Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
11.4K subscribers
5.16K photos
76 videos
20 files
867 links
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
Download Telegram
ጥቅምት 25፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ኡላ 2፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሴቶችና ወጣቶች ዘርፍ እና ዳብሊ ፋውንዴሽን አብሮ ለመሥራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሴቶችና ወጣቶች ዘርፍ ዳብሊ (DABLIE) ከተባለ ሀገር በቀል ድርጅት ጋር የወጣቶችን አቅም በመገንባት፣ የሙስሊም ሴቶችን ሁለንተናዊ ዕድገት ከፍ የሚያደርጉ የተቀናጁ ፕሮግራሞች በትብብር በማዘጋጀትና በመተግበር ዙሪያ አብሮ ለመሥራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ።

የመግባቢያ ሰነዱን የጠቅላይ ምክር ቤቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ አብዱልዓዚዝ አሎ እና የዳብሊ ፋውንዴሽን ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ኢማድ አብዱልመጂድ ፈርመዋል።

በዚሁ ጊዜ የዳብሊ ፋውንዴሽን ባልደረባ ድርጅቱ ስለሚያካሂዳቸው እንቅስቃሴዎች በስላይድ የተደገፈ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ፋውንዴሽኑ ከጠቅላይ ምክር ቤቱ የሴቶችና ወጣቶች ዘርፍ ጋር የሚሠራበት ማዕቀፍ እና የጋራ ዓላማ በመግባቢያ ሰነዱ ውስጥ መካተቱ ተነግሯል።

የሙስሊም ወጣቶችን ክህሎት ማጎልበት እና በማኅበረሰብ ውስጥ ንቁ ተሳትፎ እንዲኖራቸው የሙያ ሥልጠና መስጠት የመግባቢያ ሰነዱ አካል መሆኑን ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ አብዱልዓዚዝ አሎ ጠቅላይ ምክር ቤቱ መስሊሙን እና በአጠቃላይም ሀገርን በሚጠቅም ጉዳይ ላይ አቅምና ብቃት ካላቸው ድርጅቶችና ተቋማት ጋር ለመሥራት በሩ ክፍት ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በመግባቢያ ሰነዱ ፊርማ ስነ ሥርዓት ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሴቶችና የወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ ዑስታዛ ፋጡማ ሐሰን፣ የመጅሊሱ ሥራ አስፈጻሚ አባልና የትምህርትና ማኅበራዊ ዘርፍ ተጠሪ ኢንጅነር አንዋር ሙስጠፋ፣ እንዲሁም የዳብሊ ፋውንዴሽን አመራር አባላት ተገኝተዋል።

••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc13
ጥቅምት 27፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ኡውላ 5፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የዑለማ ጉባዔ ጽ/ቤት ለክልል የዑለማ ጉባዔ ጽሕፈት ቤቶች ሥጦታ አበረከተ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ስር ያለው የዑለማ ጉባዔ ጽ/ቤት ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ጋር በመተባበር የክልል ዑለማ ጉባኤ ጽሕፈት ቤቶችን ለማጠናከር የኮምፒዩተር፣ የፎቶኮፒ ማሸን እና የፕሪንተር ሥጦታዎች አበረከተ፡፡

ለክልል የዑለማ ጉባዔ ጽሕፈት ቤቶች ሥጦታ በተበረከተበት ስነ-ሥርዓት ላይ የተገኙት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት
እና የዑለማ ጉባዔ ሰብሳቢው የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ እንደተናገሩት፣ "ሥጦታው ለክልል የዑለማ ጉባዔ ጽሕፈት ቤቶች ምቹ የሥራ ሁኔታ ለመፍጠር ያለመ ነው" ብለዋል።

"የኢትዮጵያ ዓሊሞች ከመቀበል አልፈው እንዲህ እንደዛሬው መስጠት መቻላቻው ትልቅ ለውጥ በመሆኑ፣ አልሃምዱሊላህ ለዚህ ያደረሰን አላህ (ሱ.ወ.) ምሥጋና ይገባዋል" ብለዋል፡፡

ክቡር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም አያይዝውም "የቀድሞ ዓሊሞች እኛን ጨምሮ በሉህ (አነስተኛ መክተፊያ የሚያህል ዝርግ ጣውላ) እየተጻፈና እየታጠበ ስንማር (ስንቀራ) የነበረበት ጊዜ ሩቅ አይደለም" ሲሉ አስታውሰዋል፡፡

"ዓሊሞቻችን ዛሬ ዓለም የደረሰበትን የቴክኖሎጂ ደረጃ የሚወክል እና የዳዕዋ ሥራቸውን የሚያቀልል ዘመናዊ መገልገያ ለመጠቀም መድረሳቸው ትልቅ የለውጥ ሂደት ነው" ብለዋል፡፡ ቀኑንም "የሥጦታ ቀን" በማለት ደስታቸውን አካፍለዋል።

የኢትዮጵያ ዓሊሞች ጉባዔ ጽሕፈት ቤት ከሦስት ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ለ12 ክልሎች እና ለሁለት የከተማ አስተዳደር የዑለማ ጉባዔ ጽሕፈት ቤቶች ያበረከተው ሥጦታ ዋና ዓላማው ለዳዕዋ ሥራ ምቹሁኔታን መፍጠር በመኾኑ፣ የየክልሉ የዑለማ ጉባዔ ጽሕፈት ቤቶች ይህን አማና ተቀብላችሁ በዳዕዋ ሥራ አንድትበረቱ ሲሉ አደራ ሰጥተዋል።

በጠቅላይ ምክር ቤቱ አዳራሽ በተካሄደው የሥጦታ ርክክብ ስነ-ሥርዓት መረኃግብር ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን፣ የዓሊሞች ጉባዔ ምክትል ሰብሳቢና የፈትዋ ኮሚቴ ዋና ሰብሳቢው ዶክተር ጄይላን ኸድር፣ ምክትል ፕሬዚደንትና የሐጅ እና ዑምራ ዘርፍ ኃላፊው ሸይኽ አብዱልዓዚዝ አብዱልወሊ፣ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሐጅ ከማል ሐሩን፣ የኦሮሚያ መጅሊስ ፕሬዚደንት እና የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እና የዑለማ ጉባዔ ምክር ቤት አባላት ተገኝተዋል።
••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc13
ጥቅምት 27፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ኡላ 4፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የጋምቤላ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ዓመታዊ የሥራ ግምገማ አደረገ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የጋምቤላ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ (ተቅዪም) ጋምቤላ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት አካሄደ።

ትላንት የተጀመረው የጋምቤላ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ በ2016 ዓ.ል በምክር ቤቱ በተከናወኑ ሥራዎች ላይ ትኩረት ማድረጉን የግምገማ መድረኩን የመሩት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ተጠሪ ሸይኽ ሑሴን ሐሰን ተናግረዋል።

ዛሬ የተጠናቀቀው የጋምቤላ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ዓመታዊ ግምገማ በ2016 ዓ.ል በምክር ቤቱ የተመዘገቡ ውጤቶችን በማስቀጠል፣ በታዩ ውሱንነቶች ላይ የማስተካከያ እርምጃ እንደሚወሰድ ሸይኽ ሑሴን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ነሐሴ 18፣ 2016 ዓ.ል በአዲስ አበባ ባደረገው የ2ኛ ዓመት፣ 4ኛ መደበኛ ጉባዔ፣ የክልልና የከተማ አሥተዳደር የእስልምና ጉዳይ ምክር ቤቶች የ2016 ዓ.ል የሥራ አፈጻጸማቸውን እንዲገመግሙ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል።

የጋምቤላ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የሥራ አፈጻጸም ገምጋሚ ቡድን በዛሬ ውሎው በከፍተኛ ምክር ቤቱ የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውሮ መጎብኘቱን ከሸይኽ ሑሴን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc13
ጥቅምት 28፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ኡላ 6፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት የዓረብ ሊግ ተጠባባቂ ኃላፊን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የዐረብ ሊግ ተጠባባቂ ኃላፊ የኾኑትን ሰዒዳ (Saida) ሙሐመድ ዑመር በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።

ፕሬዚደንቱ የዓረብ ሊግ ተወካይን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው ሲያነጋግሩ የአሁኑ የመጀመሪያቸው መኾኑ በውይይቱ ወቅት ተነስቷል።

በአፍሪካ ሕብረት እና በተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የዓረብ ሊግ ተወካይ የሆኑት ሰዒዳ ሙሐመድ ዑመር የዓረብ ሊግ ጽሕፈት ቤት ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ጋር በትምህርት፣ በማኀበራዊ ጉዳይ እና በልማት አብሮ ለመሥራት ፍላጎት እንዳለው ተናግረዋል።

በጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት ጽሕፈት ቤት በተደረገው ውይይት ኢትዮጵያ የዓረብ ሊግ አባል በምትኾንበት መንገድ ጉዳይ ዙርያ ሐሳብ ተነስቷል።

የዐረብ ሊግ ተጠባባቂ ኃላፊዋ ጥያቄው ተገቢውን መስፈርት አሟልቶ በኢትዮጵያ መንግሥት የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ከቀረበ ሁኔታዎችን በቅርበት ለመከታተል ያስችላል ብለዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሐጂ ኢብራሂም የውይይቱን በጎነት ገልፀው፣ የተፈጠረውን ዕድል ተጠቅመን መስሊሙን እና ሀገርን በሚጠቅም መልኩ ከዐረብ ሊግ ጋር ተቀራርቦ ለመሥራት የሚታየው ፍላጎት አበረታች እንደኾነ ተናግረዋል።

በውይይቱ ላይ የዐረብ ሊግ የፕሬስ ክፍል ኃላፊ ኢብራሂም አል ሱዳኒ፣ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ጸሐፊ ሸይኽ ሐሚድ ሙሳ እና የውጪ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊው ረዳት ፕሮፈሰር አደም ካሚል ተገኝተዋል።
========
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc13
ጥቅምት 28፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ኡላ 5፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የሕንጻ ዲዛይን አማካሪ ተወዳዳሪ ድርጅቶች የፋይናንስ ሰነድ ተከፈተ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በምክር ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ለሚያስገነባው ባለ 2 ምድር ቤት እና ባለ 13 ወለል የአፓርትመንት ሕንጻ ተጫራች የዲዛይን አማካሪ ድርጅቶች ያቀረቡት የፋይናንስ ሰነድ በዛሬው ዕለት በተጫራቾችና በታዛቢዎች ፊት ተነበበ።

