ኢርከብ ማዓና إركب معنا
268 subscribers
522 photos
43 videos
1 file
194 links
۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩
በቴሌ ግራም መረጃዎች ልዩ ልዩ ኢስላማዊ ስነ ፅሁፎች ፤ ሙሓደራዎች ፤ የተለያዮ ቂርዓቶች እንዲደርሳችሁ ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉን
http://t.me/erkebmeana
ለሀሳብና ለጥቆማ 👇
@ErkebmeanaBot
Download Telegram
የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦

«በጁምዓ ሌሊትና በጁምዓ ቀን ላይ በእኔ ላይ ሰለዋት ማውረድ አብዙ፣ በእኔ ላይ አንድ ሰለዋት ያወረደ አላህ በእርሱ ላይ አስር ሰለዋት ያወርድለታል።»

ኢማሙ አልባኒ ሀዲሱን ፦ " ሐሰን " ብለውታል።
አትተች
Hamid Hadi
=========
መኪናህ ውስጥ ገብቶ "ውይ መኪናህ እንዴት አርጅታለች እባክህ ። "
         ቤትህ ሲመጣ ደግሞ " የቤት እቃዎችህ ሁሉ የበፊቶቹ ናቸው አልቀየርካቸውም እንዴ?? 

       አንድ እንግዳህ  በርህን አንኳኳ ፣ እንኳን ደህና መጣህ ብለህ ሳሎንህ ውስጥ አስገብተህ ። ሻይ ቀድተህ ስትሰጠው ብርጭቆውን ተመልክቶ "ለምን አልሞላከውም? " ይልሓል ። አምጣው ልሙላልህ ስትለው " አይ ይበቃል ተወው ይልሓል ።

      ሁሌም የእስልምና ጢቢባኖች ፐፕሊክ ፊገር ላይ ወጥተው ዲኑን፣ ተውሒዱን እንዲያስተምሩልን እንፈልጋለን ። ይናገራሉ ያስተምራሉ
ግን ትተቻቸዋለህ ፣ አቋሙ ውረደዋል ። አረ እንዲህ ብሎ መቅረብ የለበትም ትላለህ ..... ወዘተ እያልክ ትተቻለህ  እሺ ና እና ቦታውም ተረከብ ሲባል አይ እኔ ምን አቃለው ገና ነኝ ይልሓል ። አይ ሰው !!

ይህን ስል ለሰዎች ምክር አትስጡ ወይም ሲሳሳቱ ዝም ብላችሁ እይዋቸው ማለቴ አይደለም ።ይልቁንም ሰዎች የሚሰሩትን ነገር ሁሉ በጥንቃቄ አትመርምሩ ለማለት ነው ።

ነብዮ (ሰ.ዐ.ወ)  አንድ ሰው ስህተት መስራቱን መስራቱን ሲረዱ ሰውዬውን በቀጥታ አይጋፈጡትም ። " እንዲህ እንዲህ የሚያደረጉ ሰዎች ምን ነካቸው? " ነበር የሚሉት ። በብዙ ሀዲሶች ላይ እንዲህ አይነት ምክሮች አሏቸው ።
         
      በአጭሩ እሳቸው "ዱላቸውን ከእርቀት ነው የሚያውለበልቡት ።ሆኖም ማንንም አይመቱበትም "።

በስተመጨረሻም 👇

ምንም መተቸት አስፈላጊ ሲሆንብህ በርህራሔ አድርገው እደግመዋለው በርህራሔ አድርገው  ። ከመተቸት ይልቅ እንደ አስተያየት አድርገህ አቅርበው ።

አላህ የበለጠውን ያውቃል
ኢንተሓ ከላሙሁ ሀፊዘሁላሁ ተዓላ
# ግልባጭ ለተቺያን ማህበር
ሁሌም ህያው በሆነው በአርሹ ባለቤት ተመካ ከጭቃ የተፈጠሩና ነገም ወደዛው የሚመለሱ ደካማ የሰው ልጆችን ተስፋ አታድርግ ፤የነርሱ መራቅና መቅረብ መውደድና መጥላታቸውም አንተ ዘንድ እኩል ይሁኑ...!!
ኡስታዝ አህመድ አደም ሀፊዘሁሏህ
ጁነይድ ከሱብሒ በፊት ጭልጥ ባለ እንቅልፍ ከንፏል። በዚህ መሃል፦ «ባርያዬ ሆይ ንቃ! ያን ባርያ ሂደህ ድረስለት» የሚል ድምፅ ሰማ።(ህልም)

«ጌታዬ ሆይ! ያን ባርያህን ከየት አገኘዋለሁ?» አለ።
«ፈረስህ ላይ ወጥተህ ጋልብ ፈረሱ ሚቆምበት ባርያዬን ታገኘዋለህ» የሚል ምላሽ ሰማ።

ከእንቅልፉ ነቃ። ሱብሂ መቃረብያ ስለነበረም ውዱእ አድርጎ ፈረሱን ይጋልብ ጀመር። የባግዳዳን ከተማ ከፊሉን እየጋለበ ካገመሰ በኋላ ፈረሱ ከመስጅድ ደጃፍ ቀጥ አለ።

ያ ሰው እዚህ ይኖራል ብሎ ከመስጅዱ ዘልቆ ቢገባ፦ «ያ ረብ ፈርጀኝ...! ያ ረብ ድረስልኝ....! » እያለ የሚያለቅስ ሰው ተመለከተ።

ተፈላጊው ሰውዬ መገኘቱን ያረጋገጠው ጁነይድ መቶ ዲናር አውጥቶ ከሰውዬ እጅ ላይ አሳረፈ። ሰውዬ የምስጋናም ቃላት ከአፉ ሳይወጣ፤ ገንዘቡን የሰጠውንም አካል ዞር ብሎ ሳያይ፦ «ያ ረብ ምስጋና ላንተ ይሁን! » እያለ ያለቅስ ጀመር።

