በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የደቡብ ምስራቅ አዲስ አበባ እና አካባቢው ክልል የወንጌል መስካሪዎች የአንድነት ፕሮግራም ተካሄደ።
ነሐሴ 6/2017 ዓ.ም በሴሚሲ ሙሉ ወንጌል አጥቢያ በተካሄደው የወንጌላውያን እና የወንጌል መስካሪ አገልጋዮች የአንድነት ፕሮግራም ላይ 118 አገልጋዮች ተገኝተዋል። በዘማሪ አላምረው ኢያሱ ዝማሬ ቀርቦ ጉባኤው እግዚአብሔርን አምልኳል።
በመቀጠል በክልሉ የወጣቶች ቤተሰብ አገልግሎት ፣ የወንጌል ስርጭት አገልግሎት ሃላፊ በሆኑት በመጋቢ ኤልያስ አየለ "መቼ እንደ ሐዋርያቶችሁ" በሚል ርዕስ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት አቅርበዋል።
የፕሮግራሙ አላማ አመቱን ሙሉ ወንጌልን ሲሰብኩ የቆዩትን አገልጋዮች ጌታ ስለረዳቸው ለማመስገን እና ለማበረታታት መሆኑን ታውቋል።
መረጃው የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ነው።
ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ

❤3
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የልጆች እና ወጣቶች አገልግሎት መምሪያ ለሲኖዶሶች የመንፈሳዊ መጽሐፍት ድጋፍ ተደረገ።
የኢ/ወ/ቤ/መ/ኢ የልጆች እና ወጣቶች አገልግሎት መምሪያ ለመማር ማስተማር ሂደት እና ለአገልጋዮች የሚረዱ የተለያዩ መንፈሳዊ መጽሐፍትን ለቤጊ ግዳሚ ሲኖዶስ (ቤጊ): ለቦረናና አካባቢው ሲኖዶስ (ያቤሎ): ለአዶላ ገናሌ ሲኖዶስ (አዶላ ወዩ) በድጋፍ መልክ አበርክቷል። መጽሐፍቶቹም በየሲኖዶሶቹ ለሚገኙ የትምህርት ተቋማት እና ምዕመናን አገልግሎት የሚውሉ መሆኑ ተገልጿል።
የመምሪያው ዳይሬክተር ወንድማገኝ ኡዴሳ የተለያዩ መንፈሳዊ መጽሐፍትን ለቤተክርስቲያኒቱ ድጋፍ ያደረጉትን ተቋማትን ማለትም ራፊኪ ፋውንዴሽን (Rafiki Foundation) ፣ ሉተራን ሄሪቴጅ(Lutheran Heritage Foundation) እና ሌሎችንም በማመስገን ፣ መጽሐፍቶቹን ለቤተክርስቲያኒቱ ሴሚናሪዎች ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጆች እና ት/ቤቶች ፣ እና ማ/ምዕመናን ጥቅም እንደሚውል እና ከተባባሪ ድርጅቶች ጋር በመሆን ድጋፍ የማድረጉ ስራ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
መረጃውን ከኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ አገኘነው።

👍1
የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን ሀገርዓቀፍ ጾም እና ጸሎትን አወጀች።
የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን ከጳጉሜ 1 -3 ድረስ በሁሉም የቤተ ክርስቲያኒቷ ክልሎች ፣ አጥቢያዎች እና አዳጊ ቤተ ክርስቲያናት ህብረት ጾም እና ጸሎት አውጃለች።
ጾም እና ጸሎት እንዲደረግባቸው የታሰቡት ርዕሶችም በመላው አገራችን በሁሉም ቦታ ሰላም እና ፍቅር እንዲሰፍን ፣ በሕዝቦች መካከል መፈቃቀርና መግባባት እንዲኖር ፣ በቀጣይ ዓመት ወንጌል ለምድራችን በመንፈስ ቅዱስ ሀይልና ጉልበት እንዲዳረስ ፣ በቤተ እምነት ደረጃ ተዘጋጅቶ ለሁሉም የቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅሮች የተላለፈው የ5 ዓመት ስልታዊ እቅድ ጌታ መከናወንን እንዲሰጥ ፣ በቀጣይ ዓመት በቤተ እምነት ደረጃ ስላለው የመሪዎች ምርጫ በተመለከተ ጸሎት እንዲደረግ እንዲሁም በ2018 ዓ.ም የሚደረገው የመንግስት ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅና ሰላማዊ እንዲሆን ጸሎት እንዲደረግ የሚሉት ናቸው።
ቤተ ክርስቲያኒቱ ባወጣችው በዚህ አዋጅ መሰረት የቤተ ክርስቲያኒቱ አባላት እና መላው የወንጌል አማኙ ማህበረሰብ በእነዚህ ቀናት በተሰጡት ርዕሶች ላይ በጾም እና በጸሎት በእግዚአብሔር ፊት እንደሚቀርብ ይጠበቃል።
መረጃውን ከቤተ ክርስቲያኒቱ የፌስቡክ ገጽ ላይ አገኘነው።
ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ አማኑኤል ዴቢሶ

የምስራቅ ጋምቤላ ቤቴል ሲኖዶስ መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ከGRAND PROJECT ጋር በመተባበር በሰላም ግንባታ ዙሪያ ያተኮረ የምክክር መድረክ በጋምቤላ ከተማ አካሄደ።
የምስራቅ ጋምቤላ ቤቴል ሲኖዶስ መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ዘላቂ ሰላም ማምጣት እንዲቻል የሁሉም ባለድርሻ ካላት ተሳትፎ ሊጠናከር እንደሚገባ አስታውቃለች።
በመድረኩም ከጋምቤላ ከተማ ከአምስቱም ቀበሌ ከአኝዋሃ ዞን እና ጎግ ወረዳ የተወጣጡ የሀይማኖት አባቶች ፣የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
የምስራቅ ጋምቤላ ቤቴል ሲኖዶስ መካነ ኢየሱስ ፕሬዝዳንት ቄስ ኝጎዎ ኡሞድ በመድረኩ እንደተናገሩት ዘላቂ ሰላም እንዲኖር የሰላም ግንባታ ማዳበር እንዲቻል የሀይማኖት ተቋማት የሀገር ሽማግሌዎች ጨምሮ ሁሉም አካላት ለሰላም ዘብ ሊቆሙ እንደሚገባ ተናግረዋል።
ሰላም ለሰዉ ልጅ ከሚያስፈልጉት እጅግ መሰረታዊ ነገሮች ዉስጥ አንዱና ግንባር ቀደም መሆኑን ገልፀዉ የክልሉን ማህበረሰብ ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ ዋነኛ ተግባር አድርጋ ቤተክርስቲያኗ እየሰራች እንደምትገኝ ተናግረዋል።
የሰላም እጦት በክልሉ ባለፉት ጊዜያት በተፈጠሩ አለመግባባቶች ብዙ የልማት ስራዎች ሳንሰራ የቀረን ሲሆን የሰላምን ዋጋ በመገንዘብ የሰላም ግንባታዉ እንዲዳብር ብዙ መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
የእምነት ተቋማቱ በጋራ በመሆን ያለዉን ሰላም ለማስቀጠል የጋራ የሆኑ ጉዳዮች ላይ ልንሰራ ይገባልም ብለዋል።
በክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ የሰላም እሴት ግንባታ ዳይሬክተር አቶ ኡጁሉ ቢሩ እንዳሉት ዘላቂ ሰላም ለማምጣት እንዲቻል በየደረጃዉ ያሉ የማህበረሰብ ክፍሎች በየአከባቢያቸዉ ሰላም እንዳይኖር የሚያደርጉ መንስዔዎችን በመለየት የመፍትሄ አቅጣጫዎች ሊሰሩ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የሰላም ግንባታ ለማዳበር ትኩረት ተሰጥቶ ከተሰራ ለግጭት መነሻ ናቸዉ ተብለዉ የሚነሱ ጉዳዩች ቀድመን የመከላከል ስራ መስራት ይቻላል ብለዋል።
የግጭት አይነቶችን ቀድሞ በመለየት ያለዉን ሰላም በዘላቂነት ለማስቀጠል ከወጣቶችና፣ ከሴቶች ፣ ከሀይማኖት አባቶች እና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር በጋር መሰራት እንዳለበት አመላክተዋል።
አንዳንድ የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸዉ ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት በስነ ምግባር የታነፀ ትዉልድ ማፍራት ከቤተ እምነቶች ፣ ከትምህርት ቤት እንዲሁ ከወላጅ እንደሚጠበቅ ገልፀዉ ኃላፊነት እንዳለባቸዉ በመገንዘብ ጠንከር ያለ ስራ መስራት እንዳለባቸዉ አሳስበዋል።
መረጃው የጋምቤላ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ነው።