ሰኪነቱል ሩህ🖤
487 subscribers
43 photos
3 videos
1 link
መልካም የሆነ ማንፀባረቅን ከዉስጥ የሚዘልቅ ንፅፅርን እንዲሁም እርጋታን የሚሰጥ ፅሁፍን በአንድ ላይ ተሰናድቶ የሚቀርብበት channal🙌
Download Telegram
የአንዳንድ ሰዎች ልብ ግን ንፁህነቱ አያስገርምም

መሄድ ያለባቸዉ ርቀት ድረስ ሄደዉ የዋህነታቸዉን የሚያንፀባርቁ
መቆም ሲኖርባቸዉ አቋቋማቸዉን የሚያሳምሩ
ቤተሰብ ሳይሆኑ ከዛም በላይ ሆነዉ በልቦቻችን ላይ የተጠለሉ ድንቅ ፍጡራን ቢባሉ የማያንስባቸዉ
ከሩህና ከጀሰዳችን የተጣመሩ ሰዎች


ይህንን ኒእማ የተቸረን እኛ ግን በአልሀምዱሊላህ ብቻ ነዉ ምናመሰግነዉ🫠
🥰8🔥2🤝2
አልጐዱንም አላልንም እኮ ሰባብረዉናል
ነገር ግን
ስብርባሪዉን ይዘን ወደ አላህ ስንጠጋ
በኔ ያልተሰበረ ልብ አልጠግነዉም ብሎ አላሳፈረንም

መጎዳታችን እስኪረሳን ድረስ ጠግኖናል
ከደጃፉ መጠጋታችን እንኳን ሰበሩን እስኪያስብለን አሽሮናል


ይብላኝ ለሰበሩን እኛስ በማይሽር መድሃኒት ተጠግነናል🙌
6🔥3👌3
{الْيَوْمَ نَخْتِمُ عَلَىٰ أَفْوَاهِهِمْ وَتُكَلِّمُنَا أَيْدِيهِمْ وَتَشْهَدُ أَرْجُلُهُم بِمَا كَانُوا يَكْسِبُونَ} [يس : 65

በርግጥ ነገራቶች ማብቂያ አላቸዉ
ፍፃሚያቸዉ መጀመርያ ባስገኛቸዉ ስር ነዉ
ዛሬ ላይ የተሰጡን ኒዕማዎች ነገ በኛ ላይ መስካሪዎች ናቸዉ
እጆቻችን በምን ላይ እንደዎሉ እግሮቻችን ወደ የት እንዳስጓዝናቸዉ ለፈጠራቸዉ ተናጋሪዎች ናቸዉ

ኸሊቅ ቃሉን አክባሪ ነዉ እያንዳንዱን ነገር ባሻዉ ቀን በወሰነለት እለት ይቋጫል
በእያንዳንዱ ተግባር ሂሳብም ያደርጋል


إنا لله وإنا إليه راجعون
3❤‍🔥2🔥2
ሰኪነቱል ሩህ🖤 pinned «{الْيَوْمَ نَخْتِمُ عَلَىٰ أَفْوَاهِهِمْ وَتُكَلِّمُنَا أَيْدِيهِمْ وَتَشْهَدُ أَرْجُلُهُم بِمَا كَانُوا يَكْسِبُونَ} [يس : 65 በርግጥ ነገራቶች ማብቂያ አላቸዉ ፍፃሚያቸዉ መጀመርያ ባስገኛቸዉ ስር ነዉ ዛሬ ላይ የተሰጡን ኒዕማዎች ነገ በኛ ላይ መስካሪዎች ናቸዉ እጆቻችን በምን ላይ እንደዎሉ እግሮቻችን ወደ የት እንዳስጓዝናቸዉ…»
በወደድነዉ ልክ እኮ አንወደድም
ባሰብነዉ ልክም አንታሰብም
በተመኘነዉ ልክ አናገኝም
በሰጠነዉም እኩል አይሰጠንም
በቀረብነዉ ልክ አንቀረብም


