Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
11.4K subscribers
5.17K photos
76 videos
20 files
868 links
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
Download Telegram
ጥቅምት 20፣ 2017 ዓ.ል | ረቢዑል ሳኒ 26፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
በሐጅ ወቅት በጀዳ አውሮፕላን ማረፊያ #ሻንጣ_ለጠፋባችሁ የ1445 ዓ.ሒ (2016 ዓ.ል) ሐጃጆች።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በ1445 ዓ.ሒ (2016 ዓ.ል) የዘመነ መስተንግዶ ለአል ረሕማን እንግዶች በሚል መሪ ሐሳብ ሐጃጆችን ማስተናገዱ ይታወሳል።

የሐጅ ሥርዓታችሁን አጠናቅቃችሁ ሻንጣችሁን ከመካ ወደ ሀገር ቤት ለመላክ ከመካ የሽኝት አስተባባሪ የሻንጣ ታግ ወስዳችሁ፣ ነገር ግን ሻንጣችሁ በጀዳ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የጠፋባችሁ ሐጃጆች፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጀዳ አውሮፕላን ማረፊያ የተገኙ የኢትዮጵያውያን ሐጃጆች ሻንጣዎችን ወደ አገር ቤት አምጥቶ ለጠቅላይ ምክር ቤታችን ያስረከበ በመሆኑ፣ ሻንጣ የጠፋባችሁ ሐጃጆች የፓስፖርታችሁን ቅጂ (ኮፒ) እና የሻንጣችሁን ታግ ቅጂ ከዚህ በታች በተቀመጠው ስልክ ቁጥር 0911 82 19 15  (በቴሌግራም) እንድትልኩ እንጠይቃለን።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅና ዑምራ ጉዞ ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት።

ጥቅምት 20፣ 2017 ዓ.ል | ረቢዑል ሳኒ 26፣ 1446 ዓ.ሒ
ጥቅምት 21፣ 2017 ዓ.ል | ረቢዑል ሳኒ 28፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
በጠቅላይ ምክር ቤቱ ቅጥር ግቢ ሊገነባ ለታቀደ ው ሕንጻ የዲዛይን እና የኮንትራት አማካሪ ጨረታ በይፋ ተከፈተ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በጠቅላይ ምክር ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሊያስገነባ ላቀደው ባለ 2 መሠረትና ባለ 13 ወለል የአፓርትመንት ሕንጻ የዲዛይን እና የኮንትራት አማካሪ ጨረታ በይፋ ከፈተ።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብዱልሃዲ ሙሐመድ በጠቅላይ ምክር ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገነባው B+2፣ G+13 የአፓርትመንት ሕንጻ የዲዛይን እና የአማካሪ ጨረታ በተመረጡ ድርጅቶች መካከል ብቻ የተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህ ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ ስምንት (8) ድርጅቶች የተመረጡ ሲኾን፣ ከመንግሥት ድርጅቶች ሦስት (3)፣ ከግል አምስት (5) መሆናቸውን ኃላፊው ተናግረዋል።

በጨረታ መክፈቻ ስነ ሥርዓቱ ላይ ከስምንቱ (8) ድርጅቶች አራቱ (4) የተገኙ ሲኾን፣ ጨረታው ታዛቢዎች በተገኙበት ተከፍቷል።

ድርጅቶቹ በፕሮጀክት አማካሪዎች የተጠቆሙና በፕሮጀክት አፈጻጸም ጥሩ ስም ያላቸው መሆናቸውንም ኃላፊው ተናግረዋል።
ጥቅምት 22፣ 2017 ዓ.ል | ረቢዑል ሳኒ 29፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
በአዲስ አበባ ዓለምአቀፍ የሃይማኖት ጉባዔ ሊካሄድ ነዉ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የሰላም ሚኒስቴር ከሙሐመድ ቢን ዛይድ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ዓለምአቀፍ የሃይማኖት ጉባዔ ሊያካሂድ መሆኑን ተናገረ።

ጥቅምት 25 እና 26፣ 2017 ዓ.ል (ሰኞና ማክሰኞ) በአዲስ አበባ ኃይሌ ግራንድ ሪዞርት የሚካሄደውን ይህን ዓለምአቀፍ ጉባዔ አስመልክቶ ሚኒስቴሩ ዛሬ ለመገናኛ ብዙኃን ተቋማት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ደዔታ ዶክተር ኸይረዲን ተዘራ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ሲናገሩ ኢትዮጵያ ቀደምት የሰዎች መገኛ ብቻ ሳትሆን፣ እስልምናና ክርስትና ለዘመናት በሰላምና በሃገር ግንባታ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረጉባት ታሪካዊ ሀገር መሆኗን አውስተዋል።

በዓይነቱ የመጀመሪያ የኾነው ይህ ዓለምአቀፍ ጉባዔ ሃይማኖቶች ለሀገራችን ሰላምና አብሮነት ያደረጉትን ጉልህ አስተዋፅዖ ይበልጥ ለማጠናከር የሚያግዝ መሆኑን ሚኒስትር ደዔታው ተናግረዋል።

ለዚህም ዓላማ መሳካት የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከሁሉም የሃይማኖት ተቋማት ጋር ተቀራርቦ እየሠራ እንደሚቀጥል ሚኒስትር ደዔታው ተናግረዋል።

ለሁለት ቀናት በሚቆየው በዚህ ዓለምአቀፍ ጉባዔ ላይ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ አባል ቤተ እምነት አባቶች፣ አውሮጳና ኤዥያን ጨምሮ ከአሥራ ሦስት ሀገራት የሚመጡ የሃይማኖት ሊቃውንት፣ አሥራ አምስት ዩኒቨርሲቲዎችን ጨምሮ ሦስት መቶ ሰዎች በጉባዔው ላይ እንደሚሳተፉ ተነግሯል።

በጉባዔው ላይ በምሑራን የተለያዩ ጥናታዊ ጽሑፎች እንደሚቀርቡ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ተናግሯል።

••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc13
ጥቅምት 23፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል አወል፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ስትራቴጂያዊ እቅድ ንድፈ ሐሳብ ለጠቅላይ ምክር ቤቱ ሥራ አስፈጻሚዎች ቀርቦ ፀደቀ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ስትራቴጂያዊ እቅድ ንድፈ ሐሳብ ለጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ እና ለሥራ አስፈጻሚዎች ቀርቦ ማሻሻያዎችን በማከል ወደ ሥራ እንዲገባ ፀድቋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት ስትራቴጂያዊ እቅድ ምክር ቤቱ በ50 ዓመት ታሪኩ ያላሳካው የሕገ-መጅሊሱ አካል በመኾኑ ሁሉን አካታች የለውጥ ብርሃን ሆኖ በታሪክ ትልቅ መሠረት የሚጥል ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ባለንበት የሃለፊነት ጊዜ የአላህ ባሪያዎች የሚገለገሉበት እንደ ዘመናቸውና ተጨባጩ እያሳደጉ የሚሰሩበት ትልቅ ታሪክ ነው ብለዋል።

ፕሬዚደንቱ አያይዘውም የሥራ አስኪያጅ ጽሕፈት ቤት ኃላፊነት ወስዶ ከቦርዱ ጋር ተቀናጅቶ የስትራቴጂያዊ እቅዱን ንድፈ ሐሳብ ለፍሬ በማብቃቱ ምሥጋና አቅርበዋል።

የምክር ቤቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅና የስራትራቴጃዊ እቅድ ዝግጅት ዐብይ ኮሚቴ ዋና ሰብሳቢው አቶ አብዱልዓዚዝ አሎ የስትራቴጂያዊ እቅድ ንድፈ ሐሳቡን ለማበልፀግ ላለፈው አንድ ዓመት የተከናወኑትን የፕሮሲጀርና የዝግጅት ሂደቶችን ያብራሩ ሲኾን፣ እቅዱ በስድስት ወር ተጠናቅቆ ወደ ሥራ እንደሚገባ ተናግረዋል።

የስራትራቴጂያዊ እቅድ ዐብይ ኮሚቴ አባላት ላለፈው አንድ ዓመት ያህል ያለምንም ክፋያ ላደረጉት የጊዜና የሙያ አስተዋጽዖ ክቡር ፕሬዚደንቱ ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ምሥጋና አቅርበዋል።

የስራትራቴጂያዊ እቅድ ዝግጅት ዐብይ ኮሚቴው ያወጣውን መስፈርት ያሟሉ የመስኩ ባለሙያና በእስላማዊ ትምህርት በቂ ዝግጅት ያላቸው አማካሪው አቶ ሺሃቡዲን ሼኽ ኑራ በተቋሙ ስራትራቴጂያዊ እቅድ ንድፈ ሐሳብ ዙሪያ ሰፊ ገለጻ አድርገዋል።

ባለሙያው የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሥራ ስትራቴጂያዊ እቅድ ለተቋማዊ ለውጥና ለሁለንተናዊ እድገት ያለውን ፋይዳ፣ አቃፊነት እና ዘላቂነት ያለው እድገት ለማምጣት ለመሪዎች ትልቅ መሣሪያ እንደሆነም በንድፈ ሐሳብ አሳይተዋል።

የእቅዱ ንድፈ ሐሳብ ዝግጅት ዐብይ ኮሚቴ አባላት ስትራቴጃዊ እቅድ በመሪዎች ንቁነትና ተግባራዊነት የሚታገዝ በመሆኑ፣ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሥራ አስፈጻሚዎች እስከታች በመውረድ የለውጥ መሣሪያ እንዲያደርጉት አደራ ብለዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሥራ አስፈጻሚዎችም በቀረበው የስትራቴጂያዊ እቅዱ ንድፈ ሐሳብ ላይ ግብዓት ሰጥተው፣ ማብራሪያ የሚስፈልገውን ጠይቀው ምላሽ ተሰጥቷቸዋል።

እቅዱ የተበታተነ ሥራችን መርኅ እና ስትራቴጂን የተከተለ እንዲሆን እገዛ የሚያደርግ፣ ሁለን የሚያስተናግድ፣ ከአካባቢያዊና ከተጨባጩ ሁኔታ ጋር እየተገናዘበ ሊሻሻልና ሊጎለብት የሚችል በመኾኑ በኃላፊነት ለመሥራት የሚያነሳሳ ነው ሲሉም ተናግረዋል።

በዚህ ስትራቴጂያዊ እቅድ ንድፈ ሐሳብ ማብራሪያ መድረክ ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን፣ ምክትል ፕሬዚደንትና የሐጅ እና ዑምራ ዘርፍ ኃላፊ ሸይኽ አብዱልዓዚዝ አብዱልወሊ፣ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ጸሐፊ ሸይኽ ሐሚድ ሙሳ፣ እንዲሁም ባለሙያዎችና የቦርድ አባላት ተገኝተዋል።

••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc13
ጥቅምት 25፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል አወል 2፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ዓለምአቀፉ የሃይማኖት ጉባዔ  በአዲሰ አበባ ተጀመረ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የሰላም ሚኒስቴር ከሙሐመድ ቢን ዛይድ ፎር ሂዩማኒቲ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ጉባዔ አዲስ አበባ በሚገኘው ኃይሌ ግራንድ ሪዞርት ተጀመረ።

የኢፌዴሪ ፕሬዚደንት ታዬ አጽቀሥላሴ ለሁለት ቀናት የሚቆየውን ይህን ዓለምአቀፍ ጉባዔ ሲከፍቱ ባደረጉት ኢትዮጵያ ለአያሌ ዘመናት የኖረ የሃይማኖቶች የመከባበርና የመቻቻል ታሪክ ያላት አገር መሆኗን ተናግረዋል።

በዓለማችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይህን የአብሮነት ባህል የሚንዱ ትርክቶች በማኅበራዊ ትስስር ገፆች እየተነዙ ለክቡሩ የሰዎች ሰላም እጦት ምክንያት መኾናቸውን ተናግረዋል።

ፕሬዚደንቱ የሃይማኖት አባቶች አሁን ዓለም ያለችበትን ዉስብስብ ሁኔታ በመቀየር በሰላምና በጋራ አብሮ መኖር ላይ የምንናፍቃትን ዓለም እንድንጨብጥ አባታዊ ትምህርታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

የሰላም ሚኒስትሩ አቶ ብናልፍ አንዷለም በበኩላቸው ሃይማኖቶች የአገር አንድነትና የጥንካሬ ምንጭ መኾናቸውን ተናግረዋል።

የሃይማኖት ተቋማት በአገር ላይ ያላቸውን ከፍተኛ ኃላፊነት በመጠቀም የሰዎች በሰላም አብሮ የመኖር እሴት እንዲጠናከር መሥራት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል።

አገራችን ኢትዮጵያ በሃይማኖት ብዝኃነት የተገነባች መሆኗን የተናገሩት ሚኒስትሩ፣ ሰላምና መቻቻል የሰፈነባት አገር እንድትሆን መስሪያ ቤታቸው ከሁሉም የሃይማኖት ተቋማት ጋር ተቀራርቦ እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጠቅላይ ፀሐፊ ቀሲስ ታጋይ ታደለ፣ ሀገራችን ኢትዮጵያ በዕምነት መጻሕፍት የተወሳች አገር ነች ካሉ በኋላ፣ ዓለማችን የሰላም እጦት ላይ በመሆኗ የሃይማኖት አባቶችን ልብ የሰበረ ክስተት መሆኑን ተናግረዋል።

የሃይማኖት አባቶች ለሰው ልጆች ሁለንተናዊ ሰላም በቀጣይ ተጠናክረው እንደሚሠሩ ተናግረዋል።

የተባበሩት አረብ ኤሚሬት መሐመድ ቢን ዛይድ  ፎር ሂዩማኒቲ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር ዶ/ር ኸሊፋ ሙባረክ ዳኽሪ በአገራቸው እና በኢትዮጵያ መካከል የሰላም እሴትን በማጠናከር ማኅበራዊ ሰላምን ለማጎልበትና ወንድማማችነትን ለማጠናከር ያለመ አዲስ የግንኙነት ምዕራፍ መከፈቱን ተናግረዋል።

ዩኒቨርሲቲው ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በሕዝቦች መካከል የመነጋገር ባሕልን የሚያጎለብቱ ሥራዎች መሥራት እንደሚሻ ተናግረዋል።

በጉባዔው ላይ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ አባል ቤተ እምነት አባቶች፣ አሜሪካ፣ አውሮጳ እና ኤዥያን ጨምሮ ከአሥራ ሦስት ሀገራት የመጡ የሃይማኖት ሊቃውንት፣ አሥራ አምስት ዩኒቨርሲቲዎችን ጨምሮ ሦስት መቶ ሰዎች በጉባዔው ላይ ተሳታፊ ሆነዋል።

ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ጉባዔ ላይ የተለያዩ ጥናታዊ ጽሑፎች በምሁራን እንደሚቀርቡ ለማወቅ ተችሏል።

••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc13
ጥቅምት 25፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ኡውላ 2፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት በዓለም አቀፍ የሃይማኖት ጉባዔ ላይ ጽሑፍ አቀረቡ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ  በአዲስ አበባ ዛሬ በተከፈተው ዓለም ዓቀፍ የሃይማኖት ጉባዔ ላይ ጽሑፍ አቀረቡ።

ክቡር ፕሬዚደንቱ ያቀረቡት ጽሑፍ "የመከባበርና የመቻቻል ባህልን ለማዳበር የሃይማኖት ተቋማት የሚያደርጉት አስተዋጽዖ" የሚል ርዕስ ያለው ሲኾን፣ ሸይኽ ሐጂ ከ1440 ዓመታት በፊት እስልምና ወደ ኢትዮጵያ በገባበት ጊዜ በሐበሻው ንጉሥ አስሐመተል ነጃሺ እና ወደ ሐበሻ በስደት የመጡት የነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ.) ባልደረቦች መሪ በነበረው ታላቁ ሶሃባ ጃዕፈር ቢን አቡ ጧሊብ መካከል እምነትን አስመልክቶ የተካሄደውን ውይይትና መተማመን የመቻቻል አብነት እንደኾነ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ነብያችን ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) "ከእናቴ ቀጥላ ሁለተኛ እናቴ (ሞግዚቴ)" ያሏት የዑሙ አይመን አገር መሆኗን የጠቀሱት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም፣ ታላቁ ነብይ (ሶ.ዐ.ወ) ቀደምት ተከታዮቻቸው በመካ የቁረይሽ ባላባቶች ግፍ እና መከራ በደረሰባቸው ጊዜ፣ "ወደ ሐበሻ ሂዱ፤ እርሷ እርሱ ዘንድ አንድም ሰው የማይበደልበት እውነተኛ መሪ ያለባት የፍትኅ አገር ናት" ማለታቸው በጽሑፋቸው ጠቅሰዋል።

ሼይኽ ሐጂ አክለውም አገራችን ኢትዮጵያ የነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) ሙአዚን የቢላል ኢብኑ ረባህ አገር እንደኾነችና የታላቁ ነቢይ (ሶ.ዐ.ወ) ቀደምት ባልደረቦች ቀብር የሚገኝባት ታላቅ አገር መሆኗን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ልዩነትን የማስተናገድ ከአስሐመተል ነጃሺ የተወረሰ የረጅም ዘመን ታሪክ ያላት አገር መሆኗን የጠቀሱት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም፣ ዓለም ይህንን ልምድ ከኢትዮጵያ ሊወስድ ይገባዋል ብለዋል።

ዛሬ በተጀመረው ዓለምአቀፍ የሃይማኖት ጉባዔ ላይ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ አባል ቤተ እምነት አባቶች፣ አሜሪካ፣ አውሮጳ እና ኤዥያን ጨምሮ ከአሥራ ሦስት ሀገራት የመጡ የሃይማኖት ሊቃውንት፣ አሥራ አምስት ዩኒቨርሲቲዎችን ጨምሮ ከሦስት መቶ በላይ ሰዎች በጉባዔው ላይ ተሳታፊ ሆነዋል።

ለሁለት ቀናት በሚካሄደው በዚህ ዓለም አቀፍ ጉባዔ ላይ በምሁራን የተለያዩ ጥናታዊ ጽሑፎች መቅረባቸው እንደሚቀጥል ተነግሯል።

••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc13
ጥቅምት 25፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ኡላ 2፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሴቶችና ወጣቶች ዘርፍ እና ዳብሊ ፋውንዴሽን አብሮ ለመሥራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሴቶችና ወጣቶች ዘርፍ ዳብሊ (DABLIE) ከተባለ ሀገር በቀል ድርጅት ጋር የወጣቶችን አቅም በመገንባት፣ የሙስሊም ሴቶችን ሁለንተናዊ ዕድገት ከፍ የሚያደርጉ የተቀናጁ ፕሮግራሞች በትብብር በማዘጋጀትና በመተግበር ዙሪያ አብሮ ለመሥራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ።

የመግባቢያ ሰነዱን የጠቅላይ ምክር ቤቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ አብዱልዓዚዝ አሎ እና የዳብሊ ፋውንዴሽን ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ኢማድ አብዱልመጂድ ፈርመዋል።

በዚሁ ጊዜ የዳብሊ ፋውንዴሽን ባልደረባ ድርጅቱ ስለሚያካሂዳቸው እንቅስቃሴዎች በስላይድ የተደገፈ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ፋውንዴሽኑ ከጠቅላይ ምክር ቤቱ የሴቶችና ወጣቶች ዘርፍ ጋር የሚሠራበት ማዕቀፍ እና የጋራ ዓላማ በመግባቢያ ሰነዱ ውስጥ መካተቱ ተነግሯል።

የሙስሊም ወጣቶችን ክህሎት ማጎልበት እና በማኅበረሰብ ውስጥ ንቁ ተሳትፎ እንዲኖራቸው የሙያ ሥልጠና መስጠት የመግባቢያ ሰነዱ አካል መሆኑን ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ አብዱልዓዚዝ አሎ ጠቅላይ ምክር ቤቱ መስሊሙን እና በአጠቃላይም ሀገርን በሚጠቅም ጉዳይ ላይ አቅምና ብቃት ካላቸው ድርጅቶችና ተቋማት ጋር ለመሥራት በሩ ክፍት ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በመግባቢያ ሰነዱ ፊርማ ስነ ሥርዓት ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሴቶችና የወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ ዑስታዛ ፋጡማ ሐሰን፣ የመጅሊሱ ሥራ አስፈጻሚ አባልና የትምህርትና ማኅበራዊ ዘርፍ ተጠሪ ኢንጅነር አንዋር ሙስጠፋ፣ እንዲሁም የዳብሊ ፋውንዴሽን አመራር አባላት ተገኝተዋል።

••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc13
ጥቅምት 27፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ኡውላ 5፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የዑለማ ጉባዔ ጽ/ቤት ለክልል የዑለማ ጉባዔ ጽሕፈት ቤቶች ሥጦታ አበረከተ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ስር ያለው የዑለማ ጉባዔ ጽ/ቤት ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ጋር በመተባበር የክልል ዑለማ ጉባኤ ጽሕፈት ቤቶችን ለማጠናከር የኮምፒዩተር፣ የፎቶኮፒ ማሸን እና የፕሪንተር ሥጦታዎች አበረከተ፡፡

ለክልል የዑለማ ጉባዔ ጽሕፈት ቤቶች ሥጦታ በተበረከተበት ስነ-ሥርዓት ላይ የተገኙት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት
እና የዑለማ ጉባዔ ሰብሳቢው የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ እንደተናገሩት፣ "ሥጦታው ለክልል የዑለማ ጉባዔ ጽሕፈት ቤቶች ምቹ የሥራ ሁኔታ ለመፍጠር ያለመ ነው" ብለዋል።

"የኢትዮጵያ ዓሊሞች ከመቀበል አልፈው እንዲህ እንደዛሬው መስጠት መቻላቻው ትልቅ ለውጥ በመሆኑ፣ አልሃምዱሊላህ ለዚህ ያደረሰን አላህ (ሱ.ወ.) ምሥጋና ይገባዋል" ብለዋል፡፡

ክቡር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም አያይዝውም "የቀድሞ ዓሊሞች እኛን ጨምሮ በሉህ (አነስተኛ መክተፊያ የሚያህል ዝርግ ጣውላ) እየተጻፈና እየታጠበ ስንማር (ስንቀራ) የነበረበት ጊዜ ሩቅ አይደለም" ሲሉ አስታውሰዋል፡፡

"ዓሊሞቻችን ዛሬ ዓለም የደረሰበትን የቴክኖሎጂ ደረጃ የሚወክል እና የዳዕዋ ሥራቸውን የሚያቀልል ዘመናዊ መገልገያ ለመጠቀም መድረሳቸው ትልቅ የለውጥ ሂደት ነው" ብለዋል፡፡ ቀኑንም "የሥጦታ ቀን" በማለት ደስታቸውን አካፍለዋል።

የኢትዮጵያ ዓሊሞች ጉባዔ ጽሕፈት ቤት ከሦስት ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ለ12 ክልሎች እና ለሁለት የከተማ አስተዳደር የዑለማ ጉባዔ ጽሕፈት ቤቶች ያበረከተው ሥጦታ ዋና ዓላማው ለዳዕዋ ሥራ ምቹሁኔታን መፍጠር በመኾኑ፣ የየክልሉ የዑለማ ጉባዔ ጽሕፈት ቤቶች ይህን አማና ተቀብላችሁ በዳዕዋ ሥራ አንድትበረቱ ሲሉ አደራ ሰጥተዋል።

በጠቅላይ ምክር ቤቱ አዳራሽ በተካሄደው የሥጦታ ርክክብ ስነ-ሥርዓት መረኃግብር ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን፣ የዓሊሞች ጉባዔ ምክትል ሰብሳቢና የፈትዋ ኮሚቴ ዋና ሰብሳቢው ዶክተር ጄይላን ኸድር፣ ምክትል ፕሬዚደንትና የሐጅ እና ዑምራ ዘርፍ ኃላፊው ሸይኽ አብዱልዓዚዝ አብዱልወሊ፣ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሐጅ ከማል ሐሩን፣ የኦሮሚያ መጅሊስ ፕሬዚደንት እና የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እና የዑለማ ጉባዔ ምክር ቤት አባላት ተገኝተዋል።
••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc13
ጥቅምት 27፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ኡላ 4፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የጋምቤላ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ዓመታዊ የሥራ ግምገማ አደረገ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የጋምቤላ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ (ተቅዪም) ጋምቤላ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት አካሄደ።

ትላንት የተጀመረው የጋምቤላ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ በ2016 ዓ.ል በምክር ቤቱ በተከናወኑ ሥራዎች ላይ ትኩረት ማድረጉን የግምገማ መድረኩን የመሩት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ተጠሪ ሸይኽ ሑሴን ሐሰን ተናግረዋል።

ዛሬ የተጠናቀቀው የጋምቤላ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ዓመታዊ ግምገማ በ2016 ዓ.ል በምክር ቤቱ የተመዘገቡ ውጤቶችን በማስቀጠል፣ በታዩ ውሱንነቶች ላይ የማስተካከያ እርምጃ እንደሚወሰድ ሸይኽ ሑሴን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ነሐሴ 18፣ 2016 ዓ.ል በአዲስ አበባ ባደረገው የ2ኛ ዓመት፣ 4ኛ መደበኛ ጉባዔ፣ የክልልና የከተማ አሥተዳደር የእስልምና ጉዳይ ምክር ቤቶች የ2016 ዓ.ል የሥራ አፈጻጸማቸውን እንዲገመግሙ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል።

የጋምቤላ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የሥራ አፈጻጸም ገምጋሚ ቡድን በዛሬ ውሎው በከፍተኛ ምክር ቤቱ የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውሮ መጎብኘቱን ከሸይኽ ሑሴን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc13
ጥቅምት 28፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ኡላ 6፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት የዓረብ ሊግ ተጠባባቂ ኃላፊን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የዐረብ ሊግ ተጠባባቂ ኃላፊ የኾኑትን ሰዒዳ (Saida) ሙሐመድ ዑመር በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።

ፕሬዚደንቱ የዓረብ ሊግ ተወካይን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው ሲያነጋግሩ የአሁኑ የመጀመሪያቸው መኾኑ በውይይቱ ወቅት ተነስቷል።

በአፍሪካ ሕብረት እና በተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የዓረብ ሊግ ተወካይ የሆኑት ሰዒዳ ሙሐመድ ዑመር የዓረብ ሊግ ጽሕፈት ቤት ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ጋር በትምህርት፣ በማኀበራዊ ጉዳይ እና በልማት አብሮ ለመሥራት ፍላጎት እንዳለው ተናግረዋል።

በጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት ጽሕፈት ቤት በተደረገው ውይይት ኢትዮጵያ የዓረብ ሊግ አባል በምትኾንበት መንገድ ጉዳይ ዙርያ ሐሳብ ተነስቷል።

የዐረብ ሊግ ተጠባባቂ ኃላፊዋ ጥያቄው ተገቢውን መስፈርት አሟልቶ በኢትዮጵያ መንግሥት የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ከቀረበ ሁኔታዎችን በቅርበት ለመከታተል ያስችላል ብለዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሐጂ ኢብራሂም የውይይቱን በጎነት ገልፀው፣ የተፈጠረውን ዕድል ተጠቅመን መስሊሙን እና ሀገርን በሚጠቅም መልኩ ከዐረብ ሊግ ጋር ተቀራርቦ ለመሥራት የሚታየው ፍላጎት አበረታች እንደኾነ ተናግረዋል።

በውይይቱ ላይ የዐረብ ሊግ የፕሬስ ክፍል ኃላፊ ኢብራሂም አል ሱዳኒ፣ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ጸሐፊ ሸይኽ ሐሚድ ሙሳ እና የውጪ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊው ረዳት ፕሮፈሰር አደም ካሚል ተገኝተዋል።
========
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc13
ጥቅምት 28፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ኡላ 5፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የሕንጻ ዲዛይን አማካሪ ተወዳዳሪ ድርጅቶች የፋይናንስ ሰነድ ተከፈተ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በምክር ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ለሚያስገነባው ባለ 2 ምድር ቤት እና ባለ 13 ወለል የአፓርትመንት ሕንጻ ተጫራች የዲዛይን አማካሪ ድርጅቶች ያቀረቡት የፋይናንስ ሰነድ በዛሬው ዕለት በተጫራቾችና በታዛቢዎች ፊት ተነበበ።

በዛሬው ዕለት የፋይናንስ ሰነዳቸው በጠቅላይ ምክር ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተከፍቶ የተነበበው የዲዛይን አማካሪ ድርጅቶች ጥቅምት 21፣ 2017 ዓ.ል. በዚሁ አዳራሽ በይፋ በተከፈቱ የቴክኒክ ሰነድ : ሰነዶቻቸው መስፈርቶቹን ማሟላታቸው በቴክኒክ ኮሚቴ የተረጋገጠላቸው ድርጅቶች መኾናቸው ተነግሯል።

በጠቅላይ ምክር ቤቱ የፕሮጀክት ፅ/ቤት አማካሪዎች ጠቋሚነት በፕሮጀክት አፈጻጸማቸው መልካም ስም ካላቸው የመንግሥት እና የግል ድርጅቶች ወደ ፋይናንስ ሰነድ ውድድር ምዕራፍ ካለፉት ተወዳዳሪዎች መካከል አንደኛውየመወዳደሪያ ሰነድ ማቅረቢያ መስፈርቱን ባለሟሟላቱ ከጨረታው መሰረዙ ተነግሯል።

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገነባው ባለ 2 ምድር ቤት (B2)፣ 13 ወለል (G+13) የአፓርትመንት ሕንጻ የዲዛይን አማካሪ ድርጅቶች ጨረታ በተመረጡ ድርጅቶች መካከል ብቻ የተከናወነ እንደኾነ መነገሩ ይታወሳል።

የጨረታውን ሂደት አስመልክቶ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ አብዱልዓዚዝ አሎ ጠቅላይ ምክር ቤቱ የፋይናንስ ግልፀኝነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የአሠራር ሂደቶችን ተግባራዊ በማድረግ ላይ እንደኾነ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ ሕግን መሠረት አድርጎ እየሠራ ለመሆኑ ይህኛውን ጨምሮ ለተለያዩ ፕሮጀክቶች እየወጡ ያሉ ጨረታዎች እየተካሄዱ ያሉበት ሂደት አመላካች እንደኾነ አቶ አብዱልዓዚዝ ተናግረዋል።

ዛሬ በተጫራቾችና በታዛቢዎች ፊት በይፋ ተከፍቶ የተነበበው የዲዛይን አማካሪ ድርጅቶች የፋይናንስ ሰነድ ተጣርቶ ከቀናት በኋላ አሸናፊው ድርጅት ለሕዝብ ይፋ እንደሚሆን ምክትል ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል።

​========
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc13
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የልማት ክንፍ ለኾነው ለኢትዮጵያ ሙስሊሞች የልማት ኤጀንሲ የቢሮ ማስፋፊያ ግንባታ ግልፅ ጨረታ መስከረም 28፣ 2017 ዓ.ል በተቋሙ የፌስቡክ ገጽ፣ በኤጀንሲውና በተለያዩ መስጂዶች የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያውን ለሕዝብ ይፋ  አድርጎ ጥቅምት 19፣ 2017 ዓ.ል | ረቢዑል ሳኒ 26፣ 1446 ዓ.ሒ  የተከፈተው ጨረታ ፣ ጊዜያዊ የጨረታ ውጤት
ሕዳር 2፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ኡላ 9፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
በሸሪዓ ፍርድ ቤቶች በሚታዩ ችግሮችና መፍትኄዎቻቸው ላይ ጥናት ያካሄደው ኮሚቴ የጥናቱን ሰነድ ለጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት አስረከበ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

በፌዴራል የሸሪዓ ፍርድ ቤቶች በሚታዩ ችግሮችና መፍትኄዎቻቸው ላይ ያተኮረ ጥናት ለማካሄድ የተቋቋመው ኮሚቴ የጥናቱን ሰነድ ለኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት ለክቡር ዶክተር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ አስረከበ።

የጥናት ኮሚቴው በጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት፣ በሸሪዓ ፍርድ ቤት እና በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አማካይነት መዋቀሩን ክቡር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ተናግረዋል።

የጥናት ኮሚቴው ስብጥርን በተመለከተ ከጠቅላይ ምክር ቤቱ የዓሊሞች ጉባዔ ጽሕፈት ቤት የተመረጡ ዓሊሞችና ሦስቱ ከፍተኛ የሕግ ባለሙያዎች ዳኞች መኾናቸውን የክብር ዶክተር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ተናግረዋል።

ሚያዚያ 30፣ 2016 ዓ.ል የተመሠረተውና በፌደራል የሸሪዓ ፍርድ ቤቶች አደረጃጀት፣ በሰው ኃይል አስተዳደርና በአገልግሎት አሰጣጥ፣ እንዲሁም በሕጉ ማዕቀፍ ላይ የሚታዩ ችግሮችን በመለየት የመፍትኄ ሐሳብ ያቀረበውን ሰነድ፣ የጥናት ኮሚቴው አባላት ዶክተር ሼይኽ ሙሐመድ ሐሚዲንና የሕግ ባለሙያው አብዱልሐኪም ጀማል ለክቡር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም አስረክበዋል።

በሰነዱ ርክክብ ወቅት ፕሬዚደንቱ ሲናገሩ የሸሪዓ ፍርድ ቤቶች አገልግሎት አሰጣጥና መፍትኄው ላይ ያተኮረውን ይህን ጥናት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ላከናወኑት የጥናት ቡድኑ አባላት በራሳቸውና በጠቅላይ ምክር ቤቱ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ፕሬዚደንቱ ይህን ሰነድ ከጠቅላይ ምክር ቤቱ የዓሊሞች ጉባዔ ምክትል ሰብሳቢና የፈትዋ ኮሚቴ ሰብሳቢ ከኾኑት ከዶክተር ጀይላን ኸድር ጋር አብረው መቀበላቸውን ጠቅሰው ጥናቱን ወደ ሥራ ለመተርጎም ከሚመለከተው አካል ጋር በመኾን እንሠራለን ብለዋል።
••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በምክር ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ለሚያስገነባው ባለ 2 ምድር ቤት እና ባለ 13 ወለል የአፓርትመንት ሕንጻ ተጫራች የዲዛይን አማካሪ ድርጅቶች ያቀረቡት የአፓርትመንት ሕንጻ የዲዛይን እና የኮንትራት አማካሪ የፋይናንስ ሰነድ
ጥቅምት 28፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ኡላ 5፣ 1446 ዓ.ሒ ተከፍቶ መነበቡ ይታወሳል።

የጊዜያዊ የጨረታዊ ውጤት መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል።
ኅዳር 3 ፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ኡላ 11፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት የሱዳን ዓለምአቀፍ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዚደንትን ተቀብለው አነጋገሩ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የሱዳን ዓለምአቀፍ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዚደንት የኾኑትን ፕሮፈሰር ጧሃ አብዲ ጧሃን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።

የትምህርት (Education) ባለሙያ የኾኑት ፕሮፈሰር ጧሃ አብዲ በኢትዮጵያ የዓረብኛ ትምህርትን ለማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት እና ሌሎች የጠቅላይ ምክር ቤቱ አመራሮች ጋር ሰፋ ያለ የሐሳብ ልውውጥ አድርገዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ጠቅላይ ምክር ቤቱ የአረብኛ ትምህርትን ለማሳደግ ተግቶ እንደሚሠራ በውይይቱ ላይ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ የሦስት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኙት ፕሮፌሰር ጧሃ አብዲ ከአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ቀጥሎ በትምህርት ሚኒስቴር ዓረብኛን ለማስተማር እውቅና የተሰጠውን አወልያ የዓረብኛ ኮሌጅን መጎብኘታቸውን ለማወቅ ተችሏል።

በጉብኝታቸው ወቅትም፣ በኮሌጁ ስለሚሰጠው የዓረብኛ ትምህርት ይዘቶች እና በሥርዓተ ትምህርቱ ዙሪያ ሰፋ ያለ ገለጻ እንደተደረገላቸው ታውቋል።

ፕሮፌሰር ጧሃ አብዲ ጧሃ ከክቡር ሸይኽ ሐጂ ጋር በተወያዩበት ወቅት የአወልያ የዓረብኛ ኮሌጅ መምህራንን አቅም በመገንባት ኮሌጁን ወደ ዩኒቨርሲቲ ማሳደግ በሚቻልበት መንገድ ዙሪያ ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ጋር አብሮ ለመሥራት ፍላጎት ያላቸው መኾኑን ተናግረዋል።
========
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
ሕዳር 4፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ኡላ 11፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
………………………………………………………………………
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሠራተኞች የምስጋና መርኃግብር አካሄዱ፡፡
………………………………………………………………………

አዲስ አበባ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሠራተኞች በዛሬው ዕለት በጠቅላይ ምክር ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ለአዲሱ የለውጥ አመራር የምሥጋና መርኃግብር አዘጋጁ፡፡

በምሥጋና መርኃግብሩ ላይ አዲሱ የለውጥ አመራር ሥራ ከጀመረ በኋላ ባሉት ሁለት ዓመታት ለተቋሙ ሠራተኞች በጥናት ላይ የተመሠረተ የደሞዝ ጭማሪና የጥቅማ ጥቅም ማስተካከያ ማድረጉ ተነግሯል።

በመርኃግብሩ ላይ የተቋሙን ሠራተኞች በመወከል ንግግር ያደረጉት ሐጂ አብዱልፈታህ ብርሃኑ፣ በተለያዩ ጊዜያት ጠቅላይ ምክር ቤቱን የመሩ ኃላፊዎች የሠሯቸው በጎ ተግባራት እንደተጠበቁ ሆነው፣ አዲሱ የለውጥ አመራር ከሐምሌ 2014 ዓ.ል ጀምሮ የሕዝበ ሙስሊሙ የጋራ ተቋም ጠንካራ እንዲኾን፣ በሰው ኃይል፣ በአደረጃጀት እና በአሠራር በርካታ ጠቃሚ ተግባራት ማከናወኑን አስታውሰዋል።

