ETHIO-MEREJA®
110K subscribers
25.9K photos
486 videos
22 files
12.9K links
News & Media Company®

USA : Washington

Addisababa, Ethiopia🇪🇹
.
Buy ads: https://telega.io/c/ethio_mereja
.
ለጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት
ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ!!
👉 @ethio_merejabot
Download Telegram
ዛሬ ምሽት በደስታ ርችት የደመቀው
የሕዳሴ ግድብ የምረቃ ዋዜማ - (በምሥል)
93🥰18👏6👍1
ታላቁ_የኢትዮጵያ_ህዳሴ_ግድብ ፕሮጀክት በይፋ ተመረቀ

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዛሬ ጳጉሜን 4 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ ተመርቋል።

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)፣ የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ፣ የጂቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦመር ጊሌህ እና የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት ተገኝተዋል።

በተጨማሪም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ሀላፊዎች በምረቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተገኝተዋል፡፡

መጋቢት 24/2003 ዓ.ም የተጀመረው የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ግንባታ 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ የሚይዝ ሲሆን 5,150 ሜጋ ዋት ሃይል የማመንጨት አቅም አለው።



      T.me/ethio_mereja
           ኢትዮ-መረጃ
107👍12🤔8🥰4👏3👎2😱1
🌼እንኳን አደረሳችሁ🌼

ውድ የኢትዮመረጃ ቤተሰቦች በቅድሚያ እንኳን ለ2018 አዲስ አመት በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ ለማለት እንወዳለን።

አዲሱአመት
🌻ብሩህ ተስፋ የምንሰንቅበት፣
🌻መልካም ነገሮችን የምናገኝበት፣
🌻ሀገራችን ሰላሟ ተጠብቆ በሰላም እና በፍቅር ወተን የምንገባበት፣ መለያየት ጠቦ ወደ አንድነት የምንመለስበት፣ የተቸገሩ የምንረዳበት፣ ሀዘን ላይ ያሉ የሚፅናኑበት መልካም መልካሙን የምንሰማበት አመት እንዲሆን እንመኛለን።

🌼መልካም አዲስ አመት🌼

T.me/ethio_mereja
29🥰11🙏3👏2👍1
Play | Enjoy | Win. Betting Tips. Free Spins. Aviator Rain. Join the Free Channel
9👎4
ኳታር ላይ ጥቃት እንዲፈጸም ያዘዙት ኔታኒያሁ ናቸዉ አሜሪካ ጣልቃ ለመግባት ጊዜ አልነበራትም ሲሉ ትራምፕ ገለጹ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እስራኤል ኳታርን እንድታጠቃ የተደረገው ውሳኔ ሙሉ በሙሉ በእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የተሰጠ ነው ሲሉ አስተዳደራቸው ጥቃቱን ለመከላከል በቂ ጊዜ እንዳልነበረዉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል አካውንታቸው ላይ ባወጡት መግለጫ፤ በእስራኤል ኳታር በሚገኝ የሃማስ ተደራዳሪዎች ልዑክ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት አዉግዘዋል፡፡

እሳቸውም ኳታር ሉዓላዊት ሀገር እና የአሜሪካ የቅርብ ወዳጅ ስትሆን ከእኛ ጋር ሰላም ለመፍጠር በትጋት እና በድፍረት እየሰራች ባለችበት ወቅት ያለ ማስጠንቀቂያ ቦምብ መጣል ለእስራኤልም ሆነ ለአሜሪካ ዓላማ አይጠቅምም ብለዋል።

ትራምፕ አክለውም ይህ ውሳኔ የተደረሰዉ በጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ እንጂ በእኔ የተደረገ ውሳኔ አይደለም ብለዋል፡፡

አስተዳደራቸው ጥቃቱ ከመፈጸሙ ጥቂት ቀደም ብሎ በአሜሪካ ጦር በኩል እንደደረሳቸዉ የጠቆሙት ትራምፕ፤ ልዩ መልዕክተኛቸውን ስቲቭ ዊትኮፍን የሚመጣውን ጥቃት ለኳታሮች እንዲያሳውቁ እንዳዘዙ ገልፀዉ በሚያሳዝን ሁኔታ ለማስቆም በጣም ዘግይቶ ነበር ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ መንግሥት ስለ ጥቃቱ አስቀድሞ መረጃ ነበረው የሚለው አባባል ፍጹም ውሸት ነው ብለዋል።

ከአንድ የአሜሪካ ባለሥልጣን የተቀበልነዉ ጥሪ የመጣው በእስራኤል ጥቃት በዶሃ ከተከሰቱት ፍንዳታዎች ድምፅ በኋላ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሼክ መሐመድ ቢን አብዱልራህማን አል ታኒ እንደተናገሩት፤ ከዩናይትድ ስቴትስ የተደረገው ጥሪ ጥቃቱ ከጀመረ ከአሥር ደቂቃ በኋላ የመጣ ሲሆን፤ ክስተቱንም የመንግሥት ሽብርተኝነት ነዉ ሲሉ ገልጸውታል።

ትራምፕ በኋላም ስለ ጥቃቱ በጣም አዝኛለሁ ብለው እንደተናገሩ እና ዳግም እንደማይከሰት ለኳታር ማረጋገጫ እንደሰጡ ተናግረዋል ሲል የዘገበዉ አልጀዚራ ነዉ።
98👍15😁15👎2🥰1🤯1😢1
ETHIO SPARK LAPTOP STORE

ETHIO SPARK LAPTOP STORE ፈጣን እና ዘመናዊ  የሆኑ የዓለምችንን ምርጥ
🖥  አዳዲስ  ላፕቶፖች
🖥  ጌሚንግ  ላፕቶፖች
🖥  ቢዝነስ  ላፕቶፖች
🖥  ዱባይ ዩዝድ ላፕቶፖች እና
🖥  የተለየዩ የላፕቶፕ  አክሰሰሪዎችን ከ አንድ አመት ዋስትና ጋር እንዲሁም  ከልዩ  የአዲስ ዓመት የበዓል ቅናሽ ጋር  እርሶን ይንጠብቃልን

 ይደውሉ 👇

☎️+251974967884

የፁሁፍ መልዕክት 👇👇

💌    @Dm4ethio

📍 Location: 📌 Addis Ababa, Megenagn

Telegram link: https://t.me/EthioSpark16

You tube link:https://www.youtube.com/@EthioSpark0

Instagram link: https://www.instagram.com/ethiopark16/

Facebook :https://www.facebook.com/share/177eogKin1/

Tiktok link: tiktok.com/@ethiospark

🌐 Website:www.ethiospark16.com
37👎1😱1
የጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ 4ኛ መፅሐፍ የሆነው "የመደመር መንግሥት" በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬሽን ማዕከል ተመረቀ

"የመደመር መንግሥት ዋነኛ ግቡ ኢትዮጵያን ለኢትዮጵያውያን ማስረከብ ነው" ተብሏል፡፡

መጽሐፉ በሦስት ዋና ዋና ክፍሎች፣ በ418 ገጾችና በ13 ምዕራፎች የተቀነበበ ነው፡፡

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ ባቀረቡት የመጽሐፍ ዳሰሳ፤ “ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመጽሐፋቸው እንደ አገር እንዴት ኋላ ቀረን የሚለውን ጉዳይ ፈትሸው፣ ህዝባችንን እንዴት ወደ ሁለንተናዊ ብልጽግና እናድርሰው የሚለውን መፍትሄ አስቀምጠዋል።” ብለዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ጌታቸው ረዳ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና መምህር ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ እና ሌላው የፍልስፍና ምሁር ዘሪሁን ተሾመ በመጽሐፉ ዙሪያ ያላቸውን ምልከታ ለታዳምያን አካፍለዋል።

በምረቃ ሥነ ስርዓቱ ላይ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ፣ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀስላሴና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የኪነጥበብና የሚዲያ ባለሙያዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
75😁61👎34👏6👍4🤔1
በአዲስ አበባ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአንድ ሰው ህይወት አለፈ

የመንገድ ትራፊክ አደጋው የደረሠው መስከረም 7 ቀን 2018 ዓ/ም ከንጋቱ 12:10 ሠዓት በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው አፍንጮ በር አካባቢ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታዉቋል፡፡

የጉዞ አቅጣጫውን ከሽሮ ሜዳ ወደ አፍንጮ በር ያደረገው የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 1-12770 አ/አ ሚኒባስ ታክሲ አፍንጮ በር አካባቢ እየተሠራ ከሚገኘው በግምት 30 ሜትር ከሚሆን የወንዝ ዳር ልማት ፕሮጀክት ውስጥ በመግባት ለጊዜው ዕድሜዋ 22 ዓመት አካባቢ የምትሆን ወጣት ህይወት ያለፈ ሲሆን ሌሎች ተጎጂዎች ለህክምና ርዳታ ወደ የካቲት አስራ ሁለትና አቤት ሆስፒታል ተወስደዋል፡፡

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ እንደሚገኝ እና ዝርዝር መረጃዎችን በቀጣይ የሚሠጥ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በላከዉ መረጃ አስታዉቋል፡፡

      T.me/ethio_mereja
           ኢትዮ-መረጃ
45😱11😢8👏2
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት #እስራኤል በጋዛ ላይ ያተካሄደችው ጦርነት “የዘር ማጥፋት ተግባር” መሆኑን ገለፀ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባካሄደው ምርመራ እስራኤል በጋዛ ላይ ያካሄደችው ጦርነት “የዘር ማጥፋት ተግባር” መሆኑን ማረጋገጡን ገለጸ።

በተያዘው የፍልስጤም ግዛት የተመድ ገለልተኛ ዓለም አቀፍ የምርመራ ኮሚሽን ሊቀመንበር የሆኑት ናቪ ፒላይ የተመድ የምርመራ ውጤትን ማክሰኞ ዕለት ለአልጀዚራ አስታውቀዋል።

ከዜና አውታሩ ጋር ባደረጉት ቆይታ ፒላይ፤ “ ፕሬዚዳንት አይዛክ ሄርዞግ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና የቀድሞ የመከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት በሰጡት መግለጫዎቻቸው እና ትዕዛዞች ላይ ተመስርተን ለይተናል” ብለዋል።

አክለውም፣ “እነዚህ ሶስት ግለሰቦች የመንግስት ተወካዮች በመሆናቸው፣ በህጉ መሰረት መንግስት ተጠያቂ ይሆናል። ስለዚህ የዘር ማጥፋት ወንጀሉን የፈጸመው የእስራኤል መንግስት ነው እንላለን” ብለዋል።

በሪፖርቱ መሠረት ኮሚሽኑ የእስራኤል ባለሥልጣናት ከሰጡት መግለጫ በተጨማሪ የዘር ማጥፋት ዓላማ እንዳላቸው ለመደምደሚያ ያደረሰ "ማስረጃዎች" መኖራቸውን ገልጿል ሲል አልጀዚራ ዘግቧል።

"ኮሚሽኑ የእስራኤል ባለሥልጣናት እና የእስራኤል የፀጥታ ኃይሎች በጋዛ ሰርጥ ውስጥ ያሉትን ፍልስጤማውያንን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ለማጥፋት የዘር ማጥፋት ዓላማ አላቸው" ሲል ሪፖርቱ አመልክቷል። ይሁን እንጂ የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የምርመራውን ውጤት "ሀሰት" ሲሉ በኤክስ ገጹ ላይ በመግለጸ፤ የሪፖርቱ ጸሃፊዎች "ለሃማስ የሚወግኑ" እንደሆኑ ገልጿል።
78👎25👍13🤔3🤯3
ETHIO SPARK LAPTOP STORE

ETHIO SPARK LAPTOP STORE ፈጣን እና ዘመናዊ  የሆኑ የዓለምችንን ምርጥ
🖥  አዳዲስ  ላፕቶፖች
🖥  ጌሚንግ  ላፕቶፖች
🖥  ቢዝነስ  ላፕቶፖች
🖥  ዱባይ ዩዝድ ላፕቶፖች እና
🖥  የተለየዩ የላፕቶፕ  አክሰሰሪዎችን ከ አንድ አመት ዋስትና ጋር እንዲሁም  ከልዩ  የአዲስ ዓመት የበዓል ቅናሽ ጋር  እርሶን ይንጠብቃልን

 ይደውሉ 👇

☎️+251974967884

የፁሁፍ መልዕክት 👇👇

💌    @Dm4ethio

📍 Location: 📌 Addis Ababa, Megenagn

Telegram link: https://t.me/EthioSpark16

You tube link:https://www.youtube.com/@EthioSpark0

Instagram link: https://www.instagram.com/ethiopark16/

Facebook :https://www.facebook.com/share/177eogKin1/

Tiktok link: tiktok.com/@ethiospark

🌐 Website:www.ethiospark16.com
25
እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) የብሔራዊ ባንክ ገዥ ሆነው ተሾሙ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከመስከረም 9 ቀን ጀምሮ ለሁለት አመራሮች ሹመት ሰጥተዋል።

በዚህም

1ኛ. ዶ/ር እዮብ ተካልኝ - የብሔራዊ ባንክ ገዥ
2ኛ. ወ/ሮ እናታለም መለስ - በሚኒስትር ማዕረግ የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሃላፊ አድርገው ሾመዋል።

      T.me/ethio_mereja
           ኢትዮ-መረጃ
70👎12😁1