Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
11.4K subscribers
5.05K photos
76 videos
20 files
858 links
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
Download Telegram
ጥር 2፣ 2017 ዓ.ል | ረጀብ 11፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
..........................

የምክር ቤቱ ልዑክ ከቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን ጎበኘ።
.............................

በአፈር ክልል በተደጋጋሚ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የካልዋሌና አጎራባች ቀበሌዎች የአደጋ ተጋላጭ መሆናቸው ተገለፀ።

በክልሉ የገቢረሱ ዞን አስተዳደሪ አቶ ዓሊ ለኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤቱ ልዑክ በሰጡት ማብራሪያ የመሬት መንቀጥቀጡ የአደጋ ስጋት በፈጠረባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ኮማድ ፖስት ታውጇል ብለዋል።

አስተዳዳሪው እንዳሉት ከአዋሽ ፈታሌ የ4 ቀበሌ እና ከድሉቻ ደግሞ የ2 ቀበሌ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ለቀው አስቦሌ ቦራ እና ዳኢዶ በሚባል አካባቢ ሰፍረዋል። መንግስት ለተፈናቃዮች ድጋፍ እያደረገ እንደሆነ የገፁት አስተዳዳሪው ከችግሩ ስፋት አንፃር የሁሉንም ኢትዮጵያዊ ርብርብ ይጠይቃል ብለዋል።

የጥናት ባለሙያዎች ከፈንጋሌ እስከ ደፋን ባሉ አካባቢዎች የሚኖሩ ወገኖች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ቢጠይቁም አሁንም በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰዎች አካባቢውን ለቀው ለመውጣት ፈቃደኛ ሊሆኑ እንዳልቻሉም አስተዳዳሪው ጠቅሰዋል።

በጠቅላይ ምክር ቤቱ የሥራ አስፈጻሚ አባልና የፈትዋና ምርምር ዘርፍ ተጠሪ በሆኑት ሼይኽ ኢድሪስ አሊ ሑሴን የተመራው የምክር ቤቱ ልዑክ በመሬት መንቀጥቀጡ ሳቢያ በነዋሪዎች ላይ የደረሰውን ጉዳት ተመልክቷል።

ሼይኽ ኢድሪስ አሊ ሑሴን የመሬት መንቀጥቀጡ በዜጎች ላይ ያደረሰውን ችግር አስከፊነት በአካል ተገኝተን መመልከታችን በችግሩ ስፋት ልክ መፍትሄ ለማፈላለግ ይረዳናል ብለዋል።

የችግሩን ሰለባዎች መጎብኘታችን ለህዝብ ያለንን አጋርነት ያሳያል ያሉት ሼይኽ ኢድሪስ የተከሰተው የተፈጥሮ አደጋ ሰዎች በተውበት ወደ አላህ እንዲመለሱ የሚያስገነዝብ ነውም ብለዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ልዑክ በመሬት መንቀጥቀጡ ከፍተኛ ወድመት የደረሰበትን የከሰም ስኳር ፋብሪካም የጎበኘ ሲሆን ጉዳቱን የፋብሪካው የሲቪል ስራዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ አሰመላሽ ፍሳሃዬ ለልዑካኑ ገለፃ አድረገዋል።

ኃላፊው በገለፃቸው በአካባቢው በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ከ20 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን ገልፀው በፋብሪካው ላይ የኢሌትሪክና መካኒካል ብልሽቶችን ሳይጨምር ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ውድመት ደርሷል ብለዋል።

የአፋር ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት እና የክልሉ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝደንት ሸይህ ሙሳ ሙሐመድ ዑመር በበኩላቸው በስኳር ፋብሪካው አካባቢ በነበረ መስጅድ ላይ ከደረሰው ውድመት በስተቀር እስከ አሁን በሰዎች ላይ የደረሰ የሞት እና የአካል ጉዳት የለም ብለዋል።

የኢትዮጵያን እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ልዑክ ከተፈናዮች ጋር የጁምዓ ሰላትን የሰገደ ሲሆን የጠቅላይ ምከር ቤቱ የመስጂድና አውቃፍ ዘርፍ ተጠሪ ሸይኽ መሐመድ አህመድ አውስዮ እና የምክር ቤቱ የሕዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍ ተጠሪ ሸይህ ሁሴን ሀሰን በተፈጥሮ አደጋው ምክንያት ከቀያቸው ተፈናቅለው ለከፋ ማህበራዊ ቀውስ ለተጋለጡ ወገኖች የአብሮነት መልዕት አስተላልፈዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ የልዑክ ቡድኑ በቀጣይ ምልዓተ ህዝቡን በማስተባበር አስፈላጊ የሆኑ ሰብዓዊ እርዳታዎችን እንደሚያደርግም ቃል ገብቷል።
ጥር 3፣ 2017 ዓ.ል | ረጀብ 11፣ 1446 ዓ.ሒ

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ                  
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝደንት የክብር ዶክተር ሸይህ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋ፣ ምክትል ፕሬዝደንት ሸይህ አብዱልአዚዝ ሸይህ አብዱልወሌ እንዲሁም የምክር ቤቱ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በጠቅላይ ምክር ቤቱና በባንኮች መካከል ያለውን የስራ ግንኙነት ሊያጠናክሩ በሚችሉ አሰራሮች ዙሪያ በትላንትናው ዕለት ከተለያዩ ባንክ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል።