ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከሐምሌ 27 ቀን 2016 ዓ.ል. ጀምሮ ሲያካሂድ የቆየውን የ2016 ዓ.ል. ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ በዛሬው ዕለት አጠናቅቋል፡፡
ጠቅላይ ምክር ቤቱ ለ13 ተከታታይ ቀናት ሲያካሂድ በቆየው በዚህ ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ፣ በበጀት ዓመቱ በምክር ቤቱ የተለያዩ ዳይሬክቶሬቶች እና የሥራ ክፍሎች የተከናወኑ ተግባራት በጥልቀት ተገምግመዋል፡፡
ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከሙስሊሙ ማኅበረሰብ የተሰጠውን ኃላፊነት የመወጣት አቅሙን ከጊዜ ወደ ጊዜ በማሳደግ፣ ተስፋ ሰጪ ውጤት ላይ መድረሱን የሥራ አስፈጻሚ አካሉ በግምገማው ለማረጋገጥ ችሏል፡፡
በዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ግምገማው (ተቅዪም) ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ልዩ ልዩ የሥራ ዘርፎች የ2016 የበጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቶች ቀርበው መጠነ ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ የእያንዳንዱን የሥራ ዘርፍ ጠንካራ እና ደካማ ጎን በመለየት በአዲሱ የበጀት ዓመት ጠንካራ ጎኖችን ይበልጥ በማሳደግ፣ የታዩ ውስንነቶችን ለመቅረፍ የሚያስችል አቅጣጫ ተመላክቷል፡፡
የሥራ አስፈጻሚ አካሉ በጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት ጽሕፈት ቤት በተከናወኑ የሀገር ዉስጥና የዉጪ ሀገራት የሥራ እንቅስቃሴዎች የተገኙ ውጤቶችን ጨምሮ፣ የሁሉንም ዳይሬክቶሬቶች እና ጽሕፈት ቤቶች የሥራ አፈጻጸም በጥልቀት ፈትሿል፡፡
በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው የሁለተኛ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ፣ የ1445 ዓ.ሒ. የሐጅ መስተንግዶን የተመለከተ ዝርዝር ሪፖርት ቀርቦ ጥልቅ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
በጠቅላይ ምክር ቤቱ ታሪክ 12 ሺህ ሐጃጆች የተስተናገዱበት የ1445 ዓ.ሒ. የሐጅ አፈጻጸም ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ የሀገር ውስጥ የምዝገባ ሥርዓቱ መዘመን እና በሳዑዲ አረቢያ የነበረው መስተንግዶ ከፍተኛ መሻሻል የታየበት መሆኑ በግምገማው እንደ ጠንካራ ጎን ተጠቅሷል፡፡
በሚና የሐጃጆች ማረፊያ ድንኳኖች ላይ የተስተዋለው ችግር በቀጣይ እንዲሻሻል የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው የአፈጻጸም አቅጣጫ አመላክቷል፡፡
በጠቅላይ ምክር ቤቱ የግማሽ ምዕተ ዓመት ታሪክ አገሪቱን እና ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን በሚያኮራ መልኩ በተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ በመሳተፍና ጥናታዊ ጽሑፎችን በማቅረብ ተቋሙ የራሱን አሻራ ያሳረፈበት፣ በዚህም ከምንጊዜውም የተሻለ የውጪ ግንኙነት ውጤት የተመዘገበበት ዓመት መኾኑን የሥራ አስፈጻሚ አካሉ አረጋግጧል፡፡
በተለይም የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ በBRICS ሐገራት ጉባዔ ላይ ጥናታዊ ጽሑፍ በማቅረብ ጭምር ያደረጉት ተሳትፎ የሀገራችን መልካም ገጽታ እና የሕዝበ ሙስሊሙ ተቋም ስም ከፍ ያለበት መኾኑን በመጥቀስ፣ መሰል ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ውሳኔ ተላልፏል፡፡
ሙስሊሙን ማኅበረሰብ ተጠቃሚ ከሚያደርጉ ፕሮጀክቶች መካከል በጠቅላይ ምክር ቤቱ በእቅድ የተያዘው የነጃሺ መስጂድ ግንባታ በአፋጣኝ ወደ ትግበራ ምዕራፍ እንዲገባ ውሳኔ ተላልፏል፡፡
የዑለሞች የአንድነትና የትብብር ሰነድን መሠረት በማድረግ የሙስሊሙን አንድነት በሚያረጋግጥ መልኩ በብሔራዊ ኮሚቴው የተከናወኑት ሥራዎች የሚያስመሠግኑ መኾናቸውን ያወሳው ይኸው የግምገማ መድረክ፣ መሰል የሙስሊሙን አንድነት የሚያጠናክሩ ሥራዎች የሚሠሩበት አቅጣጫ ተመላክቷል፡፡
ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከሌሎች ቤተ እምነቶች ጋር የጋራ የኾኑ የሰላምና የልማት ሥራዎችን ለመሥራት የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔን በመመሥረት እየተንቀሳቀሰ መሆኑ የተጠቀሰ ሲኾን፣ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በጉባዔው ውስጥ የሙስሊሙ ውክልናና ተሳትፎ ፍትኀዊነትን ጉዳይ የሚያጠና ኮሚቴ አዋቅሯል፡፡
ጠቅላይ ምክር ቤቱ የጀመራቸውን ሁሉን አቀፍ የሃይማኖትና የልማት ሥራዎች በቀጣይም በተቀናጀ መልኩ አጠናክሮ ተግባራዊ እንዲያደርግ፣ ውሱንነት በታየባቸው ዘርፎች ላይ ስር ነቀል የማስተካከያ ሥራዎች ከወዲሁ እንዲሠሩ አቅጣጫ በማስቀመጥ ግምገማውን በዛሬው ዕለት አጠናቅቋል፡፡
ነሐሤ 10 ቀን 2016 ዓ.ል. | ሰፈር 12፣ 1446 ዓ.ሒ.
አዲስ አበባ፡፡

ነሐሴ 11፣ 2016 ዓ.ል | ሰፈር 13፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيم
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጠቅላይ ምክር ቤቱ ለክልል የእስልምና ጉዳይ ከፍተኛ ም/ቤት አመራሮች የ1445 ዓ.ል. የሐጅ መስተንዶ ሪፖርት አቀረበ።

