Ethiopian Trading Businesses Corporation (ETBC)
1.61K subscribers
1.43K photos
25 videos
30 files
88 links
Download Telegram
ለኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች በሙሉ (አስቸኳይ)

ጉዳዩ:- በሥነምግባር ምስጉን የሆነውን ሠራተኛ ዕውቅና እንድትሰጡት መጠየቅን ይመለከታል፤

በተባበሩት መንግስታት የፀረ ሙስና ኮንቬንሽን አባል ሀገራት ስምምነት ውሳኔ መሠረት ቀኑ በአባል ሀገራት በየዓመቱ እንዲከበር በተወሰነው መሠረት ዘንድሮ ማለትም በ2014 ዓ.ም በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ18ኛ ጊዜ በሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ ለ17ኛ ጊዜ "ሥነ ምግባርን በመገንባትና ሙስናን በመከላከል የግልፅነትና የተጠያቂነት መርህን ተግባራዊ እናድርግ!" በሚል መሪ ቃል በድምቀት ይከብራል፡፡

በኮርፖሬሽን ደረጃ ይህን ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በዓል ህዳር 25 ቀን 2014 ዓ.ም በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በማክበር በዝግጅቱ ሥነ-ሥርዓት ላይ በኮርፖሬሽንና በዘርፍ ደረጃ በሥነምግባራቸው ለተመሰገኑ የድርጅቱ ሠራተኞች እውቅናና ሽልማት ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡

በዚህም መሠረት በኮርፖሬሽን ደረጃ ሆነ በዘርፍ ደረጃ 12ቱን የሥነምግባር መርሆዎችን መሠረት በማድረግ ከሌሎች ሠራተኞች በተለየ መልኩ ምስጉን የሆኑ ማለትም በታማኝነታቸው፣በቅን አገልግሎታቸው፣ሙስናና ብልሹ አሠራሮችን በመታገልና በማጋለጥ፣የድርጅቱን ሀብትና ንብረት በማዳን፣በልዩ የፈጣራሥራና በወጪ ቁጠባ ሥርዓት እንዲሁም በሌሎችም መልካም የሥነምግባር ድርጊቶች የተመሰገኑ ሠራተኞች በመለየትና በመምረጥ ለኮርፖሬሽኑ ሰው ሀብት ወይም ለዘርፍ ሰው ሀብት ሥራ አመራር እንድታሳወቁ በማክበር እንጠይቃለን፡፡

ለትብብራችሁ በቅድሚያ እናመሰግናለን!!

የኮርፖሬት ሥነምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት
በሥነ ምግባር፣ በሕግና በፋይናንስ ደንብና አሠራር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጠ

የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የሚያካሂዳቸውን የንግድ ሥራዎች በዘመናዊ፣ ደንበኛ ተኮርና ከብልሹ አሠራር ነጻ በሆኑ አሠራሮች የማጎልበት ዕቅዱን ለማሳካት የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ትኩረት ከተሰጣቸው ጉዳዮች አንዱ በዋነኝነት በሽያጭና ተያያዥ በሆኑ የምርት ሥርጭትና የጥራት ቁጥጥር ሥራዎች ላይ የተሠማሩ ባለሙያዎችንና የሥራ ኃላፊዎችን የሥነ-ምግባር፣ የሕግ እና የፋይናንስ ግንዛቤ በሥልጠና ማጎልበት ነው፡፡

በዚህ ረገድ በኢንሥኮና በአትክልትና ንግድ ሥራ ዘርፍ ሰው ኃብት የሥራ ክፍሎች አስተባባሪነት በሥነ-ምግባር፣ ሕግና ፋይናንስ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ከዘርፉ ለተውጣጡ የሽያጭ፣ የምርት ሥርጭትና ጥራት ቁጥጥር ባለሙያዎችና ኃላፊዎች ከኅዳር 13-15 ቀን 2014 ዓ/ም በዘርፉ ዋና መ/ቤት የሥልጠና አዳራሽ ተሰጥቷል፡፡

በሦስት ዙር በተካሄደው ሥልጠና ለደንበኞች ሙያዊ ሥነ-ምግባር የተላበሰ አገልግሎት የመስጠትን አስፈላጊነትና ተቋማዊ ፋይዳ፤ በታክስና የገቢ ግብር አዋጅ፣ በአሠሪና ሠራተኛ ሕጎች እንዲሁም ተያያዥ በሆኑ የሠራተኛ ማኅበሩ ደንቦችና እነዚህን ተግባራዊ ካለማድረግ ሊመነጩ በሚችሉ ተጠያቂነቶችና ከሽያጭ ሥራዎች ጋር ተያያዥ በሆኑ የፋይናንስ አሠራሮች ዙሪያ ዙሪያ ገለጻ ተደርጓል፡፡

በሥልጠናው ከንግድ ሥራ ዘርፉ የተውጣጡ 114 የችርቻሮ ሱቅ ሠራተኞች፣ የምርት ግዥና ሥርጭት ሠራተኞች፣ የምርት ጥራት ቡድን ባለሙያዎች፣ የምርት ጥራትና እንክብካቤ ባለሙያዎች እንዲሁም የሀብት አመራር ሠራተኞች ተሣትፈዋል፡፡
የሐዘን መግለጫ

የኮርፖሬሽናችን ኮርፖሬት ሰርቪስ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ ታሪኩ በራሱ ባደረባቸው ህመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸው የተሠማንን ጥልቅ ሐዘን እየገለጽን፤ ለቤተሰባቸው፣ ለዘመዶቻቸውና ለሥራ ባልደረቦቻቸው መጽናናትን እንመኛለን፡፡

የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን
ለኮርፖሬሽን ሠራተኞች በሙሉ (አስቸኳይ)

ጉዳዩ:- በሥነ-ምግባር ምስጉን ሆነው ለተመረጡ ሠራተኞች ዕውቅና እንድትሰጡ ስለመጠየቅ

በኮርፖሬሽን ደረጃ በ2014 ዓ.ም በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ18ኛ፣በሀገራችን ኢትዮጵያ ለ17ኛ ጊዜ፣"በሥነምግባር የታነፀ አመራር ከሙስና ለፀዳች ኢትዮÉያ!" በሚል መሪ ቃል በድምቀት ይከብራል፡፡

ይህን ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በዓል ታህሳስ 02 ቀን 2014 ዓ.ም በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በማክበር በዝግጅቱ ሥነ-ሥርዓት ላይ በኮርፖሬሽንና በዘርፍ ደረጃ በሥነምግባራቸው ለተመሰገኑ የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች እውቅናና ሽልማት ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡

በዚህም መሠረት በኮርፖሬሽን ሆነ በዘርፍ ደረጃ 12ቱን የሥነምግባር መርሆዎችን መሠረት በማድረግ ከሌሎች ሠራተኞች በተለየ መልኩ ምስጉን የሆኑ ማለትም በታማኝነታቸው፣በቅን አገልግሎታቸው፣ሙስናና ብልሹ አሠራሮችን በመታገልና በማጋለጥ፣የድርጅቱን ሀብትና ንብረት በማዳን፣የውስጥ ገቢ በማሳደግ፣በልዩ የፈጣራ ሥራና በወጪ ቁጠባ ሥርዓት እንዲሁም በሌሎችም መልካም የሥነምግባር ባህርያት የተመሰገኑ ሠራተኞችን በኮርፖሬሽንና በዘርፍ ደረጃ በሠራተኞችና በሥራ አመራሩ የመጀመሪያ ዙር ምልመላ ተካሄዶ ሠራተኞች ተመርጠዋል፡፡

ስለዚህ ከዚህ በታች በተቀመጠው መስፈርት መሠረት የተመለመሉ 16 ሠራተኞች በተመለከተ አስተያየት እንድትሰጡ እንዲሁም ለሌሎች አርዓያ ሊሆኑ የሚችሉ ሠራተኞች ካሉም ይህ ማስታወቂያ በወጣ በ2/ሁለት/ ቀን ውስጥ ለኮርፖሬት ሰው ሀብትና ሥራ አመራር ዳይሬክቶሬትና ለዘርፍ ሀብት አመራር መምሪያ ሪፖርት እንድታደርጉ እንጠይቃለን፡፡
የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን አመራርና ሠራተኞች ዓለም አቀፉን የፀረ-ሙስና፣ የኤች አይቪ ኤድስና ፀረ-ጾታዊ ጥቃት ቀናትን በጋራ አከበሩ

የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን አመራርና ሠራተኞች በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ18ኛ በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ17ኛ ጊዜ ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በዓል እንዲሁም ዓለም አቀፍ የኤች አይቪ ኤድስ ቀንን ታህሳስ 2 ቀን 2014 ዓ/ም ጎተራ በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ሁለገብ የስብሰባ አዳራሽ አክብረዋል፡፡

"በሥነምግባር የታነፀ አመራር ከሙስና ለፀዳች ኢትዮጵያ!" እና "አገልግሎቶችን ለተጠቃሚዎች በእኩልነት ማድረስ- ወረርሽኙን መግታት!!" በሚሉ መሪ ቃሎች በተከበረው በዚህ በዓል ላይ ከ230 በላይ የኮርፖሬሽኑ አመራርና ሠራተኞች ተገኝተዋል፡፡ በዕለቱ ከኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማህበር የተጋበዙ ባለሙያዎች የኤች አይቪ ኤድስ ምንነትና መከላከያ ዘዴዎች እንዲሁም ጾታዊ ጥቃቶች በሴቶች ላይ የሚያደርሱት ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ሥነልቦናዊ ጉዳቶች በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርቶች ሰጥተዋል፡፡

ባለሙያዎቹ ከዚህ ጋር አያይዘውም በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ በገዳይነት በቀዳሚነት ከተመዘገቡት የካንሰር ዓይነቶች ውስጥ አንዱ ስለሆነው የጡት ካንሰርና የማህጸን በር የጤና እክሎች ገለጻ የሰጡ ሲሆን ካንሰር እድሜያቸው ከ30-49 ክልል ውስጥ ያሉ ሴቶችን የሚያጠቁ በሽታዎች በመሆናቸው ክፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚያስፈልገው ሆኖም በሽታዎቹ ፈዋሽና ቀላል ህክምናዎች ስላላቸው በየትኛውም የጤና ማዕከል ምርመራ በማድረግ መከላከል እንደሚቻል ለተሳታፊዎቹ ትምህርት ሰጥተዋል፡፡

ከፌደራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን የመጡ ባለሙያ የሙስና ምንነት፣የሙስና ዓይነቶች፣የሙስና መንስኤዎች፣ ሙስና የሚያስከትለው ጉዳቶችና የመከላከያ ስልቶች በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ ከሰጡ በኃላ ሙስና የሰው ልጆችን ሰላም በማሳጣት፣ፍትህ በመጓደል፣የሀገርን ኢኮኖሚ በማድቀቅ፣ማህበራዊ ኪሳራ በማድረስ እና ዲሞክራሲ ሥርዓትን በማቀጨጭ በኩል ዋና ሚና የሚጫወት መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ ማጠቃለያ ላይ የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አቻ ደምሴ የዕለቱን መርሃ ግብር አስመልክተው ባደረጉት ንግግር፣ ጤንነቱ የተጠበቀ አመራርና ሠራተኛ ለተቋሙ እድገት ያለው አስተዋፅኦ ወሳኝ መሆኑን ገልጸው ኮርፖሬሽኑ የንግድ ተቋም ከመሆኑ አንጻር አገልግሎት አሰጣጡን ሙያዊ ሥነ-ምግባርን በጠበቀ መልኩ ደንበኛ ተኮር በማድረግ ግልጸኝነትና ተጠያቂነት ያለው አሠራርን ለማስፈን ተከታታይ ስልጠናዎች እንደተሰጠ እና ወደፊትም እንደሚሰጥ አመልክተዋል፡፡

አያያዘውም የድርጅቱ ውጤታማነት የሚለካው በደንበኞቻችን እርካታ ብቻ በመሆኑ ሁሉም ሠራተኛ በድርጅቱ ውስጥ ሙስናና ብልሹ አሠራር ተፈጽሞ ሲገኝ ለሚመለከተው የሥራ ክፍል ጥቆማ በመስጠት፣አገልግሎት ሲሰጥም የመልካም ሥነምግባር እሴቶች በመላበስ ማገልገል እንዳለበት አሳስበው በተለይ በፀረ-ሙስና ትግሉ ሁሉም ሠራተኛ ንቁ ተሳትፎ የማድረግ ተግባሩን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ በመጨረሻም በዓሉ በደመቀ ሁኔታ እንዲከበር አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የኮርፖሬሽኑ አመራር እና ሰራተኞች ለሀገር መከላከያ ሰራዊትና በጦርነቱ ለተፈናቀሉ ወገኖች ለሁለተኛ ጊዜ የደም ልገሳና ቁሳቁሶች የማሰባሰብ መርኃ ግብር አካሄዱ

የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን አመራር እና ሠራተኞች ታህሳስ 12 ቀን 2014 ዓ/ም በኮርፖሬሽኑ ዋና መስሪያ ቤት ለሁለተኛ ጊዜ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የደም ልገሳ እና በጦርነቱ ለተፈናቀሉ ወገኖች የተለያዩ ቁሳቁሶችን የማሰባሰብ መርኃ ግብር አካሄዱ፡፡

በኮርፖሬት የማህበራዊ ጉዳዮች ጽ/ቤት አስተባባሪነት ከኮርፖሬሽኑ አመራር እና ሠራተኞች የተሰባሰቡት አልባሳት፣ የህጻናትና የሴቶች የንጽህና መጠበቂያ ምርቶች፣ የልጆች ወተት እና የታሸጉ ምግቦች መሆናቸውን የገለጹት የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ወ/ሮ ትዕግስት በጅጋ፤ ኮርፖሬሽኑ ለሀገር መከላከያ ሠራዊትና በጦርነቱ ለተፈናቀሉ ወገኖች ግንባር ድረስ በመሄድ ለማስረከብ በጥቅሉ የሶስት ሚሊየን ብር ድጋፍ በገንዘብና በዓይነት ማዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