በዛሬው ዕለት የፋይናንስ ሰነዳቸው በጠቅላይ ምክር ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተከፍቶ የተነበበው የዲዛይን አማካሪ ድርጅቶች ጥቅምት 21፣ 2017 ዓ.ል. በዚሁ አዳራሽ በይፋ በተከፈቱ የቴክኒክ ሰነድ : ሰነዶቻቸው መስፈርቶቹን ማሟላታቸው በቴክኒክ ኮሚቴ የተረጋገጠላቸው ድርጅቶች መኾናቸው ተነግሯል።

በጠቅላይ ምክር ቤቱ የፕሮጀክት ፅ/ቤት አማካሪዎች ጠቋሚነት በፕሮጀክት አፈጻጸማቸው መልካም ስም ካላቸው የመንግሥት እና የግል ድርጅቶች ወደ ፋይናንስ ሰነድ ውድድር ምዕራፍ ካለፉት ተወዳዳሪዎች መካከል አንደኛውየመወዳደሪያ ሰነድ ማቅረቢያ መስፈርቱን ባለሟሟላቱ ከጨረታው መሰረዙ ተነግሯል።

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገነባው ባለ 2 ምድር ቤት (B2)፣ 13 ወለል (G+13) የአፓርትመንት ሕንጻ የዲዛይን አማካሪ ድርጅቶች ጨረታ በተመረጡ ድርጅቶች መካከል ብቻ የተከናወነ እንደኾነ መነገሩ ይታወሳል።

የጨረታውን ሂደት አስመልክቶ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ አብዱልዓዚዝ አሎ ጠቅላይ ምክር ቤቱ የፋይናንስ ግልፀኝነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የአሠራር ሂደቶችን ተግባራዊ በማድረግ ላይ እንደኾነ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ ሕግን መሠረት አድርጎ እየሠራ ለመሆኑ ይህኛውን ጨምሮ ለተለያዩ ፕሮጀክቶች እየወጡ ያሉ ጨረታዎች እየተካሄዱ ያሉበት ሂደት አመላካች እንደኾነ አቶ አብዱልዓዚዝ ተናግረዋል።

ዛሬ በተጫራቾችና በታዛቢዎች ፊት በይፋ ተከፍቶ የተነበበው የዲዛይን አማካሪ ድርጅቶች የፋይናንስ ሰነድ ተጣርቶ ከቀናት በኋላ አሸናፊው ድርጅት ለሕዝብ ይፋ እንደሚሆን ምክትል ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል።

​========
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc13
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የልማት ክንፍ ለኾነው ለኢትዮጵያ ሙስሊሞች የልማት ኤጀንሲ የቢሮ ማስፋፊያ ግንባታ ግልፅ ጨረታ መስከረም 28፣ 2017 ዓ.ል በተቋሙ የፌስቡክ ገጽ፣ በኤጀንሲውና በተለያዩ መስጂዶች የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያውን ለሕዝብ ይፋ  አድርጎ ጥቅምት 19፣ 2017 ዓ.ል | ረቢዑል ሳኒ 26፣ 1446 ዓ.ሒ  የተከፈተው ጨረታ ፣ ጊዜያዊ የጨረታ ውጤት
ሕዳር 2፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ኡላ 9፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
በሸሪዓ ፍርድ ቤቶች በሚታዩ ችግሮችና መፍትኄዎቻቸው ላይ ጥናት ያካሄደው ኮሚቴ የጥናቱን ሰነድ ለጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት አስረከበ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

በፌዴራል የሸሪዓ ፍርድ ቤቶች በሚታዩ ችግሮችና መፍትኄዎቻቸው ላይ ያተኮረ ጥናት ለማካሄድ የተቋቋመው ኮሚቴ የጥናቱን ሰነድ ለኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት ለክቡር ዶክተር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ አስረከበ።

የጥናት ኮሚቴው በጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት፣ በሸሪዓ ፍርድ ቤት እና በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አማካይነት መዋቀሩን ክቡር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ተናግረዋል።

የጥናት ኮሚቴው ስብጥርን በተመለከተ ከጠቅላይ ምክር ቤቱ የዓሊሞች ጉባዔ ጽሕፈት ቤት የተመረጡ ዓሊሞችና ሦስቱ ከፍተኛ የሕግ ባለሙያዎች ዳኞች መኾናቸውን የክብር ዶክተር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ተናግረዋል።

ሚያዚያ 30፣ 2016 ዓ.ል የተመሠረተውና በፌደራል የሸሪዓ ፍርድ ቤቶች አደረጃጀት፣ በሰው ኃይል አስተዳደርና በአገልግሎት አሰጣጥ፣ እንዲሁም በሕጉ ማዕቀፍ ላይ የሚታዩ ችግሮችን በመለየት የመፍትኄ ሐሳብ ያቀረበውን ሰነድ፣ የጥናት ኮሚቴው አባላት ዶክተር ሼይኽ ሙሐመድ ሐሚዲንና የሕግ ባለሙያው አብዱልሐኪም ጀማል ለክቡር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም አስረክበዋል።