አዲስ አበባ |
የኢትዮጵያ አስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ለክልል የእስልምና ጉዳይ ከፍተኛ ምክር ቤት አመራሮች የ1445 ዓ.ሒ. የሐጅ መስተንግዶ ሥራ ክንውን ሪፖርት አቀረበ።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት ክቡር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ በመሩት በዚሁ መድረክ ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ምክትል ፕሬዚደንትና የሐጅና ዑምራ ዐብይ ኮሚቴ ሰብሳቢና የዘርፍ ተጠሪ ሸይኽ አብዱልዓዚዝ ሸይኽ አብዱልዋሊ በሪፖርታቸው በ1445 ዓ.ሒ. ሐጅ በአገር ውስጥ እና በውጪ ሀገር የተሠሩ ሥራዎችን በዝርዝር አቅርበዋል።
ኃላፊው በ1445ዓ.ሒ. የሐጅ መስተንግዶ ከቅድመ ዝግጅቱ እስከ አፈጻጸሙ መጠነኛ ችግሮች የታዩ ቢኾንም፣ ከቀደሙት ዓመታት አንጻር ከፍተኛ መሻሻል የታዩበት መኾኑን ተናግረዋል።
የሐጅና ዑምራ ዐብይ ኮሚቴ ሰብሳቢው ያቀረቡትን ሪፖርት ተከትሎ የክልል እስልምና ጉዳይ ከፍተኛ አመራሮች የተለያዩ ጥያቄዎችን እና በሐጅ ወቅት ያስተዋሏቸውን ክፍተቶችም አንስተዋል።
እንደ ክፍተት ከቀረቡ ነጥቦች መካከል፣ ሚና እና አረፋ ላይ የሕክምና አገልግሎት "የለም" በሚባል ደረጃ መኾኑ እና በሌላም በኩል ሑጃጁን ለማስተናበር የሚሄዱ አባላት ቁጥር እና ኮታ ለክልሎች ትኩረት የሰጠ አልነበረም የሚሉ ይገኙበታል።
በተጨማሪም፣ "ለሐጅ ሥርዓት መመሪያ አላችሁ ወይ?" እና "የተጋባዥ ሑጃጆች መረጣ መርኅን የተከተለ ነው ወይ?" የሚሉ ጥያቄዎችም ተነስተዋል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ምክትል ፕሬዚደንትና የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ኃላፊው ሸይኽ አብዱልዓዚዝ ለተነሱት ጥያቄዎች፣ በተለይም ትልቅ ብዥታ ታይቶባቸዋል ባሏቸው ጉዳዮች ላይ፣ ምላሽና ማብራሪያዎች ሰጥተዋል።
ኃላፊው ከሳዑዲ አረቢያ የሐጅ ሚኒስቴር በነፃ የሚሰጥ ኮታ እንደሌለ ጠቅሰው፣ በ100 ሑጃጅ ለአንድ አገልግሎት ሰጪ እንደሚፈቀድ ተናግረዋል።
በ1445 ዓ.ሒ. የሐጅ ሥርዓት ለመፈፀም በጠቅላይ ምክር ቤቱ በኩል 12 ሺህ ሐጃጆች የተስተናገዱ ሲሆን፣ ይህን ተከትሎ 120 የሑጃጅ አገልግሎት ሰጪዎች ወደዚያው መሄዳቸውን ተናግረዋል።
ሚና ላይ የመኝታ ስፍራ ጥበትና የርቀት ችግሮች እንደነበሩ የጠቀሱት ኃላፊው፣ በወቅቱ ለሳዑዲ የሐጅ ሚኒስቴር ቀድመን ገንዘብ ለመክፈል ዶላር እስከምናገኝ እና የጠቅላላ ሑጃጁ ቁጥር ኮታ ባለመታወቁ፣ ቦታ ከሚያዝበት ዘግይተን በመክፈላችን ችግሩ የተፈጠረ መሆኑን አስረድተዋል።
መድረኩን የመሩት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት ክቡር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ባለፈው የሐጅ መስተንግዶ በዶላር የምንዛሪ ተመን ከፍና ዝቅ ማለት፣ እንዲሁም እጥረት ሳቢያ ከሐጅ የቀረ ሰው ባይኖርም፣ የመስተንግዶ ሥራው ግን አድካሚና ከእንከን የሚጠራ አለመኾኑን ተናግረዋል።
•••••••••••
የኢ.እ.ጉ.ጠ. ም/ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር |https://x.com/eiasc1

Telegram
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
ነሐሴ 11፣ 2016 ዓ.ል | ሰፈር 13፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيم
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የሐጅ መስተንግዶ ሥራን 'ለግል ኤጀንሲዎች' ለማስተላለፍ የቀረበ ሐሳብ በከፍተኛ ድምጽ ውድቅ ተደረገ።

የኢትዮጵያ አስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅና ዑምራ ዐብይ ኮሚቴ የ1445 ዓ.ሒ. የሐጅ መስተንግዶ ሥራ ክንውን ሪፖርት ባቀረበበት መድረክ፣ የሐጅ መስተንግዶ ሥራን 'ለግል ኤጀንሲዎች' ለማስተላለፍ የቀረበ ምክረ-ሐሳብ በከፍተኛ ድምጽ ውድቅ ተደረገ።
የሐጅ መስተንግዶ ሥራን 'ለግል ኤጀንሲዎች' በማስተላለፍ ላይ ያተኮረውን ምክረ-ሐሳብ ያቀረቡት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት ክቡር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ፣ ምክረ ሐሳቡ ያሉትን አዎንታዊ እና አሉታዊ ገጽታዎች አብራርተዋል።
ክቡር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የሐጅ መስተንግዶ ሥራ 'ለግል ኤጀንሲዎች" ቢተላለፍ የሚለውን ምክረ ሐሳብ አስመልክቶ ለክልል የእስልምና ጉዳይ ከፍተኛ አመራሮች ማብራሪያ ሰጥተዋል።
"የሐጅ መስተንግዶ ገቢ ከማስገኘት አኳያ ለተቋሙ የጀርባ አጥንት ቢሆንም፣ የጀርባ ውጋትም ነው" ያሉት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም፣ በኃላፊነት ላይ ያለው መጅሊስ በተቻለው መጠን የሐጅ መስተንግዶን እያዘመነ መምጣቱን ጠቅሰዋል።
ምንም እንኳን በ1445 ዓ.ሒ. የሐጅ መስተንግዶ በዶላር የምንዛሪ ተመን ከፍና ዝቅ ማለት እንዲሁም እጥረት ሳቢያ ከሐጅ የቀረ ሰው ባይኖርም፣ የመስተንግዶ ሥራው ግን አድካሚና ከእንከን የሚጠራ አለመኾኑን ተናግረዋል።
"የሐጅ ሥራ ለግል ኤጀንሲዎች ቢስሰጥ የገንዘብ አቅም ስላላቸው ዶላር ፍለጋው ጭንቀት ውስጥ የሚከታቸው አይሆንም፤" ያሉት ፕሬዚደንቱ፣ ኤጀንሲዎቹ በሐጃጆች ተመራጭ ለመኾን በሚያደርጉት ውድድር ሑጃጁ የተሻለ መስተንግዶ ተጠቃሚ የሚኾንበት ሁኔታ እንደሚፈጠርም ተናግረዋል።
ፕሬዚደንቱ የመስተንግዶ ሥራውን የግል ኤጀንሲዎች ይሥሩት እንጂ፣ ጉዳዩ የሃይማኖት እንደመኾኑ ጠቅላይ ምክር ቤቱ አስፈላጊ ደንብና መመሪያዎችን በማውጣት ሥራቸውን በበላይነት የመቆጣጠር ኃላፊነት እንደሚኖረው ተናግረዋል።
የክልል የእስልምና ጉዳይ ከፍተኛ ምክር ቤት አመራሮች የሐጅ መስተንግዶ ሥራ ለግል ኤጀንሲዎች ቢፈቀድ በሚል በፕሬዚደንቱ የቀረበውን ምክረ ሐሳብ በከፍተኛ ድምጽ ተቃውመውታል።
የክልል የእስልምና ጉዳይ ከፍተኛ ምክር ቤት አመራሮቹ የሐጅ መስተንግዶ ሥራ እንደነበረው በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስተባባሪነት ማዕከላዊነቱን ጠብቆ ሊካሄድ ይገባዋል ብለዋል።
በዚህ የክልል እስልምና ጉዳይ ከፍተኛ አመራሮች ውይይት ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከሐምሌ 27 ቀን 2016 ዓ.ል. ጀምሮ ሲያካሂድ በቆየው የ2016 ዓ.ል. ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ሪፖርት በጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ጸሐፊ ሸይኽ ሀሚድ ሙሳ ቀርቧል።
****
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት

ትዊተር | https://x.com/eiasc

የክልል መጅሊስ አመራሮች በተገኙበት መድረክ ለትግራይ መጅሊስ የ7 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገ።

የኢትዮጵያ አስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅና ዑምራ ዐብይ ኮሚቴ የ1445 ዓ.ሒ. የሐጅ መስተንግዶ ሥራ ክንውን ሪፖርት ባቀረበበት መድረክ፣ ለትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የ7 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገ።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የትግራይ ክልል መጅሊስ ከአምስት ዓመታት በኋላ የፌደራል መጅሊሱ አካል ሆኖ የውይይቱ ተሳታፊ በመኾኑ ደስታቸውን ገልጸዋል።
የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚደንት ሸይኽ አደም አብዱልቃድር የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ተነጥሎ የቆየው አሁን ያለው የመጅሊስ አመራር ከመመረጡ በፊት መሆኑን አስታውሰው፣ የለውጡ መጅሊስ የወንድሞቹን ችግር ተረድቶ "ሕብረታችን አንዲጠነክር" ላደረገው ጥረት አመሥግነዋል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ
"የትግራይ ክልል ከጦርነት እያገገመ የሚገኝና ብዙ ችግሮች ያሉበት መኾኑን በክልሉ ተገኝተን ያየነው በመሆኑ፣ የክልል እስልምና ጉዳይ ከፍተኛ አመራሮች የክልሉን ከፍተኛ ምክር ቤት ልናግዘው ይገባል" የሚል ሐሳብ አቅርበዋል።
ይህን ሐሳብ የክልል እስልምና ጉዳይ ከፍተኛ አመራሮቹ ተቀብለውት በዚያው ጊዜ በተደረገው የእገዛ እንቅስቃሴ፣ ከተለያዩ ክልሎች የትግራይ መጅሊስን ለመደገፍ የሚውል በድምሩ 7 ሚሊዮን ብር የሚደርስ መዋጮ ቃል ተገብቷል።
የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚደንት ሸይኽ አደም አብዱልቃድር፣ "የጠቅላይ ምክር ቤታችን ፕሬዚደንት እና የክልሎች የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት መሪዎች የኾናችሁ ወንድሞቻችን የትግራይ መጅሊስ ችግርን ለመቅረፍ ያደረጋችሁት መረባረብ ልባችንን የነካ ነው" ሲሉ በጥልቅ ስሜት ካመሠገኑ በኋላ፣ "ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን፤ የተሻለ ነገን እናያለን" ብለዋል።

ነሐሴ 12፣ 2016 ዓ.ል | ሰፈር 14፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ለ1445 ዓ.ሒ. የሐጅ ጉዞ የዋስትና ብር ላስያዛችሁ ሐጃጆች!

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በ1445 ዓ.ሒ. (2016 ዓ.ል.) እድሜያቸው ከ35 ዓመት በታች ለሆኑ የሐጅ ተጓዦች ብር 160,000.00 (አንድ መቶ ስድሳ ሺህ) የሐጅ ጉዞ የዋስትና ብር መያዙ ይታወሳል።
ምክር ቤቱ አስፈላጊውን ማጣሪያ አድርጎ የጉዞ የዋስትና ብር ባስያዘው ሐጃጅ ስም በተከፈተው የባንክ ሒሳብ ቁጥር ገንዘቡን ገቢ ማድረጉ ይታወቃል።
ሆኖም አንዳንድ ሐጃጆች ያስያዙት የጉዞ ዋስትና ብር በባንክ ሒሳባቸው እንዳልገባላቸው ለተቋማችን ተናግረዋል።
ስለሆነም የጉዞ ዋስትና ብር አስይዛችሁ በባንክ የሒሳብ ቁጥራች ገቢ ያልተደረገላችሁ ሐጃጆች የዋስትና ገንዘብ ለምክር ቤቱ ገቢ ያደረጋችሁበትን ሰነድ ቅጂ በቴሌግራም ቁጥር +251-920 400 400 እንድታያይዙልን በአክብሮት እናሳስባለን።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት።
•••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1

ነሐሴ 14፣ 2016 ዓ.ል | ሰፈር 16፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ፕሬዝዳንቱ ፒያሳ የሚገኘውን አወሊያ አሁናዊ ሁኔታን ጎበኙ።
"ዘመኑን የዋጀ ግንባታ ለመገንባት ጠቅላይ ምክር ቤቱ ዝግጁ ነው"ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
በችግኝ ተከላና ፤በጉብኝቱ መርሐ ግብር ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የክቡር ዶክተር ሼይ ኽ ሐጂ የሐገራች ሙስሊሞች የዕውቀት ብርሐን ከፋች የሆነችውን አወሊያ (ፒያሳ) ሕብረተሰቡን በማስተባበር በቀ ጣይ ዘመኑን የዋጀ ግንባታ ለመገንባት ጠቅላይ ምክር ቤቱ ዝግጁ መሆኑን ተናገሩ።
የአወሊያ ትምህርት ቤት(ፒያሳ) በቀጣይ ለሚገነባው ዘመናዊ ግንባታ ማስጀመሪያ የግንባታ ፈቃድ የከተማ አስተዳደሩ በፍጥነት እንዲሰጣቸው ፕሬዝዳንቱ ጠይቀዋል።
መንግስት የሙስሊሙን ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ እየሰጠ መሆኑን የገለፁት ፕሬዝዳንቱ ፤ በየደረጃው የሚገኘውን የመንግስት አካላት በራሳቸውና በጠቅላይ ምክር ቤቱ ስም አመስግነዋል።
ከተማችን በአሁኑ ሰዓት ሰፊ ልማት እየተካሄደባት በመሆኗ የከተማዋ ልማት ውጤታማነት መስሊሙ ማሕበረሰብ የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል።
የአወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ጀማል መሐመድ (ዶክተር ) የአወሊያ ሙስሊም ሚሲዮን ትምህር ቤት ከተመሰረተ የሰባ ሁለት ዓመታት እድሜ ማስቆጠሩን ተናግረዋል።
በሺዎች የሚቆጠሩ የተማረ ትውልድ ያፈራችው አወሊያን ዘመኑ የሚመጥነውን ግንባታ በመገንባት ታሪክ ለሚቀጥለው ትውልድ ማስተላለፍ የሁሉም ሙስሊም ማሕበረሰብ ኅላፊነት እንደሆነ ዶክተር ጀማል ተናግረዋል።
የአወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ ሐጂ ሰዒድ አስማረ ባለፈው 2015 ዓ.ል ደረጃውን የጠበቀ ግንባታ ለመገንባት ተጨማሪ የማስፋፊያ 3600 ሜትር ካሬ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ባደረገው ሰፊ ጥረት በካርታ ላይ ባለው 1449 ሜትር ካሬ ስፋት ላይ የኤሌክትሮኒክስ ካርታ ፣የዕዳና እገዳ እንዲሁም የግንባታ ፈቃድ ከሚመለከተው መንግስት አካላት እየተጠናናቀ መሆኑን ዋና ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል።
በአንድ ቢሊዮን ብር (በወቅቱ በነበረው ዋጋ) በ1449 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ሊገነባ በታቀደው ባለ 19 የወለል ሕንፃ፤ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት የክብር ዶክተር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ፣የዓለም ሙስሊም ሊግ ዋና ፀሐፊ ዶክተር ሙሐመድ ቢን አብዱልከሪም አለኢሳ እና የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ነሐሤ 9፣ 2015 ዓ.ል የመሠረተ ድንጋይ ማስቀመጣቸው ይታወሳል።
አንጋፋው አወሊያ ትምህርት ቤት በ1950 ዓ.ል በታላቁ አንዋር መስጂድ አቅራቢያ በበጎ አድራጊ ወንድሞች የተመሰረተ ሲሆን ፣ ከ1958 ዓ.ል ጀምሮ ፒያሳ አካባቢ(ሰባራ ባቡር ) አቅራቢያ ላለፉት አምሳ ስምንት ዓመታት የትምህርት አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል።
ዛሬ በአወሊያ (ፒያሳ) በተደረገው ጉብኝት እና የችግኝ ተከላ ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ሼይኽ አብዱል ከሪም ሼይኽ በድረዲን ሱሩር እና የአዲስ አበባ መጅሊስ ስራ አስፈፃሚዎች ፣ ዓሊሞች ፣ ዱዓቶች ፣የአወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት የስራ ሃላፊዎች የስራ አመራር የቦርድ አባላትና የቀድሞ ተማሪዎች ተገኝተዋል።
••••••••••

ነሐሴ16፣ 2016 ዓ.ል | ሰፈር 18፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيم
••••••••••••••••••••••••••••••
ጠቅላይ ምክር ቤቱ ጉባዔ ያካሂዳል።
••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ቅዳሜ ነሐሴ 18፣ 2016 ዓ.ል በስቴይ ኢዚ-ፕላስ ሆቴል የ2ኛ ዓመት 4ኛ መደበኛ ጉባዔውን ያካሂዳል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሐጂ ከማል ሀሩን በጉባዔው የ2015 የውጪ ኦዲት ሪፖርት እንደሚቀርብ ተናግረዋል።
ዋና ሥራ አስኪያጁ እንዳሉት በጉባዔው የ2016 የሥራ ክንውን፣ የፋይናስ፣ እና የሐጅ ሪፖርቶች፣ እንዲሁም የ2017 እቅድ እንደሚቀርቡ ተናግረዋል።
•••••••••••••••

ሰኔ 17፣ 2016 ዓ.ል | ሰፈር 19፣ 1445 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር አሻራቸውን አኖሩ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የክብር ዶክተር ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር አሻራቸውን አኖሩ
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ጫካ ፕሮጀክት አካባቢ አሻራቸውን አኑረዋል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ኸይረዲን ተዘራ(ዶ/ር)፣ የሚኒስቴሩ አመራሮችና ሰራተኞች ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር አባይ፣ የሃይማኖት አባቶችና የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ ሆነዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በአንድ መንፈስ በመላው ኢትዮጵያ ዓሻራችንን እናኑር ፤ አንድ ከሆንን ከዚህም በላይ እንችላለን ሲሉ ጥሪ ማስተላለፋቸው ይታወቃል፡፡
#መረጃው :- የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ነው
•••••••••••••••••••••••••

