Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
11.4K subscribers
5.16K photos
76 videos
20 files
866 links
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
Download Telegram
ታህሳስ  8፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ሳኒ 16፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ             
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ፕሬዚደንቱ የሃይማኖት መሪዎች የአቅም ግንባታ ዐውደጥናት መድረክ ላይ ለመሳተፍ ሞምባሳ ገቡ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ረቡእ በኬኒያዋ ከተማ ሞምባሳ በሚጀመረው የሃይማኖት መሪዎች የአቅም ግንባታ ዐውደጥናት መድረክ ላይ ለመሳተፍ ኬኒያ ገቡ።

ክቡር ፕሬዚደንቱ በዐውደጥናቱ ላይ የሚሳተፉት የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን (IGAD) ባቀረበላቸው ግብዣ መሠረት ሲኾን፣ በዛሬው ዕለት ዐውደ ጥናቱ በሚካሄድባት የወደብ ከተማ ሞምባሳ ገብተዋል።

ነገ ታሕሣሥ 9፣ 2017 ዓ.ል የሚጀምረው "የሃይማኖት  መሪዎች የአቅም ግንባታ ዐውደጥናት" መድረክ በቀጠናው ሰላምና በሰላም አብሮ የመኖር አጀንዳዎች ላይ ውይይት ያደርጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ለማወቅ ተችሏል።

ኢጋድ እ.ኤ. አቆጣጠር በ1986 በኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ጂቡቲ እና ዩጋንዳ የተመሠረተ ክፍለ-አህጉራዊ (ቀጠናዊ) ተቋም ሲኾን፣ ዋና ጽሕፈት ቤቱ በጂቡቲ ይገኛል።

ከቀጠናው ሀገራት ኤርትራ እና ደቡብ ሱዳን ዘግየት ብለው ድርጅቱን ተቀላቅለዋል።
•••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
ታህሳስ  9፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ሳኒ 15፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ             
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የምክክር ባሕልን በማዳበር ልዩነቶችን የመፍታት  ልምድን ማሳደግ እንደሚገባ ፕሬዚደንቱ  ተናገሩ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

በኬንያ፣ሞምባሳ ዛሬ በተጀመረው  "የሃይማኖት መሪዎች የአቅም ግንባታ ዐውደጥናት" ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ ንግግር አደረጉ።

ክቡር ፕሬዚደንቱ በንግግራቸው፣  ከ1440 ዓመታት በፊት እስልምና ወደ ኢትዮጵያ በገባበት ጊዜ በሐበሻው ንጉሥ አስሐመተል ነጃሺ እና ወደ ሐበሻ በስደት የመጡት የነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ.) ባልደረቦች መሪ በነበረው ታላቁ ሶሃባ ጃዕፈር ቢን አቡ ጧሊብ መካከል እምነትን አስመልክቶ የተካሄደው ውይይት እና መተማመን የመቻቻል አብነት እንደኾነ አውስተዋል።

ስለኾነም የውይይት ባህልን በማዳበር  ልዩነቶችን የመፍታት አቅምን ማሳደግ እንደሚገባ ተናግረዋል።

የምሥራቅ አፍሪካ በይነ-መንግሥታት የልማት ድርጅት (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) መድረኩን በንግግር ሲከፍቱ ባደረጉት ንግግር፣ በምስራቅ አፍሪካ የተቀሰቀሱ ግጭቶች በፈጠሩት የሰላም እጦት ምክንያት  በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ሞትና መፈናቀል እንደገጠማቸው የሱዳንና የሶማሊያ ሀኔታን በማሳያነት አቅርበዋል።

