Ethiopian Trading Businesses Corporation (ETBC)
1.61K subscribers
1.43K photos
25 videos
30 files
88 links
Download Telegram
በመደበኛ ግዢ ላይ የተሰጠው ስልጠና ወቅቱን የጠበቀ መሆኑ ተገለጸ
ከነሀሴ 9-13/ 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት ቀናት በመደበኛ ግዢ ላይ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡ በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት አቶ ይርጋሸዋ ተሾመ የኮርፖሬት ህግ፣ ማህበራዊ ጉዳዮችና የአሰራር ዘዴ ማሻሻያ ም/ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እንደገለጹት ስልጠናው የ2015 በጀት ዓመት የግዢ ስራ ከመጀመሩ በፊት መሰጠቱ ወቅታዊ ስልጠና ያደርገዋል፡፡ በስልጠናው ሰልጣኞች የኮርፖሬሽኑን የግዢ ሂደትና አፈጻጸም ያለበትን ችግር የተገነዘቡበት መሆኑን ገልጸው በቀጣይ አመራሩም ሆነ ሰራተኛው መሰል ስልጠናዎችን እየወሰዱ አቅማቸውን ማጠናከርና ተመሳሳይ ግንዛቤ መያዝ አለባቸው ብለዋል፡፡
ም/ሥ/ አስፈጻሚው አክለውም በግዢ አሰራር ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት የግዢ መመሪያ መጽደቁን ጠቁመው፣ ከተሰጠው ስልጠና ጋር በቂ ስንቅ በመሆኑ ሁሉም ለስራ ዝግጁ መሆን እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ አያይዘውም ከግዢ ባለሙያዎች የሚጠበቁ ነገሮች በማለት ባስተላለፉት መልእክት የግዢ ባለሙያዎች የግዢን ዓላማ ማወቅና የግዢን ሂደት መገምገም ላይ ትኩረት አድርገው መስራት እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡ በእቅድ የተመራ ጥራት ያለው ግዢ በመፈጸም ተደጋጋሚ ግዢን ማስቀረትና ኮርፖሬሽኑን ከአላስፈላጊ ወጪ ማዳን እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡
የስልጠናው ተሳታፊዎች ስልጠናው በብቁ ባለሙያዎች የተሰጠ እና ወቅቱን የጠበቀ ስልጠና መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በመጨረሻም ስልጠናውን ለተከታተሉት ተሳታፊዎች የተሳትፎ የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል፡፡
IMG_20220902_110635.jpg
354.2 KB
የዝውውር/የውስጥ ዕድገት ማስታወቂያ
ከባድ የእምነት ማጉደል የሙስና ወንጀል የፈጸመ የኮርፖሬሽኑ ሠራተኛ በእስርና በገንዘብ ተቀጣ