ነሐሴ18 ፣ 2016 ዓ.ል | ሰፈር 20 ፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيم
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ጉባኤ እየተከናወነ ይገኛል
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት መደበኛ የ2ኛ ዓመት 4ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በእስቴይ ኢዚ- ፕላስ ሆቴል በቁርአን ተከፍቶ ጉባኤው በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ነሐሴ 21፣ 2016 ዓ.ል | ሰፈር 23፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ፕሬዚደንቱ በኢትዮጵያ የአልጄሪያ አምባሳደርን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙት የአልጄሪያ አምባሳደር ክብርት ሰልማ ማሊክን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።
በዚሁ ጊዜ ክቡር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የኢትዮጵያ እና የአልጄሪያ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረ መምጣቱን ጠቅሰው፣ አዲስ ለተሾሙት ክብርት አምባሳደር ሰልማ ማሊክ መልካም የሥራ ጊዜ ይሆንላቸው ዘንድ ምኞታቸውን ገልፀዋል።
አምባሳደር ሰልማ ማሊክ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለተደረገላቸው አቀባበል አመሥግነው፣ የኢትዮጵያና የአልጄሪያ የሁለትዮሽ ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን ተናግረዋል።
ክብርት አምባሳደሯ፣ በአልጄሪያ ዘንድሮ የሚጀመር ነፃ የትምህር ዕድል መኖሩንና የዚህ ዕድል ተጠቃሚ ከሚኾኑ ሀገራት አንዷ ኢትዮጵያ እንደኾነች ጠቅሰው፣ ለዚህ የከፍተኛ ትምህርት ዕድል የምልመላ መስፈርት ሰነዱን ለክቡር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም አስረክበዋል።
ክቡር ሼይኽ ሐጂ በበኩላቸው የአልጄሪያ መንግሥት ለኢትዮጵያ ለሰጠው ነጻ የትምህርት ድል በጠቅላይ ምክር ቤቱ እና በራሳቸውም ስም ምሥጋና አቅርበዋል።
በቀጣይም ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከኤምባሲው ጋር በጋራ ጉዳዮች ላይ በትብብር እንደሚሠራ ክቡር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም መናገራቸውን የፕሬዚደንቱ ጽሕፈት ቤት ቃል አቀባይ ተናግረዋል።
••••••••••
የኢ.እ.ጉ.ጠ. ም/ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | twitter.com/eiasc1

ነሐሴ 25፣ 2016 ዓ.ል | ሰፈር 27፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيم
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጠቅላይ ምክር ቤቱ በቀጣዩ ዓመት ሸሪዓን መሠረት ያደረገ ምርጫ ያከናውናል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በዛሬው ዕለት የምክር ቤቱን አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ አስመልክቶ ለጋዜጠኞች ገለጻ አደረገ።
በዚሁ ገለጻ ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ፣ ጠቅላይ ምክር ቤቱ በቀጣዩ ዓመት ምርጫ እንደሚያካሂድና ምርጫው ሸሪዓን መሠረት ያደረገ እንደሚኾን ተናግረዋል።
"ለሃይማኖት ተቋማት አመራርነት የሚካሄድ ምርጫ ፖለቲካዊ ምርጫ አይደለም" ያሉት ፕሬዚደንቱ፣ "የሃይማኖት ተቋም 'ከመረጣችሁኝ ይህን እሠራለሁ፣ ምረጡኝ' ተብሎ ለሥልጣን የሚፎካከሩበት አይደለም" ሲሉ ተናግረዋል።
ቀጣዩ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ምርጫ በሰላማዊ እና ኃላፊነት በተሞላበት መንፈስ እንዲካሄድም አሳስበዋል።
አሁን በአመራር ላይ የሚገኘው መጅሊስ ሕዝበ ሙስሊሙን ለማገልገል ኃላፊነት ከተረከበ 25 ወራትን እንዳስቆጠረ የጠቀሱት ክቡር ፕሬዚደንቱ፣ ኃላፊነቱን ከተረከበ ጀምሮ ሥራ አስፈጻሚው ራሱን አደራጅቶ፣ የአካታችነት መርኅን በመከተል በክልሎችም እስከ አካባቢ (አጥቢያ) መስጂድ ድረስ የሕዝበ ሙስሊሙን የጋራ ተቋም ለማጠናከር በርካታ ሥራዎች መሠራታቸውን አብራርተዋል።
ክቡር ፕሬዚደንቱ የጠቅላይ ምክር ቤቱ አመራር ኃላፊነቱን ከተረከበበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት ሁለት ዓመታት ያከናወናቸውን ዐበይት ተግባራት ሲያብራሩ፣ በአብሮነት እና በሰላም ጉዳይ፣ በአማራጭ የፋይናንስ ምንጭ ዙሪያ፣ በግልግል ሸንጎ እና በሸሪዓ ፍርድ ቤት የተሠሩ ሥራዎችንና ያጋጠሙ ችግሮችን አብራርተዋል።
በተጨማሪም ፕሬዚደንቱ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የጋራ ተቋም የኾነው ጠቅላይ ምክር ቤቱ፣ በውጪ ግንኝነት ረገድ ከምንጊዜውም በላቀ ደረጃ ሰፊ ሥራዎችን መሥራቱን ተናግረዋል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራር ከ40 በላይ በሚኾኑ ዓለም አቀፍ ጉባዔዎች ላይ በመድረክ ጥናታዊ ጽሑፎችን በማቅረብ ጭምር ባደረገው ንቁ ተሳትፎ፣ የኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ገጽታ ከፍ ወዳለ ምዕራፍ መሻገሩን ክቡር ፕሬዚደንቱ ተናግረዋል።
በተጨማሪም፣ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ የሙስሊም ሀገራት አምባሳደሮች ከተቋሙ ጋር ባደረጉት ግንኙነት ከሙስሊሙ ማኅበረሰብም አልፎ ለሀገር በሚጠቅም ጉዳይ ላይ የሁለትዮሽ ግንኙነት መደረጉን ክቡር ፕሬዚደንቱ አውስተዋል።
የ1445 ዓ. ሒጅራ የሐጅ ክንውንን በተመለከተ፣ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ያሳካቸውን፣ የነበሩበትን ክፍተቶች እና የተገኙ ተመክሮዎችን በተመለከተ ደግሞ፣ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ምክትል ፕሬዚደንትና የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ተጠሪው ሸይኽ አብዱልዓዚዝ ለጋዜጠኞቹ ማብራራያ ሰጥተዋል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሐጅ ከማል ሐሩን በበኩላቸው አዲሱ አመራር የሕዝበ ሙስሊሙን አማና ተቀብሎ ወደሥራ ከገባ ጀምሮ ጥሩ መሻሻል እያደረገ ዋና ዋና በሚላቸው የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ አቅሙን በማዋል የተሻለ ተቋማዊ አሠራርን ለመገንባት ጥረት ሲያደርግ እንደቆየ አስረድተዋል።
ተቋማዊ ለውጡ አሁንም በሂደት ላይ መኾኑን የጠቀሱት ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ ሕግ በማጽደቅ፣ በአንድነትና በመተባበር ዙሪያ፣ በአቅም ግንባታና በማኅበረሰብ ተሳትፎ፣ እንዲሁም በተለያዩ ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ዙርያ የተከናወኑ ተግባራትን አውስተዋል።
በተጨማሪም ዋና ሥራ አስኪያጁ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ሙስሊሙ በአገራዊ ጉዳይ ላይ በቀጥታም ኾነ በተዘዋዋሪ የሀገር ገፅታን በበጎ መልኩ ለመቀየር፣ ሕገ-መጅሊሱን ተግባራዊ ለማድረግ እና ግልፅነት የሰፈነበት አሠራር ለመዘርጋት ትኩረት ሰጥቶ ያከናወናቸውን ተግባራት እና የገጠሙ ተግዳሮቶችን ለጋዜጠኞች በሰፊው አብራርተዋል።
በመጨረሻም፣ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሥራ ኃላፊዎች ወደ ኃላፊነት ከመጡ ጀምሮ የሠሩትንና ያለባቸውን ክፍተት አስመልክተው የሰጡትን ማብራሪያና ጋዜጠኞች ከማኅበረሰቡ ይደመጣሉ ያሏቸውን ቅሬታዎች መነሻ በማድረግ የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀርበዋል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት የተቋሙ የሥራ ኃላፊዎች ከሚዲያ ተቋማት የተሰጡ አስተያየቶችን በገንቢነት ተቀብለው፣ ለጥያቄዎቹ ምላሽ እንዲሰጥባቸው አድርገዋል።