በሰነዱ ርክክብ ወቅት ፕሬዚደንቱ ሲናገሩ የሸሪዓ ፍርድ ቤቶች አገልግሎት አሰጣጥና መፍትኄው ላይ ያተኮረውን ይህን ጥናት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ላከናወኑት የጥናት ቡድኑ አባላት በራሳቸውና በጠቅላይ ምክር ቤቱ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ፕሬዚደንቱ ይህን ሰነድ ከጠቅላይ ምክር ቤቱ የዓሊሞች ጉባዔ ምክትል ሰብሳቢና የፈትዋ ኮሚቴ ሰብሳቢ ከኾኑት ከዶክተር ጀይላን ኸድር ጋር አብረው መቀበላቸውን ጠቅሰው ጥናቱን ወደ ሥራ ለመተርጎም ከሚመለከተው አካል ጋር በመኾን እንሠራለን ብለዋል።
••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በምክር ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ለሚያስገነባው ባለ 2 ምድር ቤት እና ባለ 13 ወለል የአፓርትመንት ሕንጻ ተጫራች የዲዛይን አማካሪ ድርጅቶች ያቀረቡት የአፓርትመንት ሕንጻ የዲዛይን እና የኮንትራት አማካሪ የፋይናንስ ሰነድ
ጥቅምት 28፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ኡላ 5፣ 1446 ዓ.ሒ ተከፍቶ መነበቡ ይታወሳል።

የጊዜያዊ የጨረታዊ ውጤት መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል።
ኅዳር 3 ፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ኡላ 11፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት የሱዳን ዓለምአቀፍ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዚደንትን ተቀብለው አነጋገሩ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የሱዳን ዓለምአቀፍ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዚደንት የኾኑትን ፕሮፈሰር ጧሃ አብዲ ጧሃን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።

የትምህርት (Education) ባለሙያ የኾኑት ፕሮፈሰር ጧሃ አብዲ በኢትዮጵያ የዓረብኛ ትምህርትን ለማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት እና ሌሎች የጠቅላይ ምክር ቤቱ አመራሮች ጋር ሰፋ ያለ የሐሳብ ልውውጥ አድርገዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ጠቅላይ ምክር ቤቱ የአረብኛ ትምህርትን ለማሳደግ ተግቶ እንደሚሠራ በውይይቱ ላይ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ የሦስት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኙት ፕሮፌሰር ጧሃ አብዲ ከአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ቀጥሎ በትምህርት ሚኒስቴር ዓረብኛን ለማስተማር እውቅና የተሰጠውን አወልያ የዓረብኛ ኮሌጅን መጎብኘታቸውን ለማወቅ ተችሏል።

በጉብኝታቸው ወቅትም፣ በኮሌጁ ስለሚሰጠው የዓረብኛ ትምህርት ይዘቶች እና በሥርዓተ ትምህርቱ ዙሪያ ሰፋ ያለ ገለጻ እንደተደረገላቸው ታውቋል።

ፕሮፌሰር ጧሃ አብዲ ጧሃ ከክቡር ሸይኽ ሐጂ ጋር በተወያዩበት ወቅት የአወልያ የዓረብኛ ኮሌጅ መምህራንን አቅም በመገንባት ኮሌጁን ወደ ዩኒቨርሲቲ ማሳደግ በሚቻልበት መንገድ ዙሪያ ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ጋር አብሮ ለመሥራት ፍላጎት ያላቸው መኾኑን ተናግረዋል።
========
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
ሕዳር 4፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ኡላ 11፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
………………………………………………………………………
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሠራተኞች የምስጋና መርኃግብር አካሄዱ፡፡
………………………………………………………………………

አዲስ አበባ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሠራተኞች በዛሬው ዕለት በጠቅላይ ምክር ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ለአዲሱ የለውጥ አመራር የምሥጋና መርኃግብር አዘጋጁ፡፡

በምሥጋና መርኃግብሩ ላይ አዲሱ የለውጥ አመራር ሥራ ከጀመረ በኋላ ባሉት ሁለት ዓመታት ለተቋሙ ሠራተኞች በጥናት ላይ የተመሠረተ የደሞዝ ጭማሪና የጥቅማ ጥቅም ማስተካከያ ማድረጉ ተነግሯል።

በመርኃግብሩ ላይ የተቋሙን ሠራተኞች በመወከል ንግግር ያደረጉት ሐጂ አብዱልፈታህ ብርሃኑ፣ በተለያዩ ጊዜያት ጠቅላይ ምክር ቤቱን የመሩ ኃላፊዎች የሠሯቸው በጎ ተግባራት እንደተጠበቁ ሆነው፣ አዲሱ የለውጥ አመራር ከሐምሌ 2014 ዓ.ል ጀምሮ የሕዝበ ሙስሊሙ የጋራ ተቋም ጠንካራ እንዲኾን፣ በሰው ኃይል፣ በአደረጃጀት እና በአሠራር በርካታ ጠቃሚ ተግባራት ማከናወኑን አስታውሰዋል።

ሐጂ አብዱልፈታህ መጅሊሱ ለሕዝበ ሙስሊሙ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት የሚችል ጠንካራ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ግንኙነት ያለው ተቋም እንዲኾን አዲሱ አመራር እየሠራ ያለው የለውጥ ሥራ የሚመሠገን መኾኑን ተናግረዋል።

