Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
11.4K subscribers
5.18K photos
76 videos
20 files
870 links
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
Download Telegram
ነሐሴ18 ፣ 2016 ዓ.ል | ሰፈር 20 ፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيم

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ጉባኤ እየተከናወነ ይገኛል

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት መደበኛ የ2ኛ ዓመት 4ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በእስቴይ ኢዚ- ፕላስ ሆቴል በቁርአን ተከፍቶ ጉባኤው በመካሄድ ላይ ይገኛል።
ነሐሴ 21፣ 2016 ዓ.ል | ሰፈር 23፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ፕሬዚደንቱ በኢትዮጵያ የአልጄሪያ አምባሳደርን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙት የአልጄሪያ አምባሳደር ክብርት ሰልማ ማሊክን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።

በዚሁ ጊዜ ክቡር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የኢትዮጵያ እና የአልጄሪያ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረ መምጣቱን ጠቅሰው፣ አዲስ ለተሾሙት ክብርት አምባሳደር ሰልማ ማሊክ መልካም የሥራ ጊዜ ይሆንላቸው ዘንድ ምኞታቸውን ገልፀዋል።

አምባሳደር ሰልማ ማሊክ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለተደረገላቸው አቀባበል አመሥግነው፣ የኢትዮጵያና የአልጄሪያ የሁለትዮሽ ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን ተናግረዋል።

ክብርት አምባሳደሯ፣ በአልጄሪያ ዘንድሮ የሚጀመር ነፃ የትምህር ዕድል መኖሩንና የዚህ ዕድል ተጠቃሚ ከሚኾኑ ሀገራት አንዷ ኢትዮጵያ እንደኾነች ጠቅሰው፣ ለዚህ የከፍተኛ ትምህርት ዕድል የምልመላ መስፈርት ሰነዱን ለክቡር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም አስረክበዋል።

ክቡር ሼይኽ ሐጂ በበኩላቸው የአልጄሪያ መንግሥት ለኢትዮጵያ ለሰጠው ነጻ የትምህርት ድል በጠቅላይ ምክር ቤቱ እና በራሳቸውም ስም ምሥጋና አቅርበዋል።

በቀጣይም ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከኤምባሲው ጋር በጋራ ጉዳዮች ላይ በትብብር እንደሚሠራ ክቡር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም መናገራቸውን የፕሬዚደንቱ ጽሕፈት ቤት ቃል አቀባይ ተናግረዋል።
••••••••••
የኢ.እ.ጉ.ጠ. ም/ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | twitter.com/eiasc1
ነሐሴ 25፣ 2016 ዓ.ል | ሰፈር 27፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيم
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጠቅላይ ምክር ቤቱ በቀጣዩ ዓመት ሸሪዓን መሠረት ያደረገ ምርጫ ያከናውናል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በዛሬው ዕለት የምክር ቤቱን አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ አስመልክቶ ለጋዜጠኞች ገለጻ አደረገ።

በዚሁ ገለጻ ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ፣ ጠቅላይ ምክር ቤቱ በቀጣዩ ዓመት ምርጫ እንደሚያካሂድና ምርጫው ሸሪዓን መሠረት ያደረገ እንደሚኾን ተናግረዋል።

"ለሃይማኖት ተቋማት አመራርነት የሚካሄድ ምርጫ ፖለቲካዊ ምርጫ አይደለም" ያሉት ፕሬዚደንቱ፣ "የሃይማኖት ተቋም 'ከመረጣችሁኝ ይህን እሠራለሁ፣ ምረጡኝ' ተብሎ ለሥልጣን የሚፎካከሩበት አይደለም" ሲሉ ተናግረዋል።

ቀጣዩ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ምርጫ በሰላማዊ እና ኃላፊነት በተሞላበት መንፈስ እንዲካሄድም አሳስበዋል።

አሁን በአመራር ላይ የሚገኘው መጅሊስ ሕዝበ ሙስሊሙን ለማገልገል ኃላፊነት ከተረከበ 25 ወራትን እንዳስቆጠረ የጠቀሱት ክቡር ፕሬዚደንቱ፣ ኃላፊነቱን ከተረከበ ጀምሮ ሥራ አስፈጻሚው ራሱን አደራጅቶ፣ የአካታችነት መርኅን በመከተል በክልሎችም እስከ አካባቢ (አጥቢያ) መስጂድ ድረስ የሕዝበ ሙስሊሙን የጋራ ተቋም ለማጠናከር በርካታ ሥራዎች መሠራታቸውን አብራርተዋል።

ክቡር ፕሬዚደንቱ የጠቅላይ ምክር ቤቱ አመራር ኃላፊነቱን ከተረከበበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት ሁለት ዓመታት ያከናወናቸውን ዐበይት ተግባራት ሲያብራሩ፣ በአብሮነት እና በሰላም ጉዳይ፣ በአማራጭ የፋይናንስ ምንጭ ዙሪያ፣ በግልግል ሸንጎ እና በሸሪዓ ፍርድ ቤት የተሠሩ ሥራዎችንና ያጋጠሙ ችግሮችን አብራርተዋል።

በተጨማሪም ፕሬዚደንቱ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የጋራ ተቋም የኾነው ጠቅላይ ምክር ቤቱ፣ በውጪ ግንኝነት ረገድ ከምንጊዜውም በላቀ ደረጃ ሰፊ ሥራዎችን መሥራቱን ተናግረዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራር ከ40 በላይ በሚኾኑ ዓለም አቀፍ ጉባዔዎች ላይ በመድረክ ጥናታዊ ጽሑፎችን በማቅረብ ጭምር ባደረገው ንቁ ተሳትፎ፣ የኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ገጽታ ከፍ ወዳለ ምዕራፍ መሻገሩን ክቡር ፕሬዚደንቱ ተናግረዋል።

በተጨማሪም፣ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ የሙስሊም ሀገራት አምባሳደሮች ከተቋሙ ጋር ባደረጉት ግንኙነት ከሙስሊሙ ማኅበረሰብም አልፎ ለሀገር በሚጠቅም ጉዳይ ላይ የሁለትዮሽ ግንኙነት መደረጉን ክቡር ፕሬዚደንቱ አውስተዋል።

የ1445 ዓ. ሒጅራ የሐጅ ክንውንን በተመለከተ፣ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ያሳካቸውን፣ የነበሩበትን ክፍተቶች እና የተገኙ ተመክሮዎችን በተመለከተ ደግሞ፣ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ምክትል ፕሬዚደንትና የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ተጠሪው ሸይኽ አብዱልዓዚዝ ለጋዜጠኞቹ ማብራራያ ሰጥተዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሐጅ ከማል ሐሩን በበኩላቸው አዲሱ አመራር የሕዝበ ሙስሊሙን አማና ተቀብሎ ወደሥራ ከገባ ጀምሮ ጥሩ መሻሻል እያደረገ ዋና ዋና በሚላቸው የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ አቅሙን በማዋል የተሻለ ተቋማዊ አሠራርን ለመገንባት ጥረት ሲያደርግ እንደቆየ አስረድተዋል።

ተቋማዊ ለውጡ አሁንም በሂደት ላይ መኾኑን የጠቀሱት ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ ሕግ በማጽደቅ፣ በአንድነትና በመተባበር ዙሪያ፣ በአቅም ግንባታና በማኅበረሰብ ተሳትፎ፣ እንዲሁም በተለያዩ ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ዙርያ የተከናወኑ ተግባራትን አውስተዋል።

በተጨማሪም ዋና ሥራ አስኪያጁ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ሙስሊሙ በአገራዊ ጉዳይ ላይ በቀጥታም ኾነ በተዘዋዋሪ የሀገር ገፅታን በበጎ መልኩ ለመቀየር፣ ሕገ-መጅሊሱን ተግባራዊ ለማድረግ እና ግልፅነት የሰፈነበት አሠራር ለመዘርጋት ትኩረት ሰጥቶ ያከናወናቸውን ተግባራት እና የገጠሙ ተግዳሮቶችን ለጋዜጠኞች በሰፊው አብራርተዋል።