ነሐሴ 27፣ 2016 ዓ.ል | ሰፈር 29፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ፕሬዝዳንቱ ሸሪዓን መሠረት ያደረገ የምርጫ መመሪያ እንዲዘጋጅ ትዕዛዝ ሰጡ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የክቡር ዶክተር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ በ2017 ዓ.ል ለሚደረገው የመጅሊስ ምርጫ ሸሪዓን መሠረት ያደረገ የምርጫ መመሪያ እንዲዘጋጅ ትዕዛዝ ሰጡ።
አዲሱ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አመራር ሀምሌ 11/2014 በሸራተኑ ጉባዔ ላይ በገባው ቃል መሠረት በ2017 ዓ.ል በቀጣይ ተቋሙን የሚመሩ አመራር አካላትን ምርጫ እንደሚያደርግ መግለፁ ይታወሳል ።
በዚህም መሰረት ጠቅላይ ምክር ቤቱ ለዑለማ ጉባዔ እና ለአማካሪ ቦርድ ፅ/ቤቶች እስከ መስከረም 3/2017 ዓ.ል ሸሪዓን መሠረት ያደረገ የምርጫ መመሪያ እንዲያዘጋጁ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት የክቡር ዶክተር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ትዕዛዝ አስተላልፈዋል ።
***

ነሐሴ 28፣ 2016 ዓ.ል | ሰፈር 30፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيم
ለጠቅላይ ምክር ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት እና የሚዲያ ዘርፍ
ሰነድ አዘጋጅ ኮሚቴ ተመረጠ።
አዲስ አበባ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ በዛሬው ዕለት የጠቅላይ ምክር ቤቱን የሕዝብ ግንኙነትና የሚዲያ ዘርፍ ለማጠናከር ከመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ጋር የግማሽ ቀን ውይይት አካሄደ።
በአያ ሆቴል በተካሄደው በዚህ ውይይት ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ተጠሪ ሸይኽ ሑሴን ሐሰን፣ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎቹ የምክር ቤቱን ጥሪ አክብረው በመምጣታቸው ምሥጋና አቅርበው፣ የሕዝበ መስሊሙ ተቋም ከተመሠረተ 50 ዓመት ቢያስቆጥርም፣ የሕዝብ ግንኙነትና የሚዲያ ዘርፉ በሚፈለገው ደረጃ ያደገ አለመኾኑን ተናግረዋል።
ሸይኽ ሑሴን አክለውም የሕዝብ ግንኙነት ዘርፉ በአደረጃጀት እና በአሠራር የተዳከመ በመኾኑ ሙስሊሞች በሀገራቸው በተለያዩ ዘርፎች የሚጫወቱት ሚና እና ኢትዮጵያ በእስልምና ታሪክ ውስጥ ያላት ደማቅ አሻራ በስፋት እንዳይታወቅ ትልቅ ክፍተት እንደፈጠረ አብራርተዋል።
አያይዘውም፣ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ጋር የሚያደርገው ውይይት ክፍተቶችን ደፍኖ የተሻለ አሠራር ለመዘርጋት ትልቅ አርምጃ እንደሚሆን ተናግረዋል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ አብዱል ዓዚዝ አሎ በበኩላቸው የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ አሁናዊ ቁመናን ለባለሙያዎቹ አብራርተው ባለሙያዎቹ በነፃ መንፈስ መፍትኄ-ተኮር ውይይት እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱን የሕዝብ ግንኙነትና የሚዲያ ዘርፍ ለማጠናከር ለውይይት መነሻ የሚኾን ሰነድ ቀርቦ፣ ባለሙያዎቹ በቡድን ተከፋፍለው ውይይት አድርገዋል።
በቡድን ውይይቱ መጨረሻ ላይ ከየቡድኑ የተጨመቁ ሐሳቦች የቀረቡ ሲኾን፣ የሕዝብ ግንኙነትና የሚዲያ ዘርፍን በተመለከተ ከእስልምና ባህሪያት አኳያ ያሉ ተግዳሮቶች፣ ጥንካሬዎች፣ ስጋቶች፣ ዕድሎችና የመፍትኄ ሐሳቦች ተነስተዋል።
ከየቡድኖቹ የቀረቡ ሐሳቦችን እንደ መነሻ በመውሰድ ለጠቅላይ ምክር ቤቱ የሕዝብ ግንኙነትና የሚዲያ ዘርፍ ሙያዊ የሥራ ሰነድ የሚያዘጋጅ ሰባት አባላት ያሉት ኮሚቴ ተመርጧል።
በመጨረሻም የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሐጂ ከማል ሐሩን የጠቅላይ ምክር ቤቱን የሕዝብ ግንኙነትና የሚዲያ ዘርፍ ወደ ከፍታ ለመውሰድ እና በመረጃ ፍሰቱ ከሙስሊሙ ማኅበረሰብ ባሻገር ሀገርን ተጠቃሚ ለማድረግ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎቹ ለሚያበረክቱት አስተዋጽዖ ምክር ቤቱ ያለውን አድናቆት ገልፀዋል።
ዋና ሥራ አስኪያጁ አክለውም፣ ጠቅላይ ምክር ቤቱ የባለሙያዎችን ጥረቶችና አስተዋጽዖዎ አቅም በፈቀደ መጠን ሙሉ ኃላፊነት ወስዶ ለመደገፍ ዝግጁ መኾኑን ተናግረዋል።

ጷጉሜ 3፣ 2016 ዓ.ል | ረቢዓል አወል 5፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
በሀገራዊ ምክክር በሚነሱ የሙስሊሙ አጀንዳዎች ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በጅማ እየተካሄደ ነው።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጋር በመተባበር በሀገራዊ ምክክር በሚነሱ የሕዝበ-ሙስሊሙ አጀንዳዎች ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በጅማ አዌቱ ግራንድ ሆቴል እያካሄደ ነው።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሕዝብ ግንኙነት ተጠሪ ሼይኽ ሑሴን ሐሰን የውውይት መድረኩን ሲከፍቱ ባደረጉት ንግግር፣ ጠቅላይ ምክር ቤቱ የሙስሊሙን ባለ 9 ነጥብ አጀንዳዎች ለሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ በሰነድ አዘጋጅቶ መላኩን አስታውሰዋል።
ለሀገራዊ መግባባት አስፈላጊ ናቸው ተብሎ የታመነባቸው ባለ 9 ነጥብ አጀንዳዎቹ በሀገራዊ፣ በሃይማኖታዊ፣ በመከባበር እና በጋራ ዕድገት ጥያቄዎች ላይ ትኩረት ያደረጉ መኾናቸውን ያወሱት ሼይኽ ሑሴን፣ የምክክር ኮሚሽኑም በትኩረት ያጤናቸዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።
የኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ተወካይ ሼይኽ ሹዓይብ ሸምሱ ሰነዱን በዝርዝር ለውይይቱ ተሳታፊዎች አቅርበው የቡድን ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።
በጅማ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው በሀገራዊ ምክክር የሕዝበ ሙስሊሙ አጀንዳዎች ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የውይይት መድረክ የጅማ ዞን እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የሥራ ኃላፊዎች፣ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የክልሎች፣የሰላምና የዲያስፖራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሳርቱ ሸምሰዲን መገኘታቸውን በስፍራው ከሚገኘው ቃል አቀባያችን የተገኘው መረጃ ጠቁሟል።

መስከረም 2፣ 2017 ዓ.ል | ረቢዑል ዓወል 9፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የፎቶ ዐዉደ-ርዕይ በታላቁ አንዋር መስጂድ ነገ ይከፈታል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ታሪክና ቅርስ ዘርፍ : ከታላቁ አንዋር መስጂድ የወጣቶች ጀመዓና ከፎቶግራፍ ባለሙያው አሕመድ ነጋ ጋር በመተባበር "የሰላሙ ነቢይ" በሚል መሪ ሐሳብ ያዘጋጁት የፎቶግራፍ ዐውደ-ርዕይ ጁምዓ መስከረም 3፣ 2017 ዓ.ል (ረቢዑል ዓወል 10/1446 ዓ.ሒ) በታላቁ አንዋር መስጂድ ቅጥር ግቢ ለሕዝብ ክፍት ይደረጋል።
የ1499 ዓ.ሒ የመዉሊድ አዘጋጅ ኮሚቴ አባል የኾኑት ሼይኽ አብዱልሐሚድ አህመድ ዐውደ-ርዕዩ የታላቁ ነቢይ ልደት (መውሊድ) እንደ ብሔራዊ በዓል መከበር ከጀመረበት ከ1967 ዓ.ል ጀምሮ በታላቁ አንዋር መስጂድ እና በተለያዩ ቦታዎች የተካሄዱ የመውሊድ በዓል ክዋኔዎችን የሚያሳዩ ታሪካዊ ፎቶግራፎች የሚቀርቡበት እንደኾነ ተናግረዋል።
ነገ ጁምዓ በታላቁ አንዋር መስጂድ የሚከፈተው ይኸው ዐውደ-ርዕይ ከመስከረም 3 እስከ መስከረም 8፣ 2017 ዓ.ል ለሕዝብ ክፍት ኾኖ እንደሚቆይ ሼይኽ አብዱልሐሚድ ተናግረዋል።
1 ሺህ 499ኛው የታላቁ ነቢይ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ.) ዝክረ-ልደት በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች ለማክበር ዝግጅቶች እንደተጠናቀቁ ለማወቅ ተችሏል።

መስከረም 3፣ 2017 ዓ.ል | ረቢዑል ዓ. 10፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የፎቶ ዐዉደ-ርዕይ በታላቁ አንዋር መስጂድ ተከፈተ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ታሪክና ቅርስ ዘርፍ ከታላቁ አንዋር መስጂድ የወጣቶች ጀመዓ እና ከፎቶግራፍ ባለሙያው አሕመድ ነጋ ጋር በመተባበር "የሰላሙ ነቢይ" በሚል መሪ ሐሳብ ያዘጋጁት የፎቶግራፍ ዐውደ-ርዕይ በታላቁ አንዋር መስጂድ ቅጥር ግቢ ተከፈተ።
ዐዉደ-ርዕዩ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የእስላማዊ ቅርስና ታሪክ ዘርፍ ተጠሪ ሼይኽ ሙሐመድ አሚን ሰይድ አያሽ እና በታላቁ አንዋር መስጂድ ኢማምና ኸጢብ ሼይኽ ጧሀ ሙሐመድ ሐሩን ተከፍቷል።
በዐዉደ-ርዕዩ መክፈቻ ላይ ሼይኽ ሙሐመድ አሚን ሰይድ ሲናገሩ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የእስላማዊ ቅርስና ታሪክ ዘርፍ የሙስሊሙን ማኅበረሰብ ታሪክና ቅርስ ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማሸጋገር ሥራዎችን እየሠራ ነው ብለዋል።
በቀጣይም በሙስሊሙ ማኅበረሰብ እጅ የሚገኙ የሚዳሰሱ ቅርሶችን የማሰባሰብ ሥራ እንደሚሠራ ጠቅሰው፣ ሙስሊሙ ማኅበረሰብ የበኩሉን አስተዋጽዖ እንዲያበረከት ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሥራ አስፈጻሚ እና የመዉሊድ በዓል አስተባባሪ ኮሚቴ አባል የኾኑት ሼይኽ አብዱልሐሚድ ዛሬ የተከፈተው የፎቶግራፍ ዐውደ-ርዕይ መውሊድ እንደ ብሔራዊ በዓል መከበር ከጀመረበት ከ1967 ዓ.ል ጀምሮ በታላቁ አንዋር መስጂድ እና በተለያዩ ቦታዎች የተካሄዱ የመውሊድ በዓል ክዋኔዎችን የሚያሳዩ ታሪካዊ ፎቶዎች የተካተቱበት በመሆኑ ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ዐውደ-ርዕዩን እንዲመለከት ጥሪ አቅርበዋል።
የታላቁ አንዋር መስጂድ ወጣት ጀምዓ ሰብሳቢ ሐይደር ዳውድ በዚሁ ጊዜ ባደረጉት ንግግር ዛሬ የተከፈተው የፎቶግራፍ ዐውደ-ርዕይ ባለፉት አምስት አሠርት ዓመታት በታላቁ አንዋር መስጂድ የነበረውን የመውሊድ በዓል አከባበር በምልሰት ያሳያል ብለዋ።
ዐውደ-ርዕዩ እስከ መስከረም 8፣ 2017 ዓ.ል ለሕዝብ ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ ጠቅሰው፣ የጉብኝት ሰዓታቱ ለሴት ጎብኚዎች ከጧቱ 3:00 ሰዓት እስከ ረፋዱ 5:00 ሰዓት፣ ለወንድ ጎብኚዎች ደግሞ ከቀኑ 8:00 እስከ 11:00 ሰዓት እንደኾነ ተናግረዋል።
የፎቶ ባለሙያ አህመድ ነጋ በአዉደ ርዕዩ ላይ የቀረቡት ፎቶዎች በአንጋፋ ፎቶ አንሺዎች እና በእርሳቸው የተነሱ መሆናቸው ገልፀዉ ። ከአውደ ርዕዩ መጠናቀቅ በኋላ ለጠቅላይ ምክርቤቱ ኢስላማዊ ቅርስና ታሪክ ዘርፍ እንደሚያስረክቡ ተናግረዋል።
1 ሺህ 499ኛው የታላቁ ነቢይ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ.) ዝክረ-ልደት በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች የሚከበር ሲኾን፣ ከዝግጅቶቹ ውስጥ በሁለንተናዊ ስብዕናና አስተምህሯቸው ላይ ያተኮረውና "የሰላሙ ነቢይ" በሚል ርዕስ ነገ ቅዳሜ የሚደረገው የፓናል ውይይት እንደሚገኝበት ለማወቅ ተችሏል።

መስከረም 4፣ 2017 ዓ.ል | ረቢዑል ዐ. 11፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
"የሰላሙ ነቢይ" በሚል መሪ ሐሳብ ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት ተካሄደ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በነገው ዕለት በድምቀት የሚከበረውን የነቢዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ.) ልደት ለመዘከር "የሰላሙ ነቢይ" በሚል መሪ ሐሳብ ያዘጋጀው የፓናል ውይይት በአያ ሆቴል ተካሄደ።
የፓናል ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሥራ አመራር፣ የመስጂድ እና የአውቃፍ ዘርፍ ተጠሪ ሸይኽ ሙሐመድ አሕመድ ያሲን፣ መውሊድ በኢትዮጵያ ትልቅ ታሪካዊ ፋይዳ ያለው መኾኑን አውስተው፣ የመተሳሰብ እና የአብሮነት እሴቱን ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሥራ አመራር አባልና የ1499ኛው የነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ.) መውሊድ አዘጋጅ ኮሚቴ አባል የኾኑት ሸይኽ አብዱልሐሚድ አሕመድ የታላቁን ነቢይ (ሶ.ዐ.ወ.) ዝክረ ልደት ሁለተናዊ ሰብዕናቸውን እና አስተምህሯቸውን በሚዘክሩ ልዩ ልዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር ተናግረዋል።
ቁርኣናዊ ሰብዕና የነበራቸው ታላቁ ነቢይ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ.) በሰላም፣ በመከባበር እና በመቻቻል ዙርያ ሰፊ አስተምህሮዎችን ትተው ያለፉ መኾናቸውን ያወሱት ሸይኽ አብዱልሐሚድ፣ በተሟላ ሰብዕና ምሳሌነታቸው ላይ ያተኮረ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በፓናል ውይይቱ ላይ ዑስታዝ አደም ካሚል ታላቁ ነቢይ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ.) ከሐበሻው ንጉሥ፣ አስሐመተ ነጃሺ ጋር የተለዋወጧቸውን ደብዳቤዎች በማጣቀስ፣ ኢትዮጵያ በእስልምና ታሪክ ውስጥ ያላትን ጉልህ አሻራ አብራርተዋል።
ዑስታዝ አሕመድ ኢስማዒል በበኩላቸው የነቢዩ ተልዕኮ እና የሕይወት ፈለግ ከሰላም ጋር ያለውን ቁርኝት እና ፍትኅ እና መተሳሰብ በሰላም ለአብሮ ለመኖር ያለውን ፋይዳ ጠቅሰዋል።
ሌላው የመድረኩ ተናጋሪ ኡስታዝ አሕመድ ሙስጠፋ ነቢዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ.) በሰዎች መካከል በማስማማት ረገድ የነበራቸውን የተለየ ጥበብ እና የግጭት አፈታት ዘዴዎችን አስመልክተው ሐሳባቸውን አቅርበዋል።
የፓናሉ አወያይ ኡስታዝ ሙሐመድ ጀማል አብዱልአዚዝ በቀረቡት ጽሑፎችና በተወሱት የነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ.) ፈለገገዋ ሕይወት ትሩፋቶች ዙርያ ተጨማሪ ሐሳቦችን ከሰነዘሩ በኋላ፣ የታዳሚ አስተያየቶች እንዲንሸራሸሩ አድርገዋል።
በፓነል ውይይቱ መጨረሻም፣ የነቢዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ.) የሕይወት ታሪክን መሠረት ያደረገ መንዙማ በመሻኢኮች ቀርቧል።

መስከረም 5፣ 2017 ዓ.ል | ረቢዑል ዓ. 12፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
1 ሺህ 499ኛው የታላቁ ነቢይ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) መውሊድ በታላቁ አንዋር መስጂድ በድምቀት ተከበረ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
1 ሺህ 499ኛው የታላቁ ነቢይ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) የልደት በዓል (መውሊድ) በመላው ኢትዮጵያ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
የዝክረ ልደት በዓሉ በተለይ በአዲስ አበባ በታላቁ አንዋር መስጂድ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች፣ ዲፕሎማቶች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በርካታ ሕዝብ የከተማይቱ ሙስሊም ማኅበረሰብ በተገኘበት ደማቅ ስነ ሥርዓት ተከበረ።
በዓሉ በታላቁ የአንዋር መስጂድ ኢማምና ኸጢብ ሸይኽ ጧሐ ሙሐመድ ሐሩን በቁርኣን የተከፈተ ሲኾን፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ተቀዳሚ ፕሬዚደንት ሼይኽ አብዱልከሪም ሼይኽ በድረዲን ሱሩር በዓሉን አስመልክተው ንግግር አድርገዋል።
ሼይኽ አብዱልከሪም በዚሁ ንግግራቸው የአላህ (ሱ.ወ) እዝነት መገለጫ የኾኑት የታላቀ ነቢይ መወሊድ አንድነትትንና በሰላም አብሮ መኖርን፣ እንዲሁም የመተዛዘንን እሴት የሚያስታውስ በመኾኑ፣ ሕዝበ-ሙስሊሙ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ አደጋዎች ለተጎዱ ወገኖቻችን የእርዳታ እጁን እንዲዘረጋ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
አዲሱ ዓመት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ምርጫ የሚያደርግበት ወቅት መኾኑም በዓሉን ለየት እንደሚያደርገው ተናግረዋል።
ሁሉም ዜጋ ለሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም መሥራት አለበት ያሉት ተቀዳሚ ፕሬዚደንቱ፣ የሃይማኖት አባቶችና የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ለሀገር ሰላምና ለወንድማማችነት ሙጠናከር እንዲሠሩ ጥሪ አቅርበዋል።
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚደንት ሼይኽ ፈትሁዲን ሐጂ ዘይኑ ሙቅና፣ የዘንድሮው መዉሊድ "የሰላሙ ነቢይ" በሚል መሪ ቃል እየተከበረ መኾኑን ተናግረዋል።
ነብያችን ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) ሀገራችን ኢትዮጵያን የፍትኅ እና የእውነት ሀገር መኾኗን መናገራቸውን አስታውሰዋል።
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለሙስሊሙ ማኅበረሰብ የእውቀት ባለውለታ ለሆኑ ቀደምት መሻይኢኾች እውቅና መስጠት መጀመሩን ተናግረዋል።
በዚህ ዓመት ዘመን ተሻጋሪ ባለዉለታ ለሆኑት በታላቁ አንዋር መስጂድ ለአሠርት ዓመታት በኢማምነትና በምክትል ኢማምነት ዑማውን አገልግለው ላለፉት ለሐጅ ዙልመካ ጀማል እና ለሐጂ ሙስጠፋ ሐቢብ (ረሂመሁሏህ) የዘመን ተሻጋሪ ባለዉለታ የምስክር ወረቀት የተበረከተ ሲኾን፣ ሽልማቱን ቤተሰቦቻቸው ተቀብለዋል።
የዘንድሮው የመዉሊድ በዓል የሕዝበ-ሙስሊሙ የጋራ ተቋም በሆነው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ምሥረታ የ50ኛ ዓመት ዋዜማ ላይ እየተከበረ የሚገኝ መኾኑን አስታውሰዋል። ጠቅላይ ምክር ቤቱ የተመሠረተው በ1968 ሲኾን በቀጣዩ ዓመት 50ኛ ዓመቱን ይደፍናል።
የአዲስ አበባ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ የኾኑት ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ ሙስሊሙ ማኅበረሰብ በዓሉን ሲያከብር፣ የነቢዩ ሙሐመድን (ሶ.ዐ.ወ) ፈለግ በመከተል መልካም ሰናይ ምግባራቸውን አልቆ ሊያከብር እንደሚገባው ተናግረዋል።
የከተማው ሙስሊም ማኅበረሰብ የአዲስ አበባ ከተማበ አስተዳደር እያከናወናቸው በሚገኙ የሰላምና የልማት ሥራዎች ላይ ተሳታፊ በመኾኑ አመስግነው፣ በቀጣይ ይህንኑ ተሳትፎውን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።
የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ዋና ፀሐፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ ኢትዮጵያ የእውነትና የፍትኅ ሀገር እንደኾነች ነቢዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) መናገራቸው አስታውሰዉ፣ ዛሬ ሀገራቸውን ከሚወድዱ ወጣቶች ለሙሐመድ አል-አሩሲ እና ለዑስታዝ ጀማል በሽር ምሥጋናቸውን አቅርበዋል።
በበዓሉ ላይ የተገኙት የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ተሟጋች የተከበሩ ሙሐመድ ከማል አልአሩሲ፣ ሃይማኖትና ሀገርን መውደድ ነቢያችን ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) ያስተማሩን በመኾኑ ወጣቱ ትውልድ በተሰማራበት ሁሉ ለሀገሩ ዘብ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።
በበዓሉ ላይ በታላቁ ነቢይ (ሶ.ዐ.ወ) የላቀ ስብዕና እና አስተምህሮዎች ላይ ያተኮረ መንዙማ በታላቁ ማዲህ ሸይኽ ሙሐመድ አወል ሐምዛ ቀርቧል።
ዛሬ በታላቁ አንዋር መስጂድ በተከበረው 1 ሺህ 499ኛው የታላቁ ነቢይ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) የመውሊድ ክብረ በዓል ላይ በአዲስ አበባ ተቀማጭ የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶች ተገኝተዋል።

መስከረም 11፣ 2017 ዓ.ል | ረቢዑል ዓ. 18፣ 1446 ዓ.ሒ

20ኛዉ የሙስሊም ዓለም አቀፍ መድረክ በሩሲያ እየተካሄደነው።

ሀገራችን ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳትፋችበት 20ኛ የሙስሊም አለም አቀፍ መድረክ በሩስያ ሞስኮ እየተካሄደ ነው።
የሰላም መንገድ፡ “ውይይት ለጋራ አብሮ መኖር መሰረት ነው” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ የሚገኘው 20ኛ የሙስሊም አለም አቀፍ መድረክ ከዓለም ሐገራት የመጡ ዓሊሞች ተሳታፊ ሆነውበታል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳይ ጠቅላየ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የክብር ዶክተር ሼይህ ሀጂ ኢብራሂም ሀገራችንን ወክለው ንግግር ማድረጋቸውን ከስፍራው የሚገኘው የጠቅላይ ምክር ቤቱ ቃል አቀባይ የላከው መረጃ ያመላክታል።

