Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
11.4K subscribers
5.01K photos
76 videos
20 files
855 links
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
Download Telegram
ታሕሣሥ 28፣ 2017 ዓ.ል |  ረጀብ 6፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ                  
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
"ጠቅላይ ምክር ቤቱ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ጠንክሮ እየሠራ ነው።" -- ሐጂ ከማል ሐሩን
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለሠራተኞቹ ተከታታይ የአቅም ግንባታ ሥልጠና በመስጠት በበጀት ዓመቱ በተቋሙ የተያዘውን እቅድ ለማሳካት ተግቶ እየሠራ መሆኑን ዋና ሥራ አስኪያጁ ሐጂ ከማል ሐሩን ተናገሩ።

ሐጂ ከማል ይህን የተናገሩት ዛሬ በጠቅላይ ምክር ቤቱ  የስብሰባ አዳራሽ የተጀመረውንና ለሦስት ቀናት የሚቆየውን የእቅድ ዝግጅት፣ ክትትል፣ ግምገማና ግብረ መልስ ሥልጠና በንግግር በከፈቱበት ወቅት ነው።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ የሠራተኞቹንና የክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤቶችን አቅም ለማሳደግ የተለያዩ የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎችን እየሰጠ መሆኑን ዋና ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል።

ተቋሙ የአጭርና የረጅም ጊዜ እቅድ አውጥቶ እየተንቀሳቀሰ እንደኾነ የተናገሩት ዋና ሥራ አስኪያጁ፣  ሠልጣኞች በሥልጠና ያገኙትን ዕውቀት ወደ ተግባር በመቀየር የተቋሙን ለውጥ ማሳለጥ ይኖርባቸዋል ብለዋል።

በሥልጠና የዳበረ የሰው ኃይል የተቋሙን እቅድ በውጤት ያሳካል ያሉት ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ ሠልጣኞች ከሥልጠናው የሚያገኙትን እውቀት ወደ ሥራ መቀየር እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት የስትራቴጂክ ማኔጅመንት የሰው ሀብት ሥራ አስፈጻሚ፣ የሥልጠና ባለሙያ፣ ተመራማሪና አማካሪ የሆኑት አቶ አብዱልኻሊቅ ረሺድ ለአንድ ተቋም ውጤታማነት የእቅድ ዝግጅት፣ ክትትል፣ ግምገማ እና ግብረ-መልስ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

ሥልጠናው በንድፈ-ሐሳብ እና በተግባር  የታገዘ እንደሚኾን የተናገሩት አሠልጣኙ፣ ሠልጣኞች በሥልጠና ያገኙትን ዕድል ወደ ሥራ በመቀየር ወጤት ማስመዝገብ ይጠበቅባችዋል ብለዋል።

ዛሬ በጠቅላይ ምክር ቤቱ በተጀመረው የእቅድ ዝግጅት፣ ክትትል፣ ግምገማ እና ግብረ መልስ ሥልጠና ላይ የክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ተወካዮች፣ እንዲሁም የጠቅላይ ምክር ቤቱ የተለያዩ የሥራ ክፍል ኃላፊዎች እየተሳተፉበት ይገኛሉ።
••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc13
ታሕሣሥ 28፣ 2017 ዓ.ል | ረጀብ 6፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيم

#የአፋር እስልምናን ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በአክሱም ሙስሊም ማኀበረሰብ ላይ የሚፈጸመውን የእምነትና የሰብአዊ ጥሰት በፅናት እናቃወማለን ሲል መግለጫ አወጣ የመግለጫው ሙሉ ቃል ከላይ ይመልከቱ።
ታሕሣሥ 30፣ 2017 ዓ.ል | ረጀብ 10፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
በእቅድ ዝግጅት እና ሪፖርት አቀራረብ የተሰጠው ስልጠና ተጠናቀቀ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

አዲስ አበባ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ተቋማዊ አሰራሩን ለማዘመን የሚያደርገው ጥረት እንዲሳካ የሰራተኛውን አቅም የሚያጎለብቱ የተለያዩ ሰልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል።

የዚሁ አካል የሆነውና ትኩረቱን በዕቅድ ዝግጅትና ሪፖርት አቀራረብ ዙሪያ አድርጎ ለሶስት ተከታታይ ቀናት
በኢትዬጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት የስትራቴጅክ ማኔጅመንት የሰው ሀብት ስራ አስፈፃሚና የስልጠና ባለሙያ በሆኑት አቶ አብዱልኻሊቅ ረሺድ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና በዛሬው ዕለት ተጠናቋል።

ስልጠናውን በስኬት ላጠናቀቁ የተቋሙ የዘርፍ ሀላፊዎች፣ ዳይሬክቶሬቶችና የየክልሎች የመጅሊስ የስራ ሀላፊዎች የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል።

የምስክር ወረቀቱን ለሰልጣኞች ያበረከቱት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ሥራ አሰኪያጅ ሀጂ ከማል ሀሩን በጠቅላይ ምክር ቤቱና በተዋረድ ባሉ አደረጃጀቶች ያለውን አሰራር ተቋማዊና ዘመናዊ ለማድረግ የአቅም ግንባታ ሥልጠና ትልቅ መሳሪያ ነው ብለዋል።

ዋና ስራ አስኪያጁ አክለውም ሰልጣኞች ከስልጠናው የቀሰሙትን እውቀትና ክህሎት በአግባቡ ተግባራዊ በማድረግና ሌሎችን በማሰልጠን ለተቋማዊ ግንባታው ስኬት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ሊወጡ ይገባልም ብለዋል።