ታሕሣሥ 17፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ሳኒ 25፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ፕሬዚደንቱ በኢትዮጵያ የኳታር አምባሳደር ሳዓድ ሙባረክ ሳዓድ ጋር ተወያዩ።

አዲስ አበባ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ በኢትዮጵያ የኳታር አምባሳደር ሳዓድ ሙባረክ ሳዓድ አል ጃፋሊ አል ናኢሚን ጋር ተወያዩ።
አዲስ አበባ በሚገኘው የኳታር ኤምባሲ በመገኘት ከአምባሳደሩ ጋር ውይይት ያደረጉት ክቡር ፕሬዚደንቱ ሁለቱ አገራት በሚያደርጓቸው የልማት ግንኙነቶችና በጋራ ሊሠሯቸው የሚችሏቸው ሥራዎችን አጠናክረው በሚቀጥሉበት መንገድ ላይ መወያየታቸው ተነግሯል።
አምባሳደር ሳዓድ ሙባረክ ሳዓድ አል ጃፋሊ አል ናኢሚን በበኩላቸው ኤምባሲው ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ጋር የሚሠራቸውን የልማት ሥራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
በጠቅላይ ምክር ቤቱ የበላይ ጠባቂነት በዘይድ ኢብኑ ሳቢት የቁርኣን ማኅበር አስተባባሪነት በመጪው ጥር 25፣ 2017 ዓ.ል. በአዲስ አበባ ስታዲየም በሚካሄደው ሁለተኛው ዓለምአቀፍ የቁርኣንና የአዛን ውድድር ላይ የኳታር ተወዳዳሪዎች እንደሚሳተፉ አምባሳደሩ ተናግረዋል።
የኳታር ሕዝብ በርካታ የቅዱስ ቁርኣን ቅጂዎችን ለጠቅላይ ምክር ቤቱ በስጦታ (በወቅፍ) ለመስጠት ወደ አገር ዉስጥ ለማስገባት ሂደት ላይ መሆኑን አምባሳደሩ ተናግረዋል።
•••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1

Telegram
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
ታሕሣሥ 17፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ሳኒ 25፣1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የነጃሺ እስላማዊ ማዕከል ፕሮጀክት የሾሪንግ ቁፋሮና ግንባታን ለማስጀመር የውል ስምምነት ተፈራረሙ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በአዲስ አበባ፣ አፍሪካ ሕብረት አቅራቢያ የሚያስገነባው የነጃሺ እስላማዊ ማዕከል ፕሮጀክትን ለማስጀመር የሾሪንግ ቁፋሮና ግንባታ ከሚያካሂደው ኩባንያ ጋር ዛሬ የውል ስምምነት ፈጸመ።
ጠቅላይ ምክር ቤቱ የውል ስምምነት የፈፀመው ከአንከር ፋውንዴሽን ስፔሻላይዝድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት ጋር ነው።
ስምምነቱን በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በኩል ዋና ሥራ አስኪያጁ ሐጂ ከማል ሐሩን፣ በአንከር ፋውንዴሽን ስፔሻላይዝድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ በኩል ደግሞ የድርጅቱ ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ አቶ ኤርሚያስ ተሾመ ፈርመዋል።
በዚህ የፕሮጀክቱ ምዕራፍ የሚካሄደው የሾሪንግ ቁፋሮና ግንባታ ሥራ የአፈር መናድንና በድንበር ላይ የሚገኙ ሕንጻዎችን መሠረት ከመናድ ለመከላከል ያለመ መኾኑን ከባለሙያዎች ገለጻ ለማወቅ ተችሏል።
የጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ በተገኙበት በተካሄደው የፊርማ ስነ ሥርዓት ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብዱልሃዲ ሙሐመድ ሥራውን የሚያካሂደውን ኩባንያ ለመምረጥ ስለተካሄደው ጨረታ ሂደት ገለጻ አድርገዋል።
የነጃሺ መስጂድና እስላማዊ ማዕከል ግንባታ ፕሮጀክት ዐብይ ኮሚቴ የወከላቸው የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት በመረጣ ሂደቱ ላይ የአሸናፊው ኩባንያ የሥራ አፈጸጸም ብቃትና አቅም እንደተመዘነ እና ኩባንያው ውሉ በተፈረመ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሥራውን በመጀመር በአፋጣኝ ሊያጠናቅቅ ከመግባባት ላይ መደረሱን ለፕሬዚደንቱ አስረድተዋል።
በዚህ ሥራ ዘርፍ ቀደምትና የረጅም ጊዜ የካበተ ልምድ ያለው የአንከር ፋውንዴሽን ስፔሻላይዝድ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ ሥራ አስኪያጅ አቶ ኤርሚያስ ተሾመ ኩባንያው የሕዝብ ሀብት የኾነውን የነጃሺ መስጂድና እስላማዊ ማዕከል ፕሮጀክትን የሾሪንግ ሥራ ለማካሄድ ዕድል በማግኘቱ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል።
ኩባንያቸው በውሉ መሠረት ሥራውን በታማኝነት እና በጥራት
ሠርቶ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ እንደሚያስረክብም አቶ ኤርሚያስ ተናግረዋል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ በዚሁ ጊዜ የንጉሥ ነጃሺ መስጂድ እና እስላማዊ ማዕከል ፕሮጀክት እንደ ሀገርም እንደ ሙስሊም ማኀበረሰብም ትልቅ ታሪክ በመኾኑ፣ "ኩባንያችሁ በዚህ ታሪካዊ ሥራ ላይ አሻራውን ለማሳረፍ በመብቃቱ እንኳን ደስ ያላችሁ" ብለዋል።
የዚህን ፕሮጀክት ስኬትና አገልግሎት ሕዝበ-ሙስሊሙ በጉጉት እንደሚጠብቀው የጠቀሱት ክቡር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ፣ ኩባንያው ሥራውን በአጭር ጊዜና በጥራት ሠርቶ እንዲያጠናቅቅ ከእኛ የሚጠበቀውን ሁሉ እናደርጋለን ብለዋል።

ታሕሣሥ 19፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ሳኒ 27፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ኸይራት የአካል ጉዳተኞች እስላማዊ ማኅበር ጉባዔውን አካሄደ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
ኸይራት የአካል ጉዳተኞች እስላማዊ ማኅበር 2ኛ መደበኛ ጉባዔውን ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የማኀበራዊ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር አካሄደ።
በጠቅላይ ምክር ቤቱ አዳራሽ በተካሄደው ጉባዔ መክፈቻ ላይ የተገኙት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ፀሐፊ ሸይኽ ሐሚድ ሙሳ የአካል ጉዳተኛ ኾነው በእስልምና ታሪክ ውስጥ ትልልቅ ቦታ የተሰጣቸው ሙስሊሞችን ታሪክ አውግተዋል።
ኸይራት የሙስሊም የአካል ጉዳተኞ ማኅበር ከተመሠረተ ጀምሮ ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ጋር ተቀራርቦ እየሠራ መሆኑን ሸይኽ ሐሚድ ተናግረዋል።
ሸይኽ ሐሚድ አክለውም ጠቅላይ ምክር ቤቱ ለሁሉም ተደራሽ እና "ከፊሎቻችሁ ለከፊሉ ረዳቶች ናችሁ" የሚለው ቁርኣናዊ እሴት መገለጫም በመኾኑ፣ ተቋሙ በሚችለው አቅም ማኅበሩን ያግዛል ብለዋል።
በጉባዔው ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የማኀበራዊ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አልዩ ሰዒድ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ወደ ሪፎሮም ከገባ ጀምሮ ሕዝበ-ሙስሊሙን አሳታፊና ተጠቃሚ ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ተግባራት እያከናወነ መኾኑን ተናግረዋል።
በሀገራችን በሚሊዮን የሚቆጠሩ አካል ጉዳተኛ ሙስሊሞች መንፈሣዊ ሕይወታቸውና እስላማዊ አኗኗራቸው ተገቢውን ትኩረት እንዲያገኝ ኸይራት የሙስሊም የአካል ጉዳተኞች ማኅበርን የመሰሉ ተቋማትን መደገፍና ማጠናከር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
አቶ አልዩ ሰዒድ የሙስሊም አካል ጉዳተኞችን ሁለንተናዊ ችግር ለመቅረፍ የሁላችንም ድጋፍ እና የግንዛቤ ለውጥ ያስፈልጋል ሲሉ ጥሪ አድርገዋል።
የኸይራት የሙስሊም አካል ጉዳተኞች ማኀበር ፕሬዚደንት አቶ ሡልጣን ኢሰሙ፣ የማኅበሩን የሥራ አንቅስቃሴ ሪፖርት እና የ2017 እቅድ ለጉባዔተኛውና ለባለድርሻ አካላት አቅርበዋል።
አቶ ሡልጣን በሪፖርታቸው ማኀበሩ ሁሉንአቀፍ የአካል ጉዳተኞች ማኅበር እንደመሆኑ፣ የተለያዩ የአካል ጉዳተኞችን የሚወክል መሆኑን አስታውሰዋል።
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ስር የተቋቋመው ማኀበሩ 3 ሺህ 500 አባላት አሉት።
በኸይራት የአካል ጉዳተኞች እስላማዊ ማኀበር መደበኛ ጉባዔ ላይ የተሳተፉ የማኅበሩ አባላት በቀረበው ሪፖርትና እቅድ ዙርያ አስተያየትና ጥያቄዎች አቅርበዋል።
ጠቅላይ ምክር ቤቱ በመዋቅሩ ውስጥ የአካል ጉዳተኛ ሙስሊሞችን ጉዳይ የሚከታተል ራሱን የቻለ ዳይሬክቶሬት ሊኖረው ይገባል የሚል ሐሳብም ከተሳታፊዎቹ በአጽንዖት ተነስቷል።
••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc13