የእንስቶቹ ገፅ👩‍🦰👩‍🦱👩‍🦳🧕
172 subscribers
246 photos
27 videos
2 files
28 links
ይህ ሴቶች ብቻ የሚሰባሰቡበት ቻናል ነው ስለ ራሳችን የምናወራበት ከሌሎች ጋር የምናውጋበት ልዮ የእንስቶች መድረክ ነው እንስቶችን በተመለከተ ፅሁፍ,ፎቶ,ቪድዬ,ሊንክ ካገኛችሁ ማጋራታቹሁን እንዳትረሱ
እኛው ለእኛው እንሁን👩👧
Download Telegram
የምር እህቴ ቆንጆ ናት...ልቅም ያለች ቆንጆ!!እሷ ያለችበት ወንዱ ሁሉ ሲፈዝ እኔ ራሱ ታዝቤያለሁ።አበድኩልሽ የማይላት የለም...ምድረ ጀዝባ!!!ፀባይዋን ቢያቁት ኖሮ እንኳን ማበድ ለአይን አይመኟትም ነበርኮ!!እህቴ ሲበዛ ነዝናዛ አኩራፊ ቀበጥ መንቃራ ናት መልክ ሰጥቶ ፀባይ የነሳት ነገር ናት።ደሞ በመልኳ ስትመፃደቅ ለጉድ ነው!!

እና አንድቀንላችሁ አባባ ሁኔታዋ ቢመረው በጠዋት ተነስቶ ጭቃ አቡክቶ በሰሀን አድርጎ ቤት ይገባል እውነት በሁኔታው ደንግጠናል።ጭቃው ደሞ የገንፎ አይነት ቅርፅ ነው ያለው።በዛላይ ቂቤ አምጪልኝ ብሎ እህቴን ያዝዛትና ልክ ቂቤው ሲመጣ ከመጨመሩ በፊት ዛሬ ቁርስ ይሄነው ይላል።ይሄኔ መንቃራዋ እህቴ ቦግ ብላ

አባባ ልትገለን ነው እንዴ አፈር እኮ ነው!?አለች አባባም መልሶ

ግንኮ ቂቤ አለው...ይላታል ልጅትም መልሳ

ቢሆንስ ቅቤ ጣፋጭ...አፈር ደሞቆሻሻ ነው !!አለች እንደመበሳጨት እያለች አባባም ትንሽ ሳቀና

አየሽ ቂቤ ምን ቢጥም በአፈር አይበላም!!!አንቺም የፈለገ ውብ ብትሆኚ ከቂቤ ብትጥሚ አፈር ፀባይ ካለሽ ማንም አይፈልግሽም!!ልጄ ፀባይሽን አሳምሪ አፈር በቂቤ አትሁኚ ብሎ መከራት

እህት አለም....ቁንጅናሽን ተጠቀሚበት፤ራስሽን ጠብቂ፣ ሁሌም ውብ ሁኚ፤ሁሌም ንፁህ ሁኚ፤ሲጀምር ሴት ሆኖ አለማማር እራሱ አይቻልም።ሴት ሁሌም ውብ ናት!!!ግን ደሞ አደራ የፀባይሽን ነገር የምግባርሽን ነገር የጨዋነትሽን ነገር አደራ....


ከልባም ሴት..
5🙏1
1️⃣. ኢጎ ምንድን ነው? ኢጎ ከህጻንነትሽ ጀምሮ ማህበረሰቡ የፈጠረብሽ የውሸት ማንነት ነው፡፡ይህ እብድ የሆነ አለም እብድ አድርጎ አእምሮሽን ቀርጾታል፡፡

🤎መጥላት፣ መቅናት፣ መናቅ፣መፍረድ፣ መከፋፈል፣ ዘረኛ መሆን፣ በሀብት መመካት፣ እኔ እኔ ብቻ ማለት...ወዘተ ነገሮች በውስጥሽ ተሰግስገዋል፡፡አንዳንዴ ጊዜ ፡ "እንዴት እንደዚህ አይነት መጥፎ ሰው ሆንኩኝ?" ትያለሽ፡፡መጥፎ የሆንሽው ግን አንቺ ሳትሆኚ ኢጎሽ ነው፡፡

ይህ በማህበረሰቡ ከህጻንነትሽ ጀምሮ በውስጥሽ የተከማቸ ኮተት ነው፡፡አራግፊው፡፡አንቺ ውብ፣ ድንቅ፣ ደግ፣ ተወዳጅ፣ አስገራሚ፣ ባለብዙ በረከት፣ ሰው አክባሪ፣ ርህሩህ፣ የማትነካ፣ የማትዳሰስ even የማትሞትና በፈጣሪ አምሳል የተፈጠረሽ መንፈሳዊ ፍጥረት ነሽ፡፡ይህንን እኔ ልነግርሽ አይገባኝም፡፡ይህንን ስታነቢው ራስሽ ታውቂዋለሽ፡፡ውስጥሽም ይነግርሻል፡፡
+
🔢. ጓደኞችሽን አሳይኝና ማንነትሽን አሳይሻለው፡፡ከአህያ ጋር የዋለች ጊደር አመድ ቅማ ትመጣለች፡፡አመድ ከሚያስቅሙ ሰዎች ጋር የምትውል ሴትም እንደዛው አመዳም ናት፡፡ምርጥ ከሆኑ ሰዎች ጋር ብቻ ጊዜሽን አሳልፊ፡፡መጥፎ ሴት ብትሆኚም እንኳን በምርጥነታቸው ትሸነፊያለሽ፡፡ጓደኞችሽን በጥንቃቄ ምረጪ፡፡
+
🔢. ሀሳብሽን ከገንዘብሽ በላይ ተቆጣጠሪው፡፡አእምሮሽ የአሉታዊ ሀሳቦች ጭፈራ ቤት ከሆነ ሙሉ ህይወትሽ ገደል ይገባል፡፡በልብሽ ማዕከል የሚነግሰው ሀሳብ ውሎ አድሮ የህይወትሽ እውነታ ይሆናል፡፡እናም በጥንቃቄ ጠብቂው፡፡ሁልጊዜ አዎንታዊ ሀሳብን ብቻ አስቢ፡፡ለመሆኑ አሁን ምን እያሰብሽ  ነው?
+
🔢 ሰዎችን አፍቅሪ፡፡ከልብሽ አክብሪ፡፡ምን ይሉኛል ብለሽ ግን ምንም ነገር አታድርጊ፡፡ሰዎች የሚሉትን ነገር አያጡም፡፡እንደ ክርስቶስ በውሃ ላይ ብትራመጂ ራሱ ዋና ስለማትችል ነው ማለታቸው አይቀርም፡፡ራስሽ ላይ ብቻ አተኩሪ፡፡አጭር ለሆነችው ህይወት ሰው ምን ይለኛል ብሎ መጨነቅ መሸወድ ነው፡፡
+
🔢. ቁሳቁስ ደስታ አይሰጥሽም፡፡አሁን ደስታ የራቀሽ  ብራንድ ነገር ስሌለሽ ከመሠለሽ ይቅርታ፡፡አለም ውስጥ ያለው ቁሳቁስ ሁሉ የአንቺ ቢሆንም እውነተኛ ደስታን አታገኚምም፡፡አዎ ብራንድ ነገር ስትገዢው ሊያሳብድሽ ይችላል፡፡ግን አንድ ቀን ባደረ ቁጥር የገዛሽው ነገር  የሚሰጥሽ ደስታ እየተሸረሸረ ይመጣል፡፡እስቲ ከዚህ ቀደም ቋምጥሽ የገዛሻቸውን ነገሮች አስቢ፡፡

⭐️እነዛ ተንሰፍስፈሽ የገዛሻቸው ነገሮች ዛሬ ያንን የቀደመ ደስታሽን ይሰጡሻል? በፍጹም፡፡ዛሬም ለመግዛት የምትንሰፈሰፊያቸው ነገሮች እንደዛው ናቸው፡፡ከገዛሻቸው በኋላ ይደብሩሻል፡፡ይህ መጥፎ ጨዋታ ነው፡፡ደስታሽ ያለው በውስጥሽ ነው፡፡ከፍያ የለውም፡፡ነጻ ነው፡፡ጥሩ ሰው መሆን ብቻ ደስታ ይሰጥሻል፡፡አንቺ ሰው እንዲያደርግልሽ የምትፈልጊውን ነገር ለሰው ስታደርጊ ደስታ ወደ አንቺ ይመጣል፡፡
+
🔢. ሁሉም ነገር ሱስ ነው፡፡ህይወትሽን መጥፎ የሚያደርገው መጥፎ ሱስ ነው፡፡መጥፎ ሱስን ግደይው፡፡መቃም፣ ማጨስ፣ መስከር፣ መዋሸት፣ መቅናት፣ መስነፍ...ማንኛው ወደኋላ የሚጎቱትሽን ነገሮች ከህይወትሽ ነቀለሽ ጣያቸው፡፡በምትካቸው በጎ ሱስ ፈጠሪ፡፡ያ መሄድ ወደ ምትፈልጊበት አለም ይወስድሻል፡፡


✅️@Enmare1988
✅️✅️
@Enmare1988
ስሚኝ

ሴት ልጅ ባሳለፈችው ታሪክ ስለሆነ የምትመዘነው ታሪክሽን አሳምረሽ ጻፊው
ወደፊት ምትቆጪበትን ነገር   ዛሬ አታድርጊ
😔😔😊                                         

ከየህልም........
5
Forwarded from እንማር
እራሷን ልታ'ጠፋ ነበር ግን ታሪክ ተቀየረ እንዴት ?

የቡናው ግብዣ
☕️🍂

ህይወት ድክም ብሏታል ። ከቀን ወደቀን ኑሮዋ ከድጡ ወደ ማጡ እየተለወጠ ነው ። ምንም ነገር ስልችት ፣ ትክት ፣ ምርር ብሏታል ። ለፋች ጣረች ጋረች ። ግንስ ? ህይወት እንደ ዶሮ ለሌሎች እንቁላል ስትጥል ለሷ ግን ኩስ ብቻ ሆኗል ድርሻዋ ።

💠እንቅልፍ ሚያሳጣ ጭንቀትና ዝለት ብቻ አልነበረም የገጠማት :- አጥንትንና ጅማትን የሚለያይ ስቃይና ዝገት ጭምር እንጂ ። ማንም :- በሃዊ ቦታ ካልሆነ የስብራቷ ጥልቀት አይገባውም ። ክህደት ፣ የሚወዱትን በሞት ማጣት ፣ ከከፍታ ተምዘግዝጎ መከስከስ ፣ የካቡት መናድ ፣ ድግምጋሚ ኪሳራ .... ምንድነው ያልገጠማት ፈተና ? ሰው እንዴት ሁሉም ነገር ጥምምም ፍርስርስ ጭልምልም ይልበታል ? የሃዊ ኑሮ ይሄ ከሆነ ሰነበተ ።

💠 የትኛውም ሰው መቼም አላደርገውም ሲል የነበረውን ነገር ሲያደርገው ሊገኝ ይችላል ። ለብዙዎች የህይወት ስንቅ ተስፋ የነበረችው ሃዊ አሁን እራሷ ተስፋ ቆረጠች ። ያተገባውን መንገድ መረጠች ሞ'ቷን

ሃዊ ከቤቷ ከመውጣቷ በፊት ማንም ይየው ማንም የመጨረሻ ኑዛዜዋን ፣ብሶቷን በዲያሪዋ ላይ ችክችክ አድርጋ ጽፋ ነበር የወጣችው ። ወስናለች ። መ'ኖር በቅቷታል ። ፈራ ተባ ብትልም ሃሞቷ ግን ኮስተር ብሏል ።

