የእንስቶቹ ገፅ👩‍🦰👩‍🦱👩‍🦳🧕
172 subscribers
246 photos
27 videos
2 files
28 links
ይህ ሴቶች ብቻ የሚሰባሰቡበት ቻናል ነው ስለ ራሳችን የምናወራበት ከሌሎች ጋር የምናውጋበት ልዮ የእንስቶች መድረክ ነው እንስቶችን በተመለከተ ፅሁፍ,ፎቶ,ቪድዬ,ሊንክ ካገኛችሁ ማጋራታቹሁን እንዳትረሱ
እኛው ለእኛው እንሁን👩👧
Download Telegram
## ...ምን አይነት ወንድ ይመችሻል?

የሰው መለኪያው ብዙ ነው። የኔ ልኬት ለአንተ፤ የ'ሷ ልኬት ላንቺ አይሰራም። የሁላችንም መስፈርት ለየቅል ነው። ነገር ግን አንድ የማይካድ ሃቅ አለ; የሁላችንም ልኬት ከአኗኗር ስርዓታችን(ባህል) እና ከምንኖርበት ማህበረሰብ የተቀዳ ነው።

የምንኖርበት ማህበረሰብ ለዘመናት በኖረበት ባህል ለወንድ እና ለሴት የራሱን ትርጉም ሰጥቷል። ወንድ እንዲህ ነው፤ ሴት እንዲህ ናት ከሚለው ተፈጥሯዊ እና ሳይንሳዊ ትንታኔ ባሻገር ባህል ወንድን ወንድ፤ ሴትን ሴት የሚልበት የራሱ መለኪያ አለው። በባህል ውስጥ ስትኖር ተፈጥሮ ወንድ ስላረገችህ ወንድ አትሆንም፤ ተፈጥሮ ሴት ስላረገችሽም ሴት አትሆኚም።

እናም የሰው ልጅ አብሮ መኖር ከጀመረበት የስልጣኔ ማግስት ባህል በክፍለ ዘመናት ውስጥ ሲያብብ ሲከስም ኖሯል። በነዚህ ክፍለ ዘመናት ውስጥ ባህል ሴትን ገፍቷል፣ ሴት ተጨቁናለች፣ ሴት ተበድላለች– የማይካድ ሃቅ ነው። ዛሬ ግን ብዙ ለውጥ አለ–የሴትነት ሞጋቾች በየቦታው አሉ። ችግር ቢኖርም ግን ካለፉት ዘመናት አንፃር ለሴት ልጅ ቀን ወጣላት ብል ውሸት አይሆንም። መፍትሄ የሚሰጣት ብታጣ እንኳ ዛሬ ሴት ልጅ ህመሟን እና ጉዳቷን የሚያይላት አታጣም።

ግን የወንዱስ?... በመነሻዬ ላይ 'ምን አይነት ወንድ ይመችሻል?' የሚል ጥያቄ አንስቻለሁ። ቆፍጣና፣ ጠንካራ፣ ደፋር፣ ቆራጥ እና ኮስታራ ወንድ– የሁሉም ሴቶች ምርጫ ነው ማለት ባልደፍርም ብዙ ሴቶች የሚማረኩት በእንዲህ አይነት ወንድ መሆኑን አስተውያለሁ። ይህ የወንድነት መስፈርት በተፈጥሮ የተሰጠ የወንድ ባህሪ ሳይሆን ማህበረሰቡ ወንድነትን የሚለካበት ሚዛን ነው።

አንቺም እኔም የማህበረሰቡ አካል ነን፤ ይህ ማለት ወንዱም ሴቱም ወንድነትን የሚለካው በቆፍጣናው ሚዛን ነው ማለት ነው። ግን ወንድ ሰው ነው አይደል? ወንድም እንዳንቺ ይደክመዋል፣ ይከፋዋል፣ ይሰበራል፣ ይወድቃል፣ ይሸነፋል! ግን ማህበረሰቡ ወንድ እንዲደክም አልፈቀደለትም፣ እንዲከፋው አልተፈቀደም፣ ስብራት እና መውደቅ ለወንድ ነውር ነው። ስለዚህ ቆፍጠን ለማለት ሲል ወንድ ድካሙን ችሎ፣ መከፋቱን ደብቆ፣ ስብራቱን ሸፍኖ፣ ላለመውደቅ እየተሳቀቀ እና ከሽንፈት እያመለጠ ወንድ ይሆናል።

የታፈኑ ደምፆች ጩኸት ረብሻ እና የተሸፈኑ ቁስሎች እያመረቀዙ ወንድነትን ይመርዙታል። ያልፈሰሱ እምባዎች አሲድ ሆነው ወደውስጥ ሲፈሱ የወንድነትን ውስጥ ያኮማትሩታል። በዚህ ማህበረሰብ ውስጥ ወንድ ስሜት አልባ አውሬ ፍጥረት ነው–ማረፍ የማይፈቀድለት፣ ማልቀስም መሳቅም የማይችል፣ ጨካኝ ፍጥረት!

ቢያንስ አንቺ ጋር እንኳን እንዲያርፍ፣ እንዲሸነፍ፣ እና እንዲወድቅ ካልፈቀድሽለት፤ ሁሌም ባልሽ ቆፍጣና እና የማህበረሰቡን ወንድ እንዲሆን የምትፈልጊ ከሆነ፤ አውሬ አግብተሽ ነው የምትኖሪው! ከቆፍጣናነት ጀርባ፤ ከወንድነት ባሻገር ብዙ ያልታዩ ሰባራ መስታወቶች አሉ–ከ'ሱ አልፈው የነካቸውን ሁሉ የሚያቆስሉ!

...አስተውይ!!!

~ "ምን አይነት ወንድ ይመችሻል?"©️

✍️ዮናታን በጋሻው (ቀዳማዊ
)
👍2🔥2🙏1👌1
የሴትልጅ ቁንጅና ምንድነው?
_______

(ውበትና ደም-ግባትስ?)

"ቁንጅና ምንድነው ሰዎች አስረዱኝ
እኔ እሷን ወድጄ ታምሜያለሁኝ...
ውበትና ቁንጅናሺ፣ ይማርካል ለሚያይሺ.."

- ድምፃዊ ማህሙድ አህመድ

በየዘመኑ "የሴት ልጅ ውበት" የሚባለውን አስተሳሰብና መስፈርት ማን ፈጠረው? "ቆንጆ" ሴት ከቆንጆ ሰው በምን ትለያለች? ሴቶች በ"ሽንጥና ዳሌሽ ሲታዩ..." ዓይነት መስፈርቶች እንዲለኩ የበየነላቸው ማነው?

