ሕዳር 19፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ኡላ 26፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የጠቅላይ ምክር ቤቱ የማኅበራዊ አገልግሎት ዘርፍ ለአካል ጉዳተኞች ማኅበር የአቅም ግንባታ ሥልጠና መስጠት ጀመረ።

አዲስ አበባ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የማኅበራዊ አገልግሎት ዘርፍ ለአካል ጉዳተኞች ማኅበራት የሥራ ኃላፊዎች የሁለት ቀናት የአቅም ግንባታ ሥልጠና መስጠት ጀመረ።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሥራ አስፈጻሚ አባልና የፈትዋና ምርምር ዘርፍ ተጠሪ ሼይኽ ኢድሪስ አሊ ሑሴን (ደጋን) በሥልጠናው መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ አካል ጉዳተኝነት በተፈጥሮና ከጊዜ በኋላ ሊመጣ የሚችል ክስተት መኾኑን አስታውሰዋል።
በእስልምና ታሪክ ውስጥ አካል ጉዳተኛ ኾነው ትልቅ ገድል ያስመዘገቡ የነቢያችን ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) ተከታዮች እንደነበሩ የተናገሩት ሼይኽ ኢድሪስ፣ ለአብነት የአብደሏህ ኢብኑ ዑሚ መኽቱም ገድል ከፍተኛ እንደነበረ አውስተዋል።
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዓሊሞች ጉባዔ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የኾኑት ሼይኽ ሙሐመድዘይን ዘኽረዲን ጠቅላይ ምክር ቤቱ በአዋጅ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የሙስሊሙን ማኅበረሰብ ሃይማኖታዊና ልማታዊ ጥያቄዎች ለመፍታት እየተጋ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በተለያየ ምክንያት የአካል ጉዳት የገጠማቸውን ወገኖች በማደራጀት ሃይማኖታዊና ዓለማዊ ችግሮቻቸው እንዲፈቱ ጠቅላይ ምክር ቤቱ የሚያደርገው ጥረት ይበል የሚያሰኝ እንደኾነ ሼይኽ ሙሐመድዘይን ተናግረዋል።
አካል ጉዳተኝነት አለመቻል ማለት እንዳልኾነ ከሚያሳዩ ምሳሌዎች ውስጥ የታዋቂው ዓሊም የሼይኽ ኢብኑ ባዝን ገድል ያወሱት ሼይኽ ሙሐመድዘይን፣ በቀጣዮቹ ጊዜያት በእነዚህ ማኅበራት አማካይነት ብዙ ባለራዕዮች ይፈጠራሉ ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።
ለዚህም እውን መኾን የሚመለከታቸው ሁሉ የበኩላቸውን አስተዋፅዖና እገዛ እንዲያበረክቱ ሼይኽ ሙሐመድዘይን ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የተቋማት እና ማኅበራት ዳይሬክቶሬት ስር ተመዝግበው ከሚንቀሳቀሱ የበጎ አድራጎት ማኅበራት አራቱ የአካል ጉዳተኞች ማኅበራት ናቸው።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ የማኅበራዊ አገልግሎት ዘርፍ ለአካል ጉዳተኞች ማኅበራት የሥራ ኃላፊዎች እየሰጠ የሚገኘውና በአብደላ ኢብኑ ዑሚ መኽቱም ሕፃናት የዐይነ ስውራን አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በቁርኣን የተከፈተው ሥልጠና በዛሬው ዕለት ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።
••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1

Telegram
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
ሕዳር 18፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ኡላ 25፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጠቅላይ ምክር ቤቱ መላውን ሙስሊም ማኅበረሰብ በእኩልነት የማገልገል ተልዕኮና ኃላፊነቱን ለመወጣት በትጋት መሥራቱን እንደሚቀጥል ተነገረ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እስከ ታች ድረስ ባሉት መዋቅሮቹ መላውን ሙስሊም ማኅበረሰብ በእኩልነት የማገልገል ተልዕኮና ኃላፊነቱን ለመወጣት በትጋት መሥራቱን እንደሚቀጥል የምክር ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ተናገሩ።
ዋና ሥራ አስኪያጁ ሐጂ ከማል ሐሩን ይህን የተናገሩት የጠቅላይ ምክር ቤቱ የማኅበራዊ አገልግሎት ዘርፍ ለአካል ጉዳተኞች ማኅበራት አመራሮች ያዘጋጀው የሁለት ቀናት የአቅም ግንባታ ሥልጠና ዛሬ ሲጠናቀቅ ባደረጉት ንግግር ነው።
ሐጂ ከማል ሐሩን የሙስሊሙ ማኅበረሰብ አካል የኾኑትን አካል ጉዳተኛ ወገኖች በማገልገል ዓላማ ለተቋቋሙ ማኅበራት ተከታታይነት ያለው ሥልጠና በመስጠት አቅማቸውን ማሳደግ አስፈላጊ እንደኾነ ጠቅላይ ምክር ቤቱ
ይገነዘባል ብለዋል።
ጠቅላይ ምክር ቤቱ አካል ጉዳተኛ ወንድምና እህቶቻችን በተለያዩ መልኮች የሚደርሱባቸውን ማነቆዎች ለማስቀረት የሚያስችሉ ተከታታይነት ያላቸው የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎች ማዘጋጀቱን እንደሚቀጥልም ሐጂ ከማል ተናግረዋል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ የማኅበራዊ አገልግሎት ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር ተውፊቅ ቢራራ፣ ዘርፉ እስላማዊ እሴቶችን መሠረት ያደረገ ማኅበረሰባዊ ተሳትፎን ይበልጥ በማጎልበት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን እየሠራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሁሉም ዘርፎችና ዳይሬክቶሬቶች በሚሠሯቸው ሃይማኖታዊና የልማት ሥራዎች አካል ጉዳተኛና ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ወገኖቻችንን ተሳታፊነት የሚያረጋግጡ እንዲኾኑ በትብብር እየሠሩ መኾኑን ዶክተር ተውፊቅ ተናግረዋል።
በቀጣይም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት በአካል ጉዳተኞችና ልዩ ፍላጎት ባላቸው ወገኖቻችን መንፈሣዊ እና ዓለማዊ ሕይወት ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል የአሠራር ሥርዓት እንዲኖር ዘርፉ ተጠናክሮ እንደሚሠራ ዶክተር ተውፊቅ ተናግረዋል።

ሕዳር 22፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ኡላ 29፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
"የሸሪዓ ፍርድ ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ የሚሻሻልበት አዲስ ረቂቅ ይዘጋጃል።"
- የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት

በሸሪዓ ፍርድ ቤቶች ውስጥ የሚታዩ ችግሮችን መርምሮ የመፍትኄ ሐሳብ እንዲያቀርብ የተቋቋመው ኮሚቴ በዛሬው ዕለት ጥናቱን ለባለድርሻ አካላት አቀረበ።
ኮሚቴው "የሸሪዓ ፍርድ ቤቶች የሕግ ማዕቀፍ፣ አደረጃጀት እና የሰው ኃይል አስተዳደር" በሚል ርዕስ ያጠናቀረውን ጥናት ክቡር አቶ መሐመድ አሕመድ ያቀረቡ ሲኾን፣ በሸሪዓ ፍርድ ቤቶች የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚታዩ ችግሮችን በተመለከተም በሕግ ባለሙያው አቶ አብዱልሀኪም ጀማል የተዘጋጀ የጥናት ሰነድ ቀርቦ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጓል።
በቀረቡት ጥናቶች ላይ ከሕግ ባለሙያዎችና ከባለድርሻ አካላት ሰፋ ያሉ አስተያየቶችና ተሻሽሎ ለሚዘጋጀው የማቋቋሚያ አዋጅ ግብዓት የሚኾኑ ሐሳቦች ቀርበዋል።
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት አቶ ቴዎድሮስ ምህረት ወደ ኃላፊነት ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ ትኩረት ካደረጉባቸው ጉዳዮች አንዱ የሸሪዓ ፍርድ ቤቶች የአሠራር ሁኔታን ማሻሻል መኾኑን ተናግረዋል።
"የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሸሪዓ ፍርድ ቤቶች ውስጥ ከሕግ፣ ከአደረጃጀት እና ከሰው ኃይል አስተዳደር አኳያ የሚታዩ ክፍተቶችን ለመድፈን ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጋር በቅርበት አየሠራ ነው" ሲሉም ተናግረዋል።
ፕሬዚደንቱ አክለውም፣ "በዚህ የውይይት መድረክ ላይ በአካል መገኘቴ ጉዳዩን ከባለድርሻ አካል አኳያ ሁኔታውን በትኩረትና በቅርበት ለማየት አስችሎኛል" ብለዋል።
አያይዘውም የቀረቡትን ጥናቶች እና ከተሳታፊዎች የተሰጡ ግብዓቶችን መሠረት በማድረግ የሸሪዓ ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ የሚሻሻልበት አዲስ ረቂቅ ማዘጋጀት መጀመር አለበት ብለዋል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የኢትዮጵያ መስሊም ሃይማኖታዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ የሚዳኝበት የሸሪዓ ፍርድ ቤት ክብሩ የተጠበቀ እና ዘመኑን የዋጀ እንዲኾን ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
ክቡር ፕሬዚደንቱ አክለውም በሸሪዓ ፍርድ ቤት የማቋቋሚያ አዋጅ ላይ ያሉ ክፍተቶች ተገቢውን ትኩረት እንዲያገኙ ለማስቻል በተደረገው ጥረት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት ላደረጉት ትብብር አመስግነዋል።
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የፕሬዚደንቱ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የኾኑት ዑስታዝ አቡበከር አሕመድ በዚሁ ጊዜ የኢትዮጵያ ሙስሊም ማኅበረሰብ ከሸሪዓ ፍርድ ቤቶች ጋር ያለውን የትስስር ታሪክ አውስተዋል።
ዑስታዝ አቡበከር አክለውም በሸሪዓ ፍርድ ቤቶች ውስጥ የሚታዩ ዐበይት ችግሮችን በመለየት የሕግ፣ የአደረጃጀት እና የሰው ኃይል አስተዳደርን በተመለከተ ማሻሻያ የሚፈልጉ ጉዳዮችን ለመለየት የተቋቋመውን ኮሚቴ አመሠራረት፣ በኮሚቴው የተደረጉ ጥናቶችን እና ከባለድርሻ አካላት ጋር የተካሄዱ የውይይት ሂደቶችን አስመልክቶ ሰፋ ያለ ማብራሪያ አቅርበዋል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ በውይይቱ ላይ የተገኙ የሕግ ባለሙያዎችና የባለድርሻ አካላት ተወካዮችን አመስግነው ጥናቱ ከመድረኩ ተሳታፊዎች በተሰጡ ግብዓቶች ዳብሮ፣ ሕገ መንግሥትን መሠረት ባደረገ መልኩ የሸሪዓ ፍርድ ቤቶችን አሠራር፣ አደረጃጀት እና የሰው ኃይል አስተዳደር ሕዝበ-መስሊሙን ያማከለ ለማድረግ የተጀመረው ጥረት ፍሬ እስከሚያፈራ ይቀጥላል ብለዋል።
በዘመናዊት ኢትዮጵያ የሸሪዓ ፍርድ ቤቶች ሕጋዊ አውቅና አግኝተው በመጀመሪያ የተቋቋሙት ከዛሬ 85 ዓመት በፊት በታወጀው አዋጅ ቁጥር 2/1934 ነው።

ኅብረተሰቡ ለመቄዶንያ የአዕምሮ ህሙማንና የአረጋውያን መርጃ ማኅበር ሁሉንአቀፍ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ቀረበ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ለመቄዶንያ የአዕምሮ ህሙማንና የአረጋውያን መርጃ ማኀበር የበኩሉን ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቀረበ።
ጥሪው የቀረበው የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ አባል ቤተ-እምነቶችና የመቄዶንያ የአዕምሮ ህሙማንና የአረጋውያን መርጃ ማኀበር አባላት ለአገር ሰላም ፀሎት ባደረጉበትና ለማኅበሩ ድጋፍ ማሰባሰቢያ በተዘጋጀው መርኃግብር ላይ ነው።
በመርኃግብሩ ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን በመወከል የተገኙት የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ና የሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ተጠሪው ሼይኽ ሑሴን ሐሰን ነቢያችን ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) ለዓለማት እዝነት የተላኩ መኾናቸውን አውስተው፣ መስሊሙ ማኅበረሰብ መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማኅበር እየሠራ ለሚገኘው የበጎ አድራጎት ሥራ ውጤታማነት ድጋፍ የማድረግ ሃይማኖታዊ ኃላፊነት አለበት ብለዋል።
የመቄዶንያ የአዕምሮ ህሙማንና የአረጋውያን መርጃ ማኀበር መሥራችና ኃላፊ የክብር ዶክተር ቢንያም በለጠ ማዕከሉ አዲስ አበባን ጨምሮ በአርባ አራት ከተሞች ከ8 ሺህ በላይ ራሳቸውን ችለው መንቀሳቀስ የማይችሉ የአልጋ ቁራኛ አረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማንን ከጎዳና በማንሳት በመንከባከብ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
መቄዶንያ የአዕምሮ ህሙማንና የአረጋውያን መርጃ ማኀበር ዘር፣ ሃይማኖት እና ፆታ ሳይለይ ሰብዓዊ አገልግሎት የሚሰጥ የበጎ አድራጎት ድርጅት መኾኑን የጠቀሱት ክቡር ዶክተር ቢኒያም፣ በአሁኑ ጊዜ 2 ሺህ 900 የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ወገኖች በማዕከሉ እንክብካቤ እየተደረገላቸው እንደሚገኙ ተናግረዋል።
ክቡር ዶክተር ቢኒያም አክለውም ተቋሙ በማዕከሉ የሚገኙ ሙስሊሞች የሃይማኖት እውቀታቸውን ለማጎልበት የዲን ትምህርት አንዲማሩና ሶላታቸውን እንዲሰግዱ በማዕከሉ ግቢ ዉስጥ መስጂድ በማቋቋምና ዑስታዞችን በመቅጠር አገልግሎት እየሰጠ መኾኑንም ተናግረዋል።
ማኅበሩ በቀጣይ ጊዜያት ቅርንጫፎቹን ወደ 244 ለማሳደግ እየሠራ እንደሚገኝም የክብር ዶክተር ቢኒያም ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት የጋራ ጉባዔ ዋና ፀሐፊ የኾኑት ቀሲስ ታጋይ ታደለ ጉባዔው ለአገር ሰላም በጋራ እየሠራ መሆኑን ጠቅሰው፣ በአገራችን አንዳንድ ቦታዎች ላይ እየታየ ያለው የሰላም እጦት እንዲያበቃ የጋራ ጉባዔው አባል ቤተ-እምነቶች በመቄዶንያ ከሚኖሩ ወገኖቻችን ጋር የዛሬውን የፀሎትና የዱዓ መርኃግብር ማዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
መቄዶንያ የአዕምሮ ሕሙማንና የአረጋውያን መርጃ ማዕከል "ሰውን ለመርዳት፣ ሰው መኾን በቂ ነው" በሚል ወርቃማ መርኅ በታሕሣሥ ወር 2002፣ አሥር ሰዎችን በመንከባከብ ሥራውን የጀመረ የበጎ አድራጎት ድርጅት መሆኑ ተነግሯል።
ዛሬ በመቄዶንያ የአዕምሮ ህሙማን እና የአረጋውያን መርጃ ማዕከል ግቢ ውስጥ ለአገር ሰላም በተደረገው ፀሎት እና ለማዕከሉ የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርኃግብር ላይ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት የበላይ ጠባቂ አባቶች፣ የቦርድ አባላት፣ እንዲሁም የሃይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።

