ቀን ህዳር 14/2013 ዓ.ም
ኤልድራ አካዳሚ
ውድ ተማሪዎች መደበኛ ትምህርት እስከሚጀመር ድረስ ለዝግጅት የሚረዱ ትምህርቶችን በዚሁ በ telegram channel እየላክንላችሁ እንዳለ ይታወቃል እስካሁንም 2 ዙር ትምህርቶችን ልከናል በዚህም መሰረት 3ኛ ዙር ትምህርቶች የላክንላችሁ ሲሆን እናንተም እንደከዚህ ቀደሙ በደብተራችሁ እየገለበጣችሁ እና እያጠናችሁ እንድትቆዩ እናሳስባለን ።
ት/ቤቱ
ኤልድራ አካዳሚ
ውድ ተማሪዎች መደበኛ ትምህርት እስከሚጀመር ድረስ ለዝግጅት የሚረዱ ትምህርቶችን በዚሁ በ telegram channel እየላክንላችሁ እንዳለ ይታወቃል እስካሁንም 2 ዙር ትምህርቶችን ልከናል በዚህም መሰረት 3ኛ ዙር ትምህርቶች የላክንላችሁ ሲሆን እናንተም እንደከዚህ ቀደሙ በደብተራችሁ እየገለበጣችሁ እና እያጠናችሁ እንድትቆዩ እናሳስባለን ።
ት/ቤቱ
ኤልድራ አካዳሚ ቀን ህዳር 30/2013 ዓም ማስታወቂያ ለወላጆች በሙሉ ጉዳዩ ፦ የተማሪዎች የትምህርት ቤት ወርሀዊ ክፍያን ይመለከታል ፦ እንደሚታወቀው የተማሪዎች የትምህርት ቤት ወርሀዊ ክፍያ በአዋሽ ባንክ በኩል በትምህርትቤታችን ሂሳብ ቁጥር ስትከፍሉ እንደነበር ይታወቃል ነገር ግን ከዚህ በኃላ በሂሳብ ቁጥራችን መክፈላችሁ ቀርቶ ሁሉም ወላጅ ማንኛውንም የልጆቻችሁን የትምህርቤት ክፍያ የምትከፍሉት የተማሪውን ሙሉ ስም ከነ አያት እና ክፍሉን በትክክል በመፃፍ የትምህርት ቤቱ ኮድ ኤልድራ አካዳሚ EL002 በመሆኑ በዚህ ኮድ ብቻ ያለባችሁን ክፍያ አጠናቃችሁ እንድትከፍሉ በቅድሚያ እናሳስባለን ። ማሳሰቢያ ፦ 1. በትምህርት ቤቱ ኮድ ኤልድራ አካዳሚ EL002 ከፍላችሁ የባንክ እስሊፕ ይዛችሁ ትምህርት ቤት መምጣት እንዴማያስፈልግ ለማሳሰብ እንወዳለን 2. በየወሩ ኤልድራ አካዳሚ EL002 ኮድን በመፃፍ / በመጠቀም ክፍያው ወር በገባ ከ 1 እስከ 5 ባሉት ቀናት የሚከፈል ይሆናል ። ት/ቤቱ
ኤልድራ አካዳሚ ቀን 20/04/ 2013 እንኳን ደስ አላችሁ ለኤልድራ አካዳሚ ወላጆች ተማሪዎች መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች በሙሉ ሁሌም100% በማሳለፍ እና ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ በየአመቱ የዋንጫ ተሸላሚ የሆነው ትምህርትቤታችን ኤልድራ አካዳሚ የ2012 ዓ ም የ8ተኛ ክፍል ተማሪዎቻችን ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ሁሉም ወደ 9ኛ ክፍል ማለፉቸውን በደስታ እንገልፃለን። ት/ቤት
ኤልድራ አካዳሚ ቀን 24/04 2013 ጤና ይስጥልን ውድ ወላጆች :- የልጆቻችሁን የትምህርት ቤት ወርሀዊ ክፍያን እስከ ታህሳስ ወር ድረስ አጠናቃችሁ ያልከፈላችሁ ትምህርትቤቱ እስከአሁን እንድትከፍሉ በቂ ጊዜ የሰጠ በመሆኑ ያለባችሁን ክፍያ አጠናቃችሁ እንድትከፍሉ በድጋሚ በጥብቅ ለማሳሰብ እንወዳለን ክፍያውን አጠናቆ ያልከፈለ ተማሪን ከጥር 01/2013 ዓ ም ጀምሮ የማንቀበል መሆኑን በቅድሚያ ለማሳሰብ እንወዳለን። ት/ቤቱ
ውድ ወላጆች፦ እንደሚታወቀው ተማሪዎቻችን ለመጪው የሚኒስትሪ ፈተና በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ ት/ቤቱ ለተማሪዎች ይጠቅማል ለፈተናው ዝግጁ ያደርጋቸዋል ብሎ ያመነበትን መንገድ ሁሉ በመጠቀም ለተማሪዎቻችን አስፈላጊውን እገዛ በማድረግ ላይ እንገኛለን በተጨማሪም ያው እንደሚታወቀው በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት የባለፈው አመት ት/ት ሳይጠናቀቅ የተቋረጠ በመሆኑ እና የሚኒስትሪ ፈተና ደግም የ7ተኛን እና የ8ተኛን ክፍል ስለሚያጠቃልል ይህንኑ ታሳቢ አድርገን የ5 አመት የሚኒስትሪ ጥያቄዎችን በየትምህርት አይነቱ እና በየዩኒታቸው ለይተን በጥሩ ሁኔታ ተዘጋጅቷል በመሆኑም ተማሪዎቹ ይህንን ወርክቡክ በቀራቸው ጊዜ በአግባቡ ከሰሩ ሳይማሩ ያሳለፉትንም ጊዜ የሚያካክስ ይሆናል ተብሎ ታስቦ ስለተዘጋጀላቸው ወላጆች ይህንኑ በመረዳት ቀደም ሲል በኮምኒኬሽን የላክነው ኮፒ ቤት አስቀምጠንላችሁ እራሳችሁ ኮፒ እያረጋችሁ እንድትወስዱ መልክት መላካችን ይታወሳል ነገር ግን ከወዋጋውም አኳያ የተሻለ አማራጭ ስለሚሆን ፍላሸ ይዛችሁ በመምጣት ሶፍት ኮፒውን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን በተጨማሪም በቴሌግራም የምንልክላችሁ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን። ት/ቤት
ውድ ወላጆች :- የ2013 ዓ/ም የ 8ተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተናን ተማሪዎቻችን ዛሬ መጀመራቸው ይታወቃል ጥሩ ውጤትም እንደሚያመጡ እየተማመንን እሁድ ስኔ 27/2013 ዓ/ም ከ2፡00 - 6፡00 ተማሪዎቹ በት/ቤት ጊቢ ተገኝተው ፎቶ ለመነሳት ተማሪዎቹ ፈቃድ ጠይቀው የተፈቀደላቸው በመሆኑ ወላጆች ይህንን ፕሮግራም በቅድሚያ እንድታውቁት በአክብሮት እናሳስባለን።
ኤልድራ አካዳሚ 13/12/2013 ዓ.ም
ውድ ወላጆች እና ተማሪዎች
የ2013 ዓ.ም የ8ተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎቻችን ወደ ሚቀጥለው ክፍል በጥሩ ውጤት ያለፉ መሆኑን ስንገልፀ በደስታ ነው።
እንኳን ደስ አላችሁ!!
ውድ ወላጆች እና ተማሪዎች
የ2013 ዓ.ም የ8ተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎቻችን ወደ ሚቀጥለው ክፍል በጥሩ ውጤት ያለፉ መሆኑን ስንገልፀ በደስታ ነው።
እንኳን ደስ አላችሁ!!