ጥር 1፣ 2017 ዓ.ል | ረጀብ 10፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጠቅላይ ምክር ቤቱ ለክልል የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ኃላፊዎችና የምዝገባ ጣቢያ ባለሙያዎች ስልጠና እየሰጠ ነው
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለክልል የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ኃላፊዎች እና የምዝገባ ጣቢያ ባለሙያዎች የ2017 ዓ.ል ሐጅ መስተንግዶን አስመልክቶ የክህሎትና የግንዛቤ ማስጨበጫ የሁለት ቀናት ስልጠና በጠቅላይ ምክር ቤቱ መሠብሠቢያ አዳራሽ እየሰጠ ይገኛል።
ስልጠናውን በንግግር ያስጀመሩት የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሴቶችና ወጣቶች ዘርፍ ተጠሪ እንዲሁም የሀጅ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ሼይኽ አብዱልሐሚድ አህመድ እንደተናገሩት ጠቅላይ ምክር ቤቱ ለኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች በብቸኝነት የሐጅ ሥነ ስርዓት አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም በመሆኑ ግልፅ ርዕይና ተጠያቂነት ያለው አሰራር ዘርግቶ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
ባለፈዉ ዓመት በአዲስ አበባ ከተማ በተደራጀው አንድ ማዕከል ብቻ ስልጠና መሰጠቱን ያስታወሱት ሸይህ አብዱልሐሚድ በዚህ አመት ግን አዲስ አበባን ጨምሮ አማካኝ በሆኑ ሦሥት ከተሞች ስልጠናው ተዘጋጅቷል ብለዋል።
ሸይህ አብዱልሐሚድ በድሬዳዋ ከተማ ለስድስት፣ በሐዋሳ ከተማ ደግሞ ለአስር የምዝገባ ጣቢያ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተመሳሳይ የክህሎትና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እንደተሰጠ ጠቅሰው ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ለአስራ አራት የምዝገባ ጣቢያዎች የሚሰጠው ስልጠና የመጨረሻ እንደሆመ ገልፀዋል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሀጅና ዑምራ ዘርፍ ኃላፊ ሐጅ አብዱልፈታህ ሙሐመድ በበኩላቸው የ1445 ዓ.ሒ (2016 ዓ.ል) የሐጅ መስተንግዶ ከቀደምት አመታት የተሻለ ቢሆንም ከአላህ እንግዶች ፍላጎት አንፃር ግን ክፍተቶች እንደነበሩበት አልሸሸጉም።
በጠቅላይ ምክር ቤቱ የሚሰጠውን የሃጅ ጉዞ አገልግሎት በሑጃጆች ላይ እርካታን እንዲፈጥር ለማስቻል በምዝገባ ስርዓቱ ላይ አዳዲስ አሰራሮች በሲስተም ባለሙያዎች ዳብረው ወደ ስራ ለመግባት በዝግጅት ላይ መሆናቸውንም የዘርፉ ኃላፊ አስረድተዋል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ሐጂ ከማል ሐሩን በበኩላቸው ምክር ቤቱ የህዝበ ሙስሊሙን ጥያቄዎች በጥናት ላይ ተመስርቶ ለመመለስ እየሰራ እንደሆነ ገልፀዋል።
ጠቅላይ ምክር ቤቱ ባለፈው ዓመት በተከናወነው የሐጅ ጉዞ አገልግሎት አሰጣት ላይ የነበሩ ክፍተቶችን በመለየት የማስተካከያ እርምጃ እየወሰደ መሆኑንም ዋና ስራ አስኪያጁ አንስተዋል።
የሑጃጁን መብትና ግዴታ በግልፅ ለይቶ የሚያስቀምጥ ደንብ መዘጋጀቱን የተናገሩት ሀጅ ከማል ሀሩን በቀጣይም ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት ለመስጠት ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከወዲሁ አቅዶ እየሰራ ነው ብለዋል።
በ1445 ዓ.ሒ/2016 ዓ.ል ተግባራዊ የተደረገው የሁጃጆች የአንድ ለአርባ አምስት አደረጃጀት ፋይዳ በሐጅ አብዱልቃድር ሁሴን፤ የሐጅ ምዝገባ ክንውን ሪፓርትና የምዝገባ ጣቢያ ሠራተኞች ማንዋል ደግሞ በሐጅና ዑምራ ዘርፍ ኦፕሬሽን ማናጀር ሼይኽ ኢስሐቅ አደም ቀርቦ በሰላጣኞች እንዲዳብር ተደርጓል።
••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc13

Telegram
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
ጥር 2፣ 2017 ዓ.ል | ረጀብ 10፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ምክትል ፕሬዝደንቱ የ1446 ዓ.ሒ የሐጅና ዑምራ ምዝገባ መርሐ ግብር በቅርብ ቀናት ለሕዝቡ ይፋ እንደሚደረግ ገለፁ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝደንትና የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ተጠሪ ሼይኽ አብዱልአዚዝ ሼይኽ አብዱልወሊ የዘንድሮ አመት የሐጅና ዑምራ ምዝገባ መርሐ ግብር በቅርብ ቀን ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግ ተናገሩ።
ሼይኽ አብዱልአዚዝ ሼይኽ አብዱልወሊ ይሄንን የተናገሩት የ2017 ዓ.ል (1446 ዓ.ሒ ) ለክልል ሐጅና ዑምራ ኃላፊዎችና የምዝገባ ጣቢያ ባለሙያዎች ለሁለት ቀናት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና መጠናቀቁን ተከትሎ ነው።
ምክትል ፕሬዝደንቱ አክለውም የዚህ ዓመት የሐጅ ጉዞ ካለፉት ዓመታት የተሻለ ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲሰጥ በየደረጃው በሚገኙ የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ተጠሪዎችና የምዝገባ ጣቢያ ኃላፊዎች ከፍተኛ ኃላፊነት አለባቸው ብለዋል።
የ2017 ዓ.ል (1446 ዓ.ሒ) የሐጅ ምዝገባ መርሀ ግብርን ጠቅላይ ምክር ቤቱ በቅርብ ቀን ን ይፋ እንደሚያደርግም ምክትል ፕሬዝደንቱ አክለዋል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሀጅና ዑምራ ዘርፍ ኃላፊ ሐጅ አብዱልፈታህ ሙሐመድ በበኩላቸው በአዲስ አበባ ከተማ የተሰጠው የሁጃጆች ምዝገባ ስልጠና በሐዋሳና በድሬደዋ ከተማም እንደተሰጠ አስታውሰው
ከዚህ በፊት ያካበቱትን ልምድ በስልጠና ካገኙት ክህሎትና ግንዛቤ ተጠቅመው ለሀጅ ተመዝጋቢዎች አገልግሎት ሊሰጡ ይገባል ብለዋል።
የክልል ሐጅና ዑምራ ዘርፍ ኃላፊዎች እና የምዝገባ ጣቢያ ባለሙያዎች በቀጣይ ወደተግባር ስራ ሲገቡ በስራቸው ላይ ለሚገጥሟቸው ችግሮች ፈጣን እገዛና ምላሽ የሚሰጡ የባለሙያዎች ቡድን መቋቋሙን ተናግረዋል።
ለህዝበ ሙስሊሙ የተሻለ አገልግሎት በመስጠት ኢስላማዊ ኃላፊነት መወጣት ከሁሉም ሰልጣኞች እንደሚጠበቅም ሐጅ አብዱልፈታህ ተናግረዋል።
ትላንት ሐሙስ በጠቅላይ ምክር ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ የተጀመረው የክልል ሐጅና ዑምራ ዘርፍ እና ኃላፊዎች የምዝገባ ጣቢያ ባለሙያዎች ስልጠና በዛሬው ዕለት የተጠናቀቀ ሲሆን ሰልጣኞች ከስልጠናው ያገኙትን ክህሎትና ግንዛቤ ተግባራዊ በማድረግ የተሻለ አገልግሎት እንደሚሰጡ ለዝግጅት ክፍላችን ገልፀዋል።