የእንስቶቹ ገፅ👩‍🦰👩‍🦱👩‍🦳🧕
172 subscribers
246 photos
27 videos
2 files
28 links
ይህ ሴቶች ብቻ የሚሰባሰቡበት ቻናል ነው ስለ ራሳችን የምናወራበት ከሌሎች ጋር የምናውጋበት ልዮ የእንስቶች መድረክ ነው እንስቶችን በተመለከተ ፅሁፍ,ፎቶ,ቪድዬ,ሊንክ ካገኛችሁ ማጋራታቹሁን እንዳትረሱ
እኛው ለእኛው እንሁን👩👧
Download Telegram
ፅጌረዳዋ ለአፍታ ዝም አለች፡፡ ከዛም በኩራትና በስኬት በተሞላ የተዳከመ ድምፅ፣«ለአንድ ሰአት እንደ ፅጌረዳ አበባ በኩራት ኖሬአለሁ፤ ለጥቂት ጊዜም እንደ ንግስት ኖሬአለሁ፤
በፅጌረዳ አበባ አይኖችም ዓለምን ተመልክቻለሁ፤ የሰማዩን ድምፅ በፅጌረዳ አበባ ጆሮዎች አድምጫለሁ ፤የብርሀን ልብስንም በፅጌረዳ (ቅጠሎች) ዳስሻለሁ፡፡ ከእናንተ መሀል ይህን ክብር ያገኘ አለ?»

ካህሊል ጂብራን
🔥1
ከህይወት ጋር ፍቅር የያዛት ይመስላል...ከማግኘት፥ከማጣቱ ጋር ፣ ከውጣ ውረዱ ጋር ፤ ከመውጣት፥ከመውረዱ ጋር ፣ ከደስታም ከሐዘኑም ጋር ።
ከፈጣሪ ውጪ ምንም ነገርን አጥብቀህ መያዝ የለብህም...ሁሉም የሚወድህ ከራሱ ወዲያ ነው ።

የምትል መርህ አላት።
አድር ባይ አይደለችም ሐቀኛ ናት ፤ የማይደረግ ነገር ሲደረግ ያስቆጣታል ማለፍ አትችልም ፥ በዚህም ሳቢያ ጋጠወጦች ፈፅመው አይወዷትም ። የዋህ ናት በጣም ለሰው ታስባለች ፤ ልወደድ ብላ ግን የማይሆን ነገር ይሁን ማለት አይቻላትም ።
...ትለፋለች ፣ ትደክማለች
የሚሰሩ እጆች የተባረኩ ናቸው

የምትለው አባባል አላት ፤
ስራዬ ነው ረፍቴ

ደግሞም ትላለች ።
እርሷ መሽቀርቀር አይደለም ውበቷ ፤ አፈር አይንካኝ በማለት አታምንም
የሰው ልጅ ውበቱ ስራው ነው

ትላለች ።
ከህይወት ጋር ፍቅር የያዛት ትመስላለች ፤ እኔንም ልታሲዘኝ ነው።





ከ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ
©ሶፊ
4
Educational Volunteers Needed!
Do you have just 2 hours per week to volunteer? You can join us in person or online!

What’s in it for you?
A certificate of participation.
An allowance to support your transport or internet needs.

What will you do?
Tutoring and Mentorship: Support students in public schools across Addis Ababa.
Educational Material Preparation: Create engaging and effective study materials online.

We’re looking for 2,000+ volunteers to make a real difference in education!

To apply fill out this form:https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLScdxzxUL65oVGsuZUhnDVYkO44L49PmO7uZ1bu3HCvb6_-YAQ/viewform?usp=pp_url&entry.1131561500=kalkida _wegene

Deadline to apply: Tuesday, December 3, 2024.
የ በጎ አድራጎት ሥራ መስራት ለምትፈልጉ ሁሉ ነዉ apply በማድረግ መስራት ይምችሉትን ሞክሩ..... Certificate ም አለው ተጠቀሙበት


Join us and help shape the future of students!
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ደከመሽ😔
ታከተሽ 😞
አይዞሽ 😊
እንደ ሰው ሁሉ ያልፋል!!
1
እየዉልሽ ዓለሜ በዘመኔ ያስተዋልኩት ፍቅር  ሁለት አይነት መልክ አለዉ፨አንዱ በግዴታም ይሁን በዉዴታ ሲገጥምሽ ራስሽ የምታበጃጅዉ ፍቅር ነዉ፨ሌላው ደግሞ ነፋስ የሚያመጣዉ ፍቅር ነዉ፨አሏት እማማ በምሽቱ መሃል እሳት ዳር ተቀምጠዉ እያወሩ..
ነፋስ..?
አዎ ንፋስ ..!
መነሻዉን መምጫዉን ሳታዉቂዉ ድንገት ከልብሽ ኖሮ ታገኝዋለሽ፨ያዉ ራሱ ያበጃጅሻል፨

ቆይ የትኛዉ ይበልጣል?

እኔ የማዉቀዉ ያበጀሁትን ነዉ፨ያዉ እስከዚ እድሜያችን ድረስ እንደተዋደድን እንደተፋቀርን አለን፨ሰዉ ያላየዉን እንዲህ ነዉ አይልም፨ብቻ ፍቅር ያዉ ፍቅር ነዉ፨ምን ለዉጥ አለዉ ብለሽ ነዉ ዓለሜ፨
እኔ እንጃ...ግን ወደ ልብ ከሚመጣ ይልቅ ልብ ዉስጥ ያለ የሚበልጥ ይመስለኛል፨እንጃ..🩵

#ዘመኔ
https://t.me/yeesua_queen
4👍1
“ውሃ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው” አላት። ሳቀች። ወሰዳት።
“ነይ እንጫወት። ጨዋታ አዋቂ ነኝ።” አላት። “እሺ” አለች። ተጫወተባት።

Bani


@banitube
🔥4😭2
..."ለምን እንደሆነ ባላውቅም አለመፈለጋችን ላይ ትኩረት እንደምናበዛ" አለችኝ ራሷን እየታዘበች መሆኑ ነው። "ማለት እስኪ ግልፅ አድርጊልኝ" አልኳት።...

ሁላችንም ትኩረት ፈላጊዎች ነን ከሚወዱን ከሚፈልጉን ሠዎች ይልቅ ከተውን ከራቁን ጥቂት ሠዎች ላይ ትኩረት እንሰጣለን...እስከሞት ከወደደህ ፈጣሪ አብዝታ ከምትወድህ እናት በላይ በጣም ከሚወዱህ ቤተሰቦችህ ጓደኞችህ በላይ ለሆነ ሠሞን ያወከው አንድ ሠው ትንሽ ገሸሽ ሲያደርግህ ልብህ በሀዘን ይጎዳል" ።...
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እህቴ ትክክለኛ የፍቅር ግንኙነት ውስጥ መሆንሽን ማረጋገጥ ከፈለግሽ እነዚህን ነገሮች ከፍቅረኛሽ ዘንድ መኖሩን አረጋግጪ👆👆👆
🔥3
ስንቱን አስታወስኩት ስንቱን አየሁት
ልቤን በትዝታ ወዲያ እየላኩት
የትናንቱ ፍቅር ጣዕሙ ቁም ነገሩ...
...ጣዕሙ ቁም ነገሩ...



ምነዉ ሙዚቃዉ ሃዘኔን አባባሰዉ፨

የናፈቅሽዉ ሰዉ አለ የኔ ልጅ?

አይ..እንደዉ ዉዚቃዉ ሆድ አስብሶኝ ነዉ፨

እሳት በሌለበት ጭስ አይጨስም፨ዉስጥ የሌለም አይብስም፨የምንወዳቸዉን ሰዎች ስንናፍቅ ዓለምን በሙሉ እንናፍቃለን፨ምክንያቱም የእኛ ዓለም በምንወደዉ ሰዉ ዉስጥ ነዉ ያለዉ፨

እንደርሱ አይደለም እናቴ....እንደዉ ትዝታ ዉስጥ ገብቼ ነዉ፨

አይይይ...ሰዎች በትዝታ መኖር ከጀመሩ ወይ እንደ እኔ አርጅተዋል አልያም ባሉበት ቆመዋል ማለት ነዉ፨አርጅተሻል እንዴ...?

መሰለኝ 😊

እየዉልሽ የኔ ልጅ በዚች ምድር ላይ ሁለት ነገሮች አይጣጣሙም፨ፍቅርና ሕግ!!አንዱ አንዱን ያፈርሰዋል፨ለማጣጣም አትሞክሪ ጥሰቱን ኑሪዉ🖤

#ስንብት

https://t.me/yeesua_queen
1🔥1
ጠያቂው፡- << ራቢያ ሆይ! አምላክሽን ታፈቅሪያለሽ!? >>
ራቢያ፡- << በጣም አፈቅራለሁ!!>>
ጠያቂው፡- << ሰይጣንንስ ትጠያለሽ!?>>
ራቢያ፡- << አልጠላም!! ምክንያቱም ከአምላኬ ፍቅር ተርፎ ለጥላቻ የሚሆን ጊዜ የለኝምና!!>>
ጠያቂው፡-<< ራቢያ ሆይ! የፈጣሪን ነቢይ ታፈቅሪያለሽ!? >>
ራቢያ፡- << አፈቅር ነበር፡፡ ነገር ግን የፈጣሪ ፍቅር እሱ ከፈጠረው ነገር ሁሉ በልጦ ልቤን ወሰደው!!>>
© ጥበብ ከ ጲላጦስ ቅፅ ፫
ኃይለጊዮርጊስ ማሞ
🔥1🥰1
* የራስሽን ኮከብ ፈልጊ! *

አፍሪካውያን የሌላውን ሰው ኮከብ ተጠቅመህ አትነሳ የሚል አባላል አላቸው። ይህም ማለት አንድ ሰው አንድን ነገር ሲሰራ ስለተሳካለት አንቺም ተመሳሳይ ነገር በማድረግ ወይም በመስራት ስኬታማ ትሆኛለሽ ማለት አይደለም።

ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ ፍላጎት፣ አቅም እና ህልም አለው። ሰው ማሳካት ያለበት የራሱን ህልም እንጂ የሌለውን አይደለም።

እናም ወዳጄ ሆይ የራስሽን ህልም ፈልጊው፣ … እናም ኑሪው!
ያሬድ ነኝ ከዱባይ

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንልሽ😘🥇!
3
የ እኔ ፡ ውብ

ከሁሉም ፡ ይልቅ ፡ ልብሽን ፡ ማውጋትሽን ፡ ስሜትሽን ፡ ሃሳብሽን ፡ መሰተርሽን ፡ አስቀድሜ ……

አትሞኚ ፡ አትቸኩዬ ፡ እንዲች ፡ ብለሽ ፡ በጥድፍያ ፡ ውስጥ ፡ ህይወትሽን ፡ እንዳትግዬ ……

ይልቅ ፡ መለስ ፡ በይ ፡ ይልቅ ፡ አረፍ ፡ ብይ ፡ ይልቅ ፡ መስኮትሽን ፡ ክፈቺ ፡ ብዕርሽን ፡ አንሺ ፡ ልብሽን ፡ ነብስሽን ፡ ደግፊ ፡ ከጥድፍያሽ ፡ ሩጠሽ ፡ አምልጪ ………
ረጋ ፡ በይ ፡ ሁሉን ፡ በአቅሙ ፡ ለኪ ፡ መጥኒ ፡ ስፈሪ ፡ የልብሽን ፡ ሸክም ፡ አቅልዬ ………🧚‍♂
🔥31
ከንቱ ኩራትን ምን አመጣው?
ሟች መሆንሽ ተረሳ?

ምክንያትሽ ምንድን ነው?

ሰው ነሽና ሰው የማይረዳው ምክንያት አታጪም::

የምድር ህይወት መሰቃየት ነው::

የልጅነት የዋነት ተሰርቀሻል::
የአምላክ ፍቅርን ክደሽ በቁስ ፍቅር ተጠምቀሻል::

ባርነት ነው::ነፍስን አጥቶ አለምን ማግኘት ታላቅ ክስረት ነው::

ፊትሽ ይስቃል::አለባበስሽ ያንፀባርቃል::

ሰው ሁሉ አንቺን መሆን ሲመኝ ያአንቺ ውስጥ ግን ሞትን ይመኛል::

ምንድን ነው ግን ህይወት?
ምንድን ነው ግን የመኖር መጨረሻው?

ሞት?

ሞት አለ::
ሁሉን በዜሮ ያበዛል::
ከአፈር ጋር ይደምራል::

ታዲያ በምድር ቁስ መሰብሰቡ ሞትን ካላሸነፈ ምን ይሰራል?

ሞትን የሚያሸንፍ አንድ ነገር የነፍስሽ መንቃት ነው::

ነፍስ ስጋዊ ምኞትን ጥሳ መንፈሳዊ ውበቷን ስታገኝ የህይወት ብርሃን ወደ ህይወትሽ ይፈሳል::

ማንም የማያውቃቸው ልባዊ ህመሞች : በር ዘግተሽ ያፈሰስሻቸው እንባዎች ትክክለኛ መድህኒት ያገኛሉ::

ለምን እኖራለው? የሚለው አሰልቺ ጥያቄ አምላክን ስታገኚ ይቆማል::

ከንቱ የሆነው ህይወትሽ በአምላክሽ ብርሃን ትርጉም ያገኛል::

የፈጠረሽ አምላክ ባንቺ በኩል ወደ አለም ይመጣል::

ለሀሳብሽ ብርሃን ..ለስራሽ መንፈሳዊ ሐይል ..እና ..ለስኬትሽ በረከት ይችራል::

አላማሽ አላማውሲሆን
በትንሿ ልጁ ትልቁ አምላክ ይከብራል::

የመዳኛሽ ሰዓቱ አሁን ነው::

አንቺ ሺ ጊዜ ብታጠፊ እሱ ቢሊዬን ጊዜ ይረዳሻል::

ቢሊዬን ጊዜ ብትሳሳቺ ደግሞ ለዓለመ ዓለም ይጠብቅሻል::

ለከንቱ አለም ብለሽ ህያው አምላክሽን አታስጠብቂው::

አሁን ልብሽን ወደ አምላክሽ አድርጊ::

አሁን ወስኚ.........

አለም ይሻልሻል ወይስ አምላክ?
2❤‍🔥2👍1
እናቴ ሁሌ ነበር አግቢ የምትለኝ ፣  በተረት ፣በታሪክ በሃዘን አስታካ ስለ ትዳር ነበር የምትወተውተኝ ። በመወትወት ከማይሆነው ነገር ውስጥ አንደኛው ትዳር ነው ።

ውትወታዋ በቶሎ  ፍሬ አላፈራም ። ውትወታዋ ስለሚያስጨንቀኝ ክፍት ያለ ፊት ሳሳያት ጨዋታ ትቀይራለች ።

አብሪያት ሳድር ፀሎቷ ውስጥ በየቦታው አለሁ ።

ሰመረልኝ እና ....!

" እናቴ ላገባ ነው የምወደዉ ልጅ አግኝቻለሁ መስመር እስኪይዝ ነው ያላጫወትኩሽ"

"ምን አልሺኝ ?"ብላ ብድግ አለች

እጮኛዬ ሽማግሌ ሊልክ ነው አልኳት።

    እምባዋ ቃላቷን ቀደመው !

ጥሩ ሰው ነው ?? ትዋደዳላቹ ??

"አዎ" አልኳት በፈገግታ ሌላ አልጠየቀችኝም ።

አገላብጣ ሳመቺኝ ። ደስታዋ ወደር አልነበረውም ።
አንጋጣ ተመስገን አለች  ።

ደስታዋ አንጀቴን በላኝ ። እናት  ከሃዘናችን በላይ ደስታችን  ያስለቅሳታል ።  የልጅ ሃዘን ለእናት እምባ አይደለም ስብራት ነው !!


መሰበር የምንፈራው ለሚወዱን ሰዎች ብለንም ነው ።......
......... እኛ እኮ የኛ ብቻ አይደለንም !!

    © Adhanom Mitiku
5
ከሚስቱ ይልቅ ለድመቱ ትኩረት ሰጥቷል የተባለው ባል ክስ ተመሰረተበት....

ባልየው ባህሪውን እንዲያስተካክል በሚስቱ ቢነገረውም አልተስተካከለም ተብሏል

ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ይዛ የሄደችው ሚስትም ፍትህ ይሰጠኝ ብላለች

ከሚስቱ ይልቅ ለድመቱ ትኩረት ሰጥቷል የተንባለው ባል ክስ ተመሰረተበት

ድመትን ጨምሮ ብዙ የቤት እንስሳት ከሰዎች ጋር በአንድ ቤት ውስጥ መኖር የተለመደ ሆኗል፡፡

አብራቸው እንድትኖር የተፈቀደላት አንድ ድመት ግን ለትዳር መፍረስ መነሻ ሆናለች ተብሏል፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ ሕንዳዊኑ ለዓመታት ጎጆ ቀልሰው በትዳር ተጣምረው እየኖሩ ነበር፡፡

አብራቸው እንድትኖር እና እናሳድጋት ያሏት ይህች ድመት ለፍቅራቸው መበላሸት መነሻ የሆነች ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ ባልየው ድመቷ እንድትለየው አለመፈለጉ ነው፡፡

ባሏ ከእሷ ይልቅ ለድመቷ ትኩረት ማድረጉ ያበሳጫት ሚስትም ከዚች ድመት ጋር ያለህን ግንኑነት ቀንስ ስትል ስሞታ ታቀርባለች፡፡

ከድመቷ ጋር ማንም አይለየኝም ያለው ባልም የሚስቱን አስተያየት ከመቀበል ይልቅ ተቃውሞ ያሰማል፡፡

በዚህ ምክንያት ወደ አለመግባባት የገቡት ባልና ሚስቶች አላስፈላጊ ቃላት እስከመለዋወጥ እንደደረሱ ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡

ጉዳዩ ያላማራት ሚስትም ፍትህ ይሰጠኝ ስትል ወደ ፍርድ አምርታለችም ተብሏል፡፡

ሚስትየዋ ለፍርድ ቤት በጻፈችው ማመልከቻ ላይ ባሌ ከእኔ ይልቅ ድመታችንን አብዝቶ ይንከባከባል ስትል ከሳለች፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ድመቷ ለእኔ ጥሩ እይታ የላትም ልቀርባት ስሞክርም በጥፍሮቿ ጉዳት ታደርስብኛለች፣ ባሌ ይህንን ችግር እንዲፈታ ብጠይቀውም ትኩረት አልሰጠም ማለቷ ተገልጿል፡፡

ክስ የቀረበለት ፍርድ ቤቱም በጉዳዩ ዙሪያ እልባት ለመስጠት ተቸግሯል የተባለ ሲሆን ምን አይነት ውሳኔ እንደሚያሳልፍ በጉጉት እየተጠበቀ ይገኛል፡፡[አል አይን]

@Amazing_Fact_433
@Amazing_Fact_433
😁6