ሕዳር 25፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ሳኒ 2፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ሥራ አስፈጻሚ ዓመታዊ የሥራ ግምገማ ተጀመረ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ሥራ አስፈጻሚ ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ (ተቅዪም) ኮምቦልቻ ከተማ በልዑል መኮንን ሆቴል መሰብሰቢያ አዳራሽ እየተካሄደ ነው።
ዛሬ የተጀመረውና በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚደንት ሼይኽ አብዱልአዚዝ ሼይኽ አብዱልወሊ የተመራው የአማራ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ሥራ አስፈጻሚ ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ በ2016 ዓ.ል በምክር ቤቱ በተከናወኑ ሥራዎች ላይ ትኩረት አድርጓል።
ግምገማው በ2016 ዓ.ል. የተመዘገቡ ውጤቶችን አጠናክሮ በማስቀጠልና የታዩ ውሱንነቶችን ለይቶ የማስተካከያ እርምጃ በመውሰድ በ2017 ዓ.ል. ለክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ካለፈው ዓመት የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግብ አቅም እንደሚፈጥርለት ምክትል ፕሬዚደንቱ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ነሐሴ 18፣ 2016 ዓ.ል. በአዲስ አበባ ባደረገው የ2ኛ ዓመት፣ 4ኛ መደበኛ ጉባዔ ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት የክልልና የከተማ አስተዳደር የእስልምና ጉዳይ ምክር ቤቶች የ2016 ዓ.ል. የሥራ አፈጻጸማቸውን እንዲገመግሙ መወሰኑ ይታወሳል።
በኮምቦልቻ ከተማ በተጀመረው የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ዓመታዊ ግምገማ ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሥራ አስፈፃሚ አባል፣ የፈትዋና ምርምር ዘርፍ ተጠሪና የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ተወካይ ሼይኽ ኢድሪስ ዓሊ ሑሴን (ደጋን) እና የሰላምና ዲያስፖራ ዘርፍ ተጠሪው ሐጂ ሙስጠፋ ናስር ተገኝተዋል።
ዛሬ በኮምቦልቻ ከተማ የተጀመረው የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ በነገው ዕለትም እንደሚቀጥል በስፍራው የሚገኘው ቃል አቀባያችን የላከው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት 'የዋናው መግቢያ በር እና አጥሩን' እንዲሁም በጠቅላይ ምክር ቤቱ ለሚሰራው 'መስጂድ' ለወጣው ጨረታ አሸናፊው ታወቀ።
በዚህ የዲዛይን እና የአማከሪ ጨረታ አሸናፊ'ARCHI' ዲዛይን+ኮንሰልታሲ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኀበር የጨረታው አሸናፊ ሆኗል። 👇

