ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ
120K subscribers
5.91K photos
109 videos
6 files
959 links
Journalist-at-large
Download Telegram
#ለግልፅነት ቤታቸው ፈርሶባቸው፣ ከሰሞኑ ደግሞ የወታደር ልጃቸውን ማረፍ ሰምተው ፈረንሳይ ሌጋሲዮን ገነተ ማርያም እድር አጥር ግቢ ውስጥ ለቅሶ ተቀምጠው ለነበሩት ወ/ሮ አለሚቱ ዱሜሳ በዚህ ቻናል ለቀረበ ጥሪ ሁላችሁም ባደረጋችሁት መልስ 109,000 ብር (አንድ መቶ ዘጠኝ ሺህ ብር) በራሳቸው አካውንት ገቢ ተደርጎላቸዋል። እኚህ እናት በቅርቡም ማረፊያ እንዲሆናቸው አንድ አነስተኛ የቀበሌ ቤት በወረዳ 1 አስተዳደር ተሰጥቷቸዋል።

ሁላችሁም ላደረጋችሁት ትብብር ምስጋና ይድረሳችሁ!

@EliasMeseret
ትናንት ከተሰጠው አስተያየት በኋላ።

🙏🙏

@EliasMeseret
የኢሰመኮ 3ኛ ዙር የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል የፎቶግራፎች እና የአጫጭር ፊልሞች ውድድር!

በ2016 ዓ.ም. በኅዳር 30 ቀን የሚውለው ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች ቀን (December 10) የዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ (Universal Declaration of Human Rights) 75ኛ ዓመት የሚታሰብበት በመሆኑ ልዩ ያደርገዋል።

ይህንንም በማስመልከት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በ3ኛው ዙር የፊልም ፌስቲቫል ለዕይታ የሚቀርቡ የፎቶግራፍ እና የአጫጭር ቪዲዮዎች ውድድሮች በሕይወት የመኖር መብት እና በቂ የሆነ መኖሪያ ቦታ/ቤት የማግኘት መብት ዙሪያ በማተኮር  የተዘጋጀ ሲሆን፣ በውድድሩ ለመሳተፍ እና ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ዝርዝሩን ይመልከቱ። https://bit.ly/46sReAw

ለተወዳዳሪዎች መልካም እድል!
ዩጋንዳ እና ታንዛንያ ሁለት ዝሆን ሲሞት የሚጮሁለትን ያህል 230 የሀገሬ ህዝብ ባለፈው 5 ቀን ውስጥ ብቻ ደራ ወረዳ ውስጥ አልቆ በመላው ሚድያ በአብዛኛው ዝም ተብሏል!

ከደራ ወረዳ ነዋሪዎች እና አንድ "ዝም ማለት ከበደኝ" ብለው መረጃ ካደረሱኝ የአካባቢው አመራር እንዳረጋገጥኩት የዛሬ አምስት ቀን ገደማ በዚህ በሰሜን ሸዋ ዞን አካባቢ 230 ገደማ ሰዎች በታጣቂዎች ተገድለዋል፣ ከ120 በላይ ሰዎች ታግተው ወደ ጫካ ተወስደዋል። ሶሻል ሚድያ ላይ ለመለጠፍ የማይሆኑ እጅግ አሳዛኝ እና ዘግናኝ ምስሎችም ደርሰውኛል።

ነዋሪዎቹ እንደጠቆሙኝ ዛሬ ድረስ የሚቃጠሉ ቤቶች ይታያሉ፣ በርካታ ህዝብ ተሰዶ ጫካ ገብቷል።

ይሁንና የሞቱት እንዳለ ሆኖ ሌላ ተጨማሪ ህዝብ እንዳያልቅ ትኩረት እንኳን እንዲሰጠው ሚድያዎች ትኩረት አልሰጡትም፣ እስካሁን እንዳየሁት ከቲክቫህ እና ኢትዮ ኤፍኤም ውጪ።

ይህን ያህል ሞትን ተለማመድነው?

ትንሽ እንኳን የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ሰምቶ "እረፉ፣ ተጠያቂነት ያመጣል፣ ወንጀል ነው..." እንዳይል የውጪ ሚድያው እንዳይሰራ ተደረጓል፣ የሀገር ውስጥ ሚድያው ፍርሀት አለበት፣ ዲያስፖራ ሚድያው ከማጋጋል ውጪ መፍትሄ ሊሆን አልቻለም። የመንግስት ሚድያው... ጭራስ ባይነሳ ይሻላል።

ያሳዝናል!

ለሞቱት ነፍስ ይማር፣ ለተሰደዱት ፈጣሪ ይጠብቃቸው።

@EliasMeseret
ምናልባትም በኢትዮጵያ የቅርብ ግዜ ታሪክ እጅግ ከፍተኛ የሆነ የውጪ ፖሊሲ እና የጂኦፖለቲካዊ አካሄድ ለውጥ የታየበት ንግግርን ጠ/ሚር አብይ አህመድ ከደቂቃዎች በፊት በመንግስት ሚድያዎች በተላለፈ ንግግራቸው አድርገዋል።

ይህ በዋናነት ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት ልትሆን እንደሚገባ በሚያስረዳው ንግግራቸው በርካታ ነጥቦችን አንስተዋል... ከኤርትራ ጋር በንግግር እና በፌዴሬሽን/ኮንፌዴሬሽን ሊፈጠር ከሚችል ውህደት እስከ ባህር በር ባለቤት መሆን።

ይህ እጅግ ከፍተኛ ውጤት ሊኖረው የሚችል ንግግርን በርካታ ተንታኞች በተለያየ መልኩ ሊገልፁት ቢችሉም እንደ አንድ ጋዜጠኛ እና የአለም አቀፍ ግንኙነት እና ህግ ተማሪ ጎረቤት ሀገራትን ሊያስቆጣ፣ የራሳቸው የፖሊሲ (ወታደራዊም ሆነ ፖለቲካዊ) ለውጥ እንዲያረጉ ሊያስገድድ የሚችል እንዲሁም በተለይ ከኤርትራ ጋር በቅርብ አመታት ታድሶ የነበረውን ግንኙነት ሊበጣጥስ የሚችል እንደሆነ ይሰማኛል።

በግሌ እስማማበታለሁ፣ አልስማማበትም... ምንም ለውጥ ስለማያመጣ ይቅር። ነገር ግን ይህ ሀሳብ ይፋ የተደረገበት ግዜ ትክክል ነው አይደለም የሚለው ላይ ሀሳብ መሰንዘር እችላለሁ።

ሁላችንም እንደምናውቀው እና እንደሚሰማን በበርካታ የሀገራችን ስፍራዎች ግጭቶች፣ ጦርነቶች እና ብጥብጦች ይታያሉ። የሰሜኑ ጦርነት ያከተለው ጠባሳ እንኳን ሊሽር ገና አልደረቀም፣ በርካቶች ወጥቶ መግባትን የሚናፍቁባቸው ቦታዎች ሞልተዋል፣ ኢኮኖሚው በጦርነቶች ክፉኛ ተጎድቷል፣ ህዝቡ በኑሮ ውድነት እየተሰቃየ ነው፣ አንዳንድ የተጣሉ ማዕቀቦች ገና አልተነሱም፣ በርካታ የዲያስፖራው ማህበረሰብ አኩርፎ ይገኛል፣ መከላከያ ከተከታታይ ጦርነቶች በሗላ restock and replenish ሊያረግ ገና ይገባዋል... ወዘተ።

ታድያ በዚህ ሁሉ መሀል ይህ ዛሬ ሀሳቡ የቀረበው ሀሳብ ወደ ጦርነት ቢያመራ ውጤቱ ምን ይሆናል?

ይህ የብዙዎቻችን ጥያቄ ይመስለኛል።

@EliasMeseret
#Update በጃፓን የኤርትራ አምባሳደር የሆኑት እስጢፋኖስ በትዊተር ገፃቸው ትናንት ምሽት በኢትዮጵያ ለቀረበው ሀሳብ ምላሽ የሚመስል ይህን ፅሁፍ አስፍረዋል:

"ግንቦት 1998 (እአአ) የኢትዮጵያ ፓርላማ በኤርትራ ላይ ጦርነት አወጀ... ከዛ በኋላ ኤርትራን የባህር በር አልባ ለማድረግ ሁሉንም አይነት አሰቃቂ ድርጊት ፈፀመ። ድርጊቱ ግን አልተሳካም! ይህን የማያውቅ ማን ነው?"

*የዚህ የ1998 ጦርነት መነሻ ኤርትራ ኢትዮጵያን በመውረሯ እንጂ ኤርትራን ወደብ አልባ ለማድረግ እንዳልነበር ቢታወቅም የአምባሳደሩ አባባል ግን በኤርትራውያን ዘንድ የትናንቱ ንግግር የፈጠረውን ስሜት በከፊል የሚያሳይ ይመስላል።

@EliasMeseret
#የካድሬነገር ይህን ታውቁ ኖሯል?

"ማህበራዊ ሚድያ ላይ ተፅእኖ መፍጠር እና ቅቡልነትን ማሳደግ" በሚል ፕሮግራም 300 ካድሬዎች የዛሬ አመት ተኩል ገደማ ስልጠና ተሰጥቷቸው ነበር፣ ስራቸው ደግሞ እስከ 10,000 የሚደርሱ ሌሎች ካድሬዎችን አሰልጥነው ማህበራዊ ሚድያ ላይ ማሰማራት ነው።

አላማውስ?

የአመራሩን ገፅታን ሊያሳድጉ የሚችሉ መረጃዎችን ማህበራዊ ሚድያ ላይ ማሰራጨት፣ የሚቃወሙትን በአስተያየት ማውገዝ፣ በአመራሮች በቀጥታ በሚተላለፉ ስርጭቶች ላይ ጭምር በመግባት የድጋፍ አስተያየቶችን በተለያዩ ቋንቋዎች መፃፍ... ወዘተ።

እነዚህ ናቸው እንግዲህ ፌስቡክ Live ስርጭቶች ላይ ገብተው ሲፃፅፉ እና ሌላውን ሲሳደቡ የሚውሉት። ካድሬ ቢንጫጫ ለቀይ ወጥ እና አልጫ ያለው ትዝ አለኝ።

*Someone just asked me... አሁን እነሱም ቢሮ ለመግባት ታክሲ ይጋፋሉ?

በሙዝ ልጣጭ ማስኬድ ነበር እንጂ!

@EliasMeseret
ነፍሳችሁ በሰላም ትረፍ፣ ቤተሰቦችን ያፅናናልን!

ሲሆን ሲሆን በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለው የማስታወስ ፕሮግራም እና የሀዘን ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ ሊሆን ይገባ ነበር። በፖለቲከኛው ቅዠት እና ስካር ህይወቱን ለህዝቤ እና ለሀገሬ ብሎ የገበረው በመላው ኢትዮጵያ የሚገኝ ህዝብ ጭምር ስለሆነ።

#NeverAgain

Not in our lifetime!

Photo: Tigray TV

@EliasMeseret
"ይህ እንዳይመጣ ብዙ ተማጽኖ ስናቀርብ የነበረ ቢሆንም ሽበት እና ክህነት የማይከበርበት ዘመን ላይ ደርሰን ለዚህ ኀዘን በቅተናል። በኀዘን የተጎዳችሁ አባቶችና እናቶችም ይህ ቢሆን ኖሮ እያላችሁ ራሳችሁን እንዳትጎዱ፤ የእናንተ መጎሳቆል የሞቱትን ቀና አያደርግምና ልባችሁን እንድታበረቱ እናሳስባለን ምክንያቱም መቃብር መጨረሻችን ያልሆነ የትንሣኤ ሕዝብ ነን"--- ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት

እኚህ የሀይማኖት አባታችን ሰላም ይውረድ፣ በአንድ ወቅት ደግሞ ድምፄ ታፈነ ስላሉ በአክቲቪስት እና ባለስልጣናት ጭምር " ጁንታ" ሲባሉ፣ እንደተራ ግለሰብ ፌስቡክ ላይ ሲሰደቡ ነበር። በአንድ ወቅት እኔንም "ለምን ቃለ መጠይቅ አደረግክላቸው" ተብሎ ብዙ ጉምጉምታ እና ማስፈራርያ ነበር (ጭራሽ ቃለ መጠይቁን ያደረግኩት እኔ ባልሆንም)።

በረከትዎ ይደርብን አባታችን።

@EliasMeseret
እየተቀዛቀዘ ያለውን የኢትዮጵያ የፊልም ኢንደስትሪን መንግስት መቀላቀሉ ዘርፉን ያነቃቃዋል ተብሎ ይጠበቃል።

@EliasMeseret
ለልጅ፣ ልጆቼ የማወርሳቸው ትልቁ ነገር ህዝቤ በእርስ በርስ ጦርነት ሲጫረስ "ግፋ በለው፣ ቁረጠው፣ ፍለጠው፣ ግደለው..." ሳልል በሙያዬ ማድረግ የምችለውን እስከ መጨረሻው ድረስ መረጃን ለህዝብ እና ለአለም አቀፍ ማህበረሰብ ማድረስ ብቻ መስራቴ የሰጥኝን ሰብአዊነት ነው።

ይህን ማድረጌ ብዙ ነገር አስከትሎብኛል (ወደፊት እገልፀው ይሆናል) ነገር ግን ይህ እኔ ላይ የደረሰው ብዙ ሺህ መቶ ሌሎች ዜጎች ጦርነቱ ያስከተለባቸው ጉዳት እና ወዳጅ፣ ዘመድ ማጣት እጅጉን ይበልጣልና አላማርርም።

"ስልጣኔን ተነጠቅኩ" ያለ እና "ስልጣኔን ሊወስዱብኝ ነው" ብሎ የተነሳ አካል ምድሪቱን በደም አጨቅይቷል፣ አሁንም ውጊያ እና ተኩስ እዚህ እዚያም አለ። በዚህ ሁሉ መሀል ማረጋገጥ የቻልኩትን ያህል መረጃ ለህዝብ ማቅረብ እቀጥላለሁ።

አብራችሁኝ ለነበራችሁ ሁሉ ምስጋናዬ የላቀ ነው።

መልካም ምሽት።

@EliasMeseret
#ድምፅእንስጣቸው የሀገራችንን ስም ላስጠሩ እነዚህ ሪከርድ ሰባሪ ጀግኒቶች ፌስቡክ ላይ ድምፅ በመስጠት ለሽልማት እናብቃቸው!

የአለም አትሌቲክስ ተቋም የዘንድሮን ምርጥ አትሌት ምርጫ ይፋ ማድረጉን ተከትሎ የኬንያው ቴሌኮም ኩባንያ ሳፋሪኮምን ጨምሮ በርካታ የኬንያ ሚድያዎች እና ተቋማት ለአትሌቶቻቸው ድምፅ እንዲሰጥ (ፌስቡክ ላይ ከፍ ያለ Like ማግኘት አንዱ መስፈርት ነው) ጥረት እያረጉ ይገኛሉ።

ለምሳሌ ፌዝ ኪፕዬጎን 69,000 ላይክ አግኝታ እየመራች ሲሆን ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች ጉዳፍ ፀጋይ 18,000፣ እንዲሁም አትሌት ትግስት አሰፋ 15,000 ላይክ አግኝተው እየተመሩ ነው።

ትግስት ለመስበር እጅግ ያስቸግራል ተብሎለት የነበረውን የአለም የሴቶች ማራቶን የዛሬ ሶስት ሳምንት በበርሊን ከተማ 2:11:53 በመግባት ሰብራለች፣ ጉዳፍ ደግሞ ከኢትዮጵያ እርቆ የነበረውን የ5 ሺህ ሜትር የዓለም ሪከርድ ወደ ኢትዮጵያ የዛሬ ወር ገደማ መልሳለች።

ታድያ እነዚህን ጀግኒት አትሌቶቻችንን ድምፅ እንስጣቸው እና አሸናፊ እናድርጋቸው! Let's do this!

