𝐄𝐋_𝐍𝐀𝐓𝐀𝐍 | 𝐃𝐄𝐅𝐄𝐍𝐃𝐈𝐍𝐆 𝐓𝐇𝐄 𝐅𝐀𝐈𝐓𝐇
749 subscribers
6 photos
2 videos
4 links
Elnatan እባላለሁ
ክርስትና ለይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ መልሶችን ምመልስበት በተቃራኒው ደግሞ የአህዛብ አስተምህሮ ለይ ጥያቄ ማነሳበት Channel ነዉ ::
APOLOGETICS and POLEMICS ሚሰራበት Channel ::
Download Telegram
ሰላመ ክርስቶስ ይብዛላቹ 👋
500 subscriber ስንገባ እዚ ቻናል ለይ የተለያዩ ነገሮችን መልቀቅ እንጀምራለን
So ቻናሉን ለጓደኞቻቹ Share አድርጉ .
🥰10141👍31
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👏2620🥰11👍5😁1
ኢየሱስ ክርስቶስ ዘላለማዊ ነውን?

ብዙ ጊዜ በሙስሊም ወገኖቻችን ከሚነሱት ሙግቶች መካከል “የኢየሱስ ክርስቶስ ህልውና የጀመረው ከማርያም ሲወለድ ስለሆነ ዘላለማዊ ሊሆን አይችልም ” የሚለው አንዱ ሲሆን በሙግታቸው ከአምላክ ባሕርያት መካከል አንዱ ዘላለማዊነት ነውና ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ አይደለም የሚል ድምዳሜ ይሰራሉ።  ስለሆነም ለዚህ ደካማ ሙግት ከመጽሐፍ ቅዱስ ሦስት ጥቅሶችን በመምዘዝ ምላሽ የምንሰጥ ይሆናል።

1). ሚክያስ 5:2

«አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፤ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል።»

ነቢዩ ሚክያስ በ ትንቢተ ሚክያስ ምዕራፍ 5 ቁጥር 2 ላይ ስለ መሲሁ ዘላለማዊነት፣ «ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል።» በማለት መሲሑ ምንም እንኳን በሥጋ ሰው ሆኖ በመወለዱ ዘመን ቢቆጠርለትም ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለሙ ያለ መሆኑን ይናገራል። ይህ ትንቢት ደግሞ ለኢየሱስ መሆኑን በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 2 ከቁጥር 4-6 ወንጌላዊ እንዲህ ይገልጽልና ፤

“የካህናትንም አለቆች፣ የሕዝቡንም ጻፎች ሁሉ ሰብስቦ፣ ክርስቶስ ወዴት እንዲወለድ ጠየቃቸው። እነርሱም፦ ‘አንቺ ቤተ ልሔም፥ የይሁዳ ምድር፥ ከይሁዳ ገዢዎች ከቶ አታንሽም፤ ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ መስፍን ከአንቺ ይወጣልና፡’ ተብሎ በነቢይ እንዲህ ተጽፎአልና፡ በይሁዳ ቤተ ልሔም ነው፡’ አሉት።”

2). ዮሐንስ 17:5

“አሁንም፥ አባት ሆይ፥ ዓለም ሳይፈጠር በአንተ ዘንድ በነበረኝ ክብር አንተ በራስህ ዘንድ አክብረኝ።”

ጌታችን ኢያሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 17 ቁጥር 5 ላይ ስለ እራሱ ሲናገር «አሁንም፥ አባት ሆይ፥ ዓለም ሳይፈጠር በአንተ ዘንድ በነበረኝ ክብር አንተ በራስህ ዘንድ አክብረኝ።» ማለቱ ምንም እንኳን በሥጋ ከ2000 አመት በፊት ከቅድስት ድንግል ማርያም ቢወለድም ፣ እንደ አምላክነቱ ዓለም ሳይፈጠር በዘላለም ውስጥ ከአባቱ ጋር እንደነበረ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።

3). ዮሐንስ 8:56-58

“አባታችሁ አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሐሤት አደረገ፥ አየም ደስም አለው። አይሁድም፦ “ገና አምሳ ዓመት ያልሆነህ፥ አብርሃምን አይተሃልን?” አሉት። ኢየሱስም፦ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ፡” አላቸው።”