በመጨረሻም፣ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሥራ ኃላፊዎች ወደ ኃላፊነት ከመጡ ጀምሮ የሠሩትንና ያለባቸውን ክፍተት አስመልክተው የሰጡትን ማብራሪያና ጋዜጠኞች ከማኅበረሰቡ ይደመጣሉ ያሏቸውን ቅሬታዎች መነሻ በማድረግ የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀርበዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት የተቋሙ የሥራ ኃላፊዎች ከሚዲያ ተቋማት የተሰጡ አስተያየቶችን በገንቢነት ተቀብለው፣ ለጥያቄዎቹ ምላሽ እንዲሰጥባቸው አድርገዋል።

​••••••••••
የኢ.እ.ጉ.ጠ. ም/ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | twitter.com/eiasc1
ነሐሴ 27፣ 2016 ዓ.ል | ሰፈር 29፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

ፕሬዝዳንቱ ሸሪዓን መሠረት ያደረገ የምርጫ መመሪያ እንዲዘጋጅ ትዕዛዝ ሰጡ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የክቡር ዶክተር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ በ2017 ዓ.ል ለሚደረገው የመጅሊስ ምርጫ ሸሪዓን መሠረት ያደረገ የምርጫ መመሪያ እንዲዘጋጅ ትዕዛዝ ሰጡ።

አዲሱ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አመራር ሀምሌ 11/2014 በሸራተኑ ጉባዔ ላይ በገባው ቃል መሠረት በ2017 ዓ.ል በቀጣይ ተቋሙን የሚመሩ አመራር አካላትን ምርጫ እንደሚያደርግ መግለፁ ይታወሳል ።

በዚህም መሰረት ጠቅላይ ምክር ቤቱ ለዑለማ ጉባዔ እና ለአማካሪ ቦርድ ፅ/ቤቶች እስከ መስከረም 3/2017 ዓ.ል ሸሪዓን መሠረት ያደረገ የምርጫ መመሪያ እንዲያዘጋጁ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት የክቡር ዶክተር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ትዕዛዝ አስተላልፈዋል ።


***
የኢ.እ.ጉ.ጠ. ም/ቤት ሕዝብ ግንኙነት

ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | twitter.com/eiasc1
ነሐሴ 28፣ 2016 ዓ.ል | ሰፈር 30፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيم
ለጠቅላይ ምክር ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት እና የሚዲያ ዘርፍ
ሰነድ አዘጋጅ ኮሚቴ ተመረጠ።
አዲስ አበባ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ በዛሬው ዕለት የጠቅላይ ምክር ቤቱን የሕዝብ ግንኙነትና የሚዲያ ዘርፍ ለማጠናከር ከመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ጋር የግማሽ ቀን ውይይት አካሄደ።

በአያ ሆቴል በተካሄደው በዚህ ውይይት ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ተጠሪ ሸይኽ ሑሴን ሐሰን፣ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎቹ የምክር ቤቱን ጥሪ አክብረው በመምጣታቸው ምሥጋና አቅርበው፣ የሕዝበ መስሊሙ ተቋም ከተመሠረተ 50 ዓመት ቢያስቆጥርም፣ የሕዝብ ግንኙነትና የሚዲያ ዘርፉ በሚፈለገው ደረጃ ያደገ አለመኾኑን ተናግረዋል።

ሸይኽ ሑሴን አክለውም የሕዝብ ግንኙነት ዘርፉ በአደረጃጀት እና በአሠራር የተዳከመ በመኾኑ ሙስሊሞች በሀገራቸው በተለያዩ ዘርፎች የሚጫወቱት ሚና እና ኢትዮጵያ በእስልምና ታሪክ ውስጥ ያላት ደማቅ አሻራ በስፋት እንዳይታወቅ ትልቅ ክፍተት እንደፈጠረ አብራርተዋል።

አያይዘውም፣ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ጋር የሚያደርገው ውይይት ክፍተቶችን ደፍኖ የተሻለ አሠራር ለመዘርጋት ትልቅ አርምጃ እንደሚሆን ተናግረዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ አብዱል ዓዚዝ አሎ በበኩላቸው የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ አሁናዊ ቁመናን ለባለሙያዎቹ አብራርተው ባለሙያዎቹ በነፃ መንፈስ መፍትኄ-ተኮር ውይይት እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱን የሕዝብ ግንኙነትና የሚዲያ ዘርፍ ለማጠናከር ለውይይት መነሻ የሚኾን ሰነድ ቀርቦ፣ ባለሙያዎቹ በቡድን ተከፋፍለው ውይይት አድርገዋል።

በቡድን ውይይቱ መጨረሻ ላይ ከየቡድኑ የተጨመቁ ሐሳቦች የቀረቡ ሲኾን፣ የሕዝብ ግንኙነትና የሚዲያ ዘርፍን በተመለከተ ከእስልምና ባህሪያት አኳያ ያሉ ተግዳሮቶች፣ ጥንካሬዎች፣ ስጋቶች፣ ዕድሎችና የመፍትኄ ሐሳቦች ተነስተዋል።

ከየቡድኖቹ የቀረቡ ሐሳቦችን እንደ መነሻ በመውሰድ ለጠቅላይ ምክር ቤቱ የሕዝብ ግንኙነትና የሚዲያ ዘርፍ ሙያዊ የሥራ ሰነድ የሚያዘጋጅ ሰባት አባላት ያሉት ኮሚቴ ተመርጧል።

በመጨረሻም የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሐጂ ከማል ሐሩን የጠቅላይ ምክር ቤቱን የሕዝብ ግንኙነትና የሚዲያ ዘርፍ ወደ ከፍታ ለመውሰድ እና በመረጃ ፍሰቱ ከሙስሊሙ ማኅበረሰብ ባሻገር ሀገርን ተጠቃሚ ለማድረግ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎቹ ለሚያበረክቱት አስተዋጽዖ ምክር ቤቱ ያለውን አድናቆት ገልፀዋል።

ዋና ሥራ አስኪያጁ አክለውም፣ ጠቅላይ ምክር ቤቱ የባለሙያዎችን ጥረቶችና አስተዋጽዖዎ አቅም በፈቀደ መጠን ሙሉ ኃላፊነት ወስዶ ለመደገፍ ዝግጁ መኾኑን ተናግረዋል።



***
የኢ.እ.ጉ.ጠ. ም/ቤት ሕዝብ ግንኙነት

ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | twitter.com/eiasc1
ጷጉሜ 3፣ 2016 ዓ.ል | ረቢዓል አወል 5፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
በሀገራዊ ምክክር በሚነሱ የሙስሊሙ አጀንዳዎች ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በጅማ እየተካሄደ ነው።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጋር በመተባበር በሀገራዊ ምክክር በሚነሱ የሕዝበ-ሙስሊሙ አጀንዳዎች ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በጅማ አዌቱ ግራንድ ሆቴል እያካሄደ ነው።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሕዝብ ግንኙነት ተጠሪ ሼይኽ ሑሴን ሐሰን የውውይት መድረኩን ሲከፍቱ ባደረጉት ንግግር፣ ጠቅላይ ምክር ቤቱ የሙስሊሙን ባለ 9 ነጥብ አጀንዳዎች ለሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ በሰነድ አዘጋጅቶ መላኩን አስታውሰዋል።

ለሀገራዊ መግባባት አስፈላጊ ናቸው ተብሎ የታመነባቸው ባለ 9 ነጥብ አጀንዳዎቹ በሀገራዊ፣ በሃይማኖታዊ፣ በመከባበር እና በጋራ ዕድገት ጥያቄዎች ላይ ትኩረት ያደረጉ መኾናቸውን ያወሱት ሼይኽ ሑሴን፣ የምክክር ኮሚሽኑም በትኩረት ያጤናቸዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።

የኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ተወካይ ሼይኽ ሹዓይብ ሸምሱ ሰነዱን በዝርዝር ለውይይቱ ተሳታፊዎች አቅርበው የቡድን ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።