አመራሩ ሠራተኛው ያለበትን ተጨባጭ የኑሮ ሁኔታ በመረዳት ለሠራተኞቹ ያደረገው የደሞዝ ጭማሪና ጥቅማ ጥቅም የአመራሩን አርቆ አሳቢነትና መልካምነት እንደሚያሳይ የጠቀሱት ሐጂ አብዱልፈታህ፣ ይህ በጎ እርምጃ ሠራተኛው ሥራውን በበለጠ የኃላፊነት ስሜት እና በጥሩ መንፈስ እንዲያከናውን የሚያተጋ መሆኑን ተናግረዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሐጂ ከማል ሐሩን ባለፉት ሁለት ዓመታት አስተዳደሩ ከዚህ ቀደም የነበረውን ዝቅተኛ የሠራተኞች ደሞዝ በጥናት ላይ በመመሥረት ሶስት ጊዜ የደረጃው ማስተካከያ ማድረጉን ተናግረዋል።

ተቋሙ ብቃት ላለው የሰው ኃይል ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጥ መኾኑን የጠቀሱት ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ አዲሱ የሠራተኞች የደሞዝ ማስተካከያ የተቋማዊ ለውጡ ውጤታማነት አንዱ ማሳያ መኾኑን ተናግረዋል።

በቀጣይም ተቋሙ ሕዝበ ሙስሊሙ የጣለበትን አደራ ለመወጣት ከሠራተኛው ጋር ይበልጥ ተቀራርቦ እንደሚሠራ ሐጂ ከማል ሐሩን ተናግረዋል።

መርኃግብሩን መነሻ በማድረግ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሠራተኞች ለበርካታ ዓመታት ዝቅተኛ ደሞዝ ተከፋይ ኾነው መቆየታቸውን የተገነዘበው አመራሩ የሠራተኛውንና የቤተሰቡን ሕይወት ለማሻሻል በጥናት ላይ የተመሠረተ ሥራ ሲሠራ መቆየቱን ተናግረዋል።

በዚህም በየደረጃው የደመወዝና የጥቅማጥቅም ማስተካከያ መደረጉን አስታውሰው፣ ይህ በቂ ነው ብለው እንደማያምኑ ተናግረዋል።

አመራሩ በቀጣይም ከሠራተኞች ጋር ተከታታይ የምክክር መድረክ እንደሚያዘጋጅ የተናገሩት ክቡር ፕሬዚደንቱ፣ ሠራተኛው በሥራው ውጤታማ እንዲኾንና ከአሁኑ በተሻለ መሥራት እንደሚጠበቅበት ተናግረዋል።
…………………………………
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
ኅዳር 4 ፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ኡላ 12፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
………………………………………………………………………
በጠቅላይ ምክር ቤቱ ግቢ ለሚገነባ መስጂድና የቅጥረ ግቢ አጥርና ዋና በር ግንባታ የወጣው ጨረታ ተከፈተ።
………………………………………………………………………
አዲስ አበባ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በቅጥረ ግቢው ውስጥ ሊያስገነባ ላሰበው መስጂድ እና ደረጃውን የጠበቀ የቅጥረ ግቢ አጥርና ዋና በር ግንባታ ሥራ ያወጣው የዲዛይንና የኮንትራት አስተዳደር ጨረታ በይፋ ተከፈተ፡፡

የጠቅላይ ምክር ቤቱ የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብዱልሃዲ ሙሐመድ በጠቅላይ ምክር ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሊገነባ ለታቀደው መስጂድና የቅጥረ ግቢ አጥርና ዋና በር ግንባታ ሥራ የወጣውን ጨረታ ሰነድ የገዙት ተጫራች ድርጅቶች አሥራ አንድ መኾናቸውን ተናግረዋል፡፡

ከእነዚህ መካከል የጨረታውን ሰነድ ሞልተው በማስገባት ዛሬ በይፋ በተከፈተው የጨረታ ሰነድ መክፈት ስነ ሥርዓት ላይ የተገኙት ሰባቱ ድርጅቶች መኾናቸውን ተናግረዋል።

ታዛቢዎች በተገኙበት በተካሄደው የጨረታ መክፈቻ ስነ ሥርዓት ላይ በተጫራቾች የቀረቡት የቴክኒክ እና የፋይናንስ ሰነዶች መኾናቸውን ጠቅሰው፣ በጨረታው ስነ ሥርዓት መሠረት የቴክኒክ ሰነዱ ተከፍቶ በባለሙያዎች ከተገመገመ በኋላ 70 ከመቶ ያሟላ ሆኖ ሲገኝ፣ የፋይናንስ ሰነዶቹ እንዲሁ በይፋ እንደሚከፈቱ ተናግረዋል።

………………………………………………………………………
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
ኅዳር 5፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ኡላ 12፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
"ወጣቶች የየትኛውም ዘርፍ የጀርባ አጥንት፣ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ምሰሶ እና የዲኑ ብርሃን ናቸው።"
- የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

"ወጣቶች የየትኛውም ዘርፍ የጀርባ አጥንት፣ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ምሰሶ እና የዲኑ ብርሃን ናቸው" ሲሉ የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ተናገሩ።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ይህን የተናገሩት በዛሬው ዕለት በተካሄደው የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል የምሥረታ ጉባዔ ላይ ነው።

