ETHIO-MEREJA®
128K subscribers
24.1K photos
462 videos
22 files
12K links
Addisababa, Ethiopia🇪🇹

News & Media Company®
.

USA : Washington

.
Buy ads: https://telega.io/c/ethio_mereja
.
ለጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት
ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ!!
👉 @ethio_merejabot
Download Telegram
ወ/ት ፍሬህይወት ታምሩ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ቦርድ አመራርነት ተረከቡ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ነባር ስራ አመራር ቦርድ አባላት ዛሬ ሐምሌ 23 ቀን 2014 ዓ.ም ቢሾፍቱ በሚገኘው ኩሪፍቱ ሪዞርት ለአዲሱ ስራ አመራር ቦርድ አባላት የስራ ርክክብ አድርገዋል፡፡

በዶ/ር ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ ሰብሳቢነት ሲመራ የነበረው ነባሩ የስራ አመራር ቦርድ በኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ ለሚመራው አዲስ የስራ አመራር ቦርድ ሃላፊነቱን በይፋ አስረክቧል፡፡

በዕለቱ ዶ/ር ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ ነባሩ የስራ አመራር ቦርድ ከህዳር 2009 ዓ.ም እስከ ሰኔ 30/2014 ዓ.ም ያከናወናቸውን ዋና ዋና ተግባራት፣ በአፈጻፀም ሂደት የታዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖች ለተተኪው የስራ አመራር ቦርድ አባላት ገለፃ አድርገዋል፡፡

በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ነባር እና አዲስ የስራ አመራር ቦርድ አባላት፣ የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ፣ የተቋሙ ከፍተኛ ስራ አመራር አባላት እና የመሠረታዊ ሠራተኛ ማህበር አመራር አባላት ተሳትፈዋል፡፡

በመጨረሻም ለቀድሞው የስራ አመራር ቦርድ አባላት ላበረከቱት አስተዋፅኦ የምስጋና ሰርተፍኬትና ሽልማት ከተበርክተላቸው በኋላ በክብር ተሸኝተዋል፡፡
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
🌟የተለያዩ የግልዎ ሊያደርጓቸው የሚገቡ ምርጥ ምርጥ የውበት መንከባከቢያ ዕቃዎች

👉አድሚኑን ለማናገር @awasadmin1
@awasadmin2

👉አድራሻችን:-
1📍 ቦሌ መድሐኔዓለም ቦሌ መሰናዶ ት/ቤት ፊትለፊት አለምነሽ ፕላዛ ግራውንድ ሱቅ ቁጥር 05 (+251941661030 / +251943190237)

2📍ሜክሲኮ አልሳም አፓርታማ(ሳኩር) ግራውንድ
(+251972632087)

👉ለወዳጅዎ ስላጋሩ እናመሠግናለን 🙏

👉 ቴሌግራም ቻናል
https://telegram.me/onlineshoppingce
በአፍሪካ ቀንድ የአውሮፓ ኅብረት ልዩ መልዕክተኛ አን ዌበር ወደ መቀሌ ሊጓዙ መሆኑን ዛሬ በትዊተር ሰሌዳቸው ላይ ጽፈዋል።

ዌበር ወደ መቀሌ የሚጓዙት፣ አፍሪካ ኅብረት የሰሜን ኢትዮጵያውን ጦርነት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚያደርገውን ጥረት ለማገዝ እንደሆነ አስታውቀዋል። ሆኖም ዌበር መቼ ወደ መቀሌ እንደሚጓዙ፣ ስንት ቀናት እንደሚቆዩ እና በቆይታቸው ወቅት ምን ዓይነት መርሃ ግብሮች እንደሚኖራቸው አላብራሩም።

ባሁኑ ወቅት አዲስ አበባ የሚገኙት አን ዌበር፣ መንግሥት ከትግራዩ ሕወሃት ጋር ሊያደርገው ባሰበው የሰላም ድርድርና ለትግራይ ክልል የተቋረጡባትን መንግሥታዊ መሠረታዊ አገልግሎቶች እንደገና በማስቀጠል ዙሪያ ከውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ጋር ከትናንት ወዲያ ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን በዛሬው ትዊተር መልዕክታቸው ገልጸዋል።

ልዩ መልዕክተኛ አን ዌበር ወደ መቀሌ እንደሚጓዙ ያስታወቁት፣ የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የብሄራዊ ደኅንነት አማካሪ እና መንግሥት ከሕወሃት ጋር እንዲደራደርለት ያቋቋመው ተደራዳሪ ቡድን አባል የሆኑት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን መንግሥት የምዕራባዊያን አገራት አምባሳደሮችና ልዩ መልዕክተኞች ወደ መቀሌ እንዲጓዙ ፍቃድ መስጠቱን በገለጹ ማግስት ነው። ከምዕራባዊያን ዲፕሎማቶች መካከል ወደ መቀሌ ለመጓዝ ማቀዳቸውን በመግለጽ፣ ዌበር የመጀመሪያዋ ናቸው። ባሁኑ ወቅት ከዌበር በተጨማሪ፣ በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር ለተመሳሳይ ተልዕኮ አዲስ አበባ ይገኛሉ።
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
Join our telegram 👇🏻

https://t.me/+P7ctetopPExiY2Rk
⚡️⚡️A+ Consultancy⚡️⚡️

የሚፈልጉት ሀገር በተለያዩ አማራጮች የጉዞ እድሎች አመቻችቶ ይጠብቃቿል

VISIT VISA - (Spain 🇪🇸,Italy 🇮🇹 Poland🇵🇱)
STUDENT VISA- (USA🇺🇸Canada 🇨🇦)
WORK VISA- Poland🇵🇱 (እስከ August 30)

October intake
የበረራ ቲኬት 50% ቅናሽ አድርገናል ፈጥነው ይደውሉ

ለበለጠ መረጃ
0926323931
0902037642
በ ቴሌግራም👉 @tsion6

የቴሌግራ ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇
https://t.me/+x9D4c6HL0yE1ZTRk
https://t.me/+x9D4c6HL0yE1ZTRk
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የአንድ መጋዘን ግንብ ተደርምሶ በሰው ህይወትና አካል እንዲሁም በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።


አደጋው የደረሰው ሐምሌ 24 ቀን 2014 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 9:30 ሰዓት ሲሆን በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ክልል ልዩ ቦታው አማኑኤል ሆስፒታል አካባቢ ነው።

በመጋዘን ቤት ውስጥ ውሃ በመሙላቱ ግንቡ ተደርምሶ ከስር በሚገኙ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ በነበሩ 3 ግለሰቦች ላይ ጉዳት በማድረስ የ1 ሰው ህይወት ሆስፒታል ከደረሰ በኋላ ሲያልፍ ፤ 2 ግለሰቦች ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው የመሳለሚያ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የዕለቱ ተረኛ መኮንን ምክትል ኮማንደር መዓዛ ገብረማርያም ገልፀዋል።

ኮማንደሯ አክለው እንዳስታወቁት በአፋጣኝ አደጋው በደረሰበት ቦታ በመሄድ ከሌሎች የፀጥታ አካላትና ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር በመሆን ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች የማውጣትና ወደ ህክምና እንዲሄዱ የማድረግ እንዲሁም ተጨማሪ አደጋ እንዳይከሰት ሰዎችን ከአደጋው ቦታ የማሸሽ ስራዎች መሰራታቸውን ምክትል ኮማንደር መዓዛ አስረድተዋል።

ኃላፊዋ አያይዘው እንደተናገሩት ከክረምቱ ወቅት ጋር ተያይዞ ለአደጋ ስጋት የሆኑ ቦታዎችን በመለየት የሚመለከታቸው አካላት ጉዳት ከመድረሱ በፊት ትኩረት በመስጠት የመፍትሔ እርምጃዎችን መወሰድ እንዳለባቸው ተናግረዋል።

የአካባቢው ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየት የመጋዘኑ ግንብ ተደርምሶ በሰው ህይወትና በአካል ላይ ጉዳት በመድረሱ የተሰማቸውን ሃዘን ገልፀው ተጨማሪ አደጋ እንዳይከሰት ፖሊስ በፍጥነት ቦታው ላይ ደርሶ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የሰራውን ስራ አድንቀው ቀጣይም መጋዘኑ መፍትሔ ካልተበጀለት ስጋት እንደሆነባቸው ተናግረዋል።
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
ፕሬዝደንት ፑቲን አሜሪካ የሩሲያ “ዋነኛ ስጋት” ነች ሲሉ ፈረጁ!!

ፕሬዝደንት ፑቲን ይህን ያሉት በሩሲያ በሴንት ፒተርስበርግ በተከበረው እና ታሪካዊ ነው በተባለው የባህር ቀን ላይ ነው፡፡ ባለፈው ቅዳሜ አዲስ የባህር ኃይል መተዳደሪያ ላይ ፊርማቸውን ያስቀመጡት ፕሬዝደንት ፑቲን አሜሪካ ዋነኛ የሩሲያ ተቀናቃኝ አድርገው አስቀምጠዋል፡፡

በአዲሱ የባህር ኃይል መተዳደሪያ በአርክቲክ እና በጥቁር ባህር ሊኖር የሚችለው የሩሲያ እቅድ መነደፉን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ በታላቁ ቄሳር ፒተር በተመሰረተችው የቀድሞዋ የንጉሠ ነገሥት ግዛት ሴንት ፒተርስበርግ በተከበረው የሩሲያ የባህር ኃይል ቀን ላይ ንግግር ያደረጉት ፑቲን ሩሲያን ታላቅ የባህር ሃይል እንዲኖራት የያደረጉትን ፒተርን አመስግነዋል፡፡

ፑቲን የባህር ሃይሉን ከጎበኙ በኋላ አጭር ንግግር ያደረጉት ሩሲያ ልዩ የሆነችው የዚርኮን ሃይፐርሶኒክ ክሩዝ ሚሳኤሎች በማሳየት ሩሲያ ወታደራዊ አቅም እንዳላት አስጠንቅቀዋል። ፕሬዝዳንቱ ንግግር ከማድረጋቸው ቀደም ብሎ የሩሲያን የባህር ኃይል ሰፊ ስትራቴጂካዊ አላማዎችን የያዘ ባለ55 ገጽ ሪፎርም ፈርመዋል፡፡

ከሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት በኋላ በሩሲያ እና በምእራባውያን መካከል ያለው ፍጥጫ አይሏል፡፡ሩሲያ የኔቶ ጦር ወደ ቀድሞ የሶቬት ሀገራት መስፋፋት ለደህንነቷ እንደማያሰጋት በመግለጽ ነበር በዩክሬን ላይ "ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ" ያወጀችው። ከዚህ በተጨማሪም ዩክሬንን ትጥቅ ማስፈታት እና የናዚን አስተሳሰብ ማጥፋት የዘመቻው አላማ መሆኑን ሩሲያ መግለጿ ይታወሳል።

በሩሲያ ርምጃ የተቆጡት ምእራባውያን ሩሲያን ያዳክማል ያሉትን ሁሉ ማእቀብ በሩሲያ ላይ ጥለዋል። የዶምባስ ግዛትን ነጻ የማውጣት የወሰነቸው ሩሲያ አሁንም በደቡብ እና ምሰራቃዊ ዩክሬን ጦርነት እያካሄደች ትገኛለች፡
T.me/ethio_mereja
የ2014 12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን በ12 ኮድ (በጥያቄ አቀማመጥ ስብጥር) ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው።

የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከዚህ በፊት እንደነበረው በ4 ኮድ (4 የተለያዩ ፈተናዎች/በጥያቄ አቀማመጥ) ሳይሆን እስከ 12 እንዲሆን እየተሰራ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።

ይህ የፈተና ኩረጃን ለመከላከል ከሚሰሩት ስራዎች መካከል አንዱ መሆኑን የሚገልፁት ፕ/ር ብርሃኑ ጎን ለጎን ያሉ ተማሪዎች እርስ በእርስ የሚፈተኑት ፈተና የጥያቄው(order) በፍፁም የተገናኘ እንዳይሆን እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። ፈተናው በዩኒቨርሲቲዎችና በፌዴራል ተቋማት እንደሚሰጥም ገልፀዋል።

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለኢፕድ የሰጡት ቃል፦

"...የክልል ባለሟሎች፣ የክልል ኃላፊዎችን ከፈተና ጉዳይ ጋር እንለያቸው ፤ ፈተናው እራሱ የፌዴራል ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ስለሆነ በፌዴራል ተቋማት ውስጥ ብቻ እንስጥ ብለን አሁን በሙሉ ተማሪዎቹን አጓጉዘን ቢቻል ሁሉንም ከክልላቸው ውጭ በሆኑ ክልሎች ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች እና የፌዴራል ተቋማት ውስጥ ለመስጠት ነው እየተዘጋጀን ያለነው።

ያ የሚያደርገው ሁለት ነገር ነው። 1ደኛ በመንገድ ላይ ሊኖር የሚችለውን የመሰረቅ አደጋ ይቀንሰዋል። 2ተኛ ክፍል ውስጥ ከተገባ በኃላ ለመስረቅ የሚቻልበትን አደጋ ይቀንሰዋል።

ከዛም በላይ ፈተናዎቹን በማዘጋጀት ደረጃ በፊት በ4 የተለያዩ ፈተናዎች ነበር የምናዘጋጀው እስከ 12 አድርገን Completely scrambled እንዲሆኑና ማንም ጎኑ ያለው ተማሪ የሚፈተነው ፈተና አንተ ከምትፈተነው ፈተና order ጋር በፍፁም ያልተገናኘ እንዲሆን አድርገን እየሰራን ነው። ይሄ በጣም በብዙ ደረጃ የፈተና ስርቆትን ይቀንሰዋል ብለን ነው ተስፋ የምናደርገው" ብለዋል።
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
በመረጡት ፎቶ የተሰሩ ልዩ የምርቃት ስጦታዎች ለሚወዷቸው። ለማዘዝ በ 0981050835 ወይም @Liyugift_order ላይ ያናግሩን።ለበለጠ የቴሌግራም ቻናላችን t.me/liyugifts ይጎብኙ። ያሉበት እናደርሳለን
ከዱባይ ወደ ኢትዮጵያ ፓኬጆችን ለማድረስ ፈጣን እና ቀልጣፋ መንገድ እየፈለጉ ነው? እኛ ልንረዳዎ እንችላለን። የኛን አገልግሎቶች በመጠቀም ምን አይነት ዕቃዎችን መላክ እንደሚችሉ ይመልከቱ።

Join: https://t.me/aramex_ethiopia
#Ricatrip

ሪካ ትሪፕ የትራንስፖርት እና የዴሊቨሪ አገልግሎት በአንድ ላይ የሚሰጥ platform ነው።

⚠️ የተሟላ እና ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት ትክክለኛውን የሪካ ማዕበራዊ የትስስር ገፆች ይከታተሉ።
Telegram - Instagram - Facebook


=== አብረን ስለሆንን ብቻ ሌላ ዕድል ===
🌟የተለያዩ የግልዎ ሊያደርጓቸው የሚገቡ ምርጥ ምርጥ የውበት መንከባከቢያ ዕቃዎች

👉አድሚኑን ለማናገር @awasadmin1
@awasadmin2

👉አድራሻችን:-
1📍 ቦሌ መድሐኔዓለም ቦሌ መሰናዶ ት/ቤት ፊትለፊት አለምነሽ ፕላዛ ግራውንድ ሱቅ ቁጥር 05 (+251941661030 / +251943190237)

2📍ሜክሲኮ አልሳም አፓርታማ(ሳኩር) ግራውንድ
(+251972632087)

👉ለወዳጅዎ ስላጋሩ እናመሠግናለን 🙏

👉 ቴሌግራም ቻናል
https://telegram.me/onlineshoppingce
#FIAS777
ብዙዎችን ያጭበረበረው የፊያስ 777 አካውንት ታግዶ ምርመራ እየተካሄደ ነው!!

ፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት የፋይናንስ ወንጀሎች ትንተና ኃላፊ ዮናስ ማሞ ለአዲስ ማለዳ እንደገለጹት፣ በፒራሚድ የንግድ ሥራ ላይ የተሰማራው ፊያስ 777 ድርጅት ከ26 ሺሕ በላይ የውጭ አገር እና ኢትዮጵያዊያን ሰዎች የተሳተፉበት ሲሆን፣ ብዙ ሰዎች ላይ የማጭበርበር ወንጀል መፈፀሙን ጠቁመዋል።

ይህ ፊያስ 777 የተሰኘው ድርጅት እንደ ፋይናንስ ተቋም ተመዝግቦ እና እውቅና ተሰጥቶት እየተንቀሳቀሰ ያልነበረ ተቋም መሆኑንም ኃላፊው ተናግረዋል።

አክለውም ድርጅቱ እውቅና ካለማግኘቱ ባሻገር ፒራሚድ ንግድ በኢትዮጵያ ሕግ መሠረት የተከለከለ እና ወንጀል ነው ብለዋል።ነገር ግን ድርጅቱ የተቀመጠውን ሕግ በመጣስ በሕገ ወጥ ሥራ ላይ ተሳትፎ በተለያዩ የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ማለትም በቴሌግራም፣ በፌስቡክ፣ በዋትሳፕ ጓደኞችን እና ግሩፖችን ፈጥሮ ብዙዎችን እንዳጭበረበረ እና አሁን ላይ አካውንቱ ታግዶ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን ኃላፊው ገልጸዋል።

በፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት በኩል እስካሁን ባለው ድርጅቱ ምን ያህል ገንዘብ ከግለሰቦች እንዳጭበረበረ እየተጣራ ሲሆን፣ እስካሁን ባለው ምን ያህል ግለሰቦች የወንጀሉ ተሳታፊ እንደነበሩ በፌዴራል ፖሊስ በኩል የማጣራት ሥራ እየተከናወነ ይገኛል ተብሏል። የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ መረጃውን አጠናክሮ ከጨረሰ በኋላ ለህዝብ እና ለፌዴራል ፖሊስ እንደሚያሳውቅ ተነግሯል።

በተጨማሪ ቲያንስ 777 ድርጅት ውስጥ ተሳታፊ ሆነው ኅብረተሰቡን ሲያጭበረብሩ የነበሩ ግለሰቦች ጉዳይ እንዲሁ ወንጀላቸው በፌዴራል ፖሊስ ስር እየተጣራ እንደሚገኝ እና ሙሉ መረጃው ከተረጋገጠ በኋላ ይፋ እንደሚደረግ ተጠቁማል።
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
በዶ/ር ሙሉቀን ሀብቱ ላይ የ14 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ!

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት የአ/አ ከተማ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሀላፊው በሆኑት ዶ/ር ሙሉቀን ሀብቱ ምሩፅ ጉዳይ ላይ ተጨማሪ ምርመራ ማድረግ አስፈላጊነቱን ማመኑን በመግለጽ ለፖሊስ የ14 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል።

ዶ/ር ሙሉቀን ሀብቱ በሐምሌ 1 ቀን 2014 ወጥቶ በተሰረዘው የ14ተኛ ዙር 20/80 እና በ3ተኛ ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ አወጣጥ ጋር ተያይዞ ሲስተም ውስጥ ያልቆጠቡ ግለሰቦች እንዲካተቱ ተደርጓል ተብሎ በቀረበ ቅሬታ መነሻነት ተጠረጠረው በቁጥጥር ሥር ውለው ጉዳያቸው እየታየ መሆኑ ይታወቃል።

ዛሬ ጠዋት በነበረው የችሎት ውሎም ዶ/ር ሙሉቀን የታሰርኩት በኮንዶሚንየም ቤት ዕጣ አወጣጥ ላይ የትግሬ ሥም በዝቷል ተብሎ በብሔሬ ምክንያት እንጂ ወንጀል ፈጽሜ አደለም ሲሉ ለፍርድ ቤቱ መናገራቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

መርማሪ ፖሊስም በበኩሉ፤ ወንጀሉ ከተለያዩ ግለሰቦች ጋር በተደራጀ ኹኔታ የተፈጸመ መሆኑን እና ውስን በሆነ የህዝብ ሀብት ላይ ጉዳት የደረሰ መሆኑን የተሰበሰቡ ማስረጃዎች ያሳያሉ ሲል፤ ምርመራው በተገቢው ሁኔታ ማከናወን እንድንችል እና ምርመራውን በሰውና በሰነድ ለማረጋገጥ እንድንችል በወ/መ/ህ/ስ/ቁ 59/2 መሰረት የጠየቅነው ተጨማሪ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ይፈቀድልን ሲል ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

የጊዜ ቀጠሮ መፈቀድ አለበት ወይስ መፈቀድ የለበትም የሚለው መርምሮ ትዕዛዝ ለመስጠት ለዛሬ ከሰዓት የቀጠረው ፍርድ ቤቱ በጉዳይ ላይ ተጨማሪ ምርመራ ማድረግ አስፈላጊነቱን በማመኑ፤ ለፖሊስ የ14 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ መፍቀዱን ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ በላከችው መልዕክት አስታውቃለች።
T.me/ethio_mereja
#ጥንቃቄ
ነሐሴ ወር ከባድ መጠን ያለው ዝናብ የሚዘንብበትና ቅጽበታዊ ጎርፍ የሚከሰትበት ወር መሆኑን ኢኒስቲትዩቱ
ገለጸ

በቀጣዩ ነሐሴ ወር በአንዳንድ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ለተከታታይ ሰዓታትና ቀናት የሚዘንብበት መሆኑ የወንዞች ሙላትና ቅጽበታዊ ጎርፍ የሚከሰትበት ጊዜ መሆኑን የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢኒስቲትዩት አስታወቀ፡፡