ወንዶች ሴቶችን የሚስሉበት መንገድ ከስሜት ጋር የተያያዘ ለምን ሆነ? ከወሲባዊ መስህብ አሊያም ከመራባትና ከእናትነት አስተሳሰቦች ውጭ ሊታሰብ የሚችል የሴት ልጅ ሰብዓዊና ማኅበራዊ ፋይዳ ከየማኅበረሰቡ አንጎል የተነነው በምን ምክንያት ነው?

ውበት ምንድነው? ደርባባነትን ከሴት ልጅ ለምን እንድንጠብቅ ሆንን? በዘመናት ውስጥ የተቸራቸውን ማኅበራዊ ተክለሰብዕናና የተሰጣቸውን ሚና ለመጫወት እምቢ ያሉ ሴቶች ዕጣፈንታ ምንድን ነበር? አሁንስ ምንድነው?

ወንዶች በጥቅሉ ለሴቶች ያለን ዝንባሌ በጎችንና ፍየሎችን ሽንጣቸውን ለክተን፣ ጥርሳቸውን ፈልቅቀን፣ ሸሆናቸውን መትረን ለመግዛት ከምንሄድበት መንገድ ብዙም ያልተለየ ሆኖ የሚገኘው በምን የተነሳ ነው? ተፈጥሯዊ ነው? ወይስ ማኅበራዊ?

የሴቶች ተፈጥሯዊ ሰዋዊ አገልግሎት ምንድነው? ብለን ነው የምናስበው? ለምን?

የሴትን ልጅ አካላት ዕርቃን እያወጡ የተሳሉ አያሌ ክላሲካልና ሞደርን የጥበብ ሥራዎች (ሥዕሎች፣ ቅርፃቅርፆች፣ ስነፅሑፎች፣ ሙዚቃዎች፣ ወዘተ.) ለምን በየዓለሙ በሰዎች ዘንድ ተወዳጅ ሆኑ?

የሰውልጅ ሴትን ልጅ ከsensual pleasure ውጭ ለማሰብ ያልቻለበት አብይ ምክንያቱ ምንድነው? ሴቶችስ ራሳቸውን ከመኳኳልና ከማጊያጌጥ፣ ሽንጥና ዳሌያቸውን ከማጉላት፣ ፀጉራቸውን ከመሾረብና በአልባሳት ከመሸለም ውጭ ያለውን ጥልቅ የራስ ማንነታቸውን ለመፈለግ ብዙ ዝንባሌ የማያሳዩት ለምንድነው?

በሴትነት ውስጥ ከማኅበራዊው መስፈሪያ ሚዛን የማፈንገጥ ዋጋው ምን ያህል ነው? ይህች ዓለም የማን ዓለም ነች?

እውን It's a man's man's world እንደሚባለው.. ዓለማችን የወንዶች ብቻ ዓለም ነች? ከሆነች ሴቶች የተነጠቀ ሙሉ የሰውነት ክብራቸውንና ዋጋቸውን ለማስመለስ ምን ያድርጉ?

የፆታ አስተሳሰባችን በምን በምን ነገሮቻችን ውስጥ ሥር እንደሰደደ፣ እስከ ምን ከፍታ እንዳሻቀበና እንዴትስ ተብሎ እንደተድበሰበሰና እንደተሸነገለ ልብ ብለን አስተውለነዋል?

ሴትነት ምንድነው? ወንድነትስ? ውበትስ? የሴት ልጅ ውበት ምንድነው? ሴትን ልጅ ያለ ጭንና ባቷ ለማሰብ ፈቃደኝነቱ ያለው ወንድ ከመቶ ስንት ፐርሰንት ነው? ራሷን ከቀሚሷ ውጭ አድርጋ ማሰብ የምትችልስ ሴት ከመቶ መሐል ስንት ትገኛለች?

የነዳጅ ዘይትን የሚተኩ በርከት ያሉ የኃይል አማራጭ ቴክኖሎጂ ተገኝተዋል በዘመናዊዋ ዓለማችን። ግን የዔለም ኢንዱስትሪ ሁሉ ከነዳጅ ጋር የተያያዘ ነው። ዲዛይኑ፣ ሸቀጡ፣ ንግዱ፣ ኢኮኖሚው፣ ቴክኖሎጂው፣ መኪናው፣ መርከቡ፣ አውሮፕላኑ... ሁሉ ከነዳጅ ጋር የተሳሰረ ነው። በዚህ የተነሳ ዓለም የሚያውቀውንና ህልውናውን የመሠረተበትን ኋላቀሩን ነዳጅ ዘይት መተው አይፈልግም። የሴት ልጅ ውበትስ ተመሣሣይ ነገር ይኖረው ይሆን?

በዓለም ሁሉ "የሴቶችን ውበት" መሠረት አድርገው የሚመረቱ ምርቶች፣ ዲዛይኖች፣ ፅሑፎች፣ ሳይንሶች፣ ፊልሞች፣ ኢንደስትሪዎችና ማኅበራዊ አወቃቀሮች... ባንዴ ተንደው እውነተኛ የሴቶችን ሙሉ ሰውነትና ክብር ወዳረጋገጠ ዘመናዊ አስተሳሰብ መሻገር ይችላሉ? የሚቻል ነው? ሴቶች ቂጥና ፊታቸው እየታየ የሚመዘኑበት ዘመን እስኪያበቃስ ስንት ዓመት ይፈጃል?

ይህ የናዖሚ ዎልፍ መፅሐፍ ላለፉት 3ሺህ ዓመታት የተቀነቀኑ የስነውበት ፍልስፍናዎችን፣ ሳይንሶችንና አስተሳሰቦችን እጅግ ጥልቅ በሆነ መንገድ ይቃኛል። አጥብቆ ይሄሳል። እና የውበትን ትርጉም እንድንፈትሽ ያስገድዳል።

ሴቶች ከወንዶች የውበት መስፈርት ራሳቸውን ማላቀቅ አለባቸው፣ ነፃ መውጣት አለባቸው ትለናለች።

በምጥን ፈገግታዋና በመርገፍ ቀሚሷ ዓለምን የምታማልለው ሞናሊዛ የኋላቀሩ ዘመን ማስረጃ ሆና ተቀድዳ የምትጣልበት፣ የፒካሶና የሌሎች በዓለም የተደነቁ የእርቃን ሴቶች ሥዕሎችና ኃውልቶች ተጠራርገው ወደ ቆሻሻ ቅርጫት የሚጣሉበት፣ የሴት ልጅን ሉዓላዊነት ያከበረ፣ ኮርማዊውን የወንዶች ዓለም የገረሰሰ፣ አዲስ የሴቶች ነፃነት ዘመን መበሠር አለበት ትላለች።