በምሥረታ ጉባዔው ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዑስታዝ አብበከር አሕመድ የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች በለውጡ ሂደት ውስጥ ጉልህ አሻራቸውን ያሳረፉ መኾናቸውን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች በድምጻችን ይሰማ የመብት ትግል ታሪክ የጎላ ሚና የተጫወቱ መኾናቸውንም ዑስታዝ አቡበከር አስታውሰዋል።

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ስር ለተመሠረተው የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል አሥራ አንድ የአመራር አባላት ተመርጠዋል።

የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል የኃላፊነት ቦታ ውክልናን፣ የትምህርት ዝግጅትን፣ ማኅበረሰባዊ አበርክቶንና ጠንካራ ኃላፊነትን የመወጣት ዝግጁነትን ከግንዛቤ ያስገባ መኾኑን ተናግረዋል።

ለኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል በአመራርነት የተመረጡት የሚከተሉት ወጣቶች ናቸው፦

ዑስታዝ ሐይደር ከድር አብዱልቃድር (ፕሬዚደንት)
ዑስታዝ አብዱልዓዚዝ ሙሐመድ (ምክትል ፕሬዚደንት)
ኢንጂነር ዑስታዝ ከማል አረቦ አሕመድ (ዋና ፀሐፊ)
ዑስታዝ ፈናን ሙሐመድ - አባል
ዑስታዝ አማር ሸይኽ አሚኖ ኢብሮ - አባል
ዑስታዝ ዳውድ ዓሊ - አባል
ዑስታዝ ፋሩቅ ሰዒድ - አባል
ዑስታዝ ሰዒድ ሃይማኖት - አባል
ዑስታዝ ሙሐመድ አሕመድ - አባል
ዑስታዝ አብዱልፈታህ አብዱረህማን - አባል
ዑስታዝ ኢሳም አብዱረህማን - አባል ተደርገው መመረጣቸው ይፋ ሆኗል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ በጠቅላይ ምክር ቤቱ ስር ለተመሠረተው የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ባደረጉት ንግግር፣ ወጣቶቹ በጥንቃቄና ጊዜ ተወስዶ ወደ ኃላፊነት እንደመጡ ተናግረዋል።

አንድነትን መሠረት አድርገው፣ ሁሉንም ወጣት አስተሳስረው እና አስተባብረው፣ ከምንም በላይ ለሰላም ቅድሚያ በመስጠት የሀገሪቱ ሙስሊም ወጣቶች ሀገራዊ ሚና የጎላ እንዲሆን ትልቅ ኃላፊነት አለባችሁ ብለዋል።

በመጨረሻም፣ የዓሊሞች ጉባዔ ምክትል ሰብሳቢና የፈትዋ ኮሚቴ ዋና ሰብሳቢው ዶክተር ጀይላን ኸድር ለተመረጡት የካውንስሉ አመራር አባላት የአደራ ቃል አስገብተዋቸዋል።

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የስብሰባ አዳራሽ በተከናወነው የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ምሥረታ ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ምክትል ፕሬዚደንት ሸይኽ አብዱልዓዚዝ አብዱልወሊ፣ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሱልጣን አማን ኤባ፣ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሥራ አስፈጻሚዎች፣ የዑለማ ጉባዔ ጽሕፈት ቤት አባላት፣ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሐጅ ከማል ሐሩን፣ የሴቶችና የወጣቶች ዘርፍ ኃላፊዋ ዑስታዛ ፋጡማ ሐሰን እና
ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

​••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
ሕዳር 5፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ኡላ 13፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ             
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ለከፍተኛ እስላማዊ የትምህርት ተቋማት ኃላፊዎች ሥልጠና ተሰጠ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዓሊሞች ጉባዔ ጽሕፈት ቤት፣ ከሱዳን ዓለምአቀፍ እስላማዊ  ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለከፍተኛ እስላማዊ የትምህርት ተቋማት ኃላፊዎች የአቅም ግንባታ ሥልጠና ሰጠ።

የሱዳን ዓለምአቀፍ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዚደንት በኾኑት ፕሮፌሰር ጧሃ አብዲ የተሰጠው ይህ የአቅም ግንባታ ሥልጠና በከፍተኛ እስላማዊ የትምህርት ተቋማት አመሠራረት ላይ ያተኮረ መኾኑን በዓሊሞች ጉባዔ ጽሕፈት ቤት ሥርዓተ ትምህርት ማረጋገጫ ኃላፊ ዶክተር አብደላ ኸድር ተናግረዋል።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ ሁለት ሀገርአቀፋዊ ከፍተኛ እስላማዊ የትምህር ተቋማት ለመመሥረት በጥናት ላይ መኾኑን የተናገሩት ዶክተር አብደላ፣ በሰባት ሀገራት ቅርንጫፎች ከፍቶ የማስተማር ከስድሳ በላይ ዓመታት ልምድ ካለው ከሱዳን ዓለምአቀፍ ዩኒቨርሲቲ ሰፊ ልምድ መገኘቱን ዶክተር አብደላ ተናግረዋል።

ዛሬ በጠቅላይ ምክር ቤቱ የዓሊሞች ጉባዔ ጽሕፈት ቤት  መሰብሰቢያ አዳራሽ በተሰጠው የአቅም ግንባታ ሥልጠና ላይ የስምንት ከፍተኛ እስላማዊ የትምህርት ተቋማት  ኃላፊዎች ታድመውበታል።
••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
ኅዳር 7፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ኡላ 15፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፋውንዴሽን ለጠቅላይ ምክር ቤቱ ሃይማኖታዊ መጻሕፍትን አስረከበ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፋውንዴሽን በተለያዩ ጊዜያትና ሁኔታ በመንገደኞች የተረሱ ቁርኣን እና ሃይማኖታዊ መጻሕፍትን ለኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስረከበ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፋውንዴሽን የሥራ ኃላፊ አቶ ፈቲህ ካሚል አቡበከር ያመጡትን ቁርኣን እና ሃይማኖትዊ መጻሕፍት ለጠቅላይ ምክር ቤቱ የሥራ አስፈፃሚ አባል የሆኑት ሼይኽ አብዱልሐሚድ አሕመድ ተረክበዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሐጂ ከማል ሐሩን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ፋውንዴሽን ቁርኣን እና ሃይማኖታዊ መጻሕፍትን መረከባቸውን የሚገልጽ ማሥረጃ ሰጥተዋል።

በርክክብ ስነ-ሥርዓቱ ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ሐጂ ከማል ሐሩን የጠቅላይ ምክር ቤቱ አጋር የኾነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ታማኝነትና የተቀደሰ ተግባር ያስደሰታቸው መኾኑን ተናግረዋል።

ዋና ሥራ አስኪያጁ አክለውም ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ያለው የረጅም ጊዜ መልካም ግንኙነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፋውንዴሽን የሥራ ኃላፊ አቶ ፈቲህ ካሚል አቡበከር በተመሳሳይ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እና ለአብሮኆት ቤተ መጻሕፍት ማስረከባቸዉን ተናግረዋል።

​​••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
ኅዳር 9፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ኡላ 17፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
አዲስ አበባ |

ከታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አቅራቢያ መስጂድ ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ መተከል ዞን፣ ጉባ ወረዳ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አቅራቢያ 'አር ረህማን' በመባል የሚጠራ መስጂድ ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ በሕዳሴ ግድብ አቅራቢያ ባምዛ ቀበሌ ለሚሠራው መስጂድ የመሠረት ድንጋዩን በጋራ ያኖሩት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የፈትዋና ምርምር ተጠሪ ሸይኽ እንድሪስ ዓሊ ሁሴን (ደጋን)፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚደንት ሼይኽ ኢብራሒም ሲራጅ እና የአዲስ አበባ መጅሊስ ከፍተኛ አመራሮች መሆናቸው ታውቋል።

ከሕዳሴ ግድብ በቅርብ ርቀት ለመገንባት መሠረት የተቀመጠለት መስጂድ በአካባቢው ለሚገኘው ሙስሊም ማኅበረሰብ ትልቅ ጠቀሜታ እንደሚሰጥ በገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቱ ላይ በስፋት ተነግሯል።

ሙስሊሙን ማኀበረሰብ ለማገልገል የሚገነባውን 'አርረህማን' መስጂድ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መጅሊስ በተጨማሪ በአቅራቢያው የሚገኘው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ጽ/ቤት በትብብር እንደሚገነባ ተነግሯል።

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ልዑካን ውስጥ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የዑለማ ጉባዔ ጽ/ቤት ኃላፊ ሸይኽ ሙሐመድዘይን ዛኽረዲን፣ በጠቅላይ ምክር ቤቱ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተወካይ የፌደራል መጅሊስ የሥራ አስፈፃሚ አባልና የተቋማትና ማሕበራት ዘርፍ ተጠሪ ሸይኽ አልመርዲ አብዱላሂ እና የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሸይኽ ሑሴን ሐሰን ተገኝተዋል።

ከታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ከአንድ ኪሎ ሜትር ባልበለጠ ርቀት ላይ ለሚገነባው መስጂድ ግንባታ የመሠረት ድንጋይ በተቀመጠበት ስነ ሥርዓት ላይ የአዲስ አበባ መጅሊስ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የባምዛ ቀበሌ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
ኅዳር 10፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ኡላ 18፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
በጠቅላይ ምክር ቤቱ ግቢ ለሚገነባው የአፓርትመንት ሕንጻ የዲዛይን ጨረታውን ካሸነፈው ድርጅት ጋር የውል ስምምነት ተፈረመ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በቅጥረ ግቢው ውስጥ ለሚያስገነባው ባለ 2 ምድር ቤት እና ባለ 13 ወለል የአፓርትመንት ሕንጻ የዲዛይን ጨረታውን ካሸነፈው QTC ኤንጅነሪንግ ኮንሰልታንሲ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት ጋር ዛሬ የውል ስምምነት ተፈራረመ።

ስምምነቱን በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በኩል ዋና ሥራ አስኪያጁ ሐጂ ከማል ሐሩን ሲፈርሙ፣ በQTC ኤንጅነሪንግ ኮንሰልታንሲ በኩል የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ መሐመድ ሐሰን ፈርመዋል።

QTC ኢንጅነሪንግ ኮንሰልታንሲ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት የሕንጻ ዲዛይኑን በውሉ መሠረት ሠርቶ ሲያቀርብ የግንባታ ጨረታ ወጥቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ግንባታ እንደሚገባ ተነግሯል።
​••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
በ1446 ዓ.ሒ (2017 ዓ.ል) የሐጅ ጉዞ ለማድረግ ላሰባችሁ የአሏህ እንግዶች።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በ1446 ዓ.ሒ (በ2017 ዓ.ል) የሐጅ ጉዞ ለማድረግ ያሰቡ የአሏህ እንግዶችን ምዝገባ ለመጀመር ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል።

ስለሆነም በዘንድሮው ዓመት የሐጅ ጉዞ ለማድረግ ያሰባችሁ የአሏህ እንግዶች፣ ከአሁን በፊት ፓስፖርት የሌላችሁ ከወዲሁ እንድታወጡ፣ ፓስፖርት ኖሯችሁ ነገር ግን የአገልግሎት ጊዜዉ ሊያበቃ ከአንድ ዓመት በታች የቀረው ከኾነ ከወዲሁ በአቅራቢያችሁ በሚገኘው የኢምግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በመቅረብ እንድታሳድሱ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ለማስታወስ ይወዳል።

​​••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
Oduu Gammachiisaa Keessummoota Rabbii Bara 1446 AH (2017 AH) Hajjii Gochuuf Niyyatan Hundaaf.

Manni Marii Waliigalaa Dhimmoota Islaamaa Itoophiyaa bara 1446 AH (Dh.K.D bara 2017) galmee keessummoota Rabbii fedhii Hajjii godhuu qaban yeroo dhiyootti eegaluuf qophii xumuraa jira.
Kanaafuu, keessummoonni Rabbii bara kana Hajjii gochuuf niyyatan; Warri kanaan dura paaspoortii hin qabne, Paaspoortii yoo qabaattan ,garuu yeroon hojiirra ooluu waggaa tokkoo gadi yoo hafe, tajaajila immigireeshinii fi lammummaa isinitti dhihoo jirutti haaromsa akka gootan asumaan cimsinee isin beeksifna.

Mana Marii Waliigalaa Dhimmoota Islaamaa Itiyoophiyaa Damee Hajjii fi Umraa Irraa
ጥቅምት 14፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ኡላ 21፣ 1446ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጠቅላይ ምክር ቤቱ በአዳማ በትምህርት ሥራ መመሪያ አተገባበር ላይ የውይይት መድረክ አካሄደ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዳማ |

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የትምህርትና ማኅበራዊ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የትምህርት ክፍል በትምህርት ሥራ መመሪያ አተገባበር ላይ የውይይት መድረክ አዘጋጀ።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ የትምህርትና ማኅበራዊ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የትምህርት ክፍል ባዘጋጀው በዚህ የውይይት መድረክ ላይ የኦሮሚያ መጅሊስ፣ የዞን መጅሊስ ተወካዮች እና ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ኾነዋል።

በመርኃግብሩ መክፈቻ ላይ የኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚደንት ሸይኸ ዚያድ አልይ
ባደረጉት ንግግር በሙስሊሙ ማኅበረሰብ ውስጥ ለትምህርት በተሰጠው የተዛባ አመለካከት ሳቢያ ብዙዎች ከትምህርቱ ርቀው ወይም ስልታዊ በኾነ መንገድ ተገፍተው ቆይተዋል ብለዋል።

ምክትል ፕሬዚደንቱ ሸይኸ ዚያድ አልይ የሀገሪቱ ሙስሊሞች በአካዳሚክ ዘርፉ ሚናችን የሳሳ መኾኑ እንደ ሀገር ብዙ ዋጋ እያስከፈለን ነው ሲሉ ተናግረዋል።

አያይዘውም ጠቅላይ ምክር ቤቱ ሰፊ ቁጥር ያለው ሙስሊም ማኀበረሰብ መሪ በመኾኑ፣ ከዲን ትምህርት በተጨማሪ በአካዳሚክ ትምህርት ላይ ያለውን ክፍተት የመፍታት ሚና ይጫወት ዘንድ በትምህርት ሥራ መመሪያ ላይ ውይይት መደረጉ ትልቅ ኃላፊነትን የመወጣት ሥራ በመኾኑ ሊመሰገን ይገባል ብለዋል።

የዳይሬክቶሬቱ የትምህርትና ሥልጠና ኃላፊ አቶ ሙሐመድ ይመር ረቂቅ የትምህርት ሥራ መመሪያውን አስመልክተው ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች ማብራሪያውን መነሻ ያደረጉ የግብዓት ሐሳቦችና ጥያቄዎችን ለመድረኩ አቅርበዋል።

የመድረኩ አወያይና የዳይሬክቶሬቱ የትምህርትና ሥልጠና ባለሙያ የኾኑት አቶ ዓሊ ሁሴን፣ አቶ መሐመድ ይመር፣ ወይዘሮ ነስራ ነኢም ለማብራሪያና ለጥያቄዎች መልስ ሰጥተዋል።

በመጨረሻም በቀረበው የትምህርት ሥራ መመሪያ አተገባበር ላይ ያተኮረ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።

የመግባቢያ ሰነዱን በኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በኩል የምክር ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሐጂ መሐመድ ጋሊ ሲፈርሙ፣ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በኩል የትምህርትና ማኅበራዊ አገልግሎት ዳሬክትሬት የትምህርት ክፍል አቶ መሐመድ ይመር ፈርመዋል።
​••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1