🎉 ወደ አፍሮ ስፖርት ሲመጡ ባዶ እጃችንን አንጠብቅዎትም የእንኳን ደህና መጡ ስጦታ አዘጋጅተንልዎታል ! 🎉
ዛሬውኑ ይመዝገቡና እና 20% የመጀመሪያ ተቀማጭ ጉርሻ ይቀበሉ!
✨ በሚወዱት ስፖርት እና የተለያዩ ጨዋታዎቻችን እየተዝናኑ ይጫወቱ።💰
🔗 አሁኑኑ https://afrobetting.net ላይ ይመዝገቡ።
https://t.me/afrosportsbet

❤10
እስራኤል በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት ጀመረች።
በእስላማዊ ሪፐብሊክ ኢራን ብሮድካስቲንግ የሚተዳደረው የወጣት ጋዜጠኞች ክበብ እንዳስታወቀው፣ አሁን ላይ በደቡባዊ ኢራን ውስጥ በቡሼህር የአየር መከላከያ ዘዴዎች ነቅተው እየጠበቁ ነው።
በሌላ በኩልም የእስራኤል ጦር በደቡብ ምዕራብ ኢራን ወታደራዊ መሠረተ ልማቶችን መትቷል ሲል ገልጿል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ዩናይትድ ኪንግደም በኢራን ባለው የጸጥታ ሁኔታ በቴህራን የሚገኙ የኤምባሲ ሰራተኞቿን ልታስወጣ መሆኑን የዩኬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማስታወቁን ቢቢሲ ዘግቧል።
“ሰራተኞቻችንን በጊዜያዊነት ከኢራን ለማስወጣት የጥንቃቄ እርምጃ ወስደናል” ሲል የዩናይትድ ኪንግደም የውጭ፣ የኮመንዌልዝ እና ዴቨሎፕመንት ጽህፈት ቤት በመግለጫው አስታውቋል።ሆኖም ኤምባሲው ስራውን እንደማያቆምና “አገልግሎቱን በርቀት እንደሚሰጥ” ገልጿል።
በሳምንቱ መጀመሪያ በተመሳሳይ መልኩ በደህንንት ስጋት ምክንያት በእስራኤል የሚገኘውን ኤምባሲዋን እና የቆንስላ ሰራተኞቿን ለጊዜው እንደምታስወጣ ሲል የቢቢሲ ዘገባ አስረድቷል።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ

❤33😱4
ትራምፕ የቲክ ቶክ እገዳ ቀነ ገደብን ለሶስተኛ ጊዜ አራዘሙ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቲክ ቶክ እንዲታገድ ያስቀመጡትን የእገዳ ቀነ ገደብ ለሶስተኛ ጊዜ አራዝመዋል።
በትሩዝ የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ “የቲክ ቶክን ቀነ-ገደብ በ90 ቀናት እንዲራዘም የአስፈጻሚ ትዕዛዝ ፈርሜያለሁ" ብለዋል፡፡
የቀነ ገደቡ መራዘም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አሜሪካውያን የሚጠቀሙበትን የግንኙነት መረብ በድንገት ላለመዝጋት እና ተገቢውን አካሄድ በሚጠብቅ መንገድ ውሳኔ ለመስጠት ያለመ እንደሆነም ጠቅሰዋል፡፡
ቲክ ቶክ በለጠፈው መግለጫ ፕሬዝዳንት ትራምፕ መተግበሪያው ለ170 ሚሊዮን የአሜሪካ ተጠቃሚዎች እና 7.5 ሚሊዮን ለሚሆኑ ምርቶቻቸውን በቲክቶክ ላይ ለሚያስተዋውቁ አሜሪካ ነጋዴዎች እንዲደርስ እና አንዳይቋረጥ ስለረዱት አመስግነኗል ማለቱን ቢቢሲ ዘግቧል።ሁለተኛው ዙር የቲክቶክ እገዳ ቀነ ገደብ ዛሬ የሚያበቃ ሲሆን ትራምፕ ለቲክቶክ ሶስተኛ አድል መስጠታቸውን ተከትሎ አዲሱ የእገዳ ቀን እስከ ፈረንጆቹ መስከረም 17፣ 2025 ድረስ የሚቆይ ይሆናል።

❤31👎4😱1
በዳይመንድ ሊግ ዮሚፍ ቀጄልቻ እና ለሜቻ ግርማ አሸነፉ
በፓሪስ በተደረገው የ5 ሺህ ሜትር የዳይመንድ ሊግ ውድድር አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ በበላይነት አጠናቅቋል።
12 ደቂቃ 47.84 ሰከንድ ደግሞ ርቀቱን ለማጠናቀቅ የወሰደበት ሰዓት ነው። በውድድሩ ሳሙኤል ተፈራ 5ኛ ሲወጣ መዝገቡ ስሜ እና ገመቹ ዲዳ 11ኛ እና 13ኛ በመሆን ውድድርራቸውን አጠናቅቀዋል።
በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል የዳይመንድ ሊግ አካል በመሆነው ውድድር አትሌት ለሜቻ ግርማ በአንደኝት አጠናቋልቅ።
የርቀቱ የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት የሆነው ለሜቻ ግርማ 8 ደቂቃ 07.01 ሰከንድ የገባበት ሰዓት ሆኖም ተመዝግቧል።
አተሌት ጌትነት ዋለ ደግሞ 3ኛ ደረጃ ወጥቷል። 8 ደቂቃ 12.58 ጌትነት የገባበት ሰዓት ሆኗል። በርቀቱ አብርሀም ስሜ 8ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቅቋል።
በተመሳሳይ የሴቶች 3 ሺህ ሜትር መሰናክል አትሌት ሲምቦ ዓለማየው 9 ደቂቃ 01.22 በመግባ 3ኛ ወጥታለች። አትሌት ሎሚ ሙለታ ደግሞ 9ኛ በመሆን ውድድሩን ፈጽማለች።

👍14❤13
የአባይ ግድብ "እኛ ፋይናንስ አድርገን ነው የተሠራው" - ትራምፕ❗️
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢትዮጵያውን ገንዘብ የተገነባውን የሕዳሴውን ግድብ "በአሜሪካ በሞኝነት የገንዘብ ድጋፍ የተደረገለት ግዙፉ የኢትዮጵያ ግድብ" ሲሉ ገለጹት።
ፕሬዚዳንቱ ትሩዝ ሶሻል በተሰኘው ማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ አሁን በለቀቁት ጽሁፍ "አሜሪካ በሞኝነት የረዳችው የኢትዮጵያ ግድብ፣ ወደ አባይ ወንዝ የሚፈሰውን ውሃ በእጅጉ ይቀንሳል ሲሉ ጽፈዋል።
"ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋር በመሆን በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና በሩዋንዳ ሪፐብሊክ መካከል ባለው ጦርነት ላይ አስደናቂ የሆነ ስምምነት ማዘጋጀቴን ሪፖርት በማድረጌ በጣም ደስተኛ ነኝ። ይህ ጦርነት ከብዙዎቹ ጦርነቶች በበለጠ በከፋ የደም መፋሰስ እና ሞት የሚታወቅ ሲሆን ለአስርት ዓመታት የቆየ ነው።" ካሉ በኋላ "የሩዋንዳ እና የኮንጎ ተወካዮች ሰነዶችን ለመፈረም ሰኞ ዕለት ዋሽንግተን ውስጥ እንደሚገቡ ገልጸዋል። "ይህ ለአፍሪካ ታላቅ ቀን ሲሆን፣ በእውነት ለመናገር ለመላው ዓለምም ታላቅ ቀን ነው!" ሲሉ አክለዋል።
"ለዚህ የኖቤል የሰላም ሽልማት አላገኝም፣ በህንድ እና በፓኪስታን መካከል ያለውን ጦርነት በማስቆሜ የኖቤል የሰላም ሽልማት አላገኝም፣ በሰርቢያ እና በኮሶቮ መካከል ያለውን ጦርነት በማስቆሜ የኖቤል የሰላም ሽልማት አላገኝም፣ በግብፅ እና በኢትዮጵያ መካከል ሰላምን በማስፈኔ የኖቤል የሰላም ሽልማት አላገኝም" ያሉት ትራምፕ በቅንፍ ውስጥ "(በአሜሪካ በሞኝነት የገንዘብ ድጋፍ የተደረገለት ግዙፉ የኢትዮጵያ ግድብ፣ ወደ አባይ ወንዝ የሚፈሰውን ውሃ በእጅጉ ይቀንሳል)፣" ሲሉ ጽሁፋቸውን ቀጥለዋል።

