ታሕሣሥ 28፣ 2017 ዓ.ል | ረጀብ 6፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيم
#የአፋር እስልምናን ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በአክሱም ሙስሊም ማኀበረሰብ ላይ የሚፈጸመውን የእምነትና የሰብአዊ ጥሰት በፅናት እናቃወማለን ሲል መግለጫ አወጣ የመግለጫው ሙሉ ቃል ከላይ ይመልከቱ።

ታሕሣሥ 30፣ 2017 ዓ.ል | ረጀብ 10፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
በእቅድ ዝግጅት እና ሪፖርት አቀራረብ የተሰጠው ስልጠና ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ተቋማዊ አሰራሩን ለማዘመን የሚያደርገው ጥረት እንዲሳካ የሰራተኛውን አቅም የሚያጎለብቱ የተለያዩ ሰልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል።
የዚሁ አካል የሆነውና ትኩረቱን በዕቅድ ዝግጅትና ሪፖርት አቀራረብ ዙሪያ አድርጎ ለሶስት ተከታታይ ቀናት
በኢትዬጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት የስትራቴጅክ ማኔጅመንት የሰው ሀብት ስራ አስፈፃሚና የስልጠና ባለሙያ በሆኑት አቶ አብዱልኻሊቅ ረሺድ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና በዛሬው ዕለት ተጠናቋል።
ስልጠናውን በስኬት ላጠናቀቁ የተቋሙ የዘርፍ ሀላፊዎች፣ ዳይሬክቶሬቶችና የየክልሎች የመጅሊስ የስራ ሀላፊዎች የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል።
የምስክር ወረቀቱን ለሰልጣኞች ያበረከቱት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ሥራ አሰኪያጅ ሀጂ ከማል ሀሩን በጠቅላይ ምክር ቤቱና በተዋረድ ባሉ አደረጃጀቶች ያለውን አሰራር ተቋማዊና ዘመናዊ ለማድረግ የአቅም ግንባታ ሥልጠና ትልቅ መሳሪያ ነው ብለዋል።
ዋና ስራ አስኪያጁ አክለውም ሰልጣኞች ከስልጠናው የቀሰሙትን እውቀትና ክህሎት በአግባቡ ተግባራዊ በማድረግና ሌሎችን በማሰልጠን ለተቋማዊ ግንባታው ስኬት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ሊወጡ ይገባልም ብለዋል።

ጥር 1፣ 2017 ዓ.ል | ረጀብ 11፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝደንት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የልማት ኤጀንሲ ዋና መስሪያ ቤት ግንባታን አስጀመሩ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የልማት ኤጀንሲ ዋና መስሪያ ቤት ግንባታን ያስጀመሩት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝደት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ የልማት ኤጀንሲው የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና የልማት ክንፍ እንደሚሆን ገልፀው የማኀበረሰቡን ችግር ከመቅረፍ ባሸገር የምክር ቤቱ የኢኮኖሚ መሰረት ይሆናልም ብለዋል።
የክብር ዶክተር ሸይኽ ሀጂ ኢብራሂም አክለውም ግንባታው በተያዘለት ጊዜ ተጠናቆ የታለመለትን አገልግሎት ለመስጠት ብቁ እንድታደርጉት ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በለውጥ እንቅስቃሴው የሙስሊሞች የልማት ፍላጎት ከማሟላት አንፃር ያሉበትን ክፍተቶች የልማት ኤጀንሲው እንደሚሞላም ተመላክቷል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ሀጅ ከማል ሀሩን በግንባታ ማስጀመሪያ ዝግጅቱ ላይ እንደተናገሩት ጠቅላይ ምክር ቤቱ እራሱን ማስተዳደርና ለህዝበ ሙስሊሙ ተገቢውን አገልግሎት መስጠት አቅቶት እንደቆየ አስታውሰው በተሰሩ ተከታታይ ስራዎች ነባር ችግሮችን በመፍታት ውጤት ማስመዝገብ መጀመሩን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የልማት ኤጀንሲን እውን አድርጎ የምክር ቤቱ ዋነኛ የልማት ክንፍ አድርጎ ወደ ስራ ለማስገባትም መጠነ ሰፊ ስራዎች እንደተሰሩ ዋና ስራ አስኪያጁ አብራርተዋል።
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የልማት ኤጀንሲ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ጁደዲን ሰይድ በበኩላቸው በልማት ኤጀንሲው ዋና መስሪያ ቤት ግንባታ ማስጀመሪያ ላይ ለተገኙት ለጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝደንት እና ለሉዑካን ቡድናቸው የእንኳን ደህና መጣቹህ መልዕክት አስተላልፈው የልማት ኤጀንሲው እውን እንዲሆን የአመራሩ ፈጣን ውሳኔ አሰጣጥ ድርሻው ላቅ ያለ ነው ብለዋል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ድጋፍ ካልተለየን የልማት ኤጀንሲው ሃይማኖታችን በሚያዘው መሰረት እንደ ሀገር የማህበረሰቡን ችግር ለመቅረፍ በሚያስችል ሁኔታ በትጋትና በታማኝነት እንሰራለን ብለዋል።
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የልማት ኤጀንሲ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አህመድ ሁሴን የልማት ኤጀንሲው ሪፎርም እውን አንዲሆን በቅርበትና በትጋት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የልማት ኤጀንሲ ዋና መስሪያ ቤት ፕሮጀክት ከዲዛይን እስከ ግንባታ ያለውን ሂደት የሚያሳይ ገለፃ በምክር ቤቱ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ባለሙያ ኢንጅነር ሰኢድ ዲልተታ ተብራርቷል።
ፕሮጀክቱ በአራት ወራት እንደሚጠናቀቅም በመድረኩ ላይ ተገልፇል።
••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc13

Telegram
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት