Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
8.52K subscribers
118 photos
1 video
18 files
218 links
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
Download Telegram
ሰኔ 15፣ 2016 ዓ.ል | ዙልሒጃ 16፣ 1445 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ልዑካን መካ የሚገኝውን የንጉሥ አባ ጂፋር የኢትዮጵያውያን ሐጃጆች ማረፊያ ሕንፃ ጎበኙ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
በክብር ዶ/ር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የተመራ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሥራ አስፈጻሚ ቡድን፣ መካ የሚገኝውንና ለብዙ ዓመታት ኢትዮጵያውያን ሐጃጆችን ሲያገለግል የኖረውን የንጉሥ አባ ጂፋር የሐጃጆች ማረፊያ ሕንጻ ጎበኘ።

ለኢትዮጵያውያን ሐጃጆች መቀበያና ማረፊያ እንዲኾን ታስቦ በንጉሥ አባ ጂፋር ዘመን የታነፀውና የኢትዮጵያውያን ሀብት የኾነው ዘመን ተሻጋሪው ሕንጻ በዘንድሮው የሐጅ ወቅት አገልግሎት አለመስጠቱ ታውቋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ከፍተኛ የሥራ አስፈጻሚ አባላት ጉብኝት ዓላማም ታሪካዊው የኢትዮጵያውያን ሐጃጆች ማረፊያ አገልግሎት መስጠት ያቋረጠበትን መንስዔ ተረድቶ፣ በልዩ ሁኔታ ችግሩን ለመፍታት ያለመ አቅጣጫ መስጠት እንደኾነ ክቡር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ተናግረዋል።

ታሪካዊው የንጉሥ አባ ጂፋር ሕንጻ በ1445 ዓ.ሒ ሐጅ አገልግሎት ያልሰጠው፣ የሳዑዲ አረቢያ የሐጅ ሚኒስቴር የሐጃጆች ማረፊያን አስመልክቶ ያወጣውን የብቃት መስፈርት ባለማሟላቱ መኾኑ በዚሁ ጊዜ ተገልጿል።

ከብረት የተሠራው የሕንጻው የውጪ መወጣጫ ደረጃ ረጅም ዓመታት ሲያገለግል የኖረ ቢኾንም፣ የሳዑዲ አረቢያ የሐጅ ሚኒስቴር ያወጣውን የብቃት መስፈርት ባለማሟላቱ፣ ፈቃዱ ሊታደስ እንዳልቻለ በዚሁ ጊዜ ተነግሯል።

የንጉሥ አባ ጂፋር የሐጃጆች ማረፊያ ሕንጻ ታሪካዊ አሻራውን በሚያጎለብት መልኩ፣ መሟላት ያለበትን በማሟላት በሚቀጥለው ዓመት ችግሩ ተፈትቶ ለአልረህማን እንግዶች ማረፊያነት የተሻለ አገልግሎት እየሰጠ እንዲቀጥል ከወዲሁ አስፈላጊው ጥረት ሁሉ መደረግ እንዳለበት ክቡር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከሕንጻው አሥተዳደር ጋር በመኾን፣ ችግሩን ለመፍታት እንደሚሠራ ፕሬዚደንቱ ተናግረዋል።

በጉብኝት መርኃ ግብሩ ላይ የምክር ቤቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን፣ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ፀሐፊ ሸይኽ ሐሚድ ሙሳ፣ ጥሪ የተደረገላቸው የሀገር ሽማግሌዎችና የተለያዩ የክልል መጅሊስ አባላት ተገኝተዋል።

​•••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
ሰኔ 16፣ 2016 ዓ.ል | ዙልሒጃ 17 1445 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
93 በግል ከሐጅ ተመላሾች የመልስ ጉዞ መስተጓጎል ገጠማቸው።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መካ |
የ1445 ዓ.ሒ የሐጅ ሥርዓተ አምልኮን ፈጽመው ፈጥነው ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ በሳዑዲ አየር መንገድ በግል ቲኬት የቆረጡ 93 ያህል ከሐጅ ተመላሾች በመልስ ጉዟቸው ላይ መስተጓጎል እንደገጠማቸው ታወቀ፡፡

እነዚህ ሐጃጆች በመልስ ጉዟቸው መጉላላት የገጠማቸው፣ ሲገቡ ፓስፖርታቸውን የተቀበላቸው ኩባንያ በሰዓቱ ደርሶ ፓስፖርታቸውን ባለመመለሱ ሳቢያ በረራ ስላመለጣቸው መኾኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በተጨማሪም፣ ከመካ ወደ ጀዳ የሚወስዳቸው አውቶብስ ዘግይቶ መምጣት፣ የሐጃጆች በሰዓቱ ተጠቃልለው ወደ አውቶብሱ አለመግባት፣ የግል ተመላሽ ሐጃጆች የቲኬት መረጃ በሑጃጅ መስተንግዶ ሲስተም ውስጥ የሚገኝ ባለመሆኑ ያንን ከተመላሾቹ ወስዶ ለማስተካከል የወሰደው ጊዜ የተጓዦችን ጀዳ አውሮፕላን ማረፍያ የመድረሻ ሰዓት ለማዘግየት ምክንያት መኾናቸው ተጠቅሷል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የመልስ ጉዟቸው ለተስተጓጎለባቸው ከሐጅ ተመላሾች በጀዳ የመቆያ ሆቴል በመከራየት የመልስ ጉዟቸውን ለማሳለጥ አማራጭ የማፈላለግ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በመቀናጀት የሚያካሂደው የሐጃጆች የመልስ ጉዞ መርኃ ግብር፣ ሐጃጆች ከኢትዮጵያ ወደ ሳዑዲ አረቢያ (መዲና) በተሳፈሩበት ቅደም ተከተል መሠረት የሚከናወን መኾኑ ይታወቃል፡፡

ይህን የመልስ ጉዞ መርኃ ግብር እየጠበቁ መቆየትን የማይመርጡ የተወሰኑ ሐጃጆች፣ በሳዑዲ አየር መንገድ በግል ቲኬት ቆርጠው በጊዜ ለመመለስ እንደሚወስኑ ይታወቃል።

በዚህ መልኩ ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ ቲኬት የቆረጡ 93 ያህል ከሐጅ ተመላሾች ከላይ በተጠቀሱት ተደራራቢ ምክንያቶች የመልስ ጉዟቸው እንደተስተጓጎለ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ኃላፊ ሸይኽ አብዱልፈታህ ሙሐመድ ናስር ተናግረዋል፡፡

የእነዚህ ከሐጅ ተመላሾች የመልስ ጉዞ መስተጓጎል ጠቅላይ ምክር ቤቱን እንደሚያሳስበው የጠቀሱት ኃላፊው፣ ‹‹በተቻለ ፍጥነት ተለዋጭ በረራ እንዲያገኙ ጉዳዩ ከሚመለከተው አካል ጋር በመገናኘት ለችግሩ መፍትኄ በማፈላለግ ላይ ነን›› ብለዋል፡፡

የመልስ ጉዞ የቅደም ተከተል ተራን ከመጠበቅ ይልቅ ፈጥነው ለመመለስ የፈለጉ ሐጃጆች ከወትሮው በዛ ማለታቸው በአሠራራቸው ላይ ጫና እንደፈጠረ የጠቀሱት ሸይኽ አብዱልፈታህ፣ ያም ኾኖ ዘርፉ የሚመለከታቸውን አካላት በማነጋገር ለተፈጠረው ችግር መፍትኄ ለማስገኘት ጥረት እያደረገ መኾኑን ተናግረዋል፡፡

የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሥራ አስፈጻሚና የሐጅ ዐብይ ኮሚቴ አባል የኾኑት ኢንጅነር አንዋር ሙስጠፋ በበኩላቸው፣ ፈጥነው ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ በመሻት በሳዑዲ አየር መንገድ በግል ቲኬት ለቆረጡት 93 የሐጅ ተመላሾች በተለያዩ ምክንያቶች በመዘግየታቸውና ፓስፖርታቸውን የተቀበላቸው ኩባንያም በሰዓቱ ባለመድረሱ በረራ እንዳመለጣቸው ተናግረዋል፡፡

ከሐጅ ተመላሾቹ በረራ ያመለጣቸው ቢሆንም፣ ለበለጠ መጉላላት እንዳይዳረጉ መጅሊሱ በጀዳ ሆቴል ተከራይቶ ሌላ የመመለሻ አማራጭ መፍትኄ የማፈላለግ ጥረት ላይ መኾኑን ኢንጅ. አንዋር ተናግረዋል፡፡

ወቅቱ የሐጅ ተመላሽ ጫና ያለበት፣ የበረራ መደራረብና እጥረት የሚፈጠርበት በመኾኑ፣ መጅሊሱ ባሳደረው ጫና ብዙ ሰዎችን የሚይዝ ግዙፍ አውሮፕላን በመጠቀም በዕለቱ ከሚመለሱት ጋር በረራ ያመለጣቸውን ሐጃጆች ጨምሮ በማሳፈር ችግሩን ለመፍታት እየተሠራ እንደኾነ ኢንጅነር አንዋር ተናግረዋል፡፡

​•••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
ሰኔ 16፣ 2016 ዓ.ል | ዙልሒጃ 18፣ 1445 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ምክር ቤቱ 89 የግል ከሐጅ ተመላሾች ወጪያቸው ተሸፍኖ ዛሬ ለሊት ሀገራቸው እንዲገቡ አመቻቸ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መካ |
በሳዑዲ አየር መንገድ በግል ቲኬት ቆርጠው ትናንት ጉዟቸው የተስተጓጎለባቸው 90 ያህል ከሐጅ ተመላሾች ሙሉ ወጪያቸው ተሸፍኖ ዛሬ ሌሊት ወደ ሀገራቸው እንደሚገቡ ተነገረ።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሥራ አስፈጻሚና የሐጅ ዐብይ ኮሚቴ አባል የሆኑት ኢንጅነር አንዋር ሙስጠፋ በትናንትናው ዕለት ጉዟቸው የተስተጓጎለባቸውን የ90 ከሐጅ ተመላሾች የመልስ ጉዞ ለማሳካት ከሳዑዲ የሐጅ ሚኒስቴር ጋር በመነጋገር በተደረገው ጥረት 89 የሐጅ ተመላሾች ዛሬ አመሻሹን እንዲሳፈሩ ሁኔታዎች መመቻቸታቸውን ተናግረዋል።

በሐጅና ዑምራ የሲስተም ክፍል ዋና ተጠሪ የሆኑት ኢንጅነር አንዋር ሙስጠፋ አያይዘውም በግል ቲኬት ከቆረጡት 90 ከሐጅ ተመላሾች ወስጥ አንዷ በግል ምክንያት በዛሬው የሳዑዲ አየር መንገድ ተመላሾች ውስጥ አለመካተቷን ተናግረዋል።

በግል ቲኬት ቆርጠው ከበረራው ሰዓት በመዘግየታቸው ሳቢያ የትናንቱ የመልስ ጉዞ ያመለጣቸውና በመጅሊሱ ወጪ ጀዳ በሚገኝ ሆቴል ያረፉት ተመላሾች ሙሉ ወጪያቸው በሳዑዲ አረቢያ የሐጅ ሚኒስቴር ተሸፍኖ በሳዑዲ አየር መንገድ አመሻሹን ወደ ሀገራቸው ለመሳፈር ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን ለማወቅ ተችሏል።

ለችግሩ መፍትኄ የማፈላለግ ጥረቱ እንዲሳካ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅና ዑምራ ዘርፍ የሥራ ኃላፊዎች ያደረጉት ጥረት የሚመሠገን እንደሆነ ኢንጅነር አንዋር ተናግረዋል።

​​•••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
ሰኔ 19፣ 2016 ዓ.ል | ዙልሒጃ 20፣ 1445 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ከሐጅ ተመላሾች ማዑ ዘምዘም ቦሌ አይሮፕላን ማረፊያ ላይ እንደሚሰጣቸው ተነገረ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የሐጅ ሥርዓታቸውን አጠናቅቀው ሀገር ቤት ለተመለሱ ሐጃጆች ቦሌ ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፍያ ላይ ማዑ ዘምዘም እንደሚሰጣቸው ተነገረ።

የሐጅ ሥርዓትን አጠናቅቀው በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሀገር ቤት ለተመለሱ ሐጃጆች ቦሌ ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፍያ እንደደረሱ በነፍስ ወከፍ 5 ሊትር ማዑ ዘምዘም እንደሚታደላቸው በጠቅላይ ምክር ቤቱ የሐጅና ዑምራ ዘርፍ፣ የሐጃጆች አቀባበልና የማዑ ዘምዘም እደላ አስተባባሪ የኾኑት ሐጂ አብዱልፈታህ ብርሃኑ ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ምክር ቤቱ ለተከበሩት የሐጅ ተመላሾች አቀባበልና የማዑ ዘምዘም ዕደላ ኮሚቴ ማዋቀሩን የጠቀሱት

የመልስ ጉዟቸውን በኢትዮጵያ አየር መንገድ አድርገው ሀገር ቤት ለሚመለሱ ሐጃጆች በነፍስ ወከፍ የሚሰጣቸው 5 ሊትር ማዑ ዘምዘም ከተመላሾቹ ቀድሞ ቦሌ ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፍያ እንደሚደርስ አስተባባሪው ሐጂ አብዱልፈታህ ተናግረዋል።

በሳዑዲ አየር መንገድ ጉዟቸውን ያደረጉ የሐጅ ተመላሾች የነፍስ ወከፍ የማዑ ዘምዘም ድርሻቸው ጀዳ አየር መንገድ ላይ እንደሚሰጣቸው ሐጂ አብዱልፈታህ ተናግረዋል።

የተከበሩ የአርረህማን እንግዶችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ሥራን ሰኔ 18፣ 2016 ዓ.ል የጀመረው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፣ እስከ ዛሬ በተደረጉ ጉዞዎች (በኢትዮጵያና በሳዑዲ አየር መንገዶች) የዛሬውን ጨምሮ አንድ ሺህ ስምንት መቶሐጃጆችን ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ አድርጓል።
••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
ሰኔ 20፣ 2016 ዓ.ል | ዙልሒጃ 21፣ 1445 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የሐጅ ተመላሾች ኦፕሬሽን የሥራ ሂደቱን ገምግሞ የሥራ መመሪያ አወጣ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መካ |

የ1445 ዓ.ሒ የሐጅ ሥርዓትን ፈጽመው ወደ ሀገር ቤት የሚመለሱ የአርረህማን እንግዶችን የአሸኛኘት የሥራ ሂደት የሚገመግም ስብሳባ ተከናወነ።