በአገራችን ኢትዮጵያ እንዲህ ዓይነቱ የሰላም እጦት ስር እንዳይሰድድ የሃይማኖት አባቶች ስለ ሰላም ከመቼውም ጊዜ በበለጠ መሥራት እንደሚጠበቅባቸው ዋና ፀሐፊው ተናግረዋል።
በኬኒያዋ የወደብ ከተማ ሞምባሳ የተጀመረው "የሃይማኖት መሪዎች የአቅም ግንባታ ዐውደጥናት" ዛሬን ጨምሮ ለቀጣይ ሦስት ቀናት እንደሚካሄድ ከስፍራው የሚገኘው  ቃል አቀባያችን የላከው መረጃ ያመለክታል።
••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc13
ታህሳስ 12፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ሳኒ 19፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ             
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጋር በመተባበር ሥልጠና ሰጠ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጋር በመተባበር ሐሙስ ዕለት የስነ ልቦና ስብራት ለደረሰባቸው ወገኖች በመቐለ ከተማ የማገገሚያ ሥልጠና ሰጠ።

በዓምድና ሆቴል የተሰጠው ይኸው ሥልጠና ተስፋ ሰጪ መኾኑን በጠቅላይ ምክር ቤቱ የሰላም፣ የክልልና የዲያስፖራ ዘርፍ ተጠሪ ሐጅ ሙስጠፋ ናስር ተናግረዋል።

በመቐለ ከተማ በተካሄደው በዚህ ሥልጠና ላይ፣ በክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የተመረጡ ዘጠና ሦስት ተሳታፊዎች መታደማቸውን ሐጂ መስጠፋ ተናግረዋል።

ሐጂ ሙስጠፋ አክለውም፣ በቀጣይ ጠቅላይ ምክር ቤቱ እስከታችኛው የአስተዳዳር እርከን በመውረድ ትኩረት ሰጥቶ የስነ ልቦና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችን ተመሳሳይ ድጋፍ ማድረግ ያስፈልገዋል ብለዋል።

የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክርቤትን አቅም ለማጠናከር  ጠቅላይ ምክር ቤቱ በመስከረም 2017 ዓ.ል የተሽከርካሪ ድጋፍ ማድረጉን ሐጂ ሙስጠፋ አስታውሰዋል።

በትግራይ በነበረው ጦርነት ሳቢያ የስነ ልቦና ስብራት የደረሰባቸው ወገኖቻችንን በዘላቂነት ለማቋቋም የሁሉም ባለድርሻ አካላት ትብብር አስፈላጊ መሆኑን ሐጂ ሙስጠፋ ናስር አሳስበዋል::

የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕረዚደንት ሼይኽ አደም እብዱልቃድር "ጠቅላይ ምክር ቤቱ ለክልሉ መጅሊስ እያደረገ ያለውን ሁሉ አቀፍ ድጋፍ ማመስገናቸዉን ና በቀጣይም መሰል ድጋፎች እንዲቀጥሉ "መጠየቃቸውን ሐጂ ሙስጠፋ ተናግረዋል::
•••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
ታህሳስ 12፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ሳኒ 19፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ሹራ (ምክክር) ማናቸውንም ችግሮች የሚፈታ ጠቃሚ መላ መሆኑን የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት ተናገሩ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ድሬዳዋ |
የአገራችንን ሰላም ለማረጋገጥ ሹራ (ምክክር) ማናቸውንም ችግሮች የሚፈታ ጠቃሚ መላ መሆኑን የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት ተናገሩ።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ይህን የተናገሩት የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ከድሬዳዋ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጋር በመተባበር፣ "ሃይማኖቶች ለሰላም፣ ለአንድነት፣ ለአብሮነትና ለአገር ግንባታ ያላቸው ሚና" በሚል መሪ ሐሳብ ባዘጋጁት የመጀመሪያው አገር አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ ላይ ነው።

በጉባዔው ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ሹራ (ምክክር) ማናቸውንም ችግሮች የሚፈታ፣ የአገራዊ ሰላም መሠረት የኾነ እጅግ ጠቃሚ መላ መሆኑን ተናግረዋል።

ሰላምን ለማምጣት የሚታየው መነቃቃትና የሚደረገው ጥረት አገርን እና ሕዝባችንን የሚጠቅም በመሆኑ፣ ማንም ተጎጂ ወደማይሆንበት የሰላም መድረክ የሚደረገው ጉዞ አበረታታች መሆኑን ተናግረዋል።

በዚሁ አገር አቀፍ የሰላም ጉባዔ ላይ ሰላም የሃይማኖቶች ተቀዳሚና ዘላቂ ግብ መሆን እንዳለበት የተነገረ ሲኾን፣ የአገሪቱን ሰላም በዘላቂነት አጽንቶ ለማስቀጠል የሃይማኖት አባቶችና ምዕምናን ለሰላም መሥራት ትውልድን የሚያድንና አገርን የሚያረጋጋ መኾኑ በአጽንዖት ተወስቷል።

በጉባዔው ላይ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የተመራው የጠቅላይ ምክር ቤቱ ልዑካን፣ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ የበላይ ጠባቂ አባቶች፣ የሰላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ (ዶ/ር)፣ የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ የተከበሩ አቶ ከድር ጁሃር፣ የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ወይዘሮ ፈትሂያ አደን፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎች እና ዑጋዞች ታድመዋል።

​ሁለተኛ ቀን ባስቆጠረው በዚህ የሰላም ኮንፈረንስ ላይ ቀጣዩን አገር አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ የኦሮሚያ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ እንዲያካሂድ ተወስኗል።

​•••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
ታህሳስ 13፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ሳኒ 21፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የብቸና ከተማ ሙስሊሞች የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላም ምክር ቤትንና የሞጣ ሙስሊሞች መልሶ ማቋቋም እና የልማት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤትን አመሰገኑ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሞጣ ሙስሊሞች መልሶ ማቋቋምና የልማት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት በብቸና ከተማ ሲያስገነባ የቆየው የመድረሳ ሕንጻ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነ።

የመድረሳ ሕንጻ ግንባታውን መጠናቀቅ ተከትሎ የብቸና ከተማ ሙስሊሞች ተወካዮቻቸውን ጠቅላይ ምክር ቤቱ ድረስ በመላክ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የብቸና ከተማ ሙስሊም ማኅበረሰብን ወክለው ምስጋናቸውን ለጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ጸሐፊና ለሞጣ ሙስሊሞች ክትትል ዐብይ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሸይኽ ሐሚድ ሙሳ ያቀረቡት ኢንጅነር መሐመድ ዑመር እና ኢንጅነር ጀማል ሱልጣን ናቸው።

የማኅበረሰቡ ተወካዮች ግንባታዉን የሚያሳይ በተንቀሳቃሽ ምስል የታገዘ ዝርዝር ሪፖርት አቅርበዋል።

በሪፖርታቸውም የከተማዋ ሙስሊሞች የመድረሳ ግንባታው የተከናወነበትን 5 ሺህ ካሬ ሜትር ስፋት ያለው መሬት ከመንግሥት ከተረከቡ በኋላ ለረጅም ጊዜ ምንም ዓይነት የልማት ሥራ ሰይሠሩበት በመቆየቱ በሚመለከተው የመንግሥት አካል ሁለት ጊዜ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ተጽፎ እንደነበረ አስታውሰዋል።

ክስተቱ ህብረተሰቡን መሬቱ ሊነጠቅ ነው የሚል ስጋት ውስጥ በከተተበት ወቅት በጠቅላይ ምክር ቤቱ የሞጣ ሙስሊሞች መልሶ ማቋቋምና የልማት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት አስፈላጊውን የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ የመድረሳው ግንባታ እውን እንዲሆን አድርጓል ብለዋል።

ይህ ድርጊት የክልሉን ሙስሊሞች አንድነት ያጠናከረ እንደሆነ የጠቀሱት የብቸና ከተማ ሙስሊም ማኅበረሰብ ተወካዮች ለተደረገው የገንዘብ ድጋፍ በማኅበረሰቡ ስም ጠቅላይ ምክር ቤቱን እና የመልሶ ማቋቋምና የልማት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱን አመስግነዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ እና የሞጣ ሙስሊሞች ክትትል ዐብይ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሸይኽ ሐሚድ ሙሳ የብቸና ሙስሊም ማኅበረሰብ የተሰጠውን ገንዘብ በአግባቡ ለታሰበለት ዓላማ ማዋሉ የሚያስመሠግን መሆኑን ጠቅሰው፣ በልዩ ልዩ ምክንያቶች በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ ሳይጠናቀቁ የቀሩ የሞጣ ፕሮጀክቶች በአጠረ ጊዜ እንዲጠናቀቁ በልዩ ትኩረት እየተሠራ መሆኑን አንስተዋል።

በሞጣ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች ስድስት መስጂዶች፣ መድረሳዎችና የንግድ ማዕከላት እየተገነቡ እንደሆነ ያነሱት ሸይኽ ሐሚድ ሙሳ ለሁሉም ነገር መሠረቱ ሰላም በመኾኑ አላህ ሰላም እንዲያመጣ ዱዓ ልናደርግና ለሰላም ልንሠራ ይገባል ብለዋል።



​•••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
ታህሳስ 16፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ሳኒ 23፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጠቅላይ ምክር ቤቱ እና የሰላም ሚኒስቴር በሰላም ግንባታ ላይ በጋራ እንደሚሠሩ አስታወቁ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

አዲስ አበባ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እና የሰላም ሚኒስቴር በሀገራዊ የሰላም ግንባታ ሥራዎች ላይ በጋራ እንደሚሠሩ ተናገሩ።

ሁለቱ ተቋማት ይህን ያሳወቁት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የሰላም ሚኒስትር ክቡር መሐመድ ኢድሪስን ዛሬ በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ነው።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት ክቡር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ እና የሰላም ሚኒስትሩ ክቡር አቶ መሐመድ ኢድሪስ በሀገሪቱ የተጀመረውን ሰላም አጠናክሮ ማስቀጠል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ሐሳብ ተለዋውጠዋል፡፡

ፕሬዚደንቱ አዲስ የተሾሙት የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ መሐመድ ኢድሪስ ጠቅላይ መከር ቤቱን ለመጎብኘትና በሰላም ጉዳይ ላይ ለመወያየት በመምጣታቸው በራሳቸውና በጠቅላይ ምክር ቤቱ ስም አመስግነዋል።

ሥራውን ከጀመረ ሁለት ዓመት ከመንፈቅ ዕድሜ ያስቆጠረው የለውጡ መጅሊስ የነበሩበትን የተለያዩ ዕዳዎች በመክፈል ትልልቅ ፕሮጀክቶችን እውን ለማድረግ በከፍተኛ እንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝ ክቡር ፕሬዚደንቱ ተናግረዋል።

የሙስሊሙን አንድነት እና የአገራችንን ሰላም ለማጠናከር ጠቅላይ ምክር ቤቱ የተለያዩ ሥራዎችን እየሠራ እንደሚገኝ የጠቀሱት ክቡር ፕሬዚደንቱ ምክር ቤቱ የሚኒስቴሩ አጋር በመኾን ይህን ሥራ ይበልጥ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

ክቡር ሚኒስትሩ በበኩላቸው የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት ክቡር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ አገራችንን ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ለማስተዋወቅና የሙስሊሙን ብሎም የአገርን ስም ከፍ ለማድረግ እየሠሩ ያሉትን ሥራ አድንቀዋል።

በአፋር እና በሶማሊ ወንድማማች ሕዝቦች መካከል የነበረውን የቆየ የሰላም እጦት ለመቅረፍ ጠቅላይ ምክር ቤቱ የሠራው ሥራ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበ መኾኑን የጠቀሱት ክቡር ሚኒስትሩ፣ በቀጣይም ምክር ቤቱ ሁሉን አቀፍ የሰላምና የልማት ሥራዎችን አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።

የሃይማኖት አገር በኾነችውና በርካታ የችግር መፍቻ ባህሎችና ልምዶች ባላት አገራችን ላይ ዜጎች በሰላም እጦት ሳቢያ ለችግር መዳረግ እንደሌለባቸው ክቡር ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

አሁን ያለው ሰላም እንዲጎለብት፣ እየታዩ ያሉ የሰላም ፈተናዎች እንዲፈቱና ችግሮቻችን በሙሉ ዘላቂ መፍትኄ እንዲያገኙ በጁምዓ ሶላት ወቅት አገራዊ የሰላም ጥሪ እና ዱዓ እንዲደረግ ጠቅላይ ምክር ቤቱ መልዕክት እንዲያስተላልፍ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል።

በመንግሥት በኩል ለሰላም የሚከፈል ማንኛውም ዋጋ እንደሚከፈል የጠቀሱት ክቡር ሚኒስትሩ የሰላም ሚኒስቴርም ከሁሉም የእምነት አባቶች እና ተቋማት ጋር በትብብር እንደሚሠራ በአጽንዖት ተናግረዋል።

በጠቅላላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት ቢሮ በተደረገው በዚህ ውይይት ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የዓሊሞች ጉባዔ ምክትል ሰብሳቢና የፈታዋ እና ምርምር ተጠሪ ዶክተር ጀይላን ኸድር፣ ምክትል ፕሬዚደንትና የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ተጠሪው ሼይኽ አብዱልዓዚዝ ሼይኽ አብዱልወሊ፣ ሌሎች የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትና የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
••••••••••••

የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc13
ታሕሣሥ 17፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ሳኒ 25፣ 1446 ዓ.ሒ
‎بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ             
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ፕሬዚደንቱ በኢትዮጵያ የኳታር አምባሳደር ሳዓድ ሙባረክ ሳዓድ ጋር ተወያዩ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ በኢትዮጵያ የኳታር አምባሳደር ሳዓድ ሙባረክ ሳዓድ አል ጃፋሊ አል ናኢሚን ጋር ተወያዩ።

አዲስ አበባ በሚገኘው የኳታር ኤምባሲ በመገኘት ከአምባሳደሩ ጋር ውይይት ያደረጉት ክቡር ፕሬዚደንቱ ሁለቱ አገራት በሚያደርጓቸው የልማት ግንኙነቶችና በጋራ ሊሠሯቸው የሚችሏቸው ሥራዎችን አጠናክረው በሚቀጥሉበት መንገድ ላይ መወያየታቸው ተነግሯል።

አምባሳደር ሳዓድ ሙባረክ ሳዓድ አል ጃፋሊ አል ናኢሚን በበኩላቸው ኤምባሲው ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ጋር  የሚሠራቸውን የልማት ሥራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

በጠቅላይ ምክር ቤቱ የበላይ ጠባቂነት በዘይድ ኢብኑ ሳቢት የቁርኣን ማኅበር  አስተባባሪነት በመጪው ጥር 25፣ 2017 ዓ.ል. በአዲስ አበባ ስታዲየም በሚካሄደው ሁለተኛው ዓለምአቀፍ የቁርኣንና የአዛን ውድድር ላይ የኳታር ተወዳዳሪዎች እንደሚሳተፉ አምባሳደሩ  ተናግረዋል።

የኳታር ሕዝብ በርካታ የቅዱስ ቁርኣን ቅጂዎችን ለጠቅላይ ምክር ቤቱ በስጦታ (በወቅፍ) ለመስጠት ወደ አገር ዉስጥ ለማስገባት ሂደት ላይ መሆኑን አምባሳደሩ ተናግረዋል።

​•••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
ታሕሣሥ 17፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ሳኒ 25፣1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የነጃሺ እስላማዊ ማዕከል ፕሮጀክት የሾሪንግ ቁፋሮና ግንባታን ለማስጀመር የውል ስምምነት ተፈራረሙ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በአዲስ አበባ፣ አፍሪካ ሕብረት አቅራቢያ የሚያስገነባው የነጃሺ እስላማዊ ማዕከል ፕሮጀክትን ለማስጀመር የሾሪንግ ቁፋሮና ግንባታ ከሚያካሂደው ኩባንያ ጋር ዛሬ የውል ስምምነት ፈጸመ።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ የውል ስምምነት የፈፀመው ከአንከር ፋውንዴሽን ስፔሻላይዝድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት ጋር ነው።

ስምምነቱን በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በኩል ዋና ሥራ አስኪያጁ ሐጂ ከማል ሐሩን፣ በአንከር ፋውንዴሽን ስፔሻላይዝድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ በኩል ደግሞ የድርጅቱ ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ አቶ ኤርሚያስ ተሾመ ፈርመዋል።

በዚህ የፕሮጀክቱ ምዕራፍ የሚካሄደው የሾሪንግ ቁፋሮና ግንባታ ሥራ የአፈር መናድንና በድንበር ላይ የሚገኙ ሕንጻዎችን መሠረት ከመናድ ለመከላከል ያለመ መኾኑን ከባለሙያዎች ገለጻ ለማወቅ ተችሏል።

የጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ በተገኙበት በተካሄደው የፊርማ ስነ ሥርዓት ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብዱልሃዲ ሙሐመድ ሥራውን የሚያካሂደውን ኩባንያ ለመምረጥ ስለተካሄደው ጨረታ ሂደት ገለጻ አድርገዋል።

የነጃሺ መስጂድና እስላማዊ ማዕከል ግንባታ ፕሮጀክት ዐብይ ኮሚቴ የወከላቸው የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት በመረጣ ሂደቱ ላይ የአሸናፊው ኩባንያ የሥራ አፈጸጸም ብቃትና አቅም እንደተመዘነ እና ኩባንያው ውሉ በተፈረመ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሥራውን በመጀመር በአፋጣኝ ሊያጠናቅቅ ከመግባባት ላይ መደረሱን ለፕሬዚደንቱ አስረድተዋል።

በዚህ ሥራ ዘርፍ ቀደምትና የረጅም ጊዜ የካበተ ልምድ ያለው የአንከር ፋውንዴሽን ስፔሻላይዝድ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ ሥራ አስኪያጅ አቶ ኤርሚያስ ተሾመ ኩባንያው የሕዝብ ሀብት የኾነውን የነጃሺ መስጂድና እስላማዊ ማዕከል ፕሮጀክትን የሾሪንግ ሥራ ለማካሄድ ዕድል በማግኘቱ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል።

ኩባንያቸው በውሉ መሠረት ሥራውን በታማኝነት እና በጥራት
ሠርቶ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ እንደሚያስረክብም አቶ ኤርሚያስ ተናግረዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ በዚሁ ጊዜ የንጉሥ ነጃሺ መስጂድ እና እስላማዊ ማዕከል ፕሮጀክት እንደ ሀገርም እንደ ሙስሊም ማኀበረሰብም ትልቅ ታሪክ በመኾኑ፣ "ኩባንያችሁ በዚህ ታሪካዊ ሥራ ላይ አሻራውን ለማሳረፍ በመብቃቱ እንኳን ደስ ያላችሁ" ብለዋል።

የዚህን ፕሮጀክት ስኬትና አገልግሎት ሕዝበ-ሙስሊሙ በጉጉት እንደሚጠብቀው የጠቀሱት ክቡር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ፣ ኩባንያው ሥራውን በአጭር ጊዜና በጥራት ሠርቶ እንዲያጠናቅቅ ከእኛ የሚጠበቀውን ሁሉ እናደርጋለን ብለዋል።

​​•••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1