💠የመጨረሻ መፍጨርጨሪያዋ ሱቋ ነበር ። እሱንም በኪሳራ ተመታ ባለችበት ወቅት አይታውም ሰምታውም ማታውቀው ግብር ተቆልሎ መቶባት ንግድ ፍቃዷን ለማዘጋት ነበር አወጣጧ ።' ባይዘጋስ ቢቀር ? ' ብላ ነበር ግን ደሞ የተዝረከረከ ነገር ለሌሎች ትታ ማለፍ አልፈለገችም ። ጥንቅቅ ስትር ብላ ሞ'ቷን ልትጋፈጠው ወሰነች ። እንደሁልግዜው ማለዳዋ ' ሄራን የጀበና ቡና ' ጎራ ብላ ቡና አዛ ቡናዋ እስኪመጣ ከተቀመጠችበት መስኮት በስተውጪ ያለውን ትርምስ በግዴለሽነት ታስተውል ጀመር ።

🔹ቡናው ሲቀርብላት እንኳን አላስተዋለችም ነበር ። ቡናውን ለመጠጣት ትኩረቷን ወደ ቡናው አድርጋ አንድ ማንኪያ ስኳር አድርጋ ስታማስል ግዜ አንድ ብጫቂ ወረቀት ከቡናው አጠገብ አስተዋለች ። ምን ይላል ?

💠 🔻 ' ከሞ'ት ስለታደክሽኝ ከልቤ አመሰግንሻለሁ ። ዛሬ ነገ እያልኩኝ ለምስጋና ዘገየሁ ። ላታስታውሺኝ ትችይ ይሆናል ። ዛሬ በህይወት ለመኖሬ ግን ምክኒያት ሆነሽልኛል ። እውነትሽን ነበር :- የማያልፍ ችግር የለም :- ደስታም ቢሆን ! ከጨለምተኝነትና ተስፋ ከመቁረጥ ወጥቼ የህይወት መነጽሬን እንዳስተካክል ስላደረክሽኝ ምን ልክፈልሽ ? ህይወት ከነ ግሳንግሷ ውብ ናት ብለሺኝ ነበር ትዝ ይልሽ ይሆን ? ልክ ነበርሽ ህይወት ውብ ናት ልክ እንዳንቺ ፈገግታ ። በቻልኩ ግዜ ሁሉ ያኔ ያየሁትን ፈገግታሽን ሳይ ይበልጥ መኖር ያምረኛል ! የውስጥሽ ሰላም ይጋባብኛል ።

🔹 ቢከፋም ቢለማም ህይወቴን እንድወደው ስላረክሽኝ በድጋሚ አመሰግንሻለሁ :- የቡናው ሂሳብ ተከፍሏል !' ሃዊ ግራ ገባት ማነው የጻፈው ?

ባለ ቡናዋን ስምረትን ጠራቻት :- ' ስምሩ ይሄን ወረቀት ማነው የጻፈው ? ' ስምረት ግራ ተጋባች ! እኔንጃ ሃዊዬ ግን አንድ ልጅ ያንቺን ቡና ሂሳብ ከፍሎልሽ ወቷል ።
ማን ይሆን ?

ብታወጣ ብታወርድ ወረቀቱን የጻፈውን ሰው ማንነት ልታስታውስ አልቻለችም ። ' በዚህ ልክ ህይወቱ ላይ ትንሽም ቢሆን ተጽእኖ ያደረኩበት ሰው ይኖራል ? ምን አድርጌ ? እንዴትስ ሆኖ ?

💠ድንገት ቅልል ነገር አላት ! ንግድ ፍቃዷን አዘግታ አድካሚ ውሎ ውላ ወደቤቷ ገባች ። ከራሷ ጋር ቀጠሮ ይዛ ነበር ። መኖሯን ወደ አለመኖር ልትቀይር ። ውዝግብ አለች ። በሃሳቧ መግፋት አልቻለችም ። ማነው ይሄ ሰው ? ምን አድርጌለት ነው ? ከጨለማ ህይወቱ ወደ ብርሃን ተለውጦ ነው ? ወይስ ድራማ ነው ? ጭራሽ ደሞ የህይወቱ መቀየር ምክኒያት እኔው ነኝ ? እኮ እንዴት ?

ህይወቷን ለመደምደም አሁንም እንደቆረጠች ነው ። ግን ደሞ የዚህን ሰው ማንነት ማወቅ ፈለገች ። እስከዛሬስ ኖሬ የለ ? ታግሼ የዚህን ሰው ማንነት ማወቅ ከቻልኩ እስኪ ልሞክር ። ለምን እየከነከነኝ ል'ሙት ?

እናም ሃዊ በጠዋት ወደ ' ሄራን የጀበና ቡና ' አቀናች ። ማነው ጠዋት ጠዋት የኔን ፈገግታ ለማየት ሚታደመው ? ጥያቄ ፈጥሮባታል ። እንደሁልግዜው የሄራን የጀበና ቡና በተስተናጋጅ ጢም ብሏል ። ምናልባት ያንን ሰው ለማየት አይኗ ተቅበዘበዘ ። ግን ደግሞ አንድም ልታስታውሰው የቻለችው ሰው የለም ። ምንም አይነት ምልክትም አላየችም ። ለሶስት ሰአታት ቁጭ አለች ። ምንም አዲስ ነገር አላየችም ። ተነስታ ወደ ቤቷ ሄደች ። ውስጧ ግን የዚህን ሰው ማንነት ለማወቅ ጓጉቷል ።

መሸ 🌙 🌌 🌠 💤
ደግሞም ነጋ 🧡☀️🌄 🌞 🌅

ድጋሚ መሸ 🌙 ደግሞም ነጋ 🌞 ለውጥ የለም ። ሰውዬው የውሃ ሽታ ሆነ

በሶስተኛው ቀን ማልዳ ወደ ሄራን የጀበና ቡና ሳታስበው እግሯ አመራ :- አይኖቿ ያንን ትእንግርት የሆነባትን ጽሁፍ የጻፈላትን ቡና ጋባዧን ለማየት እንደተቅበዘበዙ ናቸው ። ግን በቃ የመስቀል ወፍ ነገር ነው ሰውዬው ማለት ነው ።

የጅል ስራ እየሰራች እንደሆነ ውስጧ ነገራት ። ሂሳብ ከፍላ ልትወጣ ስምረትን ጠራቻት ። ' ስምሩ ሂሳብ !' ስምረት ፍልቅልቅ ብላ ' ተከፍሏል !' አለቻት ። ' ማን ከፈለ ? ' ስምረት ዞር ብላ ከጀርባዋ ወዳለው ጠረጴዛ እየጠቆመች ' እሱ ነው የከፈለው ውይ በስመአብ ወዴት ተሰለበ ? ፊት ለፊት የነበረው ልጅ እኮ ነበር ! ወቷል ማለት ነው ? '
💠ሃዊ ተነስታ ስምረት ወደ ጠቆመቻት ጠረጴዛ አመራች ።ጠረጴዛው ላይ:- በሶፍት ላይ የተጻፈ ጽሁፍ ነበር ። ' ማን እንደሆንኩ ለማወቅ እየሞከርሽ እንደሆነ አውቃለሁ ። ግን መጀመሪያ ያየሁሽ ቦታ :- ህይወቴን የቀየረልኝን ላንቺ ትንሽ ቢመስልም ለኔ ግን Turning point የሆነልኝን ነገር ያደረግሽልኝ ቦታ እዛ ነው ላገኝሽ ምፈልገው

💠 በአስር ደቂቃ ውስጥ ሱቅሽ የነበረበት ሞል አካባቢ ታገኚኛለሽ ሃዊ !'

ቀጣዪ ክፍለ ይቀጥላል አንብበው ከወደዱት ግን 👍👍 ቶሎ እንዲቀጥል

✉️@Enmare1988
✉️@Enmare1988
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
7
Forwarded from ክንፎች🧚‍♂ (frehiwot)
A woman whose mood improved with a book , a poem, a song or acup of coffe is not defeated by anyone; even life loses with her.

Khalil Gibran
💯3
Forwarded from ሳዶር ♰ (χαμένος♰)
ብቻ ጠንከር በይ 🙏.....
3
Forwarded from ልባም ሴት 😍
የማይሆንሽ ቦታ ላይ ለመቆየት በመረጥሽ ቁጥር መለየት እየከበደሽ ይመጣል። ነገሮች በጊዜ ሂደት እንደምታስቢያቸው ስለሚስተካከሉ አይደለም .... ሸክሙን እየተለማመድሽው ስለምትመጪ ነው።

መላመድ ደህንነት የሚሰጥሽ አይነት የውሸት ስሜትን ይሰጥሻል። ከስንት አንዴ የሚደረጉልሽን ጥሩ ነገሮች እንደ ማስረጃ እየቆጠርሽ እራስሽን ታታያለሽ። እንደገና ከዜሮ ከመጀመር ይኼንኑ ማስቀጠል ይሻላል ትያለሽ።

ብዙ በቆየሽ ቁጥር መጀመሪያ አካባቢ ከግንኙነቱ ትፈልጊ የነበረውን ነገር እየተውሽ በየቀኑ ምቾትሽን እና ሰላምሽን እየቆረስሽ አሳልፈሽ መስጠት ትጀምሪያለሽ። ከዛም የሆነ ቀን እውነታውን ታያለሽ .... መለያየት ማለት ህይወትሽን ለሁለት መሰንጠቅ ማለት እንደሆነ .... ምክንያቱም መጀመሪያም ህይወትሽን የገነባሽው ቀስ በቀስ እያፈረሰሽ በሚሄድ ነገር ላይ ነውና።

ነገር ግን ወደራስሽም የምትመለሽው በዚህ አጋጣሚ ነው። ለመለያየት መወሰን ውድቀትን ማወጅ አይደለምና። በመጨረሻም ራስሽን ማድመጥ መጀመርሽን ማሳያ ነው።

ህመምሽን ከመለማመድ ብዛት "ፍቅር" እያልሽ መጥራትሽን የምታቆሚበት ነው። ህይወትሽ መተንፈሻ መጠነኛ ቦታ እንደሚፈልግ የተረዳሽበት፣ ልብሽ የተረጋጋ ነገር እንደሚፈልግ ያወቅሽበት እና ነገሽ ያንቺን መጎዳት መሰረት ማድረግ እንደማይገባው የወሰንሽበት ስለሚሆን።

መለያየቱ የሚያም ቢሆንም እንኳን ባለሽበት የመቆየትን ያህል ስቃይ አይኖረውም !!

ለማንኛውም በሰላም ዋሉ !!

~

... ብቻ ነገሩ ውስብስብ ነው !!

~

ለአንዱ ፆታ የተፃፈው ለሌላኛውም ይሰራል 🤞

~

ባሻ ዘብሔረ ጠቅላይ ግምጃ ቤት

★★★ ኦሮማይ ★★★

🧘‍♀️🧘🧘‍♂️

© Abby Junior
"ፍቅረኛውን የገደለው... በፍቅረኛው ተያዘ!"

ፊልም የሚመስል እውነተኛ የድሬዳዋ ፖሊስ ገድል!

ፍቅረኛውን ገድሎና አልጋ ዉስጥ ቀብሮ ለዓመታት ተሰውሮ የነበረውን አረመኔ ነፍሰ ገዳይ፤ በዘመናዊ የቴክኖሎጂ እና የስነ-ልቦና ጥበብ ተጠቅማ በቁጥጥር ስር ያዋለችው ጀግናዋ ዋና ሳጅን ስንዱ ካሳሁን የመነጋገሪያ ርዕስ ሆናለች።

ይህች የድሬዳዋ ፖሊስ መርማሪ፤ ገዳዩን በሶሻል ሚዲያ ካገኘችው በኋላ ራሷን እንደ "ፍቅረኛ ፈላጊ ነጋዴ" በማስተዋወቅ ለወራት የፍቅር ቃላትን እየወረወረችና ፎቶዎችን እየላከች ልቡን አሸነፈችው።

ወንጀለኛው የፍቅር ጓደኛ አገኘሁ ብሎ ሲመጣ በህግ ካቴና አጠለቀችለት።

ይህ ታሪክ በቅርቡ በአባይ ቲቪ "ካቴና" ፕሮግራም ላይ የቀረበ ሲሆን፤ ፀሐፊው ዋና ሳጅን ማሙሽ አዳፍሬ፤ "ይህች ጀግና ልትሾምና ልትሸለም ይገባል" ሲሉ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።

የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን እና ከንቲባ ይህንን የሴቶችን ብቃት ያሳየ ድንቅ ስራ እውቅና እንዲሰጡ ጥሪ ቀርቧል።

ጌጡ ተመስገን
2
Forwarded from ኖኅ Book Delivery (ኖኀ Book Delivery)
ገና ለገና እድሜ ሄደ ብዬ  -:
ገና ለገና ሴት ልጅ ነኝ ግዜ አይራራልኝም ብዬ -:
ገና ለገና ቤተሰቦቼን ፍላጎት ለማሟላት -:
ገና ለገና ቆማ ቀረች ላለመባል -:
ገና ለገና ባል አለኝ ለማለት -:
ገና ለገና ባገባው አይቸግረኝም ብዬ ፦

ልቤ ያላረፈበትን ሰው፣ብዙ  የማልወደውን ሰው ፣ ሳላገኘው ስቀር ናፍቆት የማይወዘውዘኝን ሰው.. መውደዱ ያልተጋባብኝን ሰው ሲጠፋ ቅር ቅር የማይለኝን ሰው

    ለምን አገባለሁ ???

ዘገየሁ ብሎ በድፍረት መወሰን ለደስታ አልባ ቀናት  ለዱካካም ቀኖች ይዳርጋል !!

አልፈራም የኔ ቀን ይመጣል !!!
       ©  Adhanom Mitiku
🛥🛥🛥
"ማንበብ ፋሽን ነው።"🧐
Join us @noahbookdelivery
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔥3
ክብርሽን ጠብቂ፡

ወንድ ልጅ በቀላሉ ያገኘውን ነገር በቀላሉ የመርሳት ዝንባሌ አለው

ዛሬ ስጦታ ፣ አበባና ቸኮሌት ሊኖር ይችላል። እነዚህ ሁሉ ያልፋሉ፤ አንቺ ግን ከራስሽ ጋር ለዘላለም ትኖሪያለሽ። ራስሽን ዝቅ አታድርጊ።

የካቲት 14 (Valentine's Day) እንደመሆኑ መጠን፣ ብዙ ሴቶች የፍቅር መግለጫ አድርገው "ክብራቸውን" (ድንግልናቸውን) ለወንዶች የመስጠት ዝንባሌ ሊኖራቸው ይችላል።


ይህ ውሳኔ ከስሜታዊነት በላይ የሆነና ነገ ላይ ትልቅ ተጽዕኖ ሊኖረው የሚችል በመሆኑ

🌹 ለራስሽ የምትሰጪው ስጦታ

ይህ ቀን የፍቅር ቀን ነው፤ ፍቅር ደግሞ ከራስ ይጀምራል። ለአንድ ሰው መስጠት የምትችዪው ትልቁ ስጦታ "አካልሽ" ሳይሆን "ክብርሽና ታማኝነትሽ" ነው።


ጊዜያዊ ስሜትና ዘላቂ ዋጋ፡

የአንድ ቀን የፍቅር ድባብና ስሜት እንዲያሸንፍሽ አትፍቀጂ። ስሜት እንደ ደመና ጠፊ ነው፤ ክብርሽ ግን የማንነትሽ መገለጫና አንዴ ከሄደ የማይመለስ ውድ ሀብትሽ ነው።



ፍቅር በስጦታ አይለካም፡

አንድ ወንድ በእውነት የሚያፈቅርሽ ከሆነ፣ ላንቺ ያለው ክብር አካልሽን ከመፈለግ በላይ መሆን አለበት። "ካላደረግሽው አታፈቅሪኝም" የሚል ግፊት ካለ፣ ያ ፍቅር ሳይሆን የፍላጎት መገበያያ ነው።


የነገዋ አንቺ፡ ዛሬ የምታደርጊው ነገር ነገ ስታስቢው ኩራት ወይስ ጸጸት እንደሚሰጥሽ ቆም ብለሽ አስቢ። ለትክክለኛው ሰው፣ በትክክለኛው ጊዜና ቦታ (በትዳር) የሚጠበቅ ስጦታ ሁልጊዜም የበለጠ ጣፋጭ ነው።


💡 ማስታወስ የሚገቡሽ ነጥቦች

"ሰውነታችሁ  የፈጣሪ ቤተ መቅደስ ነው" እንደሚባለው፣ ይሄ መቅደስ ለማንም በሩን የሚከፍት ሳይሆን ልዩ ጥበቃ የሚደረግለት መሆን አለበት።

የግፊት ሰለባ አትሁኚ፡

ጓደኞቼ አደረጉት ወይም አለም እያደረገው ነው በሚል ውሳኔ አትሳሳቢ። አንቺ ልዩ ነሽ፣ ዋጋሽም ውድ ነው።

ክብርሽን ጠብቂ፡

ወንድ ልጅ በቀላሉ ያገኘውን ነገር በቀላሉ የመርሳት ዝንባሌ አለው። በብዙ ትግልና በክብር ያገኘሽን ሴት ግን ዕድሜ ልኩን ሲያከብርሽ ይኖራል።

ራስሽን ውደጂ

ዛሬ ስጦታ፣ አበባና ቸኮሌት ሊኖር ይችላል። እነዚህ ሁሉ ያልፋሉ፤ አንቺ ግን ከራስሽ ጋር ለዘላለም ትኖሪያለሽ። ራስሽን ዝቅ አታድርጊ።


ማጠቃለያ

ውድ እህቴ፣ የዛሬው ደስታ የነገው ቁስል እንዳይሆን ተጠንቀቂ። እውነተኛ ፍቅር "ትዕግስት" አለው። የሚወድሽ ሰው ክብርሽን ይጠብቃል እንጂ አይቀማሽም። ዛሬን በንጽህና እና በክብር በማሳለፍ ለራስሽ ትልቅ ዋጋ ስጪ።

ይህ ቀን ያልፋል፤ ማንነትሽ ግን ይቀጥላል።

ቆም ብለሽ አስቢ!
3🔥1
Forwarded from እንማር
(ሁሌ ቫለንታይን ሲደርስ ትዝ የሚለኝ ታሪክ። ሶስት አመት ሞላው ይሄ ታሪክ ትንሽ ነው ኤዲት ያደረኳት እንጂ እውነት ናት... ዝለቁ በሉ..)

