀመረው የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ግንባታ 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ የሚይዝ ሲሆን 5,150 ሜጋ ዋት ሃይል የማመንጨት አቅም አለው።



      T.me/ethio_mereja
           ኢትዮ-መረጃ
107👍12🤔8🥰4👏3👎2😱1
🌼እንኳን አደረሳችሁ🌼

ውድ የኢትዮመረጃ ቤተሰቦች በቅድሚያ እንኳን ለ2018 አዲስ አመት በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ ለማለት እንወዳለን።

አዲሱአመት
🌻ብሩህ ተስፋ የምንሰንቅበት፣
🌻መልካም ነገሮችን የምናገኝበት፣
🌻ሀገራችን ሰላሟ ተጠብቆ በሰላም እና በፍቅር ወተን የምንገባበት፣ መለያየት ጠቦ ወደ አንድነት የምንመለስበት፣ የተቸገሩ የምንረዳበት፣ ሀዘን ላይ ያሉ የሚፅናኑበት መልካም መልካሙን የምንሰማበት አመት እንዲሆን እንመኛለን።

🌼መልካም አዲስ አመት🌼

T.me/ethio_mereja
29🥰11🙏3👏2👍1
Play | Enjoy | Win. Betting Tips. Free Spins. Aviator Rain. Join the Free Channel
9👎4
ኳታር ላይ ጥቃት እንዲፈጸም ያዘዙት ኔታኒያሁ ናቸዉ አሜሪካ ጣልቃ ለመግባት ጊዜ አልነበራትም ሲሉ ትራምፕ ገለጹ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እስራኤል ኳታርን እንድታጠቃ የተደረገው ውሳኔ ሙሉ በሙሉ በእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የተሰጠ ነው ሲሉ አስተዳደራቸው ጥቃቱን ለመከላከል በቂ ጊዜ እንዳልነበረዉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል አካውንታቸው ላይ ባወጡት መግለጫ፤ በእስራኤል ኳታር በሚገኝ የሃማስ ተደራዳሪዎች ልዑክ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት አዉግዘዋል፡፡

እሳቸውም ኳታር ሉዓላዊት ሀገር እና የአሜሪካ የቅርብ ወዳጅ ስትሆን ከእኛ ጋር ሰላም ለመፍጠር በትጋት እና በድፍረት እየሰራች ባለችበት ወቅት ያለ ማስጠንቀቂያ ቦምብ መጣል ለእስራኤልም ሆነ ለአሜሪካ ዓላማ አይጠቅምም ብለዋል።

ትራምፕ አክለውም ይህ ውሳኔ የተደረሰዉ በጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ እንጂ በእኔ የተደረገ ውሳኔ አይደለም ብለዋል፡፡

አስተዳደራቸው ጥቃቱ ከመፈጸሙ ጥቂት ቀደም ብሎ በአሜሪካ ጦር በኩል እንደደረሳቸዉ የጠቆሙት ትራምፕ፤ ልዩ መልዕክተኛቸውን ስቲቭ ዊትኮፍን የሚመጣውን ጥቃት ለኳታሮች እንዲያሳውቁ እንዳዘዙ ገልፀዉ በሚያሳዝን ሁኔታ ለማስቆም በጣም ዘግይቶ ነበር ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ መንግሥት ስለ ጥቃቱ አስቀድሞ መረጃ ነበረው የሚለው አባባል ፍጹም ውሸት ነው ብለዋል።

ከአንድ የአሜሪካ ባለሥልጣን የተቀበልነዉ ጥሪ የመጣው በእስራኤል ጥቃት በዶሃ ከተከሰቱት ፍንዳታዎች ድምፅ በኋላ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሼክ መሐመድ ቢን አብዱልራህማን አል ታኒ እንደተናገሩት፤ ከዩናይትድ ስቴትስ የተደረገው ጥሪ ጥቃቱ ከጀመረ ከአሥር ደቂቃ በኋላ የመጣ ሲሆን፤ ክስተቱንም የመንግሥት ሽብርተኝነት ነዉ ሲሉ ገልጸውታል።

ትራምፕ በኋላም ስለ ጥቃቱ በጣም አዝኛለሁ ብለው እንደተናገሩ እና ዳግም እንደማይከሰት ለኳታር ማረጋገጫ እንደሰጡ ተናግረዋል ሲል የዘገበዉ አልጀዚራ ነዉ።
98👍15😁15👎2🥰1🤯1😢1
ETHIO SPARK LAPTOP STORE

ETHIO SPARK LAPTOP STORE ፈጣን እና ዘመናዊ  የሆኑ የዓለምችንን ምርጥ
🖥  አዳዲስ  ላፕቶፖች
🖥  ጌሚንግ  ላፕቶፖች
🖥  ቢዝነስ  ላፕቶፖች
🖥  ዱባይ ዩዝድ ላፕቶፖች እና
🖥  የተለየዩ የላፕቶፕ  አክሰሰሪዎችን ከ አንድ አመት ዋስትና ጋር እንዲሁም  ከልዩ  የአዲስ ዓመት የበዓል ቅናሽ ጋር  እርሶን ይንጠብቃልን

 ይደውሉ 👇

☎️+251974967884

የፁሁፍ መልዕክት 👇👇

💌    @Dm4ethio

📍 Location: 📌 Addis Ababa, Megenagn

Telegram link: https://t.me/EthioSpark16

You tube link:https://www.youtube.com/@EthioSpark0

Instagram link: https://www.instagram.com/ethiopark16/

Facebook :https://www.facebook.com/share/177eogKin1/

Tiktok link: tiktok.com/@ethiospark

🌐 Website:www.ethiospark16.com
37👎1😱1
የጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ 4ኛ መፅሐፍ የሆነው "የመደመር መንግሥት" በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬሽን ማዕከል ተመረቀ

"የመደመር መንግሥት ዋነኛ ግቡ ኢትዮጵያን ለኢትዮጵያውያን ማስረከብ ነው" ተብሏል፡፡

መጽሐፉ በሦስት ዋና ዋና ክፍሎች፣ በ418 ገጾችና በ13 ምዕራፎች የተቀነበበ ነው፡፡

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ ባቀረቡት የመጽሐፍ ዳሰሳ፤ “ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመጽሐፋቸው እንደ አገር እንዴት ኋላ ቀረን የሚለውን ጉዳይ ፈትሸው፣ ህዝባችንን እንዴት ወደ ሁለንተናዊ ብልጽግና እናድርሰው የሚለውን መፍትሄ አስቀምጠዋል።” ብለዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ጌታቸው ረዳ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና መምህር ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ እና ሌላው የፍልስፍና ምሁር ዘሪሁን ተሾመ በመጽሐፉ ዙሪያ ያላቸውን ምልከታ ለታዳምያን አካፍለዋል።

በምረቃ ሥነ ስርዓቱ ላይ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ፣ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀስላሴና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የኪነጥበብና የሚዲያ ባለሙያዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
75😁61👎34👏6👍4🤔1
በአዲስ አበባ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአንድ ሰው ህይወት አለፈ

የመንገድ ትራፊክ አደጋው የደረሠው መስከረም 7 ቀን 2018 ዓ/ም ከንጋቱ 12:10 ሠዓት በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው አፍንጮ በር አካባቢ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታዉቋል፡፡

የጉዞ አቅጣጫውን ከሽሮ ሜዳ ወደ አፍንጮ በር ያደረገው የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 1-12770 አ/አ ሚኒባስ ታክሲ አፍንጮ በር አካባቢ እየተሠራ ከሚገኘው በግምት 30 ሜትር ከሚሆን የወንዝ ዳር ልማት ፕሮጀክት ውስጥ በመግባት ለጊዜው ዕድሜዋ 22 ዓመት አካባቢ የምትሆን ወጣት ህይወት ያለፈ ሲሆን ሌሎች ተጎጂዎች ለህክምና ርዳታ ወደ የካቲት አስራ ሁለትና አቤት ሆስፒታል ተወስደዋል፡፡

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ እንደሚገኝ እና ዝርዝር መረጃዎችን በቀጣይ የሚሠጥ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በላከዉ መረጃ አስታዉቋል፡፡

      T.me/ethio_mereja
           ኢትዮ-መረጃ
45😱11😢8👏2
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት #እስራኤል በጋዛ ላይ ያተካሄደችው ጦርነት “የዘር ማጥፋት ተግባር” መሆኑን ገለፀ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባካሄደው ምርመራ እስራኤል በጋዛ ላይ ያካሄደችው ጦርነት “የዘር ማጥፋት ተግባር” መሆኑን ማረጋገጡን ገለጸ።

በተያዘው የፍልስጤም ግዛት የተመድ ገለልተኛ ዓለም አቀፍ የምርመራ ኮሚሽን ሊቀመንበር የሆኑት ናቪ ፒላይ የተመድ የምርመራ ውጤትን ማክሰኞ ዕለት ለአልጀዚራ አስታውቀዋል።

ከዜና አውታሩ ጋር ባደረጉት ቆይታ ፒላይ፤ “ ፕሬዚዳንት አይዛክ ሄርዞግ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና የቀድሞ የመከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት በሰጡት መግለጫዎቻቸው እና ትዕዛዞች ላይ ተመስርተን ለይተናል” ብለዋል።

አክለውም፣ “እነዚህ ሶስት ግለሰቦች የመንግስት ተወካዮች በመሆናቸው፣ በህጉ መሰረት መንግስት ተጠያቂ ይሆናል። ስለዚህ የዘር ማጥፋት ወንጀሉን የፈጸመው የእስራኤል መንግስት ነው እንላለን” ብለዋል።

በሪፖርቱ መሠረት ኮሚሽኑ የእስራኤል ባለሥልጣናት ከሰጡት መግለጫ በተጨማሪ የዘር ማጥፋት ዓላማ እንዳላቸው ለመደምደሚያ ያደረሰ "ማስረጃዎች" መኖራቸውን ገልጿል ሲል አልጀዚራ ዘግቧል።

"ኮሚሽኑ የእስራኤል ባለሥልጣናት እና የእስራኤል የፀጥታ ኃይሎች በጋዛ ሰርጥ ውስጥ ያሉትን ፍልስጤማውያንን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ለማጥፋት የዘር ማጥፋት ዓላማ አላቸው" ሲል ሪፖርቱ አመልክቷል። ይሁን እንጂ የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የምርመራውን ውጤት "ሀሰት" ሲሉ በኤክስ ገጹ ላይ በመግለጸ፤ የሪፖርቱ ጸሃፊዎች "ለሃማስ የሚወግኑ" እንደሆኑ ገልጿል።
78👎25👍13🤔3🤯3
ETHIO SPARK LAPTOP STORE

ETHIO SPARK LAPTOP STORE ፈጣን እና ዘመናዊ  የሆኑ የዓለምችንን ምርጥ
🖥  አዳዲስ  ላፕቶፖች
🖥  ጌሚንግ  ላፕቶፖች
🖥  ቢዝነስ  ላፕቶፖች
🖥  ዱባይ ዩዝድ ላፕቶፖች እና
🖥  የተለየዩ የላፕቶፕ  አክሰሰሪዎችን ከ አንድ አመት ዋስትና ጋር እንዲሁም  ከልዩ  የአዲስ ዓመት የበዓል ቅናሽ ጋር  እርሶን ይንጠብቃልን

 ይደውሉ 👇

☎️+251974967884

የፁሁፍ መልዕክት 👇👇

💌    @Dm4ethio

📍 Location: 📌 Addis Ababa, Megenagn

Telegram link: https://t.me/EthioSpark16

You tube link:https://www.youtube.com/@EthioSpark0

Instagram link: https://www.instagram.com/ethiopark16/

Facebook :https://www.facebook.com/share/177eogKin1/

Tiktok link: tiktok.com/@ethiospark

🌐 Website:www.ethiospark16.com
25
እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) የብሔራዊ ባንክ ገዥ ሆነው ተሾሙ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከመስከረም 9 ቀን ጀምሮ ለሁለት አመራሮች ሹመት ሰጥተዋል።

በዚህም

1ኛ. ዶ/ር እዮብ ተካልኝ - የብሔራዊ ባንክ ገዥ
2ኛ. ወ/ሮ እናታለም መለስ - በሚኒስትር ማዕረግ የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሃላፊ አድርገው ሾመዋል።

      T.me/ethio_mereja
           ኢትዮ-መረጃ
70👎12😁1
በመላ ሀገሪቱ ወጥ የሆነ የትራንስፖርት ታሪፍ ተግባራዊ ሊደረግ ነው

ክልሎችንና የከተማ አስተዳደሮችን ጨምሮ በመላ ሀገሪቱ ወጥ የሆነ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ታሪፍ ተግባራዊ ሊደረግ መሆኑን የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ለአሐዱ አስታውቋል።

ተሽከርካሪዎች ከአንዱ ክልል ወደሌላኛው ክልል ሲንቀሳቀሱ የተለያየ ታሪፍ እንደሚጠቀሙ በሚኒሰቴሩ የትራንስፖርት አገልግሎትና ቁጥጥር ዘርፍ አማካሪ አቶ አሰፋ ሀዲስ ለአሐዱ ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ እና ሸገር ከተማ እንኳን የነበረው ታሪፍ ተመሳሳይ እንዳልነበረ የገለጹም ሲሆን፤ ለአብነትም ከመገናኛ ወደ ጣፎ ሲሄድና ከጣፎ ወደ መገናኛ ሲመጣ ይለያይ እንደነበር አንስተዋል።

