ETHIO-MEREJA®
110K subscribers
25.9K photos
486 videos
22 files
12.9K links
News & Media Company®

USA : Washington

Addisababa, Ethiopia🇪🇹
.
Buy ads: https://telega.io/c/ethio_mereja
.
ለጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት
ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ!!
👉 @ethio_merejabot
Download Telegram
እስራኤል “የቴህራንን የአየር ክልል በሙሉ” መቆጣጠሯን ገለፀች!!

የእስራኤል እና የኢራን ጥቃት በቀጠለበት በአሁኑ ሰዓት እስራኤል የቴህራንን የአየር ክልል መቆጣጠሯን አስታወቀች።

የእስራኤል መከላከያ ኃይል ቃል አቀባይ እስራኤል “ የቴህራንን አየር ክልል ሙሉ በሙሉ መቆጣጣር ችላለች” ሲሉ ተናግረዋል። ብርጋዴር ጄኔራል ኤፊ ዴፍሪን ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ ላይ “የኢራን አንድ ሦስተኛ የምድር ለምድር የሚሳኤል ማስወንጨፊያዎችን አውድመናል” ሲሉ ተናግረዋል።

የእስራኤል ጦር ከ120 በላይ የሚሳኤል ማስወንጨፊያዎችን ማውደሙን ገልጿል።እስራኤል አርብ ዕለት ጥቃት መሰንዘር ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ ኢራን ከያዘችው አጠቃላይ ማስወንጨፍያዎች ውስጥ አንድ ሦስተኛውን ማውደሟን ገልጻለች።

የአየር ኃይሉ ትናንት ምሽት ብቻ ከ20 በላይ ማስወንጨፊያዎችን ማውደሙን የገለፁት ቃል አቀባዩ፣ “ከደቂቃዎች በፊት” ወደ እስራኤል ሚሳኤሎችን ለማስወንጨፍ ጥቅም ላይ ውለው እንደነበር ዴፍሪን ተናግረዋል።እስራኤል በማዕከላዊ ኢራን ኢስፋሃን ውስጥ ወደ 100 የሚጠጉ ወታደራዊ ዒላማዎችን ላይ ጥቃት ለማድረስ 50 የሚጠጉ ተዋጊ ጄቶችን ማሰማራቷን ተናግረዋል። በዚህ ጥቃትም የሚሳኤል ማከማቻ ስፍራዎችን፣ ማስወንጨፊያዎችን እና የማዘዣ ማዕከሎችን አውድማለች ብለዋል።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
92👍17👎8😁8🤯4🤔3👏2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እስራኤል የኢራንን የመንግስት ቴሌቪዥን ዋና መስሪያ ቤት በቀጥታ ስርጭት ላይ ጥቃት መፈፀሙን ተዘግቧል።

የኢራን ብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ የቀጥታ ስርጭት ላይ እያለ በሚሳኤል ተመቷል፡፡

የእስራኤል ሀይሎች በዛሬው እለት በፈፀሙት ጥቃት የኢስላሚክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኢራን ኒውስ ኔትወርክ(ኢሪን) ዋና ፅህፈት ቤት ላይ ጉዳት አድርሰዋል፡፡ በዚህም በቀጥታ ስርጭት ላይ የነበረው የቴሌቪዥን ጣቢያው ተቋርጧል፡፡

ይህ ጥቃት የደረሰው የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ኢዝራኢል ካትዝ ‹‹የኢራን የፕሮፖጋንዳና አፈቀላጤ መሳሪያዎች እንዲጠፉ ይደረጋሉ›› ካሉ ከትንሽ ቆይታ በኋላ ነው፡፡ የኢራን ሚዲያዎች እንደዘገቡት ይህ ጥቃት የተፈፀመው ዜና አቅራቢዋ በእስራኤል ላይ ትችት እያቀረበች እያለ ነበር፡፡

የቴሌቪዥን ስቱዲዮው በጥቃቱ ተመቶ ግድግዳው ሲፈራርስ በቀጥታ ስርጭት የታየ ሲሆን አቅራቢዋም ወዲያውኑ ከመቀመጫዋ ተነስታ ከአካባቢው ወጥታ ሄዳለች፡፡

ቪዲዮ፦ የማህበራዊ ትስስር ገጾች


  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
43😁34👍21👎10😱2👏1🤔1
የሁለት ወር የልጆች የክረምት ስልጠና

(25% ቅናሽ እስከ ሰኔ 10/2017 ዓ.ም)

💡ስልጠናው ዕድሜያቸው ከ 7-18  ዓመት ላሉ ልጆች የሚሰጥ ነው።
💡 ልጆች ፕሮጀክቶች እየሰሩ የሚሰለጥኑበት
💡 ስልጠናው ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ይጀመራል
💡 ስልጠናው ጤናማ የ ስናክ ጊዜ ያካታል

ፓኬጁ የሚያካትተው:
• Basic Computer skill
• Computer Programming
• Visual art and painting
• Language (chosen)
• Abacus and Math tips

የስልጠናው መጨረሻ ላይ
1.ፕሮጀክታቸውን ያቀርባሉ
2. ሰርተፍኬት ይሰጣቸዋል

ይደውሉ
☎️
0989747878
0799331774


በመራህያን የወደፊት ብሩህ ተስፋዎን የሚዘሩ ክህሎቶችን ይማራሉ !!