💠ካፈቀርኩት አመት ከሞላኝ ሰው ጋር በስልክ እያወራን ነው... በጣም ናፍቆኝ ረዥም ሰዓት አወራን። በመሃል ሳት ብሎኝ ያወራሁት ነገር ግን ህይወቴን እስከማጨለም አደረሰኝ። ከንግግራችን መሃል ይህን ሃሳብ አነሳሁለት

<ታውቃለህ ወጣትነቴን ቢያንስ በፎቶ ባስቀምጠው ደስ ይለኛል>

<ታድያ ብዙ ፎቶዎች አሉሽ እኮ>

💠<አይ እንደሱ አይነት ፎቶ ሳይሆን አለ አይደል ሰውነቴን... ይሄ መሸብሸብ ያልደረሰበት ... ሸንተረር ያላየው ሰውነቴን አንስቼ ባስቀምጥ ደስ ይለኛል። በኋላ ልጅ እና እርጅና ሲመጣ መልሼ የማላገኘውን ሰውነቴን...>

<ለሱ አታስቢ እኔ ጋር ... >

<አንተ ጋር ምን?... ንገረኝ... አንተ ጋር ምን?>

💠ከሳምንት በፊት የፍቅረኛሞች ቀን <ከቤት ወጥቼ ማደር አይፈቀድልኝም> ስለው <የታደሉ ፍቅረኛሞች ተቃቅፈው ይተኛሉ... እኔ ግን በምወዳት ልጅ ምክንያት እዚሁ አልጋዬ ላይ ተኮራምቼ...> ምናምን እያለ አለቃቀሰ። የምር አሳዝኖኛል። እወደዋለሁ። ይሄኔ ሌላ ሴት ቢያፈቅር እኮ አብራው ታድር ነበር እኔን በመምረጡ እና በማፍቀሩ ብቻ እየተቀጣ ነው... ብዬ አሰብኩ

<እሺ ምን ላድርግልህ?>

<በቃ እያሰብኩሽ ልተኛ ቢያንስ ፎቶሽን ላኪልኝ>

💠በጣም አሰብኩበት። አምነዋለው። እወደዋለው። አሳዘነኝ። በቃ ለዚህ እየቀጣሁት ላለሁት ሰው መካሻ ይሆነው ዘንድ እርቃን ፎቶዬን ልኬለት ነበር። አሁን እሱ ትዝ አለኝ። ግን ሲነጋ ወዲያው አጠፋዋለሁ ብሎኝ ስለነበር ያልጠበኩት የአፍ ወለምታ ስለሆነብኝ በጣም ደነገጥኩ

<አላጠፋኸውም እንዴ? >

<አጥፍቼዋለሁ በእውነት... ማለቴ... ሃሳቤ ውስጥ አንቺ አለሽ ለማለት ነው>

💠 ብዙም ሳንቆይ... የፍቅረኛሞች ቀን ላይ እሱ እንዳለው እና እኔ እንዳሰብኩት የላኩለትን ፎቶ አቅፎ በናፍቆት ተኮራምቶ ሳይሆን ... ከሌላኛዋ ሴት ጭን ስር ሲዋኝ እንዳደረ ሰማሁ። በጣም ተጣላን። በጣም አዘንኩ። በጣም ተከፋሁ። ራሴን እየረገምኩ ቆየሁ። ተለያየን።

በኋላ ላይ ግን ያ አሁን ሳይሆን ወደፊት... ካረጀሁ እና ከወለድኩ በኋላ ማየት የምፈልገው ገላዬ አሁን ላይ በየሶሻልሚዲያው ሲዘዋወር ተመለከትኩት። በእኔ እና በሱ መሃል ብቻ የነበረው የመሠለኝ ገላዬ የሁሉም ሆነ። ሁሉም አየው። በማመኔ ተፀፀትኩ። ስንቴ ነው የሚገለኝ? ስንቴ ነው የምሞተው? እስከመቼ ነው የሚያመኝ? የማመን ዋጋው እንዴት ነው? ምን ያስከፍለናል?

🔹ከሁሉም ያመመኝ ግን እንደኔ ሴት የሆኑት ሴቶች እንኳን በገላዬ ሲዘባበቱበት ሳይ ነው... ከሁሉም ነገር የከበደኝ እንደኔ በአንድ ወቅት አፍቅረው አምነው የነበሩ ሴቶች አሁን የኔን ሃጥያት ሲገልጡ እና ሲፈርዱብኝ ማየቴ ነው። ከሁሉም ህመሙ በራሳቸው ሲደርስ.. እንኳን ማየት ማሰብ የሚከብዳቸው ሴቶች ዛሬ የእኔን ነውር ሲቀባበሉት ሳይ ነው። ራሴን በራሴ ስቀጣው ቆይቻለሁ... በመላኬ ስሳቀቅም ስፀፀትም ቆይቻለሁ... አሁን ግን የመሰሎቼን ሳቅ እና ፌዝ መቋቋም አልቻልኩም።