«ወንድሜ የሰጠሁኽ ገንዘብ ለሀጃህ በቂ ካልሆነ ጁነይድ ማን ነው ብለህ ባግዳድ ውስጥ ማንንም ጠይቅ ይጠቁሙሃል፤ ምትፈልገውን እሰጥሃለሁ» አለ ጁነይድ።

«እንዴ! ጁነይድ ያምሃል ልበል?» አለ ሰውየው ቀና ብሎም ሳያይ።
«እንዴት አልክ?» ግራ በመጋባት ስሜት ጠየቀው።
ሰውየውም፦ «እንድያው ስታስበው ለኔ ጉዳይ ማስፈፀምያ ከተኛህበት ቀስቅሶህ ያመጣህን ጌታ መለመን ትቼ ቢቸግረኝ ያንተን ስም እየጠራሁ ከተማውን የምዞር ይመስልሃል?»
_________

የጌታህ ቋሚ ደንበኛ ስትሆን...እንዲህ ነው።
Sefwan Ahmedin
ምንጭ፦
حلية الأولياء وطبقات الأصفياء
ኢልም ከአደብ ጋ ካልተቆራኘ አጥፊ ነው፣ በራህማ ያልተገራ እውቀት አውዳሚ ነው፣ ዒልሙም ሳይኖርህ አደቡንም ካሳጣህማ አህመቅ ሆነህ ነው የምትቀረው። እያበላሸህ ያስትካከልክ ይመስልሀል፣ በግልፅ እያጠፋህ እንዳለማህ ነው የሚሰማህ። በተለይ ሶሻል ሚዲያው ለእንደዚህ አይነት አህመቆች አሪፍ የመጫወቻ ሜዳ ፈጥሮላቸዋል። ሜዳው ሀይ ባይ ዳኛ ስለሌለው ሁሉም እንዳሻው ነው የሚፈነጭበት።

ዑለማዖች ብዙ በህث አድርገው የተኻለፉባቸውን ፊቅሀዊ አጀንዳዎች ሼኽ የሌላቸው ወይም ሼኻቸው English translation ወይም Google የሆኑ አንዳንድ ሰዎች እንደቀልድ ሁክም/ብይን ሲሰጡ ማየት ወላሂ ያሳቅቃል። ወንድሜ ዒልም እኮ አማና ነው፣ ለዛውም የአላህና የረሱሉ አደራ። ቀደምቶቹ ዒልምን ፍለጋ ወራትን የተጓዙት፣ አመታትን የኳተኑት እኮ አደራው ከባድ ስለሆነ ነው። ከሁሉ የሚገርመው ለህክምናው ዶክተሩን ጠርተን ለቤት ግንባታው ኢንጂነሩን ብለን ልክ ሸሪዓዊ ዒልሙ ጋ ስንመጣ ሁላችንም ሀሳብ ካልሰጠን የምንለው ነገር ነው እያጠፋን ያለው። እውቀት ዑለማዎች ስር ተቀምጦ በመማር ብቻ ነው የሚገኘው፣ የግል ንባብ ከነሱ የተማርከውን ለማደበር ብቻ ነው የሚጠቅምህ።

"ያለ እውቀት ፈትዋ ይሰጣሉ፣ ጠመውም ያጠማሉ" ሰዐወ
አስቂኝ ክስተት ፈገግ በሉበት‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
የመን ውስጥ ዘማር የተባለ ቦታ ላይ አንድ መስጂድ ውስጥ የተከሰተ በጣም አስቂኝ ክስተት ነው አንብበው ሳይጨርሱ በሳቅ ሟቋረጥ ግን አይቻልም¡
||
ይህ ክስተት እዚያው መስጂዱ ውስጥ ሶ'ፈል አወል (የመጀመሪያው ሰፍ) ላይ ቆሞ ሲሰግድ የነበረ አንድ ሰጋጅ ነው የሚያስተላልፍልን...
*
እናም ይህ ሰው እንዲህ ይለናል:-
«አንድ ሰው ይሞትና ተሰግዶበት ተቀበረ ከዚያም ከኢሻ ሶላት በኋላ ነእሹ (ጀናዛ መሸከሚያው) ሊመልሱት ይዘውት ወደ መስጂድ ሲመጡ ሰአት ሄዶ ስለነበር መስጂዱ ተዘግቷል።

ስለዚህ ኻዲሞች ለፈጅር ሶላት ሲመጡ እንዲያነሱት በሚል ጀናዛ መሸከሚያው ከመስጂዱ በር ከደረጃ ላይ ያስቀምጡታል።
:
ነገር ግን ሌሊት 9:30 ሰአት አካባቢ አንድ ሰውዬ ወደ መስጂድ ሲመጣ መስጂዱ ዝግ ሆኖ እና በረንዳው ተከፍቶ አገኘው የተወሰነ ቢጠብቅም መስጂዱን የሚከፍተው አጣ ብርዱ በጣም ሲበረታበት ዞር ብሎ ሲያይ ጀናዛ መሸከሚያው ከአጠገቡ አገኘ በውስጡም ብርድልብስ ነገር አለ።
:
እና ይህ ሰው አገኘሁ ብሎ ጀናዛ መሸከሚያው ውስጥ ብርድ-ልብሱን ለብሶ ለጥ ብሎ እንቅልፉን ተኛ አባቴ! በብርድ ደንዝዞ የነበረው ሰውነቱ ትንሽ ምቾት ሲያገኝ ነፍሱንም አያውቅ ለጥ ብሎ ተኝቶልሀል...
ሃሃሃ!

