Ergib Media
284 subscribers
5.81K photos
1.65K videos
5 files
347 links
ይህ የቴሌግራም ገጽ ሰኔ 9/10/2016 ዓ.ም ለአማራ ህዝብ ድምፅ ይሆን ዘንድ ተከፈተ !!

የቴሌግራም ሊንክ👇👇

t.me/Ergibw

አዲሱ የፌስቡክ ገጻችን 👇👇👇 https://www.facebook.come/profile.php?id=61569368131428
Download Telegram
ተወዳጇ ድምፃዊት ማዲቱ ወደይ  Maditu Eshkem     ከፍተኛ የመኪና አዳጋ ደርሶባታል። 

እህታችን ከዚህ በፊት ወደ ደሴ ከተማ ለስራ ከአባቷ ጋር በጉዞ ላይ እያለች በጦርነት ምክንያት በተተኮሰ ጥይት ከተሳፋሪዎች መካከል ሶስት ሰወች ሲሞቱ አባቷ ሲቆስል እሷ ደግሞ በታምር ተርፋ ነበር።

ዛሬ ደግሞ በእሷ ላይ ከፍተኛ የመኪና  አደጋ የደረሰባት ሲሆን አደጋው የደረሰባት  ከወልድያ ወደ ሲሪንቃ በመጓዝ ላይ እንደነበረች ነው። 

via : Ankuar
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ፋኖ_ይችላል💪

ከጎንደር ሰማይ ስር በዛሬው
#ዘመቻ_ሰማዕታቶች በአናብስቱ እስቴ ዴንሳ ብርጌድ ገቢ የተደረጉ የአገዛዙ ስልጣን አስጠባቂ ሰራዊቶች በከፊል...
#ወጣቱ በግፍ ተገደለ‼️

በደብረ ማርቆስ ከተማ ነዋሪዎች ይወደድ የነበረው ወጣት ሐይሌ ያለው በአረመኔው ሰራዊት አባላት ከምሽቱ 2:15 በመኗሪያ ቤቱ መገደሉ ተረጋግጧል።
ሚያዚያ 28/2018 ዓ.ም
=======================================
እንደወትሮው ቁኑን በስራ አሳልፎ ማምሻውን ወደ ቤቱ የተመለሰው  የደብረ ማርቆስ ከተማ ተወላጅ የሆነውን ወጣት ኃይሌ ያለውን ተከታትለው መኗሪያ ቤቱ በመግባት የአረመኔው ሰራዊት አባላት በግፍ እረሽነውት ወጠዋል።

የጠላት ጥይት በሰውነቱ ከማረፉ በፊት 5 የሚደርሱ ወታደሮች ገንዘብ እንዲሰጣቸው አፈሙዝ ደቅነው እያስፈራሩ ቢጠይቁትም ወጣት ኃይሌ ያለው የተጠየቀውን ገንዘብ መክፈል ባለመቻሉ በአሰቃቂ ሁኔታ በደብረ ማርቆስ ከተማ ፍቅር ተራ ተብሎ ከሚጠራው ሰፈር በሚገኘው መኗሪያ ቤቱ ተገድሏል።

#መረጃዎችን #ሸር በማድረግ የሚዲያችንን የድል ራዕይ ያስቀጥሉ!

ሚያዝያ 28/2018 ዓ.ም
የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን በደብረ ማርቆስ ከተማ ከቀኑ 7:00 ሰዓት በፈፀመው ኦፕሬሽን የምስራቅ ጎጃም ነባር ካድሬዎች የሚጠቀሙበት ሰሌዳ ቁጥር (4)02916 መኪና ተማርኳል።
ሚያዚያ 29/2018ዓ.ም
=======================================
መንፈስ የሆነው የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን በደብረ ማርቆስ ከተማ እጅግ ጠንካራ ግዳጆችን የፈፀመ ሲሆን በዛሬው ዕለት ከጠላት መዳፍ መኪና ማርኮ ከደብረ ማርቆስ ከተማ ማውጣቱን አስታውቋል።

የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን ከታህሳስ 24-2018 ዓ.ም _ሚያዚያ 29 /2018 ዓ.ም የተሳኩ ኦፕሬሽን በመፈፀም ድሎችን ያስመዘገባቸው
- ደብረ ማርቆስ
-ሉማሜ
- ቁይ
- ደብረ ኤልያስ
- ጎዛምን
- ደጀን ከተሞች ላይ 41 የተሳኩ የቦምብ ጥቃት በመፈፀም 168 የጠላት ኃይል ሲደመሰስ 105 የሚሆኑት ከባድ ቁስለኛ ሲሆኑ ከ273 የጠላት ኃይል ላይ ጉዳት ማድረስ ተችሏል።
-7 የሚደርሱ ካድሬዎች ሀምሳ አለቃ፣ መቶ አለቃ፣ የኢንስፔክተርና የሻምበል ማዕረግ ያላቸው የጠላት አመራሮች ከተገደሉት መካከል የሚገኙ ሲሆን 12 የሚደርሱ ፓትሮልና የጭነት መኪኖች ከጥቅም ውጭ ሁነዋል።

የጠላት ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ማዕከል በሆነችው ደብረ ማርቆስ ከተማ የምስራቅ ጎጃም ነባር ካድሪዎች ይገለገሉባቸው የነበሩ ሁለት መኪኖችንም ማውጣት ተችሏል።

በፀረ -መረጃ ኦፕሬሽን በሰራዊታችን እና በህዝባችን የተሰገሰጉ ከጠላት ጋር ግንኙነት ያላቸው 27 ባንዳዎች 27 በቁጥጥር ስር በማድረግ በ12ቱ ላይ አስተማሪ እርምጃ ተወስዷል።

አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ለቴዲ አፍሮ ኢቶሪካ የሙዚቃ አልበም ግራፊክሱን የሠራው ዳዊት ሰሎሞን መታሰር

የግራፊክስ ባለሙያው ዳዊት ሰሎሞን በትንትናው ዕለት መታሠሩ ተሰማ። ለአርቲስት ቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ) ኢቶሪካ ለተሰኘው አዲስ የሙዚቃ አልበም ግራፊክሱን የሠራው ዳዊት ሰሎሞን መሆኑን ዶቼ ቬለ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ከቴዲ አፍሮ ጋር ቅርብ የሥራ ግንኙነት ያላቸው የመረጃ ምንጭ ለዶቼ ቬለ እደገለጹት የአርቲስት ቴዎድሮስ ካሣሁን ኢቶሪካ የተሰኘው የሙዚቃ አልበም መውጣቱን ተከትሎ ዳዊትን ጨምሮ የታሰሩ ለአርቲስቱ ቅርበት ያላቸው ሰዎች ቁጥር ስምንት ደርሷል። ዳዊት ጓደኞቹ ጋ በሄደበት አጋጣሚ መያዙን የገለፁልን ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉት የመረጃ ምንጭ፤ እሱ ከመያዙ በፊት ቤቱ በፖሊስ መፈተሹንም ተናግረዋል። ዳዊት ከግራፊክስ ሙያው ጋር በተያያዘ በዩቲዩብ የሚጫኑ ሙዚቃዎችን ከነግጥማቸው አጣጥሞ በማዘጋጀት ለሌሎች አርቲስቶችም እንደሚሠራም ለመረዳት ተችሏል። የመረጃ ምንጩ እስካሁን አርቲስት ቴዎድሮስ ላይ የደረሰ ነገር እንደሌለም አክለው ገልጸዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም፦ ከታሰረ 13ኛ ቀኑን የያዘው የቴዲ አፍሮ የቅርብ ጓደኛ አቶ ዩሱፍ ያሲን የጤናው ሁኔታ እንደሚያሳስባቸው ቤተሰቦቹ ለመረጃ ምንጩ ገልጸዋል። እስካሁንም ከአቶ ዩሱፍና ከወ/ሮ ማኅሌት ውጪ ከታሰሩት ፍርድ ቤት የቀረበ እንደሌለም ዶቼ ቬለ ለመረዳት ችሏል። 