የታሪፍ ወጥነት አለመኖር የአስተዳደር ጉዳዮችን ጨምሮ በርካታ ችግሮችን ያስከትል እንደነበር የተናገሩት አማካሪው፤ በመላ ሀገሪቱ ወጥ የሆነ ታሪፍ እንዲኖር ለማድረግ ሲሰራበት መቆየቱን ገልጸዋል።

በዚህም መሠረት ከክልሎች ጋር ውይይት በማድረግ ቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መጀመራቸውን አስረድተዋል።

አጠቃላይ ታሪፉ ከነዳጅ በተጨማሪ የተሽከርካሪው ደህንነት፣ የሹፌርና የረዳት ደመወዝ እንዲሁም፤ የገበያ ሁኔታውን በተመለከተ ጥናት እንደተካሄደበት የገለጹም ሲሆን፤ ታሪፍ የሚወጣው ይህ ሁሉ ግምት ውስጥ ገብቶ ነው ብለዋል።

በዚህም መሠረት በቅርብ ጊዜ ውስጥ ተግባራዊ እንደሚደረግ ለአሐዱ አስታውቀዋል።

አማካሪው አክለውም የታሪፍ ክፍያው በተለይም በበዓላት ወቅት እንደሚጨምሩ አንስተው፤ በቀጣይ የሚከበሩ የመስቀል እና ኢሬቻ በአላትን አስመልክቶ ከተቀመጠው በላይ የታሪፍ ክፍያ እንዳይኖር ለማድረግ እንደሚሰራበት አስታውቀዋል።


      T.me/ethio_mereja
           ኢትዮ-መረጃ
91👍3👏3👎2😱1
ላሚን ያማል የኮፓ ሽልማትን አሸነፈ

የኮፓ ሽልማት ለምርጥ ወጣት ተጫዋች የሚሰጥ ሲሆን፤ የዘንድሮውን ያሸንፋል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው ላሚን ያማል ሽልማቱን ከራፋኤል ቫራን ተቀብሏል።

በሴቶች ዘርፍ ደግሞ ቪኪ ሎፔዝ አሸናፊ ሆናለች። ሁለቱም ሽልማቶች የባርሴሎና ወጣት ተጫዋቾች እጅ ገብቷል።

"ባርሳን አመሰግናለሁ" — "ለሽልማቱ ሁላችሁንም አመሰግናለሁ፤ እዚህ መገኘት ኩራት ይሰማኛል። ባርሳንም አመሰግናለሁ። ለትልቁ ሽልማት ዝግጁ ነኝ ወይ? አላውቅም" ሲል ስፔናዊው ተጫዋች በሳቅ ተናግሯል።
20👏20👎6😁1
ኦስማን ዴምቤሌ የባሎን ዶር አሸናፊ ሆኗል
*******

ኦስማን ዴምቤሌ የ2025ቱ የወንዶች የባሎን ዶር አሸናፊ ሆኗል፡፡

በዓለም የእግር ኳስ ሽልማት ከፍተኛው እንደሆነ የሚነገርለት የባሎን ዶር የሽልማት ሥነ ሥርዓት በፈረንሳይ መዲና ፓሪስ ተካሂዷል።

በዚህም ፈረንሳዊው የአጥቂ መስመር ተጫዋች ኦስማን ዴምቤሌ የ2025 ባሎንዶር ሽልማት አሸናፊ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡


      T.me/ethio_mereja
           ኢትዮ-መረጃ
👍5747👎1🥰1🤯1
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለሙያዎችን እያስኮበለሉ ላስቸገሩት ሀገራት 1000 ቴክኒሽያኖችን አሠልጥኖ ሊሰጥ ነው

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለሙያዎችን እያስኮበለሉ ላስቸገሩት ሀገራት ወደ 1000 የሚሆኑ ቴክኒሽያኖችን አሠልጥኖ ሊሰጥ መሆኑን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው፤ የአየር መንገዱን ቴክኒሽያኖች በጣም ብዙ ገንዘብ እየከፈሉ የሚወስዱ አየር መንገዶች እንዳሉ ጠቅሰው፤ የቴክኒሽያኖቹ መኮብለል በአየር መንገዱ ላይ ፈተና ፈጥሯል ብለዋል።

በተለይ የመካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቴክኒሽያኖችን በገንዘብ እያስኮበለሉ ነው ሲሉ በኢፕድ ከምትዘጋጀው ዘመን ኢኮኖሚ ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል፡፡

