ETHIO-MEREJA®
110K subscribers
25.9K photos
486 videos
22 files
12.9K links
News & Media Company®

USA : Washington

Addisababa, Ethiopia🇪🇹
.
Buy ads: https://telega.io/c/ethio_mereja
.
ለጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት
ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ!!
👉 @ethio_merejabot
Download Telegram
Forwarded from AfroSports
🎉🎉እንኳን ደስ አላችሁ🎉🎉

አፍሮ ስፖርት ከዚህ በፊት ቃል በገባዉ መሰረት
የተለያዩ ሽልማቶችሁን ላሸናፊዎችህ ሊሸልም ጥቂት ቀን ብቻ ቀረው!🤑

🥇እጣ -- የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል 🛵

🥈እጣ --ፕለይ ስቴሽን 🎮

🥉እጣ -- 75 ኢንች ስማርት ቴሌቪዥን 🖥

4እጣ -- ላፕቶፕ 💻

5እጣ -- ስማርት ስልክ📱

6 - 10ኛ እጣ -- ዳጎስ ያለ የብር ሽልማት አዘጋጅቶላቹአል ። 💸💸

🎁🎁 COMING SOON 🎁🎁 በቅርብ ቀን 🎁🎁
28👍4🥰1😱1
ተቃዋሚው ፖለቲከኛ ልደቱ አያሌው፣ "የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ያልያዙ ፖሊሶች" ቢሸፍቱ ከተማ ከሚገኘውና ከአገር ከመውጣታቸው በፊት ለ10 ዓመት ከኖሩበት ቤት በ10 ቀናት ውስጥ እቃቸውን እንዲያወጡ የሚያስጠነቅቅ ደብዳቤ ቤቱ ላይ ለጥፈው እንደሄዱ ዛሬ ለመገናኛ ብዙኀን ባሠራጩት መረጃ አስታውቀዋል።

ደብዳቤው፣ ቤቱ "ለማኅበራዊ ፖሊስ" አገልግሎት እንደሚፈለግ የሚገልጽ መሆኑን ልደቱ ገልጸዋል። ልደቱ፣ በ10 ቀናት ውስጥ ቤቱ ውስጥ ያለውን ንብረት ካልወጣ፣ ፖሊስ ርምጃ እንደሚወስድ በደብዳቤው ላይ ማስጠንቀቁንም ጠቅሰዋል።

የማስጠንቀቂያ ትዕዛዝ የያዘውን ደብዳቤ የጻፈው፣ በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር የሆራ አርሰዴ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት እንደኾነም ልደቱ ገልጸዋል። [ዋዜማ]

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
59🤯8🤔7👎5
 🌺100 ሪሴለሮችን እንፈልጋለን።

ከቤትዎ ሆነው በነፃ በኦንላይን ከኛ ጋር ይስሩ!!!

እቃዎችን በተለያዩ የኦንላይን አማራጮች
ከኛ በኦንላይን በመሸጥ ተጨማሪ ገቢ ያግኙ፣
 
በቴሌግራም፣ በፌስቡክ፣ በማርኬትፕሌስ፣ በቲክቶክ፣
በኢንስታግራም፣ በራስዎ በማስተዋወቅ እቃዎችን መሸጥ ይችላሉ።

Contact 👉 @Addisekachat

JOIN አድርገው አብረውን መስራት ይጀምሩ!
22👎3
ደቡብ ሱዳን ፖለቲከኞች እና ጦር ያነገቡ ኃይሎች ወደብሔራዊ ምክክር እንዲመመለሱ ጥሪ አቀረበች
***

ደቡብ ሱዳን ያኮረፉ ፖለቲከኞች፣ ተፎካካሪ ፓርቲዎች እና ጦር ያነገቡ አካላት የመንግስትን ግብዣ በመቀበል ወደ ብሔራዊ ምክክር እንዲመለሱ ጥሪ አቅርባለች።

ጥሪው ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር እና በጎርጎሮሳዊው 2026 ለሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ መደላድል እንደሚሆን የሃገሪቱ ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ገልጸዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ የሕዝባቸው እልቂት እና ሰቆቃ እንዲያበቃ እ.አ.አ. በ2018 ከተደረሰው የሰላም ስምምነት ውጪ የሆኑ ኃይሎች ጦር እንዲያወርዱ ጠይቀዋል።

