በወልቂጤ ከተማ ከሆቴል ውስጥ ንብረት ሰርቆ ሲወጣ የተያዘው ተከሳሽ በ7 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ጉብሬ ክፍለ ከተማ ሆቴል ዉስጥ በመግባት ከ85 ሺህ ብር በላይ የሚያወጡ የተለያዩ ንብረቶችን ሰርቆ ሲወጣ እጅ ከፍንጅ የተያዘው ተከሳሽ በ7 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ ተላልፎበታል ።
ተከሳሽ ተባረክ መሀመድ በወልቂጤ ከተማ ጉብሬ ክፍለ ከተማ ከለሊቱ 9 ሰዓት ላይ 85 ሺህ 400 ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የተለያዩ ንብረቶችን ሰርቆ ከሆቴሉ ለመዉጣት ሲሞክር በሆቴሉ የጥበቃ ሰራተኛ እጅ ከፍንጅ ተይዞ ለፖሊስ ተላልፎ መሰጠቱን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ ክፍል ሃላፊ ምክትል ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።
በዚህ መሠረት ዐቃቤ ህግ ከፖሊስ መዝገቡን ተረክቦ የመሰረተዉ ክስ የተመለከተዉ የወልቂጤ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተከሳሽን ጥፋተኛ ሲል ብይን ሰጥቷል። ስለሆነም ፍርድ ቤቱተ ተከሳሽ ተባረክ መሀመድ በፈፀመዉ ከባድ የስርቆት ወንጀል በ7 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።

ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን በትግራይ የቀድሞ ተዋጊዎችን የመበተን (DDR) ስራን በ “ሰኔ” ወር የሚጀምር መሆኑ ተገለጸ
በኢትዮጵያ የካናዳ ኢምባሲ፤ ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን “በትግራይ ክልል የቀድሞ ተዋጊዎችን የመበተን እና መልሶ የማቋቋም ስራን በመጭው ሰኔ ወር ለመጀመር ቁርጠኛ” መሆኑን አስታወቀ።
ይህ የተገለፀው በኢትዮጵያ የካናዳ አምባሳደር የሆኑት ጆሹዋ ታባህ ከብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን ጋር በትላንትናው ዕለት "በፕሮግራሙ ቀጣይ እርምጃዎች" ላይ ትኩረቱን ያደረግ ውይይት ማደረጋቸው ተከትሎ ነው።
“በህወሓት እና በፌደራል መንግስቱ መካከል የተደረሰው የ ፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ሙሉ ለሙሉ እንዲተገበር ካናዳ ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ” መሆኗን ኢምባሲው አረጋግጠጧል።
ውይይቱን ተከትሎ አምባሳደሩ በበኩላቸው በኤክስ (የቀድሞው ትዊተር) ገጻቸው ላይ ባሰፈረው መልዕክት፤ " የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደ ሲቪል ህይወት ለማሸጋገር የሚደረገውን ቀጣይ እርምጃዎችን ለመደገፍ በጉጉት እጠብቃለሁ" ብለዋል።

👍1