Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
8.67K subscribers
117 photos
1 video
18 files
184 links
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
Download Telegram
ግንቦት 27፣ 2016 | ዙል ቂዳህ 27፣ 1445 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጠቅላይ ምክር ቤቱ ለሐጃጆች 2 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ መድኃኒት ከሀገር ቤት ወደ መካ አስገባ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መካ |
ጠቅላይ ምክር ቤቱ በተቋማዊ አግልግሎት ረገድ ለትውልድ የሚሻገር ተጨባጭ የለውጥ አሻራ ለመስቀመጥ ጥረት ከሚያደርግባቸው አገልግሎቶች አንዱ የሐጅ ሥርዓቱን ማዘመን መሆኑ ተነገረ።

የሐጃጆች የጤና አገልግሎት መጎልበት የዚህ እቅድ አካል መሆኑን የጠቀሱት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚደንትና የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ተጠሪ ሸይኽ አብዱልአዚዝ ሸይኽ አብዱልወሊ ናቸው።

ሸይኽ አብዱልአዚዝ ይህን የተናገሩት ጠቅላይ ምክር ቤቱ ለሐጃጆች የጤና አገልግሎት የሚውል 2 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ መደኃኒት ከሀገር ቤት ወደ መካ ሲያስገባ በተካሄደው የርክክብ ስነ ሥርዓት ላይ ነው።

መጅሊሱ ለሐጃጆች የገዛው መደኃኒት ርክክብ በመካ በተካሄደበት ስነ ሥርዓት ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሥራ አመራሮችም ተገኝተዋል።

በዚሁ ጊዜ፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዑለማ ጉባዔ ምክትል ሰብሳቢና የፈትዋ ዐብይ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶክተር ጀይላን ኸድር እና የተለያዩ ክልሎችን የሚወክሉ የዑለማ ጉባዔ አባላት የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱን ሁለንተናዊ የለውጥ እንቅስቃሴም አድንቀዋል።

ዶክተር ጀይላን ኸድር በዚሁ ጊዜ ባስተላለፉት መልዕክት መጅሊሱ ለአል-ረህማን እንግዶች በጤናው ዘርፍ እያደረገ ያለው መሻሻል ተቋሙ ለሚያገለግለው ሙስሊም ማኅበረሰብ ያለውን ክብር ከፍ የሚያደርግ ኃላፊነትን የመወጣት ምሳሌ ነው ብለዋል።

የ1445 የአል-ረህማን እንግዶች የሕክምና ቡድን መሪ ዶክተር አሚን ሙሐመድ በበኩላቸው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በታሪኩ ለሐጃጆች መዳኃኒት ገዝቶ መካ ሲያስገባ የመጀመሪያ ጊዜው መሆኑን ተናግረዋል።

መጅሊሱ ለአላህ እንግዶች በጤናው ዘርፍ በሰጠው ትኩረት የሕክምና ቡድኑ ልዑካን ቀደም ብለው ገብተው ከሳዑዲ የሐጅ ሚኒስቴር የሕክምና ክፍል ጋር የተለያዩ ፈቃዶችና ውሎችን እንዲፈጽም መደረጉን አስታውሰዋል።

ዶክተር አሚን ሙሐመድ አክለውም፣ "የንጉሥ አብዱልአዚዝ ቢን ሳዑድ ሆስፒታል የልብ ችግር ያለባቸውን ሐጃጆች ሊያክም ቃል ገብቶልናል" ብለዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅና ዑምራ ዘርፍ በወቅቱ 10,000 (አስር ሺህ) ኢትዮጵያውያን ሐጃጆች ቢኖሩም፣ በሐጅ ወቅት በሐጃጆች ሆስፒታል የታከሙት ከ18 ሺህ በላይ መኾናቸውን የሆስፒታሉ የታካሚዎች የምዝገባ ሰነድ ያሳያል።

ይህ ዳታ ኢትዮጵያውያን ሐጃጆች በትንሹም በትልቁም የጤና መታወክ ወደ ሆስፒታሉ መመላለሳቸውን የሚያሳይ ጤናማ ያልሆነ ዳታ እንደኾነ ተጠቁሟል።

የሕክምናው ቡድን መደራጀትና የመድኃኒቶች አቅርቦት መመቻቸት መጅሊስ በለውጥ ሂደቱ ለአል-ረህማን እንግዶች የሰጠውን ትልቅ ክብር የሚያሳይ ነው ተብሏል።

​•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
በጣም አስፈላጊ እና አስቸኳይ ማሳሰቢያ፣
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

ለውድ የ1445 ዓ.ል. ሐጃጆች።

ከቀደሙት ዓመታት በተለየ፣ የሳዑዲ አረቢያ የሐጅ ሚኒስቴር፣ ለ1445 ዓ.ል. ሐጃጆች ኑሱክ የተሰኘ ልዩ የመታወቂያ ካርድ ወይም ባጅ ማዘጋጀቱ ይታወቃል።

ይህን ልዩ መታወቂያ አለመያዝ ሐጃጁን ከሐጅ ለመታገድና ተይዞ ያልተፈቀደለት ሐጃጅ ተብሎ ከሀገር ሊያስባርረው ይችላል።

በመኾኑም፣ የተከበራችሁ የአሏህ እንግዶች ይህን የሐገሪቱ ሕግ በማክበር፣ የኑሱክ ልዩ የመታወቂያ ካርድዎን በማንኛውም ጊዜ እንዲይዙ እናሳስባለን።

እናመሠግናለን።

​•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
ሰኔ 6፣ 2016 ዓ.ል | ዙልሒጃ 7፣ 1445 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት በዞን አንድ የሚገኙ የአርረህማን እንግዶችን ጎበኙ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መካ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶ/ር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ እና የጠቅላይ ምክር ቤቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን በሁለት የሐጃጆች ማረፊያ (ሆቴል) ጉብኝት አደረጉ።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ መሪዎች ለጉብኝት በተገኙበት የዞን አንድ የሐጃጆች ማረፊያ (ሆቴል) የአርረህማን እንግዶችን አላህ ፈቅዶ እዚህ ለመገኘት በቅታችኋልና ለአላህ ምሥጋና ይገባዋል - አላህምዱሊላህ! ብለዋል።

ከሁሉ በላይ የአርረህማን እንግዶችን ማስደሰት፣ ተገቢውን ግልጋሎት መስጠት አላህ ዘንድ የሚያስገኘው ዳረጃ ከፍ ያለ በመኾኑ፣ ስለምናገኘው የአላህ ውዴታ ስንል በተቻለ መጠን በሐጅ ጉዞ አገልግሎት ላይ ያሉ ችግሮችን ኃላፊነት ከሰጣችሁን ጊዜ ጀምሮ በአላህ ፈቃድ ለማሻሻል ጥረት እየተደረገ መሆኑን አስታውሰዋል።

በዚህ የእንኳን ደህና መጣችሁ ዚያራ ላይ ፕሬዚደንቱ በዞን አንድ ውስጥ ለሚገኙት ከሶማሊ እና ከአፋር ክልሎች ለመጡ የአርረህማን እንግዶች መልዕክት አስተላልፈዋል።

"ከዓመቱ ቀናት በላቁት ቀናት ላይ እንገኛለን። አላህ (ሱ.ወ) ቻይ ነው። አላህ (ሱ.ወ) ሰሚ ነው። አላህ (ሱ.ወ)
የተዓምራት ሁሉ ባለቤት ነው። ያላችሁበት ቦታ 'ዱዓ' የሚሰማበት በመኾኑ፣ የወንድምና ወንድም ደም መፋሰስ እንዲቆም፣ እነርሱም የአርረህማን እንግዶች እንዲኾኑ፣ ስለ ሰላም ስትሉ አጥብቃቹህ ዱዓ ልታደርጉ ይገባል" ብለዋል

በጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት የአርረህማን እንግዶች ጉብኝት ላይ ሐጃጆች ምሥጋና እና የተለያዩ ጥያቄዎች አንስተዋል። በዋነኛነትም 'ኑሱክ' የተባለውን ልዩ የሐጃጅ መታወቂያ ካርድ አለማግኘታቸው እንዳሳሰባቸው ተናግረዋል።

'ኑሱክ' የተባለው ልዩ መታወቂያ ካርድ የሕጋዊ ሐጃጅነት ማረጋገጫ መኾኑን የሳዑዲ የሐጅ ሚኒስቴር ቢገልጽም፣ በሁሉም ሀገር ባሉ ሐጃጆች ላይ የዚህ ቢጣቃ ችግር መከሰቱን ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባልደረቦቼ ነግረውኛል ብለዋል።

ይህን ልዩ መታወቂያ ካርድ እስካሁን እርሳቸውም እንኳ እንዳላገኙ ሸይኽ ሐጂ ተናግረዋል።

ችግሩ የተንከባለለ መኾኑን እና ሐጅ በባህሪው ዉጣ ውረድ ያለው በመሆኑ በአገልግሎት አሰጣጥ ፍፁምነት አይጠበቅም ያሉት ፕሬዚደንቱ፣ ችግሮችን በጋራ እየቀረፍን ከፊታችን በሚጠብቀንን የሐጅ ሥርዓት አላህ የሚቀበለን እንዲኾን በአው ፉታ ጀምረን የአርረህማን እንግዶች በመሆናችን ደስ ሊለን ይገባል ብለዋል።

በመጨረሻም የሐጃጆች ጉብኝት ዱዓ ተደርጎ ተጠናቅቋል።
ሰኔ 7፣ 2016 ዓ.ል | ዙልሒጃ 9፣ 1445 ዓ.ሒ.
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ሙስሊሙ ማኅበረሰብ የአረፋን በዓል አቅመ ደካሞችን በመደገፍና በማሰብ እንዲያከብር የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት አሳሰቡ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

ሙስሊሙ ማኅበረሰብ የ1445 ዓ.ሒ. የዒድ አል-አድኃ (አረፋ) በዓልን ሲያከብር ካለው ላይ ለአቅመ-ደካማ ወገኖቹ እንዲያካፍል የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ አሳሰቡ።

ክቡር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ ይህን ያሳሰቡት፣ የዒድ አል-አድኃ በዓልን ምክንያት በማድረግ አስቀድሞ በተቀረፀ መልዕክታቸው ነው።

ሸይኽ ሐጂ በዚሁ መልዕክታቸው፣ በዙልሒጃ ወር የመጀመሪያዎቹ አሥር ቀናት የሚሥሠሩ መልካም ተግባራት አሏህ (ሱ.ወ.) ዘንድ በሌሎች ቀናት ከሚሥሠሩ መልካም ተግባራት በላጭ ምንዳ እንዳላቸው ከነቢያችን ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) ሐዲስ አጣቅሰው ተናግረዋል።

በሙስሊሙ ማኅበረሰብ በጉጉት ከሚጠበቁት የዙልሒጃ ወር የመጀመሪያዎቹ አሥር ቀናት ዘጠነኛዋ ቀን አል ሐጁል አረፋ የሚደረግበትና ማግሥቱ ቀን (የውመል ነሀር) የአረፋ በዓል የሚከበርበት መሆኑን ፕሬዚደንቱ አውስተዋል።

አሏህ (ሱ.ወ.) ሐጅን የወፈቃቸው የዓለም ሙስሊሞች አረፋ ላይ ሲቆሙ፣ ያልወፈቃቸው ወንድሞችና እህቶች ደግሞ በያሉበት የአረፋን ፆም በመፆም፣ ያለፉት ሁለት ዓመታት ወንጀሎቻቸው ከአሏህ (ሱ.ወ.) ምህረት የሚገኝባት ቀን መሆኗን ክቡር ሸይኽ ሐጂ የነቢያችን ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) ሐዲስን በማጣቀስ ተናግረዋል።

የአረፋ ቀን አሏህ (ሱ.ወ.) ፀጋውን የለገሳቸው ሙስሊሞች የዑድሂያ እርድ የሚያከናውኑበት መሆኑን የጠቀሱት ክቡር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም፣ እነዚህ ሙስሊሞች ከሚያርዱት እርድ ለተቸገሩ ወገኖቻቸው፣ በተለይም ለአቅመ ደካማና በተፈጥሮና በሰው ሠራሽ ችግሮች ሳቢያ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች ማካፈል ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

"እጅግ በጣም አዛኝና ርኅሩኅ የኾነው ጌታችን አሏህ (ሱ.ወ.) ይቅር ባይነትን ይወዳል" ያሉት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም፣ "ተበድሎ ይቅር ያለን ሰው፣ አሏህ (ሱ.ወ.) የሠራውን ጥፋት ይቅር የሚለው በመኾኑ፣ ሁላችንም ይቅር ልንባባል ይገባል" ብለዋል።

የዘንድሮውን ዒድ አል-አድኃ (አረፋ) ለየት የሚያደርገው የሀገራችን የኢትዮጵያ ልጆች ሀገራዊ ምክክር እያደረጉ የሚገኙበት ወቅት ላይ መሆኑን ጠቅሰው፣ ሀገራዊ ምክክሩ ለጋራ ሀገራችን ሰላማዊነት ጠቃሚ መኾኑን በመረዳት ሙስሊሙ ማኅበረሰብ በያለበት በሀገራዊ ምክክሩ ላይ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርግ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

ሀገራዊ ምክክሩ ለሙስሊሙ ኅብረተሰብ የሚኖረውን ፋይዳ በመረዳት ጠቅላይ ምክር ቤቱ የሕግ ባለሙያዎችን፣ ዓሊሞችን፣ ምሑራንን፣ ታዋቂ ግለሰቦችንና ለሀገር የሚያስቡ ሰዎችን በማሰባሰብ የሙስሊሙን ጥያቄዎች (concerns) በማደራጀት ለሚመለከተው አካል መላኩን ፕሬዚደንቱ ሸይኽ ሐጂ ተናግረዋል።

ሰላም የሁሉ ነገር መሠረት መሆኑን የተናገሩት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም፣ ሁሉም የሰላም ዘብ እንዲሆን ጥሪ አስተላልፈው፣ ለሀገራችንና ለመላው ዓለም ሙስሊሞች በዓሉ የደስታ እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል።

•••••••••••••••••••••​
​የኢ.እ.ጉ.ጠ. ም/ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | twitter.com/eiasc1
ሰኔ 11፣ 2016 ዓ.ል | ዙልሒጃ 12፣ 1445 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሰላም ዙሪያ በጋራ ለመሥራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሰላም ዙሪያ በቀጣይ አብረው ለመሥራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ።

ዛሬ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መሥሪያ ቤት የሁለቱ ተቋማት ኃላፊዎች የመግባቢያ ሰነዱን በተፈራረሙበት ወቅት የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ዋና ፀሐፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ የአፍሪካ ኩራት ከኾነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በሰላም ጉዳይ ላይ አብሮ ለመሥራት የመግባቢያ ሰነድ መፈረማቸው እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል።

በሁለቱ ተቋማት ኃላፊዎች የተፈረመዉ የመግባቢያ ሰነድ አየር መንገዱ እያከናወነ ከሚገኘው ሀገራዊ ሥራ በተጨማሪ በቀጣይ ከሃይማኖት ተቋማት ጋር በሀገራዊ ሰላም ዙሪያ የጋራ እሴቶችን በማስቀጠልና ሀገር ተረካቢ ወጣቶች ላይ
በመሥራት ታሪካዊ ኃላፊነትን ለመወጣት ያስችላል ተብሏል።