በተጨማሪም ጦር ካወረዱ በኋላ የደቡብ ሱዳንን ብሔራዊ ሰራዊት መቀላቀል የሚፈልጉትም እንዲቀላቀሉ ጥሪ ማቅረባቸውን የአገሪቷ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ለሰላም ጥሪው መሳካት በአገር ውስጥ እና ከአገር ውጪ ከተለያዩ ያኮረፉ ፖለቲከኞች እና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ድርድር መጀመሩን አስታውቀዋል።

በኬንያ ናይሮቢ ራሱን የተባበሩት የሕዝብ ጥምረት (United People’s Alliance - UPA) እያለ ከሚጠራው ቡድን ጋር የሰላም ድርድር መጀመሩንም ሳልቫ ኪር አስታውሰዋል።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
66👍7
Forwarded from AfroSports
💰🤑💸 በአፍሮ ስፖርት ሁሌም ማሸነፍ እንጂ ማፈር የለም! 💰🤑💸

በአፍሮ ስፖርት ቨርችዋል ጨዋታዎቻችንም ሆነ ባዘጋጀናቸው ትልልቅ ኦዶች በፈለጉት ጨዋታ በመረጡት ጊዜና ቦታ ይጫወቱ።

አሁኑኑ https://bit.ly/406HvyU ላይ ይግቡና የአሸናፊነት ጉዞውን ይቀላቀሉ።
19🤔1
🔔ዋጋ Price ➤ 49,900ብር 
ሞዴል Model  M74

🔅ለጥራቱ አያስቡ የ2 አመት ዋስትናችን በቃል አይደለም የጽሑፍ ዋስትና ነው።

🔅20 አመት በላይ አሰተማማኝ ሶፋዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ለውድ ደንበኞቻችን በማቅረብ ላይ ነን።

ሶፋ ጠረፔዛ ካላስፈለጎት ከሶፋው ዋጋ ላይ ይቀነስሎታል።

ለዋጋ መረጃና ሌሎች ምርቶቻችን የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
👇 👇 👇
t.me/AlphaFurniture

Follow Us on TikTok
👇 👇 👇
@AlphaFurnitureEthiopia
14
#ግብፅ በጋዛ እና #ኢትዮጵያ ግድብ ዙሪያ #አሜሪካ ያቀረበችው የሰጥቶ መቀበል ሀሳብ ውድቅ አደረገች

እስራኤል በጋዛ ደቡባዊ ክፍል ማቆያ ካምፕ ለመገንባት ያላትን እቅድ ግብፅ የምትደግፍ ከሆነ በምላሹ አሜሪካ በኢትዮጵያ ግድብ ውዝግብ ውስጥ ጣልቃ ለመግባት ያቀረበችውን ሀሳብ የግብፅ ባለስልጣናት ውድቅ አድረጉ።

ግብፅ በኢትዮጵያ የአባይ ግድብ ላይ ያለውን ቀውስ ለመፍታት አሜሪካ ያቀረበችውን የሰጥቶ መቀበል ሀሳብ ውድቅ አድርጋለች። ይህ ሀሳብ እስራኤል የጋዛን ህዝብ ወደ ራፋህ እንድታዘዋውር ካይሮ ድጋፍ እንድትፈቅድ የሚጠይቅ እንደሆነ ከፍተኛ የግብፅ ዲፕሎማሲ ምንጮች ለአል አረቢ አል ጃዲድ ገልጸዋል።

አንድ የግብፅ ዲፕሎማት ለዜና ምንጩ እንደተናገሩት የትራምፕ አስተዳደር አንድ ከፍተኛ የአሜሪካ ባለስልጣን በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ ያለውን ውዝግብ ለመፍታት “ቆራጥ ጣልቃ ገብነት” ብለው የጠሩትን ሀሳብ አቅርበው ነበር።

በምላሹ ግብፅ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያንን ከራፋህ ድንበር አቅራቢያ በሚገኝ ካምፕ ውስጥ ለማቆየት የእስራኤልን እቅድ መደገፍ ይኖርባታል። ዲፕሎማቱ ለአል አረቢ አል ጃዲድ እንደተናገሩት የካይሮ ባለስልጣናት እቅዱን ፍልስጤማውያንን ድንበር አቋርጠው ወደ ግብፅ እንዲገቡ የማስገደድ እርምጃ አድርገው ይመለከቱታል።
70👍14🤔2🙏2🥰1
🔔ዋጋ Price ➤ 49,900ብር 
🔅የ 2 አመት የጽሑፍ ዋስትና እና
🔅ከ 20+ አመት በላይ ልምድ

ሞዴል Model  M89

ለዋጋ መረጃና ሌሎች ምርቶቻችን የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
👇 👇 👇
t.me/AlphaFurniture

📍 አድራሻችን
🏠  በቅሎ ቤት • ግሎባል ፊት ለፊት • አልፋ ሕንፃ

Beklo Bet • Infront of Global Hotel • Alpha Building

• 0911445604
• 0979426642
• 0979420042
10
በአለልኝ አዘነ ግድያ ጥፋተኛ የተባሉ ግለሰቦች በጽኑ እስራት ተቀጡ

በቀድሞው የባህር ዳር ከተማ እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋች አለልኝ አዘነ ግድያ ጥፋተኛ የተባሉ ሁለት ግለሰቦች በ16 እና 15 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ፍርድ ቤት ወሰነ፡፡

የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ተከሳሽ የአለልኝ አዘነ ባለቤት ወ/ሮ አደይ ጌታቸው ድርጊቱን በመላ ሃሳቧና አድራጎት በወንጀሉ ድርጊትና በሚሰጠው ውጤት ሙሉ ተካፋይ በመሆን ድርጊቱን የራሷ በማድረግ እንዲሁም 2ኛ ተከሳሽ የወ/ሮ አደይ ጌታቸው እህት ባል የሆነው ሉንጎ ሉቃስ በቀጥታ ወንጀሉን በመፈፀም የተሳተፈ በመሆኑ በፈፀሙት ታስቦ በሚፈፀም ተራ የሆነ ሰው መግደል ወንጀል ተከስሰዋል፡፡

ተከሳሾቹ መጋቢት 17/ 2016 ዓ.ም ከሌሊቱ 5፡30 እስከ 8 ሰዓት ገደማ ባለው ጊዜ በአርባ ምንጭ ከተማ ነጭ ሳር ቀበሌ ልማት ሰፈር በተቀነባበረ ሁኔታ የ26 አመቱን ወጣት አለልኝ አዘነን በመግደል ራሱን ያጠፋ እንዲመስል በማድረግ የግድያ ወንጀል መፈፀማቸው በሰውና በሰነድ ማስረጃዎች በመረጋገጡ የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጥፋተኝነት ውሳኔን ማሳለፉ የሚታወስ ነው።

ፍርድ ቤቱ በቀድሞው እግር ኳስ ተጫዋች አለልኝ አዘነ ግድያ ጥፋተኛ በተባሉት 1ኛ ተከሳሽ ወ/ሮ አደይ ጌታቸው (የአለልኝ አዘነ ባለቤት) ላይ የ16 አመት እንዲሁም 2ኛ ተከሳሽ ሉንጎ ሉቃስ (የወ/ሮ አደይ ጌታቸው እህት ባል) ላይ 15 አመት ፅኑ እስራት የቅጣት ውሳኔ አስተላልፏል።


  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
62😭14🥰1
የሰሞኑን የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ንግግርን ተከትሎ ኢትዮጵያ ግድቡን በሀገር ውስጥ አቅም እየገነባች መሆኑን በዛሬው ዕለት አስታወቀች

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ከሰሞኑ በተከታታይ ሶስት ግዜ ሀገራቸው የህዳሴ ግድብን ፋይናንስ እንዳደረገች ሲናገሩ ተደምጠው ነበር።ፕሬዝደንቱ በዚህ ከግብፅ የወገነ ንግግራቸው የህዳሴ ግድብ ወደ ናይል ወንዝ የሚገባውን ውሀ እየዘጋው ነው እንዲሁም የናይል ወንዝ ለግብፅ ብቸኛው የህይወት ምንጭ ነው በማለት ተናግረዋል።

ለዚህ የፕሬዝደንቱ ምላሽ እስካሁን በሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ወይም ውጭ ጉዳይ ቢሮ የተሰጠ ምላሽ ባይኖርም የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ፅህፈት ቤት በዛሬው እለት ሚድያዎችን ጠርቶ በሰጠው መግለጫ ላይ ኢትዮጵያ ግድቡን በራሷ አቅም መገንባቷን አፅንኦት ሰጥቶ ተናግሯል።ፅህፈት ቤቱ ግድቡ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት ወጪ እንደተገነባ ያረጋገጠ ሲሆን በያዝነው አመት ብቻ ከ1.7 ቢልየን ብር በላይ ለግድቡ ማሰባሰቡን መናገሩን ካፒታል ዘግቧል።

ከግንባታው መጀመር ጀምሮ በአጠቃላይ ከ23.6 ቢሊዮን ብር በላይ ከህዝብ የተሰበሰበ ሲሆን ከ84.4 ቢሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የጉልበትና የተፋሰስ ስራዎች ተከናውነዋል ሲል ፅህፈት ቤቱ አክሏል።

የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ፅህፈት ቤት የፕሬዝደንት ትረምፕ ንግግርን በማጣጣል ግድቡ ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ሲደገፍ መቆየቱን አጽንኦት ሰጥቷል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የግድቡ ግንባታ መጠናቀቁንና በመጪው መስከረም ወር እንደሚመረቅ ገልጸው፣ ግብፅንና ሱዳንን በይፋ መጋበዛቸው ይታወሳል።
98👍12😁9🥰3
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የባንክ ሒሳብ እንዲታገድ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ አሳለፈ፣ ውሳኔው የተላለፈው የ17 ወራት ውዝፍ የመምህራን ክፍያ ጋር በተያያዘ ነው!

በትግራይ ክልል ከተካሄደው ጦርነት ጋር በተያያዘ የክልሉ መምህራን የ17 ወራት ደመወዝ እንዲከፈላቸው የመሰረቱትን ክስ የሚመለከተው የትግራይ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የጊዜያዊ አስተዳደር ባንክን ሒሳብ እንዲታገድ ውሳኔ አሳለፈ፤ ለሐምሌ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ሐምሌ 15 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት የተሰየሙት ዳኞችም ክርክሮችን ከሰሙ በኋላ በጊዜያዊ አስተዳደሩ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተከፈቱትን የባንክ ሒሳቦች እንዳይንቀሳቀሱ በማገድ ወጪ የተደረገው የገንዘቡ መጠን መቼ እንደወጣና ወደ የትኛው የባንክ ሒሳብ እንደተላለፈ ማስረጃ እንዲቀርብ ትእዛዝ አስተላልፈዋል።

የከሳሽ የመምህራን ማህበሩ ጠበቆች በእስር እንዲቀርቡልን ሲሉ የጠየቋቸው የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ እና የክልሉ የፋይናንሰ ቢሮ ሃላፊ ምሕረት በየነ (ዶ/ር) ማስረጃዎቹ ከቀረቡ በኋላ እንደሚታይ በመግለጽ የዕለቱ ዳኞች ለሐምሌ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠታቸው ተገልጿል። (Via AS)

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
50
በኢትዮጲያ ግዙፍ የአውሮፕላን ጥገና ማዕከል ተመረቀ።

የኢትዮጲያ አየር መንገድ እጅግ ዘመናዊ የአውሮፕላን ጥገና ወርክሾፕን ጨምሮ ፥ ዘመናዊ መጋዘንን አስመርቋል።

አየር መንገዱ ይህንን ዘመናዊ ልዩ ልዩ የአውሮፕላን ጥገና ማዕከላት የተካተቱበትን ግዙፍ ማእከል ከ 150 ሚሊየን ዶላር በላይ በማውጣት ማስገንባቱን የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው በምረቃው ወቅት ተናግረዋል።

በ150 ሚሊየን ዶላር ወጪ የተደረገባቸው ፕሮጀክቶች የአውሮፕላን ክፍሎች መጠገኛ፣ የአውሮፕላን ጥገና ማዕከል እና ከሰው ንከኪ ነፃ የሆነ መጋዘን ናቸው።

የጥገና ቁሳቁሶች የሚከማቹበት መጋዘኑ በ15 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ መሆኑ ተገልፃል።

የኢትዮጵያ አየር ሀይል ዋና አዛዥ እና የአየር መንገዱ የቦርድ ሰብሳቢ ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ፣ እና ሌሎች የተቋሙ እና የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ፣ዲፕሎማቶች እንዲሁም በፕሮጀክቱ የተሳተፍ አካላት በምረቃው ወቅት ተገኝተዋል።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
75😁4👍3👎1