አቶ ማስፍን የቴክኒሽያኖችን ኩብለላ ለማስቀረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፤ እያስኮበለሉ ከሚወስዷቸው ሀገራት አየር መንገዶች ጋር ንግግር መጀመሩን ተናግረዋል። በዚህም አስኮብላዮቹ የሚፈልጉትን ያህል ቴክኒሽያን አሰልጥነን እንሰጣለን ብለዋል፡፡

በተለይም ለመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት አየር መንገዶች ወደ 1000 የሚሆኑ ባለሙያዎችን አስተምሮ ለመስጠት ዝግጅት መደረጉን አብራርተዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ አየር መንገዱ ከሁለት ሺህ 500 በላይ ቴክኒሽያኖች እንዳሉትም አያይዘው ገልጸዋል፡፡


      T.me/ethio_mereja
           ኢትዮ-መረጃ
64😁52🙏4🤔2
Favspot ስቱዲዮ
የስራ ቦታ ለጀማሪዎች፣ ፈጣሪዎች እና ተማሪዎች፣ ለተለያዩ አላማ ቦታ ለሚያስፈልጋቸው አዘጋጅተናል።

💄 ለሜካፕ አርቲስቶች፣ የሂና ዲዛይነሮች።
📚 ለማጥናት እና ለማተኮር ጸጥ ያለ ቦታ ለሚፈልጉ ተማሪዎች እና አንባቢዎች።
🎨ስዕል ለመሳል
📕በግሩፕ ለማንበብ
⚡️ለስብሰባ
⚡️ከጓደኞቻችሁ ጋር ኘሮግራም ለማክበር
🛋️ ለማሰብ፣ ለማቀድ ወይም ለማረፍ
ሰላማዊ ቦታ ለሚፈልግ ማንኛውም ሰው።

ቀድመው ቦታ ያሲዙ ። በሰዓት 700 birr ( ለ አንድ ወር የሚቆይ )

ተጨማሪ :
⚡️ ሪንግ ላይት (Ring light)
⚡️ Microphone
⚡️ ስናክ

ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ :
@Fav_Spot_Eth
14😱2
ETHIO SPARK LAPTOP STORE

ETHIO SPARK LAPTOP STORE ፈጣን እና ዘመናዊ  የሆኑ የዓለምችንን ምርጥ
🖥  አዳዲስ  ላፕቶፖች
🖥  ጌሚንግ  ላፕቶፖች
🖥  ቢዝነስ  ላፕቶፖች
🖥  ዱባይ ዩዝድ ላፕቶፖች እና
🖥  የተለየዩ የላፕቶፕ  አክሰሰሪዎችን ከ አንድ አመት ዋስትና ጋር እንዲሁም  ከልዩ  የአዲስ ዓመት የበዓል ቅናሽ ጋር  እርሶን ይንጠብቃልን

 ይደውሉ 👇

☎️+251974967884

የፁሁፍ መልዕክት 👇👇

💌    @Dm4ethio

📍 Location: 📌 Addis Ababa, Megenagn

Telegram link: https://t.me/EthioSpark16

You tube link:https://www.youtube.com/@EthioSpark0

Instagram link: https://www.instagram.com/ethiopark16/

Facebook :https://www.facebook.com/share/177eogKin1/

Tiktok link: tiktok.com/@ethiospark

🌐 Website:www.ethiospark16.com
5
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሸገር ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጋዜጠኞች በዋስትና እንዲለቀቁ የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ አፀና

የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት፤ በሽብርተኝነት ወንጀል ተጠርጥረው ከሁለት ሳምንት በላይ በእስር ላይ የሚገኙት የሸገር ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጋዜጠኞች በ50 ሺህ ብር ዋስትና እንዲለቀቁ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት የሰጠውን ውሳኔ አፀና።

የሸገር ኤፍ ኤም ሬዲዮ አርታኢ ትዕግስት ዘሪሁን እና ሪፖርተር ምንታምር ፀጋው በዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ፣ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት በሰጠው ውሳኔ ላይ የፌዴራሉ ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ጋዜጠኞቹ ከእስር ቢለቀቁ ማስረጃ ሊያጠፉ ይችላሉ በሚል የጠየቀው ይግባኝ  ውድቅ ተደርጎበታል።

የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት ተጠርጣሪዎቹ ከእስር ቢለቀቁ ማስረጃ ያጠፉብኛል፣ የሚለውን የፖሊስ ማመልከቻ ባለመቀበል የዋስ መብታቸው እንዲከበር ዛሬ በዋለው መወስኖ መዝገቡን መዝጋቱን ሸገር ሬድዮ አስታውቋል።


      T.me/ethio_mereja
           ኢትዮ-መረጃ
38👍4