መጉደልና መሙላት የዱንያ ጆንያ ነዉ
ሞልቶ መፍሰስም ከዱንያ መጋዘን ነዉ
ከጆንያዉም ከመጋዘኑም አለመንገዳገድ ግን የአኼራ ቁልፍ ነዉ
🤌
🔥6🤝5👍3
በነገራችሁ ላይ ከሰዉ ምንም አለመጠበቅ የተማርኩት በራሴዉ ቻናል ነዉ😭

ጥበብን አጨናንቃታለዉ ግን ወፍ react🥲
ፈሰብሩን ጀሚል😫
😁94🤣4
ቻናሌን ቻናላችን ለማስባል አንድ ደባል ጨምረናል
new admin welcome

አታሳፍሩኝ በ react አሙቁላት❤️
1👏114🤗4
ሰኪነቱል ሩህ🖤 pinned «ቻናሌን ቻናላችን ለማስባል አንድ ደባል ጨምረናል new admin welcome አታሳፍሩኝ በ react አሙቁላት❤️»
የታመመ ሁሉ ይሞታል ማለት አይደለም
ነገር ግን የታመመ ሁሉ ይሽራል ማለትም አይቻልም
ሁሉም ሊነካካ የማይፈልገዉ ቁስል አለ

ምናልባት ከቅርቡ አልያም ከራቀዉ ካልሆነም ከጎኑ ካለዉ ፍጡር ያልተቋጠረ ህመም አለዉ

ሁሉም ያልፋል ነገርግን አትነካኩኝ የተባለለት የልብ ቁስል ተዳፍኖ ይቀራል


ይቅርታ ባይሽረዉም ማስታገሻ ይሆነዎል💔
9❤‍🔥3🔥1
በአካል የምታቁኝ ሰዎች ግን በመንገድ ስንተላለፍ ፅሑፎቹ ግን ያንቺ ናቸዉ የምትሉኝ


አይ ላልተገደበ ቀናት ተበድሬያቸዉ ነዉ 😭
ምን ይባላል ይሄ😫
🤣9😁2
የደከመች ነፍስ ትንሽ ዘንበል ካለች መዉደቂያዎ የሸይጣን ደጃፍ ላይ ነዉ

ምንም ያኽል ቢከብዳችሁ ብታዝኑ የጠበቃችሁት ነገር የዉሃ ሽታ ሆኖ የዘገየ ቢመስላችሁ እንኳን አደራ በአላህ ተስፋ እንዳትቆርጡ

የተወለደ ህፃን በሳምንቱ ቢራመድ በሽታ አልያም ሸይጣን ነዉ ብለዉ ያገሉታልም ያጠፉታል

ታድያ የዘገየዉ ነገር በጠበቃችሁት ሰአት አግኝቷቹት ቢሆን ኖሮ ጠፉቶ አጥፊያችሁ ሊሆን ይችል ነበር🙌

ትንሽ ሰብሩ

ነፍሴ በእጁ በሆነችዉ ጌታ እምላለዉ
እኛ ቸኩለን እንጂ ጀሊል ዘግይቶ አይደለም🫶
7🔥1
እመነኝ መኖርህ ማንንም ካልጠቀመ መሞትህ ማንንም ሊጎዳ አይችልም። ስለዚህ ዱንያ ላይ ስትኖር ዋጋ ያለው ሰው ሁን🤞
🔥85👍3
አንዳንድ ሰዎች ግን የሌላችሁን ነገር ልንሰጣቹ ስንሞክር ልክ እንደ ፍቅር ክብር አይነቶችን ስንቸራቹ
ቀድሞዉንም ለምን እንዳልነበራቹ ታሳዩናላቹ
😫

አላህ ይስጣቹ👩‍🦯‍➡️
4🔥4👌2
ዳቦዉን ለማዉጣት የታሰረዉን ፌስታል ስበጥስ አይታኝ

ካንቺ ግን ፅሑፎችሽ ሰብርና ቁምነገር አላቸዉ አለችኝ


ማማ ግን ተይ😭
🤣11😁3🤝1
ጁሙዓ መልዕክት:-

--ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
"مَنْ صَلَّى عَلَىَّ وَاحِدَةً صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ عَشْرًا ‏"‏ ‏
"ማንም በእኔ ላይ አንድ ሰለዋት ያወረደ፣ አላህ በእርሱ ላይ ሰለዋት ያወርዳል።"
📘 ሶሒሕ ሙስሊም 408