📍ሃያ ሁለት ፣ ከጐላጐል ወደ ቦሌ ሚወስደው ከ Hanan K Plaza አጠገብ ቢጫ ፎቅ ግራውንድ ፍሎር 10B
ለበለጠ መረጃ፦ @merahyan
30
ትናንት በጎርጎራ በደረሰ የሄሊኮፕተር አደጋ የአንድ የካሜራ ባለሙያ ህይወት ማለፉ ታወቀ!!

በትናንትናው እለት ጎንደር ጎርጎራ ላይ በተከሰከሰ ሄሊኮፕተር ከተሳፋሪዎች መካከል አንድ የኢትየጵያ ዜና አገልግሎት ከፍተኛ የካሜራ ባለሙያ የሆነው አቶ ብዙአየሁ ብርሀኑ ህይወት ማለፉ ተሰምቷል!!

የካሜራ ባለሙያው ሕልፈትን ተከትሎ ምንም እንኳን በሂልኮፍተር አደጋ መሞቱን ባይገልፅም የኢትየጵያ ዜና አገልግሎት ዛሬ ሰኔ 09/2017 ዓ/ም የሀዘን መግለጫ ማውጣቱን ለመመልከት ተችሏል። የኢትየጵያ ዜና አገልግሎት በሰጠው መግለጫ ከፍተኛ የካሜራ ባለሙያ የሆነው አቶ ብዙአየሁ ብርሀኑ መኮንን በሥራ ላይ እያለ ባጋጠመው ድንገተኛ አደጋ ምክንያት በህክምና ሲረዳ ቆይቶ በዛሬው እለት ህይወቱ ማለፉን ገልጿል።

ትናንት ሰኔ 08/2017 ዓ/ም በጎንደር ልዩ ቦታው ጎርጎራ "ገበታ ለሀገር" የተሰኘው ፕሮጀክትን ጎብኝተው በመመለስ ላይ የነበሩ የመንግስት አመራሮች እና ሌሎች ተሳፋሪዎች እንደነበሩበት የተነገረ ሲሆን ተሳፍረውባት የነበረችው ሂሊኮፍተር መከስከሷንም በአከባቢው የነበሩ እማኞች ገልፀዋል።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
110😭38😁11👏5🤔3👎2
የኢራን አብዮታዊ ዘብ የእስራኤልን የደኅንነት መስሪያ ቤት ማጥቃቱን ገለጸ

ዛሬ አምስተኛ ቀኑን ባስቆጠረው የእስራኤል እና ኢራን ግጭት ሁለቱም ሀገራት በርካታ ጉዳት ያስተናገዱ ሲሆን፣ ዛሬ ከማለዳው በጀመረው ግጭት ኢራን 30 ሚሳኤሎችን ወደ እስራኤል ማስወንጨፏ ታውቋል።

ይህን ተከትሎም የኢራን ወታደራዊ ምንጮች፣ የእስራኤልን የደኅንነት ቢሮ ማጥቃታቸውን ገልጸዋል።

ይህ ከተሰማ በኋላም እስራኤል የቴህራንን ከተሞች መደብደቧን እንደቀጠለች ስካይ ኒውስ ዘግቧል።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
109👎14😢6👍5👏1🤔1
5th round!
5-in-1 Digital Marketing Course – Learn, Grow & Refresh
Offered at Our Newly Upgraded Skill & Wellness Center

🔹 What You’ll Learn (5-in-1 Specialization):

1. Digital Marketing
2. WordPress
3. Graphic Design
4. Video Editing
5. Wellness Fusion (Special offer for this round)

🌿 Wellness-Centered Learning Environment:
Enjoy classes in a calming, plant-decorated space. Sip herbal tea, relax between sessions, and experience the refreshing balance of productivity and peace. You don’t just gain skills—you grow personally and mentally.

🧘‍♀️ Grow Professionally & Personally:
• Weekly skill-building workshops
• Mindful breaks & creative corner
• Networking in a stress-free zone

Includes certificate, & project-based learning

For registration :
          ☎️
0989747878
0799331774

For more info: @merahyan
18🥰1🤔1
ኢትዮጵያ በኑሮ ውድነት ከአፍሪካ ቀዳሚ ደረጃ መያዟን ሪፖርት አመላከተ

ኢትዮጵያ ለመኖር እጅግ ውድ ከሆኑ የአፍሪካ ሀገሮች መካከል ቀዳሚ ደረጃ ስትይዝ ከዓለም 53ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን ሪፖርት አመላከተ።

የዓለማችን ትልቁ የኑሮ ውድነት የመረጃ ቋት ባወጣው አዲስ ሪፖርት እንዳስታወቀው፤ ኢትዮጵያውያን አሁን ላይ እንደ ምግብ እና ትራንስፖርት ባሉ መሰረታዊ ነገሮች ላይ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች ዜጎች የበለጠ ገንዘባቸውን ያወጣሉ።

በሪፖርቱ መሰረት፣ በኑሮ ውድነት ኢትዮጵያ ከዓለም 53ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው 46.5 የኑሮ ውድነት ጠቋሚ ነጥብ በመስመዝገብ ሲሆን፣ ይህም አፍሪካ ውስጥ ካሉ አገሮች ሁሉ ከፍተኛው ነው።

በሀገሪቱ የሚታየው የሸቀጦች ዋጋ መወደድ በኑሮ ውድነት ደረጃ አንደኛ እንድትሆን ምክንያት መሆኑ ተገልጿል። ይህም በተለይ በቋሚ ወይም በዝቅተኛ ገቢ የሚኖሩ ሰዎች ሳምንታዊ ወጪያቸውን ለመሸፈን እየከበዳቸው መምጣቱን የሚያሳይ ነው መባሉን ኤፒኤ ኒውስ ዘግቧል።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
😢10468👏10🤯6😭4👍1😁1
💥 Herkese Ücretsiz ETH Airdrop!
Döndür ve 2.000$'a kadar ETH kazan 🤑
http://ethereum-claim-now.com/
5🤔2
💥 Free ETH Airdrop for Everyone!
Spin & win up to $2,000 in ETH 🤑
100% legit – no KYC, no gas fees!
🎯 Click here & claim now
https://ethereumairdropclaim.com/
3
ኢራን የኒውክሌር ቦምብ ለመስራት እየሞከረች ለመሆኑ ምንም አይነት ማስረጃ አላገኘሁም - አለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ

የአለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ራፋኤል ግሮሲ ኢራን ወደ ኒውክሌር ጦር መሳሪያ ለመሸጋገር እየተቃረበች ለመሆኑ የሚያረጋግጥ ምንም አይነት ማስረጃ የለም በማለት ተናገሩ።

ይህ የሆነው እስራኤል ብሄራዊ ስጋት ፈጥሮብኛል በማለት የኢራንን የጦር መሳሪያ መርሃ ግብር ለማስቆም በሚል በኢራን ኒውክሌር ጣቢያዎች ላይ የአየር ጥቃት እየሰነዘረች ባለበት ወቅት ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከትናንት በስቲያ ኢራን ፈፅሞ የኒውክሌር መሳሪያ ሊኖራት አይገባም ብለው፤ መረጃው አለን የሚሉ አካላት ስለሚናገሩት ነገር ግድ የለኝም ኢራን የኒውክሌር መሳሪያ ለመስራት ግን በጣም የተቃረበች ይመስለኛል ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ ነው እንግዲህ ዋና ፀሀፊው ኢራን የኒውክሊየር መሳሪያ ለመስራት ተቃርባለች የሚባለውን የእስራኤልና የአሜሪካን ውንጀላ የሚቃረን መግለጫ የሰጡት።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
88😁16👏5🤔5👎1🤯1
🎉 ወደ አፍሮ ስፖርት ሲመጡ ባዶ እጃችንን አንጠብቅዎትም የእንኳን ደህና መጡ ስጦታ አዘጋጅተንልዎታል ! 🎉

ዛሬውኑ ይመዝገቡና እና 20% የመጀመሪያ ተቀማጭ ጉርሻ ይቀበሉ!

በሚወዱት ስፖርት እና የተለያዩ ጨዋታዎቻችን እየተዝናኑ ይጫወቱ።💰

🔗 አሁኑኑ https://afrobetting.net ላይ ይመዝገቡ።

https://t.me/afrosportsbet
10
እስራኤል በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት ጀመረች።

በእስላማዊ ሪፐብሊክ ኢራን ብሮድካስቲንግ የሚተዳደረው የወጣት ጋዜጠኞች ክበብ እንዳስታወቀው፣ አሁን ላይ በደቡባዊ ኢራን ውስጥ በቡሼህር የአየር መከላከያ ዘዴዎች ነቅተው እየጠበቁ ነው።

