ሰኪነቱል ሩህ🖤
487 subscribers
43 photos
3 videos
1 link
መልካም የሆነ ማንፀባረቅን ከዉስጥ የሚዘልቅ ንፅፅርን እንዲሁም እርጋታን የሚሰጥ ፅሁፍን በአንድ ላይ ተሰናድቶ የሚቀርብበት channal🙌
Download Telegram
እዉነት ታምራለች
ዉበቷ ግን ለሁሉም ግልፅ አልሆነም
የመታየት ስልጣን ለጥቂቶቹ ብቻ አንግሳለች
ክብሯን ጠበቅ አድርጋ ስሜቷን ሸሽታለሽ

እዉነት ታምራለች
ጌታዎን ተመክታ መንገዱን አልፋለች
ታድያ ለምን ብላ ትገላለጣለች
ይሄ አለም እንደሚያልፍ ጠንቅቃ ታዉቃለች
እዉነት ታምራለች

የስልጣን ምሰሶ በኔ ላይ ቢያርፍ ኖሮ
ለ 1ቀን የአለም እንስቶች የዚን ጨርቅ መሳይ የሀያእ ግርዶሽን በነሱ ላይ እሾም ነበር ሰላምና መስከንም በነሱ ላይ ይንገዎለል ይሆን ይሆናል
7🥰1
ከይቅርታ በሗላ ግን የነበረዉ ቅርበት እንደነበረዉ ይሆናል ?

የሆነ ድንበር ያደረግንበት ነገር ላይ ጥሰዉ ከገቡ በሗላ
ላለማድረግ ምክንያት ያስቀመጥንበት ተግባር ላይ ወደዉ ሲገኙ
ከአካላችን ዘልቆ ልባችን ከደማበት ነገር በሗላ እንዴት ነዉ ይቅርታ የሚያብሰዉ

ልናወራ ልንስቅ ልንጫወት እንችል ይሆናል ግን በተሰባበረዉ የልብ ስባሪ መዉደድ ግን እኔጃ
🤷‍♀

አስቡት የጋዛን ህዝብ
1 ቤተሰብ በሙሉ ያለሀቅ ከጠፋ በሗላ
ልጅ ከእናት ከተነጠለ እህት ወንድሟን ካጣች በሗላ
ህፃናት መኖር ሳይጀምሩ ከሞቱ በሗላ

ይቅርታ ምንም ማድረግ ስላልቻልን
ይቅርታ ማድረግ እየቻልን ችላ ስላልን
ይቅርታ በዱኣ እንኳን አብረናቹ ስላልሆንን
ብንላቸዉ የምር ይቅርታችን እነሱ ጋር ለዉጥ ያመጣ ይሆን
ኸሊቁ ከላይ ሲመለከት ልቦቻችንን ምን ያኽል እንደነደኑ ታዝቦ አዝኖብን ቢሆንስ
ህምምምምም💔
💔4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ምንም እንኳን ትራምፕ ወዲያውኑ ጥቃት እንዲያቆም እስራኤልን ቢጣራም, ዛሬ ላይ ጋዛ ከባዱን ጊዜ እያሳለፈች ነው።
ህፃናት እንደቅጠል እየረገፉ ነው።
ዛሬ የጋዛ ውሎ ከባድ ነበር
@STRONG_IMAN
😭8
ቀኑ ዘንበል ሲል ሁኔታዎች ገልበጥ ብለዉ የፊታቸዉን ለመለየት ስትቸገር

ያቀናኛል ያልከዉ መስመር ተጣሞ ስታየዉ

መደገፍያ ያልከዉ ምርኩዝ ከጎንህ
ባታገኘዉ

የመልካም ብድሩ መሰበር ነዉና
ሳታዝን ሳታፍር አላህን ተጠጋ

መዳበር ካለበት ነገር ቢኖር ከረህማን ጋር የማንሾካሸክ ጥፍጥናን ነዉ
ሰዎች በመኝታቸዉ ደገፍ ባሉ ሰአት ለማይተኛዉ ኸሊቅ ተንፍስለት
ሸክምህ ሲወርድ በግልፅ ይታይሃል🫶
🔥5👍1
በነገራችን ላይ መርሳት የሚባል ነገር የለም መተዉ እንጂ 😮‍💨
💔5
ተጨንቀን ተጠበን ተባልተን ተሰብረን የምንዎጋለት የምንካራተትለት ዱንያ
ፍሬዉ ሲሰምርና ዉጤቱ ሲያብብ ምናልባት እኛን አያካትትም💔

ፍሬዉ አፍርቶ ዉጤቱን ከሚበሉት አላህ ያድርገን 🖤
5🙏3
ማስመሰል አካል ቢኖረዉ ኖሮ የሚመስለዉ ቲክቶክ የሚሰሩትን ሰዎች ነበር
የቲክቶክ ህይወት አራምባና ቆምቦ ያልሆነባቸዉ ከአብዛኛሆቹ ጥቂቶቹ ናቸዉ
የሚፖስተዉ ሌላ የሚኖረዉ ሌላ
ማየት ማመን ነዉ የሚሉት የኢትዮዽያ አሽቋላጭ ቃል በቲክቶክ መንደር ገለዉ ቀብረዉቷል
ያየነዉ መልካሟን የሚኖሩት ሸሩዎን


ብቻ ግን follow repost like የምታደርጉትን ሰዎች ለዩ
ነገ አላህ ፊት follow ባደረግነዉ like አድርገን ባለፍነዉ repost ብለን ለሌሎች ላሳወቅነዉ እያንዳንዷ ነገር ተጠያቂ ነንና
😁4😭3🔥2
እኔ ብቻ ነኝ ግን የሰሞኑ ፀሃይ የግብፅ እጅ እንዳለበት የሚሰማኝ 😫
😭3🤷‍♀2
ከብዙ ጊዜ መጠፋፋት በሗላ ጓደኛዬ እቤቴ ልጠይቀኝ ከታናሽ እህቷ ጋር መጣች

እህቷ ከትንሿ እህቴ ጋር እኔም ከጓደኛዬ ጋር ሆነን መጫወት ማዉጋት ጀመርን

ከትንሽ ቆይታ በሗላ እኔ ወደ ማዕድ ማቀራረብ ጓደኛዬም ወደ ቲክቶክ አለም ተፈተለክን

ታድያ በድንገት ከዚ በፊት አብራን መድረሳ የደረሰችዉን ሌላኛዎን ጓደኛችን በscreenኡ ስር በዘፈን ስትወዛወዝ የቀረፀችዉ ምስል ደረሳት

እኔም ሳየዉ እሷም ስታሳየኝ ተደናግጠን ነበር
አላህ ይመልሳት ብዬ ሾለክ አልኩኝ
ጓደኛዬ ግን በጣም በንዴት እና በቁጣ እንዴት በዘፈን እያለች መንጎራደድ ስሟን ማጠልሸት ጀመረች

ከዛ ግን በአመታት የምትበልጣት ትንሿ እህቷ አንቺ እቤት ብቻችንን ስንሆን ዘፈን ታዳምጪ ትጨፉሪ አይደል ብላ በንዴቷ ላይ ሌላ ድንጋጤ አዘነበችባት

እና ሁለታችንም ያንን ርዕስ ዘግተን በሌላ ጉዳይ መሽጉል ሆነን ተሸኛኘን
ምን ተማራቹበት እስኪ🫴
😁5🤔1
ሰኪነቱል ሩህ🖤 pinned «ከብዙ ጊዜ መጠፋፋት በሗላ ጓደኛዬ እቤቴ ልጠይቀኝ ከታናሽ እህቷ ጋር መጣች እህቷ ከትንሿ እህቴ ጋር እኔም ከጓደኛዬ ጋር ሆነን መጫወት ማዉጋት ጀመርን ከትንሽ ቆይታ በሗላ እኔ ወደ ማዕድ ማቀራረብ ጓደኛዬም ወደ ቲክቶክ አለም ተፈተለክን ታድያ በድንገት ከዚ በፊት አብራን መድረሳ የደረሰችዉን ሌላኛዎን ጓደኛችን በscreenኡ ስር በዘፈን ስትወዛወዝ የቀረፀችዉ ምስል ደረሳት እኔም ሳየዉ…»
ሰኪነቱል ሩህ🖤
ከብዙ ጊዜ መጠፋፋት በሗላ ጓደኛዬ እቤቴ ልጠይቀኝ ከታናሽ እህቷ ጋር መጣች እህቷ ከትንሿ እህቴ ጋር እኔም ከጓደኛዬ ጋር ሆነን መጫወት ማዉጋት ጀመርን ከትንሽ ቆይታ በሗላ እኔ ወደ ማዕድ ማቀራረብ ጓደኛዬም ወደ ቲክቶክ አለም ተፈተለክን ታድያ በድንገት ከዚ በፊት አብራን መድረሳ የደረሰችዉን ሌላኛዎን ጓደኛችን በscreenኡ ስር በዘፈን ስትወዛወዝ የቀረፀችዉ ምስል ደረሳት እኔም ሳየዉ…
ብቻሽን ለፍሊፊ ያለኝ እኔ😭

እኔ ግን ምን አሰብሽ ብትሉኝ
ሁላችንም የሰራናቸዉ ወይም የምንሰራቸዉ ወንጀሎች ከመሞታችን በፊት በቪድዮ ብናይ ምናልባት ሰዎችን መተቸት እናቆም ነበር
እላለዉ

እኛ የምንሰራዉን ድብቅ ወንጀሎች እነሱ በእዉኑ አለም ስላንፀባረቁት የኛ ተሸሽጎ የቀረዉ ትክክል ነዉ ማለት አይደለም
እነሱ ግልፅ አወጡት እንጂ ያዉ ያዉ ነዉ


በሰዎች ላይ መፍረድ ያቆምኩት የፈረድኩባቸዉን ሰዎች ሆኜ ስገኝ ነዉ💔

በፈረድኩት ልክ ተሰፍሮ ተሰቶኛል
ምናልባት እኮ እነሱ የእኛን ተቺዎች ወንጀል አላህ እንዲያዩት ቢያደርግ ኖሮ ከኛም የባሰ አለ ብለዉ በአፎቻቸዉ ባንጠባጠቡን ነበር🥲

ልክ ናቸዉ እያልኩኝ አይደለም ነገር ግን እኛም ልክ አይደለንም ለማለት ነዉ

ቀልብን እንዳሻዉ ሚገለባብጠዉ ጀሊል
ባለንበት እንድንፀና ያግዘን እንጂ እኛማ ከነፈሰበት ነፋሽ ከተቀመጠበት ተቀማጭ ነን


ማድረግ የምንችለዉ ነገር ከሌለ በቀልባችን ጠልተን በዱኣችን አንርሳቸዉ

🖤
9🔥1
የምፖስተዉን ፅሑፍ በ20 ሰዎች ብቻ ነዉ የሚታየዉ የተቀሩት አይነስ*ር ናቸዉ እንዴ jk🫶

እቺም ቻናል ሆና ምቀኛ በዛባት😆
😁8🤣1
Them: ጉንፋን እኮ ቀላል በሽታ ነዉ ጠንከር በይ

ሸሃዳ ያስያዘኝ እኔ 😭



የተዋበ ጁመኣ🫶
😁7😭1
የእኛ ሆነዉ የማይረዱን፣ የእኛ ሆነዉ የማያስቡልን የእኛ ሆነዉ የማያዝኑልን፣የእኛ ሆነዉ የእኛ ያልሆኑ ሰዎች ጋር ያለንን ኮንትራት እንደመቅደድ የመሰለ እፎይታ የለም🫰
🔥42
የአንዳንድ ሰዎች ልብ ግን ንፁህነቱ አያስገርምም

