ታሕሣሥ 27፣ 2017 ዓ.ል | ረጀብ 5፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የሕዝበ ሙስሊሙ የዘመናዊ ትምህርት ተሳትፎ የሚገኝበት ደረጃ አሳሳቢ መኾኑ ተነገረ።

አዲስ አበባ |
የአገራችን ሕዝበ ሙስሊም የዘመናዊ ትምህርት ተሳትፎ የሚገኝበት ደረጃ አሳሳቢ መኾኑን አንድ የትምህርት ባለሙያ ተናገሩ።
የትምህርት ባለሙያው አብዱ አባ ጊቤ (ዶ/ር) ይህን የተናገሩት በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የትምህርትና ማኀበራዊ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት "የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የትምህርት ተሳትፎ" በሚል ርዕስ ለሁለት ቀናት ባዘጋጀው የምክክር መድረክ ላይ ነው።
በምክክር መድረኩ ላይ "የአገራችን ዘመናዊ ትምህርት ያለበት ደረጃ" በሚል ርዕስ ጥናታዊ ጽሑፍ ያቀረቡት
የትምህርትና የሥራ አመራር አማካሪው ዶ/ር አብዱ አባ ጊቤ
የአገራችን ትምህርት ሃይማኖታዊ፣ አገር በቀል እና ዘመናዊ ተብሎ እንደሚፈረጅ ጠቅሰው፣ "በአገራችን የሙስሊሙ ኅብረተሰብ የዘመናዊ ትምህርት ተሳትፎ በጥናት መታወቅ ይኖርበታል" ሲሉ ተናግረዋል።
የእስልምና እውቀት ሰፊ እና ሁለገብ እንደኾነ ያወሱት ጥናት አቅራቢው፣ ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ከስነ-ምግባራዊ ከፍታ ባሻገር የሳይንስ እውቀትና ቴክኖሎጂን በመማርና አቅሙን በማሳደግ ራሱን፣ ኅብረተሰቡን እና አገሩን መቀየር እንደሚጠበቅበት ተናግረዋል።
በአገራችን በንጉሣዊው አገዛዝ ዘመን ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ዘመናዊ ትምህርት ተምሮ ለአገሩ በጎ አስተዋጽዖ እንዳያበረክት ስልታዊ ጫና ይደረግበት እንደነበር ያስታወሱት ዶ/ር አብዱ፣ በኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት የሃይማኖት እኩልነት በመረጋገጡ ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ለትምህርት ዘርፉ ዕድገት የበኩሉን አስተዋጽዖ እንዲያበረክት ምቹ ሁኔታ ተፈጥሮለታል ብለዋል።
ዶ/ር አብዱ ባቀረቡት ጥናት መነሻነት ከመድረኩ ተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎች የቀረቡ ሲኾን፣ ጽሑፍ አቅራቢው ለጥያቄዎቹ ምላሽ ሰጥተዋል።
የምክክር መድረኩ ተሳታፊዎች "በአገራችን የሕዝበ ሙስሊሙ የትምህርት ተሳትፎ በምን ደረጃ ላይ ነው?" እና "ተሳትፎውን ከፍ ለማድረግ ቀጣዩ አቅጣጫ ምን ይሁን?" በሚሉ ርዕሶች ላይ በቡድኖች ተከፍለው ያደረጓቸውን ውይይቶች ውጤት በተወካዮቻቸው አማካይነት አቅርበዋል።
በምክክር መድረኩ መዝጊያ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ሥራ አሰኪያጅ ሐጂ ከማል ሀሩን ባደረጉት የማጠቃለያ ንግግር፣ ጠቅላይ ምክር ቤቱ እንደ ተቋም ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ዐበይት ሥራዎች መስሊሙ ማኅበረሰብ በትምህርቱ ዘርፍ አገራዊ ሚናው ከፍ እንዲል የአመለካከት ለውጥ እንዲመጣ ጥረት ማድረግ መኾኑን ተናግረዋል።
"ባለፈው ሁነት ላይ ቁጭትና ለቅሶ አያስፈልግም። የግንዛቤ እጥረት፣ የክትትል ክፍተት እና የመደራጀት ማነስ ለትምህርት ትኩረት በመስጠት የሚለወጥ በመኾኑ፣ ክፍተቱን ለመሙላት ጠቅላይ ምክር ቤቱ ቀጣይና ተከታታይ ሥራዎችን ይሠራል" ብለዋል።
ዋና ሥራ አስኪያጁ አክለውም፣ የትምህርት ጉዳይ የጋራ ጉዳያችን በመኾኑ በዘርፉ ላይ ተጋግዘን የሙስሊሙን የትምህርት ተሳትፎ በማሳደግ ለፍሬ ለማብቃት መንገዱን ጀምረነዋል። ኑ አግዙን፤ በራችን ክፍት ነው" ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
የምክክር መድረኩ በመጨረሻም ባለ 12 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቅቋል።
የአቋም መግለጫውን ሙሉ ቃል ከዚህ በታች አያይዘናል።