በሌላ በኩልም የእስራኤል ጦር በደቡብ ምዕራብ ኢራን ወታደራዊ መሠረተ ልማቶችን መትቷል ሲል ገልጿል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ዩናይትድ ኪንግደም በኢራን ባለው የጸጥታ ሁኔታ በቴህራን የሚገኙ የኤምባሲ ሰራተኞቿን ልታስወጣ መሆኑን የዩኬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማስታወቁን ቢቢሲ ዘግቧል።

“ሰራተኞቻችንን በጊዜያዊነት ከኢራን ለማስወጣት የጥንቃቄ እርምጃ ወስደናል” ሲል የዩናይትድ ኪንግደም የውጭ፣ የኮመንዌልዝ እና ዴቨሎፕመንት ጽህፈት ቤት በመግለጫው አስታውቋል።ሆኖም ኤምባሲው ስራውን እንደማያቆምና “አገልግሎቱን በርቀት እንደሚሰጥ” ገልጿል።

በሳምንቱ መጀመሪያ በተመሳሳይ መልኩ በደህንንት ስጋት ምክንያት በእስራኤል የሚገኘውን ኤምባሲዋን እና የቆንስላ ሰራተኞቿን ለጊዜው እንደምታስወጣ ሲል የቢቢሲ ዘገባ አስረድቷል።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
33😱4
ትራምፕ የቲክ ቶክ እገዳ ቀነ ገደብን ለሶስተኛ ጊዜ አራዘሙ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቲክ ቶክ እንዲታገድ ያስቀመጡትን የእገዳ ቀነ ገደብ ለሶስተኛ ጊዜ አራዝመዋል።

በትሩዝ የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ “የቲክ ቶክን ቀነ-ገደብ በ90 ቀናት እንዲራዘም የአስፈጻሚ ትዕዛዝ ፈርሜያለሁ" ብለዋል፡፡

የቀነ ገደቡ መራዘም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አሜሪካውያን የሚጠቀሙበትን የግንኙነት መረብ በድንገት ላለመዝጋት እና ተገቢውን አካሄድ በሚጠብቅ መንገድ ውሳኔ ለመስጠት ያለመ እንደሆነም ጠቅሰዋል፡፡

ቲክ ቶክ በለጠፈው መግለጫ ፕሬዝዳንት ትራምፕ መተግበሪያው ለ170 ሚሊዮን የአሜሪካ ተጠቃሚዎች እና 7.5 ሚሊዮን ለሚሆኑ ምርቶቻቸውን በቲክቶክ ላይ ለሚያስተዋውቁ አሜሪካ ነጋዴዎች እንዲደርስ እና አንዳይቋረጥ ስለረዱት አመስግነኗል ማለቱን  ቢቢሲ ዘግቧል።ሁለተኛው ዙር የቲክቶክ እገዳ ቀነ ገደብ ዛሬ የሚያበቃ ሲሆን ትራምፕ ለቲክቶክ ሶስተኛ አድል መስጠታቸውን ተከትሎ አዲሱ የእገዳ ቀን እስከ ፈረንጆቹ መስከረም 17፣ 2025 ድረስ የሚቆይ ይሆናል።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
31👎4😱1
በዳይመንድ ሊግ ዮሚፍ ቀጄልቻ እና ለሜቻ ግርማ አሸነፉ

በፓሪስ በተደረገው የ5 ሺህ ሜትር የዳይመንድ ሊግ ውድድር አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ በበላይነት አጠናቅቋል።

12 ደቂቃ 47.84 ሰከንድ ደግሞ ርቀቱን ለማጠናቀቅ የወሰደበት ሰዓት ነው። በውድድሩ ሳሙኤል ተፈራ 5ኛ ሲወጣ መዝገቡ ስሜ እና ገመቹ ዲዳ 11ኛ እና 13ኛ በመሆን ውድድርራቸውን አጠናቅቀዋል።

በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል የዳይመንድ ሊግ አካል በመሆነው ውድድር አትሌት ለሜቻ ግርማ በአንደኝት አጠናቋልቅ።

የርቀቱ የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት የሆነው ለሜቻ ግርማ 8 ደቂቃ 07.01 ሰከንድ የገባበት ሰዓት ሆኖም ተመዝግቧል።

አተሌት ጌትነት ዋለ ደግሞ 3ኛ ደረጃ ወጥቷል። 8 ደቂቃ 12.58 ጌትነት የገባበት ሰዓት ሆኗል። በርቀቱ አብርሀም ስሜ 8ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቅቋል።

በተመሳሳይ የሴቶች 3 ሺህ ሜትር መሰናክል አትሌት ሲምቦ ዓለማየው 9 ደቂቃ 01.22 በመግባ 3ኛ ወጥታለች። አትሌት ሎሚ ሙለታ ደግሞ 9ኛ በመሆን ውድድሩን ፈጽማለች።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
👍1413