--እንዲሁም እንዲህ አሉ፦

أَوْلَى النَّاسِ بِي يَوْمَ الْقِيَامَةِ أَكْثَرُهُمْ عَلَىَّ صَلاَةً ‏
"
"በፍርዱ ቀን ለኔ ይበልጥ ቅርብ የሆኑት፣ በእኔ ላይ ብዙ ሰለዋት የሚያወርዱ ናቸው
።"
📘 ጃሚዕ አት-ቲርሚዚ 484

--
እንግዲ አህባቢ ሰለዋት እያበዛን🙌
8🔥3🥰1
ጌታችሁን ግን ማን ብላቹ ነዉ የምጠሩት 🙂
❤‍🔥6🔥3🏆3
ጨቅላነት ግን ደስ ሲል
የቱ ጊዜ ናፈቀሽ ብለዉ ቢጠይቁኝ
በቤተሰብ ታጅቤ በእናቴ ስር ዉስጥ የታቀፍኩበት ጨቅላነቴ እላቸዉ ነበር


ትንፋሼ ትንፋሽዎን በሚስብበት
እጆቼ እጆችዎ ላይ የሚተረማመሱበት እንቁ ጊዜያት አለመናፈቅ እንዴት ይቻላል


እድገትማ የራስሽ ወልደሽ ታቀፊ ከመባል የዘለለ ምን ተረፈኝ🥲
❤‍🔥6🥰3
Forwarded from Halal memory🫀
ተቀዳሚ ሙፍቲ ሸይኽ ዑመር ኢድሪስ ወደ አኼራ ተሻግረዋል።

ሁላችንም ኺያጆች ነን። ከአላህ ግን ዘውታሪ ነው። መልካም ጸባያቸውን የምንከተል ያድርገን።
💔12😨31😭1
ራሴን እቀየመዎለዉ

ከማይሆኑኝ ሰዎች ጎን መቀማመጤ
ስለእኔ በሌለሁበት ጠበቃ ለማይሆኑኝ ፍጥረታት ሽንጤን ገትሬ መከራከሬ


ለክብራቸዉ ማሸርጎዴ ለስሜታቸዉ መነጠፌ
ለደስታቸዉ ማጨብጨቤ ለሀዘናቸዉ መከፋቴ


ራሴን እንድቀየመዉ ያደርገኛል

አንድ ወደፊት ለማይራመዱልኝ 100 እርምጃዎችን መራመዴ
ከጀርባዬ ለሚወጉኝ ከጎናቸዉ መደገፌ
ለሚሄዱልኝ ብዙ መሮጤ
ለማይደክሙሉኝ ብዙ መንከራተቴ

እያሳነሱኝ እነሱን ማላቄ
እያዎረዱኝ እነሱን ማክበሬ
እየራቁኝ በእጥፍ መቅረቤ
ጉዳቱ ደርሶ ሲያመዝን ከጥቅሙ እየሸሸ
ዝም ማለት ሆነ ምላሹ


ብቻ ዝምብዬ ሳስበዉ
አንዳንዴ ራሴን እቀየመዎለዉ💔


🔥3👏3💔3
ሰኪነቱል ሩህ🖤 pinned «ራሴን እቀየመዎለዉ ከማይሆኑኝ ሰዎች ጎን መቀማመጤ ስለእኔ በሌለሁበት ጠበቃ ለማይሆኑኝ ፍጥረታት ሽንጤን ገትሬ መከራከሬ ለክብራቸዉ ማሸርጎዴ ለስሜታቸዉ መነጠፌ ለደስታቸዉ ማጨብጨቤ ለሀዘናቸዉ መከፋቴ ራሴን እንድቀየመዉ ያደርገኛል አንድ ወደፊት ለማይራመዱልኝ 100 እርምጃዎችን መራመዴ ከጀርባዬ ለሚወጉኝ ከጎናቸዉ መደገፌ ለሚሄዱልኝ ብዙ መሮጤ ለማይደክሙሉኝ ብዙ መንከራተቴ …»