በጅማ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው በሀገራዊ ምክክር የሕዝበ ሙስሊሙ አጀንዳዎች ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የውይይት መድረክ የጅማ ዞን እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የሥራ ኃላፊዎች፣ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የክልሎች፣የሰላምና የዲያስፖራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሳርቱ ሸምሰዲን መገኘታቸውን በስፍራው ከሚገኘው ቃል አቀባያችን የተገኘው መረጃ ጠቁሟል።

***
የኢ.እ.ጉ.ጠ. ም/ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | twitter.com/eiasc1
መስከረም 2፣ 2017 ዓ.ል | ረቢዑል ዓወል 9፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የፎቶ ዐዉደ-ርዕይ በታላቁ አንዋር መስጂድ ነገ ይከፈታል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ታሪክና ቅርስ ዘርፍ : ከታላቁ አንዋር መስጂድ የወጣቶች ጀመዓና ከፎቶግራፍ ባለሙያው አሕመድ ነጋ ጋር በመተባበር "የሰላሙ ነቢይ" በሚል መሪ ሐሳብ ያዘጋጁት የፎቶግራፍ ዐውደ-ርዕይ ጁምዓ መስከረም 3፣ 2017 ዓ.ል (ረቢዑል ዓወል 10/1446 ዓ.ሒ) በታላቁ አንዋር መስጂድ ቅጥር ግቢ ለሕዝብ ክፍት ይደረጋል።

የ1499 ዓ.ሒ የመዉሊድ አዘጋጅ ኮሚቴ አባል የኾኑት ሼይኽ አብዱልሐሚድ አህመድ ዐውደ-ርዕዩ የታላቁ ነቢይ ልደት (መውሊድ) እንደ ብሔራዊ በዓል መከበር ከጀመረበት ከ1967 ዓ.ል ጀምሮ በታላቁ አንዋር መስጂድ እና በተለያዩ ቦታዎች የተካሄዱ የመውሊድ በዓል ክዋኔዎችን የሚያሳዩ ታሪካዊ ፎቶግራፎች የሚቀርቡበት እንደኾነ ተናግረዋል።

ነገ ጁምዓ በታላቁ አንዋር መስጂድ የሚከፈተው ይኸው ዐውደ-ርዕይ ከመስከረም 3 እስከ መስከረም 8፣ 2017 ዓ.ል ለሕዝብ ክፍት ኾኖ እንደሚቆይ ሼይኽ አብዱልሐሚድ ተናግረዋል።

1 ሺህ 499ኛው የታላቁ ነቢይ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ.) ዝክረ-ልደት በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች ለማክበር ዝግጅቶች እንደተጠናቀቁ ለማወቅ ተችሏል።
​••••••••••
የኢ.እ.ጉ.ጠ. ም/ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | twitter.com/eiasc1
መስከረም 3፣ 2017 ዓ.ል | ረቢዑል ዓ. 10፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የፎቶ ዐዉደ-ርዕይ በታላቁ አንዋር መስጂድ ተከፈተ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ታሪክና ቅርስ ዘርፍ ከታላቁ አንዋር መስጂድ የወጣቶች ጀመዓ እና ከፎቶግራፍ ባለሙያው አሕመድ ነጋ ጋር በመተባበር "የሰላሙ ነቢይ" በሚል መሪ ሐሳብ ያዘጋጁት የፎቶግራፍ ዐውደ-ርዕይ በታላቁ አንዋር መስጂድ ቅጥር ግቢ ተከፈተ።

ዐዉደ-ርዕዩ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የእስላማዊ ቅርስና ታሪክ ዘርፍ ተጠሪ ሼይኽ ሙሐመድ አሚን ሰይድ አያሽ እና በታላቁ አንዋር መስጂድ ኢማምና ኸጢብ ሼይኽ ጧሀ ሙሐመድ ሐሩን ተከፍቷል።

በዐዉደ-ርዕዩ መክፈቻ ላይ ሼይኽ ሙሐመድ አሚን ሰይድ ሲናገሩ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የእስላማዊ ቅርስና ታሪክ ዘርፍ የሙስሊሙን ማኅበረሰብ  ታሪክና ቅርስ ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማሸጋገር ሥራዎችን እየሠራ ነው ብለዋል።

በቀጣይም በሙስሊሙ ማኅበረሰብ እጅ የሚገኙ የሚዳሰሱ ቅርሶችን የማሰባሰብ ሥራ እንደሚሠራ ጠቅሰው፣ ሙስሊሙ ማኅበረሰብ የበኩሉን አስተዋጽዖ እንዲያበረከት ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሥራ አስፈጻሚ እና የመዉሊድ በዓል አስተባባሪ ኮሚቴ አባል የኾኑት ሼይኽ አብዱልሐሚድ ዛሬ  የተከፈተው የፎቶግራፍ ዐውደ-ርዕይ መውሊድ እንደ ብሔራዊ በዓል መከበር ከጀመረበት ከ1967 ዓ.ል ጀምሮ በታላቁ አንዋር መስጂድ እና በተለያዩ ቦታዎች የተካሄዱ የመውሊድ በዓል ክዋኔዎችን የሚያሳዩ ታሪካዊ ፎቶዎች የተካተቱበት በመሆኑ ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ዐውደ-ርዕዩን እንዲመለከት ጥሪ አቅርበዋል።
 
የታላቁ አንዋር መስጂድ ወጣት ጀምዓ ሰብሳቢ ሐይደር  ዳውድ በዚሁ ጊዜ ባደረጉት ንግግር ዛሬ የተከፈተው የፎቶግራፍ ዐውደ-ርዕይ ባለፉት አምስት አሠርት ዓመታት በታላቁ አንዋር መስጂድ የነበረውን የመውሊድ በዓል አከባበር በምልሰት ያሳያል ብለዋ።

ዐውደ-ርዕዩ እስከ መስከረም 8፣ 2017 ዓ.ል ለሕዝብ ክፍት  ሆኖ እንደሚቆይ ጠቅሰው፣ የጉብኝት ሰዓታቱ ለሴት ጎብኚዎች ከጧቱ 3:00 ሰዓት እስከ ረፋዱ 5:00 ሰዓት፣ ለወንድ ጎብኚዎች ደግሞ ከቀኑ 8:00 እስከ 11:00 ሰዓት እንደኾነ ተናግረዋል።

የፎቶ ባለሙያ አህመድ ነጋ በአዉደ ርዕዩ ላይ የቀረቡት ፎቶዎች በአንጋፋ ፎቶ አንሺዎች እና በእርሳቸው የተነሱ መሆናቸው ገልፀዉ ። ከአውደ ርዕዩ መጠናቀቅ በኋላ ለጠቅላይ ምክርቤቱ ኢስላማዊ ቅርስና ታሪክ ዘርፍ እንደሚያስረክቡ ተናግረዋል።

1 ሺህ 499ኛው የታላቁ ነቢይ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ.) ዝክረ-ልደት በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች የሚከበር ሲኾን፣ ከዝግጅቶቹ ውስጥ በሁለንተናዊ ስብዕናና አስተምህሯቸው ላይ ያተኮረውና "የሰላሙ ነቢይ" በሚል ርዕስ ነገ ቅዳሜ የሚደረገው የፓናል ውይይት እንደሚገኝበት ለማወቅ ተችሏል።
​••••••••••
የኢ.እ.ጉ.ጠ. ም/ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | twitter.com/eiasc1
መስከረም 4፣ 2017 ዓ.ል | ረቢዑል ዐ. 11፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
"የሰላሙ ነቢይ" በሚል መሪ ሐሳብ ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት ተካሄደ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በነገው ዕለት በድምቀት የሚከበረውን የነቢዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ.) ልደት ለመዘከር "የሰላሙ ነቢይ" በሚል መሪ ሐሳብ ያዘጋጀው የፓናል ውይይት በአያ ሆቴል ተካሄደ።

የፓናል ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሥራ አመራር፣ የመስጂድ እና የአውቃፍ ዘርፍ ተጠሪ ሸይኽ ሙሐመድ አሕመድ ያሲን፣ መውሊድ በኢትዮጵያ ትልቅ ታሪካዊ ፋይዳ ያለው መኾኑን አውስተው፣ የመተሳሰብ እና የአብሮነት እሴቱን ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሥራ አመራር አባልና የ1499ኛው የነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ.) መውሊድ አዘጋጅ ኮሚቴ አባል የኾኑት ሸይኽ አብዱልሐሚድ አሕመድ የታላቁን ነቢይ (ሶ.ዐ.ወ.) ዝክረ ልደት ሁለተናዊ ሰብዕናቸውን እና አስተምህሯቸውን በሚዘክሩ ልዩ ልዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር ተናግረዋል።

ቁርኣናዊ ሰብዕና የነበራቸው ታላቁ ነቢይ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ.) በሰላም፣ በመከባበር እና በመቻቻል ዙርያ ሰፊ አስተምህሮዎችን ትተው ያለፉ መኾናቸውን ያወሱት ሸይኽ አብዱልሐሚድ፣ በተሟላ ሰብዕና ምሳሌነታቸው ላይ ያተኮረ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በፓናል ውይይቱ ላይ ዑስታዝ አደም ካሚል ታላቁ ነቢይ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ.) ከሐበሻው ንጉሥ፣ አስሐመተ ነጃሺ ጋር የተለዋወጧቸውን ደብዳቤዎች በማጣቀስ፣ ኢትዮጵያ በእስልምና ታሪክ ውስጥ ያላትን ጉልህ አሻራ አብራርተዋል።

ዑስታዝ አሕመድ ኢስማዒል በበኩላቸው የነቢዩ ተልዕኮ እና የሕይወት ፈለግ ከሰላም ጋር ያለውን ቁርኝት እና ፍትኅ እና መተሳሰብ በሰላም ለአብሮ ለመኖር ያለውን ፋይዳ ጠቅሰዋል።

ሌላው የመድረኩ ተናጋሪ ኡስታዝ አሕመድ ሙስጠፋ ነቢዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ.) በሰዎች መካከል በማስማማት ረገድ የነበራቸውን የተለየ ጥበብ እና የግጭት አፈታት ዘዴዎችን አስመልክተው ሐሳባቸውን አቅርበዋል።

የፓናሉ አወያይ ኡስታዝ ሙሐመድ ጀማል አብዱልአዚዝ በቀረቡት ጽሑፎችና በተወሱት የነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ.) ፈለገገዋ ሕይወት ትሩፋቶች ዙርያ ተጨማሪ ሐሳቦችን ከሰነዘሩ በኋላ፣ የታዳሚ አስተያየቶች እንዲንሸራሸሩ አድርገዋል።

በፓነል ውይይቱ መጨረሻም፣ የነቢዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ.) የሕይወት ታሪክን መሠረት ያደረገ መንዙማ በመሻኢኮች ቀርቧል።
​••••••••••
የኢ.እ.ጉ.ጠ. ም/ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | twitter.com/eiasc1
መስከረም 5፣ 2017 ዓ.ል | ረቢዑል ዓ. 12፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
1 ሺህ 499ኛው የታላቁ ነቢይ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) መውሊድ በታላቁ አንዋር መስጂድ በድምቀት ተከበረ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

1 ሺህ 499ኛው የታላቁ ነቢይ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) የልደት በዓል (መውሊድ) በመላው ኢትዮጵያ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

የዝክረ ልደት በዓሉ በተለይ በአዲስ አበባ በታላቁ አንዋር መስጂድ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች፣ ዲፕሎማቶች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በርካታ ሕዝብ የከተማይቱ ሙስሊም ማኅበረሰብ በተገኘበት ደማቅ ስነ ሥርዓት ተከበረ።

በዓሉ በታላቁ የአንዋር መስጂድ ኢማምና ኸጢብ ሸይኽ ጧሐ ሙሐመድ ሐሩን በቁርኣን የተከፈተ ሲኾን፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ተቀዳሚ ፕሬዚደንት ሼይኽ አብዱልከሪም ሼይኽ በድረዲን ሱሩር በዓሉን አስመልክተው ንግግር አድርገዋል።

ሼይኽ አብዱልከሪም በዚሁ ንግግራቸው የአላህ (ሱ.ወ) እዝነት መገለጫ የኾኑት የታላቀ ነቢይ መወሊድ አንድነትትንና በሰላም አብሮ መኖርን፣ እንዲሁም የመተዛዘንን እሴት የሚያስታውስ በመኾኑ፣ ሕዝበ-ሙስሊሙ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ አደጋዎች ለተጎዱ ወገኖቻችን የእርዳታ እጁን እንዲዘረጋ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

አዲሱ ዓመት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ምርጫ የሚያደርግበት ወቅት መኾኑም በዓሉን ለየት እንደሚያደርገው ተናግረዋል።

ሁሉም ዜጋ ለሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም መሥራት አለበት ያሉት ተቀዳሚ ፕሬዚደንቱ፣ የሃይማኖት አባቶችና የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ለሀገር ሰላምና ለወንድማማችነት ሙጠናከር እንዲሠሩ ጥሪ አቅርበዋል።

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚደንት ሼይኽ ፈትሁዲን ሐጂ ዘይኑ ሙቅና፣ የዘንድሮው መዉሊድ "የሰላሙ ነቢይ" በሚል መሪ ቃል እየተከበረ መኾኑን ተናግረዋል።

ነብያችን ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) ሀገራችን ኢትዮጵያን የፍትኅ እና የእውነት ሀገር መኾኗን መናገራቸውን አስታውሰዋል።

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለሙስሊሙ ማኅበረሰብ የእውቀት ባለውለታ ለሆኑ ቀደምት መሻይኢኾች እውቅና መስጠት መጀመሩን ተናግረዋል።

በዚህ ዓመት ዘመን ተሻጋሪ ባለዉለታ ለሆኑት በታላቁ አንዋር መስጂድ ለአሠርት ዓመታት በኢማምነትና በምክትል ኢማምነት ዑማውን አገልግለው ላለፉት ለሐጅ ዙልመካ ጀማል እና ለሐጂ ሙስጠፋ ሐቢብ (ረሂመሁሏህ) የዘመን ተሻጋሪ ባለዉለታ የምስክር ወረቀት የተበረከተ ሲኾን፣ ሽልማቱን ቤተሰቦቻቸው ተቀብለዋል።

የዘንድሮው የመዉሊድ በዓል የሕዝበ-ሙስሊሙ የጋራ ተቋም በሆነው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ምሥረታ የ50ኛ ዓመት ዋዜማ ላይ እየተከበረ የሚገኝ መኾኑን አስታውሰዋል። ጠቅላይ ምክር ቤቱ የተመሠረተው በ1968 ሲኾን በቀጣዩ ዓመት 50ኛ ዓመቱን ይደፍናል።

የአዲስ አበባ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ የኾኑት ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ ሙስሊሙ ማኅበረሰብ በዓሉን ሲያከብር፣ የነቢዩ ሙሐመድን (ሶ.ዐ.ወ) ፈለግ በመከተል መልካም ሰናይ ምግባራቸውን አልቆ ሊያከብር እንደሚገባው ተናግረዋል።

የከተማው ሙስሊም ማኅበረሰብ የአዲስ አበባ ከተማበ አስተዳደር እያከናወናቸው በሚገኙ የሰላምና የልማት ሥራዎች ላይ ተሳታፊ በመኾኑ አመስግነው፣ በቀጣይ ይህንኑ ተሳትፎውን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ዋና ፀሐፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ ኢትዮጵያ የእውነትና የፍትኅ ሀገር እንደኾነች ነቢዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) መናገራቸው አስታውሰዉ፣ ዛሬ ሀገራቸውን ከሚወድዱ ወጣቶች ለሙሐመድ አል-አሩሲ እና ለዑስታዝ ጀማል በሽር ምሥጋናቸውን አቅርበዋል።