የሐጅ ተመላሾች አሸኛኘት የሥራ ሂደት ግምገማውን የመሩት የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሥራ አስፈጻሚ፣ የሐጅ ዐብይ ኮሚቴ አባል እና የሲስተም ክፍል ዋና ተጠሪ ኢንጅነር አንዋር ሙስጠፋ፣ የአርረህማን እንግዶች የሐጅ ሥርዓታቸውን ጨርሰው ወደ ሀገር ቤት መመለስ ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬዋ ምሽት ድረስ 2 ሺህ 900 ሐጃጆች ወደ ሀገር ቤት መሸኘታቸውን ተናግረዋል።

በግመገማው ላይ የአሸኛኘት ሂደቱን በሚያሳልጡት አባላት ከተመላሾች በኩል ከሚፈቀደው የሚዛን ልክ በላይ ሻንጣን ማጨቅ፣ በሻንጣ እንዲያዝ የማይፈቀድ እቃ መያዝ፣ የፓስፖርት መጥፋት፣ የመሰናበቻ ጠዋፍን (ጠዋፈል ወዳዕ) በጊዜ አለመፈፀም፣ በሰዓት አለመገኘት ከገጠሙ ተግዳሮቶች መካከል ተጠቅሰዋል።

በሌላም በኩል የመረጃ በአግባቡና በግልፅነት ያለመድረስና መዘናጋት ያስከተለው ችግር በግምገማው ላይ ተነስቷል።

የሐጅ ተመላሾች የአሸኛኘት አገልግሎት አሰጣጡ የነበረበትን ደካማና ጠንካራ ጎኖች በመገምገም፣ ዘልማዳዊ አሠራሩን በመተው ተበታትኖ ያለውን ሥራ ወጥነትና ተመጋጋቢ በኾነ አግባብ የመፈፀም አስፈላጊነትና አፈጻፀሙ ላይ ማብራሪያ ተሰጥቶ የጋራ ግንዛቤ ተይዟል።

በሥራ ሂደቱ ላይ የመረጃ ክፍተት የአገልግሎት አሰጣጡ ዋነኛ እንቅፋት መኾኑ ታምኖበት፣ ይህን ለማረቅ የሚያስችል የሥራ መመሪያ መውጣቱ የተነገረ ሲኾን፣ ለመመሪያው ተግባራዊነት በይዘቱ ላይ የጋራ ግንዛቤ መያዝ የዚህ ግምገማ ውይይት ትልቅ ግብ መሆኑን ኢንጂነር አንዋር ተናግረዋል።

ይህ የግምገማ መድረክ መፈጠሩ ሁሉም በየዘርፉ ያሉ ችግሮችና የአሠራር ሂደት ክፍተቶችን ለማየት እንዲችል መኾኑን የጠቀሱት ኢንጂነር አንዋር፣ ዘልማዳዊ አሠራርን በመተው አሸኛኘቱን ይበልጥ ሊያቀላጥፍ የሚችለውን የአገልግሎት አሰጣጥ መመሪያ በመከተል በጋራ መትጋት የሥራ ሂደቱን ተመጋጋቢ በማድረግ የሐጅ ተመላሾች ጉዞ
ስኬታማ እንዲሆን ያስችላል ብለዋል።

የሐጅ ሥራ በባህሪው የብዙ ባለሙያዎችን ውህደትና መናበብ የሚጠይቅ በመኾኑ የአገልግሎት ሰጪዎችን ቅንነት እና ትዕግስት እንደሚጠይቅ የጠቀሱት ኢንጂነር አንዋር፣ ይህን ከተመላሽ ሐጃጆች ማግኘት በማይቻልበት ሁኔታ እንደ አገልግሎት ሰጪ ከእኛ የሚጠበቀውን በከፍተኛ ትዕግሥት እና አስተዋይነት መከወን ይኖርብናል ብለዋል።

​​•••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
ሰኔ 24፣ 2016 ዓ.ል | ዙልሒጃ 25፣ 1445 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
ኢንና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ከ1445 ዓ.ሒ. ኢትዮጵያውያን ሐጃጆች 10ሩ በሐጅ ላይ ሕይወታቸው አለፈ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መካ |

በ1445 ዓ.ሒ. ኢትዮጵያውያን ሐጃጆች ውስጥ በድምሩ 10 ሐጃጆች ሕይታቸው ማለፉን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሥራ አስፈጻሚና የሐጃጆች የሕክምና ቡድን ዋና አስተባባሪ ሸይኽ አል-መርዲ አብዱላሂ አሺቢ ተናገሩ።

አሥሩ ኢትዮጵያውያን ሐጃጆች በሙሉ በመካ፣ መስጂደል ሀረም ላይ ሶላተል ጀናዛ ተሰግዶባቸው የቀብር ሥርዓታቸው እንደተፈፀመ ሸይኽ አል-መርዲ አብዱላሂ ተናግረዋል።

የአምስቱ ሐጃጆች ሕይወት የሐጅ ሥርዓት ከመጀመሩ በፊት ማለፉን ያስታወሱት ሸይኽ አል-መርዲ የሌሎቹ ሕይወት ያለፈው በአረፋ ወቅት መኾኑን ተናግረዋል።

ከሟቾቹ መካከል በተለይ ሁለቱ እናቶች በሐጅ ሥርዓተ ክንዋኔ ወቅት ጠፍተው ከነበሩት አምስት ሰዎች መካከል መኾናቸውና 'ሚና' ላይ ሕይወታቸው ማለፉ እንደታወቀ ተነግሯል።

በሳዑዲ አረቢያ መንግሥት የሐጃጆችን ደኅንነት ጉዳይ ኃላፊነት ወስዶ የሚከታተለው ኤጀንሲ፣ ስድስቱ ሐጃጆች በድንገተኛ ህመም፣ ሁለቱ በክፍላቸው ውስጥ ሞተው የተገኙ ሲኾን፣ አንድ ሐጃጅ በመኪና አደጋ፣ አንድ በካንሰር፣ እንዲሁም ሌላ አንድ ሐጃጅ በህመም ምክንያት እንደሞቱ የሆስፒታሉን ውጤት አያይዞ ይፋዊ መረጃ ሰጥቷል።

የሐጃጆቹ የቀብር ሥርዓት የተፈፀመው በሀገሪቱ ደንብ መሠረት በሦስት ሰዓታት ውስጥ የሟች ቤተሰብ፣ የቅርብ ዘመድ አልያም ምስክር የሚኾን ጎረቤት በተገኘበት እንደኾነ ለማወቅ ተችሏል።

በዚሁ መሠረት የዘጠኙ ሟቾች ሥርዓተ ቀብር የተፈፀመው በዚሁ ደንብ መሠረት ሲኾን፣ ሚና ላይ ሞተው ከተገኙት የአንዷ እህት በተባለው ጊዜ ውስጥ መገኘት ባለመቻሏ ሕይወቷ ማለፉን የሚያረጋግጥ ሰርተፊኬት ተሰጥቷል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሥራ አስፈጻሚና የሐጃጆች የሕክምና ቡድን ዋና አስተባባሪ ሸይኽ አል መርዲ አብዱላሂ፣ የ1445 ዓ.ሒ. የአርረህማን እንግዶች ሆነው መጥተው ሞት ቢቀድማቸውም ኒያቸው ከፍ ያለ በመኾኑ፣ ሞታቸውን የሸሂድ (የሰማዕት) ደረጃ የሚያደርሱት አሉ ብለዋል።

"ሞት የማይቀር ተፈጥሯዊ ሕግ በመኾኑ፣ በእንዲህ ዓይነት ሂደት መሞት ትልቅ ፀጋ ነው" ብለዋል ሸይኽ አል መርዲ።

"ሀረም ላይ የዓለም ሙስሊም የአርረህማን እንግዶች ሆነው በመጡበት አጋጣሚ፣ ጀናዛቸው ላይ ተሰግዶ መካ ላይ መቀበር ትልቅ ፀጋ በመሆኑ፣ ቤተሰቦቻቸው ሊሶብሩ እና ሊፅናኑ ይገባል" ብለዋል።
ሰኔ 25፣ 2016 ዓ.ል | ዙልሒጃ 26 1445 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ከሐጅ ተመላሾች በሻንጣቸው ዉስጥ የተከለከሉ ቁሶችን ባለማስገባት የንብረታቸውን ደኅንነት እንዲጠብቁ ተጠየቀ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የሐጅ ሥርዓታቸውን ፈጽመው ወደ ሀገር ቤት የሚመለሱ ሐጃጆች የዘምዘም ውሃን ጨምሮ ሻንጣቸው ዉስጥ የተከለከሉ ቁሶችን ባለማስገባት የንብረቶቻቸውን ደኅንነት እንዲጠብቁ የ1445 ዓ.ሒ የሐጅና ዑምራ የሽኝት ኮሚቴ አሳሰበ።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከሰኔ 15፣ 2016 ዓ.ል ጀምሮ በግል እና በጠቅላይ ምክር ቤቱ አማካኝነት የአውሮፕላን ቲኬት የቆረጡ የ1445 ዓ.ሒ የተከበሩ የአላህ እንግዶችን ወደ ሐገር የመመለሻ መርኃ ግብር እያስፈፀሚ እንደሚገኝ የጠቀሱት የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ተጠባባቂ ሥራ አስኪያጅና የሽኝት ኮሚቴ አባል ሸይኽ ኢስሀቅ አደም የአላህ እንግዶችን የመልስ ጉዞ ለማሳለጥና የንብረቶቻቸውን ደኅንነት ለመጠበቅ የተለያዩ ሥራዎች ሲሠሩ መቆየታቸውን ተናግረዋል።

ከእነዚህ ሥራዎች አንዱ በአውሮፕላን ጉዞ ላይ በግል ሻንጣ ውስጥ መከተት የሌለባቸውን ነገሮች ለሐጃጆች በሀገር ውስጥና ከሳዑዲ የመልስ ጉዞ ከመጀመሩ በፊት የግንዛቤ ትምህርት መሰጠቱ እንደሚገኝበት ሼይኽ ኢስሐቅ ተናግረዋል።

ቁጥራቸው ትንሽ ቢኾንም፣ አንዳንድ ሐጃጆች የአውሮፕላን ጉዞ ሕግን በመተላለፍ ሻንጣቸው ዉስጥ የተከለከሉ ነገሮችን በመያዛቸው በሳዑዲ አየር መንገድ የበረራ ደኅንነት ሠራተኞች ተይዞ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ሻንጣዎቻቸው መከፈታቸውን ኃላፊው
ተናግረዋል።

በቀጣይ ወደ ሀገር ቤት ተመላሽ የተከበሩ የአላህ እንግዶች ለመልስ ጉዞ በሚያደርጉት ዝግጅት፣ ማዑ ዘምዘምን ጨምሮ ሻንጣ ውስጥ መገኘት የሌለባቸውን ነገሮች ባለመጨመር ንብረቶቻቸውን እንዲጠብቁ ያሳሰቡት ኃላፊው፣ በዚህ ምክንያት ለሚፈጠሩ ችግሮች ጠቅላይ ምክር ቤቱ ኃላፊነት እንደማይወስድ ተናግረዋል።
​​•••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1

ሰኔ 26፣ 2016 ዓ.ል | ዙልሒጃ 27፣ 1445 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••

በ2024ቱ የበድር ኢትዮጵያ ጉባኤ ላይ የሚሳተፉ የክብር እንግዶች ዳላስ ቴክሳስ መግባት ጀምረዋል።

በድር የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ድርጅት በአሜሪካን ሀገር ዳላስ ቴክሳ ለሚካሄደው የ2024 ጉባኤ ተጋባዥ የሆኑ የመጅሊስ አመራሮች በዛሬው ዕለት ቴክሳስ ገብተዋል።
.
የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር ዶክተር ሼህ ሱልጣን አማን ኤባ፣ የፌዴራል መጅሊስ ዋና ፀሀፊ ሼኽ ሀሚድ ሙሳ እንዲሁም የአዲስ አበባ መጅሊስ የምክር ቤት አባል ኡስታዝ ሱፍያን ኡስማን አሜሪካን ሀገር ዳላስ ቴክሳስ ሲገቡ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። በቀጣይ የፌዴራል መጅሊሱን ፕሬዝዳንት ጨምሮ ሌሎች ተጋባዥ የክብር እንግዶች ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ምንጭ፦ሀሩን ሚዲያ
ሰኔ 26፣ 2016 ዓ.ል | ዙልሒጃ 27፣ 1445 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
"የሃይማኖት ተቋሞቻችን ለዘላቂ ሰላማችን" በሚል መሪ ቃል የውይይት መድረክ በሸራተን አዲስ ተካሄደ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የሰላም ሚኒስቴር "የሃይማኖት ተቋሞቻችን ለዘላቂ ሰላማችን" በሚል መሪ ቃል የሃይማኖት አባቶች፣ መሪዎች፣ አስተማሪዎችና አመራሮች የተሳተፉበት ሀገር አቀፍ ኮንፈረንስ በሸራተን አዲስ ሆቴል አካሄደ።

ኮንፈረንሱ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የፕሬዚደንቱ ተወካይና የፈትዋና ምርምር ዘርፍ ተጠሪ ሼይኽ ኢድሪስ ዓሊ ሑሴን ዱዓና በአባቶች ፀሎት ተከፍቷል።

ኮንፈረንሱን በንግግር የከፈቱት የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዱዓለም፣ ሃይማኖቶች የተለያዩ አስተምህሮ ቢኖራቸውም ለሰው ዘር ሰላም የሚሠሩ መሆኑን ጠቅሰው፣ የጋራ ቤታችን ለሆነችው ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ሚኒስቴሩ ከሁሉም የሃይማኖት ተቋማት ጋር አብሮ እንደሚሠራ ተናግረዋል።

በኮንፈረንሱ ላይ በሰላም ሚኒስቴር እና በአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት የውይይት መነሻ ጽሑፎች ቀርቦ በተሳታፊዎች ውይይት ዳብሯል።

በኮንፈረንሱ ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የፕሬዚደንቱ ልዩ አማካሪ ዑስታዝ አቡበከር አሕመድ ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም የሃይማኖት አባቶች የማይተካ ሚና እንዳላቸው ጠቅሰው፣ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከሁሉም የሃይማኖት ተቋማት ጋር ተቀራርቦ በመሥራት ለሰላም ጥረቶች ዕድሎችን ሊሰጥ ይገባዋል ብለዋል።

"የሃይማኖት ተቋሞቻችን ለዘላቂ ሰላማችን" በሚል መሪ ቃል በተካሄደው በዚሁ ኮንፈረንስ ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤቶች ሥራ አስፈፃሚዎች፣ ኢማሞች፣ ዱዓቶች እና ምሁራን ተገኝተዋል።
​​•••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
ሰኔ 27 :2016 ዓ.ል | ዙልሒጃ 28:1445 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••