ከዚህ በፊት "ዘ ሴክስ ኦፍ ቲንግስ" የሚል አስገራሚ መሠል ይዘት ያለው በአንዲት ጀርመናዊት-እንግሊዛዊት ሪሰርቸር ዶክተር የተፃፈ አንድ ዳጎስ ያለ መፅሐፍ አግኝቼ ስገረምና የያዝኳቸውን ሁሉ የሴትልጅ አስተሳሰቦች ስሞግት ቆይቼ ነበር።

ይህን መፅሐፍ ካነበብኩ በኋላ ደግሞ ብርቱካን ከንፈርሽ፣ ብርንዶ ትንፋሽሽ፣ የዘንባባ ማር ይመስላል ፍቅርሽ፣ ፅጌረዳ ስላንቺ ልጎዳ፣ ሐር ይመስላል ፀጉርሽ፣ ሎሚ ተረከዝሽ፣ ስልታዊ ውዝዋዜሽ፣ ዓይናፋርነትሽ፣ ችቦ አይሞላም ወገብሽ፣ ካንቺ ጋር አድሬ ሲነጋ ልሙት፣ እና አንቺን ያለውን በቴስታ ጥርሱን🤩... የመሣሰሉትን የምወዳቸውን የሙዚቃ ስንኞች ከአዕምሮዬ ለማጥፋት ምን ዓይነት ላጲስ መጠቀም እንዳለብኝ በማሰላሰል ላይ ነኝ🤓!!!

ይህች ደራሲና ተመራማሪ፣ ሶስተኛው የፌሚኒዝም አብዮት ተብሎ የሚጠራውን አስተሳሰብ ያፈለቀችና ለዓለም ያስተዋወቀች ጉምቱ ምሁር ስለመሆኗ ከተለያዩ ዜና መወድሶች ለመረዳት ችዬአለሁ።

ለማንኛውም ሃሳቦቿ የያዝካቸውን የሴት ልጅ ውበት ኮተቶች ሁሉ ያስጥሉሃል። ግን ፍራቻዬ ያለንን አስጥላን... በምትኩ የምትሰጠን ውበት ምን ዓይነት እንደሆነ ደራሲዋም ራሷ በትክክል ያወቀችው አልመሠለኝም።

ሽንጥና ዳሌሽ ሲታዩን ትተን... ወደ ምን እንሻገር? ውብ የምንላትን ሴት ከየት እናግኛት? ከስንደዶ አፍንጫና ከማር ከንፈር ውጭ ያለችዋ ቆንጆ ሴት ማነች? ከወዴትስ ትገኛለች? እውን አለችስ ወይ በዓለም ላይ? ሴቶቹ ራሳቸውስ ይቀበሏታል?

ደራሲዋ የምትሰብከን ሴቶች ከሙክትነትና ከጌጥነት አሊያም ከስሜት ማስተንፈሻነት የወረደ የወንዶች አስተሳሰብ ነፃ የሚወጡባት ዓለምስ እውን በዚህ የቅርብ ዘመን ትውልድ እውን ሆና እናያት ይሆን? ...

የወንዶች አሽኮርማሚነት፣ እና የሴቶች ተሽኮርማሚነት አብቅቶ፣ ማንም ማንንም የማያሽኮረምምባትን ዓለም የምናየው መቼ ነው? መቼ ነው ያቺ የፍፃሜ (ዋንጫ) ቀን መምጫዋ? ምን ምልክትስ እንጠብቅ?

ወንድሜ (እና እህቴ🤩)... በበኩሌ ጥይቴን ጨርሼያለሁ!

በዚሁ ባበቃስ?

መልካም ጊዜ!

©Assef Hailu
👍2👌1🤝1
እንግዳ አቀባበል በናሚቢያ

በናሚቢያ የሚገኙ ኦቫሂምባና ኦቫዚምባ የተባሉት ጎሳዎች በሰሜናዊው የናሚቢያ ክፍል ይኖራሉ ።
ከ50,000 በላይ ብዛት ያላቸው እነዚህ ጎሳዎች ቀላ ያለ የቆዳ ቀለም እንዲኖራቸው የተለያዩ የተፈጥሮ ተዋፅኦዎችን በመጠቀም ከውበትም በተጨማሪ ራሳቸውን ከፀሀይና ከተባዮች ይከላከላሉ ።
ታድያ እነዚህ ጎሳዎች ለየት ያለ የእንግዳ አቀባበል አላቸው ።
እንግዳ ወደ ቤታቸው ሲመጣ አባወራው ለእንግዳው ያለውን አክብሮት የሚያሳየው ሚስቱን ለዛች ምሽት በስጦታነት በማበርከት ነው ።አባወራውም ሌላ ክፍል ውስጥ ይተኛል ፤ሌላ ክፍል እንኳን ባይኖር ውጪ መተኛት የግድ ይለዋል ።
በባህሉ መሰረት ሚስቲቱ አስተያየት የመስጠት መብት የላትም ።ከእንግዳው ጋር አላድርም ፤ አሻፈረኝ ካለች እንኳን አንድ ክፍል ውስጥ ማደር ይኖርባታል ።
😭3🤔1
የትዳር አጋር ስትመርጡ

💕ልቧን አይተህ ምረጥ።

💕ጡንቻውን ሳይሆን አዕምሮውን አይተሽ ምረጭ።

💕ለዝሙት የሚያሯሩጧችሁን ሳይሆን ለዓላማና ሕልማችሁ የሚያተጏችሁን ምረጡ።

💕ዋጋ ለምትሰጡት ነገር ዋጋ የሚሰጥሏችሁን ምረጡ።

💕ጠበቃ የሚያቆሙባችሁን ሳይሆን ጠበቃ የሚቆሙላችሁን ምረጡ።

💕ተፎካካሪ ሳሆን አማካሪያችሁ፣ጭንቀት ሳይሆን ሰላም የሚሰጧችሁን ምረጡ።

💕ታናሽ የሚያደርጏችሁን ሳይሆን፣ታላቅነታችሁን ለማውጣት የሚተጉላችሁን ምረጡ።

💕በጀርባችሁ የሚማከሩባችሁን ሳይሆን ፊትለፊት የሚጋፈጡላችሁን ምረጡ።

💕ሳትግባቡ ወደ ቤተሰብ፣ጏደኛ እና ሶስተኛ ወገን የሚወስዷችሁ ሳይሆን ወደ ፈጣሪ የሚፀልዩላችሁን ምረጡ።

💕ሞግዚት ሳይሆን እናት የምትሆንልህን ምረጥ።

💕አራቢሽ ሳይሆን አባትሽ የሚሆንልሽን ምረጭ።

💕ምንግዜም ከእያንዳንዱ ታላቅ ወንድ እና ሴት  ጀርባ ታላቅ ሴት እና ወንድ እንዳሉ አትርሱ።

በህይወታችሁ ልትረዱ የሚገባው በየትኛውም ግንኙነት ውስጥ ነፃ ፈቃድ የሚባል ትልቅ ነገር እንዳለ አለመርሳት ነው።

ፈጣሪ እንኳን ፈጥሮ ግደታ እኔን ምረጡ አላለም ።ታዳ ፈጣሪ ፈጥሮ እንድናመልከው ፣እንድናፈቅረው ያላሰ‍ገደደን እንደት እኛ ወደን እና ወልደን ነፃ ፈቃድ አናከብርም?!

