Ethiopian Trading Businesses Corporation (ETBC)
1.12K subscribers
508 photos
8 videos
29 files
34 links
Download Telegram
በሙያ ሥነ-ምግባር፣ በሙስና ወንጀል ህጎችና በምርት ጥራት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጠ

በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የኮርፖሬት ሥነ-ምግባር መከታተያ ክፍል ዳይሬክቶሬት ከአትክልትና ፍራፍሬ ንግድ ሥራ ዘርፍ ጋር በመተባበር ለዘርፉ የምርት ማከፋፈያና ሽያጭ ሠራተኞች በሥራ ሥነ-ምግባር፣ በሙስና ወንጀል የህግ ድንጋጌዎች እንዲሁም በምርት ጥራትና እንክብክካቤ ዙሪያ የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠና ሰጠ፡፡

በሥልጠናው መክፈቻ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የዘርፉ ሥራ አስፈጻሚ አቶ መህዲ አስፋው ባደረጉት ንግግር፤ ሥልጠናው ከምርት ክምችት አጠባበቅ፣ ከተገልጋዮች አያያዝ፣ ከሥራ ሰዓት አጠቃቀም፣ ከምርት አደረጃጀትና ከመሠል ጉዳዮች ጋር በተያያዙ የህግና ሥነ-ምግባር ጉዳዮች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርቱ እንደተዘጋጀ ገልጸዋል፡፡

በዕለቱ በሥራ ሥነ-ምግባር ምንነት፣ በወንጀል ህግ ዓላማ፣ በሙስና ወንጀል ድርጊቶች ምንነትና የሚያስከትሉ የቅጣት ዓይነት እንዲሁም የሙስና ወንጀል ድርጊት ምንነትና የቅጣት ዓይነቶች በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት በዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር አቶ ከድር ጀማልና በከፍተኛ የሥነ-ምግባር ባለሙያ አቶ አዲስ ዓለም አድማሱ ተሰጥቷል፡፡

የአትክልትና ፍራፍሬ ንግድ ሥራ ዘርፍ የምርት ጥራት ቡድን መሪ አቶ ሳለጌታ በምርት አቀባበል፣ አያያዝ፣ ሥርጭትና ብልሽት አወጋገድ ሂደት ጋር የተያያዙ የምርት ጥራትና እንክብክካቤ የአሠራር ሥርዓቶች ዙሪያ ትምህርት ሰጥተዋል፡፡

በአሠራርና በአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮችን በተመለከተ ከሽያጭ ሠራተኞች ጋር በተደረገው የማጠቃለያ ውይይት አሠራርን በማሻሻል የአገልግሎት አሰጣጥን ለማጎልበት የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡ በሥልጠናው 100 ሠራተኞች ተሣትፈዋል፡፡
የኮርፖሬሽኑ የበላይ አመራርና መካከለኛ ሥራ አመራር አባላት የኢትዮጵያ ስታርት አፕ" ኤግዚቢሽንን ጎበኙ

የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የበላይ አመራርና መካከለኛ ሥራ አመራር አባላት በኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዝየም በመካሄድ ላይ የሚገኘውን "የኢትዮጵያ ስታርት አፕ" ኤግዚቢሽን ሚያዚያ 17/ 2016 ዓ.ም ጎበኙ፡፡

የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አቻ ደምሴ የጉብኝቱን ፋይዳ አስመልክተው ባስተላለፉት መልእክት ጉብኝቱን ማዘጋጀት ያስፈለገው የሃገር ውስጥ የፈጠራ ስራዎችን ለማበረታታትና ቴክኖሎጂዎችን ለመጠቀም እንዲቻል እና እንደ ኮርፖሬሽን ምን መፍጠር ወይም መጠቀም እንችላለን የሚለውን አመራሩ የቤት ስራ እንዲወስድ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በጉብኝቱ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ በግብርና፣ በጤና፣ በትምህርት፣ በፋይናንስና በሌሎች መስኮች በርካታ አስደማሚ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን ለማየት ተችሏል፡፡

የኢትዮጵያ ስታርት አፕ ኤግዚቪሽን በተለያዩ ዘርፎች የተሰሩ ስታርት አፕ እና የተለያዩ ሁነቶች እየተካሄዱበት እስከ ሚያዚያ 20 ቀን 2016 ዓ.ም በሳይንስ ሙዝየም ለህዝብ ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ ከአዘጋጆቹ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ኮርፖሬሽኑ እያስገነባ የሚገኘው ሁለገብ ህንጻና ባለማቀዝቀዣ መጋዘን ተጎበኘ

የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን አቃቂ አለም ባንክ የሺ ቶታል አጠገብ እያስገነባው የሚገኘው የ2B+G+10 ባለቅይጥ ህንጻና የአትክልትና ፍራፍሬ ማቀዝቀዣ መጋዘን ግንባታ የኮርፖሬሽኑ የበላይ አመራርና የመካከለኛ አመራር አባላት በተገኙበት ሚያዝያ 18/ 2016 ዓ.ም ተጎበኘ፡፡

በጉብኝቱ ወቅት ግንባታው በተያዘለት እቅድ መሰረት እና በከፍተኛ ፍጥነት እየተካሄደ መሆኑንና በቴክኒክ ኮሚቴው በየጊዜው ክትትል እንደሚደረግለት የተገለጸ ሲሆን ግንባታው ኮርፖሬሽኑ የአገልግሎት አሰጣጡንና ተደራሽነቱን የሚያሳይበት እንዲሁም መሰል ፕሮጀክቶችን በሌሎች ቦታዎች የሚያስቀጥልበት እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

ባለቅይጥ ህንጻው የተለያዩ ሁለገብ አገልግሎቶች የሚሰጥ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የምርት ማሳያዎች፣ ቢሮዎች፣ ሱፐርማርኬት፣ ካፌ፣ የመኖሪያ አፓርታማ እና የስብሰባ አዳራሽ ይገኙበታል፡፡ ባለማቀዝቀዣ መጋዘኑ ደግሞ የተለያዩ አትክልትና ፍራፍሬዎችን ሳይበላሹ ለተጠቃሚው እንዲደርስ የሚያስችል የማቀዝቀዝ፣ የማቆየትና የማከፋፈል አገልግሎት የሚሰጥ እንደሆነ ተመልክቷል፡፡
የኮርፖሬሽኑ የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም ተገመገመ

የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን 2016 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸምን በስራ አመራር (ማኔጅመንት) ደረጃ ተገመገመ፡፡

በዘጠኝ ወራት የነበረው የእቅድ አፈጻጸም በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን በቀጣይ ቀናት አንዳንድ ማስተካከያዎች ተደርጎበትና ጸድቆ ይፋ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አቻ ደምሴ በቀሩት ሁለት ወራት የማካካሻ እቅድ በማዘጋጀት ያልተፈጸሙ ስራዎችን በመለየት፤ ከፍተኛ አፈጻጸም በማስመዝገብ ዓመቱን በስኬት ለማጠናቀቅ ሁሉም አመራርና ሰራተኛ በትጋት እንዲሰራ አሳስበዋል፡፡ አክለውም የ2017 በጀት ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ ከወዲሁ መዘጋጀት እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡

ከሪፖርቱ አስቀድሞ የኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት የቢሮ እድሳት ለማድረግ የተዘጋጀው ዲዛይን ቀርቦ አስተያየት እንዲሰጥበት የተደረገ ሲሆን የጨረታ ሂደቱ በቅርቡ ተጠናቆ ወደ ስራ እንደሚገባ ተመልክቷል፡፡
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ኮርፖሬሽኑ እያስገነባ የሚገኘው ሁለገብ ህንጻ እና ባለማቀዝቀዣ መጋዘን የግንባታ ሂደት