ፕሬዚዳንቱ የበድር ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ጉባዔ ላይ ተገኙ።

ሰኔ 27:2016 ዓ.ል (አዲስ አበባ)የኢትዮጵያ  እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የክብር  ዶክተር ሼይኽ ሐጂ  ኢብራሒም  ቱፋ የ2024 የበድር ኢትዮጵያ ጉባዔ ላይ ለመገኘት በአሜሪካዉ   በቴክሳስ ግዛት፡ ዳላስ ከተማ ፎርዝ ወርዝ አየር ማረፊያ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው።


ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል በራሳቸውና በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

"በኢስላማዊ መርሆች ላይ ፀንቶ መቆም" በሚል መሪ ቃል በቴክሳስ ሪቻርድ ሰን ሲቲ ሬናይሰስ ሆቴል የሚካሄደው ይኽ ጉባዔ ማምሻውን በይፋ ተከፍቷል።

በዓመታዊዉ የበድር ዓለም አቀፍ ጉባዔ ላይ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ፅሁፎች ቀርበው ዉይይት እንደሚያደረግባቸዉ ለማወቅ ተችልዋል።

ከሰኔ 27 -30 /2016 ዓ፡ል(ከጁላይ 4-7/2024 እ.ኤ. አ) የሚካሄደውን ይኽ ንን ጉባዔ በዳላስ የሚገኘዉ የቢላል ኮሚኒቲ ማዕከል እንዳዘጋጀዉ ሀሩን ሚዲያ ዘግቦታል፡፡


የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1

ሙሃረም 1፣ 1446 ዓ.ሒ. | ሰኔ 30፣ 2016 ዓ.ል.

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ሙስሊሙ ማኅበረሰብ በድሬደዋ አሸዋ ገበያ ንብረታቸው በእሳት አደጋ ለወደመባቸው ወገኖች የእርዳታ እጁን እንዲዘረጋ ተጠየቀ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

ሙስሊሙ ማኅበረሰብ በድሬዳዋ አሸዋ ገበያ ንብረታቸው በእሳት አደጋ ለወደመባቸው ወገኖች የእርዳታ እጁን እንዲዘረጋ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጥሪ አድርጓል።

ጥሪው የተደረገው በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የፕሬዚደንቱ ተወካይና የፈትዋና ምርምር ዘርፍ ተጠሪ ሸይኽ ኢድሪስ ዓሊ የተመራው ልዑክ በእሳት አደጋ ሳቢያ ጉዳት የደረሰበትን የድሬዳዋ አሸዋ የገበያ ማዕከል ከጎበኙ በኋላ ነው።

የእሳት አደጋው በንብረት ላይ ያስከተለው ጉዳት ከፍተኛ መኾኑን መረዳታቸውን የተናገሩት ሸይኽ ኢድሪስ፣ በጉዳቱ ዙሪያና በንብረታቸው ላይ ጉዳት ለደሰባቸው የማኅበረሰቡ አባላት የሚደረገውን ቀጣይ ድጋፍ በተመለከተ ከድሬዳዋ አሥተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሐር እና ጉዳት ከደረሰባቸው የንግዱ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

ሙስሊሙ ማኅበረሰብ በድሬዳዋ ከተማ አሥተዳደር አሸዋ ገበያ ሰልባጅ ተራ በተነሳው የእሳት አደጋ ንብረታቸው የወደመባቸው ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም በተከፈቱ አራት የእርዳታ ማሰባሰቢያ ዝግ የባንክ ሒሳብ ቁጥሮች ድጋፍ እንዲያደርግ ሸይኽ ኢድሪስ ጥሪ አቅርበዋል።

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዓሊሞች ጉባዔ ምክትል ሰብሳቢ የሆኑት ዶክተር ጀይላን ኸድር በእሳት አደጋ ንብረታቸውን ያጡ ወገኖችን አሏህ ሶብር እንዲሰጣቸው፣ መላው ሙስሊሙ ማኅበረሰብም የበኩሉን አስተዋፅዖ እንዲያበረክት መልዕክታቸው አስተላልፈዋል።

ሰኔ 25፣ 2016 ዓ.ል የእሳት ቃጠሎ በደረሰበት አሸዋ ገበያ ትናንት በተካሄደው ጉብኝት ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የዓሊሞች ጉባዔ ምክትል ሰብሳቢ ዶክተር ጀይላን ኸድር፣ የዳዕዋ ዘርፍ ተጠሪ ሼይኽ አሚን ኢብሮ እና የድሬዳዋ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ተገኝተዋል።


​​•••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
ሐምሌ 3፣ 2016 ዓ.ል | ሙሐረም 4፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ሞሮኳዊው የቁርኣን ውድድር ዳኛ ዑስማን ሰ ቀሊ ሑሴን አዲስ አበባ ገቡ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የሞሮኮዉ ንጉሥ ሙሐመድ 6ተኛ ፋውንዴሽን ዋና ፀሐፊ የዶክተር ሲዲ ሙሐመድ ሪፍቂ አማካሪ በሆኑት ዑስታዝ ዑስማን ሰ ቀሊ ሑሴን የተመራ የልዑካን ቡድን የቁርኣን ውድድር ለመዳኘት አዲስ አበባ ገባ።

የልዑካን ቡድኑ ቦሌ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የትምህርትና ማህበራዊ አገልግሎቶ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶክተር አብደላ ከድር እንዲሁም ሌሎች የምክር ቤቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውለታል።

በዑስታዝ ዑስማን ሰ ቀሊ ሑሴን የተመራው የልዑካን ቡድን አዲስ አበባ የገባው፣ የፊታችን ጁምዓ ሐምሌ 5፣ 2016 ዓ.ል. (ሙሐረም 6፣ 1446 ዓ.ሒ) በስካይላይት ሆቴል የሚካሄደውን ሀገር አቀፍ የቁርኣን ዉድድርን ከሀገራችን ዓሊሞች ጋር በጋራ ለመዳኘት ነው።  

ዛሬ አዲስ አበባ የገቡት ዑስታዝ ዑስማን ሰ ቀሊ በጠቅላይ ምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች በተደረገላቸው አቀባበል መደሰታቸውን ተናግረዋል።

የፊታችን ጁምዓ የሚጠናቀቀው ሀገራዊ የቁርኣን ዉድድር በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዓሊሞች ጉባዔ ጽ/ቤት የተዘጋጀ ሲኾን፣ ለአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር የደረሱት ሐፊዞች በክልልና የከተማ አስተዳደር የእስልምና ጉዳይ ከፍተኛ ምክር ቤቶች በተዘጋጁ ውድድሮች ተሳትፈው ያሸነፉ መኾናቸውን ዶክተር አብደላ ተናግረዋል።

በስካይላይት ሆቴል የሚካሄደው ውድድር በቀጣይ ኢትዮጵያን ወክለው በዓለም አቀፍ የቁርኣን ውድድር መድረክ የሚሳተፉ ተወዳዳሪዎች የሚለዩበት መሆኑ ዉድድሩን በጉጉት የሚጠበቅ እንደሚያደርገው ዶክተር አብደላ ተናግረዋል።

ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ በቁርኣን ዉድድር የሀገራችንን ስም በዓለምአቀፍ ደረጃ ያስጠሩ ወጣቶች እንዳሉ የጠቀሱት ዶክተር አብደላ በዚህ ዉድድር አሸናፊ የሚኾኑ ሐፊዞችም በዓለምአቀፍ የቁርኣን ውድድር መድረክ ሀገራቸውን ወክለው እንደሚወዳደሩ ተናግረዋል።

በቦሌ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በተደረገው የአቀባበል ስነ ሥርዓት ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የዉጭ ግንኙነት ኅላፊ ፕሮፌሰር አደም ካሚል ተገኝተዋል።
•••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1

ሐምሌ 4፣ 2016 ዓ.ል | ሙሐረም 5፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ፕሬዚደንቱ የሞሮኮዉ ንጉሥ ሙሐመድ 6ተኛ ፋውንዴሽን የልዑካን ቡድን አባላትን ተቀብለው አነጋገሩ።
..............................................
አዲስ አበባ |
ፕሬዚደንቱ በሞሮኮ አምባሳደር ነዚሃ አሎዩ የተመራውን የሞሮኮዉ ንጉሥ ሙሐመድ 6ተኛ ፋውንዴሽን የልዑካን ቡድን አባላት ተቀብለው አነጋገሩ።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ በኢትዮጵያ የሞሮኮ አምባሳደር ነዚሃ አሎ የተመራውን የሞሮኮዉ ንጉሥ ሙሐመድ 6ተኛ ፋውንዴሽን   የልዑካን ቡድን አባላት በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።
በዚሁ ጊዜ ክቡር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም እንግዳ ተቀባይ ወደኾሆነችው ሀገራችን ኢትዮጵያ በመምጣችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
በኢትዮጵያ የሞሮኮ አምባሳደር ክብርት ነዚሃ አሎዩ በበኩላቸው በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለተደረገላቸው መልካም አቀባበል በራሳቸውና በልዑካን ቡድኑ አባላት ስም ምሥጋና አቅርበዋል፡፡
አምባሳደሯ በሞሮኮ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን የቆየ ግንኙነት አውስተው፣ በቀጣይ ጊዜያት ኤምባሲያቸው ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ጋር በጋራ ጉዳዮች ላይ አብሮ ለመሥራት ፍላጎት እንዳለው ተናግረዋል።
በውይይቱ ላይ የተገኙት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሐጂ ከማል ሐሩን ምክር ቤቱ እንደ አዲስ ከተዋቀረ ወዲህ ሙስሊሙን ማኅበረሰብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያዩ የአጭር እና የረጅም ጊዜ ፕሮጀክቶች ቀርፆ እየሠራ መሆኑን ለቡድኑ አስረድተዋል።
የሞሮኮዉ ንጉሥ ሙሐመድ 6ተኛ ፋውንዴሽን ዋና ፀሐፊ የዶክተር ሲዲ ሙሐመድ ሪፍቂ አማካሪ የሆኑት ዑስታዝ ዑስማን ሰ ቀሊ ሑሴን ከጠቅላይ ምክር ቤቱ የዓሊሞች ጉባዔ  ጽሕፈት ቤት ጋር በመተባበር በነገው ዕለት /ጁምዓ/ በስካይላይት ሆቴል ለሚደረገው ሀገራዊ የቁርኣን ውድድር ስኬት ጠቅላይ ምክር  ቤቱን አመስግነዋል።
የሞሮኮዉ ንጉሥ ሙሐመድ 6ተኛ ፋውንዴሽን በአፍሪካ፣ በእስያና በአውሮፓ በሚገኙ 70 ማዕከላት እየሠራ እንደሚገኝ የተናገሩት ዑስማን ሰቀሊ ሁሴን፣ በቀጣይ ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ጋር በጋራ ለመሥራት ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ለልዑካን ቡድኑ በሸራተን አዲስ ሆቴል የምሳ ግብዣ አድርገዋል።
ዛሬ በጠቅላይ ምክር ቤቱ በተደረገው ውይይት ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱና የዓሊሞች ጉባዔ ጽሕፈት ቤት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1

ሐምሌ 4፣ 2016 ዓ.ል. | ሙሐረም 6፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እና በድር ኢትዮጵያ በጋራ ለመሥራት ተስማሙ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እና ከ23 ዓመታት በፊት በሰሜን አሜሪካ የተቋቋመው በድር ኢትዮጵያ ዓለምአቀፍ የሙስሊሞች ድርጅት በጋራ ለመሥራት ተስማሙ።

ስምምነቱን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ ሸይኽ ሐሚድ ሙሳ እና የበድር ኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ፕሬዚደንት አቶ አሕመድ ወርቁ ተፈራርመዋል።

በድር ኢትዮጵያ ላለፉት ሁለት አሠርት ዓመታት በሀገር ቤት ከሚገኙ የተለያዩ ተቋሞች ጋር በመተባበር የሙስሊሙን ችግር ለመቅረፍ በታለሙ የተለያዩ ተግባራት ላይ የበኩሉን አስተዋጽዖ ሲያበረክት ቆይቷል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እና በድር ኢትዮጵያ ዓለምአቀፍ የሙስሊሞች ድርጅት የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ይበልጥ በማጠናከር፣
-- በውጪ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን በሀገር ቤቱ የሙስሊም ኅብረተሰብ ልማትና ዕድገት ላይ የበኩላቸውን አስተዋጽዖ የሚያደርጉበትን ሁኔታ ማመቻቸት፣

-- በዲያስፖራውና በሀገር ቤቱ ማኅበረሰብ መካከል ያለውን ትስስር በማጠናከር የእውቀት ሽግግርን ለማጎልበት የድጋፍ ሥራዎችን፣ መድረሳዎችን፣ መስጂዶችን እንዲሁም ሌሎች የተለያዩ የልማትና ሃይማኖታዊ እውቀቶችን ለማስፋፋትና ለማጠናከር በጋራ ለመስራት፣

-- በመላው ዓለም በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች መካከል እስላማዊ አንድነት እንዲጎለብት በጋራ ለመሥራት፣

በድር-ኢትዮጵያ ዓለምአቀፍ የሙስሊሞች ድርጅት እንደ ተቋም በሀገር ቤት የትምህርት፣ የጤናና ሌሎች ማኅበራዊ ጠቀሜታ ያላቸው ፕሮጀክቶችን መሥራት የሚችልባቸውን ሁኔታዎች ማመቻቸት በጋራ ስምምነቱ ከተካተቱ ዐበይት ፍሬ ነገሮች ውስጥ መኾናቸውን ከሐሩን ሚዲያ የተገኘው ዘገባ አመልክቷል።

•••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
ሐምሌ 5፣ 2016 ዓ.ል | ሙሐረም 6፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ፕሬዚዳንቱ ሀገራዊ የቁርዓን ውድድር አስጀመሩ ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዓሊሞች ጉባዔ ፅ/ ቤት እና በሞሮኮዉ ንጉሥ ሙሐመድ 6ተኛ ፋውንዴሽን በጋራ የተዘጋጀው ሀገራዊ
የቁርዓን ውድድር በስካይ ላይት ሆቴል ተጀመረ።

የእለቱ መርሐግብር በታዎቂው ሞሮኳዊ ቃሪዕ ኢሊያስ አል - ማህያዊ ተከፍቷል።

ውድድሩ በዕለቱ የክብር እንግዳ
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የክቡር ዶክተር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ንግግር ተከፍቷል።

የሠላምና የዕውነት ሀገር መሆኗ በነብዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) የተመሠከረላት እና ከመካ ቀጥሎ ቁርዓን የተቀራባት ሀገራችን ኢትዮጵያ ላይ ይኽን አይነቱ የቁርዓን ውድድር ለማድረግ የመጡትን በሞሮኮዉ ንጉሥ ሙሐመድ 6ተኛ ፋውንዴሽን ልዑካን ቡድን እንኳን ደህና መጣችሁ ብለዋል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ ከቁርዓን ጋር ያላት ግንኙነት ከመካ ቀጥሎ መሆኑን የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ ወጣቶች ከቁርዓን ጋር ያላቸውን ግንኙነት በማጠናከርና ይኽንን መሰሉ ውድድር ላይ በመሳተፍ የሀገራችንን ስም በአለም ላይ ማስጠራት ይኖርባቸዋል ብለዋል።

በኢትዮጵያ  የሞሮኮ አምባሳደር  ነዚሃ አሎ በ ጠቅላይ ምክር ቤት  ዓሊሞች  ጉባዔ ፅ/ ቤት  እና በሞሮኮዉ ንጉሥ ሙሐመድ 6ተኛ ፋውንዴሽን በጋራ የተዘጋጀው ሀገራዊ የቁርዓን ውድድር የመክፈቻ መርሐግብር ላይ በመገኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል።

የሞሮኮ ንጉሦ ሙሐመድ ስድስተኛ ፋውንዴሽን የዋና ፀሐፊ የዶክተር ሲዲ ሙሐመድ ሪፍቂ አማካሪ ዑስታዝ ዑስማን ሰ ቀሊ ሑሴን ኢትዮጵያ ለእስልምና ያደረገችውን ታሪካዊ አስተዋፅኦ አይረሴ መሆኑን ተናግረዋል።

ዛሬ በስካይ ላይት ሆቴል በተጀመረው ሀገራዊ የቁርዓን ውድድር ላይ የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስተር ዴዔታ ዶክተር ኽይረዲን ተዘራ ፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች ፣ዑለሞች ፣የኦሮሚያና የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤቶች የስራ ኅላፊዎች ተገኝተዋል።

•••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1


​ሐምሌ 5፣ 2016 ዓ.ል | ሙሐረም 6፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የሞሮኮዉ ንጉሥ ሙሐመድ 6ተኛ ፋውንዴሽን ሀገር አቀፍ የቁርኣን ውድድር ተጠናቀቀ።
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
አዲስ አበባ |
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዓሊሞች ጉባዔ ጽሕፈት ቤት እና በሞሮኮዉ ንጉሥ ሙሐመድ 6ተኛ ፋውንዴሽን በጋራ የተዘጋጀው ሀገራዊ የቁርኣን ውድድር ተጠናቀቀ።

ውድድሩ በሁለት ዘርፎች የተካሄደ ሲሆን፣ በሒፍዝ ከ1 እስከ 3ኛ ደረጃ በመውጣት ያሸነፉት የሶማሊ ክልል ተወዳዳሪዎች ሲሆኑ፣ እነርሱም፣
1ኛ. ሐሰን ፈይሰል አሕመድ
2ኛ. ኢብራሂም አብዱራህማን አብዲ
3ኛ. ደልሐ አብዱልረሺድ ዓሊ ናቸው።

በተጅዊድ
1ኛ.ሙሐመድ አደም -- ከትግራይ
2ኛ. ኢሊያስ ኑረዲን -- ከኦሮሚያ
3ኛ. ኢዘዲን ሰኢድ -- ከአማራ ክልል በማሸነፍ ከአዘጋጅ ኮሚቴው የምስክር ወረቀታቸውንና የማበረታቻ የገንዘብ ሽልማት ተቀብለዋል።

ዛሬ በስካይላይት ሆቴል በተደረገው የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር መጨረሻ ላይ፣ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ በተወካያቸው አማካኝነት የሞሮኮዉ ንጉሥ ሙሐመድ 6ተኛ ፋውንዴሽን ዋና ፀሐፊ የዶክተር ሲዲ ሙሐመድ ሪፍቂ አማካሪ በሆኑት ዑስታዝ ዑስማን ሰ ቀሊ ሑሴን ለተመራው የልዑካን ቡድን
የኢትዮጵያን ቡና በስጦታ አበርክተዋል።
•••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
ሐምሌ 6፣ 2016 ዓ.ል | ሙሐረም 7፣1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
የመጨረሻዎቹ የ1445 ዓ.ሒ. ሐጃጆች ነገ ሀገር ቤት ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
አዲስ አበባ |
የሐጅ ሥርዓታቸውን ፈጽመው ያጠናቀቁ የመጨረሻዎቹ 107 የተከበሩ የአላህ እንግዶች እሑድ ሐምሌ 7፣ 2016 ዓ.ል. (ሙሐረም 8፣ 1446 ዓ.ሒ) ንጋት ላይ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በጠቅላይ ምክር ቤቱ የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ኃላፊ ሐጂ አብዱልፈታህ ሙሐመድ ናስር፣ የሐጅ ሥርዓታቸውን ፈጽመው ያጠናቀቁ ከሐጅ ተመላሾች ከሰኔ 16፣ 2016 ዓ.ል ጀምሮ ወደ ሀገር ቤት እየተመለሱ እንደኾነ አስታውሰዋል።

የ1445 ዓ.ሒ የመጨረሻዎቹ 107 ሐጃጆች ሌሊቱን ከጅዳ  ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተነስተው ንጋት ላይ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በአልላህ ፈቃድ ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል።

"የዘመነ መስተንግዶ ለአርረሕማን እንግዶች" በሚል መሪ ቃል በጠቅላይ ምክር ቤቱ በተከፈቱ ሠላሳ የሐጅ የምዝገባ ጣቢያዎች ምዝገባቸውን ያከናወኑ 12 ሺህ ኢትዮጵያውያን በዘንድሮው ዓመት ሐጅ ለማድረግ ሳዑዲ አረቢያ ተጉዘዋል።
​•••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
ሐምሌ 7፣ 2016 ዓ.ል | ሙሐረም 8፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የታላቁን ንጉሥ አል-ነጃሺ መስጂድ በዩኔስኮ ለማስመዝገብ እየተሠራ መሆኑ ተነገረ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መቀለ |
የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት፣ የትግራይ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ፣ የመቀለ ዩኒቨርሲቲ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በጥምረት ያዘጋጁት በጥንታዊው አል-ነጃሺ መስጂድ መልሶ ግንባታ ላይ ያተኮረ ሀገር አቀፍ ኮንፈረንስ በመቀለ እየተካሄደ ነው።

የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚደንት ሸይኽ አደም አብዱልቃድር በኮንፈረንሱ ላይ፣ ንጉሥ አል ነጃሺ በነቢዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) የተመሰከረላቸው ፍትኃዊ እና በዓለም ሙስሊሞች ዘንድ ትልቅ ስፍራ ያላቸው መሪ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የትግራይ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አጽብሃ ትግራይ የአል ነጃሺ መስጂድን ጨምሮ በሺህ የሚቆጠሩ ጥንታዊ ቅርሶች የሚገኙበት ክልል እንደኾነ አስታውሰው፣ እነዚህን ቅርሶች መንከባከብ፣ ማልማትና ማስተዋወቅ የሁሉም የትግራይ ተወላጆችና ኃላፊነት ነው ብለዋል።