ትንሽ እንደቆየ የመስጂዱ ኻዲም መጥቶ መሲጂዱ ሊከፍት ሲል በረንዳ ላይ ከነእሹ (ጀናዛ መሸከሚያው) ላይ የተኛ ሰውዬ ይመለከታል ከፈጅር በኋላ ሊሰገድበት ያመጡት ጀናዛ መሰለው...
:
ከኋላውም ሌሎች ሰዎች መጥቶ ግማሹ ሽንት ቤት ሌላው ውዱእ ሊያደርግ ይሄዳሉ ይህ በረንዳ ላይ ተኝቶ የሚያዩት ሰውዬ (ጀናዛ) ደግሞ ሁሉም ቀድመውኝ የመጡ ሰዎች ሊሰገድበት ያመጡት ጀናዛ ነው ብሎ ያስባል በውስጡ...
(ያዝ እንግዲህ¡)

በዚያ ላይ ፈጅር ነው ሰው ከእንቅልፉ ተነስቶ እየመጣ ነው ያለው ገና በደንብ ያልነቃ ህዝብ ነው።

ሊሰገድበት የመጣ ጀናዛ ይሆናል በማለት ተጋግዘው ወደ መስጂድ ኢማሙ ጋር ወደ ሚህራብ አስገቡት።
ሃሃ!
:
ብ ር ድ የቀጠቀጠው ሰውዬ ሲሸከሙት አያውቅ ተኝቷል¡ ህእ! ሰዎቹም የማን ይሁን ብለው አይጠይቁ ገና ከእንቅልፋቸው በደንብ አልነቁም እና ተሸክመው መስጂድ ውስጥ አስገቡት።

ፈጅር አዛን ብሎ ለመስገድ ወደ 50 የሚሆኑ ሰዎች ተሰበሰቡ።

ይህንን ታሪክ የሚያስተላልፍልን ሰው እኔም ከሰጋጆቹ አንዱ ነኝ የመጀመሪያው ሶፍ ላይ ነበርኩ ይላል።

ከፈርድ በኋላ ልንሰግድበት ጀናዛው ከፊት ተደርጎ የፈጅር ሶላት እየሰገድን ነው።
እህእ!
:
ልክ ለሁለተኛው ረከአ ስንነሳ ጂናዛው ሲንቀሳቀስ አየሁ እንዴዴዴ አይኔ ነው ወይስ ምንድ ነው¿ ብዬ አይኔን አበስኩ ጨፍኜም ገለጥኩ መንቀሳቀሱን ግን አልተወም በቃ እንቅልፍ አለቀቀኝም ይሆናል ብዬ አሰብኩ።

ነገር ግን ነእሹ በደንብ መንቀሳቀስ ጀመረ ያኔ መረባበሽና መፍራት ጀመርኩ።

ይህ የተኛው ሰውዬ ከብርድ ልብሱ ውስጥ ድንገት አንገቱ አውጥቶ ሰገዳችሁ? ብሎ ጠየቀ።
:
ያኔ! ሁሉም ሰጋጆች ደንግጦ መተረማመስና መሮጥ ጀመሩ እኔም አጠገቤ ከነበረው በር ወጥቼ በባዶ እግሬ ሮጥኩኝ ወደ 1 ኪ.ሜ ያክል የሚርቀውን ቤቴን በትንሽ ደቂቃዎች ደረስኩ ደግሞ ባዶ እግሬ መሆኔም የማውቀው ነገር የለም።
ኢማሙ (አሰጋጁም) ሲያየው ደንግጦ መሬት ላይ ይወድቋል ሌሎች ሰዎች ግማሹ ከግድግዳ ጋር ይጋጫል ሌላው ደግሞ ልክ እንደኔው በባዶ እግሩ ይሮጣል መስጂድ ውስጥ አንድ ሰው አልቀረም።
:
አሁንም ሌላኛው በጣጣጣም የሚያስቀው ክስተት ተከሰተ

ያ ከሬሳ መሸከሚያ(ከነእሹ) ላይ ተኝቶ የነበረው ሰውዬ ሲነሳ ሰዎች ሲሸሹ ሲሮጡ ሲያይ ከኋላቸው ተከትሎ መሮጥ ጀመረ።
እናንተ ምን ሆናችሁ ነው ? ቂያማ ቆሞ ነው እንዴ? እያለ ከኋላ ኋላቸው መሮጥ ጀመረ።
ሃሃሃ!
:
ሰዎቹ ደግሞ ወደ ኋላቸው ሲዞሩ ይህ ሰውዬ እየተከተላቸው መሆኑ ያያሉ ያኔ ይብስባቸዋል ባለ በሌለ ሀይላቸው ይሮጣሉ።
በዚህ መልኩ ሁሉም ሰላታቸውን አቋርጠው ሮጡ...»
ይለናል ቦታው ላይ የነበረ አንዱ ሰጋጅ።
:
መቼም ይህንን አንብቦ ያልሳቀ ካለ እኔንጃ¡
ሳቃችሁን በኮመንት!
||
አረበኛው👇
اقامو الصلاة
انا من بينهم وقفت بالصف الاول.
وبدئنا ودخلنا بالصلاة
وبالركعة الثانية يا جماعة شفت النعش بيتحرك !
ايش في مش معقول !
مسحت عيوني وغمضتهم وفتحتهم .. قلت يمكن انا في حلم ..
المهم النعش بجانب المحراب مازال بيتحررك أمام المصليين والإمام !!!!
هنا بدأت الوساويس تجي برأسي والخوف والقلق .
​المهم
قام الاخ اللي داخل النعش صحى من النوم وفتح غطاء النعش وخرج راسه .
وقال : صليتوا ؟؟؟؟؟؟

​هنا وقعت الفاجعة للجميع​
وعينك ماتشوف الا النور لو تشوفوا ايش حصل بالمسجد
انا من ناحيتي خرجت من المسجد حافي وبسرعة ​كيلو متر بالدقيقة​ للبيت ومش عارف اننا حافي ..
شفت الإمام دوخ وسقط بالارض
وباقي الناس الي صدم راسة بالجدار والي خرج حافي مثلي
والي سقط عند مكان الوضوء في البركة
وعينك ما تشوف الا النور،
ولا بقى واحد بالمسجد
الكل هرب
​واللي يموتك ضحك​
ان الرجال الذي خرج من النعش هرب مع من هرب ويلحق وراهم ويصيح ياناس ايش حصل او قامت القيامة ولا ايش وهم كل مايلتفتوا يلقوه داعس وراهم ويزيدوا يطيروا اكثر وهو جالس يصيح ليش ما صحيتوني اصلي الفجر حسابكم على الله بدون ما يعرف انه سبب الذعر والخوف هذا كله فعلا والله حصلت بليمن مش كذب...

أبو عبدالرحمن بن علي
هل حصلت في ذمار صحيح
Yasin Mohammed
Hassen Ibn Hussen
#አቡበክር_አልባቅላኒይ
ይህ ሰው ትልቅ ዓሊም ከመሆኑም ባሻገር ክርክር ላይ ሚስተካከለው ሰው የለም ነበር።
እናላችሁ የሆነ ቀን ይህ ሰው ከአንድ ጳጳስ ጋር ይገናኙ'ና
ጳጳሱ፦"እናንተ ሙስሊሞች ከባድ የሆነ ወገንተኝነት ይታይባችኋል"

አቡበክር፦"እንዴት?"
ጳጳሱ፦"ምክንያቱም እናንተ ለራሳችሁ ክርስትያን ሴቶችን እና የአይሁድ ሴቶችን ታገባላችሁ፤ ነገር ግን የናንተን ሴቶች ለማንም አሳልፋችሁ አትሰጡም፤ ሀራም ትላላችሁ።"

አቡበክር፦"አሃ! እኛ እኮ ክርስቲያን ሴቶችን ምናገባው በዒሳ ስለምናምን ነው። የአይሁድ ሴቶችን ምናገባው ደግሞ በሙሳ ስለምናምን ነው፤ እናንተም በሙሀመድ ካመናችሁ ሴቶቻችንን እንድርላችኋለን።"
____________

አቡ በክር በሂጅራ አቆጣጠር በ 371 ላይ ከነበሩ ተፅዕኖ ፈጣሪ ዑለማኦች ይመደብ ስለነበር የግዜው የነበረው የዒራቅ ገዢ አቡ በክርን ወደ ቆስጠንጢንያ/በግዜው የሮም ዋና ከተማ (Constantinople) ለክርክር ላከው።

የሮሙ ንጉስ የአቡ በክርን መድረስ በሰማ ግዜ ለወታደሮቹ የቤተ-መንግስቱን በር እንዲያሳጥሩት'ና፤ አቡ በክር ሲገባ አጎብድዶ እንዲጋባ ሁኔታዎችን እንዲያመቻቹ ባዘዛቸው መሰረት ወደ ቤተ መንግስ እሚገባ ሰው ሁሉ ዝቅ ብሎ እንዲገባ በሩን አሳጠሩት።

አቡ በክርም ቤተ መንግስት ደርሶ ሊገባ ሲል በሩ አጥሮ ተመለከተ'ና የተሸረበውን ሴራ በመረዳት ፊቱን አዞሮ፤ ወደ ኋላ በማጎብደድ ለንጉሱ ፊት ቂጡን ሰጥቶ ገባ።ይህን ግዜ ንጉሱ የአቡ በክርን ከባድነት ተገነዘበ።

አቡ በክር ከገባ በኋላ ከንጉሱ ዙርያ የተሰለፉትን ጳጳሳት ሲያይ <<እንኳን ደህና ቆያችሁኝ>> አይነት ነገር አላቸው።
ከዝያም ወደ ዋናው ጳጳሳቸው ዞር ብሎ፦"እንዴት ነህ? ቤተሰብ ልጆች እንዴን ናቸው?" አለው።
ይህን ሲሰማ ንጉሱ እጅግ በመቆጣት፦"ጳጳሶቻችን እንደማይጋቡ እና እንደማይዋለዱ እያወቅክ እንዴት እንዲህ አይነት ጥያቄ ትጠይቃለህ?" አለው።

አቡበክርም፦"አላሁ አክበር!!! ጳጳሶቻችሁን ልጅ ከመውለድ እና ሚስት ከማግባት እያጥራራችሁ ለአላህ ግን የመርየም ልጅ የሆነውን ዒሳን ልጁ ነው በማለት ትቀጥፋላችሁ" አለው።

የንጉሱ ንዴት እየጨመረ በንቀት ተውጦ፦"ዓኢሻ ስለፈፀመችው ቅጥፈት ምን ትላለህ" አለው።
አቡ በክርም፦"ዓኢሻ ባልሰራችው ያወሩባት ሙናፊቆች ናቸው። መርየምም ባልሰራችው ያወሩባት የሁዶች ናቸው፤ ሁለቱም ግን ንፁሃን ናቸው።

እውነት እናውራ ካልን ዓኢሻ ትዳር ይዛለች ግን በውሸት ቢቀጠፍባትም አልወለደችም። መርየም ደግሞ ትዳር አልያዘችም ፤ግን ወልዳለች። ታዲያ ማን ናት እስቲ ከሁለቱ ለጭፍን ወቀሳ ቅርብ የሆነችው። ሁለቱም ንፁሃን እንስቶች ናቸው" አለ።

ንጉሱ ብስጭቱ ጨመረ እና፦"ነብያችሁ ለጦርነት ይዘምት ነበር?" አለው።
አቡ በክርም፦"አዎን" አለ።
ንጉሱም፦"በጦርነት ሰዐት ፊት ለፊት ገብቶ ይጋፈጥ ነበር?" አለው።
አቡበክርም፦"አዎን" አለው።
ንጉሱም፦"ድልን ይቀዳጅ ነበር?" አለው።
አቡ በክርም፦"አዎን" አለው።
ንጉሱም፦"ይሸነፍስ ነበር?" አለው።
አቡበክርም፦"አዎን" አለው።
ንጉሱም፦"ይገርማል!!! ነቢይ ይሸነፋል እንዴ?" አለ።
አቡበክርም፦"ይገርማል!!! ጌታ ይሰቀላል እንዴ?" ብሎ ክርክሩን አሳመረለት።
_________
طرفة :

تشاجر رجلٌ مع زوجته في زمن الإمام مالك رحمه الله
وكانت الزوجة واقفةٌ على سُلمٍ في البيت !
فلما اشتد غضب زوجها منها أثناء المشاجرة، قال لها :
( أنتِ طالقٌ إن صعدتِ، وطالقٌ إن وقفتِ، وطالقٌ إن نزلتِ ) !

فلم تصعد، ولم تنزل، ولم تقف
بل ألقَتْ بنفسها عليه، حتى سقط على الأرض تحتها، وأصيب رأسه.
فقام وهو يقول لها :
فداك أبي وأمي، إن مات الإمامُ مالك احتاج إليك أهل المدينة في الفتوى. 😂😂😂😂
هُوَ الَّذِي أَرْسَلَ رَسُولَهُ بِالْهُدَىٰ وَدِينِ الْحَقِّ لِيُظْهِرَهُ عَلَى الدِّينِ كُلِّهِ وَلَوْ كَرِهَ الْمُشْرِكُونَ

እርሱ ያ አጋሪዎቹ ቢጠሉም መልክተኛውን (ሙሐመድን) በቅን መንገድና በእውነተኛ ሃይማኖት ላይ ከሃይማኖት ሁሉ በላይ ይፋ ያደርገው ዘንድ የላከው ነው፡፡
የአንድ ኩባያ ውሃ ዋጋ!

አንድ ቀንም ኢብን ሰምክ የተባሉት ዐሊም ከኸሊፋው ሐሩን አር-ረሺድ ጋር ማዕድ ቀርበው ሐሩን ውሃ እየጠጣ ሳለ «የምዕመናን መሪ ሆይ! እስኪ አንዴ መጠጣትህን አቁም።» አሉት። ሐሩንም መጠጣቱን አቆመ።

ከዚያም ኢብን ሰምክ «ምንም ውሃ በሌለበት በረሃ ላይ አንድ ኩባያ ውሃን ከንግስናህ በምን ያህሉ ልትለውጥ ትችላለህ?» አሉት። ሐሩንም «ከንግስናየ ግማሹን እሰጣለሁ።» አላቸው። ኢብን ሰምክም «እሽ አሁን ጠጣ።» አሉት። ሐሩንም የቀረውን ጠጣ።

ከዚያም ኢብን ሰምክ «የምዕመናን መሪ ሆይ! የጠጣኸው ውሃ በሽንት አልወጣም ቢልህ ለዚህ ፈውስ ከንግስናህ ምን ያህሉን ትሰጣለህ?» አሉት። ሐሩንም «ግማሹን እሰጣለሁ።» አላቸው።

ኢብን ሰምክም «አየህ! የአንተ የንግስና ዋጋ ከአንድ ኩባያ ውሃ እና ከአንድ ኩባያ ሽንት ጋር እኩል ነው። እናም በዚህ ኩራት እንዳይዝህ።» አሉት። ሐሩንም ለረጅም ደቂቃዎች አለቀሰ።
(አል-ካሚል 6/219)
ለሚመለከተው ሁሉ!!!


በሀይድ ፣ በወሊድ ፣ በህመም ፣ በጉዞ ወይም በሌሎች ምክንያቶች ረመዳን ቀዷ ያለባችሁ ሙስሊም ወንድምና እህቶች በቀሩት ቀናቶች ቀዷችሁን አዉጡ!

ጊዜዉ ገና ነዉ በማለት ተዘናግተን ሲያልፈን ፈትዋ ለመጠየቅ እንዳንሮጥ!
ጉንችሬ ላይ እየተፈጠረ ያለው ችግር ሙሉ ለሙሉ ኃላፊነት ወስዶ ህግ ፊት መቅረብ ያለበት የቀድሞ የጉንችሬ ወረዳ አስተዳደር የሆነው የአሁኑ የዞኑ ሰላምና ፀጥታ ዘርፍ ኃላፊው ያዕቆብ ነው።

ይህ ግለሰብ ከደቡብ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ርስቱ ጋር እና ከሽማግለዎቹ በተለይ የተስፉ ነጋ አባት ሙስሊም እስከመጠየፍ በጋር በመሆን ሰፊ ቁጥር ያለው የጉንችሬ ሙስሊሞችን ተማሪዎችን የመማር ማስተማር ሂደት በማወክ እስከ አዲስ አበባ ከትምህርት ሚንስትሩ ጭምር ውይይት ቢደረግም በምን ታመጣላችሁ የተልዕኮ አላማ በተለይም ሴት ሙስሊም ተማሪዎችን ኢላማ ያደረገ ጥቃቶች መፈፀም ከጀመሩ ውሎ አድሯል።

በኢድ ሶላት ሙስሊሙ ማህበረሰብ በሰላማዊ መንገድ ድምፁ አሰምቶ ቀናት ቢያልፍ አሁን አመሻሹ የፌደራል ፖሊስና ይፍረስ የተባለው ልዩ ኃይል በጋራ ሙሊሙን እያጠቃ ይገኛል።

ህገወጥነትን ማስቆም የፀጥታ አካል ግዴታ ነው በኃይል እና በጉልበት የሚለወጥ አንዳንች ነገር እንደሌለ በመንግስትና ህወሃት መካከል የነበረው ጦርነት የዛሬ ማስረጃ ነው።

ተማሪዎቻችን ወደ ትምህርት ገበታቸው ይመለሳሉ፣ የተልዕኮ ዘመቻ ላይ ያሉ እነ ተስፋ እና መሰል ሰዎች ህግ ፊት ቆመው በሀገርና በህዝብ ላይ እንዲሁም በ እህቶቻችን ላይ የሰሩትን ግፍ ይወራረዳሉ ይኸው ነው።
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

“ከዐረፋ ቀን የበለጠ አላህ ባሪያውን ከአሳት ነፃ የሚያወጣበት ቀን የለም። እርሱም ይቀርባል። ከዚያሞ በነርሱ መላእክቶችን ይፎካከርባቸዋል። አንዲህም ይላል፦ ‘እነዚህ (ባሮቼ) ሞን ፈልው ነው?’”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 1348
ነገ ማክሰኞ ዙል-ሒጃ 9 ነው ቀኑን የጾመ ሰው ያለፈውና መጪው ዓመት ወንጀል ይሰረዝለታል

🔅ይጹሙ፤ ዘመድ፣ጓደኛና ጎረቤትም ያስታውሱ::
የረመዷን ቀዷ ያለበት ሰውም ቢሆን ለቀዷው ሰፊ ጊዜ ስላለ የዐረፋን (9ኛውን ቀን) መጾም ይችላል
Aselamu aleykum werahmetullah nege jumu’a new sellu alen'nebi  
👳‍♀🧕📿
دعْ الإعتراض ، فما الحُكمُ لكْ
وما الأمرُ في حركات الفلكْ
ولا تسألِ الله عن حُكمِهِ
فمنْ خاضَ لُجّة بحرٍ هَلكْ...
سَلِّمْ أَمرك لله وَأكثر من الصلاة
سيدنا رسول اللهﷺْ تكن من السُعداء
ከጁመዓ ቀን ሱናዎች
➠➻➠➻➠➻➠➻➠➧
↩️#سنن_يوم_الجمعة

➊ الغسل
➋ الطيب
➌ السواك
➍ لبس الجميل
➎ قراءة سورة الكهف
➏ التبكير لصلاة الجمعة
➐ الإكثار من الدعاء والصلاة على النبي ﷺ
🔹ገላን መታጠብ
🔹ሽቶ መቀባት(ለወንድ)
🔹ሲዋክ መጠቀም
🔹ጥሩ ልብስ መልበስ
🔹ሱረቱ ከህፍን መቅራት
🔹በጧት ለጁመዓ ሶላት መጣድ
🔹በነብዩ ﷺ ላይ ዱዓና ሰለዋት  ማብዛት
ኢላሂ
•እንደ አደም ተውባን፣
•እንደ አዩብ ትዕግስትን፣
•እንደ ሱለይማን ሀብትን፣
•እንደ ኢብራሂም ፅናትን፣
•እንደ የዕቁብ ተስፋን፣
•እንደ ዩሱፍ ጨዋነትን፣
•እንደ ሙሐመድ  ﷺ ሥነ-ምግባር'ን ወፍቀን ያረብ
➥ጌታዬ ሆይ  ልቦቻችን ወደአንተ ናፍቀዋል ወዳንተ አዘንብልልን
አላሁመ አሚን ! አላሁመ አሚን ! አላሁመ አሚን

اللهم صلِ و سلم و بارك على سيدنا محمد ﷺ 💚
صلو 😘
Forwarded from TR Am
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ለሰው ልጆች ሁሉ የተደረገ ጥሪ
“ከሙዕሚን ወንድሙ የዱንያን ጭንቀት የገላገለ ሰው አላህ (ሱ.ወ) ከቂያማ ቀን ጭንቀት እርሱን ይገላግለዋል” ነብዩ መሀመድ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)

በባዩሽ መስጅድ የዲን ትምህርትን ጨምሮ ቁርኣንን በመሀፈዝ ፣ በኡስታዝነትና በኢማምነት እያገለገለ የሚገኘው ኡስታዝ ኸሊፋ በርታ በኮልፌ የገበያ ማዕከል በደረሰው የእሳት አደጋ በመጋዘናቸው ውስጥ የነበረ ግምቱ 15 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ንብረት ውድመት ደርሶበታል።

ወንድማችን የቤተሰብ አስተዳዳሪ ከመሆኑም በተጨማሪ አብዛኛው ንብረት በዕዳ የገባ በመሆኑ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ወንድማችንን ከጭንቀት ለመፈረጅ የበኩላችንን ድጋፍ እናደርግ  ዘንድ እንጠይቃለን።

የአካውንት ስም:- ከሊፋ በርታ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ:-1000230579548
አዋሽ ባንክ:- 01425224548200
ዳሽን ባንክ:- 2920310294311
አቢሲኒያ ባንክ:-47469767
ኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ:- 1000068036805
⇄ተንቢሃት ሙስሊም ሴቶችን ልዩ የሚያደርጉ ህግጋት⇄
===============
  === ክፍል ① ====
 
       ===መቅድም====

⇨እጅግ አዛኝ እና ሩህሩህ በሆነው በአላህ ስም እጀምራለሁ።

⇨ምስጋና ለአላህ ነው፤ እሱ ሰዎችን ፈጥሮ በውሳኔቀጥተኛውን መንገድ ለመራው፤ በእውነት የሚገዙት አምላክ እሱ ብቻ ነው ብየ እመሰክራለሁ፤ እሱ ፦ አጋር ፣ አምሣያና ቢጤ የሌለው፣ እሱ የሁሉ ነገር ፈጣሪ፣ አስተናባሪ እና ሰጪ ነው፤ በመተናነስ በመውደድ፣ በፍራቻና በተስፋ መመለክ የእሱ ብቻ ሲሆን፤ እሱ በመልካም ስሞቹና ባህሪይዎቹ አምሳያ የለውም።

⇨ ነብዩ ሙሐመድ ሰለላህ አለይሂ ወሰለም  የአላህ ባሪያና መልክተኛ ናቸው ብየ እመሰክራለሁ። የአላህ ሶላት እና ሰላም በእርሳቸው በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረቦቻቸውና በመልካም በተከተላቸው ላይ ይሁን።

⇨በጃሂልያ ዘመን አባቶች ሴት ልጆች ሲወለዱላቸው እንደውርደት በመቁጠር ሴት ልጆችን ከነህይወታቸው እስከሚቀብሩ ድረስ ከሰው ተደብቀው ይኖሩ ነበር። ከመቀበር የተረፉት እና በህይወት የቆዩት ሴቶች የጭቆናን ቀንበር ተሸክመው እንደ ሰብዓዊ ፍጡር ሳይሆን እንደ ተራ መገልገያ እቃ የሚቆጠሩና ዘግናኝ በሆነ ሁኔታ በደል ሲፈፀምባቸው እንደ ነበር ታሪክ የሚረሳው አይደለም።

⇨ነብዩ ﷺ ኢስላምን ለማደስ ከተላኩ በኋላ አላህ(ሱባሃነሁ ወታአላ ) ይህንን ግፍና በደል በማየት ለችግሩ መፍትሄ ከመስጠት ባሻገር የተፈፀመው ግፍ በመጨረሻው ቀን ለፍርድ እንደሚያቀርብ ያወሳል።

⇨ ለሴት ልጅም ክብሯና የበላይነቷ ተመልሶ ከወንድ ጋር ፍትሃዊ ግምት እዲሰጣት እና የሚደርስባትን ማንኛውንም ጥቃት በማውገዝ ለደህንነቷ በትክክል ዋስትና የሰጣት ኢስልምና ብቻ ነው።ነገር ግን የኢስላም ጠላቶች እውነታውን ሆዳቸው እያወቀ፥ ኢስልምና ስለሴቶች ያለውን ቦታ በተቃራኒው ሲያወሩ አይናቸውን በጨው አጥበው የአደባባይ ሚስጥር በሆነ ውሸት ነው።

⇨ ይህንንም የሚቀጥፉትና የሚለፍፉት ሙስሊም ሴቶች በኢስላም ውስጥ ያገኙት ከለላና ጥብቅነት ያስቆጫቸውና የእግር እሳት የሆነባቸው የኢስላም ጠላቶች ኧረ እንድያውም የሰው ልጅ ጠላቶች እኩልነት የሚል ካባ በማልበስ ሙስሊም ሴቶች በማይነቁበት ዘዴ ለማጥመድና አላማቸውን ለማስፈፀም የሴቶች ተቆርቋሪ በመምሰል የተጠማ ስሜታቸውን ለማርካት፣ በመጥፎ አስተሳሰብ የላሸቀ አዕምሯቸውን ለማደስና ድሪቶ ድብርታቸውን ለማራገፍ ሲሉ ሴት ልጅ ከቤት ወጥታ ከወንዶች ጋር መዋል አለባት እያሉ ሲለፍፉ ይሰማሉ።

⇨ ይህ ያልገባት የዋኋ ሙስሊም ሴት የሚጮኹት ለእርሷ እየመሰላት ሚስጥሩን ባለማወቅ ወጥመዳቸው ውስጥ ትገባለች። በዚህም የተነሳ ከአላህ (ሱ.ወ) ጋር ትጣላለች።ኢስላም ከፈጣሪዋ ጋር የሚያስታርቃትን እና ጀነት የሚያወርሳትን መንገድ በትክክል ግልፅ አድርጎ አስቀምጧል።

ይህንን በተመለከተ ይህ ኪታብ ሰፊ የሆነ እውቀትን የያዘ በመሆኑ የታላቁን አሊም ሸኽ ሳሊህ ኢብኑ ፈውዛንን ተንቢሃት የሚለውን ኪታባቸውን ለመተርጎም አላህ ወፍቆኛል። አረብኛ ወደ አማረኛ ማዞር(መተርጎም) ከባድ ቢሆንም በተቻለኝ መጠን የትርጉም እና የሐሳብ ለውጥ ሳይኖረው የቃል በቃል ትርጉም ላይ ጥረት አድርጊያለሁ።
================
ኢንሻ አላህ ይ ቀ ጥ ላ ል

  ለእህቶቻችን ሸር በማድረግ የኽይር 
  ተካፍይ እንሁን
منقول
📮ተራዊሕ በመስገድ ከሚገኙ  ጥቅሞች...

🔹ተራዊሕ የረመዷን ወር ምሽቶች ላይ በጋራም ይሁን በተናጠል የሚሰገድ ነቢዩ صلى الله عليه وسلم እና ሰሓቦቻቸው ያደረጉት ተወዳጅ ዒባዳህ ነው።

የተራዊሕ ሰላት በርካታ ጠቀሜታዎችና ምንዳዎችም አሉት፤ ከነዚህም በጥቂቱ:-

① ቀኑን በጾም፣ ሌሊቱን በሰላት በማሳለፋችን ከደጋግ የአላህ ባሪያዎች መሆን ያስችላል።

② ቁርኣን በብዛት በማድመጣችን የአላህን እዝነት እናገኝበታለን።

③ ተራዊሕ በዛ ያለ ሩኩዕና ሱጁድ ስላለበት ሰፊ የዱዓና የዚክር እድል እናገኛለን።

④ ከወንጀልና ከማይጠቅሙ ነገሮች ርቀን ጊዜያችንን በመልካም ስራ እናሳልፋለን።

⑤ ዒባዳህ ላይ መታገስን እንማርበታለን።

⑥ አመቱን ሙሉ ሰላተል-ለይል ለመስገድ ልምምድ እናደርግበታለን።

⑦ በተደጋጋሚ ከኢማምና ከማእሙሞች ጋር "ኣሚን" በማለታችን ወንጀላችን ይማራል።

⑧ መስጂድ ስንሄድና ስንመለስ በእርምጃችን ልክ ወንጀሎች ተራግፈው መልካም ስራዎች ይጻፉልናል።

⑨ ሰላት እየጠበቀን በምናሳልፋቸው ጊዜያቶች መላኢካዎች ምህረት ይጠይቁልናል።

①∅ የሙስሊሞችን ጀማዓ በማብዛት ሸይጣንና አጋዦችን እናስቆጫለን።

①① ከመልካም ሰዎች ጋር በመቀላቀላችን መልካም ስራዎቻችን ወደ ሰማይ እንዲወጡና ተቀባይነት እንዲያገኙ እድል ይፈጥራል።

①② ከአልባሌ ነገሮች ለመራቅና ዲን ላይ ቀጥ ማለት ለሚፈልገው ወጣት መልካም አርዓያና ማበረታቻ እንሆናለን።

①③ ካመኑበትና ጥቅሙን ካወቁት ሁሉም ነገር ቀላልና የሚቻል መሆኑን በተጨባጭ እንረዳበታለን።

①④ ቁርኣንን በብዛት በመስማታችን እንገሰጻለን፤ እንዲሁም የተለያዩ አንቀጾችን በተደጋጋሚ በመስማታችን ትክክለኛውን የቁርኣን አቀራር ለማወቅም ይረዳናል።

①⑤ በቁኑት ዱዓ ወቅት ብዙ እኛ ያላሰብናቸውና መግለጽ የማንችላቸው ነገሮች ዱዓ ተደርጎ "ኣሚን" በማለታችን ትርፋማ እንሆናለን።

①⑥ ከኢማሙ ጋር እስከሰላቱ ፍጻሜ ድረስ አብረን እየሰገድን ከቆየን ሌሊቱን በሙሉ ሲሰግድ ያደረን ሰው እጅር /ምንዳ እናገኛለን።

①⑦ ለሰላት ረጅም ጊዜ መቆማችን የቂያማ ቀን መቆምን ያቀልልናል፤ ዱኒያ ላይ ለጌታው ብሎ ረጅም ሰዓት የቆመ የቂያማ ቀን መቆም አይከብደውምና።

①⑧ ሰግደን ስንመለስ አላህ የሚወደውን ስራ በመስራት የሚገኘውን የውስጥ ደስታና እፎይታ እናገኛለን።

💠ሌሎችንም የዱኒያም የኣኺራህ በርካታ ጥቅሞችን እናገኛልንና ተራዊሕን መቼም አንተው! አላህ ያግራልን።

اللهم أعز الإسلام والمسلمين وأذل الشرك والمشركين ووحد صفوفنا وقنا شرور أنفسا يارب العالمين
ኡስታዝ አሕመድ ሼኽ ኣደም
ይድረስ!
~
1- ይድረስ ሚስትህን ለፈታኸው፡
ልጆችህን ለዒድ አስበሃቸዋል? ወይስ እነሱንም ከናታቸው ጋር ፈተሃቸዋል?

2- ይድረስ የየቲሞች አጎት ለሆንከው፡
የሟች ወንድምህን ልጆች ትጠይቃለህ? ወይስ ከቀበርከው ወንድምህ ጋር ረስተሃቸዋል?

3- ይድረስ ባሏ የሞተባት እህት ያለችህ :
እህትህን ትኑር ትሙት ጠይቀሀል? በልታለች ወይስ ተርባለች? ወይስ እህትነቷ ቁጥር ብቻ ነው?

ይድረስ ለሁላችን፡

እጃችንን የሚጠብቁ፣ ከኛ የቀረበ ሰው የሌላቸው ቤተሰቦቻችን በምን ላይ ናቸው? በዒድ በምን መልኩ እንዲያስታውሱን እንፈልጋለን? ያቅማችንን ያክል ከልባቸው ውስጥ ደስታ ማስገባት ያሳስበናል? ወይስ ሀዘን ትካዜያቸው ምንም አይመስለንም?!
-
ተነካክቶ ከዐረብኛ የተመለሰ
በጸጋ እየተንበሻበሽክ ነውና አልሀምዱሊላህ በል።

"ጫማ ለብሶ የተንቀሳቀሰ በመጓጓዣ እንደተጓዘ ይወሰዳል ብለዋል ነብዩ صلى الله عليه وسلم።

============================

የዚህን ሀዲስ ዋጋ ለማወቅ ከሁለት አስርት አመታት በፊት ገጠር ይኖሩ የነበሩ ዘመዶችህን የኑሮ ሁኔታ መጠየቅ በቂ ነው። ጧት ላይ እንደበረዶ በሚያደነዘዝ ቅዝቃዜ፣ ከሰአት ደግሞ እንደ እሳት በሚያቃጥል ሙቀት በዚያ ላይ ከእሾህ በማይተናነስ የሚወጋ ድንጋይ ላይ ከጧት እስከማታ ድረስ በባዶ እግራቸው ሲኳትኑ የሚውሉ ቤተሰቦች ነበሩን።

አልሀምዱሊላሂ ሀምደን ከሲረን ጦይበን ሙባረከን ፊሂ