አወሊያ ትምህርት ቤቶችን በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ።

የአወሊያ ትምህርት ቤቶች የቀጣይ አምስት ዓመታት ስልታዊ እቅድን (Strategic Plan) ለማዘጋጀት በዛሬው ዕለት በጠቅላይ ምክር ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሐጂ ከማል ሐሩን የውይይት መድረኩን በንግግር ሲከፍቱ ጠቅላይ ምክር ቤቱ በለውጥ ሂደት ላይ ያለ ተቋም መሆኑን ተናግረዋል።
ሐጂ ከማል አክለውም አወሊያ ትምህርት ቤት የተቋቋመበትን ዓላማ ለማሳካት የሚያስችል ስልታዊ እቅድ ለመንደፍ ከባለድርሻ አካላት ተቀራርቦ መወያየትና ለእቅዱ ግብዓት የሚኾኑ ሐሳቦችን ማሰባሰብ አስፈላጊ ነው ብለዋል።
አወልያ ትምህርት ቤቶች የለውጡ ታሪክ አካል መኾኑን ያስታወሱት ሐጂ ከማል፣ ትምህርት ቤቶቹ በለውጡ ሂደት መለወጥ ያለበትን እና መለወጥም የሚችለውን እውን ማድረግ እንዲችሉ ነፃነት ሊኖራቸው እንደሚገባ ተናግረዋል።
በመዘጋጀት ላይ ያለው ስልታዊ እቅድ የአወሊያ ተማሪዎችን ሁሉን አቀፍ በኾነ መልኩ ተወዳዳሪ ለማድረግና ተቋሙም የተሻለ ቁመና ላይ እንዲገኝ አስፈላጊ በመኾኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በዚህ የውይይት መድረክ ላይ በቅንነት ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ዋና ሥራ አስኪያጁ አሳስበዋል።
ሙስሊሙን ማኅበረሰብ በሀገሩ ጉዳይ ላይ ንቁ ተሳታፊ እና በሁሉም ዘርፍ ተወዳዳሪ ለማድረግ ስልታዊ እቅድ ነድፎ ሁሉን አቀፍ ማኅበረሰባዊ ለውጥ ማምጣት አስፈላጊ መሆኑን በአፅንዖት ተናግረዋል።
የአወሊያ እርዳታና ልማት ድርጅት ከሰኔ 2003 ዓ.ል ጀምሮ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አንዱ የማኅበራዊ ልማት ቅርንጫፍ በመኾን እያገለገለ መኾኑን የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ ሐጂ ሰዒድ አስማረ ተናግረዋል።
የትምህርቱ ዘርፍ በአሁኑ ጊዜ ከፍተኛ ተግዳሮት ያለበት በመኾኑ የአወሊያ ትምህርት ቤቶችን የቀጣይ አምስት ዓመታት ስልታዊ እቅድ ለማዘጋጀት የሚደረገው ጥረት ትውልዳዊም ሀገራዊም ኃላፊነት እንደሆነ ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል።
የአወልያ ትምህርት ቤቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ የትምህርት ጥራቱን እየጠበቀ በመምጣቱ በ2016 በተሰጠው አገር አቀፍ ፈተና የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተማሪዎቹን 97 በመቶ ያሳለፈ ሲሆን፣ የ12ኛ ክፍል ዉጤቱም ከቀዳሚው ዓመት መሻሻል የታየበት መኾኑን ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል።
አወሊያ የእርዳታና የልማት ድርጅት የጤና፣ የረድዔት እና የትምህርት አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም ቢኾንም፣ አብዛኛው ትኩረቱ (70 በመቶ) በትምህርት አገልግሎት ላይ መሆኑን ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል።
አወልያ ከ1988 ዓ.ል ጀምሮ የአረብኛ ቋንቋ ሲያስተምር የቆየና በመስኩም ብቸኛ እውቅና ያለው ኮሌጅ መሆኑን የጠቀሱት ሥራ አስኪያጁ፣ ከማኅበረሰብ አቃፊነቱ አኳያም 710 ተማሪዎችን በነጻ እንደሚያስተምር ተናግረዋል።
በዚሁ ጊዜ፣ የአወሊያ የቀድሞ ተማሪዎች ትምህርት ቤቱን ወደላቀ ደረጃ ለማድረስ በመሻት የሚካሄደውን የስልታዊ እቅድ ዝግጅት ወጪ ለመሸፈን ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የድርጅቱ የሥራ አመራር ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ አሽረፍ ጀማል የሀገራችን ትምህርት በአሁኑ ዘመን የገጠመውን ፈተና ተቋቁሞ ተወዳደሪ እና በስነ-ምግባር የታነጸ ትውልድ ለማፍራት ከአወልያ ባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር ማድረግና ዘመኑን የሚዋጅ ስልታዊ እቅድ የመንደፍ አስፈላጊነትን ተናግረዋል።
ስልታዊ እቅድ የማዘጋጀት ሐሳቡ ከተወጠነ የቆየ ቢኾንም፣ በነበረው የበጀት እጥረት ሳቢያ ውጥኑን ወደ ሥራ መቀየር ሳይቻል እንደቆየ አብራርተዋል።
የአወሊያ ትምህርት ቤቶች የአምስት ዓመት ስልታዊ እቅድን ለማዘጋጀት ከባለድርሻ አካላት ጋር የተካሄደውን የውይይት መድረክ የስልታዊ እቅዱ አዘጋጅ የኾነው ጋላክሲ ዊዝደም የምክር አገልግሎት እንዳዘጋጀው ለማወቅ ተችሏል።

መስከረም 12፣ 2017 ዓ.ል | ረቢዑል ዓ. 19፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
20ኛዉ የሙስሊም ዓለምአቀፍ መድረክ ሙፍቲ ሸይኽ ራዊ ዐይነዲንን በመምረጥ ተጠናቀቀ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
በሩስያ መዲና፣ መስኮብ የተካሄደውና ሀገራችን ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፈችበት 20ኛዉ የሙስሊም ዓለምአቀፍ መድረክ ሸይኽ ራዊ ዐይነዲንን በሙፍቲነት በመምረጥ ተጠናቀቀ።
በ20ኛዉ የሙስሊም ዓለምአቀፍ መድረክ ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ኢትዮጵያን በመወከል ታድመውበታል።
ሞስኮ ውስጥ በሚገኘው መስጂደል ጀዋሚዕ የመሰብሰቢያ አዳራሽ "የሰላም መንገድ፡ ውይይት የተጣጣመ አብሮ መኖር መሠረት" በሚል መርኅ በተካሄደው በዚህ ጉባዔ ላይ ንግግር እንዲያደርጉ ከተመረጡ አሥራ አምስት ሀገራት አንዷ ሀገራችን ኢትዮጵያ ነች።
ክቡር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ ኢትዮጵያ ከንጉሥ አስሐመተል ነጃሺ የተወረሰ ልዩነትን የማስተናገድ የረጅም ዘመን ታሪክ ያላት መኾኗን ጠቅሰው፣ ዓለም ይህን ልምድ ከኢትዮጵያ ሊወስድ ይገባዋል ብለዋል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት ከጉባዔው ጎን ለጎን ከሩሲያ መጅሊስ ፕሬዚደንት ጋር ተገናኝተው የተወያዩ ሲኾን፣ የሁለቱ አገራት መጅሊሶች በጋራ ጉዳዮች ላይ አብረው ለመሥራት አሥር ነጥቦችን የያዘ የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል።
በተጨማሪም፣ ክቡር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ በጉባዔው ላይ ተሳታፊ ከነበሩ የሕንድ፣ የናይጄሪያ፣ የቱኒዝያ እና የኳታር መፍቲዎች ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።
በሞስኮ ከተማ በተካሄደው 20ኛው የሙስሊም ዓለምአቀፍ መድረክ ላይ ከአርባ ሀገራት የተውጣጡ ሙስሊም ሊቃውንት (ዓሊሞች) ተሳታፊ ሆነዋል።
ከተመሠረተ 30ኛ ዓመቱን በማክበር ላይ የሚገኘው የሙስሊም ዓለምአቀፍ መድረክ ላለፉት 20 ዓመታት በየዓመቱ ጉባዔ ሲያካሂድ የቆየ መኾኑ ታውቋል።
ሀገራችን ኢትዮጵያ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በተሳተፈችበት በዚህ ጉባዔ ላይ ከዚህ በኋላ በየዓመቱ ቋሚ ተሳታፊ እንደምትሆን በስፍራው የሚገኘው የጠቅላይ ምክር ቤቱ ቃል አቀባይ ያደረሰን መረጃ ያመላክታል።
••••••••••••••••••