"የሃይማኖት አባቶች የኢትዮጵያ አየር መንገድ አምባሳደሮች ናቸው" ያሉት ዋና ፀሐፊው፣ 75 ዓመታትን በስኬት ያሳለፈው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቀጣይም ኢትዮጵያዊ ማንነቱን ይዞ በስኬት እንዲያስቀጥል የሃይማኖት አባቶቹ በሚችሉት ሁሉ ከጎኑ እንደሚቆሙ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው የአፍሪካ ኩራት የኾነው አየር መንገዱ ከጊዜ ወደ ጊዜ መዳረሻውን እያሰፋ መምጣቱን ጠቅሰው፣ በያዝነው 2016 ዓ.ል 2.6 ሚሊዮን የሀገር ውስጥ መንገደኞችን ማስተናገዱን ተናግረዋል።

አየር መንገዱ ከ26 ሺህ በላይ ለሚኾኑ ሰዎች የሥራ ዕድል መፍጠሩን ያወሱት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ የሥራ ዕድል ከተፈጠረላቸው ሰዎች አብዛኛዎቹ በአየር መንገዱ የነፃ ሥልጠና ተጠቃሚዎች መሆናቸውን ተናግረዋል።

አየር መንገዱ የቱሪዝም ሥራ በሀገራችን እንዲስፋፋ ደረጃውን ከጠበቀ የሆቴል አገልግሎት በተጨማሪ የውጪ ምንዛሪ ገቢን ለሀገራችን ለማምጣት የስጋ፣ የአትክልት እና ፍራፍሬ ምርቶችን ወደተለያዩ ሀገራት የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጠ መኾኑንም ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ መስፍን ተናግረዋል።
አየር መንገዱ እነዚህን ተግባራት የሚያከናውነው፣ ደከመኝ ሰለቸኝ በማይሉ ጠንካራ ሡራተኞቹ አማካኝነት መኾኑን ዋና ሥራ አስፈጻሚው ተናግረዋል።

በሁለቱ ተቋማት ከተደረገው የመግባቢያ ሰነድ የፊርማ ስነ ሥርዓት በተጨማሪ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት የበላይ ጠባቂ አባቶች ወደ ዩኒቨርሲቲ ደረጃ ያደገውን የአየር መንገዱን የምስለ በረራ ትምህርት ክፍል ጎብኝተዋል።

በዚሁ ጊዜም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ አራት ነፃ የቢዝነስ የአውሮፕላን ቲኬት አበርክቷል።

•••••••••••••••••••••••
የኢ.እ.ጉ.ጠ. ም/ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | twitter.com/eiasc1
ሰኔ 15፣ 2016 ዓ.ል | ዙልሒጃ 16፣ 1445 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ልዑካን መካ የሚገኝውን የንጉሥ አባ ጂፋር የኢትዮጵያውያን ሐጃጆች ማረፊያ ሕንፃ ጎበኙ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
በክብር ዶ/ር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የተመራ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሥራ አስፈጻሚ ቡድን፣ መካ የሚገኝውንና ለብዙ ዓመታት ኢትዮጵያውያን ሐጃጆችን ሲያገለግል የኖረውን የንጉሥ አባ ጂፋር የሐጃጆች ማረፊያ ሕንጻ ጎበኘ።

ለኢትዮጵያውያን ሐጃጆች መቀበያና ማረፊያ እንዲኾን ታስቦ በንጉሥ አባ ጂፋር ዘመን የታነፀውና የኢትዮጵያውያን ሀብት የኾነው ዘመን ተሻጋሪው ሕንጻ በዘንድሮው የሐጅ ወቅት አገልግሎት አለመስጠቱ ታውቋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ከፍተኛ የሥራ አስፈጻሚ አባላት ጉብኝት ዓላማም ታሪካዊው የኢትዮጵያውያን ሐጃጆች ማረፊያ አገልግሎት መስጠት ያቋረጠበትን መንስዔ ተረድቶ፣ በልዩ ሁኔታ ችግሩን ለመፍታት ያለመ አቅጣጫ መስጠት እንደኾነ ክቡር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ተናግረዋል።

ታሪካዊው የንጉሥ አባ ጂፋር ሕንጻ በ1445 ዓ.ሒ ሐጅ አገልግሎት ያልሰጠው፣ የሳዑዲ አረቢያ የሐጅ ሚኒስቴር የሐጃጆች ማረፊያን አስመልክቶ ያወጣውን የብቃት መስፈርት ባለማሟላቱ መኾኑ በዚሁ ጊዜ ተገልጿል።

ከብረት የተሠራው የሕንጻው የውጪ መወጣጫ ደረጃ ረጅም ዓመታት ሲያገለግል የኖረ ቢኾንም፣ የሳዑዲ አረቢያ የሐጅ ሚኒስቴር ያወጣውን የብቃት መስፈርት ባለማሟላቱ፣ ፈቃዱ ሊታደስ እንዳልቻለ በዚሁ ጊዜ ተነግሯል።

የንጉሥ አባ ጂፋር የሐጃጆች ማረፊያ ሕንጻ ታሪካዊ አሻራውን በሚያጎለብት መልኩ፣ መሟላት ያለበትን በማሟላት በሚቀጥለው ዓመት ችግሩ ተፈትቶ ለአልረህማን እንግዶች ማረፊያነት የተሻለ አገልግሎት እየሰጠ እንዲቀጥል ከወዲሁ አስፈላጊው ጥረት ሁሉ መደረግ እንዳለበት ክቡር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከሕንጻው አሥተዳደር ጋር በመኾን፣ ችግሩን ለመፍታት እንደሚሠራ ፕሬዚደንቱ ተናግረዋል።

በጉብኝት መርኃ ግብሩ ላይ የምክር ቤቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን፣ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ፀሐፊ ሸይኽ ሐሚድ ሙሳ፣ ጥሪ የተደረገላቸው የሀገር ሽማግሌዎችና የተለያዩ የክልል መጅሊስ አባላት ተገኝተዋል።

​•••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
ሰኔ 16፣ 2016 ዓ.ል | ዙልሒጃ 17 1445 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
93 በግል ከሐጅ ተመላሾች የመልስ ጉዞ መስተጓጎል ገጠማቸው።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መካ |
የ1445 ዓ.ሒ የሐጅ ሥርዓተ አምልኮን ፈጽመው ፈጥነው ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ በሳዑዲ አየር መንገድ በግል ቲኬት የቆረጡ 93 ያህል ከሐጅ ተመላሾች በመልስ ጉዟቸው ላይ መስተጓጎል እንደገጠማቸው ታወቀ፡፡

እነዚህ ሐጃጆች በመልስ ጉዟቸው መጉላላት የገጠማቸው፣ ሲገቡ ፓስፖርታቸውን የተቀበላቸው ኩባንያ በሰዓቱ ደርሶ ፓስፖርታቸውን ባለመመለሱ ሳቢያ በረራ ስላመለጣቸው መኾኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በተጨማሪም፣ ከመካ ወደ ጀዳ የሚወስዳቸው አውቶብስ ዘግይቶ መምጣት፣ የሐጃጆች በሰዓቱ ተጠቃልለው ወደ አውቶብሱ አለመግባት፣ የግል ተመላሽ ሐጃጆች የቲኬት መረጃ በሑጃጅ መስተንግዶ ሲስተም ውስጥ የሚገኝ ባለመሆኑ ያንን ከተመላሾቹ ወስዶ ለማስተካከል የወሰደው ጊዜ የተጓዦችን ጀዳ አውሮፕላን ማረፍያ የመድረሻ ሰዓት ለማዘግየት ምክንያት መኾናቸው ተጠቅሷል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የመልስ ጉዟቸው ለተስተጓጎለባቸው ከሐጅ ተመላሾች በጀዳ የመቆያ ሆቴል በመከራየት የመልስ ጉዟቸውን ለማሳለጥ አማራጭ የማፈላለግ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በመቀናጀት የሚያካሂደው የሐጃጆች የመልስ ጉዞ መርኃ ግብር፣ ሐጃጆች ከኢትዮጵያ ወደ ሳዑዲ አረቢያ (መዲና) በተሳፈሩበት ቅደም ተከተል መሠረት የሚከናወን መኾኑ ይታወቃል፡፡

ይህን የመልስ ጉዞ መርኃ ግብር እየጠበቁ መቆየትን የማይመርጡ የተወሰኑ ሐጃጆች፣ በሳዑዲ አየር መንገድ በግል ቲኬት ቆርጠው በጊዜ ለመመለስ እንደሚወስኑ ይታወቃል።

በዚህ መልኩ ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ ቲኬት የቆረጡ 93 ያህል ከሐጅ ተመላሾች ከላይ በተጠቀሱት ተደራራቢ ምክንያቶች የመልስ ጉዟቸው እንደተስተጓጎለ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ኃላፊ ሸይኽ አብዱልፈታህ ሙሐመድ ናስር ተናግረዋል፡፡

የእነዚህ ከሐጅ ተመላሾች የመልስ ጉዞ መስተጓጎል ጠቅላይ ምክር ቤቱን እንደሚያሳስበው የጠቀሱት ኃላፊው፣ ‹‹በተቻለ ፍጥነት ተለዋጭ በረራ እንዲያገኙ ጉዳዩ ከሚመለከተው አካል ጋር በመገናኘት ለችግሩ መፍትኄ በማፈላለግ ላይ ነን›› ብለዋል፡፡

የመልስ ጉዞ የቅደም ተከተል ተራን ከመጠበቅ ይልቅ ፈጥነው ለመመለስ የፈለጉ ሐጃጆች ከወትሮው በዛ ማለታቸው በአሠራራቸው ላይ ጫና እንደፈጠረ የጠቀሱት ሸይኽ አብዱልፈታህ፣ ያም ኾኖ ዘርፉ የሚመለከታቸውን አካላት በማነጋገር ለተፈጠረው ችግር መፍትኄ ለማስገኘት ጥረት እያደረገ መኾኑን ተናግረዋል፡፡

የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሥራ አስፈጻሚና የሐጅ ዐብይ ኮሚቴ አባል የኾኑት ኢንጅነር አንዋር ሙስጠፋ በበኩላቸው፣ ፈጥነው ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ በመሻት በሳዑዲ አየር መንገድ በግል ቲኬት ለቆረጡት 93 የሐጅ ተመላሾች በተለያዩ ምክንያቶች በመዘግየታቸውና ፓስፖርታቸውን የተቀበላቸው ኩባንያም በሰዓቱ ባለመድረሱ በረራ እንዳመለጣቸው ተናግረዋል፡፡

ከሐጅ ተመላሾቹ በረራ ያመለጣቸው ቢሆንም፣ ለበለጠ መጉላላት እንዳይዳረጉ መጅሊሱ በጀዳ ሆቴል ተከራይቶ ሌላ የመመለሻ አማራጭ መፍትኄ የማፈላለግ ጥረት ላይ መኾኑን ኢንጅ. አንዋር ተናግረዋል፡፡

ወቅቱ የሐጅ ተመላሽ ጫና ያለበት፣ የበረራ መደራረብና እጥረት የሚፈጠርበት በመኾኑ፣ መጅሊሱ ባሳደረው ጫና ብዙ ሰዎችን የሚይዝ ግዙፍ አውሮፕላን በመጠቀም በዕለቱ ከሚመለሱት ጋር በረራ ያመለጣቸውን ሐጃጆች ጨምሮ በማሳፈር ችግሩን ለመፍታት እየተሠራ እንደኾነ ኢንጅነር አንዋር ተናግረዋል፡፡

​•••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
ሰኔ 16፣ 2016 ዓ.ል | ዙልሒጃ 18፣ 1445 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ምክር ቤቱ 89 የግል ከሐጅ ተመላሾች ወጪያቸው ተሸፍኖ ዛሬ ለሊት ሀገራቸው እንዲገቡ አመቻቸ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መካ |
በሳዑዲ አየር መንገድ በግል ቲኬት ቆርጠው ትናንት ጉዟቸው የተስተጓጎለባቸው 90 ያህል ከሐጅ ተመላሾች ሙሉ ወጪያቸው ተሸፍኖ ዛሬ ሌሊት ወደ ሀገራቸው እንደሚገቡ ተነገረ።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሥራ አስፈጻሚና የሐጅ ዐብይ ኮሚቴ አባል የሆኑት ኢንጅነር አንዋር ሙስጠፋ በትናንትናው ዕለት ጉዟቸው የተስተጓጎለባቸውን የ90 ከሐጅ ተመላሾች የመልስ ጉዞ ለማሳካት ከሳዑዲ የሐጅ ሚኒስቴር ጋር በመነጋገር በተደረገው ጥረት 89 የሐጅ ተመላሾች ዛሬ አመሻሹን እንዲሳፈሩ ሁኔታዎች መመቻቸታቸውን ተናግረዋል።

በሐጅና ዑምራ የሲስተም ክፍል ዋና ተጠሪ የሆኑት ኢንጅነር አንዋር ሙስጠፋ አያይዘውም በግል ቲኬት ከቆረጡት 90 ከሐጅ ተመላሾች ወስጥ አንዷ በግል ምክንያት በዛሬው የሳዑዲ አየር መንገድ ተመላሾች ውስጥ አለመካተቷን ተናግረዋል።

በግል ቲኬት ቆርጠው ከበረራው ሰዓት በመዘግየታቸው ሳቢያ የትናንቱ የመልስ ጉዞ ያመለጣቸውና በመጅሊሱ ወጪ ጀዳ በሚገኝ ሆቴል ያረፉት ተመላሾች ሙሉ ወጪያቸው በሳዑዲ አረቢያ የሐጅ ሚኒስቴር ተሸፍኖ በሳዑዲ አየር መንገድ አመሻሹን ወደ ሀገራቸው ለመሳፈር ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን ለማወቅ ተችሏል።

ለችግሩ መፍትኄ የማፈላለግ ጥረቱ እንዲሳካ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅና ዑምራ ዘርፍ የሥራ ኃላፊዎች ያደረጉት ጥረት የሚመሠገን እንደሆነ ኢንጅነር አንዋር ተናግረዋል።

​​•••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
ሰኔ 19፣ 2016 ዓ.ል | ዙልሒጃ 20፣ 1445 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ከሐጅ ተመላሾች ማዑ ዘምዘም ቦሌ አይሮፕላን ማረፊያ ላይ እንደሚሰጣቸው ተነገረ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የሐጅ ሥርዓታቸውን አጠናቅቀው ሀገር ቤት ለተመለሱ ሐጃጆች ቦሌ ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፍያ ላይ ማዑ ዘምዘም እንደሚሰጣቸው ተነገረ።

የሐጅ ሥርዓትን አጠናቅቀው በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሀገር ቤት ለተመለሱ ሐጃጆች ቦሌ ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፍያ እንደደረሱ በነፍስ ወከፍ 5 ሊትር ማዑ ዘምዘም እንደሚታደላቸው በጠቅላይ ምክር ቤቱ የሐጅና ዑምራ ዘርፍ፣ የሐጃጆች አቀባበልና የማዑ ዘምዘም እደላ አስተባባሪ የኾኑት ሐጂ አብዱልፈታህ ብርሃኑ ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ምክር ቤቱ ለተከበሩት የሐጅ ተመላሾች አቀባበልና የማዑ ዘምዘም ዕደላ ኮሚቴ ማዋቀሩን የጠቀሱት

የመልስ ጉዟቸውን በኢትዮጵያ አየር መንገድ አድርገው ሀገር ቤት ለሚመለሱ ሐጃጆች በነፍስ ወከፍ የሚሰጣቸው 5 ሊትር ማዑ ዘምዘም ከተመላሾቹ ቀድሞ ቦሌ ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፍያ እንደሚደርስ አስተባባሪው ሐጂ አብዱልፈታህ ተናግረዋል።

በሳዑዲ አየር መንገድ ጉዟቸውን ያደረጉ የሐጅ ተመላሾች የነፍስ ወከፍ የማዑ ዘምዘም ድርሻቸው ጀዳ አየር መንገድ ላይ እንደሚሰጣቸው ሐጂ አብዱልፈታህ ተናግረዋል።

የተከበሩ የአርረህማን እንግዶችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ሥራን ሰኔ 18፣ 2016 ዓ.ል የጀመረው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፣ እስከ ዛሬ በተደረጉ ጉዞዎች (በኢትዮጵያና በሳዑዲ አየር መንገዶች) የዛሬውን ጨምሮ አንድ ሺህ ስምንት መቶሐጃጆችን ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ አድርጓል።
••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
ሰኔ 20፣ 2016 ዓ.ል | ዙልሒጃ 21፣ 1445 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የሐጅ ተመላሾች ኦፕሬሽን የሥራ ሂደቱን ገምግሞ የሥራ መመሪያ አወጣ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መካ |

የ1445 ዓ.ሒ የሐጅ ሥርዓትን ፈጽመው ወደ ሀገር ቤት የሚመለሱ የአርረህማን እንግዶችን የአሸኛኘት የሥራ ሂደት የሚገመግም ስብሳባ ተከናወነ።

የሐጅ ተመላሾች አሸኛኘት የሥራ ሂደት ግምገማውን የመሩት የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሥራ አስፈጻሚ፣ የሐጅ ዐብይ ኮሚቴ አባል እና የሲስተም ክፍል ዋና ተጠሪ ኢንጅነር አንዋር ሙስጠፋ፣ የአርረህማን እንግዶች የሐጅ ሥርዓታቸውን ጨርሰው ወደ ሀገር ቤት መመለስ ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬዋ ምሽት ድረስ 2 ሺህ 900 ሐጃጆች ወደ ሀገር ቤት መሸኘታቸውን ተናግረዋል።

በግመገማው ላይ የአሸኛኘት ሂደቱን በሚያሳልጡት አባላት ከተመላሾች በኩል ከሚፈቀደው የሚዛን ልክ በላይ ሻንጣን ማጨቅ፣ በሻንጣ እንዲያዝ የማይፈቀድ እቃ መያዝ፣ የፓስፖርት መጥፋት፣ የመሰናበቻ ጠዋፍን (ጠዋፈል ወዳዕ) በጊዜ አለመፈፀም፣ በሰዓት አለመገኘት ከገጠሙ ተግዳሮቶች መካከል ተጠቅሰዋል።

በሌላም በኩል የመረጃ በአግባቡና በግልፅነት ያለመድረስና መዘናጋት ያስከተለው ችግር በግምገማው ላይ ተነስቷል።

የሐጅ ተመላሾች የአሸኛኘት አገልግሎት አሰጣጡ የነበረበትን ደካማና ጠንካራ ጎኖች በመገምገም፣ ዘልማዳዊ አሠራሩን በመተው ተበታትኖ ያለውን ሥራ ወጥነትና ተመጋጋቢ በኾነ አግባብ የመፈፀም አስፈላጊነትና አፈጻፀሙ ላይ ማብራሪያ ተሰጥቶ የጋራ ግንዛቤ ተይዟል።

በሥራ ሂደቱ ላይ የመረጃ ክፍተት የአገልግሎት አሰጣጡ ዋነኛ እንቅፋት መኾኑ ታምኖበት፣ ይህን ለማረቅ የሚያስችል የሥራ መመሪያ መውጣቱ የተነገረ ሲኾን፣ ለመመሪያው ተግባራዊነት በይዘቱ ላይ የጋራ ግንዛቤ መያዝ የዚህ ግምገማ ውይይት ትልቅ ግብ መሆኑን ኢንጂነር አንዋር ተናግረዋል።

ይህ የግምገማ መድረክ መፈጠሩ ሁሉም በየዘርፉ ያሉ ችግሮችና የአሠራር ሂደት ክፍተቶችን ለማየት እንዲችል መኾኑን የጠቀሱት ኢንጂነር አንዋር፣ ዘልማዳዊ አሠራርን በመተው አሸኛኘቱን ይበልጥ ሊያቀላጥፍ የሚችለውን የአገልግሎት አሰጣጥ መመሪያ በመከተል በጋራ መትጋት የሥራ ሂደቱን ተመጋጋቢ በማድረግ የሐጅ ተመላሾች ጉዞ
ስኬታማ እንዲሆን ያስችላል ብለዋል።

የሐጅ ሥራ በባህሪው የብዙ ባለሙያዎችን ውህደትና መናበብ የሚጠይቅ በመኾኑ የአገልግሎት ሰጪዎችን ቅንነት እና ትዕግስት እንደሚጠይቅ የጠቀሱት ኢንጂነር አንዋር፣ ይህን ከተመላሽ ሐጃጆች ማግኘት በማይቻልበት ሁኔታ እንደ አገልግሎት ሰጪ ከእኛ የሚጠበቀውን በከፍተኛ ትዕግሥት እና አስተዋይነት መከወን ይኖርብናል ብለዋል።

​​•••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
ሰኔ 24፣ 2016 ዓ.ል | ዙልሒጃ 25፣ 1445 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
ኢንና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ከ1445 ዓ.ሒ. ኢትዮጵያውያን ሐጃጆች 10ሩ በሐጅ ላይ ሕይወታቸው አለፈ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መካ |

በ1445 ዓ.ሒ. ኢትዮጵያውያን ሐጃጆች ውስጥ በድምሩ 10 ሐጃጆች ሕይታቸው ማለፉን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሥራ አስፈጻሚና የሐጃጆች የሕክምና ቡድን ዋና አስተባባሪ ሸይኽ አል-መርዲ አብዱላሂ አሺቢ ተናገሩ።

አሥሩ ኢትዮጵያውያን ሐጃጆች በሙሉ በመካ፣ መስጂደል ሀረም ላይ ሶላተል ጀናዛ ተሰግዶባቸው የቀብር ሥርዓታቸው እንደተፈፀመ ሸይኽ አል-መርዲ አብዱላሂ ተናግረዋል።

የአምስቱ ሐጃጆች ሕይወት የሐጅ ሥርዓት ከመጀመሩ በፊት ማለፉን ያስታወሱት ሸይኽ አል-መርዲ የሌሎቹ ሕይወት ያለፈው በአረፋ ወቅት መኾኑን ተናግረዋል።

ከሟቾቹ መካከል በተለይ ሁለቱ እናቶች በሐጅ ሥርዓተ ክንዋኔ ወቅት ጠፍተው ከነበሩት አምስት ሰዎች መካከል መኾናቸውና 'ሚና' ላይ ሕይወታቸው ማለፉ እንደታወቀ ተነግሯል።

