ታሕሣሥ 25፣ 2017 ዓ.ል | ረጀብ 2፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيم
#ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት
ኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ
ምክር ቤት የአክሱም ሙስሊም ማህበረሰብ መብቶች ሳይሸራረፋ እንዲከበር መግለጫ አወጣ !
በመግለጫቸው በሃይማኖት ግዴታ የሆነውን ሂጃብ ተማሪዎችን አውልቁ በማለት የጭለማ ዘመን ድርጊት የፈጸመውን ግለሰብ ህጋዊ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድ መንግስት እንጠይቃለን ብለዋል።
የመግለጫው ሙሉ ቃል

ታሕሣሥ 26፣ 2017 ዓ.ል | ረጀብ 3፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيم
አዲስ አበባ |
ፕሬዚደንቱ ሕዝበ ሙስሊሙ ለትምህርት ከፍተኛ ትኩረት እንዲሰጥ አሳሰቡ
"ልጆቻችንን አላስተማርንም፤ አሁን ያገኘነውን ዕድል ተጠቅመን ጠንክረን በቁጭት ልንጠቀምበት ይገባል!" ሲሉ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት ተናገሩ።
ፕሬዚደንቱ ይህን የተናገሩት፣ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የትምህርትና ማኀበራዊ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት "የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የትምህርት ተሳትፎ" በሚል ርዕስ ባዘጋጀው የምክክር መድረክ ላይ ነው።
የክብር ዶክተር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር በኢትዮጵያ ከትምህርት አጀማመር ታሪክ አንስቶ ሙስሊሞች መዋቅራዊ በኾነ መልኩ ከትምህርቱ ዓለም የተገለሉ እንደነበረ አስታውሰዋል።
"ሴት ልጆቻችን ዲናቸውን እንደጠበቁ ይማራሉ፤ ሕግና ሕግን መሠረት አድርገን ሕገ-ወጥ ድርጊቶች ሕጋዊ መፍትኄ እንዲያገኙ የሚመለከታቸውን አካላት በሮች እያንኳኳን ነው" ብለዋል።
ፕሬዚደንቱ አያይዘውም መስሊሞች የሁሉም ነገር መነሻ እውቀት መሆኑን ሳይዘነጉ፣ ያገኙትን ዕድል ተጠቅመው በቁጭት ልጆቻቸውን ሊያስተምሩ ይገባል" ብለዋል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እና የትምህርትና ማኅበራዊ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ተጠሪ ኢንጂነር አንዋር ሙስጠፋ፣ ትምህርት ማኅበረሰባዊም ሆነ ሀገራዊ ፈይዳው የላቀ እንደኾነ ጠቅሰው፣ ዳይሬክቶሬቱ የትምህርት ዘርፍ መመሪያ አጸድቆ እየሠራ መሆኑን እና የዛሬው የምክክር መድረክ የዚሁ አካል መሆኑን ተናግረዋል።
ለሁለት ቀናት በሚቆየው በዚህ መድረክ ላይ ሁለት ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት እየተደረገባቸው ይገኛል።
"የትምህርት ምንነት እና ትምህርት ለሀገር ዕድገት ያለው ፋይዳ" በሚል ርዕስ ጽሑፍ ያቀረቡት አቶ ባህሩ ሽኩር፣ 'የትምህርት ምንነትን'፣ 'የትምህርት ታሪካዊ እድገት'ን፣ 'የትምህርት አይነቶች'ን እና 'ትምህርት ያለውን ፋይዳ' በጽሑፋቸው ዳስሰዋል።
በትምህርት ዙሪያ የረጅም ጊዜ ተሳትፎ ያላቸውና በእስላማዊ የምርምር ማዕከል የቦርድ አባል የሆኑት ኢንጅነር ቢንመሊክ አብዶ "ትምህርት በእስልምና ዕይታ" በሚል ርዕስ ትምህርትና ዕወቀት በእስልምና ያለውን ቦታ የተመለከተ ጽንሰ ሐሳባዊ ማብራሪያ አቅርበዋል።
የመድረኩ አወያይ ወይዘሮ ዘቢባ መልኪ የፓናል ውይይት ተሳታፊዎች በቡድን ተከፍለው በቀረቡላቸው ጥያቄዎች ላይ ተወያይተው ለቀጣዩ ቀን ሪፖርት እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።
መድረኩ ነገ እሑድ ሕዳር 27/2017 በሀገራችን የሕዝበ ሙስሊሙ የትምህርት ተሳትፎ በምን ደረጃ ላይ ነው? በሚለው እና መሰል የመወያያ ሪፖርቶችን በመስማት እንደሚቀጥል ተነግሯል።
••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc13

Telegram
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት