ኢማን🌸🧕
70 subscribers
1 link
ወንጀል መስራት ሰውኛ ባህሪ ነው፣ወደ አላህ አለመመለስ ማህርታን አለመጠየቅና በወንጀል ላይ መዘውተር ግን በእርግጥ የጤነኛ ሰው አኽላቅ አይደለም.ኑኑኑ ወደ አዛኙ እና ማኻሪው አላህ እንመለስ
Download Telegram
بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ
አሰላሙአለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካትሁ

ያ ጀመአ እንዴት ናችሁ🥰🥰

እንኳን ወደ አዲሱ ቻናላችን በሰላም መጣችሁ አላህ ሁላችንንም በተሰብንበት እና ባወራንበት የምንጠቀም ያድርገን....አሚን

ይህ ቻናል የተከፈተው፦

*በዱንያ የማያልቅ ሩጫ እና የማይሞላ ጣጣ ተወጥረን ፣ልባችን ጌታችንን ሲረሳ ለማስታወስ
*ዲናችን ያስቀመጠልንን ክብር ለመማማር
*እንደቀልድ የምናያቸው ግን ከአላህ መንገድ የሚያርቁይ ነገሮች ላይ ለመወያየት
*ስለ ምህረት፣እዝነት፣ትዕግስት....0ስለሁሉም ለመተዋወስ
*ከወንጀል እንዴት መውጣት አለብን?የሚለውን ለመነጋገር
*ወንጀልን እንዴት እንከላከል?ለሚለው ጥያቄ መልስ ለመስጠት

በጥቅሉ የደከመች እና ከጌታዋ የራቀች ነፍስን ወደ እሱ ለመመለስ እና በዲናችን ጠንካራ ለመሆን ለመተዋወስ ነው........

አልሃምዱሊላህ ረቢየል አለሚን❤️

https/t.me/emanandtemir
🥰1
«ልጆቼን ለሶላት ቀስቅሺልኝ! ሪዝቅ (ሲሳይ) የአላህ ነውና!
አንድ አባት ወደ ቤቱ ሲገባ ባለቤቱን «ልጆቹ ሰግደዋልን?» ብሎ ጠየቃት።

እርሷም በሐዘንና በተሰበረ ድምፅ፡- «የሚቀመስ ነገር በቤታችን አልነበረምና ረሃቡን እንዲረሱት ብዬ አጫውቼ አሰተኛኋቸው፤ አልሰገዱም» አለችው።

አባትየው ግን ባልጠበቀችው መልኩ ቁርጠኝነት በተሞላበት እምነት፡- «ቀስቅሻቸው ይስገዱ!» አላት።

ሚስት ተጨነቀች፤ «ያ አባ ጃድ! ከቀሰቀስኳቸው እኮ ረሃቡ አላስተኛ ብሎ ሊያለቅሱብኝ ነው፤ በቤቱ ደግሞ ምንም ምግብ የለም"ኘ» አለች።

አባት ግን አላህ በቁርኣኑ የገባውን ቃል አስታወሳት፡-
አላህ እኮ እንዲህ ብሎ አዞናል፡-

( وَأْمُرْ أَهْلَكَ بِالصَّلَاةِ وَاصْطَبِرْ عَلَيْهَا ۖ لَا نَسْأَلُكَ رِزْقًا ۖ نَّحْنُ نَرْزُقُكَ ۗ وَالْعَاقِبَةُ لِلتَّقْوَىٰ)

«ቤተሰብህንም በስግደት እዘዝ፡፡ በእርሷም ላይ ዘውትር፤ (ጽና)፡፡ ሲሳይን አንጠይቅህም፡፡ እኛ እንሰጥሃለን፡፡ መልካሚቱ መጨረሻም ለጥንቁቆቹ ናት፡፡
Âť
[ጦሃ:132]

ስለዚህ ቀስቅሻቸው፤ ሪዝቃቸው በአላህ እጅ ነው!" አላት።
እናት ትዕዛዙን ተቀብላ ልጆቹን ቀሰቀሰች፤ ሁሉም ተነስተው ውዹእ አድርገው ተሰባስበው ሰገዱ። ልክ አሰላምተው እንደጨረሱ የቤታቸው በር ተንኳኳ።

አባትየው ሲከፍት አንድ ሰው በርካታ ዓይነት ምግቦችን በትሪ ተሸክሞ ቆሟል። አባትየው በድንጋጤ «ይህ ምንድን ነው?» አለው።

ሰውየውም እንዲህ አለ፡- «ይህ ምግብ ለአንድ የከተማው ቱጃር ተዘጋጅቶ ነበር። ነገር ግን ገና ከመቅረቡ ተጣሉና 'ይህ ምግብ እዚህ ቤት አይበላም፤ ተሸክመህ ውጣና እግርህ መጀመሪያ የቆመበት ቤት ስጠው' ብሎ ምሎ አዘዘኝ። እኔም የምሰጠውን ሰው ሳስብ እግሬ እዚህ ቤት ላይ ቆመ!»

አባትየው እጆቹን ወደ ሰማይ ዘርግቶ አለቀሰ።
«ጌታዬ ሆይ! እኔንም ልጆቼንም ሶላትን አዘውትረው ከሚሰግዱት አድርገን» እያለ ዱዓ አደረገ።


ከዚህ የምንወስደው ቁም ነገር፡-
ሪዝቅ (ሲሳይ) የሚመጣው በመስራት ብቻ ሳይሆን አላህን በመታዘዝ ጭምር ነው። የቤተሰብ ድህነት ወይም ችግር ከሶላት ሊያዘናጋን አይገባም።

የአላህ ቃል እውነት ነው፤ አንተ የአላህን ሐቅ (ሶላት) ጠብቅ፤ አላህ ያንተን ድርሻ ይሞላልሃል።

አላህ ሆይ! እኛንም ዘሮቻችንንም ሶላትን አዘውትረው ከሚሰግዱትና ሪዝቃቸው ከሰፋላቸው ባሮችህ አድርገን!
❤2
ኢላሂዬ 😢ልቤን ካንተ ውጪ በሌላ ነገር ላይ አታንጠልጥልብኝ🤲
❤4
ከሸይጧን ስራዎች ውስጥ ከንዱ የቆሸሸች ነፍስ መጥሪያ እንደሌላት እና እንዳበቃላት መወስወስ ነው.......

ብዙ ወንጀሎችን ሰርተን ይሆናል....አትቅረቡት ብሎ ያስጠነቀቀን የጌታችን ድንበርን ጥሰን ከከለከለው ወድቀንም ይሆናል....የሰው ሀቅ አጓድለን...ዝምድናን በጥሰን....ዋሽተን....ሰርቀን....ያዘዘንን አጓድለን ይሆናል.......

ፍፁም አይደለንም እና በትናንት ህይወታችን የሚያሳፍር፣የሚያዋርድ ወንጀል ውስጥ ተዘፍቀን ቆይተን ይሆናል...........

ግን ዛሬ ሌላ ቀን ነው.......ጌታችን እኮ ረሂም ነው.....አዛኝነቱ እኮ ድንበር የለውም!!!

ታዲያ እንዴት ብላችሁ በሱ እዝነት ተስፋ ትቆርጣላችሁ?......ባሪያዬ ወደ ኔ ሲቀርበኝ እኔ በዕጥፍ እቀርበዋለሁ እያለን.....ወደ ሱ በስንዝር መጠጋት ለምን ከበደን?

አዎ ይገባኛል እኮበእርግጥ ወንጀላችን ቀላል አይደለም......ፊቱ ለመቆም እዝነቱን ለመጠየቅ ያሳፍራል፣አንገትን ያስደፋል.......ግን እዝነቴ ቁጣዬን በለጠች ማለቱን እንዴት እንዘነጋለን......አዛኙ ጌታችን ተመላሾችን እንዴት እንደሚወድስ ለምን ረሳን???!

እዝነቱ እኮ ተቆጥሮ አይደለም ታስቦ የማይዘለቅ ሰፊ እና ጥልቅ ነው.....ወደሱ ስንመለስ ወንጀላችንን ከመማር አልፎ በአጅር የሚቀይር ገ'ፋር የሆነ ጌታ እኮ ነው..........እና የሱን ቤት ማንኳኳት ለምን ከበደን?በወንጀላችን ታጥረን እኔ መመለስ አይሆንልኝም እያልን እዛው ወንጀላችን ላይ በመዘወትር የሸይጧንን መንገድ አብልጠን መከተልን ለምን መረጥን?

አንቺ በወንጀል የተከበበሽ !አንተ በወንጀል የሰመጥ እህት ወንድሜ ሆይ👉 የጌታህ ራህመት ሰፊ ሆኖ ሳለ በሱ ተስፋ አትቁረጥ!!.....በየቀኑ እድሜህን የሚጨምርልህ እሱን ልትገዛበት፤ያዘዘውን ፈፅመህ የከለከለውን ልትከለኸልበት ነው........ተመልከት!!ዛሬ በሰላም አድረህ ሌላ የተውባ ጊዜ ተሰጥቶሀል......ቆይ እስኪ አሁን ባለህበት ሁኔታ ላይ ሆነህ ሞት የሚመጣ ቢሆን ለደሙን ትችለዋለህ???

ወላሂ ይበቃል ከጌታችን እንታረቅ....አሁን ደግሞ መጪው ረመዳን ነው .....ወንጀሎች የሚማሩበት የእዝነት እና ራህመት ወር......ስንቶች በምኞት ጠብቀውት መድረስ ሳይታደሉ....አንተ አንቺ እና እኔን ግን.....ደርሰው ከሚፆሙት እና ከሚማሩት ያድርገን እና ይኼው ለዚህ የተባረከ ወር አቅርቦናል......አልሀምዱሊላህ.......ታዲያ በዚህ አላህ ከፍ ባደረገው ወር ወደ እሱ ፊታችንን በመመለስ እና መሀርታውን በመጠየቅ ቀን ከሌት እንትጋ........

የትናንት የወንጀል ማንነታችንን አጥበን ሌላ ሰው ለመሆን እመኑኝ ከዚህ የተሻለ ወቅት የለም....

አህለን ቢከ ያ ረመዳን❤️❤️

✍️ተምር አህመድ
❤3
የቀብር ጓደኛ

ስልቱ የተለየ ቃላቱ ማራኪ
ፍፁም የሌለበት ሰብአዊ ንኪኪ
ታሪክ ስነፅሁፍ ሳይንስ በሙሉ
ምንጩ ቁርአን ነው ስልጣኔ ሁሉ
መፅሀፍ ቢበዛ ሺውን ቢያገላብጥ
ምን አነበብኩ ሊል ቁርአንን ሳይገልጥ

.
.....ቁርአን ❤️
❤3🥰3