አትሌት ትግስት አሰፋ:
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid024j37JK7wv2YuLe8gRbNCwK8Yp6WCxzVHwUihpwj92bDknTPreC4YkYmv928koCEwl&id=100064391421386&mibextid=Nif5oz

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid02kyjKTiCpm9jJzDhGRa4zkkm7PJA2whqojcLtQQgtuBuSeJk5Ytz1vxQAqRCRghfEl&id=100064391421386&mibextid=Nif5oz

@EliasMeseret
አሁን አሁን እየተለመደ የመጣ ነገር ቢኖር መንግስት ሊሄድባቸው ያሰበባቸውን መንገዶች ቀድሞ ለአክቲቪስቶች ማሾለክ እና በግልፅ ሊናገራቸው የማይፈልጋቸውን ነጥቦች በእነሱ በኩል ማስተላለፍ ነው።

ይህን ለማለት ያነሳሳኝ በቅርቡ ጠ/ሚሩ ስለ ባህር በር ጉዳይ ባደረጉት ገለፃ ዙርያ እነዚህ አክቲቪስቶች እያነሷቸው ያሉ አስገራሚ ነጥቦች ናቸው። ለምሳሌ ባለፉት ጥቂት ቀናት ከሰማኋቸው መሀል የተወሰኑት እነዚህ ይገኙበታል:

- ኤርትራ ከፈለገች አሸዋውን ትብላው፣ እኛ የዘይላ ወደብን እንጂ አሰብን እና ምፅዋን አላልንም

- የኤርትራ ወደቦች ካስፈለጉንም በፀባይ ጠይቀን እምቢ ካሉ በፈለጉት መልኩ መቀበል እንችላለን

- ጅቡቲን የምታክል ሀገር ወደብ ኖሯት እኛ የለንም ማለት ውርደት ነው፣ በወታደር ከቦ ማስጨነቅ ነው

ታድያ እነዚህ ነጥቦችን ሲያነሱ እና ሲጥሉ የሚውሉት አብዛኞቹ ታማኝ ሎሌ አክቲቪስቶች ናቸው፣ በብሄራዊ ቴሎቭዥን ቀርበው ሴራ ሲተነትኑ የሚውሉም አሉ።

የዲፕሎማሲ ስራውን በከፊል ለአክቲቪስት አስረክቦ በእንደዚህ አይነት አካሄድ የት እንደምንደርስ እንጃ፣ ምክንያቱም የኢትዮጵያ ህዝብም ሆነ በቅርበት ሀገሪቱን የሚከታተል ሁሉ ይህን ያለተለመደ አካሄድ በደንብ ተረድቶታል፣ ከመንግስት በተዋረድ "እንደዚህ በሉ..." ተብለው እንደሆነ ተገንዝቧል።

የሀገር ጉዳይ ነውና ይታሰብበት!

@EliasMeseret
እንደምን አመሻችሁ፣ በቅድሚያ የወደብ ዜናዎቻችንን እናቀርባለን...

በቅርብ ቀን አይቀርም 🫣

@EliasMeseret
የፍርድ ቤት ዘገባዎች ላይ ፋና ብሮድካስቲንግ ይበል የሚያሰኝ በእውቀት የሚሰራ ዜና እየሰራነው፣ ኢቢሲ ግን አሁንም በተጠርጣሪ እና ወንጀለኛ መሀል ብዥታ ያለበት ዜና እያቀረበ ነው።

ለምሳሌ በእነዚህ የቀድሞ የኢሚግሬሽን ሰራተኞች ዙርያ ገና የፍርድ ሂደታቸው እየተጀመረ ባለበት ሁኔታ "በሙስና የተዘፈቁ" ብሎ ማቅረብ አንድ ግለሰብ ንፁህ ሆኖ የመገመት መብቱን በጣሰ መልኩ ወንጀለኛ ብሎ መግለጫ ማውጣት በራሱ ህግ መጣስ ነው።

ሁላችንም በኢሚግሬሽን መስሪያ ቤት ውስጥ ባሉ አንዳንድ ግለሰቦች አማካኝነት ፓስፖርት በተለይ ለጎረቤት ሀገራት ዜጎች ሲቸበቸብ እንደነበር እናውቃለን፣ ለዚህም በህግ ይዳኙ። ነገር ግን ንጹህ ናቸው፣ አይደሉም የሚለው በፍርድ ቤት እንጂ ሚድያ አይደለም።

የፋና የፍርድ ቤት ሪፖርተር ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ በርቺ 🙏

@EliasMeseret
በባህር በር ጉዳይ ላይ የተነሳውን ሀሳብ ተመርኩዞ የሰጠሁትን አስተያየት አንዳንዱ የተቃውሞ አድርጎ ስሎታል።

ግን አይደለም፣ የድጋፍም የተቃውሞም አይደለም፣ በግልፅ እንዳሰፈርኩት እንደ አንድ ተራ ግለሰብ የእኔ አቋም ዋጋ እምብዛም የለውም፣ ስለዚህ ይቆይ ብያለሁ።

እርግጠኛ ሆኜ መናገር የምችለው ግን ይፋ የተደረገበት ግዜ ትክክለኛ አይደለም፣ timing አመራረጥ ላይ ችግር አለ ብዬ ከነ ምክንያቱ በግልፅ አስፍሬያለሁ።

አሁንም ኢትዮጵያውያን ልብ ልንል የሚገባው ሌላው ጉዳይ የመንግስት ሚድያዎች እና አክቲቪስቶቻቸው እንደሚሉት "እንነጋገር ነው የተባለው... ስለ ጦርነት የተናገረ የለም" የሚለው የማለሳለስ አካሄድ ህዝብን አዘናግቶ ጦርነት መሀል ሊማግድ የሚችል አደገኛ ጉዳይ መሆኑን ነው... ልክ በ15 ቀን የሚያልቅ "የህግ ማስከበር ነው" ተብሎ በሁለት አመት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን እንደፈጀው ጦርነት ማለት ነው።

የዲፕሎማቲክ ምንጮች እንደሚነግሩን ከሆነ በጎረቤት ሀገራት ዘንድ "confusion, tension and unease" የፈጠረ ንግግር እንደሆነ፣ በተጨማሪም የወደብ ጉዳዩ አሁን ሊፈታ ባይችል በልጅ፣ ልጆቻችን ይፈታል መባሉ ከዚህ በኋላ የሚመጣው ትውልድ ጭምር እስከመጨረሻው በጥርጣሬ እንዲተያይ እና በቀጠናው አስተማማኝ እና ቋሚ ሰላም እንዳይፈጠር ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ያስረዳሉ።

እስካሁን ኤርትራ፣ ጅቡቲ እና ሶማልያ ለጉዳዩ negative መልስ ሰጥተዋል፣ ከ OSINT ምንጮች የሚገኙ መረጃዎች ደግሞ በኤርትራ በኩል የጦር እንቅስቃሴ እንዳለ ያሳያሉ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ይህ የኢትዮጵያ ሀሳብ በቴሌቭዥን መስኮት ይፋ ከመደረጉ በፊት ለኤርትራ መንግስት በውስጥ ቀርቦ "a resounding no!" የተባለ መልስ በመመለሱ ጉዳዩ ለህዝብ ይፋ እንደተደረገ የደረሰኝ መረጃ ይጠቁማል።

እነዚህ እንደ ማሳያ ያነሳኋቸው ነጥቦች የሚያመላክቱት ጉዳዩ ጥልቅ የሆነ ጂኦፖለቲካዊ ውጤት ያለው እንደሆነ፣ ሊያስከትል የሚችለውን ከፍተኛ ፖለቲካዊ፣ ወታደራዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጫና ለመቋቋም ውስጣዊ ጥንካሬ እና አንድነት እንደሚያስፈልግ ያሳያሉ።

በመጨረሻም፣ እንደፈረደብን ከዚህ በኋላ ደግሞ የተለየ ሀሳብ ያለውን "የኤርትራ ተላላኪ፣ የታሪካዊ ጠላቶቻችን ተባባሪ፣ የሻዕቢያ ደጋፊ...ወዘተ" ስሞችን ወይም እንደ ጁንታ እና ጃውሳ የሚወጣ አዲስ ስም በስፋት እንደምናይ ይታየኛል። Mark my word!

ሰላም ለሀገራችን፣ ሰላም ለሰው ዘር በሙሉ!

@EliasMeseret
ተዘርፎ የተዘረፈው ወርቅ!

ጉዳዩ እንዲህ ነው: የሰሜኑ ጦርነት ከጀመረ በኋላ በርካታ የፀጥታ አካላት ከሹማምንት ጋር በመሆን የትግራይ ተወላጅ ቤቶችን እየፈተሹ በተለይ ወርቅ እና ብር ይዘርፉ ነበር።

እነዚህ ዜጎች ፍርድ ቤት እንዳይሄዱ እና ለማንም አቤት እንዳይሉ ማስፈራርያ ይነገራቸዋል፣ አለበለዛ በ "ጁንታ" ደጋፊነት አስከፊ ነገር እንደሚጠብቃቸው ስለሚነገራቸው ዝም ብለው ይቀመጣሉ።

ታድያ በዚህ መልኩ ከተዘረፈው ወርቅ ውስጥ እጅግ በርካታ መጠን ያለው ወርቅ የደረሳቸው አንዱ ከፍተኛ ሹም (የፍትህ አካል ከፍተኛ አመራር ነበሩ፣ የህዝብ ተወካይም ናቸው) ቤታቸው በሌባ ይሰበርና ወርቁ በሙሉ ይወሰዳል (በጥቆማ የተደረገ ይመስላል)።

ከዛማ እንዴት አርገው ያስመልሱ ወይም ለፖሊስ እንኳን ያመልክቱ!?

ይህ ሁሉ ወርቅ ከየት መጣ እንዳይባል እና እንዳይጠቆሩ ዝም... ጭጭ... ዋጥ አርገውት እንደቀሩ በቅርብ ጉዳዩን ከሚያውቁ ሁለት ሰዎች ከሰሞኑ ያገኘሁት መረጃ ይጠቁማል።

የሰው ወርቅ አያደምቅ ይልሀል ይሄ ነው።

@EliasMeseret
ፕሮፌሰር ገቢሳ ኤጀታ የአሜሪካን ብሄራዊ የሳይንስ ሜዳሊያ ሽልማትን ከፕሬዚደንት ጆ ባይደን እጅ ዛሬ ተቀብለዋል።

በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ፈጠራ ዘርፍ እጅግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላደረጉ የአሜሪካ ዜጎች በሚሰጠው በዚህ ሽልማት 19 ሰዎች የተካተቱ ሲሆን የፐርዱ ዩኒቨርሲቲ ባልደረባው ፕሮፌሰር ጋቢሳ አንዱ ሆነዋል።

መምህርና ተመራማሪው ፕሮፌሰር ጋቢሳ ኤጄታ ለሽልማቱ ያበቃቸው በከፍተኛ የምርምር ስራቸው  የእፅዋት ዘረመል ምህንድስና በመጠቀም በረሃማ የአየር ንብረት እና ነፍሳትን የሚቋቋሙ የአዝርዕት ዘሮችን በማግኘታቸው ነው። ግኝታቸው በሚሊዮን ለሚቆጠሩ የምግብ ዋስትናን እንደሚያረጋግጥ ታምኖበታል።

ፕሮፌሰር ጋቢሳ ኤጄታ በምግብ ዘርፍ ላበረከቱት አስተዋፅዖ ከዚህ በፊት ከዓለም የምግብ ፕሮግራሙ ሽልማት የተበረከተላቸው መሆኑ የሚታወቅ ነው።

Via White House/EPA

@EliasMeseret