ሐጂ አብዱልፈታህ መጅሊሱ ለሕዝበ ሙስሊሙ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት የሚችል ጠንካራ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ግንኙነት ያለው ተቋም እንዲኾን አዲሱ አመራር እየሠራ ያለው የለውጥ ሥራ የሚመሠገን መኾኑን ተናግረዋል።

አመራሩ ሠራተኛው ያለበትን ተጨባጭ የኑሮ ሁኔታ በመረዳት ለሠራተኞቹ ያደረገው የደሞዝ ጭማሪና ጥቅማ ጥቅም የአመራሩን አርቆ አሳቢነትና መልካምነት እንደሚያሳይ የጠቀሱት ሐጂ አብዱልፈታህ፣ ይህ በጎ እርምጃ ሠራተኛው ሥራውን በበለጠ የኃላፊነት ስሜት እና በጥሩ መንፈስ እንዲያከናውን የሚያተጋ መሆኑን ተናግረዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሐጂ ከማል ሐሩን ባለፉት ሁለት ዓመታት አስተዳደሩ ከዚህ ቀደም የነበረውን ዝቅተኛ የሠራተኞች ደሞዝ በጥናት ላይ በመመሥረት ሶስት ጊዜ የደረጃው ማስተካከያ ማድረጉን ተናግረዋል።

ተቋሙ ብቃት ላለው የሰው ኃይል ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጥ መኾኑን የጠቀሱት ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ አዲሱ የሠራተኞች የደሞዝ ማስተካከያ የተቋማዊ ለውጡ ውጤታማነት አንዱ ማሳያ መኾኑን ተናግረዋል።

በቀጣይም ተቋሙ ሕዝበ ሙስሊሙ የጣለበትን አደራ ለመወጣት ከሠራተኛው ጋር ይበልጥ ተቀራርቦ እንደሚሠራ ሐጂ ከማል ሐሩን ተናግረዋል።

መርኃግብሩን መነሻ በማድረግ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሠራተኞች ለበርካታ ዓመታት ዝቅተኛ ደሞዝ ተከፋይ ኾነው መቆየታቸውን የተገነዘበው አመራሩ የሠራተኛውንና የቤተሰቡን ሕይወት ለማሻሻል በጥናት ላይ የተመሠረተ ሥራ ሲሠራ መቆየቱን ተናግረዋል።

በዚህም በየደረጃው የደመወዝና የጥቅማጥቅም ማስተካከያ መደረጉን አስታውሰው፣ ይህ በቂ ነው ብለው እንደማያምኑ ተናግረዋል።

አመራሩ በቀጣይም ከሠራተኞች ጋር ተከታታይ የምክክር መድረክ እንደሚያዘጋጅ የተናገሩት ክቡር ፕሬዚደንቱ፣ ሠራተኛው በሥራው ውጤታማ እንዲኾንና ከአሁኑ በተሻለ መሥራት እንደሚጠበቅበት ተናግረዋል።
…………………………………
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
ኅዳር 4 ፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ኡላ 12፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
………………………………………………………………………
በጠቅላይ ምክር ቤቱ ግቢ ለሚገነባ መስጂድና የቅጥረ ግቢ አጥርና ዋና በር ግንባታ የወጣው ጨረታ ተከፈተ።
………………………………………………………………………
አዲስ አበባ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በቅጥረ ግቢው ውስጥ ሊያስገነባ ላሰበው መስጂድ እና ደረጃውን የጠበቀ የቅጥረ ግቢ አጥርና ዋና በር ግንባታ ሥራ ያወጣው የዲዛይንና የኮንትራት አስተዳደር ጨረታ በይፋ ተከፈተ፡፡

የጠቅላይ ምክር ቤቱ የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብዱልሃዲ ሙሐመድ በጠቅላይ ምክር ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሊገነባ ለታቀደው መስጂድና የቅጥረ ግቢ አጥርና ዋና በር ግንባታ ሥራ የወጣውን ጨረታ ሰነድ የገዙት ተጫራች ድርጅቶች አሥራ አንድ መኾናቸውን ተናግረዋል፡፡

ከእነዚህ መካከል የጨረታውን ሰነድ ሞልተው በማስገባት ዛሬ በይፋ በተከፈተው የጨረታ ሰነድ መክፈት ስነ ሥርዓት ላይ የተገኙት ሰባቱ ድርጅቶች መኾናቸውን ተናግረዋል።

ታዛቢዎች በተገኙበት በተካሄደው የጨረታ መክፈቻ ስነ ሥርዓት ላይ በተጫራቾች የቀረቡት የቴክኒክ እና የፋይናንስ ሰነዶች መኾናቸውን ጠቅሰው፣ በጨረታው ስነ ሥርዓት መሠረት የቴክኒክ ሰነዱ ተከፍቶ በባለሙያዎች ከተገመገመ በኋላ 70 ከመቶ ያሟላ ሆኖ ሲገኝ፣ የፋይናንስ ሰነዶቹ እንዲሁ በይፋ እንደሚከፈቱ ተናግረዋል።

………………………………………………………………………
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
ኅዳር 5፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ኡላ 12፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
"ወጣቶች የየትኛውም ዘርፍ የጀርባ አጥንት፣ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ምሰሶ እና የዲኑ ብርሃን ናቸው።"
- የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

"ወጣቶች የየትኛውም ዘርፍ የጀርባ አጥንት፣ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ምሰሶ እና የዲኑ ብርሃን ናቸው" ሲሉ የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ተናገሩ።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ይህን የተናገሩት በዛሬው ዕለት በተካሄደው የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል የምሥረታ ጉባዔ ላይ ነው።

በምሥረታ ጉባዔው ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዑስታዝ አብበከር አሕመድ የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች በለውጡ ሂደት ውስጥ ጉልህ አሻራቸውን ያሳረፉ መኾናቸውን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች በድምጻችን ይሰማ የመብት ትግል ታሪክ የጎላ ሚና የተጫወቱ መኾናቸውንም ዑስታዝ አቡበከር አስታውሰዋል።

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ስር ለተመሠረተው የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል አሥራ አንድ የአመራር አባላት ተመርጠዋል።

የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል የኃላፊነት ቦታ ውክልናን፣ የትምህርት ዝግጅትን፣ ማኅበረሰባዊ አበርክቶንና ጠንካራ ኃላፊነትን የመወጣት ዝግጁነትን ከግንዛቤ ያስገባ መኾኑን ተናግረዋል።

ለኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል በአመራርነት የተመረጡት የሚከተሉት ወጣቶች ናቸው፦

ዑስታዝ ሐይደር ከድር አብዱልቃድር (ፕሬዚደንት)
ዑስታዝ አብዱልዓዚዝ ሙሐመድ (ምክትል ፕሬዚደንት)
ኢንጂነር ዑስታዝ ከማል አረቦ አሕመድ (ዋና ፀሐፊ)
ዑስታዝ ፈናን ሙሐመድ - አባል
ዑስታዝ አማር ሸይኽ አሚኖ ኢብሮ - አባል
ዑስታዝ ዳውድ ዓሊ - አባል
ዑስታዝ ፋሩቅ ሰዒድ - አባል
ዑስታዝ ሰዒድ ሃይማኖት - አባል
ዑስታዝ ሙሐመድ አሕመድ - አባል
ዑስታዝ አብዱልፈታህ አብዱረህማን - አባል
ዑስታዝ ኢሳም አብዱረህማን - አባል ተደርገው መመረጣቸው ይፋ ሆኗል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ በጠቅላይ ምክር ቤቱ ስር ለተመሠረተው የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ባደረጉት ንግግር፣ ወጣቶቹ በጥንቃቄና ጊዜ ተወስዶ ወደ ኃላፊነት እንደመጡ ተናግረዋል።

አንድነትን መሠረት አድርገው፣ ሁሉንም ወጣት አስተሳስረው እና አስተባብረው፣ ከምንም በላይ ለሰላም ቅድሚያ በመስጠት የሀገሪቱ ሙስሊም ወጣቶች ሀገራዊ ሚና የጎላ እንዲሆን ትልቅ ኃላፊነት አለባችሁ ብለዋል።

በመጨረሻም፣ የዓሊሞች ጉባዔ ምክትል ሰብሳቢና የፈትዋ ኮሚቴ ዋና ሰብሳቢው ዶክተር ጀይላን ኸድር ለተመረጡት የካውንስሉ አመራር አባላት የአደራ ቃል አስገብተዋቸዋል።

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የስብሰባ አዳራሽ በተከናወነው የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ምሥረታ ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ምክትል ፕሬዚደንት ሸይኽ አብዱልዓዚዝ አብዱልወሊ፣ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሱልጣን አማን ኤባ፣ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሥራ አስፈጻሚዎች፣ የዑለማ ጉባዔ ጽሕፈት ቤት አባላት፣ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሐጅ ከማል ሐሩን፣ የሴቶችና የወጣቶች ዘርፍ ኃላፊዋ ዑስታዛ ፋጡማ ሐሰን እና
ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

​••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
ሕዳር 5፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ኡላ 13፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ             
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ለከፍተኛ እስላማዊ የትምህርት ተቋማት ኃላፊዎች ሥልጠና ተሰጠ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዓሊሞች ጉባዔ ጽሕፈት ቤት፣ ከሱዳን ዓለምአቀፍ እስላማዊ  ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለከፍተኛ እስላማዊ የትምህርት ተቋማት ኃላፊዎች የአቅም ግንባታ ሥልጠና ሰጠ።

የሱዳን ዓለምአቀፍ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዚደንት በኾኑት ፕሮፌሰር ጧሃ አብዲ የተሰጠው ይህ የአቅም ግንባታ ሥልጠና በከፍተኛ እስላማዊ የትምህርት ተቋማት አመሠራረት ላይ ያተኮረ መኾኑን በዓሊሞች ጉባዔ ጽሕፈት ቤት ሥርዓተ ትምህርት ማረጋገጫ ኃላፊ ዶክተር አብደላ ኸድር ተናግረዋል።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ ሁለት ሀገርአቀፋዊ ከፍተኛ እስላማዊ የትምህር ተቋማት ለመመሥረት በጥናት ላይ መኾኑን የተናገሩት ዶክተር አብደላ፣ በሰባት ሀገራት ቅርንጫፎች ከፍቶ የማስተማር ከስድሳ በላይ ዓመታት ልምድ ካለው ከሱዳን ዓለምአቀፍ ዩኒቨርሲቲ ሰፊ ልምድ መገኘቱን ዶክተር አብደላ ተናግረዋል።

ዛሬ በጠቅላይ ምክር ቤቱ የዓሊሞች ጉባዔ ጽሕፈት ቤት  መሰብሰቢያ አዳራሽ በተሰጠው የአቅም ግንባታ ሥልጠና ላይ የስምንት ከፍተኛ እስላማዊ የትምህርት ተቋማት  ኃላፊዎች ታድመውበታል።
••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
ኅዳር 7፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ኡላ 15፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፋውንዴሽን ለጠቅላይ ምክር ቤቱ ሃይማኖታዊ መጻሕፍትን አስረከበ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፋውንዴሽን በተለያዩ ጊዜያትና ሁኔታ በመንገደኞች የተረሱ ቁርኣን እና ሃይማኖታዊ መጻሕፍትን ለኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስረከበ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፋውንዴሽን የሥራ ኃላፊ አቶ ፈቲህ ካሚል አቡበከር ያመጡትን ቁርኣን እና ሃይማኖትዊ መጻሕፍት ለጠቅላይ ምክር ቤቱ የሥራ አስፈፃሚ አባል የሆኑት ሼይኽ አብዱልሐሚድ አሕመድ ተረክበዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሐጂ ከማል ሐሩን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ፋውንዴሽን ቁርኣን እና ሃይማኖታዊ መጻሕፍትን መረከባቸውን የሚገልጽ ማሥረጃ ሰጥተዋል።

በርክክብ ስነ-ሥርዓቱ ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ሐጂ ከማል ሐሩን የጠቅላይ ምክር ቤቱ አጋር የኾነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ታማኝነትና የተቀደሰ ተግባር ያስደሰታቸው መኾኑን ተናግረዋል።

ዋና ሥራ አስኪያጁ አክለውም ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ያለው የረጅም ጊዜ መልካም ግንኙነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፋውንዴሽን የሥራ ኃላፊ አቶ ፈቲህ ካሚል አቡበከር በተመሳሳይ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እና ለአብሮኆት ቤተ መጻሕፍት ማስረከባቸዉን ተናግረዋል።

​​••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1