በፍቅር እንጅ በትግል አትመኑ።ከፍቅር ክብር ይቀድማልና ፍቅር እየሰጡ ክብራችሁን ከሚያሳጡ ሰዎች ራቁ።



🕊️መሄድ ከፈለጉ ... ፍቀዱላቸው

🕊️ሌላ ሰው ከመረጡ… ፍቀዱላቸው

🕊️ካልደገፏችሁ… ፍቀዱላቸው

🕊️ካልጋበዟችሁ… ፍቀዱላቸው

🕊️ቢጠሏችሁም… ፍቀዱላቸው

ሌሎች ሰዎችን ለመቆጣጠር ጉልበታችሁን ማባከን አቁሙ።

እናንተ  የምትችሉት ቀጣይ ምን ማድረግ እንዳለባችሁ፣መምረጥ ብቻ ነው።

ሕይወት ምንም ገደብ የላትም፤እኛ ካስቀመጥናቸው ገደቦች በስተቀር።

ስትመርጧቸው የሚመርጧችሁን አክብሩ።

ትዳርን ለዘለአለም ከሚያስቡ እንጅ ለወለምዘለም ሃሳባቸው ካደረጉ ሰዎች ራቁ።

 

እግዚአብሔር ማስተዋልን ጥበብን እውቀትን ከፍቅር ጋር ይስጠን!

አሜን🙏
🙏6👍2
"የሴት ልጅ ክብር በትጥቅ ትግልም በአደባባይ ጩኸትም አይመጣም! በቤቱ ሚስቱ የገፋችው፣ ፍቅረኛው ያቀለለችው ወንድ ሺ ሕግ፣ ሚሊዮን መመሪያ ቢወጣ ሴትን ያከብራል ማለት ዘበት ነው።"
"አባትና እናቱ ሲደባደቡና ባለመከባበር አፍ ሲካፈቱ እያየ ያደገ ሕጻን ባባቱ ሲወጣ እያዩ፣ 'ልጅ የፍቅር ገመድ ነው' ይሉናል። በጥላቻና በመናናቅ ትዳር ውስጥ የበቀለ ሕጻን የፍቅር ሳይሆን የማሕበረሰቡን ሕግና ባሕል ማነቂያ ገመድ ነው! ብዙዎች 'ዘመናዊነት' ፍዳቸውን የሚያበላቸውን ሴቶች ታዘብ እስቲ፣ መነሻቸው ፍቅሩን አሟጥጦ እየተቋሰለ የኖረ ግድ የለሽ ቤተሰብ ነው። ካልተፋቀርን ምን አወላለደን! ልጅ አሻንጉሊት አይደለም! ቃላችንን ማፅናት ሲያቅተን፣ ሥጋ ለበስ ሐውልት ቤታችን ውስጥ ተክለን ልናመልክ ይዳዳናል! 'ልጅ ወለድን' ብለን አንመፃደቅ። በልጆቻችን እናት ካልተደሰትን የልጆቻችንን ግማሽ አንወደውም ማለት ነው። እናቶች ቢሆኑ 'ለልጄ ስል እንዲህ ሆንኩ፣ ለልጄ ስል ተፈለጥኩ…'፤ እስቲ መጀመሪያ ለእኛ ለባሎቻቸው ሲሉ ይፈለጡ፣ ይቆረጡ። የልጅሽ ግማሽ አካል እኛ ባሎች አይደለንም እንዴ? እነዚህ ኮተታም ዘፈኖችና ፊልሞች በቀጥታም በተዘዋዋሪ የወንድን ልክስክስነት ለሴቶቻችን ሲሰብኩ፣ 'ታዲያ ለማን ብለሽ ነው የምትታመኚው' እያሉ ለመደዴነት ሚስታችንን፣ እህታችንን እያዘጋጇት መሆኑን ዘግይቶ ነው የሚገባን።"

"ዙቤይዳ፣ ሚስቴን አከሸፏት"
✍️በአሌክስ አብርሃም
❤‍🔥3
Forwarded from 💙..ነጠብጣብ 🧩 (Yodi)
እናቴን እወዳታለሁ ቃል የማይገድበው ስንኝ የማይቋጥረው ፍቅር እንዲህ ያለው ፍቅር ነው ከሷ ያለኝ
ከሷ ጋ ያለኝን ብጥቅጣቂ ሰአቶች በጥቂት በጥቂት እየቆነጠስኩ ነው ለልቤ ጆሮዎች የማደርሰው በእርሷ የጠራ የነፍሷ ልብ ውስጥ እንደ ልእልት መንገሴን ሳስብ ለከት አልባ ከገፅ የተሻገረ የልብ ደስታ ይለኳኩፈኛል
ጠንካራ ናት ልባም የኔ የሴትነት መለኪያ እርሷ ናት ዝቅ ስትል እንደታናሽ እህት ሲያሻኝ እንደጓደኛ ደግሞ እንደ እናት በጉያዋ ወሽቃ ገበናዬን ትሰውርልኛለች ውይ እናቴ ባትኖር ታስብለኛለች
የእናቴ ሴትነት ሴትነቴን ያስወድደኛል🤍🤍
ፈትለወርቅ
የህይወትን ምንነት የሚያጠቃልል አጭር ታሪክ ይህ ነው።

ልጅ አባቷን ጠየቀችው፦“ምርጥና ደግ ሰዎች ለምንድነው ቶሎ የሚሞቱት?”

አባትም ጥያቄዋን በጥያቄ መለሰ፦“የአትክልት ስፍራ ውስጥ ብትሆኚ የትኛውን አበባ ነበር የምትመርጪው?”
👍31
Forwarded from 💙..ነጠብጣብ 🧩 (𝖊𝓶𝓾𝔂𝓮𝓮 💙)
የሁልጊዜ ጸሎትሽ ምንድን ነዉ? አልኳት

እ..የምወደዉ ሰዉ አታሳጣኝ🩵

ለምን...?