ዶይቸ ቬለ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት የፌዴራል ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጄላን አብዲ ጋር ደውሎ በስልክ አግኝቷቸው ነበር ። ስለ ዳዊት ሰሎሞን እስር በተመለከተ ለጠየቅናቸው መምሸቱን በመግለጥ፦ «አሁን ከስብሰባ መውጣቴ ነው ገና አጣርቼ ነው» የምናገረው ብለዋል ። በአጠቃላይ ታሳሪዎች ስምንት ደርሰዋል ስለመባሉ እና ስለ አቶ ዩሱፍ ያሲን የጤና ሁኔታም ተጠይቀው፦ «የፍርድ ቤት ጉዳይ ቀርቦ ከሆነ የፍርድ ቤት ጉዳይ አናነሳም፤ ፖሊስ ጋር የታሰረ ሰው ከሆነ አጣራለሁ፥ አሁን ነው የምሰማው፤ መረጃ የለኝም» ብለዋል ። መረጃውን ማግኘት የሚችሉትም ነገ እንደሆነ አክለው ተናግረዋል ። በነገው ዕለት ተጨማሪ መረጃ ካገኝን ለማቅረብ እንሞክራለን ።
የሬሳ ክምር‼️

በምኒልክ ልጆች፣በአሳምነው ግርፎች፣ በአምባሰል ተራሮች ላይ የረገፈው የአብይ አህመድ ቅጥረኛ ዘራፊ መከላከያ ሰራዊት
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የልጀን ሞት የነገረኝ ፋኖ ነው፡፡እናቶች ልጅ የት ደረሰ ብለው መጠየቅ ጀምረዋል፡፡
አብይም ሁለተኛ ብትጠይቂ ትታሰሪያለሽ ብሏታል፡፡እናቶች ልጆቻችሁን ላኩ፡፡የአማራ መሬት ተፈጥሯዊ ማዳበሪያ ይፈልጋል፡፡
1
እየመጡ ነው!💪

የፀረ አማራውና ተላላኪው የብልፅግና አገዛዝ ሴራ እንዲሁም ህዝብና ሃገር አውዳሚነቱ የገባቸው ወታደሮች ከነሙሉ ትጥቃቸው ፋኖን መቀላቀላቸውን ቀጥለዋል።

1ኛ/ ክንዱ እንግዳ ወርቅ
2ኛ/ ከማል ፈጠነ
3ኛ/ ጄጄው ሐብታሙ
4ኛ/ ዋሲሁን ዘለቀ
5ኛ/ ጋሻው መለስ
6ኛ/ አባትነህ አለኸኝ የተባሉ የአድማ ብተና አባላት ትላንት ሚያዝያ 30/2018 ዓ.ም በአፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 74ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል።

ገና ይቀጥላል!!
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ምኒልክ ዕዝ 101ኛ ኮር & 104ኛ ኮር በአምባሰል ግንባር ከሰሩት ጀብድ በከፊል!

ቢዛሞ ሚዲያ
02/09/2018 ዓ.ም
#ከቤንሻንጉል አሶሳ ለፋኖ የተላከ ምስጋና!!

እኔ ባለሁበት ከተማ ይላል መልክቱን የላከልኝ!! እኔ ባለሁበት ከተማ አሶሳ ላይ የአንድ ወረዳ አመራሮች ህዝብ ሰብስበው ፋኖን እያነሱ ያው የተለመደውን ዘራፊ ቀማኛ የወያኔ ተላላኪ በጣም ጨካኝ ገዳይ ናቸው እያለ ስማችሁን ያብጠለጥላል።

ይህን የሰማ አንድ የአካባቢው ተወላጅ/የበርታ ብሔረሰቤብ/አካሔድ ብሎ የወረዳውን አስተዳዳሪ ንግግሩን አቋረጠው ይህ ሰው ልጅ መከላከያ የነበረና በመካነ ሰላም ግምባር ተማርኮ የቤተ አምሓራ ፋኖ ልብስ ገዝተውና ቀይረው፤ገንዘብ ሰተው በደምብ ተንከባክበው ወደ አትውልድ አካባቢው ለመላክ ለጎጃም ፋኖዎች አሸጋግረው በመስጠት ወደ አካባቢው እንዲደርስ ያደረጉት።

ልጁም ወደ ትውልድ ቦታው ደርሶ ለወላጆቹ ፋኖ ያደረገለትን ይነግራቸዋል።  ቀጥሎ ለአካባቢው ማህበሰብ በመናገሩ ለአካባቢው ህ/ሰብ የፋኖን መልካምነትና ተግባር ይመሰክራል።ይህ በእንድህ እንዳለ ወደ አባቱ ስመለስ ይህን የሰማ አባቱና የአካባቢው ሰዎች ፋኖማ የተማረከውን ልጃጅን ልብስ አልብሶ አብልተው በደንብ ተንከባክበው ነው የሸኙት።
ገዳይ አደሉም። እናንተ እንደምትሉት ዘራፊም አይደሉም። መንገድ አይዘጉም። በማለት አስተዳዳሪውን አፉን ሲያሲይዙት ሊያስተባብል ቢሞክርም ባለመግባባት ስብሰባው ተበትኗል። የአሶሳ ማህበረሰብም ከስብሰባ አዳራሽ ሲወጣ በመፈከር" ፋኖ ገዳይ አይደለም! ብልፅግኔ ጋፎ ወደ ሞት የወሰደብንን የነጠቀንን ልጆቻችንን  ፋኖ ወልዶ ሰቶናል!! ፋኖ አራት ኪሎ ገብቶ የኢትዮጲያን ሰላም ያምጣልን!" በማለት ድምፃቸውን እያሰሙ ከአዳራሹ ወጡ!
#ይሄንን ጉዳይ ፋኖ እሸቱ አባተ ሚድያ ላይ አውልልን። ሲሉ በውስጥ መስመር ልከውልኛል። ሰፊው ህዝብ ሆይ ከአሶሳ የተላከውን የህዝብ ድምፅ እነሆ ብያለሁ።
ድል ለፋኖ!
ሞትና ውድቀት ለብልፅግና ስርዓት!
እሸቱ አባተ
በአማራ ፋኖ ክንድ ክፉኛ የተመታውና የውድቀት ዋዜማ ላይ የሚገኘው የአብይ አህመድ አገዛዝ ሰራዊት እርስ በእርሱ መበላላት ጀምሯል።

አጥቢያ ለሊቱን በሰሜን ወሎ ዞን ኮን ከተማ በአድማ ብተና እና በመከላከያ ሰራዊት መካከል በተቀሰቀሰ ከባድ የእርስ በእርስ ተኩስ ከተማዋ ስትናጥ ያደረች ሲሆን፡ በጋሸና ከተማ ደግሞ "ወደ ፋኖ ልትቀላቀሉ ነው" በሚል ሰበብ ሁለት የአማራ ተወላጅ ወታደሮች በገዛ አዛዦቻቸው አረመኔያዊ ግድያ ተፈፅሞባቸዋል።

አጥቢያ ለሊቱን የተካሄደው የኮን ከተማ የእርስ በእርስ ውጊያና ጋሼና ከተማ ውስጥ በሁለቱ ወታደሮች ላይ የተፈፀመው አሰቃቂ ግድያ የብልፅግና ሰራዊት በጥልቅ መፈረካከስ ውስጥ መግባቱን በገሃድ ያሳየ ነው ተብሏል።
ከጦላይ የመከላከያ ማሰልጠኛ ተቋም ለሽምቅ ውጊያ ስልጠና ወደብርሸለቆ ማስልጠኛ ተቋም የመጡ 8 የመከላከያ አባላት  አፋብን 109ኛ ኮር 77ኛ ክፍለጦር ተቀላቀሉ።

1ኛ _አምሳያው አበበ
  2ኛ-ፈንታሁን እሸቴ
  3ኛ_ ጋሻው ያሴ
4ኛ_እንዳልክ አየን
5ኛ_ አድማሱ አየን
6ኛ _ሙልጌታ ተገኘ
7ኛ _ዘዉደ አላዩ
8ኛ _እሱባለው መልኬ
በዛሬው ዕለት የአረመኔው አገዛዝ ስርዓቱን በመጥላት ከአገዛዙ ማሰልጠኛ ካምፕ በመውጣት አፋብን 109ኛ ኮር  77ኛ ክፍለጦር 5ኛ ሻለቃ ተቀላቅለዋል። በመውጣታቸው ደስተኛ መሆናቸውን የገለፁ ሲሆን ሌሎች አባላትም በተመሳሳይ የመውጣት ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል።

#ድል ለአፋብን💪

አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
ግንቦት 3/2018 ዓ.ም
ከላሊበላ ወደ ሰቆጣ ይጓዝ የነበረ የብልፅግና ሰራዊት በደፈጣ ተመታ!

የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ወሎ ቤተ አማራ ምኒልክ ዕዝ 303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር አካል የሆነው 30ኛ ክፍለ ጦር ቃኝዎች ባደረጉት የደፈጣ ጥቃት ከላሊበላ ወደ ሰቆጣ ይጓዝ የነበረውን የብልፅግና ሰራዊት ሰኞ ገበያ ከምትባል ቦታ ደፈጣ በመጣል ከባድ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ እንዲያስተናግድ ተደርጓል።

ጥቃቱ የተፈፀመው ግንቦት 06/2018 ዓ/ም ከንጋቱ 12:30 ሰዓት እስከ ጧቱ 3:00 ሰዓት ገደማ ሲሆን ሁለት መድፍ፣ አምስት ኦራል፣ ሁለት ሲኖትራክ፣ ስድስት አይሱዙ፣ ሶስት ፓትሮል ከነሙሉ ቁሳቁሱ ግራና ቀኝ አጅቦ ለማሳለፍ በተንቀሳቀሰበት ጊዜ ፋኖዎቹ ገዥ ቦታና ደፈጣ በመያዝ የጠላትን ኃይል ሲያራግፉት አርፍደዋል።

በተደረገው የደፈጣ ጥቃት ኦፕሬሽን 16 የተደመሰሰና 11 የቆሰለ ሲሆን በደረሰበት መብረቃዊ የደፈጣ ጥቃት የተደናገጠው የብልፅግና አገዛዝ ጦር ዙ-23 መሳሪያን በመጠቀም በዘፈቀደ በመተኮስ የሁለት(2) አርሶ አደሮችን ቤትና ንብረት ማቃጠሉ ታውቋል።

መዳረሻዉ ድል እና ነፃነት የሆነዉ የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የ303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ መረጃውን አድርሷል።

አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ግንቦት 06/2018 ዓ/ም
ጀብደኛው ምኒልክ ዕዝ በምዕራብ ወሎ ግንባር በዘረ-ፈጁ እና ጨፍጫፊው የአገዛዙ ሰራዊት ላይ ድልን ተቀዳጀ!

አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር 47ኛ ክፍለጦር አትሮንስ ሻለቃ ከአማራ ሳይንት(አጅባር) ከተማና ከመሃል ሳይንት(ደንሳ) ከተማ ከወርቅ ማውጫ እስከ መሃል ሳይንት ትምህርት ቤት የጠላት ጥምር ጦርን ማለትም መከላከያ ሰራዊት፣ አድማ ብተና፣ ሚኒሻ እና የፓሊስ ሀይሎች ላይ በእነ አልሞ አይስቴ የቀኝአዝማች ይታገሱ አራጋው ልጆች ለወሬ ነጋሪት ሳይተርፍ ሙት እና ቁስለኛ አድርገውታል።

የአትሮንስ ሻለቃ አናብስቶች የጠላትን እንቅስቃሴ ቀድመው በማንበብና የጠራ መረጃ በመስራት ለማጥቃት የመጣውን ወኔውንም ጥበቡንም የተነጠቀውን የብርሃኑ ጁላ ሰራዊት ደፈጣ ውስጥ በማስገባት አይቀጡ ቅጣት ቀጥተውታል። በዚህ አውደ ውጊያ የተገኙ ድሎች ሰብዓዊ ጉዳት፦
የተደመሰሰ 45 የጥምር ጦር አባላት
38 ቁስለኛ
ከጠላት የተገኘ (የተማረከ) መሳሪያ፦
ክላሽንኮቭ =9
አብራራው=3
ፋል=1
የብሬን ተተኳሽ=1700
የክላሽ ተተኳሽ=812
ቦንብ=18
የወገብ ትጥቅ=18

ከዚህ በተጨማሪም ዙ-23 ከጥቅም ውጭ ማድረግ የተቻለ ሲሆን ጠላት ሲጠቀምበት የነበረ ሶስት(3) መኪኖች ከጥቅም ውጭ ማድረግ ተችሏል ሲል የክፍለጦሯ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ኋላፊ አርበኛ እዮብ አሸናፊ አስታውቋል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ግንቦት 06/2018 ዓ.ም