በበዓሉ ላይ የተገኙት የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ተሟጋች የተከበሩ ሙሐመድ ከማል አልአሩሲ፣ ሃይማኖትና ሀገርን መውደድ ነቢያችን ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) ያስተማሩን በመኾኑ ወጣቱ ትውልድ በተሰማራበት ሁሉ ለሀገሩ ዘብ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።

በበዓሉ ላይ በታላቁ ነቢይ (ሶ.ዐ.ወ) የላቀ ስብዕና እና አስተምህሮዎች ላይ ያተኮረ መንዙማ በታላቁ ማዲህ ሸይኽ ሙሐመድ አወል ሐምዛ ቀርቧል።

ዛሬ በታላቁ አንዋር መስጂድ በተከበረው 1 ሺህ 499ኛው የታላቁ ነቢይ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) የመውሊድ ክብረ በዓል ላይ በአዲስ አበባ ተቀማጭ የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶች ተገኝተዋል።

​••••••••••
የኢ.እ.ጉ.ጠ. ም/ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | twitter.com/eiasc1
መስከረም 11፣ 2017 ዓ.ል | ረቢዑል ዓ. 18፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
20ኛዉ የሙስሊም ዓለም አቀፍ መድረክ በሩሲያ እየተካሄደነው።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |


20ኛዉ  የሙስሊም  ዓለም አቀፍ መድረክ  በሩሲያ  እየተካሄደነው።


ሀገራችን ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳትፋችበት 20ኛ የሙስሊም አለም አቀፍ መድረክ በሩስያ ሞስኮ እየተካሄደ ነው።

የሰላም መንገድ፡  “ውይይት ለጋራ አብሮ መኖር መሰረት ነው” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ የሚገኘው 20ኛ የሙስሊም አለም አቀፍ መድረክ ከዓለም ሐገራት የመጡ ዓሊሞች ተሳታፊ ሆነውበታል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳይ ጠቅላየ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የክብር ዶክተር ሼይህ ሀጂ ኢብራሂም ሀገራችንን ወክለው ንግግር ማድረጋቸውን ከስፍራው የሚገኘው የጠቅላይ ምክር ቤቱ ቃል አቀባይ የላከው መረጃ ያመላክታል።


••••••••••
የኢ.እ.ጉ.ጠ. ም/ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | twitter.com/eiasc1
መስከረም 11፣ 2017 ዓ.ል | ረቢዑል ዓ. 18፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አወሊያ ትምህርት ቤቶችን በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የአወሊያ ትምህርት ቤቶች የቀጣይ አምስት ዓመታት ስልታዊ እቅድን (Strategic Plan) ለማዘጋጀት በዛሬው ዕለት በጠቅላይ ምክር ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሐጂ ከማል ሐሩን የውይይት መድረኩን በንግግር ሲከፍቱ ጠቅላይ ምክር ቤቱ በለውጥ ሂደት ላይ ያለ ተቋም መሆኑን ተናግረዋል።

ሐጂ ከማል አክለውም አወሊያ ትምህርት ቤት የተቋቋመበትን ዓላማ ለማሳካት የሚያስችል ስልታዊ እቅድ ለመንደፍ ከባለድርሻ አካላት ተቀራርቦ መወያየትና ለእቅዱ ግብዓት የሚኾኑ ሐሳቦችን ማሰባሰብ አስፈላጊ ነው ብለዋል።

አወልያ ትምህርት ቤቶች የለውጡ ታሪክ አካል መኾኑን ያስታወሱት ሐጂ ከማል፣ ትምህርት ቤቶቹ በለውጡ ሂደት መለወጥ ያለበትን እና መለወጥም የሚችለውን እውን ማድረግ እንዲችሉ ነፃነት ሊኖራቸው እንደሚገባ ተናግረዋል።

በመዘጋጀት ላይ ያለው ስልታዊ እቅድ የአወሊያ ተማሪዎችን ሁሉን አቀፍ በኾነ መልኩ ተወዳዳሪ ለማድረግና ተቋሙም የተሻለ ቁመና ላይ እንዲገኝ አስፈላጊ በመኾኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በዚህ የውይይት መድረክ ላይ በቅንነት ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ዋና ሥራ አስኪያጁ አሳስበዋል።

ሙስሊሙን ማኅበረሰብ በሀገሩ ጉዳይ ላይ ንቁ ተሳታፊ እና በሁሉም ዘርፍ ተወዳዳሪ ለማድረግ ስልታዊ እቅድ ነድፎ ሁሉን አቀፍ ማኅበረሰባዊ ለውጥ ማምጣት አስፈላጊ መሆኑን በአፅንዖት ተናግረዋል።

የአወሊያ እርዳታና ልማት ድርጅት ከሰኔ 2003 ዓ.ል ጀምሮ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አንዱ የማኅበራዊ ልማት ቅርንጫፍ በመኾን እያገለገለ መኾኑን የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ ሐጂ ሰዒድ አስማረ ተናግረዋል።

የትምህርቱ ዘርፍ በአሁኑ ጊዜ ከፍተኛ ተግዳሮት ያለበት በመኾኑ የአወሊያ ትምህርት ቤቶችን የቀጣይ አምስት ዓመታት ስልታዊ እቅድ ለማዘጋጀት የሚደረገው ጥረት ትውልዳዊም ሀገራዊም ኃላፊነት እንደሆነ ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል።

የአወልያ ትምህርት ቤቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ የትምህርት ጥራቱን እየጠበቀ በመምጣቱ በ2016 በተሰጠው አገር አቀፍ ፈተና የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተማሪዎቹን 97 በመቶ ያሳለፈ ሲሆን፣ የ12ኛ ክፍል ዉጤቱም ከቀዳሚው ዓመት መሻሻል የታየበት መኾኑን ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል።

አወሊያ የእርዳታና የልማት ድርጅት የጤና፣ የረድዔት እና የትምህርት አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም ቢኾንም፣ አብዛኛው ትኩረቱ (70 በመቶ) በትምህርት አገልግሎት ላይ መሆኑን ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል።

አወልያ ከ1988 ዓ.ል ጀምሮ የአረብኛ ቋንቋ ሲያስተምር የቆየና በመስኩም ብቸኛ እውቅና ያለው ኮሌጅ መሆኑን የጠቀሱት ሥራ አስኪያጁ፣ ከማኅበረሰብ አቃፊነቱ አኳያም 710 ተማሪዎችን በነጻ እንደሚያስተምር ተናግረዋል።

በዚሁ ጊዜ፣ የአወሊያ የቀድሞ ተማሪዎች ትምህርት ቤቱን ወደላቀ ደረጃ ለማድረስ በመሻት የሚካሄደውን የስልታዊ እቅድ ዝግጅት ወጪ ለመሸፈን ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የድርጅቱ የሥራ አመራር ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ አሽረፍ ጀማል የሀገራችን ትምህርት በአሁኑ ዘመን የገጠመውን ፈተና ተቋቁሞ ተወዳደሪ እና በስነ-ምግባር የታነጸ ትውልድ ለማፍራት ከአወልያ ባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር ማድረግና ዘመኑን የሚዋጅ ስልታዊ እቅድ የመንደፍ አስፈላጊነትን ተናግረዋል።

ስልታዊ እቅድ የማዘጋጀት ሐሳቡ ከተወጠነ የቆየ ቢኾንም፣ በነበረው የበጀት እጥረት ሳቢያ ውጥኑን ወደ ሥራ መቀየር ሳይቻል እንደቆየ አብራርተዋል።

የአወሊያ ትምህርት ቤቶች የአምስት ዓመት ስልታዊ እቅድን ለማዘጋጀት ከባለድርሻ አካላት ጋር የተካሄደውን የውይይት መድረክ የስልታዊ እቅዱ አዘጋጅ የኾነው ጋላክሲ ዊዝደም የምክር አገልግሎት እንዳዘጋጀው ለማወቅ ተችሏል።



••••••••••
የኢ.እ.ጉ.ጠ. ም/ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | twitter.com/eiasc1
መስከረም 12፣ 2017 ዓ.ል | ረቢዑል ዓ. 19፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
20ኛዉ የሙስሊም ዓለምአቀፍ መድረክ ሙፍቲ ሸይኽ ራዊ ዐይነዲንን በመምረጥ ተጠናቀቀ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
በሩስያ መዲና፣ መስኮብ የተካሄደውና ሀገራችን ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፈችበት 20ኛዉ የሙስሊም ዓለምአቀፍ መድረክ ሸይኽ ራዊ ዐይነዲንን በሙፍቲነት በመምረጥ ተጠናቀቀ።

በ20ኛዉ የሙስሊም ዓለምአቀፍ መድረክ ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ኢትዮጵያን በመወከል ታድመውበታል።

ሞስኮ ውስጥ በሚገኘው መስጂደል ጀዋሚዕ የመሰብሰቢያ  አዳራሽ "የሰላም መንገድ፡ ውይይት የተጣጣመ አብሮ መኖር መሠረት" በሚል መርኅ በተካሄደው በዚህ ጉባዔ ላይ ንግግር እንዲያደርጉ ከተመረጡ አሥራ አምስት ሀገራት አንዷ ሀገራችን ኢትዮጵያ ነች።

ክቡር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ ኢትዮጵያ ከንጉሥ አስሐመተል ነጃሺ የተወረሰ ልዩነትን የማስተናገድ የረጅም ዘመን ታሪክ ያላት መኾኗን ጠቅሰው፣ ዓለም ይህን ልምድ ከኢትዮጵያ ሊወስድ ይገባዋል ብለዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት ከጉባዔው ጎን ለጎን ከሩሲያ መጅሊስ ፕሬዚደንት ጋር ተገናኝተው የተወያዩ ሲኾን፣ የሁለቱ አገራት መጅሊሶች በጋራ ጉዳዮች ላይ አብረው ለመሥራት አሥር ነጥቦችን የያዘ የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል።

በተጨማሪም፣ ክቡር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ በጉባዔው ላይ ተሳታፊ ከነበሩ የሕንድ፣ የናይጄሪያ፣ የቱኒዝያ እና የኳታር መፍቲዎች ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።

በሞስኮ ከተማ በተካሄደው 20ኛው የሙስሊም ዓለምአቀፍ መድረክ ላይ ከአርባ ሀገራት የተውጣጡ ሙስሊም ሊቃውንት (ዓሊሞች) ተሳታፊ ሆነዋል።

ከተመሠረተ 30ኛ ዓመቱን በማክበር ላይ የሚገኘው የሙስሊም ዓለምአቀፍ መድረክ ላለፉት 20 ዓመታት በየዓመቱ ጉባዔ ሲያካሂድ የቆየ መኾኑ ታውቋል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በተሳተፈችበት በዚህ ጉባዔ ላይ ከዚህ በኋላ በየዓመቱ ቋሚ ተሳታፊ እንደምትሆን በስፍራው የሚገኘው የጠቅላይ ምክር ቤቱ ቃል አቀባይ ያደረሰን መረጃ ያመላክታል።
••••••••••••••••••
የኢ.እ.ጉ.ጠ. ም/ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | twitter.com/eiasc1
ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!

"እኛ የአላህ ነን ወደ አላህም ተመላሾች ነን"
إنا لله وإنا إليه راجعون



የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፤የቀድሞ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ  ምክር ቤት  የዓሊሞች  ምክር ቤት አባል የነበሩት ሸይኽ አደም ሙሀመድ  ሕልፈተ ሕይወት የተሰማውን ሀዘን ይገልፃል።

ሸይኽ አደም ሙሀመድ  (ሸይኽ አደም ከራሃማ) በሀራ ከተማ በታላቁ መስጂድ ለብዙ አመታት  በዒማምነት አገልግለዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች  ጠቅላይ  ምክር ቤት  በሚያዚያ  2011  ዓ.ል  ባደረገው  ጉባዔ ላይ  ከተወከሉ 26 የዓሊሞች ምክር ቤት አባላት መካከል አንዱ ነበሩ ።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ ለሼይኽ   አደም  ጀነተል ፍርዶስን  እንዲወፍቃቸው ፤   ለቤተሰቦቻቸውና ለሙስሊም  ማሕበረሰብ  መፅናናትን ፈጣሪያችን አሏህ  እንዲሰጠን ልባዊ ምኞቱን ይገልፃል።


ሸይኽ አደም ሙሀመድ  (ሸይኽ አደም ከራሃማ የቀብር ስነ _ስርዓት ዛሬ በታላቁ የዳና መስራች  የአህመዱ ዳንይ ዶሪህ በሚገኝበት መንደር ይከናወናል።

የኢትዮጵያ  እስልምና ጉዳዮች  ጠቅላይ ምክር  ቤት

መስከረም 14/2017  ዓ.ል
ረቢዑል ዓ.ል 21/1446  ዓ.ሒ
ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!

"እኛ የአላህ ነን ወደ አላህም ተመላሾች ነን"
إنا لله وإنا إليه راجعون



በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዓሊሞች ጉባዔ ፅህፈት ቤት


የቀድሞ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ  ምክር ቤት  የዓሊሞች  ምክር ቤት አባል የነበሩት ሸይኽ አደም ሙሀመድ  ሕልፈተ ሕይወት የተሰማውን ሀዘን ይገልፃል።

ሸይኽ አደም ሙሀመድ  (ሸይኽ አደም ከራሃማ) በሀራ ከተማ በታላቁ መስጂድ ለብዙ አመታት  በዒማምነት አገልግለዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች  ጠቅላይ  ምክር ቤት  በሚያዚያ  2011  ዓ.ል  ባደረገው  ጉባዔ ላይ  ከተወከሉ 26 የዓሊሞች ምክር ቤት አባላት መካከል አንዱ ነበሩ ።

የጉባዔ ፅህፈት  ቤቱ ለሼይኽ   አደም  ጀነተል ፍርዶስን  እንዲወፍቃቸው ፤   ለቤተሰቦቻቸውና ለሙስሊም  ማሕበረሰብ  መፅናናትን ፈጣሪያችን አሏህ  እንዲሰጣቸው ልባዊ ምኞቱን ይገልፃል።


በኢትዮጵያ  እስልምና ጉዳዮች  ጠቅላይ ምክር  ቤት የዓሊሞች ጉባዔ ፅ/ ቤት

መስከረም 14/2017  ዓ.ል
ረቢዑል ዓ.ል 21/1446  ዓ.ሒ
መስከረም 16፣ 2017 ዓ.ል | ረቢዑል ዓ. 23፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጠቅላይ ምክር ቤቱ ለትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የተሽከርካሪ ድጋፍ አደረገ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከክልልና የከተማ አስተዳደር እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤቶች ጋር በመተባበር ለትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የተሽከርካሪ ድጋፍ አደረገ።

ዛሬ በጠቅላይ ምክር ቤቱ ቅጥረ ግቢ በተካሄደው የርክክብ ስነ ሥርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ጸሐፊ ሸይኽ ሐሚድ ሙሳ የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት እንደ ሀገር ተከስቶ በነበረው ጦርነት ለከፍተኛ ችግር ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ጋር መዋቅራዊ ግንኝነቱ ተቋርጦ እንደነበር አስታውሰዋል።

በተፈጠረው የሰላም አጋጣሚ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ለአቃፊነትና ለሰላም ባደረገው ጥረት ከትግራይ መጅሊስ ጋር ተቋርጦ የነበረው ትስስር እየተጠናከረ መምጣቱን ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስተባባሪነት በጉዳት ላይ የነበረውን የትግራይ መጅሊስ ለማገዝ በተደረገው ንቅናቄና የክልል መጅሊሶች ባደረጉት ትብብር የሕዝብ ለሕዝብ ትስስሩን ለማጠናከር ለትግራይ መጅሊስ ተሽከርካሪ መገዛቱን ተናግረዋል።

በርክክብ ስነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን ሱሩር መረዳዳት የሃይማኖቱ ትልቁ ባህርይ መኾኑን አውስተው፣ የትግራይ መጅሊስ በጦርነቱ ብዙ ማኅበራዊና መንፈሳዊ ጉዳቶችን እንዳስተናገደ አስታውሰዋል።

ለትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለተበረከተው ተሽከርካሪ ፌደራል መጅሊስን ጨምሮ 14 የክልል መጅሊሶች የመዋጮ ትብብር ማድረጋቸው ተነግሯል።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ አቅሙ በፈቀደ መጠን ተሽከርካሪ ለሌላቸው የክልል መጅሊሶች ተመሳሳይ ድጋፍ ለማድረግ ጥረት እንደሚያደርግ የተናገሩት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንቱ የተሽከርካሪውን ቁልፍ ለትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚደንት ሸይኽ አብዱልቃድር አደም አስረክበዋል።

የትግራይ መጅሊስ ፕሬዚደንት ሸይኽ አደም አብዱልቃድር
በጠቅላይ ምክር ቤቱ አስተባባሪነት የክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤቶች በጦርነት ያሳለፍነውን ችግር ከግምት በማስገባት ለትግራይ መጅሊስ ላበረከቱት ሥጦታ በራሳቸውና በክልሉ መጅሊስ ስም አመስግነዋል።

በመጨረሻም ሸይኽ አደም አብዱልቃድር ሀገራችን የሰላም፣ የመተሳሰብ የፍቅር ሆና ለሁላችንም አላህ የደስታ ብርሃን ያግናጽፈን በማለት ዱዓ አድርገዋል።

በርክክብ ስነ ሥርዓቱ ላይ የኦሮሚያ መጅሊስ ፕሬዚደንት፣ የአዲስ አበባ መጅሊስ ተወካይ፣ የዑለማ ጉባዔ ተወካይ፣ እንዲሁም የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሥራ አስፈጻሚዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ቀደም ሲል የክልል መጅሊስ አመራሮች በተገኙበት መድረክ ለትግራይ መጅሊስ የሰባት ሚሊዮን ብር ድጋፍ መደረጉ ይታወሳል።

••••••••••
የኢ.እ.ጉ.ጠ. ም/ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | twitter.com/eiasc1
መስከረም 16፣ 2017 ዓ.ል | ረቢዑል ዓ. 23፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
በ1445 ዓ.ሒ. የሐጅ ጉዞ በግል ቲኬት ቆርጣችሁ ለተጓዛችሁ ሐጃጆች፣ እንዲሁም ክፍያ ፈጽማችሁ ጉዞውን ማድረግ ላልቻላችሁ በሙሉ!
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በ1445 ዓ.ሒ. (2016 ዓ.ል.) የሐጅ ጉዞ በጠቅላይ ምክር ቤቱ የባንክ ሒሳብ ቁጥር ሙሉ ክፍያ አስገብታችሁ፣ ነገር ግን በግላችሁ የአውሮፕላን የደርሶ መልስ ቲኬት ቆርጣችሁ በመጓዛችሁ ምክንያት የቲኬት ክፍያ ተመላሽ ገንዘብ ለጠየቃችሁ፣ እንዲሁም በ1445 ዓ.ሒ የሐጅ ጉዞ ለማድረግ ተመዝግባችሁ፣ ገር ግን በተለያየ ምክንያት መጓዝ ላልቻላችሁ፤ ጠቅላይ ምክር ቤቱ አስፈላጊውን ማጣሪያ ካደረገ በኋላ ተመላሽ ገንዘብ በሐጃጅ ስም በተከፈተው የባንክ ሒሳብ ቁጥር ገቢ ማድረጉ ይታወቃል።

ሆኖም አንዳንድ ሐጃጆችና ምዝገባውን አከናውነው ነገር ግን ጉዞ ማድረግ ያልቻሉ ተመዝጋቢዎች፣ ተመላሹ ብር በባንክ ሒሳብ ቁጥራቸው እንዳልገባላቸው ለተቋማችን ተናግረዋል።

ስለሆነም፣ በባንክ ሒሳብ ቁጥራችሁ ገቢ ያልተደረገላችሁ የአውሮፕላን ቲኬት ክፍያ ተመላሽና ለሐጅ ጉዞ ተመዝግባችሁ ነገር ግን በተለያየ ምክንያት ጉዞውን ማድረግ ያልቻላችሁ ተመላሽ ገንዘብ ጠያቂዎች፣ ለጠቅላይ ምክር ቤቱ ገቢ ያደረጋችሁበትን ሰነድ ቅጂ በቴሌግራም ቁጥር +251-920400400 እንድታያይዙልን በአክብሮት  እናሳስባለን።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት።
•••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
መስከረም 18፣ 2017 ዓ.ል | ረቢዑል ዓ. 25፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የጠቅላይ ምክር ቤቱ የልማት ኤጀንሲ የአመራር ለውጥ አደረገ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የልማት ክንፍ የኾነው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የልማት ኤጀንሲ (ኢሙልኤ) አዲስ ለተሾሙት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጁደዲን ሰይድ የኃላፊነት ርክክብ አካሄደ።

በልማት ኤጀንሲው ቅጥረ ግቢ ዛሬ በተካሄደው መርኃ ግብር ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሐጂ ከማል ሐሩን ጠቅላይ ምክር ቤቱ በለውጥ ሂደት ላይ መኾኑን ጠቅሰው፣ ከለውጦቹ አንዱ የልማት ኤጀንሲውን በቀጣይ ለሕዝብ ተደራሽ ማድረግ መኾኑን ተናግረዋል።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ ላለፉት ዘጠኝ ወራት የተቋሙን የወደፊት አቅጣጫ ለመቅረጽ በባለሙያ ጥናት ሲያስደርግ መቆየቱን ሐጂ ከማል ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የልማት ኤጀንሲ ቀደም ሲል በነበረበት የአቅም ውሱንነት ሳቢያ ሰፊውን ሙስሊም ማኅበረሰብ ተጠቃሚ ማድረግ አለመቻሉን ተናግረዋል።

የኢሙልኤ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አሕመድ ሑሴን ኤጀንሲው የሚሰጠውን አገልግሎት ለሕዝብ ተደራሽ ለማድረግና አቅሙን ለማሳደግ የተለያዩ ጥናቶች ሲያስጠና መቆየቱን ጠቅሰው፣ ጥናቱን ወደተግባር ለመለወጥ የተቋሙን ሥራ ወደ ከፍታ ሊያደርሱ የሚችሉ የሙያ ዘርፎች ላይ ቦርዱ ቅጥር መፈፀሙን ተናግረዋል።

ኢሙልኤ ከተቋቋመበት ዓላማ አኳያ ሰፊ ሥራ መሥራት ይጠበቅበታል ያሉት የቦርድ ሰብሳቢው በቀጣይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተባብሮ በመሥራት አዲሱ አመራር ለውጥ ማምጣት ይጠበቅበታል ብለዋል።

አዲሱ የኢሙልኤ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጁደዲን ሰዒድ ኤጀንሲው የሚሰጠውን ሰብኣዊ አገልግሎት በማሳደግ እንደ አገር የተጣለበትን ኃላፊነት ለመወጣት አዲሱ አመራር ከመቼውም በላይ ዝግጁ መኾኑን ተናግረዋል።

ኤጀንሲው የተለያዩ የሰብኣዊ አገልግሎቶች ላይ የሚሠራውን ሥራ እንደሚያሰፋ የተናገሩት ዳይሬክተሩ፣ ዘር፣ ቀለም እና ሃይማኖት ሳይለይ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የሰብዓዊ አገልግሎት እንደሚሰጥ ተናግረዋል።

በቀጣይም ሰዎች ከተረጂነት ወጥተው ወደ ረጂነት እንዲቀየሩ የተለያዩ የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎች እና የገቢ ማስገኛ ሥራዎች ላይ እንደሚሰማራና፣ "ከከጃይ እጅ የላይ እጅ ይበልጣል" የሚለውን የነቢያችን ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) ሐዲስ አስታውሰዋል።

