Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
11.4K subscribers
5.01K photos
76 videos
20 files
855 links
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
Download Telegram
ታሕሣሥ 27፣ 2017 ዓ.ል |  ረጀብ 5፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيم

#የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እስልምን ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በአክሱም ሙስሊም ማኀበረሰብ ላይ የሚፈጸመውን የእምነትና የሰብአዊ ጥሰት በፅናት በመቃወም ከትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጎን እንደሚሰለፍ መግለጫ አውጥቷል ።
የመግለጫው ሙሉ ቃል ከላይ ይመልከቱ
ታሕሣሥ 27፣ 2017 ዓ.ል | ረጀብ 5፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ክቡር ፕሬዚደንቱ "ለሕዝበ ሙስሊሙ እና ለአገር የሚሠሩ ማኅበራት ሊበራከቱ ይገባል" አሉ።

• የሙስሊም ባለሙያዎች ማኅበር መሥራች ጠቅላላ ጉባዔ አካሄደ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ በሙስሊሙ ማኅበረሰብ ውስጥ ለሕዝበ ሙስሊሙ እና ከፍ ሲልም ለአገር የሚሠሩ ማኅበራት ሊበራከቱ ይገባል አሉ።

ክቡር ፕሬዚደንቱ ይህን ያሉት በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ስር ካለው 'የተቋማትና ማኅበራት አስተዳደር' ሕጋዊ ፈቃድ የወሰደው የሙስሊም ባለሙያዎች ማኅበር በዛሬው ዕለት የምሥረታ ጠቅላላ ጉባዔውን በኤልያናሞል ያካሄደበትን መርኃግብር ሲከፍቱ ባደረጉት ንግግር ነው።

በማኅበሩ የምሥረታ ጉባዔ ላይ የተገኙት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ፣ አዲሱ አመራር ወደ ኃላፊነት የመጣው ሠርቶ ለማሠራት መኾኑን ጠቅሰው፣ "ከማኅበሩ ጋራ በመተባበር ለአገር እና ለማኅበረሰቡ ጠቀሜታ ባላቸው ጉዳዮች ላይ አብረን በመሥራት ትውልዳዊ ኃላፊነታችንን እንወጣለን" ብለዋል።

ክቡር ፕሬዚደንቱ አክለውም፣ "ሥራችን ኃላፊነት ያለበት፣ ከኩራት የራቀ እና የዑለማ ይሁንታ ያለው እንዲሆን አደራ!" ብለዋል።

የሙስሊም ባለሙያዎች ማኅበር ምሁራዊ መሠረት ያለውና በተለያዩ ዘርፍ የሚገኙ ሙስሊም ባለሙያዎችን ያሰባሰበ ተቋም መሆኑ ከመድረኩ ተነግሯል።

ማኀበሩ ተጠናክሮ ማኅበረሰባዊ አገልግሎቱን እንዲያሰፋ የሙስሊሙ ማኀበረሰብ ድጋፍ እንዳይለየው ጥሪ አቅርቧል።

በማኅበሩ የምሥረታ እና የመጀመሪያ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚደንት ሸይኽ ሡልጣን አማን እና የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ፕሬዚደንት ዑስታዝ ሐይደር ከድር መልዕክት ያስተላለፉ ሲኾን፣ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ሥራ አሰኪያጅ ሐጂ ከማል ሀሩን፣ የሥራ አመራር አባላት እና ዑስታዝ አህመዲን ጀበልን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው በርካታ ምሁራን ታድመዋል።
ታሕሣሥ 28፣ 2017 ዓ.ል |  ረጀብ 6፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ                  
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
"ጠቅላይ ምክር ቤቱ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ጠንክሮ እየሠራ ነው።" -- ሐጂ ከማል ሐሩን
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለሠራተኞቹ ተከታታይ የአቅም ግንባታ ሥልጠና በመስጠት በበጀት ዓመቱ በተቋሙ የተያዘውን እቅድ ለማሳካት ተግቶ እየሠራ መሆኑን ዋና ሥራ አስኪያጁ ሐጂ ከማል ሐሩን ተናገሩ።

ሐጂ ከማል ይህን የተናገሩት ዛሬ በጠቅላይ ምክር ቤቱ  የስብሰባ አዳራሽ የተጀመረውንና ለሦስት ቀናት የሚቆየውን የእቅድ ዝግጅት፣ ክትትል፣ ግምገማና ግብረ መልስ ሥልጠና በንግግር በከፈቱበት ወቅት ነው።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ የሠራተኞቹንና የክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤቶችን አቅም ለማሳደግ የተለያዩ የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎችን እየሰጠ መሆኑን ዋና ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል።

ተቋሙ የአጭርና የረጅም ጊዜ እቅድ አውጥቶ እየተንቀሳቀሰ እንደኾነ የተናገሩት ዋና ሥራ አስኪያጁ፣  ሠልጣኞች በሥልጠና ያገኙትን ዕውቀት ወደ ተግባር በመቀየር የተቋሙን ለውጥ ማሳለጥ ይኖርባቸዋል ብለዋል።

በሥልጠና የዳበረ የሰው ኃይል የተቋሙን እቅድ በውጤት ያሳካል ያሉት ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ ሠልጣኞች ከሥልጠናው የሚያገኙትን እውቀት ወደ ሥራ መቀየር እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት የስትራቴጂክ ማኔጅመንት የሰው ሀብት ሥራ አስፈጻሚ፣ የሥልጠና ባለሙያ፣ ተመራማሪና አማካሪ የሆኑት አቶ አብዱልኻሊቅ ረሺድ ለአንድ ተቋም ውጤታማነት የእቅድ ዝግጅት፣ ክትትል፣ ግምገማ እና ግብረ-መልስ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

ሥልጠናው በንድፈ-ሐሳብ እና በተግባር  የታገዘ እንደሚኾን የተናገሩት አሠልጣኙ፣ ሠልጣኞች በሥልጠና ያገኙትን ዕድል ወደ ሥራ በመቀየር ወጤት ማስመዝገብ ይጠበቅባችዋል ብለዋል።

ዛሬ በጠቅላይ ምክር ቤቱ በተጀመረው የእቅድ ዝግጅት፣ ክትትል፣ ግምገማ እና ግብረ መልስ ሥልጠና ላይ የክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ተወካዮች፣ እንዲሁም የጠቅላይ ምክር ቤቱ የተለያዩ የሥራ ክፍል ኃላፊዎች እየተሳተፉበት ይገኛሉ።
••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc13
ታሕሣሥ 28፣ 2017 ዓ.ል | ረጀብ 6፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيم

#የአፋር እስልምናን ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በአክሱም ሙስሊም ማኀበረሰብ ላይ የሚፈጸመውን የእምነትና የሰብአዊ ጥሰት በፅናት እናቃወማለን ሲል መግለጫ አወጣ የመግለጫው ሙሉ ቃል ከላይ ይመልከቱ።