ኅዳር 9፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ኡላ 17፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
አዲስ አበባ |
ከታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አቅራቢያ መስጂድ ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ መተከል ዞን፣ ጉባ ወረዳ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አቅራቢያ 'አር ረህማን' በመባል የሚጠራ መስጂድ ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ በሕዳሴ ግድብ አቅራቢያ ባምዛ ቀበሌ ለሚሠራው መስጂድ የመሠረት ድንጋዩን በጋራ ያኖሩት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የፈትዋና ምርምር ተጠሪ ሸይኽ እንድሪስ ዓሊ ሁሴን (ደጋን)፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚደንት ሼይኽ ኢብራሒም ሲራጅ እና የአዲስ አበባ መጅሊስ ከፍተኛ አመራሮች መሆናቸው ታውቋል።
ከሕዳሴ ግድብ በቅርብ ርቀት ለመገንባት መሠረት የተቀመጠለት መስጂድ በአካባቢው ለሚገኘው ሙስሊም ማኅበረሰብ ትልቅ ጠቀሜታ እንደሚሰጥ በገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቱ ላይ በስፋት ተነግሯል።
ሙስሊሙን ማኀበረሰብ ለማገልገል የሚገነባውን 'አርረህማን' መስጂድ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መጅሊስ በተጨማሪ በአቅራቢያው የሚገኘው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ጽ/ቤት በትብብር እንደሚገነባ ተነግሯል።
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ልዑካን ውስጥ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የዑለማ ጉባዔ ጽ/ቤት ኃላፊ ሸይኽ ሙሐመድዘይን ዛኽረዲን፣ በጠቅላይ ምክር ቤቱ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተወካይ የፌደራል መጅሊስ የሥራ አስፈፃሚ አባልና የተቋማትና ማሕበራት ዘርፍ ተጠሪ ሸይኽ አልመርዲ አብዱላሂ እና የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሸይኽ ሑሴን ሐሰን ተገኝተዋል።
ከታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ከአንድ ኪሎ ሜትር ባልበለጠ ርቀት ላይ ለሚገነባው መስጂድ ግንባታ የመሠረት ድንጋይ በተቀመጠበት ስነ ሥርዓት ላይ የአዲስ አበባ መጅሊስ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የባምዛ ቀበሌ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

ኅዳር 10፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ኡላ 18፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
በጠቅላይ ምክር ቤቱ ግቢ ለሚገነባው የአፓርትመንት ሕንጻ የዲዛይን ጨረታውን ካሸነፈው ድርጅት ጋር የውል ስምምነት ተፈረመ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በቅጥረ ግቢው ውስጥ ለሚያስገነባው ባለ 2 ምድር ቤት እና ባለ 13 ወለል የአፓርትመንት ሕንጻ የዲዛይን ጨረታውን ካሸነፈው QTC ኤንጅነሪንግ ኮንሰልታንሲ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት ጋር ዛሬ የውል ስምምነት ተፈራረመ።
ስምምነቱን በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በኩል ዋና ሥራ አስኪያጁ ሐጂ ከማል ሐሩን ሲፈርሙ፣ በQTC ኤንጅነሪንግ ኮንሰልታንሲ በኩል የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ መሐመድ ሐሰን ፈርመዋል።
QTC ኢንጅነሪንግ ኮንሰልታንሲ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት የሕንጻ ዲዛይኑን በውሉ መሠረት ሠርቶ ሲያቀርብ የግንባታ ጨረታ ወጥቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ግንባታ እንደሚገባ ተነግሯል።
••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1

Telegram
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
በ1446 ዓ.ሒ (2017 ዓ.ል) የሐጅ ጉዞ ለማድረግ ላሰባችሁ የአሏህ እንግዶች።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በ1446 ዓ.ሒ (በ2017 ዓ.ል) የሐጅ ጉዞ ለማድረግ ያሰቡ የአሏህ እንግዶችን ምዝገባ ለመጀመር ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል።
ስለሆነም በዘንድሮው ዓመት የሐጅ ጉዞ ለማድረግ ያሰባችሁ የአሏህ እንግዶች፣ ከአሁን በፊት ፓስፖርት የሌላችሁ ከወዲሁ እንድታወጡ፣ ፓስፖርት ኖሯችሁ ነገር ግን የአገልግሎት ጊዜዉ ሊያበቃ ከአንድ ዓመት በታች የቀረው ከኾነ ከወዲሁ በአቅራቢያችሁ በሚገኘው የኢምግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በመቅረብ እንድታሳድሱ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ለማስታወስ ይወዳል።

Oduu Gammachiisaa Keessummoota Rabbii Bara 1446 AH (2017 AH) Hajjii Gochuuf Niyyatan Hundaaf.
Manni Marii Waliigalaa Dhimmoota Islaamaa Itoophiyaa bara 1446 AH (Dh.K.D bara 2017) galmee keessummoota Rabbii fedhii Hajjii godhuu qaban yeroo dhiyootti eegaluuf qophii xumuraa jira.
Kanaafuu, keessummoonni Rabbii bara kana Hajjii gochuuf niyyatan; Warri kanaan dura paaspoortii hin qabne, Paaspoortii yoo qabaattan ,garuu yeroon hojiirra ooluu waggaa tokkoo gadi yoo hafe, tajaajila immigireeshinii fi lammummaa isinitti dhihoo jirutti haaromsa akka gootan asumaan cimsinee isin beeksifna.
Mana Marii Waliigalaa Dhimmoota Islaamaa Itiyoophiyaa Damee Hajjii fi Umraa Irraa

ጥቅምት 14፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ኡላ 21፣ 1446ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጠቅላይ ምክር ቤቱ በአዳማ በትምህርት ሥራ መመሪያ አተገባበር ላይ የውይይት መድረክ አካሄደ።

አዳማ |
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የትምህርትና ማኅበራዊ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የትምህርት ክፍል በትምህርት ሥራ መመሪያ አተገባበር ላይ የውይይት መድረክ አዘጋጀ።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ የትምህርትና ማኅበራዊ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የትምህርት ክፍል ባዘጋጀው በዚህ የውይይት መድረክ ላይ የኦሮሚያ መጅሊስ፣ የዞን መጅሊስ ተወካዮች እና ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ኾነዋል።
በመርኃግብሩ መክፈቻ ላይ የኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚደንት ሸይኸ ዚያድ አልይ
ባደረጉት ንግግር በሙስሊሙ ማኅበረሰብ ውስጥ ለትምህርት በተሰጠው የተዛባ አመለካከት ሳቢያ ብዙዎች ከትምህርቱ ርቀው ወይም ስልታዊ በኾነ መንገድ ተገፍተው ቆይተዋል ብለዋል።
ምክትል ፕሬዚደንቱ ሸይኸ ዚያድ አልይ የሀገሪቱ ሙስሊሞች በአካዳሚክ ዘርፉ ሚናችን የሳሳ መኾኑ እንደ ሀገር ብዙ ዋጋ እያስከፈለን ነው ሲሉ ተናግረዋል።
አያይዘውም ጠቅላይ ምክር ቤቱ ሰፊ ቁጥር ያለው ሙስሊም ማኀበረሰብ መሪ በመኾኑ፣ ከዲን ትምህርት በተጨማሪ በአካዳሚክ ትምህርት ላይ ያለውን ክፍተት የመፍታት ሚና ይጫወት ዘንድ በትምህርት ሥራ መመሪያ ላይ ውይይት መደረጉ ትልቅ ኃላፊነትን የመወጣት ሥራ በመኾኑ ሊመሰገን ይገባል ብለዋል።
የዳይሬክቶሬቱ የትምህርትና ሥልጠና ኃላፊ አቶ ሙሐመድ ይመር ረቂቅ የትምህርት ሥራ መመሪያውን አስመልክተው ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች ማብራሪያውን መነሻ ያደረጉ የግብዓት ሐሳቦችና ጥያቄዎችን ለመድረኩ አቅርበዋል።
የመድረኩ አወያይና የዳይሬክቶሬቱ የትምህርትና ሥልጠና ባለሙያ የኾኑት አቶ ዓሊ ሁሴን፣ አቶ መሐመድ ይመር፣ ወይዘሮ ነስራ ነኢም ለማብራሪያና ለጥያቄዎች መልስ ሰጥተዋል።
በመጨረሻም በቀረበው የትምህርት ሥራ መመሪያ አተገባበር ላይ ያተኮረ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።
የመግባቢያ ሰነዱን በኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በኩል የምክር ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሐጂ መሐመድ ጋሊ ሲፈርሙ፣ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በኩል የትምህርትና ማኅበራዊ አገልግሎት ዳሬክትሬት የትምህርት ክፍል አቶ መሐመድ ይመር ፈርመዋል።
••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጠቅላይ ምክር ቤቱ በአዳማ በትምህርት ሥራ መመሪያ አተገባበር ላይ የውይይት መድረክ አካሄደ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዳማ |
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የትምህርትና ማኅበራዊ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የትምህርት ክፍል በትምህርት ሥራ መመሪያ አተገባበር ላይ የውይይት መድረክ አዘጋጀ።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ የትምህርትና ማኅበራዊ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የትምህርት ክፍል ባዘጋጀው በዚህ የውይይት መድረክ ላይ የኦሮሚያ መጅሊስ፣ የዞን መጅሊስ ተወካዮች እና ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ኾነዋል።
በመርኃግብሩ መክፈቻ ላይ የኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚደንት ሸይኸ ዚያድ አልይ
ባደረጉት ንግግር በሙስሊሙ ማኅበረሰብ ውስጥ ለትምህርት በተሰጠው የተዛባ አመለካከት ሳቢያ ብዙዎች ከትምህርቱ ርቀው ወይም ስልታዊ በኾነ መንገድ ተገፍተው ቆይተዋል ብለዋል።
ምክትል ፕሬዚደንቱ ሸይኸ ዚያድ አልይ የሀገሪቱ ሙስሊሞች በአካዳሚክ ዘርፉ ሚናችን የሳሳ መኾኑ እንደ ሀገር ብዙ ዋጋ እያስከፈለን ነው ሲሉ ተናግረዋል።
አያይዘውም ጠቅላይ ምክር ቤቱ ሰፊ ቁጥር ያለው ሙስሊም ማኀበረሰብ መሪ በመኾኑ፣ ከዲን ትምህርት በተጨማሪ በአካዳሚክ ትምህርት ላይ ያለውን ክፍተት የመፍታት ሚና ይጫወት ዘንድ በትምህርት ሥራ መመሪያ ላይ ውይይት መደረጉ ትልቅ ኃላፊነትን የመወጣት ሥራ በመኾኑ ሊመሰገን ይገባል ብለዋል።
የዳይሬክቶሬቱ የትምህርትና ሥልጠና ኃላፊ አቶ ሙሐመድ ይመር ረቂቅ የትምህርት ሥራ መመሪያውን አስመልክተው ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች ማብራሪያውን መነሻ ያደረጉ የግብዓት ሐሳቦችና ጥያቄዎችን ለመድረኩ አቅርበዋል።
የመድረኩ አወያይና የዳይሬክቶሬቱ የትምህርትና ሥልጠና ባለሙያ የኾኑት አቶ ዓሊ ሁሴን፣ አቶ መሐመድ ይመር፣ ወይዘሮ ነስራ ነኢም ለማብራሪያና ለጥያቄዎች መልስ ሰጥተዋል።
በመጨረሻም በቀረበው የትምህርት ሥራ መመሪያ አተገባበር ላይ ያተኮረ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።
የመግባቢያ ሰነዱን በኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በኩል የምክር ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሐጂ መሐመድ ጋሊ ሲፈርሙ፣ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በኩል የትምህርትና ማኅበራዊ አገልግሎት ዳሬክትሬት የትምህርት ክፍል አቶ መሐመድ ይመር ፈርመዋል።
••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
Telegram
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
ሕዳር 14፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ኡላ 21፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
በዓሊሞች ጉባዔ ሲሰጥ የነበረው የአመራርና የክህሎት ሥልጠና ተጠናቀቀ።

ጋምቤላ |
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዓሊሞች ጉባዔ ጽሕፈት ቤት አማካይነት ለጋምቤላ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የሥራ ኃላፊዎች፣ የመስጂድ ኢማሞች፣ ዑስታዞችና ዱዓቶች ሲሰጥ የነበረው የአመራርና የዳዕዋ ክህሎት ሥልጠና ተጠናቀቀ።
ከሕዳር 12፣ 2017 ዓ.ል ጀምሮ በጋምቤላ ከተማ ጊዋ ሆቴል ለተከታታይ ሦስት ቀናት የተሰጠው ይህ የአቅም ግንባታ ሥልጠና ውጤታማ እንደነበር በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የክልልና ዲያስፖራ ዘርፍ ምክትል ኃላፊና የጋምቤላ ክልል ተወካይ ሸይኽ ዛኪር ኢብራሂም ተናግረዋል።
ይህ ሥልጠና በክልሉ ለሚገኙ ዓሊሞች ሲሰጥ የመጀመሪያ መሆኑን የተናገሩት ሸይኽ ዛኪር፣ በክልሉ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ሥልጠናው በቀጣይ ጊዜያት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
የጋምቤላ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚደንት ሸይኽ በሽር ሑሴን ኢብራሂም ከጠቅላይ ምክር ቤቱ የዓሊሞች ጉባዔ በተውጣጡ ዓሊሞች የተሰጠው ሥልጠና ለሠልጣኞቹ ቀጣይ ሥራዎች አቅም እንደሚሆን ተናግረዋል።
የፌደራሉ የዓሊሞች ጉባዔ በክልሉ የዳዕዋ ሥራን ለዑማው ተደራሽ ለማድረግ በቀጣይም ተከታታይ የአመራርና የዳዕዋ ክህሎት ማሳደጊያ ሥልጠናዎች መዘጋጀት ይገባቸዋል ብለዋል።
••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።

ትዊተር | https://x.com/eiasc13

•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የዋኮ ሞጌሾ ቤተሰቦች ሃያ ሺህ ሜትር ካሬ መሬት ለሶዶ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ወቅፍ አደረጉ።

ሶዶ |
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ወላይታ ዞን፣ ሶዶ ከተማ ነዋሪ የኾኑት የአቶ ዋኮ ሞጌሾ ልጆችና የልጅ ልጆች ከአያት ቅድመ አያቶቻቸው ሲወራረስ የመጣውን ሃያ ሺህ ሜትር ካሬ መሬት ለዲን አገልግሎት እንዲውል ለከተማው እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ወቅፍ አደረጉ።
በሶዶ ከተማ ኮካቴ ወዞ ቀበሌ ነዋሪ የኾኑት የአቶ ዋኮ ሞጌሾ ልጆችና የልጅ ልጆች የአያት ቅድመ አያቶቻቸው ይዞታ ኾኖ የተላለፈላቸውን መሬት ለሙስሊሙ ማኅበረሰብ መንፈሳዊ አገልግሎት እንዲውል ወቅፍ በማድረግ ትናንት (እሑድ) ለሶዶ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በይፋ አስረክበዋል።
የአቶ ዋኮ ሞጌሾ ልጅና የደቡብ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት የኾኑት ሸይኽ ዑስማን ዋኮ አሕመድ በርክክቡ ወቅት የአቶ ዋኮ ሞጌሾ ልጆችና የልጅ ልጆች ይህን መሬት ከአያት ቅድመ አያቶቻቸው በውርስ ማግኘታቸውን ተናግረዋል።
የቤተሰቡ አባላት በደቡብ ክልላዊ መንግሥት፣ በወላይታ ዞን የመጀመሪያ ደረጃ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ቀርበው በወቅፍ ያስተላለፉትን መሬት የሶዶ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት እንዲያስተዳድረው ማስወሰናቸውን ሸይኽ ዑስማን ዋኮ ተናግረዋል።
ሼይኽ ዑስማን አክለውም በአካባቢው ከጊዜ ወደጊዜ የዲን ትምህርት የሚስሰጥባቸው ማዕከላት (መርከዞች) ቁጥር በማነሳቸው ምክንያት የአካባቢው ሙስሊም ማኅበረሰብ አባላት ሃይማኖታዊ እውቀት (ኢልም) ፍለጋ ራቅ ወዳለ አካባቢ ለመሄድ መገደዳቸውን ተናግረዋል።
ከብዙ ዓመታት በፊት በቅድመ አያቶቻቸው ኑዛዜ ወቅፍ የተደረገው ሃያ ሺህ ሜትር ካሬ መሬት፣ በአካባቢው ያለውን የዒልም ማዕከላት እጥረት ለመቅረፍ እና ለሙስሊሙ ማኅበረሰብ መንፈሳዊ አገልግሎት እንዲውል ማስረከባቸውን ሸይኽ ዑስማን ተናግረዋል።
ከአቶ ዋኮ ሞጌሾ ልጆችና የልጅ ልጆች የተሰጠውን የወቅፍ ቦታ የተረከቡት የሶዶ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ሰብሳቢ ሼይኽ አንዋር አወል፣ በአካባቢው የመስጂድና የእስላማዊ ትምህርት ማዕከላት (መድረሳ) ቁጥር አነስተኛ መሆኑን ተናግረዋል።
ሼይኽ አንዋር በዚሁ ጊዜ ወቅፉን ላበረከቱት የአቶ ዋኮ ሞጌሾ ልጆችና የልጅ ልጆች ፈጣሪያችን አሏህ (ሱ.ወ.) የሁለት ዓለም ምንዳ እንዲመነዳቸው ዱዓ አድርገዋል።
ከአቶ ዋኮ ሞጌሾ ልጆችና የልጅ ልጆች ለከተማው ሙስሊም ማኅበረሰብ በወቅፍ በተበረከተው ቦታ ላይ በአጭር ጊዜ ውስጥ ደረጃውን የጠበቀ መስጂድና መድረሳ ተገንብቶ መንፈሣዊ አገልግሎት እንዲሰጥ መላው ሙስሊም ማኅበረሰብ የድጋፍ እጁን እንዲዘረጋ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
በወቅፍ ርክክቡ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ዓሊሞች ጉባዔ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሸይኽ ሙሐመድዘይን ዘኽረዲን፣ "ላለፉት 37 ዓመታት በዳዕዋ ዘርፍ ኢትዮጵያ ውስጥ ተንቀሳቅሻለሁ፣ ነገር ግን እንዲህ ዓይነት ሰፊ መሬት በወቅፍ የሰጠ አንድም ቤተሰብ አላጋጠመኝም" በማለት ስሜታቸውን አጋርተዋል።
ሸይኽ ሙሐመድዘይን አያይዘውም "እነዚህ ቤተሰቦች የአያት ቅድመ አያቶቻቸውን የኑዛዜ ቃል አክብረው መሬታቸውን ለሙስሊሙ ማኅበረሰብ ሰጥተዋል፤ መላው ሙስሊም ማኅበረሰብ ደግሞ በመሬቱ ላይ የመስጂድና መድረሳ ግንባታው ሥራ ላይ እንዲረባረብ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
በወቅፍ ርክክብ መርኃግብሩ ላይ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ሥራ አስፈጻሚዎች፣ ከሻሸመኔና ከወላይታ ሶዶ የመጡ መሻዒኾች እና ዓሊሞች፣ እንዲሁም የአከባቢው ማኅበረሰብ መታደማቸውን ከክልሉ እስልምና ጉዳዮች ሕዝብ ግንኙነት የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

ሕዳር 19፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ኡላ 26፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የጠቅላይ ምክር ቤቱ የማኅበራዊ አገልግሎት ዘርፍ ለአካል ጉዳተኞች ማኅበር የአቅም ግንባታ ሥልጠና መስጠት ጀመረ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የማኅበራዊ አገልግሎት ዘርፍ ለአካል ጉዳተኞች ማኅበራት የሥራ ኃላፊዎች የሁለት ቀናት የአቅም ግንባታ ሥልጠና መስጠት ጀመረ።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሥራ አስፈጻሚ አባልና የፈትዋና ምርምር ዘርፍ ተጠሪ ሼይኽ ኢድሪስ አሊ ሑሴን (ደጋን) በሥልጠናው መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ አካል ጉዳተኝነት በተፈጥሮና ከጊዜ በኋላ ሊመጣ የሚችል ክስተት መኾኑን አስታውሰዋል።
በእስልምና ታሪክ ውስጥ አካል ጉዳተኛ ኾነው ትልቅ ገድል ያስመዘገቡ የነቢያችን ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) ተከታዮች እንደነበሩ የተናገሩት ሼይኽ ኢድሪስ፣ ለአብነት የአብደሏህ ኢብኑ ዑሚ መኽቱም ገድል ከፍተኛ እንደነበረ አውስተዋል።
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዓሊሞች ጉባዔ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የኾኑት ሼይኽ ሙሐመድዘይን ዘኽረዲን ጠቅላይ ምክር ቤቱ በአዋጅ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የሙስሊሙን ማኅበረሰብ ሃይማኖታዊና ልማታዊ ጥያቄዎች ለመፍታት እየተጋ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በተለያየ ምክንያት የአካል ጉዳት የገጠማቸውን ወገኖች በማደራጀት ሃይማኖታዊና ዓለማዊ ችግሮቻቸው እንዲፈቱ ጠቅላይ ምክር ቤቱ የሚያደርገው ጥረት ይበል የሚያሰኝ እንደኾነ ሼይኽ ሙሐመድዘይን ተናግረዋል።
አካል ጉዳተኝነት አለመቻል ማለት እንዳልኾነ ከሚያሳዩ ምሳሌዎች ውስጥ የታዋቂው ዓሊም የሼይኽ ኢብኑ ባዝን ገድል ያወሱት ሼይኽ ሙሐመድዘይን፣ በቀጣዮቹ ጊዜያት በእነዚህ ማኅበራት አማካይነት ብዙ ባለራዕዮች ይፈጠራሉ ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።
ለዚህም እውን መኾን የሚመለከታቸው ሁሉ የበኩላቸውን አስተዋፅዖና እገዛ እንዲያበረክቱ ሼይኽ ሙሐመድዘይን ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የተቋማት እና ማኅበራት ዳይሬክቶሬት ስር ተመዝግበው ከሚንቀሳቀሱ የበጎ አድራጎት ማኅበራት አራቱ የአካል ጉዳተኞች ማኅበራት ናቸው።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ የማኅበራዊ አገልግሎት ዘርፍ ለአካል ጉዳተኞች ማኅበራት የሥራ ኃላፊዎች እየሰጠ የሚገኘውና በአብደላ ኢብኑ ዑሚ መኽቱም ሕፃናት የዐይነ ስውራን አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በቁርኣን የተከፈተው ሥልጠና በዛሬው ዕለት ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ሕዳር 18፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ኡላ 25፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጠቅላይ ምክር ቤቱ መላውን ሙስሊም ማኅበረሰብ በእኩልነት የማገልገል ተልዕኮና ኃላፊነቱን ለመወጣት በትጋት መሥራቱን እንደሚቀጥል ተነገረ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እስከ ታች ድረስ ባሉት መዋቅሮቹ መላውን ሙስሊም ማኅበረሰብ በእኩልነት የማገልገል ተልዕኮና ኃላፊነቱን ለመወጣት በትጋት መሥራቱን እንደሚቀጥል የምክር ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ተናገሩ።
ዋና ሥራ አስኪያጁ ሐጂ ከማል ሐሩን ይህን የተናገሩት የጠቅላይ ምክር ቤቱ የማኅበራዊ አገልግሎት ዘርፍ ለአካል ጉዳተኞች ማኅበራት አመራሮች ያዘጋጀው የሁለት ቀናት የአቅም ግንባታ ሥልጠና ዛሬ ሲጠናቀቅ ባደረጉት ንግግር ነው።
ሐጂ ከማል ሐሩን የሙስሊሙ ማኅበረሰብ አካል የኾኑትን አካል ጉዳተኛ ወገኖች በማገልገል ዓላማ ለተቋቋሙ ማኅበራት ተከታታይነት ያለው ሥልጠና በመስጠት አቅማቸውን ማሳደግ አስፈላጊ እንደኾነ ጠቅላይ ምክር ቤቱ
ይገነዘባል ብለዋል።
ጠቅላይ ምክር ቤቱ አካል ጉዳተኛ ወንድምና እህቶቻችን በተለያዩ መልኮች የሚደርሱባቸውን ማነቆዎች ለማስቀረት የሚያስችሉ ተከታታይነት ያላቸው የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎች ማዘጋጀቱን እንደሚቀጥልም ሐጂ ከማል ተናግረዋል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ የማኅበራዊ አገልግሎት ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር ተውፊቅ ቢራራ፣ ዘርፉ እስላማዊ እሴቶችን መሠረት ያደረገ ማኅበረሰባዊ ተሳትፎን ይበልጥ በማጎልበት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን እየሠራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሁሉም ዘርፎችና ዳይሬክቶሬቶች በሚሠሯቸው ሃይማኖታዊና የልማት ሥራዎች አካል ጉዳተኛና ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ወገኖቻችንን ተሳታፊነት የሚያረጋግጡ እንዲኾኑ በትብብር እየሠሩ መኾኑን ዶክተር ተውፊቅ ተናግረዋል።
በቀጣይም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት በአካል ጉዳተኞችና ልዩ ፍላጎት ባላቸው ወገኖቻችን መንፈሣዊ እና ዓለማዊ ሕይወት ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል የአሠራር ሥርዓት እንዲኖር ዘርፉ ተጠናክሮ እንደሚሠራ ዶክተር ተውፊቅ ተናግረዋል።

ሕዳር 22፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ኡላ 29፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
"የሸሪዓ ፍርድ ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ የሚሻሻልበት አዲስ ረቂቅ ይዘጋጃል።"
- የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት

በሸሪዓ ፍርድ ቤቶች ውስጥ የሚታዩ ችግሮችን መርምሮ የመፍትኄ ሐሳብ እንዲያቀርብ የተቋቋመው ኮሚቴ በዛሬው ዕለት ጥናቱን ለባለድርሻ አካላት አቀረበ።
ኮሚቴው "የሸሪዓ ፍርድ ቤቶች የሕግ ማዕቀፍ፣ አደረጃጀት እና የሰው ኃይል አስተዳደር" በሚል ርዕስ ያጠናቀረውን ጥናት ክቡር አቶ መሐመድ አሕመድ ያቀረቡ ሲኾን፣ በሸሪዓ ፍርድ ቤቶች የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚታዩ ችግሮችን በተመለከተም በሕግ ባለሙያው አቶ አብዱልሀኪም ጀማል የተዘጋጀ የጥናት ሰነድ ቀርቦ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጓል።
በቀረቡት ጥናቶች ላይ ከሕግ ባለሙያዎችና ከባለድርሻ አካላት ሰፋ ያሉ አስተያየቶችና ተሻሽሎ ለሚዘጋጀው የማቋቋሚያ አዋጅ ግብዓት የሚኾኑ ሐሳቦች ቀርበዋል።
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት አቶ ቴዎድሮስ ምህረት ወደ ኃላፊነት ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ ትኩረት ካደረጉባቸው ጉዳዮች አንዱ የሸሪዓ ፍርድ ቤቶች የአሠራር ሁኔታን ማሻሻል መኾኑን ተናግረዋል።
"የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሸሪዓ ፍርድ ቤቶች ውስጥ ከሕግ፣ ከአደረጃጀት እና ከሰው ኃይል አስተዳደር አኳያ የሚታዩ ክፍተቶችን ለመድፈን ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጋር በቅርበት አየሠራ ነው" ሲሉም ተናግረዋል።
ፕሬዚደንቱ አክለውም፣ "በዚህ የውይይት መድረክ ላይ በአካል መገኘቴ ጉዳዩን ከባለድርሻ አካል አኳያ ሁኔታውን በትኩረትና በቅርበት ለማየት አስችሎኛል" ብለዋል።
አያይዘውም የቀረቡትን ጥናቶች እና ከተሳታፊዎች የተሰጡ ግብዓቶችን መሠረት በማድረግ የሸሪዓ ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ የሚሻሻልበት አዲስ ረቂቅ ማዘጋጀት መጀመር አለበት ብለዋል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የኢትዮጵያ መስሊም ሃይማኖታዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ የሚዳኝበት የሸሪዓ ፍርድ ቤት ክብሩ የተጠበቀ እና ዘመኑን የዋጀ እንዲኾን ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
ክቡር ፕሬዚደንቱ አክለውም በሸሪዓ ፍርድ ቤት የማቋቋሚያ አዋጅ ላይ ያሉ ክፍተቶች ተገቢውን ትኩረት እንዲያገኙ ለማስቻል በተደረገው ጥረት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት ላደረጉት ትብብር አመስግነዋል።
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የፕሬዚደንቱ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የኾኑት ዑስታዝ አቡበከር አሕመድ በዚሁ ጊዜ የኢትዮጵያ ሙስሊም ማኅበረሰብ ከሸሪዓ ፍርድ ቤቶች ጋር ያለውን የትስስር ታሪክ አውስተዋል።
ዑስታዝ አቡበከር አክለውም በሸሪዓ ፍርድ ቤቶች ውስጥ የሚታዩ ዐበይት ችግሮችን በመለየት የሕግ፣ የአደረጃጀት እና የሰው ኃይል አስተዳደርን በተመለከተ ማሻሻያ የሚፈልጉ ጉዳዮችን ለመለየት የተቋቋመውን ኮሚቴ አመሠራረት፣ በኮሚቴው የተደረጉ ጥናቶችን እና ከባለድርሻ አካላት ጋር የተካሄዱ የውይይት ሂደቶችን አስመልክቶ ሰፋ ያለ ማብራሪያ አቅርበዋል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ በውይይቱ ላይ የተገኙ የሕግ ባለሙያዎችና የባለድርሻ አካላት ተወካዮችን አመስግነው ጥናቱ ከመድረኩ ተሳታፊዎች በተሰጡ ግብዓቶች ዳብሮ፣ ሕገ መንግሥትን መሠረት ባደረገ መልኩ የሸሪዓ ፍርድ ቤቶችን አሠራር፣ አደረጃጀት እና የሰው ኃይል አስተዳደር ሕዝበ-መስሊሙን ያማከለ ለማድረግ የተጀመረው ጥረት ፍሬ እስከሚያፈራ ይቀጥላል ብለዋል።
በዘመናዊት ኢትዮጵያ የሸሪዓ ፍርድ ቤቶች ሕጋዊ አውቅና አግኝተው በመጀመሪያ የተቋቋሙት ከዛሬ 85 ዓመት በፊት በታወጀው አዋጅ ቁጥር 2/1934 ነው።

ኅብረተሰቡ ለመቄዶንያ የአዕምሮ ህሙማንና የአረጋውያን መርጃ ማኅበር ሁሉንአቀፍ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ቀረበ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ለመቄዶንያ የአዕምሮ ህሙማንና የአረጋውያን መርጃ ማኀበር የበኩሉን ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቀረበ።
ጥሪው የቀረበው የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ አባል ቤተ-እምነቶችና የመቄዶንያ የአዕምሮ ህሙማንና የአረጋውያን መርጃ ማኀበር አባላት ለአገር ሰላም ፀሎት ባደረጉበትና ለማኅበሩ ድጋፍ ማሰባሰቢያ በተዘጋጀው መርኃግብር ላይ ነው።
በመርኃግብሩ ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን በመወከል የተገኙት የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ና የሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ተጠሪው ሼይኽ ሑሴን ሐሰን ነቢያችን ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) ለዓለማት እዝነት የተላኩ መኾናቸውን አውስተው፣ መስሊሙ ማኅበረሰብ መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማኅበር እየሠራ ለሚገኘው የበጎ አድራጎት ሥራ ውጤታማነት ድጋፍ የማድረግ ሃይማኖታዊ ኃላፊነት አለበት ብለዋል።
የመቄዶንያ የአዕምሮ ህሙማንና የአረጋውያን መርጃ ማኀበር መሥራችና ኃላፊ የክብር ዶክተር ቢንያም በለጠ ማዕከሉ አዲስ አበባን ጨምሮ በአርባ አራት ከተሞች ከ8 ሺህ በላይ ራሳቸውን ችለው መንቀሳቀስ የማይችሉ የአልጋ ቁራኛ አረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማንን ከጎዳና በማንሳት በመንከባከብ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
መቄዶንያ የአዕምሮ ህሙማንና የአረጋውያን መርጃ ማኀበር ዘር፣ ሃይማኖት እና ፆታ ሳይለይ ሰብዓዊ አገልግሎት የሚሰጥ የበጎ አድራጎት ድርጅት መኾኑን የጠቀሱት ክቡር ዶክተር ቢኒያም፣ በአሁኑ ጊዜ 2 ሺህ 900 የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ወገኖች በማዕከሉ እንክብካቤ እየተደረገላቸው እንደሚገኙ ተናግረዋል።
ክቡር ዶክተር ቢኒያም አክለውም ተቋሙ በማዕከሉ የሚገኙ ሙስሊሞች የሃይማኖት እውቀታቸውን ለማጎልበት የዲን ትምህርት አንዲማሩና ሶላታቸውን እንዲሰግዱ በማዕከሉ ግቢ ዉስጥ መስጂድ በማቋቋምና ዑስታዞችን በመቅጠር አገልግሎት እየሰጠ መኾኑንም ተናግረዋል።
ማኅበሩ በቀጣይ ጊዜያት ቅርንጫፎቹን ወደ 244 ለማሳደግ እየሠራ እንደሚገኝም የክብር ዶክተር ቢኒያም ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት የጋራ ጉባዔ ዋና ፀሐፊ የኾኑት ቀሲስ ታጋይ ታደለ ጉባዔው ለአገር ሰላም በጋራ እየሠራ መሆኑን ጠቅሰው፣ በአገራችን አንዳንድ ቦታዎች ላይ እየታየ ያለው የሰላም እጦት እንዲያበቃ የጋራ ጉባዔው አባል ቤተ-እምነቶች በመቄዶንያ ከሚኖሩ ወገኖቻችን ጋር የዛሬውን የፀሎትና የዱዓ መርኃግብር ማዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
መቄዶንያ የአዕምሮ ሕሙማንና የአረጋውያን መርጃ ማዕከል "ሰውን ለመርዳት፣ ሰው መኾን በቂ ነው" በሚል ወርቃማ መርኅ በታሕሣሥ ወር 2002፣ አሥር ሰዎችን በመንከባከብ ሥራውን የጀመረ የበጎ አድራጎት ድርጅት መሆኑ ተነግሯል።
ዛሬ በመቄዶንያ የአዕምሮ ህሙማን እና የአረጋውያን መርጃ ማዕከል ግቢ ውስጥ ለአገር ሰላም በተደረገው ፀሎት እና ለማዕከሉ የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርኃግብር ላይ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት የበላይ ጠባቂ አባቶች፣ የቦርድ አባላት፣ እንዲሁም የሃይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።

ሕዳር 25፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ሳኒ 2፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ሥራ አስፈጻሚ ዓመታዊ የሥራ ግምገማ ተጀመረ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ሥራ አስፈጻሚ ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ (ተቅዪም) ኮምቦልቻ ከተማ በልዑል መኮንን ሆቴል መሰብሰቢያ አዳራሽ እየተካሄደ ነው።
ዛሬ የተጀመረውና በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚደንት ሼይኽ አብዱልአዚዝ ሼይኽ አብዱልወሊ የተመራው የአማራ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ሥራ አስፈጻሚ ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ በ2016 ዓ.ል በምክር ቤቱ በተከናወኑ ሥራዎች ላይ ትኩረት አድርጓል።
ግምገማው በ2016 ዓ.ል. የተመዘገቡ ውጤቶችን አጠናክሮ በማስቀጠልና የታዩ ውሱንነቶችን ለይቶ የማስተካከያ እርምጃ በመውሰድ በ2017 ዓ.ል. ለክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ካለፈው ዓመት የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግብ አቅም እንደሚፈጥርለት ምክትል ፕሬዚደንቱ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ነሐሴ 18፣ 2016 ዓ.ል. በአዲስ አበባ ባደረገው የ2ኛ ዓመት፣ 4ኛ መደበኛ ጉባዔ ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት የክልልና የከተማ አስተዳደር የእስልምና ጉዳይ ምክር ቤቶች የ2016 ዓ.ል. የሥራ አፈጻጸማቸውን እንዲገመግሙ መወሰኑ ይታወሳል።
በኮምቦልቻ ከተማ በተጀመረው የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ዓመታዊ ግምገማ ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሥራ አስፈፃሚ አባል፣ የፈትዋና ምርምር ዘርፍ ተጠሪና የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ተወካይ ሼይኽ ኢድሪስ ዓሊ ሑሴን (ደጋን) እና የሰላምና ዲያስፖራ ዘርፍ ተጠሪው ሐጂ ሙስጠፋ ናስር ተገኝተዋል።
ዛሬ በኮምቦልቻ ከተማ የተጀመረው የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ በነገው ዕለትም እንደሚቀጥል በስፍራው የሚገኘው ቃል አቀባያችን የላከው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት 'የዋናው መግቢያ በር እና አጥሩን' እንዲሁም በጠቅላይ ምክር ቤቱ ለሚሰራው 'መስጂድ' ለወጣው ጨረታ አሸናፊው ታወቀ።
በዚህ የዲዛይን እና የአማከሪ ጨረታ አሸናፊ'ARCHI' ዲዛይን+ኮንሰልታሲ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኀበር የጨረታው አሸናፊ ሆኗል። 👇

ሕዳር 26፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ሳኒ 3፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ዑስታዝ አቡበከር አሕመድ የሸይኻ ፋጢማ ቢንት ሙባረክ ዓይነ‐ሥውራን አዳሪ ትምህርት ቤትን ጎበኙ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የፕሬዚደንቱ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዑስታዝ አቡበከር አሕመድ ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ጋር በመኾን ክብርት ሸይኻ ፋጢማ ቢንት ሙባረክ የዐይነ‐ስውራን አዳሪ ትምህርት ቤትን ጎበኙ።
ዑስታዝ አቡበከር በጉብኝታቸው ወቅት የትምህርት ቤቱ ሙስሊም ተማሪዎች የጀመዓ ሶላት የሚሰግዱበት ቦታ ተመቻችቶላቸው በጋራ ሲሰግዱ ማየታቸውን ተናግረዋል።
ይህን መሰል ተቋም ሁሉንም የማኅበረሰብ ክፍሎች እኩል ተጠቃሚ የሚያደርግ መኾኑ የሚደገፍ እንደኾነ የጠቀሱት ዑስታዝ አቡበከር፣ ክፍተቶችን ሲኖሩም ጠቅላይ ምክር ቤቱ ክፍተቶቹን ለመሙላትና ችግሮችን በጋራ ለመፍታት የሁልጊዜ ጥረቱ መሆኑን ተናግረዋል።
"በጉብኝታችን ወቅት በትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህርት አማካኝነት ተቋሙ ለተማሪዎቹ የሚሰጠውን አገልግሎት ተዟዙረን ተመልክተናል" ያሉት ዑስታዝ አቡበከር፣ "ተቋሙ በከፍተኛ ጥንቃቄ ደረጃውን ጠብቆ የተሠራ ከመሆኑም ባሻገር፣ እንደ ሀገር በየተሰማራንባቸው መስኮች ትኩረት ሰጥተን ከሠራን የላቁ አበርክቶዎችን እውን ማድረግ እንደሚቻል ዓይነተኛ ማሳያ እንደሆነ ታዝቤያለሁ" ብለዋል።
ዑስታዝ አቡበከር በዚሁ ጊዜ ሸይኻ ፋጢማ ቢንት ሙባረክ የዓይነ‐ስውራን አዳሪ ትምህርት ቤት ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ፣ ውብ እና የሀገራችንን መፃዒ ገፅታ በሚያንፀባርቅ መልኩ እውን እንዲኾን የበኩላቸውን ሚና የተወጡ ባለድርሻ አካላትን አመስግነዋል።
"ለትምህርት ቤቱ እውን መሆን ጉልህ አሻራቸውን ካሳረፉት መካከል ከተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ንጉሣዊ ቤተሰብ የተገኙት ክብርት ሸይኻ ፋጢማ ቢንት ሙባረክን፣ የክብርት ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጽሕፈት ቤትን፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርንና የከተማውን ትምህርት ቢሮ ከፍ አድርጌ ለማመስገን እወዳለሁ" ብለዋል።
ሸይኻ ፋጢማ ቢንት ሙባረክ የዓይነ‐ስውራን አዳሪ ትምህርት ቤት እንደ ሞዴል ተወስዶ፣ ሁሉንም የማኅበረሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ የሚያደርጉ መሰል የትምህርትና የልኅቀት ማዕከላት በሁሉም የአገራችን ክልሎች ሊገነቡ ይገባል ብለው እንደሚያምኑ ዑስታዝ አቡበከር ተናግረዋል።
"ሰሞኑን በትምህርት ተቋሙ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ስለሚገኙ ሙስሊም ተማሪዎች አያያዝ ሲሰሙ በቆዩ ቅሬታዎች ዙርያ ከትምህርት ቤቱ አስተዳደርና ከተማሪዎቹ ጋር ሰፊ ውይይት አካሂደናል" ያሉት ዑስታዝ አቡበከር፣ "በውይይታችንም መሰል ችግሮች ዳግም እንዳይፈጠሩና ለተፈጠሩትም በጋራ ዘላቂ መፍትኄ በመፈለግ አስፈላጊነት ላይ ከመግባባት ደርሰናል" ብለዋል።
ቅሬታ የተነሳባቸው ጉዳዮችን ለመፍታት በተደረገው ጥረት ችግሩ የተፈታ መኾኑን እና የተቋሙ ሙስሊም ተማሪዎች የጀመኣ ሶላት (የሕብረት ስግደት) የሚፈጽሙበት ቦታ ተመቻችቶላቸው ሶላታቸውን በወቅቱ መስገድ መቻላቸውን በጉብኝታቸው ወቅት ለማረጋገጥ መቻላቸውን ተናግረዋል።
ሙስሊም ተማሪዎቹን በግል እና በቡድን እንዳነጋገሩ የጠቀሱት ዑስታዝ አቡበከር፣ ተማሪዎቹ የነበሩ ችግሮች መቀረፋቸውን በማረጋገጥ ትምህርታቸውን በአግባቡ መከታተል መቀጠላቸውን እንዳሳወቋቸው ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የፕሬዚደንቱ ጽሕፈት ት ቤት ኃላፊ ችግሩ እንዲፈታ ሚናቸውን በአግባቡ ለተወጡት የትምህርት ቤቱ አስተዳደር እና የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ኃላፊነትን ለመወጣት ያሳዩትን ትጋት በማድነቅ አመስግነዋል።

ታህሳስ 4፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ሳኒ 11፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጠቅላይ ምክር ቤቱ ግምቱ 800 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ መድኃኒት እና የሕክምና ግብዓቶችን ለአምስት የመንግሥት ሆስፒታሎች አበረከተ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከሙስሊም ኤይድ ዩ.ኤስ.ኤ. በሥጦታ ያገኛቸውን ግምታቸው 800 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ መድኃኒት እና የሕክምና መገልገያ ሣሪያዎች ለአምስት የመንግሥት ሆስፒታሎች ዛሬ በሥጦታ አበረከተ።
በጠቅላይ ምክር ቤቱ ቅጥር ግቢ በተካሄደው የርክክብ ስነ ሥርዓት ላይ የመድኃኒትና የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎቹን የክብር ዶ/ር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ለድል ጮራ፣ ለአሶሳ፣ ለጅግጅጋ፣ ለስልጤ እና ለሙሁር አክሊል ሆስፒታል ተወካዮች አስረክበዋል።
ለሆስፒታሎቹ የተበረከቱት የመድኃኒትና የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎች አሜሪካ ከሚገኘው ሙስሊም ኤይድ ዩ.ኤስ.ኤ የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት በጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት የጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዑስታዝ አቡበከር አሕመድ አስተባባሪነት የተገኙ መኾኑን ለማወቅ ተችሏል።
•••••••••••••••