የአል ነጃሺ የተሃድሶና ልማት ኢኒሼቲቭ የቦርድ ሰብሳቢ የኾኑት ዶክተር አብራር ፍትዊ በበኩላቸው የአል-ነጃሺ መስጂድ የሁሉም ሕዝብ ነው ካሉ በኋላ፣ መስጂዱ ታሪካዊ በመኾኑ በዓለም ሙስሊም ማኅበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ ክብር እንዳለው ተናግረዋል።

በኮንፈረንሱ ላይ የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አመራሮች፣ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ምሁራን እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን የትግራይ ቴሌቪዥንን ዋቢ አድርጎ ሀሩን ሚድያ ዘግቧል።
••••••••••••••••••
​የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
ሐምሌ 12፣ 2016 ዓ.ል | ሙሐረም 13፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••
የዳዒዎች ሥልጠና ተጠናቀቀ።
•••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ስር ያለው የዑለማ ጉባዔ ጽ/ቤት ከአል ቡንያን ዓለምአቀፍ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የአቅም ግንባታ ሥልጠና የሰጣቸውን 105 ዳዒዎች በሰርተፊኬት አስመረቀ።

የሥልጠናው ተሳታፊዎች በዚህ ሥልጠና እስልምናን ሙስሊም ላልሆነው ማኀበረሰብ የማስተማር ክህሎት ወይም ወደ እስልምና የመጣራት ክህሎትን እንደቀሰሙ በኢትዮጵያ የአል ቡንያን ዓለምአቀፍ ዩኒቨርሲቲ አስተባባሪ የኾኑት ዑስታዝ አብዱልጀዋር ቢያ ተናግረዋል።

በሥልጠናው ላይ የተሳተፉት ዳዒዎች ከተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች የመጡና የተለያዩ ቋንቋ ተናጋሪዎች መሆናቸውንም አስተባባሪው አስታውሰዋል።

ሌላው የሥልጠናው አስተባባሪ አቶ አብዱሰላም ጫጮ በበኩላቸው በሥልጠናው ለተሳተፉት ዳዒዎች ዘመኑን የዋጀ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣ ወደ እስልምና የመጣራት ቁርኣናዊ ስነ-ምግባር፣ ከሽብርና ከግጭት የራቀ የአቃፊነት ክህሎት ማጎልበቻ ትምህርቶች እንደተሰጣቸው ተናግረዋል።

በምረቃው ስነ ሥርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት የሀገር አቀፉ የዑለማ ጉባዔ ምክትል ሰብሳቢና የፈትዋ ዐብይ ኮሚቴ ሰብሳቢው ዶክተር ጀይላን ኸድር ሥልጠናው የእስልምና እውቀታችሁን ሙስሊም ላልኾኑ ወገኖች የምታደርሱበትን ክህሎት የሚያዳብር በመሆኑ ትልቅ አቅም የሚፈጥርላችሁ ነው ብለዋል።

ዶክተር ጀይላን አክለውም፣ በሥልጠናው የተሳተፋችሁ ዳዒዎች በአይማዎች በኩል ያለውን ክፍተት የምትሞሉ እንደመኾናችሁ፣ ለዓሊሞች ክብር እየሰጣችሁ፣ ዝቅ ብላችሁ እውቀት በመጨመር የእስልምናን ጥሪ በስፋት የማሰራጨትና ትልቅ ኃላፊነት ወድቆባችኋል ብለዋል።

በኢትዮጵያ የአል ቡንያን ዓለምአቀፍ ዩኒቨርሲቲ ዋና ኃላፊ የኾኑት ዶክተር ሙሐመድ አል-ቁረይሺ ኢትዮጵያ ለዓለም ሙስሊሞች ባለውለታ መሆኗን ጠቅሰው፣ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ለሃይማኖታቸው ያላቸው ጽናት እና ለማወቅ ያላቸው ተነሳሽነት የሚያበረታታ ነው ብለዋል።

ዩኒቨርሲቲው ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጋር ያለውን ግንኙነት በማጠናከር በትብብር ለመሥራት ዝግጁ መኾኑንም ተናግረዋል።

የዑለማ ጉባዔ ጽ/ቤት ኃላፊ ሸይኽ ሙሐመድዘይን ዘኽረዲን በምረቃው ስነ ሥርዓት ላይ ሲናገሩ ከሥልጠናው ለየትኛው ዓይነት ደዕዋ ማን አቅም እንዳለው፣ አቅሙን ለየትኛው ዘርፍ መጠቀም እንደምንችል አመላክቶናል ብለዋል።

ሸይኽ ሙሐመድዘይን አክለውም፣ ገና ጀመራችሁ እንጂ ጨረሳችሁ ማለት አለመሆኑን ተረድታችሁ ለተሻለ ሥልጠና መነቃቃት አለባችሁ ካሉ በኋላ፣ ይህ ሥልጠና ምን አቅም እንዳላችሁ ብቻ ሳይኾን፣ ምን እንደጎደላችሁም አሳይቷችኋል ብለዋል።

ሥልጠናውን ወስደው ዛሬ በሰርተፊኬት የተመረቁት ዳዒዎች በምረቃው ስነ ሥርዓት ላይ በአረብኛ የተለያዩ ዝግጅቶችን አቅርበዋል።

በዚህ ሥልጠና ኢማም ቡኻሪ ኢስላሚክ አሶሴሽን ትልቅ ተባባሪ እንደነበር ከመድረኩ ተገልጿል።

በዝግጅቱ ላይ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚደንት ሐጂ ፈትሁዲን ሐጂ ዘይኑ፣ ታላላቅ ዓሊሞች እና ታዋቂ ዳዒዎች ተገኝተዋል።
****
የኢ.እ.ጉ.ጠ. ም/ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc
ኢንና ሊላሂ ወኢንና ኢለይሂ ራጅዑን

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በደቡብ ኢትዮጵያ፣ ጎፋ ዞን፣ ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በድንገተኛ የመሬት ናዳ በወገኖቻችን ላይ በደረሰው የሞት አደጋ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልጻል።

በተለይም በመጀመሪያው የመሬት ናዳ ጉዳት የደረሰባቸውን የአካባቢውን ነዋሪዎች ለመታደግና የጉዳቱን መጠን ለመቀነስ የአካባቢው ማኅበረሰብ በስፋት በመውጣት ጥረት እያደረገ በነበረበት ሰዓት በተከሰተው ሁለተኛ ዙር የመሬት ናዳ ምክንያት ተጨማሪ የዜጎች ሕይወት መጥፋቱና ከፍተኛ የንብረት ውድመት መከሰቱ ሐዘናችንን የከፋ አድርጎታል።

በዚህ የከፋ አደጋ ውስጥ፣ ኢትዮጵያዊነት አንዱ ለሌላው ችግር ፈጥኖ የመድረስና ለወንድም እህቶቹ ሕይወት እስከ መክፈል የሚደርስ መስዋዕትነት የታየበት ክስተት ኾኖ አልፏል።

በእንዲህ ዓይነት ድንገተኛ አደጋ ወቅት ሕዝባችን እርስ በርሱ የመረዳዳት ባህሉን እንደቀድሞው በማድረግ ጉዳት ከደረሰባቸው ወገኖቹ ጎን በመቆም የተለመደ የአብሮነት ባህሉን እንዲያዳብር ጠቅላይ ምክር ቤታችን በዚህ አጋጣሚ ጥሪውን ያስተላልፋል።

ምክር ቤቱ በአደጋው ቤተሰቦቻቸውንና ወዳጅ ዘመዶቻቸውን ላጡ በሙሉ ፈጣሪያችን አሏህ ጽናቱን እንዲሰጣቸው ይለምናል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት