Ethio Book Review
20K subscribers
436 photos
11 videos
5 files
305 links
The largest Ethiopian Digital Book Platform. Visit https://ethiobookreview.com
Download Telegram
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
4
ያነበባችሁ አላቹ? ይነበብ ወይስ?
👍3512
የመጽሐፍ ምረቃ እና የፊርማ ስነ-ስርዓት
የመጽሐፍ ርዕስ - ያልተመለሱ ዳናዎች
ዕለቱ - ቅዳሜ ሕዳር 27
ቦታ - ለገሃር ተወልደ ሕንጻ ስር አዲሱ ጃዕፈር መጻሕፍት
10👍4
የአቤ ጉበኛ የህይወት ታሪክ
ምንጭ፡ ሀሁ መጽሐፍ መደብር ፌስቡክ ገጽ

ደራሲ አቤ በምዕራብ ጎጃም ዞን በአቸፈር ወረዳ በልዮ ስሙ ኮረንች አቦ በተባለ ቀበሌ ከአባቱ አቶ ጉበኛ አምባየነና ከእናቱ ወ/ሮ ይጋርዱ በላይ ሰኔ 25/1925 ዓ.ም ተወለደ።

ዕድሜው ለትምህርት ሲደርስ በመጀመሪያ የአብነት በይስማላ ደብረ ገነት ቅ/ጊ ቤ/ክርስቲያን ዜማውን ዳዊቱን ቅንኔውን ለ12 ዓመታት የተከታተለ ሊቅ ነው። አቤ በዘመናዊ ትምህርቱን በዳንግላ ከተማ ይከታተል የነበረ ሲሆን በ1946 ዓ.ም ዳንግላን ትቶ ወደ አ/አ በመሄድ ባዕታ ቤ/ክርስቲያን ተጠግቶ እንደ ቆሎ ተማሪ ሆኖ ቆይተዋል።

አቤ ከልጅነቱ ጀምሮ ውስጡ የፁሑፍ ፍላጎት እና ችሎት ስለነበረው በ1949 ዓ.ም “ከመቅሰፍት ሰራዊት ይጠንቀቅ ሰውነት” በሚል ርዕስ አነስተኛ የግጥም መፅሐፍ አሳትሟል። አቤ በ26 ዓመቱ በማስታወቂያ ሚኒስቴር በጋዜጠኝነት ተቀጥሮ ሰርቷል። በ1953 ዓ.ም ባሳተመው “የሮም አወዳደቅ” ስያሜ ያለው የተውኔት መፅሐፍ በወቅቱ ገበሬው በንጉሡ ስርአት ያለውን ብሶት እና ቁጭት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ፅሁፍ ነበር።
በ1955 ዓ.ም ባወጣው “የአመፅ ኑዛዜ” በተሰኘው ልብወለድ መፅሀፍ ተምረው ሆነ ሰርተው ሀብት ያገኙ ሰዎች ድሀ ወገኖቻቸውን እንዲረዱ የሚያሳስብ ነበር።

ይቀጥላል...

www.ethiobookreview.com
29👍7😁3👎1
ሮማን ተወልደ "ዮዲታ" በተሰኘ አዲስ የግለ ታሪክ መጽሕፍ ይዛልን መታለች። እንኳን ደስ አለሽ እንበላት። ሮሚ የንባብ ባህል እንዲዳብር ለምትሰራው ስራ እናመሰግናታለን።
👍2613👏1
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን። ዌብሳይታችን www.ethiobookreview.com አሁን ላይ በወር እስከ 60ሺ ክሊኮችን በጉግል ሰርች ላይ እያገኘ ነው። እኛም በተቻለን መጠን መጻሕፍትንና የመጻሕፍት መረጃን የንባብ ባህላችን እንዲዳድብር ለማዳረስ እንሰራለን።

Nu faana waan taataniif galatoomaa! Marsariitiin keenya fayyadamtoota baay'ee horachaa kan jiru yoo ta'u nutis odeeffannoo kitaabolee garaagaraa aadaa dubbisaa cimsuu danda'an isiniif ni dhiyeessina. Galatoomaa!
32👍5
ልክ እንደችግሩ ይሄንንም ተሻምታችሁ ሸር አድርጉት!

ይሄው እንግዲህ ሜዳው! የግድ ሰው ካለመነ አንረዳም ካላልን በስተቀር ይሄ ሰው የማንንም እርዳታ ሳይሆን የስራውን ውጤት ያገኝ ዘንድ ይህን እናድርግ ...

በቅርቡ ተቸገረ ብለን ስንቀባበለው የነበረው ደራሲ ሀብታሙ አለባቸው እነዚህ የፃፋቸው መፅሐፍት ባለመሸጣቸው መጋዘን ውስጥ ተቆልፎባቸው የተገኙ ናቸው። ያሉት መፅሐፎች ብዛትና የአንዱን ዋጋ ከጋዜጠኛ ወሰንሰገድ ገብረኪዳን ፅሁፍ ላይ ኮፒ አድርጌ እንዲህ በአጭሩ አስቀምጨዋለሁ። እስቲ ሁላችንም ቢያንስ አንድ መፅሐፍ በመግዛት በቀናት ውስጥ እንጨርሳቸው። ከአገር ውጭ የሆንን ደግሞ እንደተለመደው! የገዛችሁ ፎቶ ተነስታችሁ ብትልኩልኝ በደስታ ፖስት አደርገዋለሁ! መፅሐፎቹ ሸልፋችን ላይ መገኘታቸው ለእኛም ትልቅ ሐብት ናቸው!!
👉 የሱፍ አበባ 384 መጽሐፍ ተገኝቷል ....የአንዱ ዋጋ 580 ብር
👉ጉልጥምት ኢትዮጵያ 378 ፍሬ.......580ብር
👉 አውሮራ 44 ፍሬ......400 ብር
👉አስኳላ 264ፍሬ.......450 ብር
👉 ታላቁ ተቃርኖ 700ፍሬ....700 ብር
👉 የቄሳር እምባ 1178 ፍሬ .....450ብር

የምትገዙበትን ቦታና ሁኔታ ለማወቅ ወሰንሰገድ ገብረኪዳንን ፃፉለት።

... ብሏል አሌክስ አብረሃም (Alex Abreham on Facebook)
51👍4🔥2👎1
እባክዎ በዌብሳይታችንና አገልግሎታችን ላይ ያለወትን ሀሰብ ይስጡን፣ ጉግል ላይም ሬት አድርጉንና የበለጠ ተደራሽ እንሁን!

https://g.page/r/CQzBsWRB7D8AEAE/review
9
አንዳንድ ሞቶችን ማመን ይከብዳል! ነፍስህ በሰላም ትረፍ ወንድማችን! 😭
😭2215💔8
ሲሳይን የምትወዱ እስኪ እንያችሁ!

Coming soon
42👍18🥰6👏4👎2
ተወዳጁ ደራሲ አለማየሁ ገላጋይ በ አዲስ መጽሐፍ እየመጣ ነው።

ፈሪሳ


https://www.ethiobookreview.com/book/-ferisa-alemayehu-gelagay
19🔥2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
Ethiopian Artificial Intelligence Institue ከ EhudAI ጋ በመተባበር ያዘጋጁት በAI በተሰራ ሙዝቃ አድዋን የመግለጽ ውድድር እየተካሄደ ነው።

እናንተም እንድትሳተፉ እየጠቆምናችሁ ይህንን የኛን ስራ ከወደዳችሁ በዚህ ሊንክ ገብታችሁ Vote እንድታደርጉልን በአክብሮት እንጠይቃችኋለን።

https://www.creativeaward.ai/submission/d605c3cf-0104-4c16-8c45-13eefd3ec40c
11👏1
👍205🔥2
የ Robert Kiyosaki "Rich Dad Poor Dad" ቁልፍ ሃሳቦች
በቀጣይ ይትኛውን መጽሐፍ እንስራላችሁ?
15👍1👌1