EPS (Ethio-Parents' school)
9.16K subscribers
54 photos
4 videos
1.35K files
41 links
Ethio-Parent's School Student Resource Center
Download Telegram
አክሲዮን ለመሸጥ በድጋሚ የወጣ ማስታወቂያ ኆኅተ ጥበብ አክሲዮን ማህበር አዳዲስ አክሲዮኖችን በማውጣት ለነባርና አዲስ ለሚገዙ ባለአክሲዮኖች በመሸጥ ላይ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ የተራዘመው የመሸጫው የጊዜ ገደብ ታህሣሥ 17ቀን 2016 ዓ.ም ያበቃ ቢሆንም የማህበሩ ዳይሬክተሮች ቦርድ ሽያጩ እስከ የካቲት 17 ቀን 2016 ዓ.ም እንዲራዘም የወሰነ ስለሆነ ለመግዛት የምትፈልጉ ዘወትር በሥራ ሰዓት ገርጂ በሚገኘው የማህበሩ ጽ/ቤት በመቅረብ አክሲዮኖችን ለመግዛት የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡ የኆኅተ ጥበብ አክሲዮን ማህበር የዲሬክተሮች ቦርድ
አክሲዮን ለመሸጥ በድጋሚ የወጣ ማስታወቂያ ኆኅተ ጥበብ አክሲዮን ማህበር አዳዲስ አክሲዮኖችን በማውጣት ለነባርና አዲስ ለሚገዙ ባለአክሲዮኖች በመሸጥ ላይ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ለሦስተኛ ጊዜ የተራዘመው የመሸጫው የጊዜ ገደብ የካቲት 17ቀን 2016 ዓ.ም ያበቃ ቢሆንም የማህበሩ ዳይሬክተሮች ቦርድ ሽያጩ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ.ም እንዲራዘም የወሰነ ስለሆነ ለመግዛት የምትፈልጉ ዘወትር በሥራ ሰዓት ገርጂ በሚገኘው የማህበሩ ጽ/ቤት በመቅረብ አክሲዮኖችን ለመግዛት የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡ የኆኅተ ጥበብ አክሲዮን ማህበር የዲሬክተሮች ቦርድ
በገርጂ፣ ጉለሌ፣ እና ጉርድ ሾላ ኢትዮ-ፓረንትስ ት/ቤቶች ልጆቻችሁን በማስተማር ላይ ለምትገኙ የተማሪ ወላጆች/አሳዳጊዎች በሙሉ የ2016 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የአራተኛው ሩብ ዓመት የትምህርት አገልግሎት የመክፈያ ጊዜ የሚጠናቀቀው ግንቦት 05 ቀን 2016 ዓ.ም ( May 13/2024) ስለሆነ የተሰጠው ጊዜ ከመጠናቀቁ በፊት ክፍያውን እንድታከናውኑ አበክረን እናሳስባለን፡፡ ኆኅተ ጥበብ አ.ማ(ኢትዮ-ፓረንትስ ት/ቤት)
reminder
አክሲዮን ለመሸጥ በድጋሚ የወጣ ማስታወቂያ ኆኅተ ጥበብ አክሲዮን ማህበር አዳዲስ አክሲዮኖችን በማውጣት ለነባርና አዲስ ለሚገዙ ባለአክሲዮኖች በመሸጥ ላይ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ለሦስተኛ ጊዜ የተራዘመው የመሸጫው የጊዜ ገደብ የካቲት 17ቀን 2016 ዓ.ም ያበቃ ቢሆንም የማህበሩ ዳይሬክተሮች ቦርድ ሽያጩ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ.ም እንዲራዘም የወሰነ ስለሆነ ለመግዛት የምትፈልጉ ዘወትር በሥራ ሰዓት ገርጂ በሚገኘው የማህበሩ ጽ/ቤት በመቅረብ አክሲዮኖችን ለመግዛት የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡ የኆኅተ ጥበብ አክሲዮን ማህበር የዲሬክተሮች ቦርድ
የ2015ዓ.ም የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና የፈተና አስተዳደር ማስፈጸሚያ ሰነድ
የሚኒስትሪ መልስ መስጫ ወረቀት አጠቃቀም መመሪያ ለተማሪዎች