ሕዳር 26፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ሳኒ 3፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ዑስታዝ አቡበከር አሕመድ የሸይኻ ፋጢማ ቢንት ሙባረክ ዓይነ‐ሥውራን አዳሪ ትምህርት ቤትን ጎበኙ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የፕሬዚደንቱ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዑስታዝ አቡበከር አሕመድ ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ጋር በመኾን ክብርት ሸይኻ ፋጢማ ቢንት ሙባረክ የዐይነ‐ስውራን አዳሪ ትምህርት ቤትን ጎበኙ።
ዑስታዝ አቡበከር በጉብኝታቸው ወቅት የትምህርት ቤቱ ሙስሊም ተማሪዎች የጀመዓ ሶላት የሚሰግዱበት ቦታ ተመቻችቶላቸው በጋራ ሲሰግዱ ማየታቸውን ተናግረዋል።
ይህን መሰል ተቋም ሁሉንም የማኅበረሰብ ክፍሎች እኩል ተጠቃሚ የሚያደርግ መኾኑ የሚደገፍ እንደኾነ የጠቀሱት ዑስታዝ አቡበከር፣ ክፍተቶችን ሲኖሩም ጠቅላይ ምክር ቤቱ ክፍተቶቹን ለመሙላትና ችግሮችን በጋራ ለመፍታት የሁልጊዜ ጥረቱ መሆኑን ተናግረዋል።
"በጉብኝታችን ወቅት በትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህርት አማካኝነት ተቋሙ ለተማሪዎቹ የሚሰጠውን አገልግሎት ተዟዙረን ተመልክተናል" ያሉት ዑስታዝ አቡበከር፣ "ተቋሙ በከፍተኛ ጥንቃቄ ደረጃውን ጠብቆ የተሠራ ከመሆኑም ባሻገር፣ እንደ ሀገር በየተሰማራንባቸው መስኮች ትኩረት ሰጥተን ከሠራን የላቁ አበርክቶዎችን እውን ማድረግ እንደሚቻል ዓይነተኛ ማሳያ እንደሆነ ታዝቤያለሁ" ብለዋል።
ዑስታዝ አቡበከር በዚሁ ጊዜ ሸይኻ ፋጢማ ቢንት ሙባረክ የዓይነ‐ስውራን አዳሪ ትምህርት ቤት ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ፣ ውብ እና የሀገራችንን መፃዒ ገፅታ በሚያንፀባርቅ መልኩ እውን እንዲኾን የበኩላቸውን ሚና የተወጡ ባለድርሻ አካላትን አመስግነዋል።
"ለትምህርት ቤቱ እውን መሆን ጉልህ አሻራቸውን ካሳረፉት መካከል ከተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ንጉሣዊ ቤተሰብ የተገኙት ክብርት ሸይኻ ፋጢማ ቢንት ሙባረክን፣ የክብርት ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጽሕፈት ቤትን፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርንና የከተማውን ትምህርት ቢሮ ከፍ አድርጌ ለማመስገን እወዳለሁ" ብለዋል።
ሸይኻ ፋጢማ ቢንት ሙባረክ የዓይነ‐ስውራን አዳሪ ትምህርት ቤት እንደ ሞዴል ተወስዶ፣ ሁሉንም የማኅበረሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ የሚያደርጉ መሰል የትምህርትና የልኅቀት ማዕከላት በሁሉም የአገራችን ክልሎች ሊገነቡ ይገባል ብለው እንደሚያምኑ ዑስታዝ አቡበከር ተናግረዋል።
"ሰሞኑን በትምህርት ተቋሙ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ስለሚገኙ ሙስሊም ተማሪዎች አያያዝ ሲሰሙ በቆዩ ቅሬታዎች ዙርያ ከትምህርት ቤቱ አስተዳደርና ከተማሪዎቹ ጋር ሰፊ ውይይት አካሂደናል" ያሉት ዑስታዝ አቡበከር፣ "በውይይታችንም መሰል ችግሮች ዳግም እንዳይፈጠሩና ለተፈጠሩትም በጋራ ዘላቂ መፍትኄ በመፈለግ አስፈላጊነት ላይ ከመግባባት ደርሰናል" ብለዋል።
ቅሬታ የተነሳባቸው ጉዳዮችን ለመፍታት በተደረገው ጥረት ችግሩ የተፈታ መኾኑን እና የተቋሙ ሙስሊም ተማሪዎች የጀመኣ ሶላት (የሕብረት ስግደት) የሚፈጽሙበት ቦታ ተመቻችቶላቸው ሶላታቸውን በወቅቱ መስገድ መቻላቸውን በጉብኝታቸው ወቅት ለማረጋገጥ መቻላቸውን ተናግረዋል።
ሙስሊም ተማሪዎቹን በግል እና በቡድን እንዳነጋገሩ የጠቀሱት ዑስታዝ አቡበከር፣ ተማሪዎቹ የነበሩ ችግሮች መቀረፋቸውን በማረጋገጥ ትምህርታቸውን በአግባቡ መከታተል መቀጠላቸውን እንዳሳወቋቸው ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የፕሬዚደንቱ ጽሕፈት ት ቤት ኃላፊ ችግሩ እንዲፈታ ሚናቸውን በአግባቡ ለተወጡት የትምህርት ቤቱ አስተዳደር እና የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ኃላፊነትን ለመወጣት ያሳዩትን ትጋት በማድነቅ አመስግነዋል።

ታህሳስ 4፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ሳኒ 11፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጠቅላይ ምክር ቤቱ ግምቱ 800 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ መድኃኒት እና የሕክምና ግብዓቶችን ለአምስት የመንግሥት ሆስፒታሎች አበረከተ።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከሙስሊም ኤይድ ዩ.ኤስ.ኤ. በሥጦታ ያገኛቸውን ግምታቸው 800 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ መድኃኒት እና የሕክምና መገልገያ ሣሪያዎች ለአምስት የመንግሥት ሆስፒታሎች ዛሬ በሥጦታ አበረከተ።
በጠቅላይ ምክር ቤቱ ቅጥር ግቢ በተካሄደው የርክክብ ስነ ሥርዓት ላይ የመድኃኒትና የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎቹን የክብር ዶ/ር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ለድል ጮራ፣ ለአሶሳ፣ ለጅግጅጋ፣ ለስልጤ እና ለሙሁር አክሊል ሆስፒታል ተወካዮች አስረክበዋል።
ለሆስፒታሎቹ የተበረከቱት የመድኃኒትና የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎች አሜሪካ ከሚገኘው ሙስሊም ኤይድ ዩ.ኤስ.ኤ የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት በጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት የጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዑስታዝ አቡበከር አሕመድ አስተባባሪነት የተገኙ መኾኑን ለማወቅ ተችሏል።
•••••••••••••••

ጠቅላይ ምክር ቤቱ 800 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ መድኃኒትና የሕክምና ግብዓቶች ለአምስት የመንግሥት ሆስፒታሎች አበረከተ።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከሙስሊም ኤይድ ዩ.ኤስ.ኤ. በሥጦታ ያገኛቸውን 800 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ መድኃኒትና የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎችን ለአምስት የመንግሥት ሆስፒታሎች አበረከተ።
ዛሬ በጠቅላይ ምክር ቤቱ ቅጥር ግቢ በተካሄደው የርክክብ ስነ ሥርዓት ላይ የመድኃኒትና የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎቹን የክብር ዶ/ር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ለድል ጮራ (ድሬዳዋ)፣ ለአሶሳ፣ ለጅግጅጋ፣ ለስልጤ እና ለሙሁር አክሊል ሆስፒታል ተወካዮች አስረክበዋል።

በጠቅላይ ምክር ቤቱ ቅጥር ግቢ በተካሄደው የርክክብ ስነ ሥርዓት ላይ የመድኃኒትና የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎቹን የክብር ዶ/ር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ለድል ጮራ ሆስፒታል (ድሬደዋ)፣ ለአሶሳ ሆስፒታል (ቤኒሻንጉል ጉሙዝ)፣ ለጅግጅጋ ሆስፒታል (ሶማሌ)፣ ለስልጤ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እና ለሙሁር አክሊል ሆስፒታል (ማዕከላዊ ኢትዮጵያ) ተወካዮች አስረክበዋል።
ሼይኽ ሐጂ በርክክቡ ወቅት ሲናገሩ ድጋፉን ያደረጉትን እና በሂደቱ ላይ አስተዋፅዖ የነበራቸው ግለሰቦችን፣ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማትን አመስግነዋል።
የመንግሥት ተቋማትም ድጋፎቹ በተቀላጠፈ መንገድ ለታለመላቸው አካላት እንዲደርስ ለሰጡት ቀልጣፋ አገልግሎትና እገዛ አመስግነዋል።
ክቡር ሸይኽ ሐጂ መድኃኒቶቹና ግብዓቶቹ ለታለመላቸው ዓላማ እንዲውሉ የጤና ሚኒስቴር ጥብቅ ቁጥጥር ሊያደርግ ይገባልም ብለዋል።
የሕክምና ቁሳቁሶቹን ድጋፍ አስመልክቶ የተናገሩት ዑስታዝ አቡበከር አሕመድ ሙስሊም ኤይድ ዩ.ኤስ.ኤ. መሰል ድጋፍ ሲያደርግ የአሁኑ ለሰባተኛ ጊዜ ነው ብለዋል።
ሙስሊም ኤይድ ዩ.ኤስ.ኤ. በቀጣይ ድጋፉን እንደሚያደርግ እና በአሁኑ ሰዓት አምስት ኮንቴይነር የሕክምና ግብዐት ጅቡቲ ወደብ መድረሱን የተናገሩት ዑስታዝ አቡበከር ይህ ግብዓት በቀጣይ ጊዜያት ለተለያዩ ክልሎች እንደሚከፋፈል ጠቅሰዋል።
የጤና ሚኒስትር ተወካይ ዶክተር መብራቱ ማሴቦ መንግሥት የጤና አገልግሎቱን እያሰፋ መኾኑን ተናግረው ድጋፉ እየተሰጠ ያለውን አገልግሎት እንደሚያግዝ ጠቅሰዋል።
ጠቅላይ ምክር ቤቱ ያደረገው ድጋፍ በተለይ ከፍለው መታከም የማይችሉ ዜጎችን ጫና እንደሚያቃልል ዶክተር መብራቱ ተናግረዋል።
ዛሬ በጠቅላይ ምክር ቤቱ የተበረከተው የመድኃኒትና የሕክምና ቁሳቁስ አገር ቤት እንዲገባ ሚና ለነበራቸው መንሥታዊ ተቋማትና ግለሰቦች ሽልማት ተበርክቷል።
ለአምስቱ የመንግስት ሆስፒታሎች በተደረገው የመድኃኒትና የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ መርሐ ግብር ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕረዚዳንት ሼይኽ አብዱልከሪም ሼይኽ በድረዲን ሙሐምድ ሱሩር ን ጨምሮ ዓሊሞች :የተለያዩ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የዝግጅቱ ታዳሚ ሆነዋል:

ትዊተር |

ታህሳስ 8፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ሳኒ 16፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ፕሬዚደንቱ የሃይማኖት መሪዎች የአቅም ግንባታ ዐውደጥናት መድረክ ላይ ለመሳተፍ ሞምባሳ ገቡ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ረቡእ በኬኒያዋ ከተማ ሞምባሳ በሚጀመረው የሃይማኖት መሪዎች የአቅም ግንባታ ዐውደጥናት መድረክ ላይ ለመሳተፍ ኬኒያ ገቡ።
ክቡር ፕሬዚደንቱ በዐውደጥናቱ ላይ የሚሳተፉት የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን (IGAD) ባቀረበላቸው ግብዣ መሠረት ሲኾን፣ በዛሬው ዕለት ዐውደ ጥናቱ በሚካሄድባት የወደብ ከተማ ሞምባሳ ገብተዋል።
ነገ ታሕሣሥ 9፣ 2017 ዓ.ል የሚጀምረው "የሃይማኖት መሪዎች የአቅም ግንባታ ዐውደጥናት" መድረክ በቀጠናው ሰላምና በሰላም አብሮ የመኖር አጀንዳዎች ላይ ውይይት ያደርጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ለማወቅ ተችሏል።
ኢጋድ እ.ኤ. አቆጣጠር በ1986 በኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ጂቡቲ እና ዩጋንዳ የተመሠረተ ክፍለ-አህጉራዊ (ቀጠናዊ) ተቋም ሲኾን፣ ዋና ጽሕፈት ቤቱ በጂቡቲ ይገኛል።
ከቀጠናው ሀገራት ኤርትራ እና ደቡብ ሱዳን ዘግየት ብለው ድርጅቱን ተቀላቅለዋል።

ታህሳስ 9፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ሳኒ 15፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የምክክር ባሕልን በማዳበር ልዩነቶችን የመፍታት ልምድን ማሳደግ እንደሚገባ ፕሬዚደንቱ ተናገሩ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
በኬንያ፣ሞምባሳ ዛሬ በተጀመረው "የሃይማኖት መሪዎች የአቅም ግንባታ ዐውደጥናት" ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ ንግግር አደረጉ።
ክቡር ፕሬዚደንቱ በንግግራቸው፣ ከ1440 ዓመታት በፊት እስልምና ወደ ኢትዮጵያ በገባበት ጊዜ በሐበሻው ንጉሥ አስሐመተል ነጃሺ እና ወደ ሐበሻ በስደት የመጡት የነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ.) ባልደረቦች መሪ በነበረው ታላቁ ሶሃባ ጃዕፈር ቢን አቡ ጧሊብ መካከል እምነትን አስመልክቶ የተካሄደው ውይይት እና መተማመን የመቻቻል አብነት እንደኾነ አውስተዋል።
ስለኾነም የውይይት ባህልን በማዳበር ልዩነቶችን የመፍታት አቅምን ማሳደግ እንደሚገባ ተናግረዋል።
የምሥራቅ አፍሪካ በይነ-መንግሥታት የልማት ድርጅት (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) መድረኩን በንግግር ሲከፍቱ ባደረጉት ንግግር፣ በምስራቅ አፍሪካ የተቀሰቀሱ ግጭቶች በፈጠሩት የሰላም እጦት ምክንያት በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ሞትና መፈናቀል እንደገጠማቸው የሱዳንና የሶማሊያ ሀኔታን በማሳያነት አቅርበዋል።
በአገራችን ኢትዮጵያ እንዲህ ዓይነቱ የሰላም እጦት ስር እንዳይሰድድ የሃይማኖት አባቶች ስለ ሰላም ከመቼውም ጊዜ በበለጠ መሥራት እንደሚጠበቅባቸው ዋና ፀሐፊው ተናግረዋል።
በኬኒያዋ የወደብ ከተማ ሞምባሳ የተጀመረው "የሃይማኖት መሪዎች የአቅም ግንባታ ዐውደጥናት" ዛሬን ጨምሮ ለቀጣይ ሦስት ቀናት እንደሚካሄድ ከስፍራው የሚገኘው ቃል አቀባያችን የላከው መረጃ ያመለክታል።
••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc13

ታህሳስ 12፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ሳኒ 19፣ 1446 ዓ.ሒ

ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጋር በመተባበር ሥልጠና ሰጠ።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጋር በመተባበር ሐሙስ ዕለት የስነ ልቦና ስብራት ለደረሰባቸው ወገኖች በመቐለ ከተማ የማገገሚያ ሥልጠና ሰጠ።
በዓምድና ሆቴል የተሰጠው ይኸው ሥልጠና ተስፋ ሰጪ መኾኑን በጠቅላይ ምክር ቤቱ የሰላም፣ የክልልና የዲያስፖራ ዘርፍ ተጠሪ ሐጅ ሙስጠፋ ናስር ተናግረዋል።
በመቐለ ከተማ በተካሄደው በዚህ ሥልጠና ላይ፣ በክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የተመረጡ ዘጠና ሦስት ተሳታፊዎች መታደማቸውን ሐጂ መስጠፋ ተናግረዋል።
ሐጂ ሙስጠፋ አክለውም፣ በቀጣይ ጠቅላይ ምክር ቤቱ እስከታችኛው የአስተዳዳር እርከን በመውረድ ትኩረት ሰጥቶ የስነ ልቦና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችን ተመሳሳይ ድጋፍ ማድረግ ያስፈልገዋል ብለዋል።
የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክርቤትን አቅም ለማጠናከር ጠቅላይ ምክር ቤቱ በመስከረም 2017 ዓ.ል የተሽከርካሪ ድጋፍ ማድረጉን ሐጂ ሙስጠፋ አስታውሰዋል።
በትግራይ በነበረው ጦርነት ሳቢያ የስነ ልቦና ስብራት የደረሰባቸው ወገኖቻችንን በዘላቂነት ለማቋቋም የሁሉም ባለድርሻ አካላት ትብብር አስፈላጊ መሆኑን ሐጂ ሙስጠፋ ናስር አሳስበዋል::
የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕረዚደንት ሼይኽ አደም እብዱልቃድር "ጠቅላይ ምክር ቤቱ ለክልሉ መጅሊስ እያደረገ ያለውን ሁሉ አቀፍ ድጋፍ ማመስገናቸዉን ና በቀጣይም መሰል ድጋፎች እንዲቀጥሉ "መጠየቃቸውን ሐጂ ሙስጠፋ ተናግረዋል::

••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ሹራ (ምክክር) ማናቸውንም ችግሮች የሚፈታ ጠቃሚ መላ መሆኑን የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት ተናገሩ።

ድሬዳዋ |
የአገራችንን ሰላም ለማረጋገጥ ሹራ (ምክክር) ማናቸውንም ችግሮች የሚፈታ ጠቃሚ መላ መሆኑን የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት ተናገሩ።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ይህን የተናገሩት የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ከድሬዳዋ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጋር በመተባበር፣ "ሃይማኖቶች ለሰላም፣ ለአንድነት፣ ለአብሮነትና ለአገር ግንባታ ያላቸው ሚና" በሚል መሪ ሐሳብ ባዘጋጁት የመጀመሪያው አገር አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ ላይ ነው።
በጉባዔው ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ሹራ (ምክክር) ማናቸውንም ችግሮች የሚፈታ፣ የአገራዊ ሰላም መሠረት የኾነ እጅግ ጠቃሚ መላ መሆኑን ተናግረዋል።
ሰላምን ለማምጣት የሚታየው መነቃቃትና የሚደረገው ጥረት አገርን እና ሕዝባችንን የሚጠቅም በመሆኑ፣ ማንም ተጎጂ ወደማይሆንበት የሰላም መድረክ የሚደረገው ጉዞ አበረታታች መሆኑን ተናግረዋል።
በዚሁ አገር አቀፍ የሰላም ጉባዔ ላይ ሰላም የሃይማኖቶች ተቀዳሚና ዘላቂ ግብ መሆን እንዳለበት የተነገረ ሲኾን፣ የአገሪቱን ሰላም በዘላቂነት አጽንቶ ለማስቀጠል የሃይማኖት አባቶችና ምዕምናን ለሰላም መሥራት ትውልድን የሚያድንና አገርን የሚያረጋጋ መኾኑ በአጽንዖት ተወስቷል።
በጉባዔው ላይ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የተመራው የጠቅላይ ምክር ቤቱ ልዑካን፣ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ የበላይ ጠባቂ አባቶች፣ የሰላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ (ዶ/ር)፣ የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ የተከበሩ አቶ ከድር ጁሃር፣ የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ወይዘሮ ፈትሂያ አደን፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎች እና ዑጋዞች ታድመዋል።
ሁለተኛ ቀን ባስቆጠረው በዚህ የሰላም ኮንፈረንስ ላይ ቀጣዩን አገር አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ የኦሮሚያ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ እንዲያካሂድ ተወስኗል።

ታህሳስ 13፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ሳኒ 21፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የብቸና ከተማ ሙስሊሞች የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላም ምክር ቤትንና የሞጣ ሙስሊሞች መልሶ ማቋቋም እና የልማት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤትን አመሰገኑ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሞጣ ሙስሊሞች መልሶ ማቋቋምና የልማት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት በብቸና ከተማ ሲያስገነባ የቆየው የመድረሳ ሕንጻ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነ።
የመድረሳ ሕንጻ ግንባታውን መጠናቀቅ ተከትሎ የብቸና ከተማ ሙስሊሞች ተወካዮቻቸውን ጠቅላይ ምክር ቤቱ ድረስ በመላክ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የብቸና ከተማ ሙስሊም ማኅበረሰብን ወክለው ምስጋናቸውን ለጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ጸሐፊና ለሞጣ ሙስሊሞች ክትትል ዐብይ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሸይኽ ሐሚድ ሙሳ ያቀረቡት ኢንጅነር መሐመድ ዑመር እና ኢንጅነር ጀማል ሱልጣን ናቸው።
የማኅበረሰቡ ተወካዮች ግንባታዉን የሚያሳይ በተንቀሳቃሽ ምስል የታገዘ ዝርዝር ሪፖርት አቅርበዋል።
በሪፖርታቸውም የከተማዋ ሙስሊሞች የመድረሳ ግንባታው የተከናወነበትን 5 ሺህ ካሬ ሜትር ስፋት ያለው መሬት ከመንግሥት ከተረከቡ በኋላ ለረጅም ጊዜ ምንም ዓይነት የልማት ሥራ ሰይሠሩበት በመቆየቱ በሚመለከተው የመንግሥት አካል ሁለት ጊዜ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ተጽፎ እንደነበረ አስታውሰዋል።
ክስተቱ ህብረተሰቡን መሬቱ ሊነጠቅ ነው የሚል ስጋት ውስጥ በከተተበት ወቅት በጠቅላይ ምክር ቤቱ የሞጣ ሙስሊሞች መልሶ ማቋቋምና የልማት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት አስፈላጊውን የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ የመድረሳው ግንባታ እውን እንዲሆን አድርጓል ብለዋል።
ይህ ድርጊት የክልሉን ሙስሊሞች አንድነት ያጠናከረ እንደሆነ የጠቀሱት የብቸና ከተማ ሙስሊም ማኅበረሰብ ተወካዮች ለተደረገው የገንዘብ ድጋፍ በማኅበረሰቡ ስም ጠቅላይ ምክር ቤቱን እና የመልሶ ማቋቋምና የልማት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱን አመስግነዋል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ እና የሞጣ ሙስሊሞች ክትትል ዐብይ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሸይኽ ሐሚድ ሙሳ የብቸና ሙስሊም ማኅበረሰብ የተሰጠውን ገንዘብ በአግባቡ ለታሰበለት ዓላማ ማዋሉ የሚያስመሠግን መሆኑን ጠቅሰው፣ በልዩ ልዩ ምክንያቶች በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ ሳይጠናቀቁ የቀሩ የሞጣ ፕሮጀክቶች በአጠረ ጊዜ እንዲጠናቀቁ በልዩ ትኩረት እየተሠራ መሆኑን አንስተዋል።
በሞጣ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች ስድስት መስጂዶች፣ መድረሳዎችና የንግድ ማዕከላት እየተገነቡ እንደሆነ ያነሱት ሸይኽ ሐሚድ ሙሳ ለሁሉም ነገር መሠረቱ ሰላም በመኾኑ አላህ ሰላም እንዲያመጣ ዱዓ ልናደርግና ለሰላም ልንሠራ ይገባል ብለዋል።