Ethiel Academy📕
106K subscribers
375 photos
10 videos
259 files
132 links
Be educated so that you can change the world. An educated mind can teach many
📥📥
@Yempire
Download Telegram
#Update

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከብሪቲሽ ካውንስል ጋር በመተባበር የእንግሊዘኛ ቋንቋ መመዘኛ ፈተና (IELTS Test) ይሰጣል።

ህዳር 15/2016 ዓ.ም ለሚሰጠው የእንግሊዘኛ ቋንቋ መመዘኛ ፈተና የኦንላይን ምዝገባ በዩኒቨርሲቲው እየተከናወነ ይገኛል፡፡

ለመመዝገብ ➧ ielts@hu.edu.et

ለበለጠ መረጃ  ➧ 0925629589

ስለፈተናው ክፍያና ሌሎች መረጃዎች በተከታዩ ሊንክ ማግኘት ይችላሉ፦
https://ethiopia.britishcouncil.org/exam/ielts/dates-fees-locations
#Update

በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም ምርጫችሁን በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ ህዳር 12/2016 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል የምትችሉ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

ከታች የተዘረዘሩ ዩኒቨርሲቲዎች የሪሚዲያል ፕሮግራም #የማያስተናግዱ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል፦

1. አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
2. አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
3. አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
4. ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
5. አርሲ ዩኒቨርሲቲ
6. ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ
#Update

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2016 የትምህርት ዘመን በመደበኛ መርሐግብር የመጀመሪያ ዲግሪ አዲስ የተመደቡ ተማሪዎች የማመልከቻ እና ወደ ዩኒቨርሲቲ ሪፖርት ማድረጊያ እንዲሁም የግል አመልካቾች የመመዝገቢያ ጊዜን አራዝሟል፡፡

በዚህም በ2016 ዓ.ም በመደበኛ የዲግሪ መርሐግብር በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁተማሪዎች በተመደባችሁበት የዩኒቨርሲቲው ካምፓስ ሪፖርት ማድረጊያ ጊዜ ታህሣሥ 09 እና 10/2016 ዓ.ም መሆኑን ተቋሙ አሳውቋል፡፡

ወደ ዩኒቨርሲቲዉ ከመሔዳችሁ በፊት በ https://portal.aau.edu.et በመግባት ➧ Freshman ➧ Student Profile የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም የግል መረጃቻችሁን እንድታሟሉ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል፡፡

በሌላ በኩል፤ በ2015 እና 2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈትናችሁ ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መስፈርት መሰረት ለከፍተኛ ትምህርት መግቢያ የመቁረጫ ነጥብ የምታሟሉ የቅድመ ምረቃ የግል አመልካቾች የመግቢያ ፈተና የማመልከቻ ቀናት ከህዳር 20 እስከ 27/2016 ዓ.ም ሲሆን የመግቢያ ፈተና ታህሣሥ 02 እና 03/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።
#Update

የ2016 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና የሚሰጥበት ጊዜ ተራዝሟል።

የመውጫ ፈተናው ከጥር 27 እስከ የካቲት 01/2016 ዓ.ም ይሰጣል ተብሎ እንደነበር አይዘነጋም።

ትምህርት ሚኒስቴር አዲስ ይፋ ባደረገው መርሐግብር ፈተናው ከየካቲት 06 እስከ 09/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ታውቋል።

ለአዲስ ተፈታኞች ሞዴል ፈተና ከጥር 27 እስከ 30/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ቲክቫህ ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘው መረጃ ያሳያል።

የተፈታኞች ዝርዝር ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ በቀጣይ ቀናት እንደሚላክም ተገልጿል።
#Update

ከየካቲት 6-9/2016 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና ለመፈተን በመጠባበቅ ላይ የምትገኙ የድጋሚ (Re-exam) ተፈታኞች በሙሉ የመፈታኛ የይለፍ-ቃል (Password) ከስር በተገለፁት አማራጮች ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

1. በምዝገባ ወቅት በሞላችሁት email በኩል፣
2. https://exam.ethernet.edu.et ላይ በመግባት የከፈላችሁበትን Transaction Number በማስገባት፣
3. ከተመደባብችሁብት የመፈተኛ ተቋም ማግኘት ትችላላችሁ።

ማሳሰቢያ፦

ለመጀመሪያ ጊዜ የመውጫ ፈተና የምትፈተኑ እጩ ተመራቂዎች የይለፍ-ቃል የምታገኙት ከምትማሩበት ወይም ከተመደባብችሁበት የመፈተኛ ተቋም ብቻ መሆኑ ተገልጿል።

ተፈታኞች የሞዴል ፈተና እስከ የካቲት 5/2016 ዓ.ም መውሰድ እንዳለባችሁ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።
#Update

" የሳይበር ወይም ሌላ ተመሳሳይ ጥቃት አልደረሰብኝም " - የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

የኤቲኤም (ATM) አገልግሎት መጀመሩን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስታወቀ።

ባንኩ ፤ ተቋርጦ የነበረው የኤቲኤም(ATM) አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ስራ የጀመረ መሆኑን  ገልጾ በቀጣም ሁሉንም ዲጂታል የባንክ አገልግሎቶች ሥራ እናስጀምራለን ብሏል።

በሌላ በኩል ባንኩ ፤ በሲስተም ችግር ምክንያት በጊዜያዊነት የተከሰተውን የአገልግሎት መስተጓጎልን ምክንያት በማድረግ ሀሰተኛ መረጃዎች በማህበራዊ ትስሥር ገፆች በመዘዋወር ላይ ይገኛሉ ብሏል።

" የተከሰተው የአገልግሎት መቋረጥ በባንኩ የውስጥ የሲስተም ችግር ነው " ያለው ባንኩ   ፤ ከባንኩ ውጭ በደረሰ የሳይበር ወይም ሌላ ተመሳሳይ ጥቃት የለም የሚሰራጨው መረጃም ሀሰት ነው ብሏል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፤ አስተማማኝ የሳይበር ደህንነት ጥበቃ እንዳለው ገልጾ ከዚህ ጋር በተያያዘ ደንበኞቹ ምንም አይነት ስጋት እንዳይገባቸው አሳስቧል።

ሌሎች ያልተጀመሩ አገልግሎቶች በሰዓታት ልዩነት ሙሉ በሙሉ በማስተካከል እንዲጀምሩ እየተሰራ መሆን አሳውቋል።

በሌላ በኩል ፤ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከባንኩ ደንበኞች ባገኘው መረጃ ከባንኩ አገልግሎት መስተጓጎል ጋር በተያያዘ የኤቲኤም ማሽን የታዘዘውን ገንዘብ ሲሰጥ እንደነበር (በአካውንታቸው ገንዘብ ለሌላቸው) ፣ በሞባይል ባንኪግም ገንዘብ በአካውንታቸው የሌላቸው ሰዎችም ሲያስተላልፉ እንደነበር ተረድቷል።

በተለይ አንዳንድ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ገንዘብ ሲያወጡ ነው።

ይህ ተከትሎ ተቋማት በትላንትናው ዕለት መጋቢት 6 2016 ዓ.ም ከኢትዮጰያ ንግድ ባንክ ኤቲ ኤም ላይ በትርፍ የሌላቸውን ገንዘብ በማወቅም ባለማወቅም ያወጡ በፍጥነት እንዲመልሱ እያሳሳቡ ይገኛሉ።
#Update

ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውና ሌሎችም የተቋሙ አካላት በካሽ የወሰዱትን እና ለሌላ ሶስተኛ ወገን ያስተላለፉትን ገንዘብ እንዲመልሱ አስጠነቀቁ።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲስተም ላይ ካጋጠመው ችግር ጋር በተያያዘ በርካቶች ገንዘብ ያለገደብ ሲያወጡና ሲያስተላልፉ ነበር።

በተለይም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና የዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አካላት ትላንት ካጋጠመው ችግር ጋር በተያያዘ ገንዘብ ወጭ ሲያደርጉና ወደ ሌላም ሲያስተላልፉ እንደነበር ተነግሯል።

ይህንን ተከትሎ የራሳቸው ያልሆነን ገንዘብ ያወጡና ያስተላለፉ እንዲመልሱ ተቋሞቻቸው እያሳሰቡ ይገኛሉ።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ባንኩ የተፈጠረዉን ችግር በተመለከተ ፦
* ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፤
* የመረጃ እና ደህንነት እንዲሁም ከሌሎች ከሚመለከታቸዉ ተቋማት ጋር በመሆን እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

በባንኩ የተፈጠረዉን የሲስተም መቋረጥ ምክንያት እንደ አጋጣሚ በመጠቀም ፦
➡️ የራሳቸው ያልሆነን ገንዘብ #በካሽ ወጭ ያደረጉና በማንኛዉም የባንኩ የድጅታል አማራጮች የተቀበሉ
➡️ ወደ 3ኛ ወገን ያስተላለፉ ተማሪዎች እና የዩንቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት የወሰዱትን እና የተላለፈላቸውም አካላት ገንዘቡን ተመላሽ እንዲያደርጉ አስጠንቅቀዋል።

ገንዘቡ ተመላሽ የሚደረገው በአቅራቢያ ባለ የባንኩ ቅርንጫፍ መሆኑን አሳውቀዋል።

ለመመለስ ፈቃደኛ ካልሆኑ ጉዳዩ የሕግ ተጠያቂነትን የሚያስከትል መሆኑንም እየገለጹ ናቸው። ገንዘብ ያወጡ ተማሪዎች እና የዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት ስም ዝርዝር እንዳላቸውም ጠቁመዋል።
#Update #CBE

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ በሴቻ ቅርንጫፍ እና በነጭ ሳር ቅርንጫፍ በሚገኙ የኤቲኣም ማሽኖች ገንዘብ ያወጡ ሰዎችን ዝርዝር ለጥፏል።

ባንኩ አያይዞም በግል ባንክ ኤቲኤም ማሽኖች ገንዘብ ወደ ቴሌብር አካውንት እና ወደ ግል ባንኮች ያስተላለፉ ሰዎችን ስም ዝርዝር እንደሚለጥፍ ገልፆ ስም ዝርዝር እስከሚለጠፍ ሳትጠብቀ ገንዘቡን #መልሱ ብሏል።
#Update

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ።

የ2016 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆኗል።

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሐምሌ 3 እስከ 5 ለማህበራዊ ሳይንስ ፤ ሐምሌ 9 እስከ 11/2016 ዓ/ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብ (Online) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት ይሰጣል።

በወረቀት ላይ የሚፈተኑ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 30-ሐምሌ 01/2016 ዓ/ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ሐምሌ 6-7/2016 ዓ/ም ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ይሆናል።

መረጃው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ነው።
#Update

የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ፈተና ከሰኔ 3-10/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ ሰኔ 9/2016 ዓ.ም የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል ስለሆነ፣ በዕለቱ ይሰጥ የነበረው ፈተና ሰኔ 11/2016 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