መሄድ ያለባቸዉ ርቀት ድረስ ሄደዉ የዋህነታቸዉን የሚያንፀባርቁ
መቆም ሲኖርባቸዉ አቋቋማቸዉን የሚያሳምሩ
ቤተሰብ ሳይሆኑ ከዛም በላይ ሆነዉ በልቦቻችን ላይ የተጠለሉ ድንቅ ፍጡራን ቢባሉ የማያንስባቸዉ
ከሩህና ከጀሰዳችን የተጣመሩ ሰዎች


ይህንን ኒእማ የተቸረን እኛ ግን በአልሀምዱሊላህ ብቻ ነዉ ምናመሰግነዉ🫠
🥰8🔥2🤝2
አልጐዱንም አላልንም እኮ ሰባብረዉናል
ነገር ግን
ስብርባሪዉን ይዘን ወደ አላህ ስንጠጋ
በኔ ያልተሰበረ ልብ አልጠግነዉም ብሎ አላሳፈረንም

መጎዳታችን እስኪረሳን ድረስ ጠግኖናል
ከደጃፉ መጠጋታችን እንኳን ሰበሩን እስኪያስብለን አሽሮናል


ይብላኝ ለሰበሩን እኛስ በማይሽር መድሃኒት ተጠግነናል🙌
6🔥3👌3
{الْيَوْمَ نَخْتِمُ عَلَىٰ أَفْوَاهِهِمْ وَتُكَلِّمُنَا أَيْدِيهِمْ وَتَشْهَدُ أَرْجُلُهُم بِمَا كَانُوا يَكْسِبُونَ} [يس : 65

በርግጥ ነገራቶች ማብቂያ አላቸዉ
ፍፃሚያቸዉ መጀመርያ ባስገኛቸዉ ስር ነዉ
ዛሬ ላይ የተሰጡን ኒዕማዎች ነገ በኛ ላይ መስካሪዎች ናቸዉ
እጆቻችን በምን ላይ እንደዎሉ እግሮቻችን ወደ የት እንዳስጓዝናቸዉ ለፈጠራቸዉ ተናጋሪዎች ናቸዉ

ኸሊቅ ቃሉን አክባሪ ነዉ እያንዳንዱን ነገር ባሻዉ ቀን በወሰነለት እለት ይቋጫል
በእያንዳንዱ ተግባር ሂሳብም ያደርጋል


إنا لله وإنا إليه راجعون
3❤‍🔥2🔥2
ሰኪነቱል ሩህ🖤 pinned «{الْيَوْمَ نَخْتِمُ عَلَىٰ أَفْوَاهِهِمْ وَتُكَلِّمُنَا أَيْدِيهِمْ وَتَشْهَدُ أَرْجُلُهُم بِمَا كَانُوا يَكْسِبُونَ} [يس : 65 በርግጥ ነገራቶች ማብቂያ አላቸዉ ፍፃሚያቸዉ መጀመርያ ባስገኛቸዉ ስር ነዉ ዛሬ ላይ የተሰጡን ኒዕማዎች ነገ በኛ ላይ መስካሪዎች ናቸዉ እጆቻችን በምን ላይ እንደዎሉ እግሮቻችን ወደ የት እንዳስጓዝናቸዉ…»
በወደድነዉ ልክ እኮ አንወደድም
ባሰብነዉ ልክም አንታሰብም
በተመኘነዉ ልክ አናገኝም
በሰጠነዉም እኩል አይሰጠንም
በቀረብነዉ ልክ አንቀረብም


መጉደልና መሙላት የዱንያ ጆንያ ነዉ
ሞልቶ መፍሰስም ከዱንያ መጋዘን ነዉ
ከጆንያዉም ከመጋዘኑም አለመንገዳገድ ግን የአኼራ ቁልፍ ነዉ
🤌
🔥6🤝5👍3
በነገራችሁ ላይ ከሰዉ ምንም አለመጠበቅ የተማርኩት በራሴዉ ቻናል ነዉ😭

ጥበብን አጨናንቃታለዉ ግን ወፍ react🥲
ፈሰብሩን ጀሚል😫
😁94🤣4