💠ከደረሰብኝም በደል ካደረሰብኝም ሰው በላይ እኒህ መሰሎቼ ደጋግመው ገደሉኝ። እንዴት ብለው ፈረዱብኝ።

Fantu emu
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
1
Forwarded from እንማር
ዘማነቱ አይኑ ላይ ሲንቀለቀል ብዙ ቀን አይቼዋለሁ!! ከኔ ጋ ሆኖ የሌላ ሴት ዳሌ አንገቱን ጠምዝዞ ሲመለከት ተናግሬው አላቅም።እውነት ለመናገር ወድጄው ነበር... ከዚህ አመሉ ሌላ ሁሉ ነገሩ ሚወደድ ነው ።አለባበስ ያውቅበታል ፤ወሬ ያምርበታል፤ በተለይ ሲስቅ ቀልብ ይሰርቃል ፤ስራ ሲባል ልቡ ይሸፍታል ፤የስራ ሰው ነው።ለዚህ ነው ድክመቱን እያወቅኩ አንድ አመት ያፈቀርኩት.....

አንድ ቀን ላገባሽ እፈልጋለሁ ሲል እራት እየበላን ጠየቀኝ ...ለምን እንደሆን እንጃ ደስታ ቀደመኝ፤ሳቅ ሳቅ አለኝ፤ እዛው ትንሽዬ የቀለበት ፕሮግራም አድርገን ለመጋባት ቀን ቆርጠን ተለያየን።Chachaአእምሮዬ አልፈጠንሽም???ቆይ አስቢበት?? ተረጋጊ በደንብ አጥኚው...እያለ እየወተወተኝ ቆየሁ ብሰማውም አልተቀበልኩት።እያብሰለሰልኩ ሳምንታት ተቆጥረው የቀጠረኝ ሆቴል ልቤ እየፈራ ዘንጬ ተገኘሁ... ጓደኞቼን ጨምሮ ጥቂት ሰወች ሆቴል ውስጥ ተሰብስበዋል። ግማሹ ወይን ሌላው ቢራ በእጁ አንቆ የኔን መምጣት ከበር ይጠባበቃል። እኔም እግሬ እየሰነፈብኝ ቢሆንም የግዴን እየታሸው ወደ ሆቴሉ ገባው.

.. chachaሆቴሉ በጭብጨባ እና በሳቅ ተሞላ ከፊት ለፊቴ በቀይ በአበባ የተንቆጠቆጠው ልዩ ቦታ ላይ ነጭ የለበሰው ፍቅረኛዬ ቆሟል ልክ ወደሱ እንደተጠጋሁ ግን ተንበርክኮ የቀለበት ሳጥኑን እንደከፈተው ድንገት ከኋላ አንድ የሴት ድምፅ ተሰማ....

እሺ እንዳትዪው!!! የሚል ነበር ሁላችንም ደንግጠን ታዳሚ ወደተሰበሰበበት ጀርባ አየን።የቆመው ሰው ሁሉ እየከፈተ በዊልቸር የምትሄድ ..ፊቷ በማድያት ተጠብሶ ያደፈ ሺቲ የለበሰች ጥቁር ሻርብ የተከናነበች ሴት አጠገባችን ደርሳ ቆመች።chachaሁሉም በያለበት ረጭ ብሎ ክፍሉ ኦና የሆነ ያህል ሆኗል። ሁላችንም የምንጠብቀው የሷን አፍ ነው.....

የሰማንያ ባሌ ነው!!!chachaፊርማችን እንኳን አልተቀደደም።አንድ ሴት ልጅ ወልጄለታለሁ ...ወጣትነቴን ተጠቅሞ ተጫውቶብኝ መታመሜን ሲያውቅ ጥሎኝ ጠፋ!!ብከሰው እጁ ረጅም ነው...ዝም ብዬ ባየው ልጄን ማኖርበት እንኳ ሳንቲም አይሰጠኝም። chachaከኩላሊት ህመሜ ጋ እየታገልኩ ገፍትሮ ጥሎኝ በህመሜ ላይ ህመም የሰጠኝ እሱ ነው!!!ሰባራ አርጎ አጨልሞኝ ከድቶኝ የሄደው እሱ ነው!!!ሁሉንም ነገር እከታተላለሁ አንቺም እንዳትሸወጂ ይኸው ፍረዱኝ!! ፍረዱኝኝ በልጅ አምላክክክክ !!!እንባዋ መንታ ሆኖ እየወረደ ስታለቅስ አብረን አለቀስን አጅሬ አንገቱን ሰብሮ እንደተንበረከከ ነው

በጥፊ ልምታው?? ልርገጠው ???ልንከሰው??በኬኩ ቢላ ወጋግቼ ልግደለው??የቱ ቅጣት የዚህን ሰው ክፋት ይመልሳል??የቱ ፍርድ እቺን ምስኪን ቀና ያደርጋታል ??እንጃ!!

ለመሆኑ...."ታገቢኛለሽ ወይ?"ብሎ ፊትለፊትሽ የተንበረከከውን ወንድ ታቂዋለሽ ወይ??ሀላፊነት ሚሰማው ሚያከብርሽ እንደሴትነትሽ በወንድነቱ አክብሮሽ የሚያኖርሽ መሆኑን ታምኚበታለሽ ወይ??እሺ ብላለች ከመባሉ በፊት ጣትሽ ላይ ቀለበት ከመግባቱ በፊት አንቺ እና እሱ ተግባብታችኋል ወይ ታውቂዋለሽ ወይ????