😁110❤41👎14👍5🤔3👏2🤯2😱2🥰1
የኢራኑ ፕሬዚዳንት ማስጠንቀቂያ እና የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር የመከላከያ ስለላ ማዕከል ጉብኝት
****
እስራኤል በኢራን ላይ የጀመረችውን ጥቃት ካላቆመች ሀገራቸው ለፀፀት የሚዳርግ ኃይለኛ ምላሽ እንደምትሰጥ የኢራኑ ፕሬዚዳንት መስኡድ ፔዜሽኪያን አስጠንቅቀዋል።
በእስራኤልና በኢራን መካከል የተፈጠረውን ግጭት ለማስወገድ ያለው ብቸኛ መንገድ እስራኤል በኢራን ላይ የምታካሂደውን የአየር ድብደባ ማቆም ነው ሲሉ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።
ኢራን ሁሌም የምትከተለው የሰላምና የመረጋጋትን መንገድ ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ ሆኖም አሁን ባለው ሁኔታ ዘላቂ ሰላም ሊፈጠር የሚችለው እስራኤል የጦረኝነት የሽብር ቅስቀሳዋን ለማቆም ዋስትና ስትሰጥ ብቻ ነው ብለዋል።
ይህ ሳይሆን ቀርቶ እስራኤል አሁን በያዘችው መንገድ ኢራንን ማጥቃት ከቀጠለች ግን እስራኤል እንድትፀፀት የሚያደርግ ኃይለኛ ምላሽ ኢራን እንደምትሰጥ መናገራቸውን አናዶሉ የኢራንን ሚዲያ ዋቢ በማድረግ ዘግቧል።
በሌላ በኩል የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ከሀገሪቱ ከፍተኛ ወታደራዊና ደህንነት ሃላፊዎች ጋር በመሆን የእስራኤል መከላከያ ኃይል የስለላ ማዕከልን ጎብኝተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት፥ "እስራኤል በጦርነቱ አሸንፋ እንድትወጣ የሚያስችላትን ጠቃሚ የስለላ መረጃ እየሰጠን ያለው የመከላከያችን የስለላ ማዕከል" በማለት በክፍሉ እያገለገሉ ላሉ ወታደሮች አድናቆታቸውን ገልጸዋል።
ብጥቅሉ የእስራኤል መከላከያ ኃይል አባላት እስካሁን ላበረከቱት እና ወደፊትም ሀገሪቱ ድል እስክትቀዳጅ ለሚያበረክቱት አስዋጽኦ አመስግነዋል።

❤82🤯3🤔2👍1😁1😱1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🏆🎰በአፍሮ ራፍል እድልዎን ወደ ገንዘብ ለመለወጥ ይፈልጋሉ?🏆🎰
እንግዲያስ ምን ይጠብቃሉ በአፍሮ ቤት ላይ የተለያዩ ጨዋታዎችን በመጫወትና ነጥብ በመሰብሰብ የተለያዩ ሽልማቶችን ያሸንፉ!
እንዴት?
1️⃣ በሚወዱት ስፖርት ወይም ጨዋታ አፍሮ ቤት ላይ ውርርድዎን ያስቀምጡ
2️⃣ የተለያዩ ጨዋታዎችን በመጫወት ብዙ ነጥብ ይሰብስቡ
3️⃣ ብዙ ነጥብ ይዘው ተዘጋጅተው ይጠብቁ አሸናፊዎች በቅርቡ ይለያሉ!
ሽልማቶቹ የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል፣ ፕለይ ስቴሽን እንዲሁም ሰባ ሁለት ኢንች ስማርት ቲቪን ያካትታሉ! 💰🎁
እንዳያመልጥዎት! የበለጠ ሲጫወቱ የማሸነፍ እድልዎ ይሰፋል!🎉💪
አሁኑኑ https://afrobetting.net ይቀላቀሉ እና እየተዝናኑ ይጫወቱ ያሸነፉ!🎯🎊

❤21
አዲስ አበባ📍
100 ሺህ ብር ተቀጣች
በብስክሌት መንገድ ላይ በመኪና የነዳች ግለሰብ የ100,000 ብር ቅጣት ተጣለባት
አዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በለሚኩራ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 8፣ ሲኤምሲ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ በልማት ኮሪደር ውስጥ በተዘጋጀው የብስክሌት መንገድ ላይ መኪና ስታሽከረክር የተገኘች ግለሰብ ላይ የገንዘብ ቅጣት እንደጣለ አስታወቀ።
ግለሰቧ በሰላምና ጸጥታ አካላት እና በአዲስ አበባ ትራፊክ ፖሊስ ትብብር በቁጥጥር ስር ውሎ የተሽከርካሪዋ ባለቤት 100,000 ብር እንዲከፍል ተደርጓል። ባለስልጣኑ ግለሰቧ በቸልተኝነት የፈፀመችውን የትራፊክ ደንብ ጥሰት
የባለስልጣኑ ኦፊሰሮች ባደረጉት ክትትልና ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት እርምጃ መወሰዱን ገልጿል።
Via የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባ/ኮ ዳይሬክቶሬት

❤63👎56👏16👍12😁11🤯4😱4
አሜሪካ በ3 የኢራን የኒውክሌር ተቋማት ላይ ጥቃት ሰነዘረች
አሜሪካ ፎርዶውን ጨምሮ ኢራን ውስጥ በሚገኙ 3 የኒውክሌር ተቋማት ላይ ጥቃት ማድረሷን ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስታውቀዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ትራምፕ የአሜሪካ ወታደራዊ ኃይሎች በፎርዶ፣ ናታንዝ እና ኢስፋሃን በሚገኙ የኢራን የኒውክሌር ጣቢያዎች ላይ “በጣም የተሳኩ” ጥቃቶችን ማድረጋቸውን እና አሁን ሁሉም የአሜሪካ አውሮፕላኖች ከኢራን የአየር ክልል ውጭ ናቸው ሲሉ ተናግረዋል።
በጥቃቱ የዩኤስ ቢ-2 ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች ተሳትፈዋል ተብሏል፡፡
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትሩዝ የማህበራዊ ትስሰር ገፃቸው ባስተለለፉት መልዕከት “የቴህራን የኒውክሌር መርሃግብር ዘውድ” የሆነው ፎርዶው ጠፍቷል ሲሉ ገልፀዋል።
ሮይተርስ እንደዘገበው ኢራን በፎርዶው የኒውክሌር ጣቢያ ጥቃት መድረሱን አረጋግጣለች።
ኢራን በእስራኤል ጥቃት ከተከፈተባት ወዲህ 400 ሰዎች መገደላቸውን እንዲሁም በትንሹ 3ሺ 56 ዜጎቿ ደግሞ መቁሰላቸውን ገልፃለች፡፡ በኢራን ጥቃት የሞቱት እስራኤላውያን 24 ናቸው፡፡