አገራችን ኢትዮጵያ የመልማት ተፈጥሯዊ ፀጋ የታደለች አገር መሆኗን የተናገሩት ዳይሬክተሩ፣ በቀጣይ ከሚመለከተው ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የድህነት ቅነሳ ፕሮጀክቶች ላይ ትኩረት አድርገው እንደሚሠሩ ተናግረዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሥራ አስፈፃሚ አባልና የትምህርትና ማኅበራዊ ዘርፍ ተጠሪ ኢንጅነር አንዋር ሙስጠፋ በአንዳንድ የአገራችን ክፍሎች በደረሱት የተፈጥሮና ሰው ሠራሽ ችግሮች ሳቢያ የእርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ በመምጣቱ የዕለት ደራሽ ሥራዎች ላይ ኤጀንሲው ጥናት በማድረግ መሥራት ይጠበቅበታል ብለዋል።
መስከረም 20፣ 2017 ዓ.ል | ረቢዑል ዓ. 27፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ለእስላማዊ የትምህርት ተቋማት አመራሮች የአቅም ግንባታ  ሥልጠና መስጠት ተጀመረ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዑለማ ጉባዔ ጽሕፈት ቤት በአገራችን በሥራ ላይ ለሚገኙና አዲስ ለሚመሠረቱ ከፍተኛ እስላማዊ የትምህርት ተቋማት አመራሮች የሁለት ቀናት የአቅም ግንባታ ሥልጠና መስጠት  ጀመረ።

"የአካዳሚያዊ አመራር ክህሎት ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በጠቅላይ ምክር ቤቱ  የስብሰባ አዳራሽ የተጀመረው ይህ ሥልጠና በጠቅላይ ምክር ቤቱ የዓሊሞች ጉባዔ ዋና ፀሐፊ በሼይክ ሙሐመድ ሐሚዲን (ዶ/ር) ንግግር ተከፍቷል።

ሼይኽ ሙሐመድ ሐሚዲን በንግግራቸው እስልምና ትልቅ ቦታ ከሚሰጣቸው ጉዳዮች አንዱ ትምህርት መኾኑን ጠቅሰው፣ የትምህርት ተቋማትን ለሚመሩ ኃላፊዎች የሚሰጡ እኒህን መሰል ተከታታይ ሥልጠናዎች ሥራቸው ውጤታማ እንዲሆን ይረዳቸዋል ብለዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት ክቡር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ ለሁለት ቀናት በሸይኽ ሲዲቅ በረካት (ዶ/ር) የሚሰጠው የአቅም ግንባታ ሥልጠና የተሳካ እንዲሆን ላደረጉት ጥረት ምስጋና ቀርቦላቸዋል።

ዛሬ በተጀመረው የአቅም ግንባታ ሥልጠና መክፈቻ ላይ በጠቅላይ ምክር ቤቱ የዓሊሞች ጉባዔ ምክትል ሰብሳቢና የፈትዋ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶክተር  ጄይላን ኸድር እና ሌሎችም ጠቅላይ ምክር ቤቱ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።


የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት።
•••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
መስከረም 21፣ 2017 ዓ.ል | ረቢዑል ዓ. 28፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የትምህርት ተቋማት አመራሮች የአቅም ግንባታ ሥልጠና ተጠናቀቀ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት "የአካዳሚያዊ አመራር ክህሎት ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት" በሚል መሪ ሐሳብ ለእስላማዊ የትምህርት ተቋማት መሪዎች ያዘጋጀው የአቅም ግንባታ ሥልጠና ዛሬ ተጠናቀቀ።

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዑለማ ጉባዔ ምክትል ዋና ጸሐፊና ቋሚ የፈትዋ አባል ዶክተር አብደላ ኸድር ሥልጠናው የእስላማዊ የትምህርት ተቋማትን የአመራር ብቃት ለማሻሻል ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል።

በምክር ቤቱ የሥርዓተ-ትምህርት ክፍል ግምገማ መሠረት ብዙዎቹ የከፍተኛ ደረጃ የእስላማዊ የትምህርት ተቋማት መስፈርቱን ያሟሉ ባለመሆኑ፣ ይህን ሥልጠና ማዘጋጀት አስፈልጓል ብለዋል።

ለእስላማዊ የትምህርት ተቋማት አመራሮች በተዘጋጀው የአቅም ግንባታ ሥልጠና ላይ የ16 የትምህርት ተቋማት አመራሮች ተሳትፈዋል።

ሥልጠናውን የተካፈሉት የከፍተኛ እስላማዊ ትምህርት ተቋማት አመራሮች ከሥልጠናው ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ተሳታፊዎቹ፣ "ሥልጠናው ራሳችንን የመዘንንበት፣ ምን ደረጃ ላይ እንደምንገኝ ያወቅንበትና ክፍተታችንን ያየንበት ለሥራ ያነሳሳን ነው" ሲሉ በመግለጽ፣ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ትውልዳዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ በመሆኑ አመስግነዋል።

የአቅም ግንባታ ሥልጠናውን ላጠናቀቁ የእስላማዊ ትምህርት ተቋማት አመራሮች የምስክር ወረቀት የሰጡት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን ሱሩር፣ ሥልጠናው ለሙስሊሙ ማኅበረሰብ መንፈሳዊ ከፍታ፣ አብሮ ለመሥራት፣ የጋራ ርዕይ ለመሰነቅ ትልቅ መሳሪያ በመሆኑ ተቋማትን ማጠናከር ያስፈልጋል" ብለዋል።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ በየዘርፉ የተቋማትን አቅም በማሳደግ ለሰላምና ለአብሮነት የቻለውን ያህል ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።

በሥልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ የዓሊሞች ጉባዔ ምክትል ሰብሳቢና የፈትዋ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶክተር ጄይላን ኸድር፣ በጠቅላይ ምክር ቤቱ የዓሊሞች ጉባዔ ዋና ፀሐፊ ሼይክ ሙሐመድ ሐሚዲን (ዶ/ር)፣ በአፍሪካ እና በዓለምአቀፍ እስላማዊ ዩንቨርሲቲ ከ30 ዓመት በላይ የማስተማር ልምድ ያላቸው ሸይኽ ሲዲቅ በረካት (ዶ/ር) ተገኝተዋል።


•••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
መስከረም 29፣ 2017 ዓ.ል | ረቢዑል ሳኒ ዓ. 6፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጣ የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን በሞሮኮ የልምድ ልውውጥ እያደረገ ነው
.............................................

ከተለያዩ ተ
ቋማት የተውጣጣ የኢትዮጵያ መንግሥት የልዑካን ቡድን በሞሮኮ የልምድ ልውውጥ እያደረገ ይገኛል።

ቡድኑ የመንግሥት የሰላምና ፀጥታ የሥራ ኃላፊዎች፣ የፌዴራልና የክልል የጸጥታ ኃላፊዎች እንዲሁም የሃይማኖት አባቶች የተካተቱበት ነው።

ጉብኝቱ በሁለቱ ሀገራት ያለውን ጠንካራ የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ እንደሚያጠናክር የገለጹት የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር)፤ ሞሮኮ የተለያዩ ሃይማኖቶችና ሕዝቦችን ተከባብረው እንዲኖሩ በማድረግ በአፍሪካ ጠንካራ ኢኮኖሚ የገነባችበት መንገድ ለሀገራችን ጥሩ ልምድ ይሆናል።

የልዑካን ቡድኑ የሞሮኮ ዋና ከተማ ራባት እና ዋና የንግድ ከተማ ካዛብላንካን ጨምሮ በአራት ትላልቅ ከተሞች የሚገኙ ታሪካዊ፣ ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ ተቋማትን እንደሚጎበኝ እና ከከተሞቹ የሥራ ኃላፊዎች ጋር እንደሚወያይ ተገልጿል።

ጉብኝቱን ያስተባበረው የሰላም ሚኒስቴር መሆኑ ገልፆ ኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዘግቦታል።



•••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1