እየውልሽ እህቴ..."አንዳንድ ክፋቶች ምድር ላይ ያሉ ቅጣቶች አይመጥኗቸውም!!ትዳር ከማያውቁት ጋ ትዳር ሳይሆን ረመጥ ነው
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
4🔥2
ሴት በወንድ ሕይወት ውስጥ ሦስት መልክ አላት፦ እናት፣ እህትና ሚስት። እናት መጀመሪያው ናት፣ እህት መንገዱ ናት፣ ሚስት ደግሞ መድረሻው ናት። ሴት ማለት የሕይወት መዝሙር፣ የወንድ ልጅ የልብ ትርታና የነፍሱ መስታወት ናት።

መራራው እውነት  የሰው ልጅ ሴትን እንደ "ዕቃ" ወይም እንደ "ንብረት" አድርጎ መመልከቱ ነው። ወንድ ሴትን ሊገዛትና ሊቆጣጠራት ይሞክራል፣ ነገር ግን ሴት ማለት እንደ ንፋስ ነጻ የሆነች ነፍስ ናት። ትልቁ ግጭት የሚፈጠረው ወንድ የሴትን "አካል" እንጂ "ነፍስ" መውደድ ሲያቅተው ነው። ሴት የአበባ ዘር ናት፤ በፍቅርና በክብር ካልተያዘች ትጠወልጋለች። ነገር ግን ስትፈካ ዓለምን በመዓዛዋ ትሞላለች። የሴት ስቃይ የዓለም ሁሉ ስቃይ ነው፤ ምክንያቱም ዓለም የምትኖረው በእሷ ትዕግስትና መስዋዕትነት ውስጥ ነውና።

📕 ርዕስ፦የጥበብ መንገድ
✍🏻 ደራሲ፦ካህሊል ጂብራን
🔥42
Forwarded from Bemnet Library
አንዲት ሴት ለማትወደው ሰው በወርቅና በሀብት ስትሸጥ አየሁ፤ ቤተሰቦቿም "ይህ ለደስታሽ ነው" አሏት። እሷ ግን በመጋረጃው ውስጥ ሆና በዝምታ ታለቅስ ነበር።በዚህ መካከል ትልቁ ሐዘን የሰውን ልጅ ልብ በገንዘብ መመዘናቸው ነው። ፍቅር ነጻ መሆን ሲገባው፣ በወርቅ ሰንሰለት ታስሮ ወደ መኝታ ክፍል ይወሰዳል። ያንን ሰው ስታቅፈው፣ የምታቅፈው ስጋውን እንጂ ነፍሱን አይደለም።

ይህ "ሕጋዊ ግልሙትና" ይባላል፤ ስሙ ግን "ጋብቻ" ተብሎ ይከበራል። ነፍስህ ከሌላ ጋር ሆና፣ ስጋህ ግን ከሌላ ጋር እንዲሆን መገደድ ከገሃነም በላይ የሚያም ስቃይ ነው።ሕብረተሰቡ "ክብር  ይለዋል፣ እኔ ግን "ሞት" እለዋለሁ። ስንት ንጹህ ልቦች በዚህ በወግና በልማድ ሰይፍ ተሰልበዋል? ስንት ህልሞችስ በሀብታሞች እግር ስር ተረግጠዋል? ይህ ግፍ በየቀኑ በቤቶቻችሁ ውስጥ ይፈጸማል፤ እናንተ ግን በዝምታ ትመለከታላችሁ። የሰው ልጅ ትልቁ ውድቀት፣ ፍቅርን ከመንፈስ አውጥቶ ወደ ንግድ የቀየረበት ዕለት ነው።

📕 ርዕስ፦የተሰበሩ ክንፎች
✍🏻 ደራሲ፦ካህሊል ጂብራን

📚 @Bemnet_Library
1🔥1
Forwarded from ካሊድ አቅሉ
ዐይን የሚሰማው ንግግር
(ካሊድ አቅሉ)

" ካላየነው በቀር የማንረዳው ብዙ ንግግር አለ ። "
----------------------------

ከአለቃዬ ጋር በመስሪያ ቤት Cafe ውስጥ ሻይ ቡና እያልን ነው በጫወታ መሀል ስላለፈው የአፍላ ወጣትነት ዘመንዋ በቁጭት አነሳች ፣ " እኔ እኮ ቃሊ ሚቆጨኝ ያኔ መንገድ ስስት ተመለሺ ብሎ ሚይዘኝ አንድ የቤተሰብ እንዴት አይኖርም ? ሁሉም እንደፈቀድሽ ብለው እሳት ውስጥ ስገባ ዳር ይዘው አዩኝ እናት ,አባት, ወንድም,እህት ጎረቤት .... አንድም አንቺ ልጅ ተመለሽ አይልም ? "

" እነሱን ወቀስሽ እንጂ ያኔ ቢመክሩሽስ ከጥፋት መንገድ እንደምትመለሺ እርግጠኛ አትሁኚ በወጣትነት ያውም ደሞ አፍላው ሰዓት ከምክር በላይ ዱላ ይቀለናል" አልኳት መብሰልሰልዋን ለመቀነስ በሚጥር ድምፅ . . . . " ልክ ነህ ደግሞም ካላየነው በቀር የማንረዳው ብዙ ንግግር አለ ፤ ወጣትነቴን ተጠቅሞ አንድ ልጅ አስታቅፎኝ ጥሎኝ ሄደ ፈጣሪዬን አመሰግነዋለው ጥርሴን ነክሼ ልጄን አሳደግኩ በማታ ፕሮግራም ማስተርሴን ተማርኩ ግን አሁንም ከሱ ጋር ያባከንኩት የመሸነጋገል ዘመን እንደ እግር እሳት ያንገበግበኛል !" ጥርስዋን አሁንም በቁጭት ስትነክስ "አይ አሁንም እኮ አረፈደም አንቺ እንደው ገና ነሽ " አልኳት ስላሳዎቹን ወደ መጨረስ ያለችዋን ሰብሊን በሙሉ አይኔ እያየው . . . . . . " እሱስ አዎ ግን ቀትር ላይ ያለው ፀሐይና አመሻሽ ላይ ምትጠልቀው ፀሐይ እኩል ብርሃን አይሰጡም " አለችኝ ለዘብ ብላ " ያንቺ ግዴታ በነቃሽ ሰዓት ያገኘሻትን ብርሃን በአግባብ መጠቀም ነው ። " ብዬ ከአፎችዋ መልስ ጠበኩ ሁለታችንም አቀርቅረን በትዝታ በየፈርጃችን ነጎድን . . . . .

@kalidakelu