❤43👍24👎15😁6
አሜሪካ በፈፀመችው ጥቃት የኒውክሌር ብክለት አልተከሰተም - ኢራን
**
አሜሪካ ኢስፋሃን፣ ፎርዶ እና ናታንዝ በተባሉ የኢራን የኒውክሌር ማብላያ ጣቢያዎች ላይ የፈፀመችው ጥቃት የኒውክሌር ብክለት አለመከሰቱን ኢራን ገለጸች።
የኢራን ብሔራዊ ሚዲያ የሀገሪቱን ብሔራዊ የኒውክሌር ደኅንነት ሥርዓት ማዕከልን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ የጨረራ ቁጥጥር መሣሪዎች ጥቃቱ በደረሰባቸው አካባቢዎች ምንም ዓይነት የራዲዮአክቲቭ ልቀትን አልመዘገቡም።
በጣቢያዎቹ የሚገኙ የዩራንየም ንጥረ ነገሮች ከጥቃቱ ቀደም ብሎ ወደ ሌላ ቦታ በመወሰዳቸው በአካባቢው ምንም የሚፈጠር የራዲዮአክቲቭ ልቀት እንደማይኖር እየተነገረ ይገኛል።
በመሆኑም ጥቃቱ እንደተፈፀመባቸው በተጠቀሱት አካባቢዎች በሚኖሩ ሰዎች ላይ የሚደርስ አደጋ እንደማይኖር ማዕከሉ ባወጣው መግለጫ መግለጹን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል።
ቀደም ብሎም እስራኤል በኢራን የኒውክሌር ማብላያ ጣብያዎች ላይ ያደረሰችው የአየር ድብደባ በተመሳሳይ መልኩ በተቋማቱ ዙሪያ ምንም ዓይነት ራዲዮአክቲቭ ንጥረ ነገር እንዲለቀቅ አለማድረጉን ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ አስታውቆ ነበር።

❤93😁16👍3👏3😱3🤔1🤯1
🥳 ጓደኛዎችዎን ወደ አፍሮቤት ይጋብዙ እና አስደሳች ቦነስ ያግኙ!
👇 የእርስዎ ልዩ መለያዎን ለጓደኛዎ ወይም ለቅርብ ወዳጅዎ ያጋሩ ሽልማቶችን ያግኙ።
💸💰ለእያንዳንዱ አዲስ ስኬታማ ምዝገባዎች 15% ቦነስ ያገኛሉ።
🔗 አሁኑኑ ማጋራት ይጀምሩ እና ገቢዎትን ያሳድጉ!
ከ https://bit.ly/3XbY3o7 ጋር ያሸንፉ።

❤6👎1😱1
የኢራን ፓርላማ ወሳኙን የሆርሙዝ የባህር ሰርጥን ለመዝጋት የቀረበውን ሀሳብ አፀደቀ
**
የኢራን ፓርላማ የአለማችን 20 በመቶ የሚሆነው ድፍድፍ ነዳጅ የሚተላለፍበት የባህር ሰርጥን ለመዝጋት የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ አፅድቋል፡፡
ፓርላማው ውሳኔውን ያስተላለፈው አሜሪካ እስራኤልን በማገዝ በኢራን ሶስት የኒውክሌር ማብለያ ተቋማት ወታደራዊ እርምጃ መውሰዷን ተከትሎ ነው።
የፓርላማው ውሳኔ ተፈጻሚ የሚሆነው የኢራኑ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሚኒ በሚያሳልፉት የመጨረሻ ትእዛዝ መሆኑ ተነግሯል።
40 ኪሎ ሜትር ብቻ ስፋት ያለው የሆርሙዝ የባህር ሰርጥ የመዘጋት አደጋ ካጋጠመው በአለም የነዳጅ ዋጋ ላይ ትልቅ ተፅእኖ ሊፈጥር እንደሚችልም ተገልጿል፡፡
የኢራን ፓርላማ ያቀረበው ይህ ውሳኔ የኢራኑን መሪ የአያቶላህ አሊ ኻሚኒን የመጨረሻ ውሳኔ እየጠበቀ ነው ሲል ኒውስ ዊክ የኢራን ቴሌቪዥንን ጠቅሶ ዘግቧል።
የሆርሙዝ የባህር ሰርጥ ፈሳሽ ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ የጫኑ መርከቦች ዋነኛ መተላለፊ ሲሆን፤ እኤአ 2024 በየቀኑ ብቻ 20.3 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅና ፔትሮሊየም ተላልፎበታል ተብሏል።
አሜሪካ ፎርዶውን ጨምሮ ኢራን ውስጥ በሚገኙ 3 የኒውክሌር ተቋማት ላይ ጥቃት ማድረሷን ተከትሎ ኢራን በቀጣይ ምን አይነት እርምጃ ትወስዳለች የሚለው የሚጠበቅ ሆኗል።

❤67👍22😁7🤯3