Ethiopian Police University Official Page
17K subscribers
5.71K photos
41 videos
77 files
132 links
Protect with courage ;Serve with Compassion!
EPU Social Media link
@https://www.facebook.com/ethiopianpolice
Download Telegram
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በጋራና በትብብር የመስራት አቅሙን ይበልጥ እያጠናከረ ይገኛል
**
ግንቦት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ሰንዳፋ
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገራት የዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በጋራና በትብብር የመስራት ባህሉን ይበልጥ በማሳደግ፣ ለጸጥታ ኃይሉ መጠናከርና ለሰላም ማስከበር ተልዕኮ ስኬት ከፍተኛ ድርሻ እየተወጣ ይገኛል።

ዩኒቨርሲቲው ተቋማዊ ሪፎርሙንና የልህቀት ማዕከል የመሆን ራዕዩን ለማሳካት ከዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር ያለውን ስትራቴጂካዊ ግንኙነት በስፋት እያጠናከረ የመጣ ሲሆን፣ ይህም በተግባር የሚታዩ ውጤቶችን እያሰገኘ ይገኛል።
በዚሁ የትብብርና አጋርነት ተግባር መሰረት ፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የደህንነት እና ጥበቃ መምሪያ (UNDSS Ethiopia) ለዩኒቨርሲቲ ለትራንስፖርት አገልግሎት የሚውል የተሽከርካሪ ድጋፍ አድርጓል።
ዩኒቨርሲቲው ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር የሚፈጥራቸው መሰል ጠንካራ ትስስሮች የሎጂስቲክስና የቴክኖሎጂ አቅምን ለማሳደግ ብቻ ሳይሆን፣ የጸጥታና ደህንነት ዘርፉን በዕውቀትና በክህሎት የበለጸገ ለማድረግ የሚደረገውን ጉዞ የሚያፋጥኑ መሆናቸው ተመላክቷል።
❤29👏10👍6
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ከዓለም አቀፍ የፍልሰተኞች ድርጅት (IOM) ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ::
**
​ግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ.ም ኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ሰንዳፋ
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ከዓለም አቀፍ የፍልሰተኞች ድርጅት (IOM) ጋር ተቋማዊ ግንኙነቱን ይበልጥ የሚያጠናክር የመግባቢያ ስምምነት (MoU) ፊርማ ተፈራረመ።
በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክቡር የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታምራት ሙሉጌታ እንደገለጹት፤ በዕለቱ የተፈራረሙት የመግባቢያ ስምምነት በሁለቱ ተቋማት መካከል ለዓመታት የቆየውን መልካም ግንኙነት ወደ ሕጋዊና ስትራቴጂካዊ ግንኙነትን ይበልጥ ወደተቀናጀ ምዕራፍ የሚያሸጋግር ታሪካዊ እርምጃ መሆኑን ገልጸዋል። ​
አክለውም ክቡር ፕሬዝዳንቱ ይህ ስምምነት በወረቀት ላይ የሚሰፍር ፊርማ ብቻ አለመሆኑን ጠቅሰው፣ በአሁኑ ወቅት እንደ ሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር እና የተለያዩ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች በአይነታቸውና በስልታቸው እጅግ ውስብስብ እየሆኑ መምጣታቸውን በማስገንዘብ እነዚህን ውስብስብ ወንጀሎች በአስተማማኝ ሁኔታ ለመከላከልና ለመቆጣጠር ይቻል ዘንድ፤ በቴክኖሎጂ የዳበረ፣ በዓለም አቀፍ ሕጎች ላይ በቂ ዕውቀት ያለው እና በዘመናዊ የወንጀል ምርመራ ጥበብ የሰለጠነ የፖሊስ ኃይል ማፍራት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የፍልሰተኞች ድርጅት (IOM) የፕሮግራም ኃላፊ ሳሻ ፓትሪክ ንላቡ በበኩላቸው፤ የዓለም አቀፍ የፍልሰተኞች ድርጅት (IOM) ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን ለመከላከልና የሕግ አስከባሪ አካላትን አቅም ለመገንባት ከዩኒቨርሲቲው ጋር በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ገልጸዋል።
❤12👍9