ETHIO-MEREJA®
110K subscribers
25.9K photos
486 videos
22 files
12.9K links
News & Media Company®

USA : Washington

Addisababa, Ethiopia🇪🇹
.
Buy ads: https://telega.io/c/ethio_mereja
.
ለጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት
ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ!!
👉 @ethio_merejabot
Download Telegram
ማንቼስተር ዩናይትድ 17ኛ ሽንፈቱን አስተናገደ

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቼስተር ዩናይትድ በ2024/25 የውድድር ዘመን 17ኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል፡፡

በኦልድትራፎርድ ዌስትሃም ዩናይትድን ያስተናገደው ዩናይትድ ጃሮድ ቦውን እና ቶማስ ሱቼክ ባስቆጠሯቸው ግቦች 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል፡፡

በሌሎች የሊጉ 36ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ጨዋታዎች ክሪስታል ፓላስ ቶተንሃምን 2 ለ 0 ሲያሸነፍ ኖቲንግሃም ፎረስት ከሌስተር ሲቲ 2 አቻ ተለያተዋል፡፡

በሌሎች ጨዋታዎች ኒውካስትል ዩናይትድ ቼልሲን 2 ለ 0 ሲረታ፤ ቶተነሃም በሜዳው በክሪስታል ፓላስ 2 ለ 0 ተሸንፏል፡፡ ኖቲንግሃም ፎረስት እና ሌስተር ሲቲ ያደረጉት ጨዋታ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
👍61😁233👎3😱3👏2
በወላይታ ዞን ሰርጉን አቋርጦ ቀዶ ህክምና የሰራው ሐኪም አድናቆት እየተቸረው ይገኛል

ዶ/ር ብሩክ ወይሻ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በወላይታ ዞን፣ በበሌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የቀዶ ጥገና ስፔሻሊስት ነው።

ወጣቱ ሐኪም ታዲያ የራሱን የሰርግ ዝግጅት አቋርጦ ወጥቶ ታካሚን ቀዶ ጥገና በማድረግ ሕይወት የማዳኑ ጉዳይ የአካባቢው ነዋሪዎች መነጋገሪያ ሆኗል።

የሰርጉ ዝግጅት ከነበረበት ከ40 በላይ ኪሎ ሜትር በላይ ወደ ሆስፒታሉ ተጉዞ ቀዶ ጥገና በማድረግ የሰው ሕይወት ማዳን መቻሉን ዶ/ር ብሩክ ለኢቢሲ ተናግሯል።

ወጣቱ ሐኪም የተሟላ የቀዶ ጥገና ሕክምና ገና በቅርቡ በጀመረው ሆስፒታል የመጀመሪያው ስፔሻሊስት ቅጥር ሲሆን፤ በሆስፒታሉ ሥራ ከጀመረም ገና ሶስት ሳምንቱ ነው።

በቀዶ ጥገና የታከመው በሽታ ከጨጓራ ሕመም ጋር ተያይዞ የሚከሰትና ሕይወትን አደጋ ላይ የሚጥል ሲሆን፤ ታካሚው በሰዓቱ ሕክምና ባይደረግለት ኖሮ ሕይወቱ ሊያልፍ ይችል እንደነበርም ነው የተገለፀው።

ቀዶ ጥገና የሕክምና ባለሙያዎች የቡድን ሥራ ነው ያለው ዶ/ር ብሩክ፤ በአጠቃላይ በቀዶ ጥገናው ለተሳተፈው የሕክምና ቡድን ምስጋና አቅርቧል ።

የቀዶ ጥገና ሕክምናው የተደረገለት የ40 ዓመት ታካሚ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ የገለፀው ዶ/ር ብሩክ፤ ከዚህ የሚበልጥ ደስታ የለም ብሏል።

በሙያዬ የፈፀምኩትን ቃለ-መሃላ እና የገባሁትን ቃል-ኪዳን መቼም ቢሆን አላጥፍም፤ ለሙያው የሚገባውን ክብር እሰጣለሁ ብሏል ወጣቱ ሐኪም ብሩክ ወይሻ።(Via ETV)

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
👍302👏3429🙏27🥰10🤔5
ጤና ባለሙያዎች!!

የደሞዝ እና ጥቅማ ጥቅም ጥያቄ በማንሳት ለመንግሥት የሰላሳ ቀናት የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ጊዜ ሰጥተው የነበሩት የጤና ባለሙያዎች ምላሽ ባለማግኘታቸው ከፊል የሥራ ማቆም አድማ መምታታቸውን ለቢቢሲ ተናገሩ።

ባለሙያዎች ከጥቂት "የተመረጡ የሕክምና ክፍሎች" ውጪ ያሉ ክፍሎች ከዛሬ ግንቦት 5/2017 ዓ.ም. ጀምሮ ሥራ ማቆማቸውን ገልፀዋል።

ቢቢሲ ያነጋገራቸው አምስት በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የሚገኙ ባለሙያዎች ከድንገተኛ፣ ከማዋለጃ፣ ከፅኑ ሕሙማን እንዲሁም ከድንገተኛ ቀዶ ሕክምና ክፍሎች ውጪ ያሉ የሕክምና ተቋማት ክፍሎች አገልግሎቶች ማቋረጣቸውን ተናግረዋል።

በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 5 ቀን 2017 ዓ.ም. በመላ ሀገሪቱ የተጀመረውን የከፊል የስራ ማቆም አድማ ለማካሄድ ሲሞክሩ ከመንግሥት አካላት ማስፈራሪያና ጫና እንደደረሰባቸውም አስታውቀዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ በዛሬው ዕለት ተጠርቷል የተባለውን የህክምና ባለሙያዎች አድማ በዋና ዋና የመንግስት ሆስፒታሎች ማለትም በዳግማዊ #ምኒልክ ሪፈራል ሆስፒታል፣ #በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል እና #በየካቲት12 ሜዲካል ኮሌጅ ሆስፒታል ጠዋት ላይ የከፊል የስራ ማቆም መካሄዱን ለመታዘብ ተችሏል።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
👍14711🤔6👎2
ሕወሓት ከፖለቲካ ፓርቲነት ተሠረዘ

ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ከፖለቲካ ፓርቲነት መሠረዙን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡

ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከፖለቲካ ፓርቲነት መሠረዙን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያወጣው መግለጫ ሙሉ ቃል ቀጥሎ ቀርቧል፡-


  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
👍67👎1611😱3👏2🥰1
"ሁሉን የሚያግባባ ነገር ፈልጉና ችግሮችን በሰላማዊ ውይይት ፍቱ" - ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት በጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ ተጀምሯል።

የርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤ መጀመሩን አስመልክቶ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም "ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ልማትና ዕድገት እናሻግራለን ብላችሁ እየደከማችሁ ያላችሁ ወገኖቻችን እባካችሁ መለስ ብላችሁ እናታችሁ የተንገላታችበትን እዩና በቃ በሉ" ብለዋል።

"ሁሉን የሚያግባባ ነገር ፈልጉና ችግሮችን በሰላማዊ ውይይት ፍቱ" ያሉ ሲሆን፤ "በዚህ ኣማራጭ እናት ሀገር እፎይታ እንድታገኝ ኣድርጉ፤ ይህንም ለውድ እናት የሚደረግ ካሣ ኣድርጋችሁ ውሰዱት፤ የቤተ ክርስቲያናችን ወቅታዊ መልእክትና ጥሪም ይህ ነው" ብለዋል።

ከሰላም እጦት የተነሣ በእጅጉ እየተጎዳ ያለውን ሕዝባችን ሰላምና ፍትሕ እንዲያገኝ በጸሎትም በትምህርትም፣ በምክርም መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

"የኢትዮጵያ ህዝብ ለእንግልት እየተዳረገ ያለውም የሌሎች እጅ ባይለየውም በዋናነት በገዛ ልጆቹ ነው" ያሉት ፓትርያርኩ፤ "እናት በገዛ ልጆቿ ስትንገላታ ማየት እጅግ ኣሳዛኝ ነገር ነው፤ እንደዚህ ያለው ነገር በደንብ ያልታሰበበት ኣካሄድ በብስለትና በንስሓ ማስተካከል አሸናፊነትን እንጂ ተሸናፊነትን አያሳይምና እንዲታሰብበት እንመክራለን" ብለዋል።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
👍15432🤯3👎2😱2🥰1
ETHIO-MEREJA® pinned Deleted message
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከዓለም ከፍተኛው ተከፋይ ስፖርተኛ ሆነ

የእግር ኳሱ ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በ2025 ከ275 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ በማግኘት የዓለም ከፍተኛው ተከፋይ ስፖርተኛ መሆን ችሏል።

ለሳዑዲዉ ክለብ አልናስር እየተጫወተ የሚገኘው ሮናልዶ ከስፖንሰር ሺፕ እና ከደሞዝ ጥቅማጥቅሞች ያገኘው ገቢ ከዓለም ቀዳሚው ስፖርተኛ አድርጎታል።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ የዓለም ከፍተኛው ተከፋይ ስፖርተኛ ሲሆን ይህ ለ3ኛ ተከታታይ ዓመታት መሆን ፎርብስ ዘግቧል።

የቅርጫት ኳሱ ኮከብ ስቴፈን ከሪ በ 156 ሚሊዮን ዶላር ሁለተኛ ደረጃን ሲይዝ፤ ብሪታንያዊው ቦክሰኛ ታይሰን ፉሪ በ146 ሚሊዮን ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

ሌላኛው የእግር ኳስ ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ 135 ሚሊዮን ዶላር ገቢ በማግኘት 5ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል፡፡ እንዲሁም ሌላኛው የእግር ኳስ ተጫዋቾች ካሪም ቤንዜማ 104 ሚሊዮን ዶላር ገቢ በማግኘት 8ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ተጫዋች ሆኗል።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
👍8627🤔5😢2👏1😁1🤯1
ክሪስታል ፓላስ ማንችስተር ሲቲን በማሸነፍ የኤፍ ኤ ዋንጫ አሸነፈ

በእንግሊዝ ኤፍ ኤ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ ክሪስታል ፓላስ ማንችስተር ሲቲን 1 ለ 0 በማሸነፍ የኤፍ ኤ ዋንጫን ማሸነፍ ችሏል፡፡

በግዙፉ ዌምብሌይ ስታዲየም በተካሄደው የፍጻሜ ጨዋታ ኤዜ በ17ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠራት ብቸኛ ግብ ክሪስታል ፓላስን ባለድል አድርጋለች፡፡

በፍጻሜው ጨዋታ የፔፕ ጓርዲዮላን ቡድን የረቱት ክሪስታል ፓላሶችም በታሪካቸው ለመጀመሪያ ጊዜ የኤፍኤ ዋንጫን ማሳካት ችለዋል፡፡

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
👍9315👏6👎5