በሳዑዲ አረቢያ መንግሥት የሐጃጆችን ደኅንነት ጉዳይ ኃላፊነት ወስዶ የሚከታተለው ኤጀንሲ፣ ስድስቱ ሐጃጆች በድንገተኛ ህመም፣ ሁለቱ በክፍላቸው ውስጥ ሞተው የተገኙ ሲኾን፣ አንድ ሐጃጅ በመኪና አደጋ፣ አንድ በካንሰር፣ እንዲሁም ሌላ አንድ ሐጃጅ በህመም ምክንያት እንደሞቱ የሆስፒታሉን ውጤት አያይዞ ይፋዊ መረጃ ሰጥቷል።

የሐጃጆቹ የቀብር ሥርዓት የተፈፀመው በሀገሪቱ ደንብ መሠረት በሦስት ሰዓታት ውስጥ የሟች ቤተሰብ፣ የቅርብ ዘመድ አልያም ምስክር የሚኾን ጎረቤት በተገኘበት እንደኾነ ለማወቅ ተችሏል።

በዚሁ መሠረት የዘጠኙ ሟቾች ሥርዓተ ቀብር የተፈፀመው በዚሁ ደንብ መሠረት ሲኾን፣ ሚና ላይ ሞተው ከተገኙት የአንዷ እህት በተባለው ጊዜ ውስጥ መገኘት ባለመቻሏ ሕይወቷ ማለፉን የሚያረጋግጥ ሰርተፊኬት ተሰጥቷል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሥራ አስፈጻሚና የሐጃጆች የሕክምና ቡድን ዋና አስተባባሪ ሸይኽ አል መርዲ አብዱላሂ፣ የ1445 ዓ.ሒ. የአርረህማን እንግዶች ሆነው መጥተው ሞት ቢቀድማቸውም ኒያቸው ከፍ ያለ በመኾኑ፣ ሞታቸውን የሸሂድ (የሰማዕት) ደረጃ የሚያደርሱት አሉ ብለዋል።

"ሞት የማይቀር ተፈጥሯዊ ሕግ በመኾኑ፣ በእንዲህ ዓይነት ሂደት መሞት ትልቅ ፀጋ ነው" ብለዋል ሸይኽ አል መርዲ።

"ሀረም ላይ የዓለም ሙስሊም የአርረህማን እንግዶች ሆነው በመጡበት አጋጣሚ፣ ጀናዛቸው ላይ ተሰግዶ መካ ላይ መቀበር ትልቅ ፀጋ በመሆኑ፣ ቤተሰቦቻቸው ሊሶብሩ እና ሊፅናኑ ይገባል" ብለዋል።
ሰኔ 25፣ 2016 ዓ.ል | ዙልሒጃ 26 1445 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ከሐጅ ተመላሾች በሻንጣቸው ዉስጥ የተከለከሉ ቁሶችን ባለማስገባት የንብረታቸውን ደኅንነት እንዲጠብቁ ተጠየቀ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የሐጅ ሥርዓታቸውን ፈጽመው ወደ ሀገር ቤት የሚመለሱ ሐጃጆች የዘምዘም ውሃን ጨምሮ ሻንጣቸው ዉስጥ የተከለከሉ ቁሶችን ባለማስገባት የንብረቶቻቸውን ደኅንነት እንዲጠብቁ የ1445 ዓ.ሒ የሐጅና ዑምራ የሽኝት ኮሚቴ አሳሰበ።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከሰኔ 15፣ 2016 ዓ.ል ጀምሮ በግል እና በጠቅላይ ምክር ቤቱ አማካኝነት የአውሮፕላን ቲኬት የቆረጡ የ1445 ዓ.ሒ የተከበሩ የአላህ እንግዶችን ወደ ሐገር የመመለሻ መርኃ ግብር እያስፈፀሚ እንደሚገኝ የጠቀሱት የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ተጠባባቂ ሥራ አስኪያጅና የሽኝት ኮሚቴ አባል ሸይኽ ኢስሀቅ አደም የአላህ እንግዶችን የመልስ ጉዞ ለማሳለጥና የንብረቶቻቸውን ደኅንነት ለመጠበቅ የተለያዩ ሥራዎች ሲሠሩ መቆየታቸውን ተናግረዋል።

ከእነዚህ ሥራዎች አንዱ በአውሮፕላን ጉዞ ላይ በግል ሻንጣ ውስጥ መከተት የሌለባቸውን ነገሮች ለሐጃጆች በሀገር ውስጥና ከሳዑዲ የመልስ ጉዞ ከመጀመሩ በፊት የግንዛቤ ትምህርት መሰጠቱ እንደሚገኝበት ሼይኽ ኢስሐቅ ተናግረዋል።

ቁጥራቸው ትንሽ ቢኾንም፣ አንዳንድ ሐጃጆች የአውሮፕላን ጉዞ ሕግን በመተላለፍ ሻንጣቸው ዉስጥ የተከለከሉ ነገሮችን በመያዛቸው በሳዑዲ አየር መንገድ የበረራ ደኅንነት ሠራተኞች ተይዞ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ሻንጣዎቻቸው መከፈታቸውን ኃላፊው
ተናግረዋል።

በቀጣይ ወደ ሀገር ቤት ተመላሽ የተከበሩ የአላህ እንግዶች ለመልስ ጉዞ በሚያደርጉት ዝግጅት፣ ማዑ ዘምዘምን ጨምሮ ሻንጣ ውስጥ መገኘት የሌለባቸውን ነገሮች ባለመጨመር ንብረቶቻቸውን እንዲጠብቁ ያሳሰቡት ኃላፊው፣ በዚህ ምክንያት ለሚፈጠሩ ችግሮች ጠቅላይ ምክር ቤቱ ኃላፊነት እንደማይወስድ ተናግረዋል።
​​•••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1

ሰኔ 26፣ 2016 ዓ.ል | ዙልሒጃ 27፣ 1445 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••

በ2024ቱ የበድር ኢትዮጵያ ጉባኤ ላይ የሚሳተፉ የክብር እንግዶች ዳላስ ቴክሳስ መግባት ጀምረዋል።

በድር የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ድርጅት በአሜሪካን ሀገር ዳላስ ቴክሳ ለሚካሄደው የ2024 ጉባኤ ተጋባዥ የሆኑ የመጅሊስ አመራሮች በዛሬው ዕለት ቴክሳስ ገብተዋል።
.
የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር ዶክተር ሼህ ሱልጣን አማን ኤባ፣ የፌዴራል መጅሊስ ዋና ፀሀፊ ሼኽ ሀሚድ ሙሳ እንዲሁም የአዲስ አበባ መጅሊስ የምክር ቤት አባል ኡስታዝ ሱፍያን ኡስማን አሜሪካን ሀገር ዳላስ ቴክሳስ ሲገቡ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። በቀጣይ የፌዴራል መጅሊሱን ፕሬዝዳንት ጨምሮ ሌሎች ተጋባዥ የክብር እንግዶች ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ምንጭ፦ሀሩን ሚዲያ
ሰኔ 26፣ 2016 ዓ.ል | ዙልሒጃ 27፣ 1445 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
"የሃይማኖት ተቋሞቻችን ለዘላቂ ሰላማችን" በሚል መሪ ቃል የውይይት መድረክ በሸራተን አዲስ ተካሄደ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የሰላም ሚኒስቴር "የሃይማኖት ተቋሞቻችን ለዘላቂ ሰላማችን" በሚል መሪ ቃል የሃይማኖት አባቶች፣ መሪዎች፣ አስተማሪዎችና አመራሮች የተሳተፉበት ሀገር አቀፍ ኮንፈረንስ በሸራተን አዲስ ሆቴል አካሄደ።

ኮንፈረንሱ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የፕሬዚደንቱ ተወካይና የፈትዋና ምርምር ዘርፍ ተጠሪ ሼይኽ ኢድሪስ ዓሊ ሑሴን ዱዓና በአባቶች ፀሎት ተከፍቷል።

ኮንፈረንሱን በንግግር የከፈቱት የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዱዓለም፣ ሃይማኖቶች የተለያዩ አስተምህሮ ቢኖራቸውም ለሰው ዘር ሰላም የሚሠሩ መሆኑን ጠቅሰው፣ የጋራ ቤታችን ለሆነችው ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ሚኒስቴሩ ከሁሉም የሃይማኖት ተቋማት ጋር አብሮ እንደሚሠራ ተናግረዋል።

በኮንፈረንሱ ላይ በሰላም ሚኒስቴር እና በአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት የውይይት መነሻ ጽሑፎች ቀርቦ በተሳታፊዎች ውይይት ዳብሯል።

በኮንፈረንሱ ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የፕሬዚደንቱ ልዩ አማካሪ ዑስታዝ አቡበከር አሕመድ ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም የሃይማኖት አባቶች የማይተካ ሚና እንዳላቸው ጠቅሰው፣ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከሁሉም የሃይማኖት ተቋማት ጋር ተቀራርቦ በመሥራት ለሰላም ጥረቶች ዕድሎችን ሊሰጥ ይገባዋል ብለዋል።

"የሃይማኖት ተቋሞቻችን ለዘላቂ ሰላማችን" በሚል መሪ ቃል በተካሄደው በዚሁ ኮንፈረንስ ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤቶች ሥራ አስፈፃሚዎች፣ ኢማሞች፣ ዱዓቶች እና ምሁራን ተገኝተዋል።
​​•••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
ሰኔ 27 :2016 ዓ.ል | ዙልሒጃ 28:1445 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••



ፕሬዚዳንቱ የበድር ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ጉባዔ ላይ ተገኙ።

ሰኔ 27:2016 ዓ.ል (አዲስ አበባ)የኢትዮጵያ  እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የክብር  ዶክተር ሼይኽ ሐጂ  ኢብራሒም  ቱፋ የ2024 የበድር ኢትዮጵያ ጉባዔ ላይ ለመገኘት በአሜሪካዉ   በቴክሳስ ግዛት፡ ዳላስ ከተማ ፎርዝ ወርዝ አየር ማረፊያ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው።


ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል በራሳቸውና በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

"በኢስላማዊ መርሆች ላይ ፀንቶ መቆም" በሚል መሪ ቃል በቴክሳስ ሪቻርድ ሰን ሲቲ ሬናይሰስ ሆቴል የሚካሄደው ይኽ ጉባዔ ማምሻውን በይፋ ተከፍቷል።

በዓመታዊዉ የበድር ዓለም አቀፍ ጉባዔ ላይ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ፅሁፎች ቀርበው ዉይይት እንደሚያደረግባቸዉ ለማወቅ ተችልዋል።

ከሰኔ 27 -30 /2016 ዓ፡ል(ከጁላይ 4-7/2024 እ.ኤ. አ) የሚካሄደውን ይኽ ንን ጉባዔ በዳላስ የሚገኘዉ የቢላል ኮሚኒቲ ማዕከል እንዳዘጋጀዉ ሀሩን ሚዲያ ዘግቦታል፡፡


የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1

ሙሃረም 1፣ 1446 ዓ.ሒ. | ሰኔ 30፣ 2016 ዓ.ል.

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ሙስሊሙ ማኅበረሰብ በድሬደዋ አሸዋ ገበያ ንብረታቸው በእሳት አደጋ ለወደመባቸው ወገኖች የእርዳታ እጁን እንዲዘረጋ ተጠየቀ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

ሙስሊሙ ማኅበረሰብ በድሬዳዋ አሸዋ ገበያ ንብረታቸው በእሳት አደጋ ለወደመባቸው ወገኖች የእርዳታ እጁን እንዲዘረጋ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጥሪ አድርጓል።

ጥሪው የተደረገው በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የፕሬዚደንቱ ተወካይና የፈትዋና ምርምር ዘርፍ ተጠሪ ሸይኽ ኢድሪስ ዓሊ የተመራው ልዑክ በእሳት አደጋ ሳቢያ ጉዳት የደረሰበትን የድሬዳዋ አሸዋ የገበያ ማዕከል ከጎበኙ በኋላ ነው።

የእሳት አደጋው በንብረት ላይ ያስከተለው ጉዳት ከፍተኛ መኾኑን መረዳታቸውን የተናገሩት ሸይኽ ኢድሪስ፣ በጉዳቱ ዙሪያና በንብረታቸው ላይ ጉዳት ለደሰባቸው የማኅበረሰቡ አባላት የሚደረገውን ቀጣይ ድጋፍ በተመለከተ ከድሬዳዋ አሥተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሐር እና ጉዳት ከደረሰባቸው የንግዱ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

ሙስሊሙ ማኅበረሰብ በድሬዳዋ ከተማ አሥተዳደር አሸዋ ገበያ ሰልባጅ ተራ በተነሳው የእሳት አደጋ ንብረታቸው የወደመባቸው ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም በተከፈቱ አራት የእርዳታ ማሰባሰቢያ ዝግ የባንክ ሒሳብ ቁጥሮች ድጋፍ እንዲያደርግ ሸይኽ ኢድሪስ ጥሪ አቅርበዋል።

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዓሊሞች ጉባዔ ምክትል ሰብሳቢ የሆኑት ዶክተር ጀይላን ኸድር በእሳት አደጋ ንብረታቸውን ያጡ ወገኖችን አሏህ ሶብር እንዲሰጣቸው፣ መላው ሙስሊሙ ማኅበረሰብም የበኩሉን አስተዋፅዖ እንዲያበረክት መልዕክታቸው አስተላልፈዋል።

ሰኔ 25፣ 2016 ዓ.ል የእሳት ቃጠሎ በደረሰበት አሸዋ ገበያ ትናንት በተካሄደው ጉብኝት ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የዓሊሞች ጉባዔ ምክትል ሰብሳቢ ዶክተር ጀይላን ኸድር፣ የዳዕዋ ዘርፍ ተጠሪ ሼይኽ አሚን ኢብሮ እና የድሬዳዋ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ተገኝተዋል።


​​•••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
ሐምሌ 3፣ 2016 ዓ.ል | ሙሐረም 4፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ሞሮኳዊው የቁርኣን ውድድር ዳኛ ዑስማን ሰ ቀሊ ሑሴን አዲስ አበባ ገቡ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የሞሮኮዉ ንጉሥ ሙሐመድ 6ተኛ ፋውንዴሽን ዋና ፀሐፊ የዶክተር ሲዲ ሙሐመድ ሪፍቂ አማካሪ በሆኑት ዑስታዝ ዑስማን ሰ ቀሊ ሑሴን የተመራ የልዑካን ቡድን የቁርኣን ውድድር ለመዳኘት አዲስ አበባ ገባ።

የልዑካን ቡድኑ ቦሌ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የትምህርትና ማህበራዊ አገልግሎቶ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶክተር አብደላ ከድር እንዲሁም ሌሎች የምክር ቤቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውለታል።

በዑስታዝ ዑስማን ሰ ቀሊ ሑሴን የተመራው የልዑካን ቡድን አዲስ አበባ የገባው፣ የፊታችን ጁምዓ ሐምሌ 5፣ 2016 ዓ.ል. (ሙሐረም 6፣ 1446 ዓ.ሒ) በስካይላይት ሆቴል የሚካሄደውን ሀገር አቀፍ የቁርኣን ዉድድርን ከሀገራችን ዓሊሞች ጋር በጋራ ለመዳኘት ነው።  

ዛሬ አዲስ አበባ የገቡት ዑስታዝ ዑስማን ሰ ቀሊ በጠቅላይ ምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች በተደረገላቸው አቀባበል መደሰታቸውን ተናግረዋል።

የፊታችን ጁምዓ የሚጠናቀቀው ሀገራዊ የቁርኣን ዉድድር በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዓሊሞች ጉባዔ ጽ/ቤት የተዘጋጀ ሲኾን፣ ለአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር የደረሱት ሐፊዞች በክልልና የከተማ አስተዳደር የእስልምና ጉዳይ ከፍተኛ ምክር ቤቶች በተዘጋጁ ውድድሮች ተሳትፈው ያሸነፉ መኾናቸውን ዶክተር አብደላ ተናግረዋል።

በስካይላይት ሆቴል የሚካሄደው ውድድር በቀጣይ ኢትዮጵያን ወክለው በዓለም አቀፍ የቁርኣን ውድድር መድረክ የሚሳተፉ ተወዳዳሪዎች የሚለዩበት መሆኑ ዉድድሩን በጉጉት የሚጠበቅ እንደሚያደርገው ዶክተር አብደላ ተናግረዋል።

ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ በቁርኣን ዉድድር የሀገራችንን ስም በዓለምአቀፍ ደረጃ ያስጠሩ ወጣቶች እንዳሉ የጠቀሱት ዶክተር አብደላ በዚህ ዉድድር አሸናፊ የሚኾኑ ሐፊዞችም በዓለምአቀፍ የቁርኣን ውድድር መድረክ ሀገራቸውን ወክለው እንደሚወዳደሩ ተናግረዋል።

በቦሌ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በተደረገው የአቀባበል ስነ ሥርዓት ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የዉጭ ግንኙነት ኅላፊ ፕሮፌሰር አደም ካሚል ተገኝተዋል።
•••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1

ሐምሌ 4፣ 2016 ዓ.ል | ሙሐረም 5፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ፕሬዚደንቱ የሞሮኮዉ ንጉሥ ሙሐመድ 6ተኛ ፋውንዴሽን የልዑካን ቡድን አባላትን ተቀብለው አነጋገሩ።
..............................................
አዲስ አበባ |
ፕሬዚደንቱ በሞሮኮ አምባሳደር ነዚሃ አሎዩ የተመራውን የሞሮኮዉ ንጉሥ ሙሐመድ 6ተኛ ፋውንዴሽን የልዑካን ቡድን አባላት ተቀብለው አነጋገሩ።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ በኢትዮጵያ የሞሮኮ አምባሳደር ነዚሃ አሎ የተመራውን የሞሮኮዉ ንጉሥ ሙሐመድ 6ተኛ ፋውንዴሽን   የልዑካን ቡድን አባላት በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።
በዚሁ ጊዜ ክቡር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም እንግዳ ተቀባይ ወደኾሆነችው ሀገራችን ኢትዮጵያ በመምጣችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
በኢትዮጵያ የሞሮኮ አምባሳደር ክብርት ነዚሃ አሎዩ በበኩላቸው በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለተደረገላቸው መልካም አቀባበል በራሳቸውና በልዑካን ቡድኑ አባላት ስም ምሥጋና አቅርበዋል፡፡
አምባሳደሯ በሞሮኮ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን የቆየ ግንኙነት አውስተው፣ በቀጣይ ጊዜያት ኤምባሲያቸው ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ጋር በጋራ ጉዳዮች ላይ አብሮ ለመሥራት ፍላጎት እንዳለው ተናግረዋል።
በውይይቱ ላይ የተገኙት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሐጂ ከማል ሐሩን ምክር ቤቱ እንደ አዲስ ከተዋቀረ ወዲህ ሙስሊሙን ማኅበረሰብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያዩ የአጭር እና የረጅም ጊዜ ፕሮጀክቶች ቀርፆ እየሠራ መሆኑን ለቡድኑ አስረድተዋል።
የሞሮኮዉ ንጉሥ ሙሐመድ 6ተኛ ፋውንዴሽን ዋና ፀሐፊ የዶክተር ሲዲ ሙሐመድ ሪፍቂ አማካሪ የሆኑት ዑስታዝ ዑስማን ሰ ቀሊ ሑሴን ከጠቅላይ ምክር ቤቱ የዓሊሞች ጉባዔ  ጽሕፈት ቤት ጋር በመተባበር በነገው ዕለት /ጁምዓ/ በስካይላይት ሆቴል ለሚደረገው ሀገራዊ የቁርኣን ውድድር ስኬት ጠቅላይ ምክር  ቤቱን አመስግነዋል።
የሞሮኮዉ ንጉሥ ሙሐመድ 6ተኛ ፋውንዴሽን በአፍሪካ፣ በእስያና በአውሮፓ በሚገኙ 70 ማዕከላት እየሠራ እንደሚገኝ የተናገሩት ዑስማን ሰቀሊ ሁሴን፣ በቀጣይ ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ጋር በጋራ ለመሥራት ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ለልዑካን ቡድኑ በሸራተን አዲስ ሆቴል የምሳ ግብዣ አድርገዋል።
ዛሬ በጠቅላይ ምክር ቤቱ በተደረገው ውይይት ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱና የዓሊሞች ጉባዔ ጽሕፈት ቤት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1

ሐምሌ 4፣ 2016 ዓ.ል. | ሙሐረም 6፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እና በድር ኢትዮጵያ በጋራ ለመሥራት ተስማሙ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እና ከ23 ዓመታት በፊት በሰሜን አሜሪካ የተቋቋመው በድር ኢትዮጵያ ዓለምአቀፍ የሙስሊሞች ድርጅት በጋራ ለመሥራት ተስማሙ።

ስምምነቱን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ ሸይኽ ሐሚድ ሙሳ እና የበድር ኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ፕሬዚደንት አቶ አሕመድ ወርቁ ተፈራርመዋል።

በድር ኢትዮጵያ ላለፉት ሁለት አሠርት ዓመታት በሀገር ቤት ከሚገኙ የተለያዩ ተቋሞች ጋር በመተባበር የሙስሊሙን ችግር ለመቅረፍ በታለሙ የተለያዩ ተግባራት ላይ የበኩሉን አስተዋጽዖ ሲያበረክት ቆይቷል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እና በድር ኢትዮጵያ ዓለምአቀፍ የሙስሊሞች ድርጅት የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ይበልጥ በማጠናከር፣
-- በውጪ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን በሀገር ቤቱ የሙስሊም ኅብረተሰብ ልማትና ዕድገት ላይ የበኩላቸውን አስተዋጽዖ የሚያደርጉበትን ሁኔታ ማመቻቸት፣

-- በዲያስፖራውና በሀገር ቤቱ ማኅበረሰብ መካከል ያለውን ትስስር በማጠናከር የእውቀት ሽግግርን ለማጎልበት የድጋፍ ሥራዎችን፣ መድረሳዎችን፣ መስጂዶችን እንዲሁም ሌሎች የተለያዩ የልማትና ሃይማኖታዊ እውቀቶችን ለማስፋፋትና ለማጠናከር በጋራ ለመስራት፣

-- በመላው ዓለም በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች መካከል እስላማዊ አንድነት እንዲጎለብት በጋራ ለመሥራት፣

በድር-ኢትዮጵያ ዓለምአቀፍ የሙስሊሞች ድርጅት እንደ ተቋም በሀገር ቤት የትምህርት፣ የጤናና ሌሎች ማኅበራዊ ጠቀሜታ ያላቸው ፕሮጀክቶችን መሥራት የሚችልባቸውን ሁኔታዎች ማመቻቸት በጋራ ስምምነቱ ከተካተቱ ዐበይት ፍሬ ነገሮች ውስጥ መኾናቸውን ከሐሩን ሚዲያ የተገኘው ዘገባ አመልክቷል።

•••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1