በሚቀጥለው ወር ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ፣ የምስራቅ እና የሆሩ ጉዱሩ ወለጋ፣ ሁሉም የሸዋ ዞኖች፣ ጂማ እና አዲስ አበባ ዙሪያ፣ አዲስ አበባ ሁሉም የአማራ ክልል እና የትግራይ ዞኖች እንዲሁም የአፋር ክልል ዞኖች በአብዛኛው ከመደበኛው ጋር የተቀራረበና በአንዳንድ ቦታዎቻቸው ላይም ከመደበኛ በላይ ዝናብ ያገኛሉ ተብሏል። ከዚህም ሌላ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከደቡብ ክልል ደግሞ የሀድያ፣ የጉራጌ፣ የስልጤ የወላይታ፣ ጌደኦ ዞኖች እንዲሁም የሲዳማ እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች ከመደበኛው ጋር የተቀራረበ የዝናብ መጠን እንደሚኖራቸው ይጠበቃል፡፡

በተመሳሳይም ከኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ፣ ኢሉአባቦራ፣ ቡኖ በደሌ፣ አርሲ እና የምዕራብ አርሲ ዞኖች፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ ድሬዳዋና ሐረሪ፣ ሁሉም የጋምቤላ ክልል ዞኖች፣ ከሶማሌ ክልል ሲቲ እና ፋፈን ዞኖች ከሚኖራቸው እርጥበት አዘል አየር ጋር ተያይዞ በአብዛኛው ከመደበኛው ጋር የተቀራረበ የዝናብ መጠን ይኖራቸዋል ተብሏል፡፡

በተጨማሪም ከሚጠበቀው ከባድ ዝናብ ጋር ተያይዞ አልፎ አልፎ በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ ጎርፍ፣ የወንዞች ሙላት እና የመሬት መንሸራተት ሊኖር እንደሚችል ይጠበቃል፡፡ በመሆኑም በየአካባቢው ኅብረተሰቡና የሚመለከታቸው አካላት ከወዲሁ ጥንቃቄ እንዲያደርጉም ኢኒስቲትዩቱ ጥሪ አስተላልፏል፡፡
T.me/ethio_mereja
አሸባሪው ሸኔ መሽጎ የሚገኝባቸውን አካባቢዎች በጥናት በመለየት የመደምሰስ እርምጃ እየተወሰደ ነው-የክፍለ ጦሩ ዘመቻ ኃላፊ

አሸባሪው ሸኔ መሽጎ የሚገኝባቸውን አካባቢዎች በጥናት በመለየት መደምሰስ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን በስፍራው የተሰማራው የክፍለ ጦር ዘመቻ ኃላፊ ገለጹ፡፡

በቄለም ወለጋ ዞን በአሸባሪው ሸኔ ቡድን ላይ የማያደግም እርምጃ እየወሰደ ያለው ክፍለ ጦር የአሸባሪውን ቡድን ታጣቂዎች እግር በእግር እየተከታተለ መደምሰሱን ቀጥሏል ነው የተባለው።

የክፍለ ጦሩ ዘመቻ ኃላፊ ፥ በህዝባችን ደጀንንነት አሸባሪውን ሸኔ በማያዳግም ሁኔታ የምናጠፋበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም ሲሉ ገልፀዋል። ኃላፊው አክለውም፥ አሸባሪው ሸኔ መሽጎ የሚገኝባቸውን አካባቢዎች በጥናት በመለየት የመደምሰስ እርምጃ መወሰዱን አስታውቀዋል። የሬጅመንቱ ዘመቻ ኃላፊ በበኩላቸው፥ ሠራዊቱ ንፁሃንን ካለርህራሄ የሚጨፈጭፈውን ቡድን ለማጥፋት ትጥቁ ሳይላላ፣ ጉልበቱ ሳይዝል፣ በሞራል እና ወኔ በመንቀሳቀስ ጠላትን እየደመሰሰና ቁስለኛ እያደረገ እንደሚገኝ ነው የገለጹት፡፡

በተጨማሪም፥ በየጫካው ስንቅና ትጥቅ ሲያጓጉዝባቸው የነበሩት የሞተር ሳይክሎችና የጋማ ከብቶችን በቁጥጥር ስር አውለናል ማለታቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja