ተፅእኖ ፈጣሪ ኢትዮጵያዊ ሴቶች
1)ሉሲ/ድንቅነሽ ―የሰው ልጆች እናት
2)ንግስት ሳባ―የሰለሞናዊ ሥርዎ–መንግስት አስጀማሪ እና የአክሱም ስልጣኔ ንግስት
3)እቴጌ ጣይቱ ―የአድዋ ድል አዝማች፣ ጠንካራ እና ብልህ መሪ፣ የአዲስአበባን መጠሪያ ያወጡ
4)ሊያ ከበደ―አለምአቀፍ ሱፐርሞዴል
5)እሌኒ ገብረመድህን ―የኢኮኖሚክስ ምሁር ፣ የኢትዮጵያን የግብርና ምርት ሽያጭ ዘመናዊ በማድረግ በመሐል ያሉ ጅምላ ነጋዴዎችን አስቀርታ ገበሬዎችን ተጠቃሚ ያደረገች። ሻጭና ገዢ በቀላሉ እንዲገኙ በማድረግ እንደ አሜሪካ የአክሲዮን ሽያጭ ገበያ ያለ ስርአት የዘረጋች
6)ቤተልሔም ጥላሁን―የሶልሬብል መስራች፣ ከጎማ በእጅ የሚሰሩ ጫማዎችን በማምረት ፣ "የአፍሪካ ናይክ" የሚል ማእረግ ያገኘች
7)አበበች ጎበና―የድሀ ልጆች እናት ፣ ከ1·5 ሚሊየን ህፃናት በላይ ያሳደጉ
8)ብርቱካን ሚደቅሳ ―ወጣት የህግ እና የፖለቲካ ሴት
9)አምባሳደር ቆንጂት ስነግዮርጊስ ―ለ50 አመታት በዲፕሎማትነት የሰሩ ጠንካራ ሴት
10) መአዛ ብሩ―ድንቅ ጋዜጠኛ
11) አስቴር አወቀና እጅጋየሁ ሽባባው/ጂጂ―ሙዚቃችንን አለምአቀፍ ያደረጉ
12) ጥሩነሽ ዲባባ―የረዥም ርቀት ሩጫ ንግስት

❤6🔥1🤗1
ትላንትሽን ብዙ ሰዎች አበላሽተውት ይሆናል ጠንካራ ስለሆንሽ ግን ያ ትላንት አልፏል።
ዛሬ ግን የራስሽ ነው በዛሬሽ ላይ የማንንም ውሳኔ አትጠብቂ ወሳኟ አንቺ ነሽ የማንንም እርዳታ እንደማትሺ እና እንደሁሌው ለራስሽ እራስሽ እንደምትበቂ አሳዪ በፍፁም አንዲት ዘለላ እምባ ....እሱ ሽንፈት ነው ሃዘኑ በርትቶ መቋቋም ቢያቅትሽ እንኳን ተደብቀሽ እስኪወጣልሽ አልቅሺ ከዛ ግን ሰዎች ፊት ፈገግ በይ...
ደካማ ጎንሽን ካሳየሽ የሚሳለቅብሽ ብዙ ነው! ማንም ምንም ቢል ከመንገድሽ ላፍታ እንዳትቆሚ እየሄድሽ ስሚያቸው አደናቅፈው ቢጥሉሽ እን'ኳ ከነሱ ጋ ቆመሽ በመሟገት ጊዜሽን አታጥፊ አፈርሽን አራግፈሽ እርምጃሽን ቀጥይ ....
እንዲሰብሩሽ አትፍቀጂላቸው!!
ከእንማር..

🔥5❤1
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢራን
ኢራን በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተከሶ ጥፋተኛ የተባለ ዜጋዋን በአደባባይ በስቅላት ገደለች።
ሞሀመድ አሊ የተባለው ይህ ኢራናዊ የ43 ዓመት ጎልማሳ ሲሆን በርካታ ሴቶች እንደሚያገባቸው ቃል በመግባት አስገድዶ ደፍሯቸዋል ተብሏል፡፡
ግለሰቡ ባሳለፍነው ጥር ወር ላይ በፖሊስ በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን ከአንድ ወር በፊት በተከሰሰበት የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች ትፋተኛ ሆኖ ተገኝቷል።
መሀመድ አሊ ከ10 በላይ ሴቶችን አስገድዶ ደፍሯል የተባለ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ የተወሰኑት ከእሱ የጸነሱትን ልጅ እንዲያስወርዱ መድሃኒት ሰጥቷልም ተብሏል፡፡
ሰውየው ባለፉት 20 ዓመታት ውስጥ 200 ሴቶች ደፍሮናል የሚል ክስም ተመስርቶበታል።
በግለሰቡ ተደፍረናል ያሉ ሴቶች ቁጥር መጨመርን ተከትሎ በርካታ ኢራናዊያን ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድበት የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍም ተደርጎበት ነበር፡፡
ሀገሪቱም ግለሰቡን በአደባባይ በስቅላት እንዲቀጣ አድርጋለች።
#አልአረቢያ #አልአይንኒውስ
@tikvahethiopia

💯2🙏1
...እሺ በቃ እወድሻለሁ "አላት የሞት ሞቱን።ቃላቱ አልወጣ ብለው ተናንቀውት ነበር። "እወድሻለሁ ማለት መሸነፍ የሚመስላችሁ ለምንድን ነው?'' አለች ሰብለ።
ደስታ የሰማውን አላመነም ''አልሰማሽም እንዴ፤እወድሻለሁ ነው እኮ ያልኩት ''አለ። 'እሱንማ ሰምቼዋለሁ።
የጠየቁህ ግን ያንን ለማለት የፈጀብህን ጊዜ እና ሂደት ከግምት ውስጥ በማስገባት "እወድሻለሁ"ብሎ ደፍሮ ፊት ለፊት መናገር ለምን ይከብዳቸዋል ብዬ ነው አለች።''ትልቅ መሸነፍ ነው የሚሆንባችሁ"አለችው ከሱ መልስ ሳትጠብቅ። "መሸነፍማ ነው አላት። "ምን?ምን አልክ?"አለች እሷም በተራዋ የሰማችውን ባለማመን።
"አዎን መሸነፍ ነው ።ፍቅር መሸነፍ ነው።ፍቅር መያዝ ነው።ፍቅር ለስሜት ተገዢ መሆን ማለት ነው።ፍቅር ከምክንያት ውጪ ሆኖ መኖርን መቀበል ነው።ፍቅር ከራስ ቁጥጥር ውጪ መሆን ነው" ስለዚህ አዎ መሸነፍ ነው።ያስፈራል ፍቅር ፣የማይታከሙት ህመም፣የማይጠገን ቁስል፣የማያባራ እንባና ሰቆቃ :: ሊሆን ይችላል።
የሚያስፈራው ያፈቀርሽው ሰው ሳይሆን ፤ማፍቀር ራሱ ነው"ካፈቀርሽ በኋላ"እኔ የምትይው ሁሉ ይጠፋል።ለራስሽ ትርፍ ትሆኛለሽ።በፈቃደኝነት ከራስሽ የምታስቀድሚውና የምታስበልጪው ሌላ ሰው ይኖራል ማለት ነው።"
ፍቅር ያለ ውጊያ መማረክ ነው፣እጅ መስጠት፣ወዶ
መግባት ፣ከራስ መነጠል፣መጥፋት ፣በማያውቁት ሰው ዓለም ውስጥ ገብቶ መሰደድ ።አያስፈራም አትበይኝ ያስፈራል ::''
ወንድ ወይንም ሴት ስለሆንን ግን አይደለም ፍቅርን የምንፈራው።ሰው ስለሆንን ነው።
ማናችንም ብንሆን የህይወታችንን መንገድ መቆጣጠር ባንችል እንኳን ማቀድና መምራት እንፈልጋለን ።አንቺን ወደድኩሽ ስል ይህን ሁሉ መተው ማለት ነው።አንቺን በመውደዴ ከዚህ ቀደም የኖርኩት፣ ያቀድኩትና እያሰብኩት ሁሉ ተጠራርጎ ገደል ይገባል። ምን እንደሚሆን፣ምን እንደሚመጣ፣ምን እንደሚፈጠር አላውቅም፡፡ምክንያቱም ከኔ ቁጥጥር ውጪ ነው"
አለማወቅ ደግሞ ያስፈራል።
ራሴን እንኳን እየተቆጣጠርኩ ባለሁበት ሁኔታ፣ስለ ህይወቴ አካሄድ የማውቀው ጥቂት ነው።ግን የማውቅ ስለሚመስለኝ በሰላም እኖራለሁ "ፍቅር ግን መምሰልን ያጠፋል።ከፊት ለፊቴ የተቀመጠው ስራዬ፣ዕውቀቴ፣ ጓደኞቼ ወዘተ የምላቸው የኑሮ ማስመስያዎች በሙሉ ትርጉም ያጣሉ።ከዚህ ሁሉ በላይ ግን ምን እንደሚያስፈራ ታውቂያለሽ ?አላት። ምን ? አለችው።
አፏን ከፍታ ስታዳምጠው ስለነበር ጥያቄውን ያነሳችው እሷ ራሷ መሆኗ ሁሉ ጠፍቶባት ነበር::
"ፍቅር መተወን አይችልም
በመሆኑም ከልቡ የወደደና ያፈቀረ ሰው ማፍቀሩን ማወጅ ቢያስፈራው አይደንቅም።በቀላሉ እወድሻለሁ የሚል ሰው መውደዱን ገና ያላወቀ ወይንም አስመሳይ ነው" አላት።
አለመኖር 📚

👍2❤🔥1🥰1
እሱ፤ አንድ ሚልዮን ብር ብሰጥሽ ከኔ ጋር ትተኛለሽ?
እሷ፤ አንድ ሚልዮን ብር? ዋው! ይመስለኛል አዎ፡፡
እሱ፤ በመቶ ብርስ?
እሷ ፤ ጥፋ ከዚህ፡፡ ምን መስዬህ ነው? ሴተኛ አዳሪ?
እሱ፤ ሴት አዳሪነትሽን መጀመሪያውኑ ተስማምተናል፡፡ አሁን በገንዘቡ ላይ እንደራደር።
ልክነት መቼ እና እንዴት ነው
የሚኖረው? መቼ ነው ይህቺን ሴት ሴተኛ አዳሪ የምንላት? መቼ ነው ይህቺን ሴት ክብሯን የጠበቀችው? መቶ ብር ወይስ መቶ ሺ ብር ላይ? ወይስ አንድ ሚሊዮን ላይ? መቼ ነው ክብሯን ያጣችው?
የገነባነው ክብር እና ፅድቅ በየትኛው የብር መጠን ላይ እንሽረዋለን? ከሻርነውስ የእውነት መልካም ሰው ነን ማለት እንችላለን?
ምናልባት ምግባራችን እንደ ሴቷ በገንዘብ ስላልተፈተነ ይሁን ጥሩ ሰው የመሰልነው ?

❤6
ፅጌረዳዋ ለአፍታ ዝም አለች፡፡ ከዛም በኩራትና በስኬት በተሞላ የተዳከመ ድምፅ፣«ለአንድ ሰአት እንደ ፅጌረዳ አበባ በኩራት ኖሬአለሁ፤ ለጥቂት ጊዜም እንደ ንግስት ኖሬአለሁ፤
በፅጌረዳ አበባ አይኖችም ዓለምን ተመልክቻለሁ፤ የሰማዩን ድምፅ በፅጌረዳ አበባ ጆሮዎች አድምጫለሁ ፤የብርሀን ልብስንም በፅጌረዳ (ቅጠሎች) ዳስሻለሁ፡፡ ከእናንተ መሀል ይህን ክብር ያገኘ አለ?»
✍ካህሊል ጂብራን

🔥1
ከህይወት ጋር ፍቅር የያዛት ይመስላል...ከማግኘት፥ከማጣቱ ጋር ፣ ከውጣ ውረዱ ጋር ፤ ከመውጣት፥ከመውረዱ ጋር ፣ ከደስታም ከሐዘኑም ጋር ።
የምትል መርህ አላት።
አድር ባይ አይደለችም ሐቀኛ ናት ፤ የማይደረግ ነገር ሲደረግ ያስቆጣታል ማለፍ አትችልም ፥ በዚህም ሳቢያ ጋጠወጦች ፈፅመው አይወዷትም ። የዋህ ናት በጣም ለሰው ታስባለች ፤ ልወደድ ብላ ግን የማይሆን ነገር ይሁን ማለት አይቻላትም ።
...ትለፋለች ፣ ትደክማለች
የምትለው አባባል አላት ፤
ደግሞም ትላለች ።
እርሷ መሽቀርቀር አይደለም ውበቷ ፤ አፈር አይንካኝ በማለት አታምንም
ትላለች ።
ከህይወት ጋር ፍቅር የያዛት ትመስላለች ፤ እኔንም ልታሲዘኝ ነው።
ከ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ
©ሶፊ
ከፈጣሪ ውጪ ምንም ነገርን አጥብቀህ መያዝ የለብህም...ሁሉም የሚወድህ ከራሱ ወዲያ ነው ።
የምትል መርህ አላት።
አድር ባይ አይደለችም ሐቀኛ ናት ፤ የማይደረግ ነገር ሲደረግ ያስቆጣታል ማለፍ አትችልም ፥ በዚህም ሳቢያ ጋጠወጦች ፈፅመው አይወዷትም ። የዋህ ናት በጣም ለሰው ታስባለች ፤ ልወደድ ብላ ግን የማይሆን ነገር ይሁን ማለት አይቻላትም ።
...ትለፋለች ፣ ትደክማለች
የሚሰሩ እጆች የተባረኩ ናቸው
የምትለው አባባል አላት ፤
ስራዬ ነው ረፍቴ
ደግሞም ትላለች ።
እርሷ መሽቀርቀር አይደለም ውበቷ ፤ አፈር አይንካኝ በማለት አታምንም
የሰው ልጅ ውበቱ ስራው ነው
ትላለች ።
ከህይወት ጋር ፍቅር የያዛት ትመስላለች ፤ እኔንም ልታሲዘኝ ነው።
ከ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ
©ሶፊ
❤4
Educational Volunteers Needed!
Do you have just 2 hours per week to volunteer? You can join us in person or online!
What’s in it for you?
A certificate of participation.
An allowance to support your transport or internet needs.
What will you do?
Tutoring and Mentorship: Support students in public schools across Addis Ababa.
Educational Material Preparation: Create engaging and effective study materials online.
We’re looking for 2,000+ volunteers to make a real difference in education!
To apply fill out this form:https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLScdxzxUL65oVGsuZUhnDVYkO44L49PmO7uZ1bu3HCvb6_-YAQ/viewform?usp=pp_url&entry.1131561500=kalkida _wegene
Deadline to apply: Tuesday, December 3, 2024.
የ በጎ አድራጎት ሥራ መስራት ለምትፈልጉ ሁሉ ነዉ apply በማድረግ መስራት ይምችሉትን ሞክሩ..... Certificate ም አለው ተጠቀሙበት
Join us and help shape the future of students!

Google Docs
Kelem Tutors Volunteer Program Application Form
Be Part of Our Volunteer Tutoring Program for over 2000 volunteers and Make a Difference!
Do you care about education and want to make a positive impact in your community? Join our one-month volunteer program and help us create a brighter future for students…

እየዉልሽ ዓለሜ በዘመኔ ያስተዋልኩት ፍቅር ሁለት አይነት መልክ አለዉ፨አንዱ በግዴታም ይሁን በዉዴታ ሲገጥምሽ ራስሽ የምታበጃጅዉ ፍቅር ነዉ፨ሌላው ደግሞ ነፋስ የሚያመጣዉ ፍቅር ነዉ፨አሏት እማማ በምሽቱ መሃል እሳት ዳር ተቀምጠዉ እያወሩ..
ነፋስ..?
አዎ ንፋስ ..!
መነሻዉን መምጫዉን ሳታዉቂዉ ድንገት ከልብሽ ኖሮ ታገኝዋለሽ፨ያዉ ራሱ ያበጃጅሻል፨
ቆይ የትኛዉ ይበልጣል?
እኔ የማዉቀዉ ያበጀሁትን ነዉ፨ያዉ እስከዚ እድሜያችን ድረስ እንደተዋደድን እንደተፋቀርን አለን፨ሰዉ ያላየዉን እንዲህ ነዉ አይልም፨ብቻ ፍቅር ያዉ ፍቅር ነዉ፨ምን ለዉጥ አለዉ ብለሽ ነዉ ዓለሜ፨
እኔ እንጃ...ግን ወደ ልብ ከሚመጣ ይልቅ ልብ ዉስጥ ያለ የሚበልጥ ይመስለኛል፨እንጃ..🩵
#ዘመኔ
https://t.me/yeesua_queen

❤4👍1