1.የተማሪዎች መለያ ቁጥር እና የትምህርት ዓይነት መለያ ቁጥር ለእያንዳንዳቸው በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ውስጥ
ከላይ ወደ ታች መፃፍ አለበት፡፡

2.በተፃፈው መለያ ቁጥር ፊት ለፊት የተፃፈውን ቁጥር የያዘውን ክብ ብቻ መጠቆር አለበት፡፡

3.ተማሪዎች የመረጡትን መልስ ትይዩ በተሰጠው ክብ ላይ በትክክል ማጥቆር አለባቸው፡፡

4.ተማሪዎች ያጠቆሩትን መልስ መቀየር ቢፈልጉ መጀመሪያ ያጠቆሩትን ክብ በደንብ ማጥፋት አለባቸው፡፡

5. በአንድ ረድፍ ከአንድ በላይ ክብ ማጥቆር የተከለከለ ነው፡፡

6) ለመፃፍ እና ለማጥቆር ከተፈቀደው ቦታ ውጭ ምንም አይነት ፅሁፍም ሆነ ጭረት ማድረግ የተከለከለ ነው፡፡

7.ለመፃፍ ከተፈቀደው ቦታ ውጭ ተፅፎ ወይም ትንሽ ጭረት እና ነጥብ ከተገኘ የመልስ መስጫ ወረቀቱ ሙሉ  በሙሉ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

8.መልስ መስጫ ኮርነር ላይ ያሉትን አራት ጠርዞች መንካትም ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡

9. ተፈታኞች የመልስ መስጫ ወረቀታቸውን በንፅህና መያዝ አለባቸው ማለትም እንዳይቆሽሽ፣ እርጥበት  እንዳይነካው፤ እንዳይቀደድ እና እንዳይታጠፍ መጠንቀቅና ሙሉ ኃላፊነት መውሰድ አለባቸው፡፡
Andaregachew1:
🫶ለ6ኛ እና ለ8ኛ ክፍል ተማሪዎች
መብቶችና እና ግዴታዎች
👉ማንኛውም ተፈታኝ የፈተና ደንብና ሥርዓት  አከባበር እንዲሁም የመልስ ወረቀት አጠቋቆርና ተዛማጅ ሁኔታዎችን አስመልክቶ በሚሰጡ ገለፃዎች ላይ የመሣተፍ ግዴታ አለበት።
👉ተፈታኙ በገለፃው ላይ ባለመሳተፉ ምክንያት በፈተና አሰጣጥ ዙሪያ ለሚያጋጥመው ችግር ኃላፊነቱን ይወስዳል።
👉በመጨረሻም የሰራበትን የመልስ ወረቀት ለፈታኙ በመስጠት  የጥያቄ ወረቀቱን ይዞ መውጣት ይችላል።
👉ማንኛውም ተፈታኝ የፈተና ጥያቄዎቹን መስራት ከመጀመሩ በፊት በፈተና የመልስ መስጫ ወረቀት ላይ የግል መለያ መረጃዎችን በሙሉ ግልፅ በሆነ ሁኔታ በቅደም ተከተል ጽፍ ማጥቆር ይኖርበታል (በተለይ የመለያ ቁጥር እና የትምህርት አይነት ኮድ)።