አቶ ሙሉጌታ ጃሌ የተባለ በደሴ ቅርንጫፍ የሸዋሮቢት ግብይትና ክምችት ጣቢያ ሠራተኛ ሆኖ ሲሰራ በህዝብና በመንግስት የተሰጠው አደራ ወደ ጎን በመተው ተገቢ ያልሆነ ብልጽግና ለማግኘት በማሰብ ከ2.8 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያለው የመንግስት ንብረት በማጉደል በፈጸመው የሙስና ወንጀል የእስርና የገንዘብ ቅጣት ተወሰነበት፡፡
የኮርፖሬት የውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት ባደረገው ጥልቅ የሰነድ ምርመራ ግለሰቡ ከተረከበው የመንግስት የእህል ምርት ውስጥ ከ2.8 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው ምርት በህገ ወጥ መንገድ ከመጋዘን አውጥቶ በመሸጥ ከባድ የእምነት ማጉደል ወንጀል መፈጸሙ በማስረጃ ይረጋግጣል፡፡ ይህን የኦዲት ግኝት መሠረት በማድረግ የኮርፖሬት የህግ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት አስፈላጊውን ማጣራት ካደረገ በ|ላ ክስ ለመመስረት የሚያስፈልጉት መሠረታዊ ጭብጦችን በማዘጋጀት ወንጀሉ እንዲመረመርና ክስ እንዲመሰረት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን ለሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊሰ የሙስና ወንጀሎች ምርመራ ክፍል ጥያቄ ያቀርባል፡፡
የምርመራ ጥያቄው የቀረበለት የሰሜን ሸዋ ፖሊስ የሙስና ወንጀሎች ምርመራ ክፍል በተሰጠው ስልጣንና ኃላፊነት መሠረት አቶ ሙሉጌታ ጃሌ የፈጸሙት የእምነት ማጉደል የሙስና ወንጀልን በጥልቀት በመመርመር ተጠርጣሪውን ተከታትሎ በመያዝ ለህግ ያቀርባል፡፡
የክስ መዝገቡም በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፍትህ ቢሮ የደብረብርሃን ምድብ ማስተባበሪያ ተልኮ አቃቤ ህግም ክስ አቀርቦ ሲከራከር ቆይቶ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዕለቱ በዋለው ችሎት በጉዳዩ ላይ ግራና ቀኙን ካከራከረ በኃላ ተከሳሽ የቀረበበትን ክስ ማስተባበል ባለመቻሉና በከሳሽ በኩል የቀረቡት የሰነድ ማስረጃዎች ግለሰቡ ከፍተኛ የእምነት ማጉደል የሙስና ወንጀል መፈጸሙ ስለታመነ ተከሳሹን ያርማል ሌሎችንም ያስጠነቅቃል ብሎ ባመነበት ተከሳሽ ከኮርፖሬሽኑ እምነት በማጉደል የዘረፈውን ብር 2.890,031 (ሁለት ሚሊዮን ስምንት መቶ ዘጠና ሺህ ሰላሳ አንድ ብር) ከወጪና ኪሳራ ተሰልቶ እንዲከፍል፣በሁለት ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣትና በ9 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ፍርድ ቤቱ ወስኗል፡፡
ማጠቃለያ
በአጠቃላይ ከዚህ ግለሰብ ከባድ የእምነት ማጉደል የሙስና ወንጀል ድርጊት፣የክስ ሂደትና የፍርድ ውሳኔ መገንዘብ የሚቻለው ማንኛውም ግለሰብ የማጭበርበር የሙስና ወንጀል በመፈጸም የመንግስትና የሕዝብ ሀብትን ወስዶ ለጊዜው ከህግ ተሰውሮ ቢቆይም ወቅቱን ጠብቆ ከህግ ተጠያቂነት ማምለጥ እንደማይቻል የጥንቃቄ መልዕክት ለማስተላለፍ ነው፡፡ ስለዚህ በሚከተሉት የጥቆማ መስጫ መንገዶች ጥቆማ፣ቅሬታና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን በቅድሚያ እናሳውቃለን፡፡
በመደበኛ ስልክ፡-011 416 88 94 በተንቀሳቃሽ ስልክ፡-09 11 96 65 09, 09 11 65 96 96 - ፖ.ሳ.ቁ፡-3321
የኮርፖሬት ሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት
VAC1220143.jpg
1.8 MB
የዝውውር/የውስጥ ዕድገት ማስታወቂያ
ኮርፖሬሽኑ የሲሚንቶ ምርት ሽያጭ በማካሄድ ላይ ይገኛል

መንግስት ከሲሚንቶ ምርት ግብይት አኳያ የሚታየውን ችግርና የዋጋ ንረት ለማረጋጋትና የምርት ስርጭቱን ቅደም ተከተል በማስቀመጥ ግብይቱን ግልጽና ተደራሽ ለማድረግ እንዲያስችል የአሰራር ስርዓት ዘርግቷል፡፡ በመሆኑም ከአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በተላከው የሲሚንቶ ምርት፣ ግብይትና ስርጭት መመሪያ መሰረት የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን ለሲሚንቶ ምርት ፈላጊዎች ሽያጭ እያከናወነ ይገኛል፡፡

አስፈላጊውን መረጃ ላሟሉ ለመንግስት ግንባታ እና ለግል ገንቢዎች እንዲሁም ለብሎኬት አምራቾች ከነሐሴ 17/ 2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሆነ የሽያጭ ፕሮግራም ኮርፖሬሽኑ ያወጣ ሲሆን ተጠቃሚ የሚሆኑት ክፍለ ከተሞች ቂርቆስ፣ ልደታ፣ አዲስ ከተማ፣ ኮልፌ ቀራንዮ፣ ጉለሌ እና ንፋስ ስልክ ላፍቶ ናቸው፡፡ ከነሐሴ 17- 27/2014 ዓ.ም የቂርቆስ፣ የልደታ እና የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተሞች ተጠቃሚ የነበሩ ሲሆን ከነሐሴ 28/ 2014 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ተጠቃሚ በመሆን ላይ ይገኛል፡፡ የጉለሌ እና ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተሞች ደግሞ በመቀጠል በወጣላቸው ፕሮግራም መሰረት ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡
ለሲሚንቶ ተጠቃሚ ደንበኞች የወጣ የሽያጭ ፕሮግራምና ግዥ ለመፈፀም ማሟላት ያለባቸው መረጃዎች
ኮርፖሬሽኑን ለተቀላቀሉ አዲስ ሰራተኞች የትውውቅ ስልጠና ተሰጠ

የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽንን በቅርቡ ለተቀላቀሉ አዲስ ሰራተኞች የትውውቅ (ኢንዳክሽን) ስልጠና ጳጉሜ 03/ 2014 ዓ.ም ተካሄደ፡፡ ስልጠናውን ያዘጋጀው የኮርፖሬት የሰው ሃብት ልማትና ሥራ አፈጸጻም አመራር ቡድን ሲሆን የስልጠናው ዓላማ ለአዲስ ሰራተኞች የኮርፖሬሽኑን አጠቃላይ ገጽታ እና አሰራር ማስተዋወቅ ላይ ያተኮረ ነው፡፡

ስልጠናውን የሰጡት የኮርፖሬት ሰው ሃብት ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት፣ የኮርፖሬት የህግ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት፣ የኮርፖሬት ሥነ-ምግባርና ጸረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት እና የኮርፖሬት ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ሲሆኑ ከተለያዩ ዘርፎችና የስራ ክፍሎች የተውጣጡ ሰራተኞች በሥልጠናው ተካፍለዋል፡፡
የ2015 በጀት ዓመት የእቅድ ትውውቅ መድረክ ተካሄደ

የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን የ2015 በጀት ዓመት የእቅድ ትውውቅ መድረክ ከአራቱም ዘርፎች የተውጣጡ ሥራ አስፈጻሚዎች፣ አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት መስከረም 9/ 2015 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሆቴል ቁ.2 ተካሄደ፡፡

የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አቻ ደምሴ በመድረኩ መክፈቻ ላይ ባስተላለፉት መልእክት መድረኩ ትልቅ ትኩረት የተሰጠው መሆኑን በመጥቀስ የዓመቱን እቅድ በውጤታማነት ለማከናወን የሚያስችል አቅም ለመፍጠር መድረኩ መዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡ ከሰራተኞችም ጠቃሚ ግብአት እንደሚጠበቅም አያይዘው ጠቁመዋል፡፡ ዋና ሥራ አስፈጻሚው አክለውም ኮርፖሬሽኑ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ትርፋማ በመሆኑ ለአጠቃላይ ሰራተኞች የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ በየደረጃው ያሉ ሰራተኞችና አመራሮች ያደረጉት ጥረት ኮርፖሬሽኑን ትርፋማ እንዳደረገ ጠቁመዋል፡፡

በመድረኩ የኮርፖሬሽኑ የ2014 በጀት ዓመት ሪፖርት፣ በ2014 በጀት ዓመት በኮርፖሬሽኑ እቅድ አፈጻጸም የነበሩ ክፍተቶች እንዲሁም የሰራተኛ ማህበር ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡ ከሰኣት በኋላ በነበረው መርኃ ግብር የ2015 በጀት ዓመት እቅድ ቀርቦ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ በዋና መ/ቤትና በዘርፍ ደረጃ ከጀማሪ እስከ መካከለኛ ደረጃ ያሉ 400 ሰራተኞች በመድረኩ የተሳተፉ ሲሆን ከጥቂት ቀናት በኋላም ሌሎች 400 ሰራተኞችን ያካተተ ተመሳሳይ መድረክ እንደሚኖር ከወጣው መርሃ ግብር ለማወቅ ተችሏል፡፡ በቀጣይም የውይይት መድረኩ በሁሉም የክልል ግብይት ማዕከላት ተካሂዶ የማጠቃለያ መድረክ እንደሚኖር ተመላክቷል፡፡

የውይይት መድረኩን መጠናቀቅ ተከትሎ የመድረኩን ተሳታፊዎች በሙሉ ያካተተ የእራት ግብዣ ሥነ-ስርዓት ተካሂዷል፡፡