ETHIO-MEREJA®
128K subscribers
24.2K photos
462 videos
22 files
12.1K links
Addisababa, Ethiopia🇪🇹

News & Media Company®
.

USA : Washington

.
Buy ads: https://telega.io/c/ethio_mereja
.
ለጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት
ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ!!
👉 @ethio_merejabot
Download Telegram
#CBE "ስም ዝርዝር ይፋ አደረገ!"

ባንኩ አላግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ያልመለሱ 565 ግለሰቦች የስም ዝርዝር ይፋ አደረገ!

ባንኩ የሲስተም ማዘመኛ ሥራ ላይ የተፈጠረውን ክፍተት በመጠቀም መጋቢት 6ቀን 2016 ዓ.ም. በሂሳብችሁ ከተቀመጠ ገንዘብ ውጭ በሕገወጥ መንገድ ገንዘብ የወሰዳችሁ ግለሰቦች በፈቃደኝነት ሂሳባችሁ በሚገኝበት ቅርንጫፍ በአካል በመቅረብ ወይም በዲጂታል የክፍያ ዘዴ ገንዘቡን እስከ ቅዳሜ መጋቢት 14/2016 ዓ.ም ተመላሽ እንዲያደርጉ መጠየቁ ይታወሳል።

በዚህ መሰረት 14441 የሚሆኑ ግለሰቦች በተሰጠው ጊዜ ገደብ ተጠቅመው የወሰዱትን ገንዘብ ሙሉ በሙሉና በከፊል መመለሳቸውን ባንኩ አስታውቋል።

ሆኖም በምስሉ ላይ የተጠቀሱት የሂሳብ ቁጥራቸው የተዘረዘረው 565 ግለሰቦች ባንኩ የሰጠውን ዕድል በመጠቀም ያላግባብ የወሰዱትን ገንዘብ አለመመለሳቸውን ባንኩ አስታውቋል።

ባንኩ ባስጠነቀቀው መሠረት ወደ ቀጣዩ ሕጋዊ እርምጃ ከማለፉ በፊት ገንዘቡን በአፋጣኝ እንዲመልሱ አንድ ተጨማሪ ዕድል በመስጠት እስከ ቅዳሜ መጋቢት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት ድረስ ገንዘቡን በሚመልሱት ላይ በባንኩ በኩል ቀጣይ ሕጋዊ እርምጃ እንደማይኖር አረጋግጧል።

ነገር ግን እስከተጠቀሰው ቀን ገንዘቡን ያልመለሱ ካሉ የተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ዘዴዎችን በመጠቀም ሙሉ ስማቸውን፣ ፎቶዋቸውን፣ በሕገ ወጥ መንገድ ገንዘብ በመውሰድ ወንጀል መጠርጠራቸውን በመጥቀስ ለሚመለከታቸው የሕግ አካላትና ተቋማት በማሳወቅ ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

በተጨማሪም ከሕግ አካላትና ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመተባበር ቀጣይ የወንጀል፣ የፍትሐ ብሔርና የአስተዳደር ሕጋዊ እርምጃዎች እንደሚወሰድ ለመጨረሻ ጊዜ አሳስቧል።

       -ETHIO-MEREJA-
      
T.me/ethio_mereja
በነገው ዕለት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ለሚካሄደው ታላቁ የኢፍጣር መርኃ ግብር ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ሆነ!

በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚካሄደው የአደባባይ ላይ የኢፍጣር ፕሮግራም በሰላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የፀጥታና ደህንነት የጋራ  ግብረ-ሐይሉ አስታወቀ፡፡

በነገው ዕለት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ከሚካሄደው ታላቁ የኢፍጣር መርኃ ግብር  ጋር ተያይዞ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ አድርጓል፡፡

የእምነቱ ተከታዮች ወደ ኢፍጣር ፕሮግራሙ ሲመጡ ለጋራ ደህንነት ሲባል ፍተሻ መኖሩን ተረድተው እንደወትሮው ሁሉ ትብብር እንዲያደርጉ የተጠየቀ ሲሆን ከፕሮግራሙ ጋር የማይሔዱ በህግ የተከለከሉ እና ስለታማ ነገሮችን ይዞ መምጣት ፈፅሞ ክልክል መሆኑን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ሐይሉ አስታውቋል፡፡

በነገው ዕለት መጋቢት 18 ቀን 2016ዓ.ም በአዲስ አበባ ከሚካሄደው ታላቁ የኢፍጣር መርኃ ግብር ጋር ተያይዞ ከ5፡00 ሰዓት ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚደረጉ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም መሰረት፡-
•  ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅ/ኡራኤል ቤ/ክርስቲያን

•  ከወሎ ሰፈር ወደ መስቀል አደባባይ   ኦሎምፒያ

•  ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ አሽከርካሪዎች ለከባድ መኪናዎች አጎና ሲኒማ፤ ለሌሎች ተሸከርካሪዎች ጥላሁን አደባባይ ጋር ዝግ የሚደረግ ይሆናል፡፡

•   ከጦር ኃይሎች በሜክሲኮ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሸከርካሪዎች  በተለምዶ አጠራሩ ክቡ ባንክ አካባቢ፡፡

•  ከፒያሳ በቸርችል ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ሐራምቤ መብራት ላይ፡፡

• እንዲሁም ከ4 ኪሎ በውጭ ጉዳይ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ብሔራዊ ቤተ መንግስት መስቀለኛው ላይ፡፡

• ከአዋሬ አካባቢ በካሳንቺስ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ኢንተርኮንትኔታል አካባቢ ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ጀምሮ የኢፍጠር ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅበት ሰዓት ድረስ ዝግ የሚደረጉ ይሆናል፡፡

በተጨማሪም በተገለፁት መንገዶች ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓታት ተሽከርካሪዎችን አቁሞ መሄድ የተከለከለ ሲሆን ኅብረተሰቡ መርኃ ግብሩ በሠላም ተጀምሮ በሠላም እንዲጠናቀቅ ለፀጥታ አካላት ተባባሪ እንዲሆንና ማንኛውም ዓይነት አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙ በፖሊስ የመረጃ ስልኮች 0111 11 01 11 እና ነፃ የስልክ መስመር 991 ላይ በመደወልና መረጃ በመስጠት የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግ የፀጥታና የደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታውቋል፡፡

       -ETHIO-MEREJA-
      
T.me/ethio_mereja
ኢትዮጵያ ኮከብ ተጨዋቿን አጣች🕯

አዲሱ ሙሽራ ማረፉ ተሰምቷል 🕯

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የባህርዳር ከነማው ድንቅ የአማካይ ተጨዋች አለልኝ አዘነ በድንገት ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል።

በቅርቡ የጋብቻ ስነ ስርዓቱን በቤተክርስቲያን የፈፀመው አዲሱ ሙሽራ ድንገት ዛሬ ለሊት ህይወቱ ማለፉ ተረጋግጧል ።

ለአርባምንጭ ታዳጊ ቡድን እስከ ዋናው፤ ለሀዋሳ ከተማና  አሁን ለባህርዳር ከተማ በሊጉ የሚጫወተው አለልኝ አዘነ  ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም ጥሪ ተደርጎለት አገልግሎት  ሰጥቷል።

አመለ ሸጋው ተጨዋች አለልኝ አዘነ ላለፉት ሁለት አመታት በጣና ሞገዶቹ ቤት አስደናቂ ብቃቱን በማሳየት ክለቡንና ሀገሩን እያገለገለ የሚገኝ ወጣት ተጨዋች ነበር። (ባላገሩ ቴሌቪዥን)

ኢትዮ መረጃ ለወዳጅ፣ ቤተሰቦቹና አድናቂዎቹ መፅናናትን ይመኛል። Rest In Peace🕯

       -ETHIO-MEREJA-
      
T.me/ethio_mereja
ሰበር ዜና!!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ዳግም በሶማሊያ አየር ላይ ከመጋጨት ለጥቂት መትረፉ ተነገረ

የኢትዮጵያ እና የኤምሬትስ አየር መንገድ አውሮፕላኖች በሶማሊያ አየር ላይ ከመጋጨት ለጥቂት መትረፋቸው ተነገረ።

ነጻ አገርነቷን ያወጀችው የሶማሊላንድ ሲቪል አቪዬሽን እና ኤርፖርቶች ባለሥልጣን ሁለቱ አውሮፕላኖች አየር ላይ ሊጋጩ ተቃርበው የነበረው በሶማሊያ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች "አሻሚ እና የተሳሳተ" ትዕዛዝ ነው ብሏል።

እንደ ባለሥልጣኑ መግለጫ፤ እሁድ መጋቢት 15/2016 ዓ.ም. ምሽት ላይ በሶማሊያ የአየር ክልል ውስጥ ሲበሩ የነበሩት አውሮፕላኖች ከመጋጨት የተረፉት የሶማሊላንድ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ አብራሪዎች በወሰዱት “ፈጣን እና ትክክለኛ እርምጃ” ነው።

የበረራ መቆጣጠሪያ ድረ-ገጽ በሆነው ፍላይትራዳር24 ላይ መመልከት እንደሚቻለው ክስተቱ ባጋጠመበት ወቅት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን እና የኤምሬትሱ ቦይንግ 777 አውሮፕላን በ37ሺህ ጫማ ከፍታ ላይ ሲበሩ ነበር።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ኢቲ690 በሶማሊያ የአየር ክልል ሲበር ከነበረበት 37ሺህ ጫማ ምሽት 21፡43 (ሌሊት 6፡43) ሲል በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ከፍታውን በፍጥነት ጨምሮ ወደ 39ሺህ ጫማ ከፍ አድርጓል።

በዚህም ምክንያት በሁለቱ የመንገደኞች አውሮፕላኖች መካከል ሊከሰት ይችል የነበረን አሰቃቂ አደጋ ለማስቀረት ችሏል ሲል ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል።በቅርቡ በተመሳሳይ መልኩ የኳታር አየር መንገድ አውሮፕላን ከፍታውን እንዲጨምር በሞቃዲሾ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ከተነገረው በኋላ ከኢትዮጵያ አውሮፕላን ጋር ለመጋጨት ተቃርቦ እንደነበረ መዘገቡ ይታወሳል።

       ETHIO-MEREJA
      
T.me/ethio_mereja
🪟ዋው የሚያስብሉ የግድግዳ ምስሎች😍

👉Shine laminated(የሚያብረቀርቅ)ናቸው።
👉በውሀ የሚፀዳ እና HD ማራኪ ናቸው!
👉በቀላሉ ባለው ማንጠልጠያ ሚሰቀል!!

     በትዛዝ በ3ቀን እናደርሳለን።

  ዋጋ :-  1.50*80 - 3500ብር
  ዋጋ :-  1.20*60 - 3000ብር

📍አድራሻ 4killo/ቀበና #ቤሊየር አልዘይን ህንፃ 207ቁ

     ☎️ 0901882392 /
     ☎️ 0931448106

ተጨማሪ T.me/Dinkwallarts
ON HAND - የጌታ እራት አለ።
የ5 አመቷን ታዳጊ የደፈረው ላይ የ6 ወር እስራት የፈረደው ዳኛ ከስራና ከደመወዝ ታገደ።

አቶ ሀብታሙ ሙሉነህ ለወንበራ ወረዳ ፍ/ቤት ዳኛ በወንጀል መዝገብ ቁጥር 8429 ተከሳሽ ተክለአብ ገላታ የወንጀል ህግ ቁጥር 622 ድንጋጌን በመተላለፍ የአምስት አመት ህጻን ልጅ አስገድዶ ድፍረት በደል ወንጀል ተከስዉ ጉዳዩን ሲዳኝ የነበረ ሲሆን ተከሳሽን በቀረበበት ክስ ጥፋተኛ ካልክ በኃላ ቅጣቱን 6 ወር ቀላል እስራት በማለት ወስናሀል ይህ ዉሳኔ ለህጻናት መብት ፍ/ቤቱ ትኩረት ሰጥቶ እንዳልሰራና የመንግስትና የህዝብን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል ዉሳኔ እንደሆነ በሰፊዉ አቤቱታዎች እየቀረቡ ስለሆነ ዉሳኔ ሰጪ ዳኛ በምን ምክንያት ይህን ዉሳኔ እንደሰጠ ማጣርት እና ማስተካከያ እርምጃ መዉሰድ እንደ ተቋም ስለሚያስፈልግ መተከል ዞን ከፍ/ፍ/ቤት ኮሚቴ በመላክ ጉዳዩን በአስቸካይ አጣርቶ እንዲልክልን ሆኖ እስከዛ ድረስ ይህ ዳኛ ስራዉን እየሰራ ይቀጥል ቢባል ሌላ በደል ሊያደርስ ይችላል የሚል እምነት ስላለን ሌላ ተለዋጭ ትእዛዝ እስከሚደርስ ድረስ ዳኛዉ ከስራ እና ከደመወዝ ታግዶ እንዲቆይ ሲል በቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ መስጠቱን ከላይ የተያያዘው ደብዳቤ ያመለክታል።

       ETHIO-MEREJA
      
T.me/ethio_mereja
#ጤናመረጃ

ፓፓያ ለጤናችን የሚሰጠን 10 አስደናቂ ጥቅሞች!

1) ፓፓያ በሆድ ውስጥ የሚገኙ ትላትሎችን ለማጥፋት እና የጨጓራን አሲድነት ይቀንሳል፡፡

2) የፓፓያ ጁስ መጠጣትን ልምድ ማድረግ በአንጀት ውስጥ የሚፈጠርን ኢንፌክሽን እና ጎጂ ፈሳሽ ጠርጎ ያወጣል፡፡ የምግብ መፈጨት ሂደትን በማገዝ ብሎም የአንጀት ካንሰር የመከሰት እድልን ይቀንሳል፡፡

3) ዝቅተኛ የካሎሪ እና ከፍተኛ የጠቃሚ ምግብ ይዘት ስላለው በውፍረት መቀነስ ሂደት ውስጥ ላሉ ሰዎች አስተዋጽዖው የላቀ ነው፡፡

4) የጸረ ካንሰርና የሰውነት መቆጣትን የሚቀንስ ባህሪ አለው፡፡ ይህ የሰውነት መቆጣትን የሚቀንስ ባህሪ በማንኛውም የሰውነታችን መገጣጠሚያ ላይ ለሚደርስ ህመምና የአጥንት መሳሳት ለመቀነስ ይረዳል፡፡

5) ፎረፎርን በመከላከል ጤናማ ጸጉር እንዲኖረን ስለሚያግዝ በተጨማሪ ከፓፓያ የተሰሩ የጸጉር ማስዋቢያ ምርቶችን መጠቀም ይመረጣል፡፡

6) ካለ እድሜ የሚመጣን የቆዳ መሸብሸብን ይከላከላል፡፡ ፓፓያን በቀጥታ ቆዳዎን በመቀባት ወይም በመመገብ የሚያምር ለስላሳ ቆዳን መጎናፀፍ ይቻላሉ፡፡ የተፈጨ ፓፓያ የተሰነጣጠቀ ተረከዝን ለማከም ይጠቅማል፡፡

7) የሞቱ የቆዳ ሴሎችን ለማስወገድ ይረዳል፣ የቆዳ ድርቀትን ይከላከላል፡፡ ጥሬ ፓፓያ ፊትዎን ለ25 ደቂቃ በመቀባት ፊት ላይ የሚገኙ ጥቃቅን ያበጡ ነጠብጣቦችን በቀላሉ ማስወገድ ይችላሉ፡፡

8) ፓፓያ አርጀኒን የተባለን ንጥረ ነገር ሲኖረው ይህም የወንድ ልጅን መሀንነት ይከላከላል፡፡

9) በቫይታሚን ኤ’ ሲ እና ኢ የበለጸገ በመሆኑ የኮሌስትሮል መጠንን ለመቀነስ በተጨማሪም የልብ ህመምን ይከላከላል፡፡

10) ራሰ በራነትን ይከላከላል፣ የፀጉር እድገትንና ጥንካሬን ይጨምራል፡፡

ጠቃሚ ነውና ለወዳጆ ያካፍሉ! ሼር!
T.me/ethio_mereja
Do you enjoy reading this channel?

Perhaps you have thought about placing ads on it?

To do this, follow three simple steps:

1) Sign up: https://telega.io/c/ethio_mereja
2) Top up the balance in a convenient way
3) Create an advertising post

If the topic of your post fits our channel, we will publish it with pleasure.
ETHIO-MEREJA®
Photo
የአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት “ዲሞግራፊ ለመቀየር” የሚካሄድ አይደለም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስተባበሉ!!

በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወነ የሚገኘው የመንገድ እና አካባቢ ልማት ፕሮጀክት፤ “ዲሞግራፊ ለመቀየር” አሊያም “ኦሮሞዎችን ወደ ከተማ ለመመለስ ነው” የሚሉ ወገኖችን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተችተዋል።

አዲስ አበባ ውስጥ “ከበቂ በላይ” የኦሮሞ እና የሌሎች ብሔር ተወላጆች መኖራቸውን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “የሌለ ሰው ኖሮ፤ ሰው ለማምጣት የምንቸገርበት አይደለም” ሲሉም አስተባብለዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ይህን ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደር ልማት ስራን ከሚያስፈጽሙ አመራሮች እና የስራ ኃላፊዎች ጋር ትላንት ረቡዕ መጋቢት 18፤ 2016 ባደረጉት ውይይት ነው። እርሳቸው የሚመሩት መንግስት ከዚህ ቀደም ባከናወናቸው የግንባታ ስራዎች “ብዙ ስሞታዎች ነበሩ” ያሉት አብይ፤ ለዚህም የምኒልክ ቤተ መንግስት እና የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እድሳትን በምሳሌነት አንስተዋል። 

“ይሄ ግቢ ሲቀየር ሀገራዊ ፖለቲካ ነበር። የእዚህን ግቢ እድሳትን እና ዩኒቲ ፓርክን ለመቃወም ሰዎች በጣም ብዙ ደክመዋል። በኋላ [የአዲስ አበባ ከተማ] ማዘጋጃ ቤት ሲጠናቀቅ፤ ‘ለምን ተሰራ’ ተብሎ ብዙ ተብሏል። አሁንም ብዙ አሉባልታዎች፤ ብዙ ወሬዎች ይሰማሉ። ‘ዲሞግራፊ ለመቀየር ነው’፤ ‘ኦሮሞዎች ለመመለስ ነው’ [የሚሉ] የተለያዩ ስሞች ይሰጣሉ” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

አብይ መንግስታቸው የአዲስ አበባ ከተማን “ዲሞግራፊ” የመቀየር እቅድ እንደሌለው ያስረዱት፤ የትውልድ ስፍራቸው የሆነችውን የበሻሻ ከተማ በምሳሌነት በመጥቀስ ነው። “ ‘ዲሞግራፊ መቀየር’ የሚባል ነገር የሚመጣው፤ በሻሻ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ቋሚ ሰዎች የነበሩ ሆነው፤ ሰዎች ከጅማ፣ ከአጋሮ ከመጡ፤ በሻሻ እንዲገቡ እና እንዲቀላቀሉ ሲፈለግ የሚሰራ ስራ ነው” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህንን ከአዲስ አበባ ከተማ ሁኔታ ጋር አነጻጽረዋል። 

“አዲስ አበባ ውስጥ፤ ከበቂ በላይ ኦሮሞ፣ አማራ፣ ጉራጌ፣ ትግሬ፣ ከበቂ በላይ ሁሉም አለበት። የሁለት፣ ሶስት ሚሊዮን ከተማ እኮ አምስት፣ ስድስት [ሚሊዮን] ገባ። የሌለ ሰው ኖሮ፤ ሰው ለማምጣት የምንቸገርበት አይደለም። አዲስ አበባስ የማን ከተማ ሆና ነው፤ ማን ዲሞግራፊ የሚሰቃይባት? አይገባኝም” ሲሉም ተደምጠዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

የአዲስ አበባ የመንገድ ኮሪደር ልማት ዓላማ ከተማይቱ “ የሁሉም እና ውብ” እንድትሆን ማድረግ መሆኑን የጠቀሱት አብይ፤ ከ“ዲሞግራፊ መቀየር” ጋር ተያይዞ የሚሰሙ አስተያየቶችን “ወሬ እና አሉባልታ” ሲሉ አጣጥለዋቸዋል። “ይሄ ወሬ እና አሉባልታ የሚፈርሰው፤ በተግባር ሰርተን ስናሳይ ነው። ከተግባር ውጭ ይህንን ወሬ ሊያፈርስ የሚችል የለም” ያሉት አብይ፤ ፕሮጀክቱ “ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ” የሚተገበር ከሆነ “ሰው ለመገንዘብ አይቸገርም” ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

የአዲስ አበባን “አጠቃላይ የመንገድ ሽፋን እና ዘመናዊነት እንዲሁም የትራንስፖርት ፍሰት ወደ ላቀ ደረጃ ሊያሳድግ የሚችል” የተባለለት “የመንገድ ኮሪደር ልማት”፤ በከተማዋ ካቢኔ የጸደቀው ከአንድ ወር በፊት የካቲት 15፤ 2016 ነበር። በዚህ ፕሮጀክት እንዲለሙ ዕቅድ የተያዘላቸው የመንገድ ኮሪደሮች፤ ዓለም አቀፍ “የስማርት ሲቲ” ስታንዳርድን በማሟላት የአዲስ አበባ ከተማን ደረጃ “ከፍ የሚያደርጉ ናቸው” ሲል የከተማይቱ አስተዳደር ከዚህ ቀደም ባወጣው መግለጫ ማስታወቁ አይዘነጋም። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)  

       ETHIO-MEREJA
      
T.me/ethio_mereja