👉ማንኛውም ተፈታኝ የራሱን ችሎታና ዕውቀት ተጠቅሞ መስራት ይጠበቅበታል፡፡
👉የሚሠራባቸው የጥያቄና የመልስ መስጫ ወረቀቶች ለሌሎች ተፈታኞች ዕይታ የተጋለጡ እንዳይሆኑ ሸፍኖ መስራት ይኖርበታል።
👉ማንኛውም ተፈታኝ ሞባይል፣ ካልኩሌተርና የመሳሰሉ ማንኛውንም ዓይነት  የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ይዞ ወደ ፈተና ክፍል መግባት በጥብቅ የተከለከለ ነው ።
👉እያንዳንዱ ተፈታኝ ይህንን አውቆ በቅድሚያ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ አለበት ።
👉ይህንን ባለማድረጉ ምክንያት በፈተና አሰጣጥ ዙሪያ ለሚያጋጥመው ችግር ተፈታኙ  ራሱ ኃላፊነቱን ይወስዳል።
👉ማንኛውም ተፈታኝ በመፈተን ላይ እያለ ፈተናውን እንዳይሠራ የሚያውኩ ሁኔታዎች ቢያጋጥመው በፈታኙ ሲፈቀደለት ችግሩን በመግለጽ አስፈላጊውን እርዳታ ማግኘት ይችላል። ይሁንና በማንኛውም ምክንያት ለባከነ ጊዜ ተጨማሪ ሰዓት አይፈቀድም።
👉ማንኛውም ተፈታኝ ፈተናው ከሚጀመርበት ጊዜ ተኩል ሰዓት /30 ደቂቃ/ ቀደም ብለው ከመፈታኛው ቦታ በመገኘት መቀመጫቸውን መያዝ አለባቸው። ፈተናው ከተጀመረ ከ15 ደቂቃ በኋላ የሚመጣ ተፈታኝ ወደ ፈተናው አዳራሽ መግባት አይፈቀድለትም።
👉ማንኛውም ተፈታኝ ፈተናው ተጀምሮ 45 ደቂቃ ሳይሞላ ፈተናውን ሠርቶ ቢያጠናቅቅም እንዲወጣ አይፈቀድለትም። ይሁን እንጂ ፈተናው ከተጀመረ ከ45 ደቂቃ በኋላ ከፈተና አዳራሹ ለመውጣት   እንዲፈቀድለት ሲጠይቅ የመልስ ወረቀቱን ለፈታኙ አስረክቦ በጸጥታ እንዲወጣ ይፈቀድለታል።
👉ፈተናው ሊጠናቀቅ ከ10 ደቂቃ ያነሰ ጊዜ ሲቀረው የሚጨርስ ተፈታኝ የሁሉም ተፈታኞች የመልስ ወረቀቶች እስኪሰበሰቡና ለፈተናው የተፈቀደው የጊዜ ገደብ አብቅቶ እስኪደወል ድረስ በቦታው ተቀምጦ እንዲቆይ ይደረጋል።
👉ፈተናው በሚሰጥበት ጊዜ ማንኛውም ተፈታኝ ትክክለኛ ያልሆነ የተቀደደ ወይም የተበላሸ የፈተና ጥያቄ ጥራዝ ከገጠመው ወይም የተሰጠው የመልስ ወረቀት የተበላሸ ከሆነ ወይም በራሱ እጅ ቢበላሽበት እጁን አንስቶ በመጠየቅ ሲፈቀድለት ሊያስቀይር ይችላል።

👉ማየት ለተሳነው እና ድጋፍ የሚሹ ተፈታኝ የፈተናውን ጥያቄዎች የሚያነብለትና የሚሰጣቸውን መልሶች የሚያጠቁርለት ፈታኝ በግሉ እንዲመደብለት ይደረጋል።
👉ተፈታኞች ፈተናውን ለመውሰድ የሚችሉት በቅድሚያ ትም/ቤት በተመዘገበበት ጣቢያ እንጂ የፈተና ጣቢያ ቀይረው ሊፈተኑ አይችሉም።
✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️
ለተፈታኞች የተከለከሉ ነገሮች
የግል ስልክ (Mobile phone)፣
ታብሌት፣
የጆሮ ማዳመጫ (earphone) እና ማንኛውም ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣የእጅ ሰአት፣
ማንኛውም የግል ጽዳት ማስጠበቂያ ሆነ ማስዋቢያ ቁሳቁስ፣
ማንኛውም ዕቃ ለመያዣነት የሚያገለግል ቦርሳ/እቃም የያዘ ቦርሳ፣
ማንኛውም ስለት ነክ ነገርና ብረት
መልካም የፈተና ዝግጅት!

Please let us share these important messages to parents 🙏

ለገርጂ፣ ጉለሌ እና ጉርድሾላ ኢትዮ-ፓረንትስ ት/ቤቶች የነባር ተማሪዎች ወላጆች በሙሉ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ባወጣው ዓመታዊ የትምህርት ካሌንደር መሠረት የ2017 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የነባር እና አዲስ ተማሪዎች ምዝገባ ከሰኔ 28 እስከ ሀምሌ 15 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ መሆኑን አውቃችሁ ከወዲሁ ዝግጅት እንድታደርጉ በአክብሮት እናሳስባለን፡፡ኆኅተ ጥበብ አክሲዮን ማህበር(ኢትዮ-ፓረንትስ ት/ቤት)
ለገርጂ እና ለጉለሌ ኢትዮ-ፓረንትስ ት/ቤቶች በ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ ወደ 9ኛ ክፍል ለተዘዋወራችሁ ተማሪዎቻችን በሙሉ በቅድሚያ እንኳን ደስ ያላችሁ እያልን የ2017 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ምዝገባ ከሐምሌ 11 ቀን እስከ ሀምሌ 15 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ መሆኑን አውቃችሁ በተሰጠው ጊዜ ውስጥ ምዝገባውን እንድታከናውኑ እናሳስባለን፡፡ኆኅተ ጥበብ አክሲዮን ማህበር/ኢትዮ-ፓረንትስ ት/ቤት/
አስደሳች ዜና
በ2016 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በገርጂ ት/ቤት ለፈተናው ከተቀመጡት 245 ተማሪዎች መካከል 244(99.6%) ወደ 9ኛ ክፍል የተዛዋወሩ ሲሆን በጉለሌ ት/ቤት ለፈተና የተቀመጡት 115 ተማሪዎች (100%) ፈተናውን አልፈዋል፡፡ በዚሁ መሰረት በሁለቱም ት/ቤቶች ፈተናውን ከወሰዱት 360 ተማሪዎች 359 (99.72%) ተማሪዎች ወደ 9ኛ ክፍል ተዛውረዋል፡፡ በመሆኑም ተማሪዎች፣ ወላጆች፣ የየት/ቤቶቹ መምህራንና ሰራተኞች እንዲሁም የማኔጅመንት አባላት የሥራ አመራር ቦርድ አባላት እንኳን ደስ አለን እንኳን ደስ አላችሁ እያልኩ 2017ዓ.ም በመማር ማስተሩ ዘርፍ የበለጠ ስኬት የምናስመዘግበበት እንዲሆንልን ልባዊ ምኞቴ ነው፡፡ ገነነ ይልማ የኆኅተ ጥበብ አክሲዮን ማህበር ዋና ሥራ አስኪያጅ፡፡
ለገርጂ፣ ጉለሌ እና ጉርድ ሾላ ኢትዮ-ፓረንትስ ት/ቤቶች ተማሪዎች ወላጆች የ2017 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የነባር ተማሪዎች ምዝገባ ከሐምሌ 01 እስከ ሐምሌ 15 ቀን 2016 ዓ.ም መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ በልዩ ልዩ ምክንያት እስካሁን ልጆቻቸውን ያላስመዘገቡ ወላጆች እንዳሉ ለመገንዘብ ችለናል፡፡ በዚሀ መሰረት ምዝገባው ለመጨረሻ ጊዜ እስከ ሐምሌ 23 ቀን 2016ዓ.ም የተራዘመ መሆኑን እየገለፅን በተሰጡት ቀናት እስካሁን ምዝገባውን ያላከናወናችሁ ወላጆች ልጆቻችሁን እንድታስመዘግቡ በአፅንኦት እናሳስባለን፡፡
ኆኅተ ጥበብ አክሲዮን ማህበር
ለገርጂ ፤ ጉለሌ እና ጉርድሾላ ኢትዮ-ፓረንትስ ት/ቤቶች በ2016 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ ወደ 7ኛ ክፍል ለተዘዋወራችሁ ተማሪዎቻችን በሙሉ በቅድሚያ እንኳን ደስ ያላችሁ እያልን የ2017 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የ7ኛ ክፍል ተማሪዎች ምዝገባ ከሐምሌ 15 እስከ ሐምሌ 23 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ መሆኑን አውቃችሁ በተሰጠው ጊዜ ውስጥ ምዝገባውን እንድታከናውኑ እናሳስባለን፡፡ኆኅተ ጥበብ አክሲዮን ማህበር/ኢትዮ-ፓረንትስ ት/ቤት/