ፍቅር እጅግ ኃያል ነገር ነዉ፨ሰዉን ስትወጅ የምታዉቂዉ አካባቢ:የምትኖሪበት ቦታና ዙሪያሽ ያሉ ሰዎች አኗኗርሽ ብቻ ብዙ ዉጪኛዉ ዓለምሽ ላይ የተቀየረ ነገር ሳይኖር እንኳን ሕይወት የተለየ ትርጉም ትሰጥሻለች፨

በየትኛዉም ፈርጅ ልትረጅዉ ትችያለሽ (ቤተሰብ:ፍቅረኛ:ጎደኞችሽ ....)ግን ፍቅር ልብሽ ዉስጥ ሲኖር የኑረትን ዳገት ትጓዥ ዘንዳ ትበረቻለሽ፨የሆነ ስታስቢዉ ፈገግ የምትይበት:መዉደድሽን ለመግለጽ የምትጨነቂለት፡የመኖርሽ ምክንያት ስትታደይ ቆንጆ ነዉ፨

ልክ ነሽ፨ግን ዓለማችን አሁን ታስፈራለች፨ብዙ ክህደቶችና የሚያሳዝኑ መለያየትችን ትሰሚያለሽ፨የወድሽዉ ሲጎዳሽ ድጋሚ ላለመሰበር ፈሪ ትሆኚና ያቅትሻል ታዲያ እንዴት...?

ታዉቂያለሽ ይህ የሕይወት መራር እዉነታ ነዉ፨የወደድሽዉ ሁሉ አይወድሽም፨የምትፈልጊዉን ሁሉም አታገኚም፨አንዳንዴ አግኝተሽወ እንኳን እንደ መሻትሽ አይሆንም፨

መኖር ቅኔ ነዉ፨በዚህ ሁሉ መኅል ግን ለእኔ ልብን ከሁለም የተሻለ የሚጎዳት በፍርሃት ታስራ ከመዉደድ ስትጎድል ነዉ፨ለእኔ የልብ ሥራ ሰዉን መዉደድ ነዉ፨ያንን ስታቆም ትበድናለች፨በወደዱት ከመጎዳት ይልቅ ከፍቅር የቀዘቀዘች ልብ ታስፈራኛለች፨የማይሞቀዉ የማይበርደዉ ሰዉ መሆን ያሳስበኛል፨ይህን ስልሽ ልቤ ወዳ የሄደችበት ቦታ ሁሉ ሳንካ አልገጠማትም ሳይሆን ግና ዛሬም ቢሆን
በኑሮዬ የምወደዉ ልቤን የሚያሞቃት ሰዉ አታሳጣኝ ነዉ ጸሎቴ አለችኝ፨

✍️𝓮𝓶𝓾𝔂𝓮𝓮


https://t.me/yeesua_queen
🔥1
.....ከሰዎች ጠብቀሽ ላታገኚው ትችያለሽ፣ በወዳጆችሽ መባል ፈልገሽ አልተባልሽም ይሆናል፣ የተለየ ቦታ በሰጠሻቸው ሰዎች እንዲሁ የተለየ ስፍራ አልተሰጠሽም ይሆናል፡፡ ነገር ግን አንድ ነገር አስታውሺ የትም ሳትሔጂ፣ ማንንም ሳትመስዪ፣ ከማንም ሳትወዳጂ፣ ማንም ሳይኖርሽ፣ ምንም ሳትጨምሪ እንዲሁ ውብ ነሽ። ውበትሽም የግድ በሰዎች ሊነገርና ሊደነቅ አይገባም። ዛሬ ውብ እንደሆንሽ የነገረሽ ሰው ነገም ውብ ስለመሆንሽ እንደሚመሰክር እርግጠኛ መሆን አትችይም፡፡ አዳማቂ የማይፈልገው ውበትሽ ከትምህርት ደረጃሽ የመጣ አይደለም፣ ከስራሽ የመጣ አይደለም፣ ከቤተሰቦችሽ የመጣ አይደለም፣ ከጓደኞችሽ የመጣ አይደለም፡፡ የውበትሽ ምንጭ የአምላክሽ ልጅ መሆንሽ ነው፤ የውበትሽ መነሻ ሴትነትሽ፣ አንቺነትሽና ጥልቁ ማንነትሽ ነው።

ልንገርሸ ውብ ነሽ!
እስካከበርሽው ድረስ ሴት በመሆንሽ ብቻ ቆንጆ ነሽ፤ አሁን ያለሽበት ስፍራ በመገኘትሽ ብቻ ብርቱ ነሽ፣ እንዳቅምሽ ስለተንቀሳቀስሽ ብቻ ጠንካራ ሴት ነሽ፡፡ አለም የሚያደንቅልሽን ሳይሆን በአምላክሽ መንፈስ የተቃኘውን ውስጣዊ ውበትን የሚያዩ፣ የስብዕናሽን ጥልቀት የሚመረምሩ፣ እንዲሁ አይተው የሚማረኩብሽ ሰዎች እስኪከቡሽ ድረስ ውበትሽን ለእራስ ተናገሪ፣ ጥንካሬሽን ደጋግመሽ ለእራስሽ መስክሪ። የሚረዱሽን መምረጥ፣ የማይረዱሽንም የመተው ምርጫ አለሽ። ማንም እንዲያምንብሽ ዝቅ ብሎ የመለመን ግዴታ የለብሽም፡፡ አንደኛው ውበትሽ ክብርሽ እንደሆነ አስታውሺ፡፡ ለእራስሽ ብርታትና ሃይል መሆን ትችያለሽ፤ ለእራስሽ የሰጠሽውን ቦታ በመቀየር ብቻ አካባቢሽንና የተሰጠሽን ቦታ መቀየር ትችያለሽ።


..መልካም ቀን🙏🙏

.... @Meklite21
👍2🔥1
"ስሜቶችሽን በመጠቀም ዘና ስትይ በሕይወትሽ ውስጥ እንዲኖሩ ማትፈልግያቸው ነገሮችን ጉልበት መንጠቅ ትችያለሽ . . . ሳቅ ሕይወትን ይቀይራል. .
መጥፎ ስሜት ሲሰማሽ ፀጉርሽን እየነጨሽ ለመጥፎ ስሜት ጉልበት አትጨምሪለት. . እንደሱ ካደረግሽ ፈረሱን የበለጠ ብስጭት ወዳለበት ቦታ እየጋለብሽ ነው. . እኔ ምልሽ መጥፎ ስሜቶችን የመጥላት አይደለም. .. መልካም ስሜቶችን ሆን ብሎ የመምረጥ ነው. . እናም ደግሞ ደጋግሞ መምረጥ. ..መጥፎ ስሜቶች ልትቋቋሚያቸው ስትሞክሪ ይጨምራሉ. . የትኛውንም ነገር ልትቋቋሚው በፈለግሽ መጠን ወዳንቺ የበለጠ ይመጣል። ስለዚህ መጥፎ ስሜቶች ሲገጥሙሽ ፍፁም ትኩረት አትስጫቸው።በፍፁም ልትቋቋሚያቸው አሞክሪ። ያኔ ጉልበታቸውን ትነጥቂቸዋለሽ. . . እናም 'የኔ ውድ እኔ 'ሳቂልኝ እሺ!! የሆነው መሆን ስላለበት ነው. . በሚችለው አምላክ ስር ነሽ!. . "

ከዛሬ ሶስት አመት በፊት ለመውደቅ ስንገዳገድ ለራሴ ፃፍኩት . . . ስሜቴ በተደበላለቀ ቁጥር አነበዋለው . . . ያለፍኩትን ወይም ማይታለፈውን ያለፉትን ወይም ማይታለፉ የሚመስሉትን ያሳለፈውን አምላክ ነፍሴ ውስጥ ያበራልኛል ያኔ በሃዘን ሳይሆን በትህትና ና በምስጋና ጎንበስ እላለው !!