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 8 ቁጥር 56 ላይ አብርሃም እርሱን እንዳየዉ ለአይሁዳዊያን ይናገራል። እነርሱም በመገረም “ገና 50 አመት አልሆነህ፥ እንዴት አብርሃም አይቶኛል ትላለህ?” በማለት ሲመልሱለት “አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ” በማለት የእርሱ ህልውና የጀመረዉ ከቅድስት ድንግል ማርያም ሲወለድ ሳይሆን፣ እርሱ ከአብርሀም በፊት የነበረ ዘላለማዊ መሆኑ ገልጾላቸዋል።

ሻሎም 🖐

ኤል-ናታን
77🥰15🔥14👍8👏8🕊4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የመጨረሻ ከFeminism ጋራ የተያያዘ Post
ልጅቷ አሪፍ አድርጋ የFeminism አላማን አብራርታለች ብዬ ስላሰብኩ ነዉ
ልጄን ስላሳደኩ ሊከፈለኝ ይገባል የሚሉ ሰዎችም መተዋል 😂
😁197
የሙስሊሞች አምላክ አላህ ይጸልያልን?

ብዙ ጊዜ ሙስሊሞች «ኢየሱስ አምላክ አይደለም» በማለት እንደ ማስረጃ የሚያቀርቡት «ኢየሱስ በምድር ሳለ ይጸልይ ነበር» የሚል ሲሆን፣ የኛም መልስ «ኢየሱስ አዎ ጸልዮአል» የሚል ነው። ነገር ግን የጸለየው አምላክ ብቻ ሳይሆን ሰውም ጭምር ስለሆነ ጸለየ በማለት እንመልሳለን። ነገር ግን በዚህ ክፍል አላህ እንደሚጸልይ፣ በዚህም ምክንያት አምላክ መሆን እንደማይችል እንመለከታለን።

1. Surah 33 Ayah 43
هُوَ الَّذِي يُصَلِّي عَلَيْكُمْ وَمَلَائِكَتُهُ لِيُخْرِجَكُم مِّنَ الظُّلُمَاتِ إِلَى النُّورِ ۚ وَكَانَ بِالْمُؤْمِنِينَ رَحِيمًا

Huwa alladhī yuṣallī ʿalaykum wa-malāʾikatuhu liyukhrijakum minaẓ-ẓulumāti ilā an-nūr, wa-kāna bil-muʾminīna raḥīmā.

«እርሱ ያ በእናንተ ላይ እዝነትን የሚያወርድ ነው፤ መላእክቶቹም (ያዝንላችኋል)፤ ለአማኞችም በጣም አዛኝ ነው።»

በዚህ የቁርኣን ክፍል ላይ «እዝነት» ለሚለው የአረብኛ ቃል የገባው yuṣallī (يُصَلِّي) የሚል ሲሆን፣ የመጣውም ṣalāh (صَلَاة) ከሚል ቃል ነው። ትርጉሙም «ጸሎት» ማለት ነው። ይህንንም ከቁርኣንም፣ ከአረብኛ መዝገበ ቃላትም መመልከት ይቻላል።
ከቁርኣን ስንጀምር በ Surah 3 Ayah 39፦
فَنَادَتْهُ الْمَلَائِكَةُ وَهُوَ قَائِمٌ يُصَلِّي فِي الْمِحْرَابِ أَنَّ اللَّهَ يُبَشِّرُكَ بِيَحْيَىٰ مُصَدِّقًا بِكَلِمَةٍ مِنَ اللَّهِ وَسَيِّدًا وَحَصُورًا وَنَبِيًّا مِنَ الصَّالِحِينَ

Fa-nādat-hul-malā’ikatu wa-huwa qā’imun yuṣallī fīl-miḥrābi anna Allāha yubashshiruka bi-Yaḥyā muṣaddiqan bi-kalimatim min Allāhi wa-sayyidan wa-ḥaṣūran wa-nabiyyan minaṣ-ṣāliḥīn.

«እርሱም በጸሎት ማድረሻው ክፍል ቆሞ ሲጸልይ መላእክት ጠራችው፤ “አላህ በየሕያ፣ ከአላህ በኾነ ቃል የሚያረጋግጥ፣ ጌታም፣ ድንግልም፣ ከደጋጎቹ ነቢይም ሲኾን ያበስርሃል” በማለት (መላእክት ጠራችው)።»

በዚህ የቁርኣን ክፍል እንደምንመለከተው ለአላህ የገባው ቃል yuṣallī (يُصَلِّي) የሚለው፣ በተመሳሳይ መልኩ ለያሕያ አባት ለዘካርያስ የገባ ሲሆን «ጸሎት» የሚል ትርጉም ሰጥተውታል። ከዚህ በመነሳት «እርሱ ያ በእናንተ ላይ እዝነትን የሚያወርድ ነው» መሆን ሳይሆን ያለበት፣ «እርሱ ያ በእናንተ ላይ የሚጸልይ ነው» መባል ነው ያለበት በቁርኣኑ መሠረት። «እዝነት» የሚለው ቃል በአረብኛው raḥmah (رَحْمَة) እንጂ ṣalāh (صَلَاة) አለመሆኑ ይታወቃልና።
ከመዝገበ ቃላትም ማስረጃ፦

Hans Wehr – A Dictionary of Modern Written Arabic ላይ፦
صلاة (ṣalāh) → prayer;

Ṣalāh የሚለውን ቃል «ጸሎት» በማለት ፈትቶታል።

ማጠቃለያ፦ አላህ በ Surah 33:43 እንደሚነግረን ሰላህ ያደርጋል (ጸሎት ያደርጋል)።

2. ሐዲሳዊ ማስረጃ

Al-Adab Al-Mufrad 645
Abu Hurayra reported that the Messenger of Allah, may Allah bless him and grant him peace, said, "If anyone prays once on me, Allah will pray ten times on him."

ትርጉም፦

አል-አዳብ አል-ሙፍራድ 645
አቡ ሁረይራ እንደዘገበው፣ የአላህ መልእክተኛ — አላህ ይባርከውና ሰላምንም ይስጠው — እንዲህ አሉ፦
«ማንም ሰው አንድ ጊዜ በእኔ ላይ ጸሎትን ካደረገ፣ አላህ በእርሱ ላይ አሥር ጊዜ ጸሎትን ያደርግበታል።»

እዚህ ሐዲስ ላይ እንደተጻፈው አንድ ሰው በሙሐመድ ላይ ከጸለየ፣ አላህ በዚያ ሰውዬ ላይ 10 ጊዜ እንደሚጸልይ ይናገራል።

ከነዚህ መረጃዎች ተነስተን አላህ እንደሚጸልይ ማሳየት እንችላለን፤ አላህ የሚጸልይ ከሆነ ደግሞ አምላክ አይደለም ማለት ነው።


🖐 ሻሎም


✍️ ኤል-ናታን
63👍18😁5🔥3
https://vt.tiktok.com/ZSV6mbHJ1/
Viral አዉጡት ሙስሊሞች ጋራ እንዲዳረስ::
🥰284🔥3
እንኳን ለኪዳነ ምህረት በአል አደረሳችሁ!

በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሀይልና ስልጣን እመቤታችን ተነስታለች ወደ ገነትም ልጇ ወስዷታል !


✍️ El-natan
98👍15🥰6🔥4
ነሀሴ 27 ማታ 3 ሰዐት ይጠብቁን !
82👍31🥰10🔥8
ዲቤቱ እንዴት ነበረ? ሃሳባችሁን በComment አሳዉቁኝ::
👏7733👍14🥰10🔥4
ዝግጁ ?
ወንድማችን እፎይ ለአዲስ አመት ስጦታ አዘጋጅቶልናል !
122❤‍🔥16🤣4😁2👍1
እንኳን ወደ ዘመነ ሉቃስ ለአዲሱ አመት 2019 አመተ ምህረት እና ለቅዱስ መጥምቁ ዮሐንስ በአል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ ሁላችሁም ይሄ አመት ወደ ጌታ ኢየሱስ የምትመለሱበት ራሳችሁን ክርስቶስን ወደ መምሰል ሂደት የምታሳድጉበት አመት ይሁንላችሁ!
77🙏14🥰6
አካውንቴን የምትችሉትን ያክል Copylink አድርጉሊኝ
https://www.tiktok.com/@el_natan10?_r=1&_t=ZS-99gykMAkyDC
👍4821🥰4