/ትዝታ/
@BetsinaD
በአንድ ወቅት አንድ ጋዜጠኛ ሄለን ኬለርን ስለ ግል ተሞክሮዋ ቃለ መጠይቅ እያደረገላት እንዲህ ሲል በብሬይል ላይ በመፃፍና እንድታነበዉ በማድረግ ጥያቄዉን አቀረበላት....

"ሚስ ኬይለር ለመሆኑ አይነ ስዉር ከመሆን በላይ ምን የከፋ ነገር አለ?"ሲል ጠየቃት።እጅግ በእርጋታ ለአፍታ በማሰብ አለምን ያስደመመና ዘመን ተሻጋሪ የሆነ መልስን መለሰችለት።
"አዎ፣ማየት የተሳነዉ ከመሆን በላይ የከፋዉ ነገር፣ ያለ ራዕይ የማየት ችሎታን ይዞ መቀመጥ ነዉ።"በማለት ነበር የመለሰችለት።


ሄለን ኬለር ምንም እንኳ የ18ወር ህፃን እያለች የማየት፣ የመስማትና የመናገር ችሎታዋን በአንድ ጊዜ ያጣች ቢሆንም፣በአካባቢዋ ከነበሩት የማየት ችሎታ ካላቸዉ ሰዎች የተሻለ የመመልከትና አርቆ የማሰብ ችሎታ ነበራት፤ ለዚህም መፀሀፎቿ በቂ ምስክሮች ናቸዉ።ሄለን ኬይለር እግዚአብሔርን 'ለምን እንዲህ አደረግከኝ' የሚል የማይረባ ወቀሳ ወስጥ ከመግባት ይልቅ በልቧ ራዕይ የሰነቀች ሴት በመሆኗ በደስታና በእርካታ ነበር የኖረችዉ
2🔥1
▶️ታናሽ እህቴ ናት ፦
በአስራ ሶስት አመት እበልጣታለሁ። እሷ ላይ ያለኝ ስልጣን የአለቃ ነው።'exercise' የማደርገው ስልጣን ብዙ ነው።
የአፍሪካ መሪዎች ዜጎቻቸው ላይ ካላቸው ስልጣን አያንስም
እሷም ስልጣኔ ነው ብየ 'exercise' የማደርገውን በፀጋ
ተቀብላለች።

ልጄ ትመስለኛለች ምግብ በጋራ ስንበላ ቀድሜ ነው በቃኝ የምለው። ከርሷ ጋር እንዳልሻማ ፍቅሬ እና ሃላፊነቴ ይገታኛል

ሁኔታዋን አየዋለሁ ሲድክካት፣ስትደሰት እንቅስቃሴዋን አስተውላለሁ። ከጓደኛዋ እንዳታንስ′Invest′አደርግባታለሁ።

የሆነ ፊልም እያየን መጥፎ ገጸ -ባህሪ ስታይ''ኤፍሬም ፊልም
ስለሆነ ነውጂ። እንደዚህ አይነት ሰው በትክክለኛ ህይወት
የለም አይደል? ''ትላለች

ሰው የፈጣሪን ስም ጠርቶ የሚዋሽ አይመስላትም፣
ለገንዘብ ብሎ ሰው ጓደኛውን የሚክድ አይመስላትም፣
የውሸት ለቅሶ ያለ አይመስላትም።ንፁህነቷ ያስደነግጠኛል።

ብስለት የሚባለውን እውቀት ማጥመቅ ፈልጌ
አጠማመቁ ግራ ይገባኛል።

'Fiminist' አደረገችኝ።ትሁቴን እያሰብኩ መደፈር፤ድብደባ
ጭቆና ፣እቃወማለሁ። ትሁቴን ስለማስብ ሴት አታልሎ
ወደ አልጋ መውሰድ አልችልም።ትሁትን እያሰብኩ ገራገር
እንስቶች ላይ ′Advantage ′ ለመውሰድ አልሞክርም።

ትሁቴ የመጀመሪያ ልጄ ነች። በሷ ጉዳይ አልራቀቅም፣
በሷ ምክንያት ሴቶች ላይ በደል አልሰራም።

ትሁቴ እንዳትኮርጀኝ ሰክሬ አላገላውጅም፣ የማይረባ ጓደኛየን እቤታችን አላመጣም፣ ትልቅ ለመሆን እባትላለሁ።

የአንዳንድ ታናሽ አሻራ እደ መምህር አይነት ነው!!!

Ⓒ Adhanom Mitiku

ለታናሾቻችን ለሴት ልጆቻችን ስንል ንፅህናን እንላበስ
3👍1🔥1
ያ ደግ ሰው ፣አፍልቃ ወደምትሞላ ምንጭ እጁንና ፊቱን ሊታጠብ ኼደ። ምንጭ ሲቀዳት የማያደፈርሳት ትወዳለች። ኩልል ብላ የሆዷን እያሳየችው ያ ደግ ሰው የሚታጠብበትን ውሃ ሰጠችው። ያ ደግ ሰው ከጠጣ፣ ከታጠበባት በዃላ እንዲ ሲል መከራት ፡" ምንም እንኳ ውቂያኖስ የሚያክል ውሃ በሆድሽ ቢኖርም ቀስ እያልሽ ካላፈለቅሽ ሰዎች አያከብሩሽም። እንዳትፈርሺ፣እንዳትደርቂ ብለውም አያጥሩሽም፣ምክንያቱም ሰዎች የሚሰጣቸውን አምላክ ሳይሆን የሚቀማቸውን ንጉስ ያከብራሉና ነው"።
🥰4👍3
“ከተለያዩ በኋላ ወንድየው ሴቷን በፍቅራቸው ጊዜ ከተመለከታት በላይ ቆንጆ ሆና ትታየቸዋለች። ሴቲቱ ግን በተቀራኒው ባየችው ግዜ ሁሌም ራሷን ትጠይቃለች፡- ይሄን ጅል ነበር ያፈቀርሽው? ቆይ ምኑን ነው የወደድሽው..?” 🧐

        ―አህመድ ካሊድ ተውፊቅ
👍3😁3
የቀጠለ ምንሆኛለሁ Book.Review

✔️አንዲት ደንበኛዬ(ስነ ልቦና ምክር ፈልጋ የመጣች) ሴት አለች፡፡

ከዩኒቨርሲቲ ሁሉንም ትምህርት "A›› አምጥታ ነው በከፍተኛ ማዕረግ የተመረቀችው፡፡ እንደተመረቀችም ሥራ ተቀጥራ ጥሩ ደመወዝ ታገኛለች፡፡


ነገር ግን በሕይወቷ ደስተኛ
አይደለችም፡፡ የምረቃዋ ዕለት እናት፣ አባት፣ ወንድም፣ እህት ሁሉም በደስታ ሲስክሩ እሷ ግን ደስተኛ አይደለችም፡፡ በተለይ ማህበራዊ ሕይወት ደስተኛ አይደለችም፡፡

የምታወራው ከእናቷ ጋር ብቻ ነው፡፡ ከሥራ  ውስጥ እናቷን በስራ ማገዝ ነው ደስታዋ፡፡ እናቷ ያለችው ነገር ተፈጻሚ ይሆናል፡፡ ‹‹ሥራሽን ልቀቂ›› ብትላትም ለመልቀቅ አታመነታም፡፡ በዚህ ባህሪዋ ሁሉም የቤተሰብ አባላትና ጓደኞቿ ይገረሙባታል፡፡

ይህቺ ደንበኛዬ ልጅ በነበረች ጊዜ እናቷ ሲበዛ አኩራፊ ነበረች፡፡ ደንበኛዬ እንደነገረቺኝ እናት ቤት ውስጥ የሆነ ጥፋት ካየች ያጠፋውን ሰው ወርና ሁለት ወር ልታኮርፈው ትችላለች፡፡

ልጅ ሆና እናቷ በምክንያት ስታኮርፋት እሷን ለማስደሰትና የእናቷን ኩርፊያ ለማስቀረት የማታደርገው ነገር የለም፡፡ ለዚህ ስትል ከአቅሟ በላይ ትሰራለች፡፡ የታዘዘችውን ታደርጋለች፡፡ ሳትታዘዝም ትሰራለች፡፡ እናቷ ከዚያ ኩርፊያ እንድትወጣ ማድረግ ያለባትን ብቻ ሳይሆን የሌለባትንም ታደርጋለች፡፡


እንግዲህ ደንበኛዬም አድጋ ያንኑ ነው የቀጠለችው፡፡ አሁንም አድጋ የልጅነት አስተሳሰቧ ውስጥ ናት ማለት ነው፡፡ በትምህርታ: በጣም ጎበዝ ናት፡፡ በሌላው አስተሳሰቧ ግን ገና ልጅነቷ ላይ ነው ያለችው፡፡ በታመመ ቤተሰብ ውስጥ በጠረጴዛ ዙሪያ መነጋገር እንግዳ ጉዳይ ነው፡፡ ድርጊቶች በኃይል ነው የሚፈፀሙት፡፡

ችግር ሲፈጠር መነሻና ግዙ አይታወቅም፡፡ ለሁኔታዎች ማን ኃላፊነት እንደሚወስድ አይታወቅም። ከኃላፊነት አለመውሰድ ውጭም ከተፈጠረው ጭማር ትምህርት መውሰድ የሚባል ነገር የለም፡፡ ስለዚህ ደግሞ ደጋግሞ የማጥፋት እድል ነው ያላቸው፡፡  ካደጉ በኋላም ያንኑ ስህተትየማረምና የማስተካከል እድል የለም፡፡

ይህቺ ደንበኛዬ ዛሬም እንደ ልጅነቷ ግንኙነቷ ከእናቷ ጋር ብቻ ነው፡፡ አሁንም እናቷ ያለችውን ፈጥና ታደርጋለች። ሌላው ማህበራዊ ግንኙነቷ ጠቦ የእናቷ ታዛዥና አድራጊ የሆነችው አሁንም አስተሳሰቧ የልጅነቷ በመሆነ ነው፡፡ በዩኒቨርሲቲ የማዕረግ ተመራቂና በመ/ቤቱ ብርቱ ሠራተኛነቷ ቢመሰከርላትም ቤት ስትገባ ግን ያቺ የልጅነቷን ነች፡፡

በስነልቦና የተደመደመ አውነት የለም። የመሆን ዕድል ነው ያለው፡፡ ይህች ደንበኛዬ ወይም በእሷ አይነት አስተዳደግ ውስጥ የመጣ ወንድ የአንድ መ/ቤት ስራ አስኪያጅ ቢሆኑም የበታች ሠራተኞችና መምሪያ ኃላፊዎች ያዘዟቸውን ሳይሰሩ ቢቀሩ ቢሯቸው ጠርተው ችግሩን (በመነጋገርከመፍታት ይልቅ ማኩረፍ ነው የሚቀናቸው፡፡

በስሜታዊነት ነው ምላሽ የሚሰጡት፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ግን በልጅነታቸው የተፈጠረባቸው የአዕምሮ ቁስለት አሁን በጉርምስናቸውና በጉልምስናቸው ችግር እየፈጠረባቸው መሆኑን አያውቁም፡፡ ለምን ይህን እንደሚያደርጉም አያውቁም፡፡

ግን መቆጣጠር በማይችሉበት መንገድ ያደርጉታል። ብዙ ሰዎች የስነልቦና ባለሙያዎች ጋ ሲመጡ ነው መነሻ ምክንያቱን የሚያውቁት፡፡ ሰው ከወላጆቹ ገንዘብ ብቻ ሳይሆን ችግርንም፣ ባህሪንም ይወርሳል፡፡

የታመመ ቤተሰብ ውስጥ ቁጭ ብሎ፣ በስርዓት መነጋገር የለም፡፡ ቀደምቶቹ ወላጆች ሁሉንም እንደሚቆጣጠሩት ሁሉ እነዚህ ደግሞ ዝም በማለት ወይም በማኩረፍ ነው ምላሽ የሚሰጡት፡፡ ማኩረፋቸውን ያምነብታል፡፡ አንዳንዴም በኩራት ያወሩታል፡፡ “ዝግት ሳደርጋት ልክትገባለች›› ይላሉ፡፡ ቤቱን በዝምታ ነው የሚያስጨንቁት፡፡


✈️@Enmare1988
✈️
@Enmare1988
🔥3
ሃሎሎሎሎሎ የኔ ወለላ... ሃሎሎሎሎ የኔ ቀይ አበባ... እንኳን አደረሰሽ የኔ ቸኮላታ

እሺሺ የጠፋ ሰው... ከየት ተገኘህ ባክህ??(አይማ..ርታ፡፡ድምጿን ሞዘዝ ማድረግ አልተወችም

ያው የደወልኩበትን ጉዳዩ ገብቷቷል Valentine ስለሆነ አብረን እንደር ምናምን....እሷም ነቄ ናት፡፡አይማርታ.....እስካሁን ባልለያት በዚህ ነገርኝነቷ ጨጓራዬን ጠብሳ ታበላኝ ነበር፡፡ አልያም ኩላሊቴን አሽጣኝ ምላስ ሰንበር ትበላበት ነው፡፡አቤት ምላስ አቤት አቤት አቤት ምላሷ አፏ ውስጥ ሲላወስ እራሱ እኔን የሚያቃጥለኝ ነገርግርምምምም ይለኛል፡፡ከተለያየን አመት ቢሆንም ያውውው ፍቅርን ለማደስ አንዳንድ መሠረታዊ ነገሮችን በአልጋ ዙርያ እንድናወራ ነበር አደዋወሌ...ታድያ ጓደኞቼ አቅፈው ሲያድሩ እኔ ለምን!!!እኮ....

ባክህ ዛሬ በጠዋቱ ቀይይይይ በቀይ ሆኛለሁ ታድያ ልምጣ??(ተሸኮረመመች፡፡እምቢ እንደማትለኝ አቃለሁ፡፡ ያ ለአመታት የለፋሁበት ብቃቴን ዛሬ....!

መሸትሸት ሲል ያለቺኝን የክፉ ቀን ገንዘብ ከባንክ መዥረጥ አድርጌ ወደተቃጠርንበት ሆቴል ስክለበለብ ሔድኩ፡፡ማርታ ከድሮዋ የወሲብ እሳት ለብሳ፤ትንቡክ ብላ በስላ ፤እምርብላ ተኳኩላ ቁጭ ብላለች፡፡ያጣላን ነገረኝነቷ እንጂ ውበትስ ሚደርስባት የለም፡፡እመቤቴን!!

ገና እንደደረስኩ ለቀብድ ማስያዥ ምትሆን ለጉንጭየራቀ ለከንፈር የቀረበ አማካኝ ስፍራ ላይ ስሜያት ተቀመጥን።የቆጥ የባጡን አወራን፡፡ወይን ተቻለስን፡፡እንደገና ምግብ በላይ።እንደገና ጨፈርንና የአልጋ ብር ብቻ ኪሴ መቅረቱን ሳረጋግጥ ግን....

የኔ ፍቅር አልኳት ለስለስስ ባለ ድምፅ (አቤት ድፍረት!! የምን ፍቅር ብትለኝስ አሁን?

ወዬዬ አባ... ( ተመስገን!!እንደውም እንግባ አይነት የወሲብ ድምፅ አለው፡፡ደሞ ትንሽ ሞቅ ብሏታል

በቃ እንግዲ ገብተን ደሞ እ?ያቺን...(አይኔና ከንፈሬ እኩል ብልጥጥ አርጌ በብልጣብልጥ ፊት አየኋት

ወዴት???ወዴት ነው ምንገባው??(አይ ማ..ርቲ ስትሰክርኮ ትዘባርቃለች፡፡ምለው ጠፍቷትኮ አደለም

ያውው.. አልጋ ይዣለኋ ማርቲዬ እ... ማለቴ....

ያምካል ናቲ???ጠዋት ምን ብዬክ ነበር ቆይ???

እንዴ ምን አልሺኝ!!(ሳላቀው ቁጣ አመለጠኝ

ቀይ በቀይ ሆኛለሁሁሁ አልኩህ አደል እንዴ!??

እና ቫላንታይን አደል እንዴ?የሆንሽ እንደሆንስ!!??(አረ ጉድ ፈላ...ላብድ ቃጣኝ፡፡ደሜ ትክትክትክትክክክክ አለ!!

ዝም በል ወደዛ... ድሮ ፍቅረኛ እያለን እኔ ፔሬድ ላይስሆን የምንግባባበት የሚስጥር አማርኛ ''ቀይ በቀይሆኛለሁ"የሚለው አደል ያ ማለት ፔሬዴ መ...

በቃሽ ወደዛ!!!አትጃጃይብኝ!!እና ያኔ ነዋ አሁን ምን ይሁን ብለሽ ነው ምታስታውሺው ያኔ ቀረ ቀረ ነው አሁን ፔ...ፔ("ስሙን ቄስ ይጥራው!!ያኔ የተባባልነው ትዝ ሲለኝ በቆምኩበት እንባ እንባ እያለኝ የበተንኩት ገንዘቤ እያሰብኩ ያልበኝ ያዞረኝ ጀመረ

አየህ የረሳከው የምንባባለውን ቃል ሳይሆን ሴትነቴን እና ክብሬን ነው!!ትላንት በቃኝ ብለህ የናቅከውን ገላ ዛሬ የዝሙት በአል ደርሶ ስትክለፈለፍ አልጋ ላይልትጥለኝ ስታስብ መጀመርያ ሴትነት ዘንግተከው

ነበር፡፡እኔም የመጣሁት ሆነ ብዬ ልፈትንህ ነው!! ወደህ

ማታገባት፤ወልደህ ማታከብራትን ሴት ፈረንጅ በሰጠህ የዝሙት ቀጠሮ ለማዋረድ ብዙ አትልፋ፡፡እዚህ ምሽት ላይእንዳንተ አይነት ክብረ ቢስ ወንዶች የንፁህ ሴቶችን እንባ እና ደም ያፈሳሉ ቀይ ለብሰው ለክፋት ይሰለፋሉ "ቫላንታይን ዴይ (day) ብለው ቫላንታይን ዴዝ (death) ይሆናሉ"

ትሰማለህ..''ፍቅረኝነት በልዩነት አንድ ቀን ሳይሆን በልዩነት ዘላለም የሚከበር በአል ነው እሺ"ለግብዣው በጣም አመሠግናለሁ በል ደህና እደር....

በቆምኩበት ታኮ ጫማዋን ቋ....ቋ....ቋ እያረገች ጥላኝ እብስ!!!


ከየታሪክ የተወሰደ
🔥4👍1
ራስን ለመሆን ራስን ማወቅ መቻል ቁልፍ ነው፡፡ራሱን ያላወቀ ሰው ሌላውን እንዲመስል ይገደዳል፡፡ «የተለየ» የመሆን መብቱንም ያጣል።ከዚህም ባሻገር ማንነቱን ማጐልበት ይሳነዋል፡፡

📓ራስህን የማወቅ ሳይኮሎጂ
✍️ቃልኪዳን አምባቸው

📖@Bemnet_Library
👍3
የትኛውን ነን?😊
👍4👌2